ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ሊ.፡ዤኔራል፡ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ•Lt. Gen. Negga Haile Sellassie

s_GA_NeggaHayleSllase

ሥልጡንሕዝብና።

ከነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴሥልጡንሕዝብና፡ማለት፥ቃል፡በቃል፥ልክ፡በልክ፥ሥልጡን፡ሕዝብነት፡ነው።የመጣውም፡ሠለጠነ፥

አ) ለገዢነት፥ተገቢነት፣መብት፣ምስፍና፣ችሎት፡አገኘ፤

በ) ዐወቀ፥ተረዳ፥ርትዕን፡ተቀባይ፣ለፍትሕ፡ታዛዥ፡ኾነ፤

ገ) ፈልስሞ፡ሠራ፥አከናወነ፥ከያኒ፣ኬንያ፡ኾነ፤

ከሚለው፥ሕዝብ፥ጥንት፡በመሠረት፥ኅሊውን፡ከኅሊናው፡አንቅቶና፡በልቦናው፡ፀንሶ፥በሥሉስ፡ባሕርዩ፡አ ምሳል፡በሦ ስት፡ቀለማት፡አድምጦ፥በሦስት፡ኅርመት፡አሥርጾ፡ካናገረው፡የግእዝ፡ቃል፡"ሠለጠ"፡የመጣ፡ነው።
የሴም፡ቋንቋ፡ባሕርዩን፡አልተነሣም፥ህልው፡ነው፤ይወልዳል፥ይዋለዳል፥ይወላለዳል።ዘሩ፡"ሠለጠ"፡ያማ ርኛን፡አን ቀጽ፡"ሠለጠነ"ን፡ወልዷል።"ሠለጠነ"ም፡"ሥልጣን"ን፡ስም፥"ሥልጡን"ን፡ቅጽል፡ወልዷል።"ሥልጡን"፡ከሕዝ ብ፡ጋ ራ፡በመጋባት፥"ሥልጡንሕዝብና"ን፡ህልው፡ስም፡ወልዷል።ውሉዱን፡ኢትዮጵያዊ፡ዅሉ፡በቀላሉ፡ያውቀዋል፤ ባዕዱ ፡አይደለም፥ዘመዱ፡ነው።የተውሶ፡ዕቃ፡ወይም፡የብድር፡ዕውቀት፡አይደለም፤የራሱ፡ባህል፥የራሱ፡ሥርዐ ት፡ነው ፤አያደናግረውም፤ዐውቆ፡ይሠራበታል፥ወዶም፡ያድርበታል።

እንግዲህ፥ወደተነሣኹለት፡ርእሰ፡ነገር፡ልመለስ።

በሥላሴ፡አምሳል፡የተፈጠረው፡ነባቢ፣ለባዊና፡ሕያው፡ሰው፥የተፈጠረለትን፡ተግባር፡የማከናወን፡ግዳጅ ፡በባሕርዩ፡እን ዳለበት፡ዅሉ፥ግዳጁን፡የሚ፟ወ፟ጣ፟በት፡ተስተካካዩ፡ችሎትም፡በዚያው፡ባሕርዩ፡ያለለት፥በቂውም፡ሀብ ት፡በብሔሩ፡(1)፡የሰፈረለት፥የራሱ፡አዛዥ፣ጌታ፥ወይም፡ገዥ፣እግዚእ፡ነው።ለጕዳዩ፡ራሱን፡ያዛል፤ሥልጡን፡ነው።ለ ራሱ፡ይታ ዘዛል፤ሥልጡን፡ነው።ያስባል፤ያቅዳል፤ይሠራል፥ሥራውንም፡ይገዛል፥ያገምራል፤ሥልጡን፡ነው።ይኸንንም ፡ሲያደ ርግ፥ከፈጣሪው፡በታች፥ከራሱ፡በቀር፡በማንም፡አይገዛ፤ከፈቃዱም፡በቀር፡ለማንም፡አይታዘዝ፤የራሱ፡ጌ ታ፡እኩል፡ ሥልጡን፣እኩል፡እግዚእ፥ለራሱ፡ታዛዥ፡እኩል፡ዜጋ፣እኩል፡ሥልጡን፡ነው።መሬት፣ውሃ፥እሳት፣ነፋስ፡የ ማይነ ፈጉት፡እኩል፡ባለጸጋ፡ነው።

