የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ወንጌል፡
ቅዱስ፡ዮሐንስ፡እንደ፡ጻፈው።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1፤
1፤በመዠመሪያው፡ቃል፡ነበረ፥ቃልም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነበረ፥ቃልም፡እግዚአብሔር፡ነበረ።
2፤ይህ፡በመዠመሪያው፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነበረ።
3፤ዅሉ፡በርሱ፡ኾነ፥ከኾነውም፡አንዳች፡ስንኳ፡ያለርሱ፡አልኾነም።
4፤በርሱ፡ሕይወት፡ነበረች፥ሕይወትም፡የሰው፡ብርሃን፡ነበረች።
5፤ብርሃንም፡በጨለማ፡ይበራል፥ጨለማም፡አላሸነፈውም።
6፤ከእግዚአብሔር፡የተላከ፡ስሙ፡ዮሐንስ፡የሚባል፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፤
7፤ዅሉ፡በርሱ፡በኩል፡እንዲያምኑ፡ይህ፡ስለ፡ብርሃን፡ይመሰክር፡ዘንድ፡ለምስክር፡መጣ።
8፤ስለ፡ብርሃን፡ሊመሰክር፡መጣ፡እንጂ፥ርሱ፡ብርሃን፡አልነበረም።
9፤ለሰው፡ዅሉ፡የሚያበራው፡እውነተኛው፡ብርሃን፡ወደ፡ዓለም፡ይመጣ፡ነበር።
10፤በዓለም፡ነበረ፥ዓለሙም፡በርሱ፡ኾነ፥ዓለሙም፡አላወቀውም።
11፤የርሱ፡ወደኾነው፡መጣ፥የገዛ፡ወገኖቹም፡አልተቀበሉትም።
12፤ለተቀበሉት፡ዅሉ፡ግን፥በስሙ፡ለሚያምኑት፡ለእነርሱ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሥልጣንን፡ሰጣ ቸው፤
13፤እነርሱም፡ከእግዚአብሔር፡ተወለዱ፡እንጂ፡ከደም፡ወይም፡ከሥጋ፡ፈቃድ፡ወይም፡ከወንድ፡ፈቃድ፡አልተወለዱ ም።
14፤ቃልም፡ሥጋ፡ኾነ፤ጸጋንና፡እውነትንም፡ተመልቶ፡በእኛ፡ዐደረ፥አንድ፡ልጅም፡ከአባቱ፡ዘንድ፡እንዳለው፡ክ ብር፡የኾነው፡ክብሩን፡አየን።
15፤ዮሐንስ፡ስለ፡ርሱ፡መሰከረ፡እንዲህም፡ብሎ፡ጮኸ፦ከእኔ፡በዃላ፡የሚመጣው፡ርሱ፡ከእኔ፡በፊት፡ነበረና፡ከ እኔ፡ይልቅ፡የከበረ፡ኾኗል፤ስለ፡ርሱ፡ያልኹት፡ይህ፡ነበረ።
16፤እኛ፡ዅላችን፡ከሙላቱ፡ተቀብለን፡በጸጋ፡ላይ፡ጸጋ፡ተሰጥቶናልና፥ሕግ፡በሙሴ፡ተሰጥቶ፡ነበርና፤
17፤ጸጋና፡እውነት፡ግን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ኾነ።
18፤መቼም፡ቢኾን፡እግዚአብሔርን፡ያየው፡አንድ፡ስንኳ፡የለም፤በአባቱ፡ዕቅፍ፡ያለ፡አንድ፡ልጁ፡ርሱ፡ተረከው ።
19፤አይሁድም፦አንተ፡ማን፡ነኽ፧ብለው፡ይጠይቁት፡ዘንድ፡ከኢየሩሳሌም፡ካህናትንና፡ሌዋውያንን፡በላኩበት፡ጊ ዜ፥የዮሐንስ፡ምስክርነት፡ይህ፡ነው።
20፤መሰከረም፡አልካደምም፤እኔ፡ክርስቶስ፡አይደለኹም፡ብሎ፡መሰከረ።
21፤እንኪያስ፡ማን፡ነኽ፧ኤልያስ፡ነኽን፧ብለው፡ጠየቁት፦አይደለኹም፡አለ፦ነቢዩ፡ነኽን፧አይደለኹም፡ብሎ፡መ ለሰ።
22፤እንኪያስ፦ማን፡ነኽ፧ለላኩን፡መልስ፡እንድንሰጥ፤ስለ፡ራስኽ፡ምን፡ትላለኽ፧አሉት።
23፤ርሱም፦ነቢዩ፡ኢሳይያስ፡እንዳለ፦የጌታን፡መንገድ፡አቅኑ፡ብሎ፡በምድረ፡በዳ፡የሚጮኽ፡ሰው፡ድምፅ፡እኔ፡ ነኝ፡አለ።
24-25፤የተላኩትም፡ከፈሪሳውያን፡ነበሩና፦እንኪያስ፡አንተ፡ክርስቶስ፡ወይም፡ኤልያስ፡ወይም፡ነቢዩ፡ካይደለኽ ፥ስለ፡ምን፡ታጠምቃለኽ፧ብለው፡ጠየቁት።
26፤ዮሐንስ፡መልሶ፦እኔ፡በውሃ፡አጠምቃለኹ፤ዳሩ፡ግን፡እናንተ፡የማታውቁት፡በመካከላችኹ፡ቆሟል፤
27፤እኔ፡የጫማውን፡ጠፍር፡ልፈታ፡የማይገ፟ባ፟ኝ፥ከእኔ፡በዃላ፡የሚመጣው፡ከእኔ፡ይልቅ፡የሚከብር፡ይህ፡ነው ፡አላቸው።
28፤ይህ፡ነገር፡ዮሐንስ፡ያጠምቅበት፡በነበረው፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በቢታንያ፡በቤተ፡ራባ፡ኾነ።
29፤በነገው፡ዮሐንስ፡ኢየሱስን፡ወደ፡ርሱ፡ሲመጣ፡አይቶ፡እንዲህ፡አለ፦እንሆ፥የዓለምን፡ኀጢአት፡የሚያስወግ ድ፡የእግዚአብሔር፡በግ።
30፤አንድ፡ሰው፡ከእኔ፡በዃላ፡ይመጣል፥ከእኔም፡በፊት፡ነበርና፥ከእኔ፡ይልቅ፡የከበረ፡ኾኗል፡ብዬ፡ስለ፡ርሱ ፡ያልኹት፡ይህ፡ነው።
31፤እኔም፡አላውቀውም፡ነበር፥ዳሩ፡ግን፡ለእስራኤል፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ስለዚህ፡በውሃ፡እያጠመቅኹ፡እኔ፡መጣኹ ።
32፤ዮሐንስም፡እንዲህ፡ብሎ፡መሰከረ።መንፈስ፡ከሰማይ፡እንደ፡ርግብ፡ኾኖ፡ሲወርድ፡አየኹ፤በርሱ፡ላይም፡ኖረ ።
33፤እኔም፡አላውቀውም፡ነበር፥ዳሩ፡ግን፡በውሃ፡አጠምቅ፡ዘንድ፡የላከኝ፡ርሱ፦መንፈስ፡ሲወርድበትና፡ሲኖርበ ት፡የምታየው፥በመንፈስ፡ቅዱስ፡የሚያጠምቅ፡ርሱ፡ነው፡አለኝ።
34፤እኔም፡አይቻለኹ፡ርሱም፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡እንደ፡ኾነ፡መስክሬያለኹ።
35፤በነገው፡ደግሞ፡ዮሐንስ፡ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ኹለት፡ቆመው፡ነበር፥
36፤ኢየሱስም፡ሲኼድ፡ተመልክቶ፦እንሆ፥የእግዚአብሔር፡በግ፡አለ።
37፤ኹለቱም፡ደቀ፡መዛሙርት፡ሲናገር፡ሰምተው፡ኢየሱስን፡ተከተሉት።
38፤ኢየሱስም፡ዘወር፡ብሎ፡ሲከተሉትም፡አይቶ፦ምን፡ትፈልጋላችኹ፧አላቸው።
39፤እነርሱም፦ረቢ፥ወዴት፡ትኖራለኽ፧አሉት፤ትርጓሜው፡መምህር፡ሆይ፡ማለት፡ነው።
40፤መጥታችኹ፡እዩ፡አላቸው።መጥተው፡የሚኖርበትን፡አዩ፥በዚያም፡ቀን፡በርሱ፡ዘንድ፡ዋሉ፤ዐሥር፡ሰዓት፡ያኽ ል፡ነበረ።
41፤ከዮሐንስ፡ዘንድ፡ሰምተው፡ከተከተሉት፡ከኹለቱ፡አንዱ፡የስምዖን፡ጴጥሮስ፡ወንድም፡እንድርያስ፡ነበረ።
42፤ርሱ፡አስቀድሞ፡የራሱን፡ወንድም፡ስምዖንን፡አገኘውና፦መሲሕን፡አግኝተናል፡አለው፤ትርጓሜውም፡ክርስቶስ ፡ማለት፡ነው።
43፤ወደ፡ኢየሱስም፡አመጣው።ኢየሱስም፡ተመልክቶ፦አንተ፡የዮና፡ልጅ፡ስምዖን፡ነኽ፤አንተ፡ኬፋ፡ትባላለኽ፡አ ለው፤ትርጓሜው፡ጴጥሮስ፡ማለት፡ነው።
44፤በነገው፡ኢየሱስ፡ወደ፡ገሊላ፡ሊወጣ፡ወደደ፥ፊልጶስንም፡አገኘና፦ተከተለኝ፡አለው።
45፤ፊልጶስም፡ከእንድርያስና፡ከጴጥሮስ፡ከተማ፡ከቤተ፡ሳይዳ፡ነበረ።
46፤ፊልጶስ፡ናትናኤልን፡አግኝቶ፦ሙሴ፡በሕግ፡ነቢያትም፡ስለ፡ርሱ፡የጻፉትን፡የዮሴፍን፡ልጅ፡የናዝሬቱን፡ኢ የሱስን፡አግኝተነዋል፡አለው።
47፤ናትናኤልም፦ከናዝሬት፡መልካም፡ነገር፡ሊወጣ፡ይችላልን፧አለው።ፊልጶስ፦መጥተኽ፡እይ፡አለው።
48፤ኢየሱስ፡ናትናኤልን፡ወደ፡ርሱ፡ሲመጣ፡አይቶ፡ስለ፡ርሱ፦ተንኰል፡የሌለበት፡በእውነት፡የእስራኤል፡ሰው፥ እንሆ፥አለ።
49፤ናትናኤልም፦ከወዴት፡ታውቀኛለኽ፧አለው።ኢየሱስም፡መልሶ፦ፊልጶስ፡ሳይጠራኽ፥ከበለስ፡በታች፡ሳለኽ፥አየ ኹኽ፡አለው።
50፤ናትናኤልም፡መልሶ፦መምህር፡ሆይ፥አንተ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኽ፤አንተ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ነኽ፡አለው ።
51፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ከበለስ፡በታች፡አየኹኽ፡ስላልኹኽ፡አመንኽን፧ከዚህ፡የሚበልጥ፡ነገር፡ታያለኽ፡አለው።
52፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ሰማይ፡ሲከፈት፡የእግዚአብሔርም፡መላእክት፡በሰው፡ልጅ፡ላይ፡ሲወጡና፡ሲወ ርዱ፡ታያላችኹ፡አለው።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2፤
1፤በሦስተኛውም፡ቀን፡በገሊላ፡ቃና፡ሰርግ፡ነበረ፥የኢየሱስም፡እናት፡በዚያ፡ነበረች፤
2፤ኢየሱስም፡ደግሞ፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡ወደ፡ሰርጉ፡ታደሙ።
3፤የወይን፡ጠጅም፡ባለቀ፡ጊዜ፡የኢየሱስ፡እናት፦የወይን፡ጠጅ፡እኮ፡የላቸውም፡አለችው።
4፤ኢየሱስም፦አንቺ፡ሴት፥ከአንቺ፡ጋራ፡ምን፡አለኝ፧ጊዜዬ፡ገና፡አልደረሰም፡አላት።
5፤እናቱም፡ለአገልጋዮቹ፦የሚላችኹን፡ዅሉ፡አድርጉ፡አለቻቸው።
6፤አይሁድም፡እንደሚያደርጉት፡የማንጻት፡ልማድ፡ስድስት፡የድንጋይ፡ጋኖች፡በዚያ፡ተቀምጠው፡ነበር፥እያንዳን ዳቸውም፡ኹለት፡ወይም፡ሦስት፡እንስራ፡ይይዙ፡ነበር።
7፤ኢየሱስም፦ጋኖቹን፡ውሃ፡ሙሏቸው፡አላቸው፦እስከ፡አፋቸውም፡ሙሏቸው፡አላቸው።እስከ፡አፋቸውም፡ሞሏቸው፦
8፤አኹን፡ቀድታችኹ፡ለአሳዳሪው፡ስጡት፡አላቸው፤ሰጡትም።
9፤አሳዳሪውም፡የወይን፡ጠጅ፡የኾነውን፡ውሃ፡በቀመሰ፡ጊዜ፡ከወዴት፡እንደ፡መጣ፡አላወቀም፤ውሃውን፡የቀዱት፡ አገልጋዮች፡ግን፡ያውቁ፡ነበር፤አሳዳሪው፡ሙሽራውን፡ጠርቶ፦
10፤ሰው፡ዅሉ፡አስቀድሞ፡መልካሙን፡የወይን፡ጠጅ፡ያቀርባል፥ከሰከሩም፡በዃላ፡መናኛውን፤አንተስ፡መልካሙን፡ የወይን፡ጠጅ፡እስከ፡አኹን፡አቈይተኻል፡አለው።
11፤ኢየሱስ፡ይህን፡የምልክቶች፡መዠመሪያ፡በገሊላ፡ቃና፡አደረገ፤ክብሩንም፡ገለጠ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡በርሱ፡ አመኑ።
12፤ከዚህ፡በዃላ፡ከእናቱና፡ከወንድሞቹ፡ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ጋራ፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡ወረደ፥በዚያም፡ጥቂት፡ቀ ን፡ኖሩ።
13፤የአይሁድ፡ፋሲካም፡ቀርቦ፡ነበር፥ኢየሱስም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጣ።
14፤በመቅደስም፡በሬዎችንና፡በጎችን፡ርግቦችንም፡የሚሸጡትን፡ገንዘብ፡ለዋጮችንም፡ተቀምጠው፡አገኘ፤
15፤የገመድም፡ጅራፍ፡አበጅቶ፡ዅሉን፡በጎችንም፡በሬዎችንም፡ከመቅደስ፡አወጣቸው፥የለዋጮችንም፡ገንዘብ፡አፈ ሰሰ፡ገበታዎቻቸውንም፡ገለበጠ፥
16፤ርግብ፡ሻጪዎችንም፦ይህን፡ከዚህ፡ውሰዱ፤የአባቴን፡ቤት፡የንግድ፡ቤት፡አታድርጉት፡አላቸው።
17፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦የቤትኽ፡ቅናት፡ይበላኛል፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ዐሰቡ።
18፤ስለዚህ፥አይሁድ፡መልሰው፦ይህን፡ስለምታደርግ፡ምን፡ምልክት፡ታሳየናለኽ፧አሉት።
19፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ይህን፡ቤተ፡መቅደስ፡አፍርሱት፥በሦስት፡ቀንም፡አነሣዋለኹ፡አላቸው።
20፤ስለዚህ፥አይሁድ፦ይህ፡ቤተ፡መቅደስ፡ከአርባ፡ስድስት፡ዓመት፡ዠምሮ፡ይሠራ፡ነበር፥አንተስ፡በሦስት፡ቀን ፡ታነሣዋለኽን፧አሉት።
21፤ርሱ፡ግን፡ስለ፡ሰውነቱ፡ቤተ፡መቅደስ፡ይል፡ነበር።
22፤ስለዚህ፥ከሙታን፡ከተነሣ፡በዃላ፥ደቀ፡መዛሙርቱ፡ይህን፡እንደ፡ተናገረ፡ዐሰቡና፥መጽሐፍንና፡ኢየሱስ፡የ ተናገረውን፡ቃል፡አመኑ።
23፤በፋሲካ፡በዓልም፡በኢየሩሳሌም፡ሳለ፥ያደረገውን፡ምልክት፡ባዩ፡ጊዜ፡ብዙ፡ሰዎች፡በስሙ፡አመኑ፤
24-25፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፡ሰዎችን፡ዅሉ፡ያውቅ፡ነበር፤ስለ፡ሰውም፡ማንም፡ሊመሰክር፡አያስፈልገውም፡ነበርና ፥አይተማመናቸውም፡ነበር፤ራሱ፡በሰው፡ያለውን፡ያውቅ፡ነበርና።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3፤
1፤ከፈሪሳውያንም፡ወገን፡የአይሁድ፡አለቃ፡የኾነ፡ኒቆዲሞስ፡የሚባል፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፤ርሱም፡በሌሊት፡ወደ ፡ኢየሱስ፡መጥቶ፦
2፤መምህር፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ከኾነ፡በቀር፡አንተ፡የምታደርጋቸውን፡እነዚህን፡ምልክቶች፡ሊያደ ርግ፡የሚችል፡የለምና፡መምህር፡ኾነኽ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡እንደ፡መጣኽ፡እናውቃለን፡አለው።
3፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥ሰው፡ዳግመኛ፡ካልተወለደ፡በቀር፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት ፡ሊያይ፡አይችልም፡አለው።
4፤ኒቆዲሞስም፦ሰው፡ከሸመገለ፡በዃላ፡እንዴት፡ሊወለድ፡ይችላል፧ኹለተኛ፡ወደ፡እናቱ፡ማሕፀን፡ገብቶ፡ይወለድ ፡ዘንድ፡ይችላልን፧አለው።
5፤ኢየሱስም፡መለሰ፥እንዲህ፡ሲል፦እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥ሰው፡ከውሃና፡ከመንፈስ፡ካልተወለደ፡በቀር፡ወ ደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ሊገባ፡አይችልም።
6፤ከሥጋ፡የተወለደ፡ሥጋ፡ነው፥ከመንፈስም፡የተወለደ፡መንፈስ፡ነው።
7፤ዳግመኛ፡ልትወለዱ፡ያስፈልጋችዃል፡ስላልኹኽ፡አታድንቅ።
8፤ነፋስ፡ወደሚወደ፟ው፡ይነፍሳል፥ድምፁንም፡ትሰማለኽ፥ነገር፡ግን፥ከወዴት፡እንደ፡መጣ፡ወዴትም፡እንዲኼድ፡ አታውቅም፤ከመንፈስ፡የተወለደ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው።
9፤ኒቆዲሞስ፡መልሶ፦ይህ፡እንዴት፡ሊኾን፡ይችላል፧አለው።
10፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለው፦አንተ፡የእስራኤል፡መምህር፡ስትኾን፡ይህን፡አታውቅምን፧
11፤እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥የምናውቀውን፡እንናገራለን፡ያየነውንም፡እንመሰክራለን፥ምስክራችንንም፡አት ቀበሉትም።
12፤ስለ፡ምድራዊ፡ነገር፡በነገርዃችኹ፡ጊዜ፡ካላመናችኹ፥ስለ፡ሰማያዊ፡ነገር፡ብነግራችኹ፡እንዴት፡ታምናላች ኹ፧
13፤ከሰማይም፡ከወረደ፡በቀር፡ወደ፡ሰማይ፡የወጣ፡ማንም፡የለም፥ርሱም፡በሰማይ፡የሚኖረው፡የሰው፡ልጅ፡ነው።
14-15፤ሙሴም፡በምድረ፡በዳ፡እባብን፡እንደ፡ሰቀለ፡እንዲሁ፡በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡እንዲ ኖረው፡እንጂ፡እንዳይጠፋ፡የሰው፡ልጅ፡ይሰቀል፡ይገ፟ባ፟ዋል።
16፤በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡እንዲኖረው፡እንጂ፡እንዳይጠፋ፡እግዚአብሔር፡አንድያ፡ልጁን ፡እስኪሰጥ፡ድረስ፡ዓለሙን፡እንዲሁ፡ወዷ፟ልና።
17፤ዓለም፡በልጁ፡እንዲድን፡ነው፡እንጂ፥በዓለም፡እንዲፈርድ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ዓለም፡አልላከውምና።
18፤በርሱ፡በሚያምን፡አይፈረድበትም፤በማያምን፡ግን፡በአንዱ፡በእግዚአብሔር፡ልጅ፡ስም፡ስላላመነ፡አኹን፡ተ ፈርዶበታል።
19፤ብርሃንም፡ወደ፡ዓለም፡ስለ፡መጣ፡ሰዎችም፡ሥራቸው፡ክፉ፡ነበርና፥ከብርሃን፡ይልቅ፡ጨለማን፡ስለ፡ወደዱ፡ ፍርዱ፡ይህ፡ነው።
20፤ክፉ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡ብርሃንን፡ይጠላልና፥ሥራውም፡እንዳይገለጥ፡ወደ፡ብርሃን፡አይመጣም፤
21፤እውነትን፡የሚያደርግ፡ግን፡ሥራው፡በእግዚአብሔር፡ተደርጎ፡እንደ፡ኾነ፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ወደ፡ብርሃን፡ይ መጣል።
22፤ከዚህ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወደይሁዳ፡አገር፡መጣ፥በዚያም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ተቀምጦ፡ያጠ ምቅ፡ነበር።
23፤ዮሐንስም፡ደግሞ፡በሳሌም፡አቅራቢያ፡በሄኖን፡በዚያ፡ብዙ፡ውሃ፡ነበርና፥ያጠምቅ፡ነበር፥
24፤እየመጡም፡ይጠመቁ፡ነበር፡ዮሐንስ፡ገና፡ወደ፡ወህኒ፡አልተጨመረም፡ነበርና።
25፤ስለዚህም፡በዮሐንስ፡ደቀ፡መዛሙርትና፡በአይሁድ፡መካከል፡ስለ፡ማንጻት፡ክርክር፡ኾነ።
26፤ወደ፡ዮሐንስም፡መጥተው፦መምህር፡ሆይ፥በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ከአንተ፡ጋራ፡የነበረው፡አንተም፡የመሰከርኽለት ፥እንሆ፥ርሱ፡ያጠምቃል፡ዅሉም፡ወደ፡ርሱ፡ይመጣሉ፡አሉት።
27፤ዮሐንስ፡መለሰ፥እንዲህ፡ሲል፦ከሰማይ፡ካልተሰጠው፡ሰው፡አንዳች፡ሊቀበል፡አይችልም።
28፤እናንተ፦እኔ፡ክርስቶስ፡አይደለኹም፥ነገር፡ግን፦ከርሱ፡በፊት፡ተልኬያለኹ፡እንዳልኹ፡ራሳችኹ፡ትመሰክሩ ልኛላችኹ።
29፤ሙሽራዪቱ፡ያለችው፡ርሱ፡ሙሽራ፡ነው፤ቆሞ፡የሚሰማው፡ሚዜው፡ግን፡በሙሽራው፡ድምፅ፡እጅግ፡ደስ፡ይለዋል። እንግዲህ፡ይህ፡ደስታዬ፡ተፈጸመ።
30፤ርሱ፡ሊልቅ፡እኔ፡ግን፡ላንስ፡ያስፈልጋል።
31፤ከላይ፡የሚመጣው፡ከዅሉ፡በላይ፡ነው፤ከምድር፡የሚኾነው፡የምድር፡ነው፥የምድሩንም፡ይናገራል።ከሰማይ፡የ ሚመጣው፡ከዅሉ፡በላይ፡ነው።
32፤ያየውንና፡የሰማውንም፡ይህን፡ይመሰክራል፥ምስክሩንም፡የሚቀበለው፡የለም።
33፤ምስክሩን፡የተቀበለ፡እግዚአብሔር፡እውነተኛ፡እንደ፡ኾነ፡አተመ።
34፤እግዚአብሔር፡የላከው፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ይናገራልና፤እግዚአብሔር፡መንፈሱን፡ሰፍሮ፡አይሰጥምና።
35፤አባት፡ልጁን፡ይወዳል፡ዅሉንም፡በእጁ፡ሰጥቶታል።
36፤በልጁ፡የሚያምን፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡አለው፤በልጁ፡የማያምን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በርሱ፡ላይ፡ይ ኖራል፡እንጂ፡ሕይወትን፡አያይም።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4፤
1፤እንግዲህ፦ኢየሱስ፡ከዮሐንስ፡ይልቅ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ያደርጋል፡ያጠምቅማል፡ማለትን፡ፈሪሳውያን፡እንደ፡ሰ ሙ፡ጌታ፡ባወቀ፡ጊዜ፥
2-3፤ይሁዳን፡ትቶ፡ወደ፡ገሊላ፡ደግሞ፡ኼደ፤ዳሩ፡ግን፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡እንጂ፡ኢየሱስ፡ራሱ፡አላጠመቀም።
4፤በሰማርያም፡ሊያልፍ፡ግድ፡ኾነበት።
5፤ስለዚህ፥ያዕቆብ፡ለልጁ፣ለዮሴፍ፡በሰጠው፡ስፍራ፡አጠገብ፡ወደምትኾን፥ሲካር፡ወደምትባል፡የሰማርያ፡ከተማ ፡መጣ፤
6፤በዚያም፡የያዕቆብ፡ጕድጓድ፡ነበረ።ኢየሱስም፡መንገድ፡ከመኼድ፡ደክሞ፡በጕድጓድ፡አጠገብ፡እንዲህ፡ተቀመጠ ፤ጊዜውም፡ስድስት፡ሰዓት፡ያኽል፡ነበረ።
7፤ከሰማርያ፡አንዲት፡ሴት፡ውሃ፡ልትቀዳ፡መጣች።ኢየሱስም፦ውሃ፡አጠጪኝ፡አላት፤
8፤ደቀ፡መዛሙርቱ፡ምግብ፡ሊገዙ፡ወደ፡ከተማ፡ኼደው፡ነበርና።
9፤ስለዚህ፥ሳምራዊቲቱ፦አንተ፡የይሁዳ፡ሰው፡ስትኾን፡ሳምራዊት፡ሴት፡ከምኾን፡ከእኔ፡መጠጥ፡እንዴት፡ትለምና ለኽ፧አለችው፤አይሁድ፡ከሳምራውያን፡ጋራ፡አይተባበሩም፡ነበርና።
10፤ኢየሱስ፡መልሶ፦የእግዚአብሔርን፡ስጦታና፦ውሃ፡አጠጪኝ፡የሚልሽ፡ማን፡መኾኑንስ፡ብታውቂ፥አንቺ፡ትለምኚ ው፡ነበርሽ፡የሕይወትም፡ውሃ፡ይሰጥሽ፡ነበር፡አላት።
11፤ሴቲቱ፦ጌታ፡ሆይ፥መቅጃ፡የለኽም፡ጕድጓዱም፡ጥልቅ፡ነው፤እንግዲህ፡የሕይወት፡ውሃ፡ከወዴት፡ታገኛለኽ፧
12፤በእውኑ፡አንተ፡ይህን፡ጕድጓድ፡ከሰጠን፡ከአባታችን፡ከያዕቆብ፡ትበልጣለኽን፧ራሱም፡ልጆቹም፡ከብቶቹም፡ ከዚህ፡ጠጥተዋል፡አለችው።
13፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ከዚህ፡ውሃ፡የሚጠጣ፡ዅሉ፡እንደ፡ገና፡ይጠማል፤
14፤እኔ፡ከምሰጠው፡ውሃ፡የሚጠጣ፡ዅሉ፡ግን፡ለዘለዓለም፡አይጠማም፥እኔ፡የምሰጠው፡ውሃ፡በርሱ፡ውስጥ፡ለዘለ ዓለም፡ሕይወት፡የሚፈልቅ፡የውሃ፡ምንጭ፡ይኾናል፡እንጂ፡አላት።
15፤ሴቲቱ፦ጌታ፡ሆይ፥እንዳልጠማ፡ውሃም፡ልቀዳ፡ወደዚህ፡እንዳልመጣ፡ይህን፡ውሃ፡ስጠኝ፡አለችው።
16፤ኢየሱስም፦ኺጂና፡ባልሽን፡ጠርተሽ፡ወደዚህ፡ነዪ፡አላት።
17፤ሴቲቱ፡መልሳ፦ባል፡የለኝም፡አለችው።ኢየሱስ፦ባል፡የለኝም፡በማለትሽ፡መልካም፡ተናገርሽ፤
18፤ዐምስት፡ባሎች፡ነበሩሽና፥አኹን፡ከአንቺ፡ጋራ፡ያለው፡ባልሽ፡አይደለም፤በዚህስ፡እውነት፡ተናገርሽ፡አላ ት።
19፤ሴቲቱ፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡ነቢይ፡እንደ፡ኾንኽ፡አያለኹ።
20፤አባቶቻችን፡በዚህ፡ተራራ፡ሰገዱ፤እናንተም፦ሰው፡ሊሰግድበት፡የሚገ፟ባ፟ው፡ስፍራ፡በኢየሩሳሌም፡ነው፡ት ላላችኹ፡አለችው።
21፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላት፦አንቺ፡ሴት፥እመኚኝ፥በዚህ፡ተራራ፡ወይም፡በኢየሩሳሌም፡ለአብ፡የማትሰግዱበት ፡ጊዜ፡ይመጣል።
22፤እናንተስ፡ለማታውቁት፡ትሰግዳላችኹ፤እኛ፡መዳን፡ከአይሁድ፡ነውና፥ለምናውቀው፡እንሰግዳለን።
23፤ነገር፡ግን፥በእውነት፡የሚሰግዱ፡ለአብ፡በመንፈስና፡በእውነት፡የሚሰግዱበት፡ጊዜ፡ይመጣል፡አኹንም፡ኾኗ ል፤አብ፡ሊሰግዱለት፡እንደ፡እነዚህ፡ያሉትን፡ይሻልና፤
24፤እግዚአብሔር፡መንፈስ፡ነው፥የሚሰግዱለትም፡በመንፈስና፡በእውነት፡ሊሰግዱለት፡ያስፈልጋቸዋል።
25፤ሴቲቱ፦ክርስቶስ፡የሚባል፡መሲሕ፡እንዲመጣ፡ዐውቃለኹ፤ርሱ፡ሲመጣ፡ዅሉን፡ይነግረናል፡አለችው።
26፤ኢየሱስ፦የምናገርሽ፡እኔ፡ርሱ፡ነኝ፡አላት።
27፤በዚያም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡መጡና፡ከሴት፡ጋራ፡በመነጋገሩ፡ተደነቁ፤ነገር፡ግን፦ምን፡ትፈልጊያለሽ፧ወ ይም፦ስለ፡ምን፡ትናገራታለኽ፧ያለ፡ማንም፡አልነበረም።
28፤ሴቲቱም፡እንስራዋን፡ትታ፡ወደ፡ከተማ፡ኼደች፡ለሰዎችም፦
29፤ያደረግኹትን፡ዅሉ፡የነገረኝን፡ሰው፡ኑና፡እዩ፤እንጃ፡ርሱ፡ክርስቶስ፡ይኾንን፧አለች።
30፤ከከተማ፡ወጥተው፡ወደ፡ርሱ፡ይመጡ፡ነበር።