ይኸን፡እኩልነት፡ጠልቶ፥በብጤው፡ላይ፡ልቆ፡ለመታየት፡ሲል፡ጌትነቱን፡ከፈጣሪው፡አምላኩ፡ልዕልና፡ላ ስታይ፡ቢል ፥በሥጋውም፡በነፍሱም፡የማይቋቋመው፡መከራ፡እንዳይመጣበት፡ስለሚሠጋ፤ከብጤው፡በላይ፡ለመኾን፡ቢንጠ ራራ፡ ደግሞ፥ከብጤው፡በመጋደር፡ክብሩን፡የሚያጣ፤ከብጤው፡ለመስተካከል፡ቢሰላ፡ግን፥ከብጤው፡በመተባበር፥ ጌትነቱ ን፡የሚያስከብር፡መኾኑን፡በባሕርዩ፡የሚያውቅ፡ብልኅ፡ስለ፡ኾነ፥ሙከራውን፡ሳይገፋበት፡በቅርቡ፡ሊተ ው፡ይፈቅዳል ፤ወይም፡ገፍቶበት፥ትርፉ፡መላው፡ጕዳት፡መኾኑን፡ሲያገኘው፥ሊተወው፡ይገደዳል።መደምደሚያውን፥ሰው፥ ለራ ሱ፡ጌትነት፡ወይም፡እግዚእና፡ሲል፥የብጤውን፡የራስ፡ጌትነት፡ያከብራል።ሲያከብርም፥ብጤውን፡በራሱ፡ ላይ፡ያሠ ለጥነዋል።ጌትነቱ፡የታወቀለትና፡በብጤው፡ላይ፡የሠለጠነውም፡ሰው፥ጌትነቱን፡ያወቀለትንና፡በራሱ፡ላ ይ፡ያሠለጠነው ን፡ብጤውን፥ተራውን፡በጌትነቱ፡ሊያውቀው፡ወንፈሉ፡ያስገድደውና፥በራሱ፡ላይ፡ያሠለጥነዋል።ኹለቱም፡ ሰዎች፥አ ንዱ፡ከሌላው፡እኩል፡ሥልጡኖች፡ይኾናሉ፥ሥልጡን፡ሰዎችም፡ይባላሉ።በነርሱው፡ዐይነት፡ሥልጡን፡ሰዎች ፡በርክተ ው፡አንድ፡ሕዝብ፡ሲኾኑ፥ወይም፡ሲሞሉ፥በቅጽላቸው፡"ሥልጡንሕዝብ"፡ይባላሉ፥ኹነታቸውም፡"ሥልጡንሕዝ ብነት "፡ይባላል፤ዐዳራቸው፣አናዎራቸው፣ሥርዐታቸው፡ደግሞ፥በጠቅላላው፡"ሥልጣኔ"፥በተለይም፡"ሥልጡንሕዝብ ና"፡ይባ ላል።እንሆ፥ሥልጡንሕዝብና፡ከዚህ፡ይነሣል።

በተመጠነ፡አነጋገር፥ሥልጡንሕዝብና፦የብጤን፡መብትና፡ነጻነት፡በማክበር፡ውዴታ፥የራስን፡መብትና፡ነ ጻነት፡በብ ጤ፡አስከብሮ፡መኖር፡ነው።ከዚህም፡የመብትና፡ግዴታ፡ተመዛዛኝነት፡የሚገኘው፡ባሕርያዊው፥ብሔራዊ፡(2)፣ተወናፋይ፡የመነሻ፡ሥልጣኔ፥ወይም፡ሥልጡንሕዝብና፥በኹለት፡ፊት፡ገደብ፡እታፈፈ፡ዛኅን፡ላይ፡የሰ ፈነ፡ርትዐ ት፥ወይም፡በፍትሕ፡የሚሠራ፣የሚያበጅና፡የሚያለማ፡የርትዕ፡ኀይል፡ነው።በተለይም፥ከጐን፡የብጤን፡መ ብትና፡ነ ጻነት፥ከላይ፡የእግዚአብሔርን፡ዳኝነት፥ከታችም፡የሕግን፡ገዥነት፡በማክበር፥የራስን፡አስከብሮ፡ከመ ኖር፡የሚገኘው፡ ኢትዮጵያዊው፣ባሕርያዊው፣ተወናፋይ፡የመድረሻ፡ሥልጣኔ፡ወይም፡ሥልጡንሕዝብና፥ባራት፡በኩል፡ተመዛዝ ኖ፡በረ ጋ፥ባራት፡በኩል፡ተመጣጥኖ፡በታፈፈ፡ዛኅን፡ላይ፡ያረፈ፡ሰላም፥ወይም፡ከማጥፋት፡የሚከለክል፣ከጥፋት ፡የሚያድን ፣ከውድቀት፡የሚያስነሣ፡ችሎት፡ነው።