31፤ይህም፡ሲኾን፡ሳለ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፦መምህር፡ሆይ፥ብላ፡ብለው፡ለመኑት።
32፤ርሱ፡ግን፦እናንተ፡የማታውቁት፡የምበላው፡መብል፡ለእኔ፡አለኝ፡አላቸው።
33፤ስለዚህ፥ደቀ፡መዛሙርቱ፦የሚበላው፡አንዳች፡ሰው፡አምጥቶለት፡ይኾንን፧ተባባሉ።
34፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦የእኔስ፡መብል፡የላከኝን፡ፈቃድ፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ሥራውንም፡እፈጽም፡ዘንድ፡ ነው።
35፤እናንተ፦ገና፡አራት፡ወር፡ቀርቷል፡መከርም፡ይመጣል፡ትሉ፡የለምን፧እንሆ፥እላችዃለኹ፥ዐይናችኹን፡አንሡ ፡አዝመራውም፡አኹን፡እንደ፡ነጣ፡ዕርሻውን፡ተመልከቱ።
36፤የሚያጭድ፡ደመ፡ወዝን፡ይቀበላል፥የሚዘራና፡የሚያጭድም፡ዐብረው፡ደስ፡እንዲላቸው፡ለዘለዓለም፡ሕይወት፡ ፍሬን፡ይሰበስባል።
37፤አንዱ፡ይዘራል፡አንዱም፡ያጭዳል፡የሚለው፡ቃል፡በዚህ፡እውነት፡ኾኗልና።
38፤እኔም፡እናንተ፡ያልደከማችኹበትን፡ታጭዱ፡ዘንድ፡ሰደድዃችኹ፤ሌላዎች፡ደከሙ፡እናንተም፡በድካማቸው፡ገባ ችኹ።
39፤ሴቲቱም፦ያደረግኹትን፡ዅሉ፡ነገረኝ፡ብላ፡ስለመሰከረችው፡ቃል፡ከዚያች፡ከተማ፡የሰማርያ፡ሰዎች፡ብዙ፡አ መኑበት።
40፤የሰማርያ፡ሰዎችም፡ወደ፡ርሱ፡በመጡ፡ጊዜ፡በእነርሱ፡ዘንድ፡እንዲኖር፡ለመኑት፤በዚያም፡ኹለት፡ቀን፡ያኽ ል፡ኖረ።
41፤ስለ፡ቃሉ፡ከፊተኛዎች፡ይልቅ፡ብዙ፡ሰዎች፡አመኑ፤
42፤ሴቲቱንም፦አኹን፡የምናምን፡ስለ፡ቃልሽ፡አይደለም፥እኛ፡ራሳችን፡ሰምተነዋልና፤ርሱም፡በእውነት፡ክርስቶ ስ፡የዓለም፡መድኀኒት፡እንደ፡ኾነ፡እናውቃለን፡ይሏት፡ነበር።
43፤ከኹለቱ፡ቀኖችም፡በዃላ፡ከዚያ፡ወጥቶ፡ወደ፡ገሊላ፡ኼደ።
44፤ነቢይ፡በገዛ፡አገሩ፡እንዳይከበር፡ኢየሱስ፡ራሱ፡መስክሯልና።
45፤ወደ፡ገሊላም፡በመጣ፡ጊዜ፥የገሊላ፡ሰዎች፡ራሳቸው፡ደግሞ፡ለበዓል፡መጥተው፡ነበርና፥በበዓል፡በኢየሩሳሌ ም፡ያደረገውን፡ዅሉ፡ስላዩ፡ተቀበሉት።
46፤ኢየሱስም፡ውሃውን፡የወይን፡ጠጅ፡ወዳደረገባት፡ወደ፡ገሊላ፡ቃና፡ዳግመኛ፡መጣ።በቅፍርናሖምም፡ልጁ፡የታ መመበት፡ከንጉሥ፡ቤት፡አንድ፡ሹም፡ነበረ።
47፤ርሱም፡ኢየሱስ፡ከይሁዳ፡ወደ፡ገሊላ፡እንደ፡መጣ፡ሰምቶ፡ልጁ፡ሊሞት፡ስለ፡አለው፡ወደ፡ርሱ፡ኼደ፡ወርዶም ፡እንዲፈውስለት፡ለመነው።
48፤ስለዚህም፡ኢየሱስ፦ምልክትና፡ድንቅ፡ነገር፡ካላያችኹ፡ከቶ፡አታምኑም፡አለው።
49፤ሹሙም፦ጌታ፡ሆይ፥ብላቴናዬ፡ሳይሞት፡ውረድ፡አለው።
50፤ኢየሱስም፦ኺድ፤ልጅኽ፡በሕይወት፡አለ፡አለው።ሰውዬውም፡ኢየሱስ፡የነገረውን፡ቃል፡አምኖ፡ኼደ።
51፤ርሱም፡ሲወርድ፡ሳለ፡ባሮቹ፡ተገናኙትና፦ብላቴናኽ፡በሕይወት፡አለ፡ብለው፡ነገሩት።
52፤ርሱም፡በጎ፡የኾነበትን፡ሰዓት፡ጠየቃቸው፤እነርሱም፦ትናንት፡በሰባት፡ሰዓት፡ንዳዱ፡ለቀቀው፡አሉት።
53፤አባቱም፥ኢየሱስ፦ልጅኽ፡በሕይወት፡አለ፡ባለው፡በዚያ፡ሰዓት፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቀ፤ርሱም፡ከቤተ፡ሰዎቹ፡ዅ ሉ፡ጋራ፡አመነ።
54፤ይህም፡ደግሞ፡ኢየሱስ፡ከይሁዳ፡ወደ፡ገሊላ፡መጥቶ፡ያደረገው፡ኹለተኛ፡ምልክት፡ነው።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5፤
1፤ከዚህ፡በዃላ፡የአይሁድ፡በዓል፡ነበረ፥ኢየሱስም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጣ።
2፤በኢየሩሳሌምም፡በበጎች፡በር፡አጠገብ፡በዕብራይስጥ፡ቤተ፡ሳይዳ፡የምትባል፡አንዲት፡መጠመቂያ፡ነበረች፤ዐ ምስትም፡መመላለሻ፡ነበረባት።
3፤በእነዚህ፡ውስጥ፡የውሃውን፡መንቀሳቀስ፡እየጠበቁ፡በሽተኛዎችና፡ዕውሮች፡ዐንካሳዎችም፡ሰውነታቸውም፡የሰ ለለ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ይተኙ፡ነበር።
4፤አንዳንድ፡ጊዜ፡የጌታ፡መልአክ፡ወደ፡መጠመቂያዪቱ፡ወርዶ፡ውሃውን፡ያናውጥ፡ነበርና፤እንግዲህ፡ከውሃው፡መ ናወጥ፡በዃላ፡በመዠመሪያ፡የገባ፡ከማናቸው፡ካለበት፡ደዌ፡ጤናማ፡ይኾን፡ነበር።
5፤በዚያም፡ከሠላሳ፡ስምንት፡ዓመት፡ዠምሮ፡የታመመ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፤
6፤ኢየሱስ፡ይህን፡ሰው፡ተኝቶ፡ባየ፡ጊዜ፥እስከ፡አኹን፡ብዙ፡ዘመን፡እንዲሁ፡እንደ፡ነበረ፡ዐውቆ፦ልትድን፡ት ወዳለኽን፧አለው።
7፤ድውዩም፦ጌታ፡ሆይ፥ውሃው፡በተናወጠ፡ጊዜ፡በመጠመቂያዪቱ፡ውስጥ፡የሚያኖረኝ፡ሰው፡የለኝም፥ነገር፡ግን፥እ ኔ፡ስመጣ፡ሳለኹ፡ሌላው፡ቀድሞኝ፡ይወርዳል፡ብሎ፡መለሰለት።
8፤ኢየሱስ፦ተነሣና፡ዐልጋኽን፡ተሸክመኽ፡ኺድ፡አለው።
9፤ወዲያውም፡ሰውዬው፡ዳነ፡ዐልጋውንም፡ተሸክሞ፡ኼደ።
10፤ያም፡ቀን፡ሰንበት፡ነበረ።ስለዚህ፡አይሁድ፡የተፈወሰውን፡ሰው፦ሰንበት፡ነው፥ዐልጋኽንም፡ልትሸከም፡አል ተፈቀደልኽም፡አሉት።
11፤ርሱ፡ግን፦ያዳነኝ፡ያ፡ሰው፦ዐልጋኽን፡ተሸክመኽ፡ኺድ፡አለኝ፡ብሎ፡መለሰላቸው።
12፤እነርሱም፦ዐልጋኽን፡ተሸክመኽ፡ኺድ፡ያለኽ፡ሰው፡ማን፡ነው፧ብለው፡ጠየቁት።
13፤ዳሩ፡ግን፡በዚያ፡ስፍራ፡ሕዝብ፡ሰለ፡ነበሩ፡ኢየሱስ፡ፈቀቅ፡ብሎ፡ነበርና፥የተፈወሰው፡ሰው፡ማን፡እንደ፡ ኾነ፡አላወቀም።
14፤ከዚህ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡በመቅደስ፡አገኘውና፦እንሆ፥ድነኻል፤ከዚህ፡የሚብስ፡እንዳይደርስብኽ፡ወደ፡ፊት፡ ኀጢአት፡አትሥራ፡አለው።
15፤ሰውዬው፡ኼዶ፡ያዳነው፡ኢየሱስ፡እንደ፡ኾነ፡ለአይሁድ፡ነገረ።
16፤ስለዚህም፡በሰንበት፡ይህን፡ስላደረገ፡አይሁድ፡ኢየሱስን፡ያሳድዱት፡ነበር፡ሊገድሉትም፡ይፈልጉ፡ነበር።
17፤ኢየሱስ፡ግን፦አባቴ፡እስከ፡ዛሬ፡ይሠራል፡እኔም፡ደግሞ፡እሠራለኹ፡ብሎ፡መለሰላቸው።
18፤እንግዲህ፡ሰንበትን፡ስለ፡ሻረ፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ደግሞ፡ራሱን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አስተካክ ሎ፦እግዚአብሔር፡አባቴ፡ነው፡ስለ፡አለ፥ስለዚህ፡አይሁድ፡ሊገድሉት፡አብዝተው፡ይፈልጉት፡ነበር።
19፤ስለዚህ፥ኢየሱስ፡መለሰ፥እንዲህም፡አላቸው፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥አብ፡ሲያደርግ፡ያየውን፡ነው፡ እንጂ፡ወልድ፡ከራሱ፡ሊያደርግ፡ምንም፡አይችልም፤ያ፡የሚያደርገውን፡ዅሉ፡ወልድ፡ደግሞ፡ይህን፡እንዲሁ፡ያደ ርጋልና።
20፤አብ፡ወልድን፡ይወዳልና፥የሚያደርገውንም፡ዅሉ፡ያሳየዋል፤እናንተም፡ትደነቁ፡ዘንድ፡ከዚህ፡የሚበልጥ፡ሥ ራ፡ያሳየዋል።
21፤አብ፡ሙታንን፡እንደሚያነሣ፡ሕይወትም፡እንደሚሰጣቸው፥እንዲሁ፡ወልድ፡ደግሞ፡ለሚወዳቸው፡ሕይወትን፡ይሰ ጣቸዋል።
22-23፤ሰዎች፡ዅሉ፡አብን፡እንደሚያከብሩት፡ወልድን፡ያከብሩት፡ዘንድ፥ፍርድን፡ዅሉ፡ለወልድ፡ሰጠው፡እንጂ፡አ ብ፡ባንድ፡ሰው፡ስንኳ፡አይፈርድም።ወልድን፡የማያከብር፡የላከውን፡አብን፡አያከብርም።
24፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ቃሌን፡የሚሰማ፡የላከኝንም፡የሚያምን፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡አለው፥ከሞትም ፡ወደ፡ሕይወት፡ተሻገረ፡እንጂ፡ወደ፡ፍርድ፡አይመጣም።
25፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ሙታን፡የእግዚአብሔርን፡ልጅ፡ድምፅ፡የሚሰሙበት፡ሰዓት፡ይመጣል፡ርሱም፡አ ኹን፡ነው፤የሚሰሙትም፡በሕይወት፡ይኖራሉ።
26፤አብ፡በራሱ፡ሕይወት፡እንዳለው፡እንዲሁ፡ደግሞ፡ለወልድ፡በራሱ፡ሕይወት፡እንዲኖረው፡ሰጥቶታልና።
27፤የሰው፡ልጅም፡ስለ፡ኾነ፡ይፈርድ፡ዘንድ፡ሥልጣን፡ሰጠው።
28-29፤በመቃብር፡ያሉቱ፡ዅሉ፡ድምፁን፡የሚሰሙበት፡ሰዓት፡ይመጣል፤መልካምም፡ያደረጉ፡ለሕይወት፡ትንሣኤ፡ክፉ ም፡ያደረጉ፡ለፍርድ፡ትንሣኤ፡ይወጣሉና፡በዚህ፡አታድንቁ።
30፤እኔ፡ከራሴ፡አንዳች፡ላደርግ፡አይቻለኝም፤እንደ፡ሰማኹ፡እፈርዳለኹ፡ፍርዴም፡ቅን፡ነው፥የላከኝን፡ፈቃድ ፡እንጂ፡ፈቃዴን፡አልሻምና።
31፤እኔ፡ስለ፡እኔ፡ስለ፡ራሴ፡ብመሰክር፡ምስክሬ፡እውነት፡አይደለም፤
32፤ስለ፡እኔ፡የሚመሰክር፡ሌላ፡ነው፥ርሱም፡ስለ፡እኔ፡የሚመሰክረው፡ምስክር፡እውነት፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቃለኹ ።
33፤እናንተ፡ወደ፡ዮሐንስ፡ልካችዃል፡ርሱም፡ለእውነት፡መስክሯል።
34፤እኔ፡ግን፡ከሰው፡ምስክር፡አልቀበልም፥እናንተ፡እንድትድኑ፡ይህን፡እላለኹ፡እንጂ።
35፤ርሱ፡የሚነድና፡የሚያበራ፡መብራት፡ነበረ፥እናንተም፡ጥቂት፡ዘመን፡በብርሃኑ፡ደስ፡ሊላችኹ፡ወደዳችኹ።
36፤እኔ፡ግን፡ከዮሐንስ፡ምስክር፡የሚበልጥ፡ምስክር፡አለኝ፤አብ፡ልፈጽመው፡የሰጠኝ፡ሥራ፥ይህ፡የማደርገው፡ ሥራ፥አብ፡እንደ፡ላከኝ፡ስለ፡እኔ፡ይመሰክራልና።
37፤የላከኝ፡አብም፡ርሱ፡ስለ፡እኔ፡መስክሯል።ድምፁን፡ከቶ፡አልሰማችኹም፥መልኩንም፡አላያችኹም፤
38፤ርሱም፡የላከውን፡እናንተ፡አታምኑምና፡በእናንተ፡ዘንድ፡የሚኖር፡ቃሉ፡የላችኹም።
39፤እናንተ፡በመጻሕፍት፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡እንዳላችኹ፡ይመስላችዃልና፥እነርሱን፡ትመረምራላችኹ፤እነርሱ ም፡ስለ፡እኔ፡የሚመሰክሩ፡ናቸው፤
40፤ነገር፡ግን፥ሕይወት፡እንዲኾንላችኹ፡ወደ፡እኔ፡ልትመጡ፡አትወዱም።
41-42፤ከሰው፡ክብርን፡አልቀበልም፤ዳሩ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ፍቅር፡በራሳችኹ፡እንደ፡ሌላችኹ፡ዐውቃችዃለኹ።
43፤እኔ፡በአባቴ፡ስም፡መጥቻለኹ፡አልተቀበላችኹኝምም፤ሌላው፡በራሱ፡ስም፡ቢመጣ፡ርሱን፡ትቀበሉታላችኹ።
44፤እናንተ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ክብር፡የምትቀባበሉ፡ከአንዱም፡ከእግዚአብሔር፡ያለውን፡ክብር፡የማትፈልጉ፥እን ዴት፡ልታምኑ፡ትችላላችኹ፧
45፤እኔ፡በአብ፡ዘንድ፡የምከሳችኹ፡አይምሰላችኹ፤የሚከሳችኹ፡አለ፤ርሱም፡ተስፋ፡የምታደርጉት፡ሙሴ፡ነው።
46፤ሙሴንስ፡ብታምኑት፡እኔን፡ባመናችኹ፡ነበር፤ርሱ፡ስለ፡እኔ፡ጽፏልና።
47፤መጻሕፍትን፡ካላመናችኹ፡ግን፡ቃሌን፡እንዴት፡ታምናላችኹ፧
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6፤
1፤ከዚህ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ወደገሊላ፡ባሕር፡ማዶ፡ተሻገረ፤ርሱም፡የጥብርያዶስ፡ባሕር፡ነው።
2፤በበሽተኛዎችም፡ያደረገውን፡ምልክቶች፡ስላዩ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ተከተሉት።
3፤ኢየሱስም፡ወደ፡ተራራ፡ወጣና፡በዚያ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ተቀመጠ።
4፤የአይሁድ፡በዓልም፡ፋሲካ፡ቀርቦ፡ነበር።
5፤ኢየሱስም፡ዐይኖቹን፡አንሥቶ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ወደ፡ርሱ፡ሲመጣ፡አየና፡ፊልጶስን፦እነዚህ፡እንዲበሉ፡እንጀራ፡ ከወዴት፡እንገዛለን፧አለው።
6፤ራሱ፡ሊያደርግ፡ያለውን፡ያውቅ፡ነበርና፥ሊፈትነው፡ይህን፡ተናገረ።
7፤ፊልጶስ፦እያንዳንዳቸው፡ትንሽ፡ትንሽ፡እንኳ፡እንዲቀበሉ፡የኹለት፡መቶ፡ዲናር፡እንጀራ፡አይበቃቸውም፡ብሎ ፡መለሰለት።
8፤ከደቀ፡መዛሙርቱ፡አንዱ፡የስምዖን፡ጴጥሮስ፡ወንድም፡እንድርያስ።
9፤ዐምስት፡የገብስ፡እንጀራና፡ኹለት፡ዓሣ፡የያዘ፡ብላቴና፡በዚህ፡አለ፤ነገር፡ግን፥እነዚህን፡ለሚያኽሉ፡ሰዎ ች፡ይህ፡ምን፡ይኾናል፧አለው።
10፤ኢየሱስም፦ሰዎቹን፡እንዲቀመጡ፡አድርጉ፡አለ።በዚያም፡ስፍራ፡ብዙ፡ሣር፡ነበረበት።ወንዶችም፡ተቀመጡ፡ቍ ጥራቸውም፡ዐምስት፡ሺሕ፡የሚያኽል፡ነበር።
11፤ኢየሱስም፡እንጀራውን፡ያዘ፥አመስግኖም፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡ለተቀመጡት፡ሰዎች፡ሰጧ ቸው፡እንዲሁም፡ከዓሣው፡በፈለጉት፡መጠን።
12፤ከጠገቡም፡በዃላ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦አንድ፡ስንኳ፡እንዳይጠፋ፡የተረፈውን፡ቍርስራሽ፡አከማቹ፡አላቸው።
13፤ሰለዚህ፡አከማቹ፥ከበሉትም፡ከዐምስቱ፡የገብስ፡እንጀራ፡የተረፈውን፡ቍርስራሽ፡ዐሥራ፡ኹለት፡መሶብ፡ሞሉ ።
14፤ከዚህ፡የተነሣ፡ሰዎቹ፡ኢየሱስ፡ያደረገውን፡ምልክት፡ባዩ፡ጊዜ፦ይህ፡በእውነት፡ወደ፡ዓለም፡የሚመጣው፡ነ ቢይ፡ነው፡አሉ።
15፤በዚህም፡ምክንያት፡ኢየሱስ፡ያነግሡት፡ዘንድ፡ሊመጡና፡ሊነጥቁት፡እንዳላቸው፡ዐውቆ፡ደግሞ፡ወደ፡ተራራ፡ ብቻውን፡ፈቀቅ፡አለ።
16፤በመሸም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ባሕር፡ወረዱ፥
17፤በታንኳም፡ገብተው፡በባሕር፡ማዶ፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡ይመጡ፡ነበር።አኹንም፡ጨልሞ፡ነበር፤ኢየሱስም፡ገና፡ ወደ፡እነርሱ፡አልመጣም፡ነበር፤
18፤ብርቱ፡ነፋስም፡ስለ፡ነፈሰ፡ባሕሩ፡ተናወጠ።
19፤ኻያ፡ዐምስት፡ወይም፡ሠላሳ፡ምዕራፍ፡ከቀዘፉ፡በዃላም፥ኢየሱስ፡በባሕር፡ላይ፡እየኼደ፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡ሲ ቀርብ፡አይተው፡ፈሩ።
20፤ርሱ፡ግን፦እኔ፡ነኝ፤አትፍሩ፡አላቸው።
21፤ስለዚህ፥በታንኳዪቱ፡ሊቀበሉት፡ወደዱ፤ወዲያውም፡ታንኳዪቱ፡ወደሚኼዱበት፡ምድር፡ደረሰች።
22፤በነገው፡በባሕር፡ማዶ፡ቆመው፡የነበሩ፡ሕዝቡ፡ከአንዲት፡ጀልባ፡በቀር፡በዚያ፡ሌላ፡ጀልባ፡እንዳልነበረች ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡ለብቻቸው፡እንደ፡ኼዱ፡እንጂ፡ኢየሱስ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡እንዳልገባ ፡አዩ፤
23፤ዳሩ፡ግን፡ሌላዎች፡ጀልባዎች፡ጌታ፡የባረከውን፡እንጀራ፡ወደበሉበት፡ስፍራ፡አጠገብ፡ከጥብርያዶስ፡መጡ።
24፤ሕዝቡም፡ኢየሱስ፡ወይም፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡በዚያ፡እንዳልነበሩ፡ባዩ፡ጊዜ፥ራሳቸው፡በጀልባዎቹ፡ገብተው፡ኢ የሱስን፡እየፈለጉ፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡መጡ።
25፤በባሕር፡ማዶም፡ሲያገኙት።መምህር፡ሆይ፥ወደዚህ፡መቼ፡መጣኽ፧አሉት።
26፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥የምትፈልጉኝ፡እንጀራን፡ስለ፡በላችኹና፡ስለ፡ጠገባችኹ፡ ነው፡እንጂ፡ምልክቶችን፡ስላያችኹ፡አይደለም።
27፤ለሚጠፋ፡መብል፡አትሥሩ፤ነገር፡ግን፥ለዘለዓለም፡ሕይወት፡ለሚኖር፡መብል፡የሰው፡ልጅ፡ለሚሰጣችኹ፡ሥሩ፤ ርሱን፡እግዚአብሔር፡አብ፡ዐትሞታልና።
28፤እንግዲህ፦የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡እንድንሠራ፡ምን፡እናድርግ፧አሉት።
29፤ኢየሱስ፡መልሶ፦ይህ፡የእግዚአብሔር፡ሥራ፡ርሱ፡በላከው፡እንድታምኑ፡ነው፡አላቸው።
30፤እንግዲህ፦እንኪያ፡አይተን፡እንድናምንኽ፡አንተ፡ምን፡ምልክት፡ታደርጋለኽ፧ምንስ፡ትሠራለኽ፧
31፤ይበሉ፡ዘንድ፡ከሰማይ፡እንጀራ፡ሰጣቸው፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥አባቶቻችን፡በምድረ፡በዳ፡መና፟፡በሉ፡አሉ ት።
32፤ኢየሱስም፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥እውነተኛ፡እንጀራ፡ከሰማይ፡የሚሰጣችኹ፡አባቴ፡ነው፡እንጂ፡ከሰ ማይ፡እንጀራ፡የሰጣችኹ፡ሙሴ፡አይደለም፤
33፤የእግዚአብሔር፡እንጀራ፡ከሰማይ፡የሚወርድ፡ለዓለምም፡ሕይወትን፡የሚሰጥ፡ነውና፥አላቸው።
34፤ስለዚህ፦ጌታ፡ሆይ፥ይህን፡እንጀራ፡ዘወትር፡ስጠን፡አሉት።
35፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦የሕይወት፡እንጀራ፡እኔ፡ነኝ፤ወደ፡እኔ፡የሚመጣ፡ከቶ፡አይራብም፡በእኔ፡የሚ ያምንም፡ዅልጊዜ፡ከቶ፡አይጠማም።
36፤ነገር፡ግን፥አይታችኹኝ፡እንዳላመናችኹ፡አልዃችኹ።
37፤አብ፡የሚሰጠኝ፡ዅሉ፡ወደ፡እኔ፡ይመጣል፥ወደ፡እኔም፡የሚመጣውን፡ከቶ፡ወደ፡ውጭ፡አላወጣውም፤
38፤ፈቃዴን፡ለማድረግ፡አይደለም፡እንጂ፡የላከኝን፡ፈቃድ፡ለማድረግ፡ከሰማይ፡ወርጃለኹና።
39፤ከሰጠኝም፡ዅሉ፡አንድን፡ስንኳ፡እንዳላጠፋ፡በመጨረሻው፡ቀን፡እንዳስነሣው፡እንጂ፡የላከኝ፡የአብ፡ፈቃድ ፡ይህ፡ነው።
40፤ልጅንም፡አይቶ፡በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡የዘለዓለም፡ሕይወትን፡እንዲያገኝ፡የአባቴ፡ፈቃድ፡ይህ፡ነው፥እኔ ም፡በመጨረሻው፡ቀን፡አስነሣዋለኹ።
41፤እንግዲህ፡አይሁድ፦ከሰማይ፡የወረደ፡እንጀራ፡እኔ፡ነኝ፡ስለ፡አለ፡ስለ፡ርሱ፡አንጐራጐሩና፦
42፤አባቱንና፡እናቱን፡የምናውቃቸው፡ይህ፡የዮሴፍ፡ልጅ፡ኢየሱስ፡አይደለምን፧እንግዲህ፦ከሰማይ፡ወርጃለኹ፡ እንዴት፡ይላል፧አሉ።
43፤ኢየሱስ፡መለሰ፡አላቸውም፦ርስ፡በርሳችኹ፡አታንጐራጕሩ።
44፤የላከኝ፡አብ፡ከሳበው፡በቀር፡ወደ፡እኔ፡ሊመጣ፡የሚችል፡የለም፥እኔም፡በመጨረሻው፡ቀን፡አስነሣዋለኹ።
45፤ዅሉም፡ከእግዚአብሔር፡የተማሩ፡ይኾናሉ፡ተብሎ፡በነቢያት፡ተጽፏል፤እንግዲህ፡ከአብ፡የሰማ፡የተማረም፡ዅ ሉ፡ወደ፡እኔ፡ይመጣል።
46፤አብን፡ያየ፡ማንም፡የለም፤ከእግዚአብሔር፡ከኾነ፡በቀር፥ርሱ፡አብን፡አይቷል።
47፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፡በእኔ፡የሚያምን፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡አለው።
48፤የሕይወት፡እንጀራ፡እኔ፡ነኝ።
49፤አባቶቻችኹ፡በምድረ፡በዳ፡መና፟፡በሉ፥ሞቱም፤
50፤ሰው፡ከርሱ፡በልቶ፡እንዳይሞት፡ከሰማይ፡አኹን፡የወረደ፡እንጀራ፡ይህ፡ነው።
51፤ከሰማይ፡የወረደ፡ሕያው፡እንጀራ፡እኔ፡ነኝ፤ሰው፡ከዚህ፡እንጀራ፡ቢበላ፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፤እኔም፡ስለ ዓለም፡ሕይወት፡የምሰጠው፡እንጀራ፡ሥጋዬ፡ነው።
52፤እንግዲህ፡አይሁድ፦ይህ፡ሰው፡ሥጋውን፡ልንበላ፡ይሰጠን፡ዘንድ፡እንዴት፡ይችላል፧ብለው፡ርስ፡በርሳቸው፡ ተከራከሩ።
53፤ስለዚህ፥ኢየሱስ፡እንዲህ፡አላቸው፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥የሰውን፡ልጅ፡ሥጋ፡ካልበላችኹ፡ደሙንም ፡ካልጠጣችኹ፡በራሳችኹ፡ሕይወት፡የላችኹም።
54፤ሥጋዬን፡የሚበላ፡ደሜንም፡የሚጠጣ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡አለው፥እኔም፡በመጨረሻው፡ቀን፡አስነሣዋለኹ።
55፤ሥጋዬ፡እውነተኛ፡መብል፡ደሜም፡እውነተኛ፡መጠጥ፡ነውና።
56፤ሥጋዬን፡የሚበላ፡ደሜንም፡የሚጠጣ፡በእኔ፡ይኖራል፡እኔም፡በርሱ፡እኖራለኹ።
57፤ሕያው፡አብ፡እንደ፡ላከኝ፡እኔም፡ከአብ፡የተነሣ፡ሕያው፡እንደምኾን፥እንዲሁ፡የሚበላኝ፡ደግሞ፡ከእኔ፡የ ተነሣ፡ሕያው፡ይኾናል።
58፤ከሰማይ፡የወረደ፡እንጀራ፡ይህ፡ነው፤አባቶቻችኹ፡መና፟፡በልተው፡እንደ፡ሞቱ፡አይደለም፤ይህን፡እንጀራ፡ የሚበላ፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፡
59፤በቅፍርናሖም፡ሲያስተምር፡ይህን፡በምኵራብ፡አለ።
60፤ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ብዙዎች፡በሰሙ፡ጊዜ፦ይህ፡የሚያስጨንቅ፡ንግግር፡ነው፤ማን፡ሊሰማው፡ይችላል፧አሉ።
61፤ኢየሱስ፡ግን፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ስለዚህ፡እንዳንጐራጐሩ፡በልቡ፡ዐውቆ፡አላቸው፦ይህ፡ያሰናክላችዃልን፧
62፤እንግዲህ፡የሰው፡ልጅ፡አስቀድሞ፡ወደነበረበት፡ሲወጣ፡ብታዩ፡እንዴት፡ይኾናል፧
63፤ሕይወትን፡የሚሰጥ፡መንፈስ፡ነው፤ሥጋ፡ምንም፡አይጠቅምም፤እኔ፡የነገርዃችኹ፡ቃል፡መንፈስ፡ነው፡ሕይወት ም፡ነው።
64፤ነገር፡ግን፥ከእናንተ፡የማያምኑ፡አሉ።ኢየሱስ፡የማያምኑት፡እነማን፡እንደ፡ኾኑ፡አሳልፎ፡የሚሰጠውም፡ማ ን፡እንደ፡ኾነ፡ከመዠመሪያ፡ያውቅ፡ነበርና።
65፤ደግሞ፦ስለዚህ፡አልዃችኹ፥ከአብ፡የተሰጠው፡ካልኾነ፡ወደ፡እኔ፡ሊመጣ፡የሚችል፡የለም፡አለ።
66፤ከዚህም፡የተነሣ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ብዙዎች፡ወደ፡ዃላ፡ተመለሱ፤ወደ፡ፊትም፡ከርሱ፡ጋራ፡አልኼዱም።
67፤ኢየሱስም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፦እናንተ፡ደግሞ፡ልትኼዱ፡ትወዳላችኹን፧አለ።
68፤ስምዖን፡ጴጥሮስ፦ጌታ፡ሆይ፥ወደ፡ማን፡እንኼዳለን፧አንተ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡ቃል፡አለኽ፤
69፤እኛስ፡አንተ፡ክርስቶስ፡የሕያው፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡እንደ፡ኾንኽ፡አምነናል፡ዐውቀናልም፡ብሎ፡መለሰለ ት።
70፤ኢየሱስም፦እኔ፡እናንተን፡ዐሥራ፡ኹለታችኹን፡የመረጥዃችኹ፡አይደለምን፧ከእናንተም፡አንዱ፡ዲያብሎስ፡ነ ው፡ብሎ፡መለሰላቸው።