የኔ፡ጥቅም፡ይቅደም፤ወይም፡የኔ፡ጥቅም፡ብቻ፡ይፈጸም፡የሚለው፡ለራሴ፡ባይነት፤ወይም፡ደግሞ፡የኔ፡ይ ቅደም፥የ ሌላው፡ይውደም፤የኔ፡እንዲፋፋ፡የሌላው፡ይጥፋ፡የሚለው፡egoism፡ግን፥ገና፡በመነሻው፥ያንዱን፡ፊት፡ ገደብ፡ያ ፈረሰ፥የብጤን፡መብትና፡ነጻነት፡የሚቀንስ፥ጨርሶም፡የሚደመስስና፥የራስ፡ነጻነትና፡መብት፡መገኛ፡የ ሚኾነውን፡ተ መዛዛኝነት፡ተመልሶ፡የሚያፈርስ፤መደምደሚያውን፥የዅሉን፡ሰላም፡የሚነሣ፣የሚያደፈርስ፣የሚያጠፋ፡ስ እነት፡(3)፡ነው።

ሰላምን፡የሚነሣው፣የሚያፈርሰው፣የሚያጠፋው፡ስእነት፥እጅግ፡የሚያርዕድ፣የሚያንቀጠቅጥ፡እቀት፡ሲኾ ን፤ማፍረሻ ፣መደምሰሻ፡ጠባዩን፥በሌላ፡አነጋገር፥ውንብድናውን፡በባሕርዩ፡የያዘ፡ስለ፡ኾነ፥ራሱን፡በራሱ፡ማፍረ ሱና፡ማጥፋቱ ፥ወይም፡ሚዛኑን፡በገዛ፡እጁ፡ደፍቶ፡መውደቁና፡መንኰትኰቱ፡የማይቀርለት፡ዕዳው፡ነው።

የሚሠራው፣የሚያበጀውና፡የሚያለማው፡ርትዐት፡ግን፥በዚያው፡አንጻር፥እጅግ፡የሚያስተማምን፣የሚያበረ ድድና፡የ ሚያዠግን፡ችሎት፡ነው።ችሎትም፥ስእነትን፡ስለሚደመስስ፥ከቶ፡ጥፋት፡አያገኘውም።(4)


(ሥልጡንሕዝብና፥3ኛ፡ዓመት፥ቍ.005፥ታኅሣሥ፡1985፡ዓ.ም።)

_________

(1) 'ብሔር'፡በግእዝ፡'ብሒር'፡(መስፋት፡መንጣለል፤መዘ፟ርጋት፥ሰፊ፣ዝርግ፣ወርዳም፣ረዥም፡መኾን፥የቦታ፣የመሬት፣የርስት፣የግዛት፤ኪ.ወ.ክ.፥ገ.261)፡ካለው፡አንቀጽ፡ይወጣል።ወሰን፡ያለው፡ወይም፡ወሰን፡የሌለው፡ሊኾን፡ይችላል።ሲወሰን፥ለምሳሌ፡'ብሔረ፡ኦሪት'፡ቢል ፥የመጽሐፍ፡ቅዱስን፡ክፍል፡ያመለክ ታል፤እንዲሁም፡'ብሔረ፡ኵሽ'፡ቢል፥የኵሽ፡ልጆችን፡ምድር፡ለማለት፡ነው።ሳይወሰን፡ደግሞ፥ጠፈርን፡ጨምሮ፥መላ፟ው፡ዓለ ም፣መላ፟ው፡ፍጥረት፡ማለት፡ነ ው፤ለምሳሌ፡'እግዚአብሔር'፡ስንል፡የፍጥረት፡ዅሉ፣የዓለም፡ዅሉ፡ገዥ፡ማለታችን፡ነው።እንደዚሁ፥ሣልስ፡ቅጽሉ፡'ብሔራ ዊ'፥ሲወሰን፡'ምድራዊ'፡(በፈረንጅኛ፡'territorial')፤ሳይወሰን፡ደግሞ፡'የመላ፡ዓለም'፡(በፈረንጅኛ፡'universal'•'universel')፡ማለት፡ነው።እዚህ፡ላይ፡'ብሔራዊ'ን፡'የመላ፟፡ዓለም'፡ብሎ፡ያነቧል።

[አዘጋጅ]

(2) ጥቅሱ፡የሚያመለክተው፡የመላ፟፡ዓለምን፡ነው።[አዘጋጅ]

(3) ስእነት፤ስኡንነት፥እቀት፥አለመቻል።

(4) ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ፡(ሊ.ዤኔራል)፥ሥልጡንሕዝብና፥3ኛ፡ዓመት፥ቍ.005፥ታኅሣሥ፡1985፡ዓ.ም.።

 

http://www.gzamargna.net