71፤ስለስምዖንም፡ልጅ፡ስለአስቆሮቱ፡ይሁዳ፡ተናገረ፤ከዐሥራ፡ኹለቱ፡አንዱ፡የኾነ፡ርሱ፡አሳልፎ፡ይሰጠው፡ዘ ንድ፡አለውና።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7፤
1፤ከዚህም፡በዃላ፡ኢየሱስ፡አይሁድ፡ሊገድሉት፡ይፈልጉ፡ስለ፡ነበር፡በይሁዳ፡ሊመላለስ፡አይወድም፡ነበርና፥በ ገሊላ፡ይመላለስ፡ነበር።
2፤የአይሁድም፡የዳስ፡በዓል፡ቀርቦ፡ነበር።
3፤እንግዲህ፡ወንድሞቹ፦ደቀ፡መዛሙርትኽ፡ደግሞ፡የምታደርገውን፡ሥራ፡እንዲያዩ፡ከዚህ፡ተነሣና፡ወደ፡ይሁዳ፡ ኺድ፤
4፤ራሱ፡ሊገለጥ፡እየፈለገ፡በስውር፡የሚሠራ፡የለምና።እነዚህን፡ብታደርግ፥ራስኽን፡ለዓለም፡ግለጥ፡አሉት።
5፤ወንድሞቹ፡ስንኳ፡አላመኑበትም፡ነበርና።
6፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦ጊዜዬ፡ገና፡አልደረሰም፥ጊዜያችኹ፡ግን፡ዘወትር፡የተመቸ፡ነው።
7፤ዓለም፡እናንተን፡ሊጠላ፡አይቻለውም፤እኔ፡ግን፡ሥራው፡ክፉ፡መኾኑን፡እመሰክርበታለኹና፡እኔን፡ይጠላኛል።
8፤እናንተ፡ወደዚህ፡በዓል፡ውጡ፤እኔስ፡ጊዜዬ፡ገና፡ስላልተፈጸመ፡ወደዚህ፡በዓል፡ገና፡አልወጣም።
9፤ይህንም፡አላቸውና፡በገሊላ፡ቀረ።
10፤ወንድሞቹ፡ግን፡ወደ፡በዓሉ፡ከወጡ፡በዃላ፡በዚያን፡ጊዜ፡ርሱ፡ደግሞ፡በግልጥ፡ሳይኾን፡ተሰውሮ፡ወጣ።
11፤አይሁድም፦ርሱ፡ወዴት፡ነው፧እያሉ፡በበዓሉ፡ይፈልጉት፡ነበር።
12፤በሕዝብም፡መካከል፡ስለ፡ርሱ፡ብዙ፡ማንጐራጐር፡ነበረ፤አንዳንዱም፦ደግ፡ሰው፡ነው፤ሌላዎች፡ግን፦አይደለ ም፥ሕዝቡን፡ግን፡ያስታል፡ይሉ፡ነበር።
13፤ዳሩ፡ግን፡አይሁድን፡ስለ፡ፈሩ፡ማንም፡ስለ፡ርሱ፡በግልጥ፡አይናገርም፡ነበር።
14፤አኹንም፡በበዓሉ፡እኩሌታ፡ኢየሱስ፡ወደ፡መቅደስ፡ወጥቶ፡ያስተምር፡ነበር።
15፤አይሁድም፦ይህ፡ሰው፡ሳይማር፡መጻሕፍትን፡እንዴት፡ያውቃል፧ብለው፡ይደነቁ፡ነበር።
16፤ስለዚህ፥ኢየሱስ፡መለሰ፥እንዲህም፡አላቸው፦ትምህርቴስ፡ከላከኝ፡ነው፡እንጂ፡ከእኔ፡አይደለም፤
17፤ፈቃዱን፡ሊያደርግ፡የሚወድ፡ቢኖር፥ርሱ፡ይህ፡ትምህርት፡ከእግዚአብሔር፡ቢኾን፡ወይም፡እኔ፡ከራሴ፡የምና ገር፡ብኾን፡ያውቃል።
18፤ከራሱ፡የሚናገር፡የራሱን፡ክብር፡ይፈልጋል፤የላከውን፡ክብር፡የሚፈልግ፡ግን፡ርሱ፡እውነተኛ፡ነው፥በርሱ ም፡ዐመፃ፡የለበትም።
19፤ሙሴ፡ሕግን፡አልሰጣችኹምን፧ከእናንተ፡ግን፡ሕግን፡የሚያደርግ፡አንድ፡ስንኳ፡የለም።ልትገድሉኝ፡ስለ፡ም ን፡ትፈልጋላችኹ፧
20፤ሕዝቡ፡መለሱና፦ጋኔን፡አለብኽ፤ማን፡ሊገድልኽ፡ይፈልጋል፧አሉት።
21፤ኢየሱስ፡መለሰ፡አላቸውም፦አንድ፡ሥራ፡አደረግኹ፡ዅላችኹም፡ታደንቃላችኹ።
22፤ስለዚህ፥ሙሴ፡መገረዝን፡ሰጣችኹ፤ከአባቶችም፡ነው፡እንጂ፡ከሙሴ፡አይደለም፤በሰንበትም፡ሰውን፡ትገርዛላ ችኹ።
23፤የሙሴ፡ሕግ፡እንዳይሻር፡ሰው፡በሰንበት፡መገረዝን፡የሚቀበል፡ከኾነስ፡ሰውን፡ዅለንተናውን፡በሰንበት፡ጤ ናማ፡ስላደረግኹ፡ትቈጡኛላችኹን፧
24፤ቅን፡ፍርድ፡ፍረዱ፡እንጂ፥በመልክ፡አትፍረዱ።
25፤እንግዲህ፡ከኢየሩሳሌም፡ሰዎች፡አንዳንዶቹ፡እንዲህ፡አሉ፦ሊገድሉት፡የሚፈልጉት፡ይህ፡አይደለምን፧
26፤እንሆም፥በግልጥ፡ይናገራል፥አንዳችም፡አይሉትም።አለቃዎቹ፥ይህ፡ሰው፡በእውነት፡ክርስቶስ፡እንደ፡ኾነ፡ በእውነት፡ዐወቁን፧
27፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ከወዴት፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቀናል፤ክርስቶስ፡ሲመጣ፡ግን፡ከወዴት፡እንደ፡ኾነ፡ማንም፡አ ያውቅም።
28፤እንግዲህ፡ኢየሱስ፡በመቅደስ፡ሲያስተምር፦እኔንም፡ታውቁኛላችኹ፡ከወዴትም፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ፤እ ኔም፡በራሴ፡አልመጣኹም፥ነገር፡ግን፥እናንተ፡የማታውቁት፡የላከኝ፡እውነተኛ፡ነው፤
29፤እኔ፡ግን፡ከርሱ፡ዘንድ፡ነኝ፡ርሱም፡ልኮኛልና፥ዐውቀዋለኹ፡ብሎ፡ጮኸ።
30፤ስለዚህ፥ሊይዙት፡ይፈልጉ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥ጊዜው፡ገና፡ስላልደረሰ፡ማንም፡እጁን፡አልጫነበትም።
31፤ከሕዝቡ፡ግን፡ብዙዎች፡አመኑበትና፦ክርስቶስ፡በመጣ፡ጊዜ፡ይህ፡ካደረጋቸው፡ምልክቶች፡ይልቅ፡ያደርጋልን ፧አሉ።
32፤ፈሪሳውያንም፡ሕዝቡ፡ሰለ፡ርሱ፡እንደዚህ፡ሲያንጐራጕሩ፡ሰሙ፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ፈሪሳውያም፡ሊይዙት ፡ሎሌዎችን፡ላኩ።
33፤ኢየሱስም፦ገና፡ጥቂት፡ጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡እቈያለኹ፡ወደላከኝም፡እኼዳለኹ።
34፤ትፈልጉኛላችኹ፡አታገኙኝምም፤እኔም፡ወዳለኹበት፡እናንተ፡ልትመጡ፡አትችሉም፡አለ።
35፤እንግዲህ፡አይሁድ፦እኛ፡እንዳናገኘው፡ይህ፡ወዴት፡ይኼድ፡ዘንድ፡አለው፧በግሪክ፡ሰዎች፡መካከል፡ተበትነ ው፡ወደሚኖሩት፡ሊኼድና፡የግሪክን፡ሰዎች፡ሊያስተምር፡አለውን፧
36፤ርሱ፦ትፈልጉኛላችኹ፡አታገኙኝምም፡እኔም፡ወዳለኹበት፡እናንተ፡ልትመጡ፡አትችሉም፡የሚለው፡ይህ፡ቃል፡ም ንድር፡ነው፧ብለው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተነጋገሩ።
37፤ከበዓሉም፡በታላቁ፡በዃለኛው፡ቀን፡ኢየሱስ፡ቆሞ፦ማንም፡የተጠማ፡ቢኖር፡ወደ፡እኔ፡ይምጣና፡ይጠጣ።
38፤በእኔ፡የሚያምን፡መጽሐፍ፡እንዳለ፥የሕይወት፡ውሃ፡ወንዝ፡ከሆዱ፡ይፈልቃል፡ብሎ፡ጮኸ።
39፤ይህን፡ግን፡በርሱ፡የሚያምኑ፡ሊቀበሉት፡ስላላቸው፡ስለ፡መንፈስ፡ተናገረ፤ኢየሱስ፡ገና፡ስላልከበረ፥መን ፈስ፡ገና፡አልወረደም፡ነበርና።
40፤ስለዚህ፥ከሕዝቡ፡ዐያሌ፡ሰዎች፡ይህን፡ቃል፡ሲሰሙ፦ይህ፡በእውነት፡ነቢዩ፡ነው፡አሉ፤
41፤ሌላዎች፦ይህ፡ክርስቶስ፡ነው፡አሉ፤ሌላዎች፡ግን፦ክርስቶስ፡በእውኑ፡ከገሊላ፡ይመጣልን፧
42፤ክርስቶስ፡ከዳዊት፡ዘር፡ዳዊትም፡ከነበረባት፡መንደር፡ከቤተ፡ልሔም፡እንዲመጣ፡መጽሐፍ፡አላለምን፧አሉ።
43፤እንግዲህ፡ከርሱ፡የተነሣ፡በሕዝቡ፡መካከል፡መለያየት፡ኾነ፤
44፤ከነርሱም፡አንዳንዶቹ፡ሊይዙት፡ወደዱ፥ነገር፡ግን፥እጁን፡ማንም፡አልጫነበትም።
45፤ሎሌዎቹም፡ወደ፡ካህናት፡አለቃዎችና፡ወደ፡ፈሪሳውያን፡መጡ፤እነዚያም፦ያላመጣችኹት፡ስለ፡ምን፡ነው፧አሏ ቸው።
46፤ሎሌዎቹ፦እንደዚህ፡ሰው፡ማንም፡እንዲሁ፡ከቶ፡አልተናገረም፡ብለው፡መለሱ።
47፤እንግዲህ፡ፈሪሳውያን፦እናንተ፡ደግሞ፡ሳታችኹን፧
48፤ከአለቃዎች፡ወይስ፡ከፈሪሳውያን፡በርሱ፡ያመነ፡አለን፧
49፤ነገር፡ግን፥ሕግን፡የማያውቀው፡ይህ፡ሕዝብ፡ርጉም፡ነው፡ብለው፡መለሱላቸው።
50፤ከነርሱ፡አንዱ፡በሌሊት፡ቀድሞ፡ወደ፡ርሱ፡መጥቶ፡የነበረ፡ኒቆዲሞስ።
51፤ሕጋችን፡አስቀድሞ፡ከርሱ፡ሳይሰማ፡ምንስ፡እንዳደረገ፡ሳያውቅ፡በሰው፡ይፈርዳልን፧አላቸው።
52፤እነርሱም፡መለሱና፦አንተም፡ደግሞ፡ከገሊላ፡ነኽን፧ነቢይ፡ከገሊላ፡እንዳይነሣ፡መርምርና፡እይ፡አሉት።
53፤እያንዳንዱም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8፤
1፤ኢየሱስ፡ግን፡ወደ፡ደብረ፡ዘይት፡ኼደ።
2፤ማለዳም፡ደግሞ፡ወደ፡መቅደስ፡ደረሰ፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡መጡ።ተቀምጦም፡ያስተምራቸው፡ነበር።
3፤ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያንም፡በምንዝር፡የተያዘችን፡ሴት፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፡በመካከልም፡ርሱዋን፡አቁመው።
4፤መምህር፡ሆይ፥ይህች፡ሴት፡ስታመነዝር፡ተገኝታ፡ተያዘች።
5፤ሙሴም፡እንደነዚህ፡ያሉት፡እንዲወገሩ፡በሕግ፡አዘዘን፤አንተስ፡ስለ፡ርሷ፡ምን፡ትላለኽ፧አሉት።
6፤የሚከሱበትንም፡እንዲያገኙ፡ሊፈትኑት፡ይህን፡አሉ።ኢየሱስ፡ግን፡ጐንበስ፡ብሎ፡በጣቱ፡በምድር፡ላይ፡ጻፈ፤
7፤መላልሰው፡በጠየቁት፡ጊዜ፡ግን፡ቀና፡ብሎ፦ከእናንተ፡ኀጢአት፡የሌለበት፡አስቀድሞ፡በድንጋይ፡ይውገራት፡አ ላቸው።
8፤ደግሞም፡ጐንበስ፡ብሎ፡በጣቱ፡በምድር፡ላይ፡ጻፈ።
9፤እነርሱም፡ይህን፡ሲሰሙ፡ኅሊናቸው፡ወቀሳቸውና፡ከሽማግሌዎች፡ዠምረው፡እስከ፡ዃለኛዎች፡አንድ፡አንድ፡እያ ሉ፡ወጡ፤ኢየሱስም፡ብቻውን፡ቀረ፥ሴቲቱም፡በመካከል፡ቆማ፡ነበር።
10፤ኢየሱስም፡ቀና፡ብሎ፡ከሴቲቱ፡በቀር፡ማንንም፡ባላየ፡ጊዜ፦አንቺ፡ሴት፥እነዚያ፡ከሳሾችሽ፡ወዴት፡አሉ፧የ ፈረደብሽ፡የለምን፧አላት።
11፤ርሷም፦ጌታ፡ሆይ፥አንድ፡ስንኳ፡አለች።ኢየሱስም፦እኔም፡አልፈርድብሽም፤ኺጂ፥ካኹንም፡ዠምሮ፡ደግመሽ፡ኀ ጢአት፡አትሥሪ፡አላት።
12፤ደግሞም፡ኢየሱስ፦እኔ፡የዓለም፡ብርሃን፡ነኝ፤የሚከተለኝ፡የሕይወት፡ብርሃን፡ይኾንለታል፡እንጂ፡በጨለማ ፡አይመላለስም፡ብሎ፡ተናገራቸው።
13፤ፈሪሳውያንም፦አንተ፡ስለ፡ራስኽ፡ትመሰክራለኽ፤ምስክርነትኽ፡እውነት፡አይደለም፡አሉት።
14፤ኢየሱስ፡መለሰ፥አላቸውም፦እኔ፡ስለ፡ራሴ፡ምንም፡እንኳ፡ብመሰክር፡ከወዴት፡እንደመጣኹ፡ወዴትም፡እንድኼ ድ፡ዐውቃለኹና፡ምስክርነቴ፡እውነት፡ነው፤እናንተ፡ግን፡ከወዴት፡እንደ፡መጣኹ፡ወዴትም፡እንድኼድ፡አታውቁም ።
15፤እናንተ፡ሥጋዊ፡ፍርድን፡ትፈርዳላችኹ፤እኔ፡ባንድ፡ሰው፡ስንኳ፡አልፈርድም።
16፤የላከኝ፡አብ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነው፡እንጂ፡ብቻዬን፡አይደለኹምና፡እኔ፡ብፈርድ፡ፍርዴ፡እውነት፡ነው።
17፤የኹለት፡ሰዎችም፡ምስክርነት፡እውነት፡እንደ፡ኾነ፡በሕጋችኹ፡ተጽፏል።
18፤ስለ፡ራሴ፡የምመሰክር፡እኔ፡ነኝ፥የላከኝም፡አብ፡ስለ፡እኔ፡ይመሰክራል።
19፤እንግዲህ፦አባትኽ፡ወዴት፡ነው፧አሉት።ኢየሱስ፡መልሶ፦እኔንም፡ወይም፡አባቴንም፡አታውቁም፤እኔንስ፡ብታ ውቁኝ፡አባቴን፡ደግሞ፡ባወቃችኹ፡ነበር፡አላቸው።
20፤ኢየሱስ፡በመቅደስ፡ሲያስተምር፡በግምጃ፡ቤት፡አጠገብ፡ይህን፡ነገር፡ተናገረ፤ጊዜው፡ገና፡አልደረሰምና፡ ማንም፡አልያዘውም።
21፤ኢየሱስም፡ደግሞ፦እኔ፡እኼዳለኹ፡ትፈልጉኛላችኹም፡በኀጢአታችኹም፡ትሞታላችኹ፡እኔ፡ወደምኼድበት፡እናን ተ፡ልትመጡ፡አትችሉም፡አላቸው።
22፤አይሁድም፦እኔ፡ወደምኼድበት፡እናንተ፡ልትመጡ፡አትችሉም፡ማለቱ፡ራሱን፡ይገድላልን፧እንጃ፡አሉ።
23፤እናንተ፡ከታች፡ናችኹ፥እኔ፡ከላይ፡ነኝ፤እናንተ፡ከዚህ፡ዓለም፡ናችኹ፥እኔ፡ከዚህ፡ዓለም፡አይደለኹም።
24፤እንግዲህ፦በኀጢአታችኹ፡ትሞታላችኹ፡አልዃችኹ፤እኔ፡እንደኾንኹ፡ባታምኑ፡በኀጢአታችኹ፡ትሞታላችኹና፡አ ላቸው።
25፤እንግዲህ፦አንተ፡ማን፡ነኽ፧አሉት።ኢየሱስም፦ከመዠመሪያ፡ለእናንተ፡የተናገርኹት፡ነኝ።
26፤ስለ፡እናንተ፡የምናገረው፡የምፈርደውም፡ብዙ፡ነገር፡አለኝ፤ዳሩ፡ግን፡የላከኝ፡እውነተኛ፡ነው፥እኔም፡ከ ርሱ፡የሰማኹትን፡ይህን፡ለዓለም፡እናገራለኹ፡አላቸው።
27፤ስለ፡አብ፡እንደ፡ነገራቸው፡አላስተዋሉም።
28፤ስለዚህም፡ኢየሱስ፦የሰውን፡ልጅ፡ከፍ፡ከፍ፡ባደረጋችኹት፡ጊዜ፡እኔ፡እኾን፡ዘንድ፡አባቴም፡እንዳስተማረ ኝ፡እነዚህን፡እናገር፡ዘንድ፡እንጂ፡ከራሴ፡አንዳች፡እንዳላደርግ፡በዚያን፡ጊዜ፡ታውቃላችኹ።
29፤የላከኝም፡ከእኔ፡ጋራ፡ነው፤እኔ፡ደስ፡የሚያሠኘውን፡ዘወትር፡አደርጋለኹና፡አብ፡ብቻዬን፡አይተወኝም፡አ ላቸው።
30፤ይህን፡ሲናገር፡ብዙዎች፡በርሱ፡አመኑ።
31፤ኢየሱስም፡ያመኑትን፡አይሁድ፦እናንተ፡በቃሌ፡ብትኖሩ፡በእውነት፡ደቀ፡መዛሙርቴ፡ናችኹ፤
32፤እውነትንም፡ታውቃላችኹ፡እውነትም፡ሐራነት፡ያወጣችዃል፡አላቸው።
33፤እነርሱም፡መልሰው፦የአብርሃም፡ዘር፡ነን፡ለአንድም፡ስንኳ፡ከቶ፡ባሪያዎች፡አልኾንም፤አንተ፦ሐራነት፡ት ወጣላችኹ፡እንዴት፡ትላለኽ፧አሉት።
34፤ኢየሱስ፡መለሰ፥እንዲህ፡ሲል፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ኀጢአት፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡የኀጢአት፡ባሪያ፡ ነው።
35፤ባሪያም፡ለዘለዓለም፡በቤት፡አይኖርም፤ልጁ፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።
36፤እንግዲህ፡ልጁ፡ሐራነት፡ቢያወጣችኹ፡በእውነት፡ሐራነት፡ትወጣላችኹ።
37፤የአብርሃም፡ዘር፡መኾናችኹንስ፡ዐውቃለኹ፥ነገር፡ግን፥ቃሌ፡በእናንተ፡አይኖርምና፡ልትገድሉኝ፡ትፈልጋላ ችኹ።
38፤እኔ፡በአባቴ፡ዘንድ፡ያየኹትን፡እናገራለኹ፤እናንተም፡ደግሞ፡በአባታችኹ፡ዘንድ፡ያያችኹትን፡ታደርጋላች ኹ።
39፤መልሰውም፦አባታችንስ፡አብርሃም፡ነው፡አሉት።ኢየሱስም፦የአብርሃም፡ልጆች፡ብትኾኑ፡የአብርሃምን፡ሥራ፡ ባደረጋችኹ፡ነበር።
40፤ነገር፡ግን፥አኹን፡ከእግዚአብሔር፡የሰማኹትን፡እውነት፡የነገርዃችኹን፡ሰው፡ልትገድሉኝ፡ትፈልጋላችኹ፤ አብርሃም፡እንዲህ፡አላደረገም።
41፤እናንተ፡የአባታችኹን፡ሥራ፡ታደርጋላችኹ፡አላቸው፦እኛስ፡ከዝሙት፡አልተወለድንም፤አንድ፡አባት፡አለን፥ ርሱም፡እግዚአብሔር፡ነው፡አሉት።
42፤ኢየሱስም፡አላቸው፦እግዚአብሔርስ፡አባታችኹ፡ከኾነ፡በወደዳችኹኝ፡ነበር፤እኔ፡ከእግዚአብሔር፡ወጥቼ፡መ ጥቻለኹና፤ርሱ፡ላከኝ፡እንጂ፡ከራሴ፡አልመጣኹምና።
43፤ንግግሬን፡የማታስተውሉ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧ቃሌን፡ልትሰሙ፡ስለማትችሉ፡ነው።
44፤እናንተ፡ከአባታችኹ፡ከዲያብሎስ፡ናችኹ፡የአባታችኹንም፡ምኞት፡ልታደርጉ፡ትወዳላችኹ።ርሱ፡ከመዠመሪያ፡ ነፍሰ፡ገዳይ፡ነበረ፤እውነትም፡በርሱ፡ስለሌለ፡በእውነት፡አልቆመም።ሐሰትን፡ሲናገር፡ከራሱ፡ይናገራል፥ሐሰ ተኛ፡የሐሰትም፡አባት፡ነውና።
45፤እኔ፡ግን፡እውነትን፡የምናገር፡ስለ፡ኾንኹ፡አታምኑኝም።
46፤ከእናንተ፡ስለ፡ኀጢአት፡የሚወቅሰኝ፡ማን፡ነው፧እውነት፡የምናገር፡ከኾንኹ፡እናንተ፡ስለ፡ምን፡አታምኑኝ ም፧
47፤ከእግዚአብሔር፡የኾነ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ይሰማል፤እናንተ፡ከእግዚአብሔር፡አይደላችኹምና፡ስለዚህ፡ አትሰሙም።
48፤አይሁድ፡መልሰው፦ሳምራዊ፡እንደ፡ኾንኽ፡ጋኔንም፡እንዳለብኽ፡በማለታችን፡እኛ፡መልካም፡እንል፡የለምን፧ አሉት።
49፤ኢየሱስም፡መለሰ፥እንዲህ፡ሲል፦እኔስ፡ጋኔን፡የለብኝም፥ነገር፡ግን፥አባቴን፡አከብራለኹ፡እናንተም፡ታዋ ርዱኛላችኹ።
50፤እኔ፡ግን፡የራሴን፡ክብር፡አልፈልግም፤የሚፈልግ፡የሚፈርድም፡አለ።
51፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ቃሌን፡የሚጠብቅ፡ቢኖር፡ለዘለዓለም፡ሞትን፡አያይም።
52፤አይሁድ፦ጋኔን፡እንዳለብኽ፡አኹን፡ዐወቅን።አብርሃም፡ስንኳ፡ሞተ፥ነቢያትም፤አንተም፦ቃሌን፡የሚጠብቅ፡ ቢኖር፡ለዘለዓለም፡ሞትን፡አይቀምስም፡ትላለኽ።
53፤በእውኑ፡አንተ፡ከሞተው፡ከአባታችን፡ከአብርሃም፡ትበልጣለኽን፧ነቢያትም፡ሞቱ፤ራስኽን፡ማንን፡ታደርጋለ ኽ፧አሉት።
54፤ኢየሱስም፡መለሰ፥አለም፦እኔ፡ራሴን፡ባከብር፡ክብሬ፡ከንቱ፡ነው፤የሚያከብረኝ፡እናንተ፡አምላካችን፡የም ትሉት፡አባቴ፡ነው፤
55፤አላወቃችኹትምም፥እኔ፡ግን፡ዐውቀዋለኹ።አላውቀውም፡ብል፡እንደናንተ፡ሐሰተኛ፡በኾንኹ፤ዳሩ፡ግን፡ዐውቀ ዋለኹ፡ቃሉንም፡እጠብቃለኹ።
56፤አባታችኹ፡አብርሃም፡ቀኔን፡ያይ፡ዘንድ፡ሐሤት፡አደረገ፥አየም፡ደስም፡አለው።
57፤አይሁድም፦ገና፡ዐምሳ፡ዓመት፡ያልኾነኽ፡አብርሃምን፡አይተኻልን፧አሉት።
58፤ኢየሱስም፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥አብርሃም፡ሳይወለድ፡እኔ፡አለኹ፡አላቸው።
59፤ስለዚህ፥ሊወግሩት፡ድንጋይ፡አነሡ፤ኢየሱስ፡ግን፡ተሰወራቸው፥ከመቅደስም፡ወጥቶ፡በመካከላቸው፡ዐልፎ፡ኼ ደ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9፤
1፤ሲያልፍም፡ከመወለዱ፡ዠምሮ፡ዕውር፡የኾነውን፡ሰው፡አየ።
2፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦መምህር፡ሆይ፥ይህ፡ሰው፡ዕውር፡ኾኖ፡እንዲወለድ፡ኀጢአት፡የሠራ፡ማን፡ነው፧ርሱ፡ወይስ፡ ወላጆቹ፧ብለው፡ጠየቁት።
3፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰ፦የእግዚአብሔር፡ሥራ፡በርሱ፡እንዲገለጥ፡ነው፡እንጂ፡ርሱ፡ወይም፡ወላጆቹ፡ ኀጢአት፡አልሠሩም።
4፤ቀን፡ሳለ፡የላከኝን፡ሥራ፡ላደርግ፡ይገ፟ባ፟ኛል፤ማንም፡ሊሠራ፡የማይችልባት፡ሌሊት፡ትመጣለች።
5፤በዓለም፡ሳለኹ፡የዓለም፡ብርሃን፡ነኝ።
6፤ይህን፡ብሎ፡ወደ፡መሬት፡እንትፍ፡አለ፡በምራቁም፡ጭቃ፡አድርጎ፡በጭቃው፡የዕውሩን፡ዐይኖች፡ቀባና፦
7፤ኺድና፡በሰሊሖም፡መጠመቂያ፡ታጠብ፡አለው፤(ትርጓሜው፡'የተላከ'፡ነው)።ስለዚህ፡ኼዶ፡ታጠበ፥እያየም፡መጣ።
8፤ጎረቤቶቹም፡ቀድሞም፡ሲለምን፡አይተውት፡የነበሩ፦ይህ፡ተቀምጦ፡ይለምን፡የነበረ፡አይደለምን፧አሉ።
9፤ሌላዎች፦ርሱ፡ነው፡አሉ፤ሌላዎች፦አይደለም፡ርሱን፡ይመስላል፡እንጂ፡አሉ፤ርሱ፦እኔ፡ነኝ፡አለ።
10፤ታድያ፦ዐይኖችኽ፡እንዴት፡ተከፈቱ፧አሉት።
11፤ርሱ፡መልሶ፦ኢየሱስ፡የሚባለው፡ሰው፡ጭቃ፡አድርጎ፡አይኖቼን፡ቀባና፦ወደሰሊሖም፡መጠመቂያ፡ኼደኽ፡ታጠብ ፡አለኝ፤ኼጄ፡ታጥቤም፡አየኹ፡አለ።
12፤ያ፡ሰው፡ወዴት፡ነው፧አሉት፦አላውቅም፡አለ።
13፤በፊት፡ዕውር፡የነበረውን፡ሰው፡ወደ፡ፈሪሳውያን፡ወሰዱት።
14፤ኢየሱስም፡ጭቃ፡አድርጎ፡ዐይኖቹን፡የከፈተበት፡ቀን፡ሰንበት፡ነበረ።
15፤ስለዚህ፥ፈሪሳውያን፡ደግሞ፡እንዴት፡እንዳየ፡እንደ፡ገና፡ጠየቁት።ርሱም፦ጭቃ፡በዐይኖቼ፡አኖረ፥ታጠብኹ ም፥አያለኹም፡አላቸው።
16፤ከፈሪሳውያንም፡አንዳንዶቹ፦ይህ፡ሰው፡ሰንበትን፡አያከብርምና፡ከእግዚአብሔር፡አይደለም፡አሉ።ሌላዎች፡ ግን፦ኀጢአትኛ፡ሰው፡እንደነዚህ፡ያሉ፡ምልክቶች፡ሊያደርግ፡እንዴት፡ይችላል፧አሉ።
17፤በመካከላቸውም፡መለያየት፡ኾነ።ከዚህም፡የተነሣ፡ዕውሩን፦አንተ፡ዐይኖችኽን፡ስለከፈተ፡ስለ፡ርሱ፡ምን፡ ትላለኽ፧ደግሞ፡አሉት።ርሱም፦ነቢይ፡ነው፡አለ።
18፤አይሁድ፡የዚያን፡ያየውን፡ወላጆች፡እስኪጠሩ፡ድረስ፡ዕውር፡እንደ፡ነበረ፡እንዳየም፡ስለ፡ርሱ፡አላመኑም ፥
19፤እነርሱንም፦እናንተ፡ዕውር፡ኾኖ፡ተወለደ፡የምትሉት፡ልጃችኹ፡ይህ፡ነውን፧ታድያ፡አኹን፡እንዴት፡ያያል፧ ብለው፡ጠየቋቸው።
20፤ወላጆቹም፡መልሰው፦ይህ፡ልጃችን፡እንደ፡ኾነ፡ዕውርም፡ኾኖ፡እንደ፡ተወለደ፡እናውቃለን፤
21፤ዳሩ፡ግን፡አኹን፡እንዴት፡እንዳየ፡አናውቅም፥ወይም፡ዐይኖቹን፡ማን፡እንደ፡ከፈተ፡እኛ፡አናውቅም፤ጠይቁ ት፡ርሱ፡ሙሉ፡ሰው፡ነው፤ርሱ፡ስለ፡ራሱ፡ይናገራል፡አሉ።
22፤ወላጆቹ፡አይሁድን፡ስለ፡ፈሩ፡ይህን፡አሉ፤ርሱ፡ክርስቶስ፡ነው፡ብሎ፡የሚመሰክር፡ቢኖር፡ከምኵራብ፡እንዲ ያወጡት፡አይሁድ፡ከዚህ፡በፊት፡ተስማምተው፡ነበርና።
23፤ስለዚህ፥ወላጆቹ፦ሙሉ፡ሰው፡ነው፥ጠይቁት፡አሉ።
24፤ስለዚህ፥ዕውር፡የነበረውን፡ሰው፡ኹለተኛ፡ጠርተው፦እግዚአብሔርን፡አክብር፤ይህ፡ሰው፡ኀጢአተኛ፡መኾኑን ፡እኛ፡እናውቃለን፡አሉት።
25፤ርሱም፡መልሶ፦ኀጢአተኛ፡መኾኑን፡አላውቅም፤ዕውር፡እንደ፡ነበርኹ፡አኹንም፡እንዳይ፡ይህን፡አንድ፡ነገር ፡ዐውቃለኹ፡አለ።
26፤ደግመውም፦ምን፡አደረገልኽ፧እንዴትስ፡ዐይኖችኽን፡ከፈተ፧አሉት።
27፤ርሱም፡መልሶ፦አስቀድሜ፡ነገርዃችኹ፡አልሰማችኹምም፤ስለ፡ምን፡ዳግመኛ፡ልትሰሙ፡ትወዳላችኹ፧እናንተ፡ደ ግሞ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ልትኾኑ፡ትወዳላችኹን፧አላቸው።
28፤ተሳድበውም፦አንተ፡የርሱ፡ደቀ፡መዝሙር፡ነኽ፥እኛ፡ግን፡የሙሴ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ነን፤
29፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንደ፡ተናገረው፡እኛ፡እናውቃለን፥ይህ፡ሰው፡ግን፡ከወዴት፡እንደ፡ኾነ፡አናውቅም፡ አሉት።
30፤ሰውዬው፡መለሰ፡እንዲህም፡አላቸው፦ከወዴት፡እንደ፡ኾነ፡እናንተ፡አለማወቃችኹ፡ይህ፡ድንቅ፡ነገር፡ነው፥ ዳሩ፡ግን፡ዐይኖቼን፡ከፈተ።
31፤እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፡ፈቃዱንም፡የሚያደርግ፡ቢኖር፡ያንን፡እግዚአብሔር፡ይሰማዋል፡እንጂ፡ኀጢአተኛዎ ችን፡እንዳይሰማ፡እናውቃለን።
32፤ዕውር፡ኾኖ፡የተወለደውን፡ዐይኖች፡ማንም፡እንደ፡ከፈተ፡ዓለም፡ከተፈጠረ፡ዠምሮ፡አልተሰማም፤
33፤ይህ፡ሰው፡ከእግዚአብሔር፡ባይኾን፡ምንም፡ሊያደርግ፡ባልቻለም፡ነበር።
34፤መልሰው፦አንተ፡ዅለንተናኽ፡በኀጢአት፡ተወለድኽ፥አንተም፡እኛን፡ታስተምረናለኽን፧አሉት።ወደ፡ውጭም፡አ ወጡት።
35፤ኢየሱስም፡ወደ፡ውጭ፡እንዳወጡት፡ሰማ፤ሲያገኘውም፦አንተ፡በእግዚአብሔር፡ልጅ፡ታምናለኽን፧አለው።
36፤ርሱም፡መልሶ፦ጌታ፡ሆይ፥በርሱ፡አምን፡ዘንድ፡ማን፡ነው፧አለ።
37፤ኢየሱስም፦አይተኸዋልም፡ከአንተ፡ጋራም፡የሚናገረው፡ርሱ፡ነው፡አለው።
38፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥አምናለኹ፡አለ፤ሰገደለትም።
39፤ኢየሱስም፦የማያዩ፡እንዲያዩ፡የሚያዩም፡እንዲታወሩ፡እኔ፡ወደዚህ፡ዓለም፡ለፍርድ፡መጣኹ፡አለ።
40፤ከፈሪሳውያንም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡ይህን፡ሰምተው፦እኛ፡ደግሞ፡ዕውሮች፡ነንን፧አሉት።
41፤ኢየሱስም፡አላቸው፦ዕውሮችስ፡ብትኾኑ፡ኀጢአት፡ባልኾነባችኹም፡ነበር፤አኹን፡ግን፦እናያለን፡ትላላችኹ፤ ኀጢአታችኹ፡ይኖራል።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10፤
1፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ወደበጎች፡በረት፡በበሩ፡የማይገባ፡በሌላ፡መንገድ፡ግን፡የሚወጣ፡ርሱ፡ሌባ፡ ወንበዴም፡ነው፤
2፤በበሩ፡የሚገባ፡ግን፡የበጎች፡እረኛ፡ነው።
3፤ለርሱ፡በረኛው፡ይከፍትለታል፤በጎቹም፡ድምፁን፡ይሰሙታል፥የራሱንም፡በጎች፡በየስማቸው፡ጠርቶ፡ይወስዳቸዋ ል።
4፤የራሱንም፡ዅሉ፡ካወጣቸው፡በዃላ፡በፊታቸው፡ይኼዳል፥በጎቹም፡ድምፁን፡ያውቃሉና፡ይከተሉታል፤
5፤ከሌላው፡ግን፡ይሸሻሉ፡እንጂ፡አይከተሉትም፥የሌላዎችን፡ድምፅ፡አያውቁምና።
6፤ኢየሱስ፡ይህን፡ምሳሌ፡ነገራቸው፤እነርሱ፡ግን፡የነገራቸው፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አላስተዋሉም።
7፤ኢየሱስም፡ደግሞ፡አላቸው፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥እኔ፡የበጎች፡በር፡ነኝ።
8፤ከእኔ፡በፊት፡የመጡ፡ዅሉ፡ሌባዎችና፡ወንበዴዎች፡ናቸው፤ዳሩ፡ግን፡በጎቹ፡አልሰሟቸውም።
9፤በሩ፡እኔ፡ነኝ፤በእኔ፡የሚገባ፡ቢኖር፡ይድናል፥ይገባልም፡ይወጣልም፡መሰማሪያም፡ያገኛል።
10፤ሌባው፡ሊሰርቅና፡ሊያርድ፡ሊያጠፋም፡እንጂ፡ስለ፡ሌላ፡አይመጣም፤እኔ፡ሕይወት፡እንዲኾንላቸው፡እንዲበዛ ላቸውም፡መጣኹ።
11፤መልካም፡እረኛ፡እኔ፡ነኝ።መልካም፡እረኛ፡ነፍሱን፡ስለ፡በጎቹ፡ያኖራል።
12፤እረኛ፡ያልኾነው፡በጎቹም፡የርሱ፡ያልኾኑ፡ሞያተኛ፡ግን፥ተኵላ፡ሲመጣ፡ባየ፡ጊዜ፥በጎቹን፡ትቶ፡ይሸሻል፤ ተኵላም፡ይነጥቃቸዋል፡በጎቹንም፡ይበትናቸዋል።
13፤ሞያተኛ፡ስለ፡ኾነ፡ለበጎቹም፡ስለማይገደው፡ሞያተኛው፡ይሸሻል።
14-15፤መልካም፡እረኛ፡እኔ፡ነኝ፥አብም፡እንደሚያውቀኝ፡እኔም፡አብን፡እንደማውቀው፡የራሴን፡በጎች፡ዐውቃለኹ ፡የራሴም፡በጎች፡ያውቁኛል፤ነፍሴንም፡ስለ፡በጎች፡አኖራለኹ።
16፤ከዚህም፡በረት፡ያልኾኑ፡ሌላዎች፡በጎች፡አሉኝ፤እነርሱን፡ደግሞ፡ላመጣ፡ይገ፟ባ፟ኛል፥ድምፄንም፡ይሰማሉ ፥አንድም፡መንጋ፡ይኾናሉ፥እረኛውም፡አንድ።
17፤ነፍሴን፡ደግሞ፡አነሣት፡ዘንድ፡አኖራለኹና፡ስለዚህ፡አብ፡ይወደኛል።
18፤እኔ፡በፈቃዴ፡አኖራታለኹ፡እንጂ፡ከእኔ፡ማንም፡አይወስዳትም።ላኖራት፡ሥልጣን፡አለኝ፡ደግሞም፡ላነሣት፡ ሥልጣን፡አለኝ፡ይህችን፡ትእዛዝ፡ከአባቴ፡ተቀበልኹ።
19፤እንግዲህ፡ከዚህ፡ቃል፡የተነሣ፡በአይሁድ፡መካከል፡እንደ፡ገና፡መለያየት፡ኾነ።
20፤ከነርሱም፡ብዙዎች፦ጋኔን፡አለበት፡አብዷልም፤ስለ፡ምንስ፡ትሰሙታላችኹ፧አሉ።
21፤ሌላዎችም፦ይህ፡ጋኔን፡ያለበት፡ሰው፡ቃል፡አይደለም፤ጋኔን፡የዕውሮችን፡ዐይኖች፡ሊከፍት፡ይችላልን፧አሉ ።
22፤በኢየሩሳሌምም፡የመቅደስ፡መታደስ፡በዓል፡ኾነ፤
23፤ክረምትም፡ነበረ።ኢየሱስም፡በመቅደስ፡በሰሎሞን፡ደጅ፡መመላለሻ፡ይመላለስ፡ነበር።
24፤አይሁድም፡ርሱን፡ከበ፟ው፦እስከ፡መቼ፡ድረስ፡በጥርጣሪ፡ታቈየናለኽ፧አንተ፡ክርስቶስ፡እንደ፡ኾንኽ፡ገል ጠኽ፡ንገረን፡አሉት።
25፤ኢየሱስም፡መለሰላቸው፥እንዲህ፡ሲል፦ነገርዃችኹ፡አታምኑምም፡እኔ፡በአባቴ፡ስም፡የማደርገው፡ሥራ፡ይህ፡ ስለ፡እኔ፡ይመሰክራል፤
26፤እናንተ፡ግን፡እንደ፡ነገርዃችኹ፡ከበጎቼ፡ስላልኾናችኹ፡አታምኑም።
27፤በጎቼ፡ድምፄን፡ይሰማሉ፡እኔም፡ዐውቃቸዋለኹ፡ይከተሉኝማል፤
28፤እኔም፡የዘለዓለም፡ሕይወትን፡እሰጣቸዋለኹ፥ለዘለዓለምም፡አይጠፉም፥ከእጄም፡ማንም፡አይነጥቃቸውም።
29፤የሰጠኝ፡አባቴ፡ከዅሉ፡ይበልጣል፥ከአባቴም፡እጅ፡ሊነጥቃቸው፡ማንም፡አይችልም።
30፤እኔና፡አብ፡አንድ፡ነን።
31፤አይሁድ፡ሊወግሩት፡ደግመው፡ድንጋይ፡አነሡ።
32፤ኢየሱስ፦ከአባቴ፡ብዙ፡መልካም፡ሥራ፡አሳየዃችኹ፤ከነርሱ፡ስለ፡ማናቸው፡ሥራ፡ትወግሩኛላችኹ፧ብሎ፡መለሰ ላቸው።
33፤አይሁድም፦ስለ፡መልካም፡ሥራ፡አንወግርኽም፤ስለ፡ስድብ፤አንተም፡ሰው፡ስትኾን፡ራስኽን፡አምላክ፡ስለ፡ማ ድረግኽ፡ነው፡እንጂ፡ብለው፡መለሱለት።
34፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰላቸው፦እኔ፦አማልክት፡ናችኹ፡አልኹ፡ተብሎ፡በሕጋችኹ፡የተጻፈ፡አይደለምን ፧
35፤መጽሐፉ፡ሊሻር፡አይቻልምና፡እነዚያን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡የመጣላቸውን፡አማልክት፡ካላቸው፥
36፤የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኝ፡ስላልኹ፡እናንተ፡አብ፡የቀደሰውን፡ወደ፡ዓለምም፡የላከውን፦ትሳደባለኽ፡ትሉታ ላችኹን፧
37፤እኔ፡የአባቴን፡ሥራ፡ባላደርግ፡አትመኑኝ፤
38፤ባደርገው፡ግን፥እኔን፡ስንኳ፡ባታምኑ፡አብ፡በእኔ፡እንደ፡ኾነ፡እኔም፡በአብ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቁና፡ታስ ተውሉ፡ዘንድ፡ሥራውን፡እመኑ።
39፤እንግዲህ፡ደግመው፡ሊይዙት፡ፈለጉ፤ከእጃቸውም፡ወጣ።
40፤ዮሐንስም፡በመዠመሪያ፡ያጠምቅበት፡ወደነበረው፡ስፍራ፡ወደዮርዳኖስ፡ማዶ፡እንደ፡ገና፡ኼደ፡በዚያም፡ኖረ ።
41፤ብዙ፡ሰዎችም፡ወደ፡ርሱ፡መጥተው፦ዮሐንስ፡አንድ፡ምልክት፡ስንኳ፡አላደረገም፥ነገር፡ግን፥ዮሐንስ፡ስለዚ ህ፡ሰው፡የተናገረው፡ዅሉ፡እውነት፡ነበረ፡አሉ።
42፤በዚያም፡ብዙዎች፡በርሱ፡አመኑ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11፤
1፤ከማርያምና፡ከእኅቷ፡ከማርታ፡መንደር፡ከቢታንያ፡የኾነ፡አልዓዛር፡የሚባል፡አንድ፡ሰው፡ታሞ፡ነበር።
2፤ማርያምም፡ጌታን፡ሽቱ፡የቀባችው፡እግሩንም፡በጠጕሯ፡ያበሰችው፡ነበረች፤ወንድሟም፡አልዓዛር፡ታሞ፡ነበር።
3፤ስለዚህ፥እኅቶቹ፦ጌታ፡ሆይ፥እንሆ፥የምትወደ፟ው፡ታሟል፡ብለው፡ወደ፡ርሱ፡ላኩ።
4፤ኢየሱስም፡ሰምቶ፦ይህ፡ሕመም፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡በርሱ፡ይከብር፡ዘንድ፡ስለእግዚአብሔር፡ክብር፡ነው፡እ ንጂ፡ለሞት፡አይደለም፡አለ።
5፤ኢየሱስም፡ማርታንና፡እኅቷን፡አልዓዛርንም፡ይወድ፡ነበር።
6፤እንደ፡ታመመም፡በሰማ፡ጊዜ፡ያን፡ጊዜ፡በነበረበት፡ስፍራ፡ኹለት፡ቀን፡ዋለ፤
7፤ከዚህም፡በዃላ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፦ወደ፡ይሁዳ፡ደግሞ፡እንኺድ፡አላቸው።
8፤ደቀ፡መዛሙርቱ፦መምህር፡ሆይ፥አይሁድ፡ከጥቂት፡ጊዜ፡በፊት፡ሊወግሩኽ፡ይፈልጉ፡ነበር፥ደግሞም፡ወደዚያ፡ት ኼዳለኽን፧አሉት።
9፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ቀኑ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ሰዓት፡አይደለምን፧በቀን፡የሚመላለስ፡ቢኖር፡የዚህን፡ዓለም፡ብርሃን ፡ያያልና፥አይሰናከልም፤
10፤በሌሊት፡የሚመላለስ፡ቢኖር፡ግን፡ብርሃን፡በርሱ፡ስለሌለ፡ይሰናከላል፡አላቸው።
11፤ይህን፡ተናገረ፤ከዚህም፡በዃላ፦ወዳጃችን፡አልዓዛር፡ተኝቷል፤ነገር፡ግን፥ከእንቅልፉ፡ላስነሣው፡እኼዳለ ኹ፡አላቸው።
12፤እንግዲህ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፦ጌታ፡ሆይ፥ተኝቶስ፡እንደ፡ኾነ፡ይድናል፡አሉት።
13፤ኢየሱስስ፡ስለ፡ሞቱ፡ተናግሮ፡ነበር፤እነርሱ፡ግን፡ስለ፡እንቅልፍ፡መተኛት፡እንደ፡ተናገረ፡መሰላቸው።
14፤እንግዲህ፡ያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡በግልጥ፦አልዓዛር፡ሞተ፤
15፤እንድታምኑም፡በዚያ፡ባለመኖሬ፡ስለ፡እናንተ፡ደስ፡ይለኛል፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ርሱ፡እንኺድ፡አላቸው።
16፤ስለዚህ፥ዲዲሞስ፡የሚሉት፡ቶማስ፥ለባልንጀራዎቹ፣ለደቀ፡መዛሙርት፦ከርሱ፡ጋራ፡እንሞት፡ዘንድ፡እኛ፡ደግ ሞ፡እንኺድ፡አለ።
17፤ኢየሱስም፡በመጣ፡ጊዜ፡በመቃብር፡እስከ፡አኹን፡አራት፡ቀን፡ኾኖት፡አገኘው።
18፤ቢታንያም፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ምዕራፍ፡ያኽል፡ለኢየሩሳሌም፡ቅርብ፡ነበረች።
19፤ከአይሁድም፡ብዙዎች፡ስለ፡ወንድማቸው፡ሊያጽናኗቸው፡ወደ፡ማርታና፡ወደ፡ማርያም፡መጥተው፡ነበር።
20፤ማርታም፡ኢየሱስ፡እንደ፡መጣ፡በሰማች፡ጊዜ፡ልትቀበለው፡ወጣች፤ማርያም፡ግን፡በቤት፡ተቀምጣ፡ነበር።
21፤ማርታም፡ኢየሱስን፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡በዚህ፡ኖረኽ፡ብትኾን፡ወንድሜ፡ባልሞተም፡ነበር፤
22፤አኹንም፡ከእግዚአብሔር፡የምትለምነውን፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡እንዲሰጥኽ፡ዐውቃለኹ፡አለችው።
23፤ኢየሱስም፦ወንድምሽ፡ይነሣል፡አላት።
24፤ማርታም፦በመጨረሻው፡ቀን፡በትንሣኤ፡እንዲነሣ፡ዐውቃለኹ፡አለችው።
25፤ኢየሱስም፦ትንሣኤና፡ሕይወት፡እኔ፡ነኝ፤የሚያምንብኝ፡ቢሞት፡እንኳ፡ሕያው፡ይኾናል፤
26፤ሕያው፡የኾነም፡የሚያምንብኝም፡ዅሉ፡ለዘለዓለም፡አይሞትም፤ይህን፡ታምኚያለሽን፧አላት።
27፤ርሷም፦አዎን፡ጌታ፡ሆይ፤አንተ፡ወደ፡ዓለም፡የሚመጣው፡ክርስቶስ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡እንደ፡ኾንኽ፡እኔ ፡አምናለኹ፡አለችው።
28፤ይህንም፡ብላ፡ኼደች፥እኅቷንም፡ማርያምን፡በስውር፡ጠርታ፦መምህሩ፡መጥቷል፡ይጠራሽማል፡አለቻት።
29፤ርሷም፡በሰማች፡ጊዜ፡ፈጥና፡ተነሣች፡ወደ፡ርሱም፡መጣች፤
30፤ኢየሱስም፡ማርታ፡በተቀበለችበት፡ስፍራ፡ነበረ፡እንጂ፡ገና፡ወደ፡መንደሩ፡አልገባም፡ነበር።
31፤ሲያጽናኗት፡ከርሷ፡ጋራ፡በቤት፡የነበሩ፡አይሁድም፡ማርያም፡ፈጥና፡እንደ፡ተነሣችና፡እንደ፡ወጣች፡ባዩ፡ ጊዜ፥ወደ፡መቃብር፡ኼዳ፡በዚያ፡ልታለቅስ፡መስሏቸው፡ተከተሏት።
32፤ማርያምም፡ኢየሱስ፡ወዳለበት፡መጥታ፡ባየችው፡ጊዜ፡በእግሩ፡ላይ፡ወድቃ፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡በዚህ፡ኖረኽ፡ ብትኾን፡ወንድሜ፡ባልሞተም፡ነበር፡አለችው።
33፤ኢየሱስም፡ርሷ፡ስታለቅስ፡ከርሷም፡ጋራ፡የመጡት፡አይሁድ፡ሲያለቅሱ፡አይቶ፡በመንፈሱ፡ዐዘነ፡በራሱም፡ታ ወከ፤
34፤ወዴት፡አኖራችኹት፧አለም።እነርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥መጥተኽ፡እይ፡አሉት።
35፤ኢየሱስም፡እንባውን፡አፈሰሰ።
36፤ስለዚህ፥አይሁድ፦እንዴት፡ይወደ፟ው፡እንደ፡ነበረ፡እዩ፡አሉ።
37፤ከነርሱ፡ግን፡አንዳንዶቹ፦ይህ፡የዕውሩን፡ዐይኖች፡የከፈተ፡ይህን፡ደግሞ፡እንዳይሞት፡ያደርግ፡ዘንድ፡ባ ልቻለም፡ነበርን፧አሉ።
38፤ኢየሱስም፡በራሱ፡ዐዝኖ፡ወደ፡መቃብሩ፡መጣ፤ርሱም፡ዋሻ፡ነበረ፤ድንጋይም፡ተገጥሞበት፡ነበር።
39፤ኢየሱስ፦ድንጋዩን፡አንሡ፡አለ።የሞተውም፡እኅት፡ማርታ፦ጌታ፡ሆይ፥ከሞተ፡አራት፡ቀን፡ኾኖታልና፥አኹን፡ ይሸታል፡አለችው።
40፤ኢየሱስ፦ብታምኚስ፡የእግዚአብሔርን፡ክብር፡እንድታዪ፡አልነገርኹሽምን፧አላት።
41፤ድንጋዩንም፡አነሡት።ኢየሱስም፡ዐይኖቹን፡ወደ፡ላይ፡አንሥቶ፦አባት፡ሆይ፥ስለ፡ሰማኸኝ፡አመሰግንኻለኹ።
42፤ዅልጊዜም፡እንድትሰማኝ፡ዐወቅኹ፤ነገር፡ግን፥አንተ፡እንደ፡ላክኸኝ፡ያምኑ፡ዘንድ፡በዚህ፡ዙሪያ፡ስለቆሙ ት፡ሕዝብ፡ተናገርኹ፡አለ።
43፤ይህንም፡ብሎ፡በታላቅ፡ድምፅ፦አልዓዛር፡ሆይ፥ወደ፡ውጭ፡ና፡ብሎ፡ጮኸ።
44፤የሞተውም፡እጆቹና፡እግሮቹ፡በመግነዝ፡እንደ፡ተገነዙ፡ወጣ፤ፈቱም፡በጨርቅ፡እንደ፡ተጠመጠመ፡ነበር።ኢየ ሱስም፦ፍቱትና፡ይኺድ፡ተዉት፡አላቸው።
45፤ስለዚህ፥ወደ፡ማርያም፡ከመጡት፥ኢየሱስም፡ያደረገውን፡ካዩት፡ከአይሁድ፡ብዙዎች፡በርሱ፡አመኑ፤
46፤ከነርሱ፡አንዳንዶቹ፡ግን፡ወደ፡ፈሪሳውያን፡ኼደው፡ኢየሱስ፡ያደረገውን፡ነገሯቸው።
47፤እንግዲህ፡የካህናት፡አለቃዎችና፡ፈሪሳውያን፡ሸንጎ፡ሰብስበው፦ምን፡እናድርግ፧ይህ፡ሰው፡ብዙ፡ምልክቶች ፡ያደርጋልና።
48፤እንዲሁ፡ብንተወው፡ዅሉ፡በርሱ፡ያምናሉ፤የሮሜም፡ሰዎች፡መጥተው፡አገራችንን፡ወገናችንንም፡ይወስዳሉ፡አ ሉ።
49፤በዚያችም፡ዓመት፡ሊቀ፡ካህናት፡የነበረ፡ቀያፋ፡የሚሉት፡ከነርሱ፡አንዱ፦እናንተ፡ምንም፡አታውቁም፤
50፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ከሚጠፋ፡አንድ፡ሰው፡ስለ፡ሕዝቡ፡ይሞት፡ዘንድ፡እንዲሻለን፡አታስቡም፡አላቸው።
51፤ይህንም፡የተናገረ፡ከራሱ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥በዚያች፡ዓመት፡ሊቀ፡ካህናት፡ነበረና፡ኢየሱስ፡ስለ፡ሕ ዝቡ፡ሊሞት፡እንዳለው፡ትንቢት፡ተናገረ፤
52፤ስለ፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥የተበተኑትን፡የእግዚአብሔርን፡ልጆች፡ደግሞ፡በአንድነት፡እን ዲሰበስባቸው፡ነው፡እንጂ።
53፤እንግዲህ፡ከዚያ፡ቀን፡ዠምረው፡ሊገድሉት፡ተማከሩ።
54፤ከዚያ፡ወዲያም፡ኢየሱስ፡በአይሁድ፡መካከል፡ተገልጦ፡አልተመላለሰም፤ነገር፡ግን፥ከዚያ፡በምድረ፡በዳ፡አ ጠገብ፡ወዳለች፡ምድር፥ኤፍሬም፡ወደምትባል፡ከተማ፡ኼደ፤በዚያም፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ተቀመጠ።
55፤የአይሁድም፡ፋሲካ፡ቀርቦ፡ነበር።ብዙ፡ሰዎችም፡ራሳቸውን፡ያነጹ፡ዘንድ፡ከፋሲካ፡በፊት፡ከአገሩ፡ወደ፡ኢ የሩሳሌም፡ወጡ።
56፤ኢየሱስንም፡ይፈልጉት፡ነበር፤በመቅደስም፡ቆመው፡ርስ፡በርሳቸው፦ምን፡ይመስላችዃል፧ወደ፡በዓሉ፡አይመጣ ም፡ይኾንን፧ተባባሉ።
57፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ፈሪሳውያንም፡ይይዙት፡ዘንድ፥ርሱ፡ያለበትን፡ስፍራ፡የሚያውቀው፡ሰው፡ቢኖር፡እን ዲያመለክታቸው፡አዘ፟ው፡ነበር።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12፤
1፤ከፋሲካም፡በፊት፡በስድስተኛው፡ቀን፡ኢየሱስ፡ከሙታን፡ያስነሣው፡አልዓዛር፡ወደ፡ነበረበት፡ወደ፡ቢታንያ፡ መጣ።
2፤በዚያም፡እራት፡አደረጉለት፤ማርታም፡ታገለግል፡ነበር፤አልዓዛር፡ግን፡ከርሱ፡ጋራ፡ከተቀመጡት፡አንዱ፡ነበ ረ።
3፤ማርያምም፡ዋጋው፡እጅግ፡የከበረ፡የጥሩ፡ናርዶስ፡ሽቱ፡ንጥር፡ወስዳ፡የኢየሱስን፡እግር፡ቀባች፤በጠጕሯም፡ እግሩን፡አበሰች፤ቤቱም፡ከናርዶስ፡ሽቱ፡ሞላ።
4፤ነገር፡ግን፥ከደቀ፡መዛሙርቱ፡አንዱ፡አሳልፎ፡ሊሰጠው፡ያለው፡የስምዖን፡ልጅ፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ።
5፤ይህ፡ሽቱ፡ለሦስት፡መቶ፡ዲናር፡ተሽጦ፡ለድኻዎች፡ያልተሰጠ፡ስለ፡ምን፡ነው፧አለ።
6፤ይህንም፡የተናገረ፡ሌባ፡ስለ፡ነበረ፡ነው፡እንጂ፡ለድኻዎች፡ተገዶ፟ላቸው፡አይደለም፤ከረጢትም፡ይዞ፡በውስ ጡ፡ከሚገባው፡ይወስድ፡ስለ፡ነበረ፡ነው።
7፤ኢየሱስም፦ለምቀበርበት፡ቀን፡እንድትጠብቀው፡ተዋት፤
8፤ድኻዎችስ፡ዅልጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኖራሉና፥እኔ፡ግን፡ዅልጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡አልኖርም፡አለ።
9፤ከአይሁድም፡ብዙ፡ሕዝብ፡በዚያ፡እንደ፡ነበረ፡ዐውቀው፡መጡ፥ከሙታንም፡ያስነሣውን፡አልዓዛርን፡ደግሞ፡እን ዲያዩ፡ነበረ፡እንጂ፡ስለ፡ኢየሱስ፡ብቻ፡አይደለም።
10፤የካህናት፡አለቃዎችም፡አልዓዛርን፡ደግሞ፡ሊገድሉት፡ተማከሩ፥
11፤ከአይሁድ፡ብዙዎች፡ከርሱ፡የተነሣ፡ኼደው፡በኢየሱስ፡ያምኑ፡ነበርና።
12፤በማግስቱ፡ወደ፡በዓሉ፡መጥተው፡የነበሩ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ኢየሱስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንዲመጣ፡በሰሙ፡ጊዜ፥
13፤የዘንባባ፡ዛፍ፡ዝንጣፊ፡ይዘው፡ሊቀበሉት፡ወጡና፦ሆሣዕና፤በጌታ፡ስም፡የሚመጣ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የተባ ረከ፡ነው፡እያሉ፡ጮኹ።
14-15፤አንቺ፡የጽዮን፡ልጅ፡አትፍሪ፤እንሆ፥ንጉሥሽ፡በአህያ፡ውርንጫ፡ላይ፡ተቀምጦ፡ይመጣል፡ተብሎ፡እንደ፡ተ ጻፈ፥ኢየሱስ፡የአህያ፡ውርንጫ፡አግኝቶ፡በርሱ፡ተቀመጠ።
16፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ይህን፡ነገር፡በመዠመሪያ፡አላስተዋሉም፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፡ከከበረ፡በዃላ፡በዚያን፡ ጊዜ፡ይህ፡ስለ፡ርሱ፡እንደ፡ተጻፈ፡ይህንም፡እንዳደረጉለት፡ትዝ፡አላቸው።
17፤አልዓዛርንም፡ከመቃብር፡ጠርቶ፡ከሙታን፡ሲያስነሣው፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ይመሰክሩለት፡ነበር።
18፤ስለዚህ፥ደግሞ፡ሕዝቡ፡ይህን፡ምልክት፡እንዳደረገ፡ስለ፡ሰሙ፥ሊቀበሉት፡ወጡ።
19፤ሰለዚህ፡ፈሪሳውያን፡ርስ፡በርሳቸው፦አንድ፡ስንኳ፡ልታደርጉ፡እንዳይቻላችኹ፡ታያላችኹን፧እንሆ፥ዓለሙ፡ በዃላው፡ተከትሎት፡ኼዷል፡ተባባሉ።
20፤በበዓሉም፡ሊሰግዱ፡ከወጡት፡አንዳንዶቹ፡የግሪክ፡ሰዎች፡ነበሩ፤
21፤እነርሱም፡ከገሊላ፡ቤተ፡ሳይዳ፡ወደሚኾን፡ወደ፡ፊልጶስ፡መጥተው፦ጌታ፡ሆይ፥ኢየሱስን፡ልናይ፡እንወዳለን ፡ብለው፡ለመኑት።
22፤ፊልጶስም፡መጥቶ፡ለእንድርያስ፡ነገረው፤እንድርያስና፡ፊልጶስ፡መጥተው፡ለኢየሱስ፡ነገሩት።
23፤ኢየሱስም፡መለሰላቸው፥እንዲህ፡ሲል፦የሰው፡ልጅ፡ይከብር፡ዘንድ፡ሰዓቱ፡ደርሷል።
24፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥የስንዴ፡ቅንጣት፡በምድር፡ወድቃ፡ካልሞተች፡ብቻዋን፡ትቀራለች፤ብትሞት፡ግ ን፡ብዙ፡ፍሬ፡ታፈራለች።
25፤ነፍሱን፡የሚወድ፡ያጠፋታል፥ነፍሱንም፡በዚህ፡ዓለም፡የሚጠላ፡ለዘለዓለም፡ሕይወት፡ይጠብቃታል።
26፤የሚያገለግለኝ፡ቢኖር፡ይከተለኝ፥እኔም፡ባለኹበት፡አገልጋዬ፡ደግሞ፡በዚያ፡ይኾናል፤የሚያገለግለኝም፡ቢ ኖር፡አብ፡ያከብረዋል።
27፤አኹን፡ነፍሴ፡ታውካለች፡ምንስ፡እላለኹ፧አባት፡ሆይ፥ከዚህ፡ሰዓት፡አድነኝ።ነገር፡ግን፥ስለዚህ፡ወደዚህ ፡ሰዓት፡መጣኹ።
28፤አባት፡ሆይ፥ስምኽን፡አክብረው።ስለዚህም፦አከበርኹት፥ደግሞም፡አከብረዋለኹ፡የሚል፡ድምፅ፡ከሰማይ፡መጣ ።
29፤በዚያ፡ቆመው፡የነበሩትም፡ሕዝብ፡በሰሙ፡ጊዜ፦ነጐድጓድ፡ነው፡አሉ፤ሌላዎች፦መልአክ፡ተናገረው፡አሉ።
30፤ኢየሱስም፡መለሰ፥እንዲህ፡ሲል፦ይህ፡ድምፅ፡ስለ፡እናንተ፡መጥቷል፡እንጂ፥ስለ፡እኔ፡አይደለም።
31፤አኹን፡የዚህ፡ዓለም፡ፍርድ፡ደርሷል፤አኹን፡የዚህ፡ዓለም፡ገዢ፡ወደ፡ውጭ፡ይጣላል፤
32፤እኔም፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡ያልኹ፡እንደ፡ኾነ፡ዅሉን፡ወደ፡እኔ፡እስባለኹ።
33፤በምን፡ዐይነትም፡ሞት፡ይሞት፡ዘንድ፡እንዳለው፡ሲያመለክታቸው፡ይህን፡ተናገረ።
34፤እንግዲህ፡ሕዝቡ፦እኛስ፥ክርስቶስ፡ለዘለዓለም፡እንዲኖር፡ከሕጉ፡ሰምተናል፤አንተስ፥የሰው፡ልጅ፡ከፍ፡ከ ፍ፡ይል፡ዘንድ፡እንዲያስፈልገው፡እንዴት፡ትላለኽ፧ይህ፡የሰው፡ልጅ፡ማን፡ነው፧ብለው፡መለሱለት።
35፤ኢየሱስም፦ገና፡ጥቂት፡ጊዜ፡ብርሃን፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነው።ጨለማ፡እንዳይደርስባችኹ፡ብርሃን፡ሳለላችኹ፡ ተመላለሱ፤በጨለማም፡የሚመላለስ፡ወዴት፡እንዲኼድ፡አያውቅም።
36፤የብርሃን፡ልጆች፡እንድትኾኑ፡ብርሃን፡ሳለላችኹ፡በብርሃኑ፡እመኑ፡አላቸው።ኢየሱስም፡ይህን፡ተናግሮ፡ኼ ደና፡ተሰወረባቸው።
37-38፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ያኽል፡ምልክት፡በፊታቸው፡ምንም፡ቢያደርግ፤ነቢዩ፡ኢሳይያስ፦ጌታ፡ሆይ፥ማን፡ምስክ ርነታችንን፡አመነ፧የእግዚአብሔርስ፡ክንድ፡ለማን፡ተገለጠ፧ብሎ፡የተናገረው፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፥በርሱ፡አ ላመኑም።
39-40፤ኢሳይያስ፡ደግሞ፦በዐይኖቻቸው፡እንዳያዩ፥በልባቸውም፡እንዳያስተውሉ፥እንዳይመለሱም፥እኔም፡እንዳልፈ ውሳቸው፥ዐይኖቻቸውን፡አሳወረ፡ልባቸውንም፡አደነደነ፡ብሏልና፥ስለዚህ፡ማመን፡አቃታቸው።
41፤ክብሩን፡ስላየ፡ኢሳይያስ፡ይህን፡አለ፥ስለ፡ርሱም፡ተናገረ።
42፤ከዚህም፡ጋራ፡ከአለቃዎች፡ደግሞ፡ብዙዎች፡በርሱ፡አመኑ፤ነገር፡ግን፥ከምኵራብ፡እንዳያስወጧቸው፡በፈሪሳ ውያን፡ምክንያት፡አልመሰከሩለትም፤
43፤ከእግዚአብሔር፡ክብር፡ይልቅ፡የሰውን፡ክብር፡ወደዋልና።
44፤ኢየሱስም፡ጮኸ፥እንዲህም፡አለ፦በእኔ፡የሚያምን፡በላከኝ፡ማመኑ፡ነው፡እንጂ፡በእኔ፡አይደለም፤
45፤እኔንም፡የሚያይ፡የላከኝን፡ያያል።
46፤በእኔ፡የሚያምን፡ዅሉ፡በጨለማ፡እንዳይኖር፡እኔ፡ብርሃን፡ኾኜ፡ወደ፡ዓለም፡መጥቻለኹ።
47፤ዓለምን፡ላድን፡እንጂ፡በዓለም፡ልፈርድ፡አልመጣኹምና፡ቃሌን፡ሰምቶ፡የማይጠብቀው፡ቢኖር፡የምፈርድበት፡ እኔ፡አይደለኹም።
48፤የሚጥለኝ፡ቃሌንም፡የማይቀበለው፡ርሱ፡የሚፈርድበት፡አለው፤እኔ፡የተናገርኹት፡ቃል፡ርሱ፡በመጨረሻው፡ቀ ን፡ይፈርድበታል።
49፤እኔ፡ከራሴ፡አልተናገርኹምና፤ነገር፡ግን፥የላከኝ፡አብ፡ርሱ፡የምለውን፡የምናገረውንም፡ትእዛዝ፡ሰጠኝ።
50፤ትእዛዙም፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡እንደ፡ኾነች፡ዐውቃለኹ።ስለዚህ፡እኔ፡የምናገረውን፡አብ፡እንደ፡ነገረኝ ፡እንዲሁ፡እናገራለኹ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13፤
1፤ኢየሱስም፡ከፋሲካ፡በዓል፡በፊት፥ከዚህ፡ዓለም፡ወደ፡አብ፡የሚኼድበት፡ሰዓት፡እንደ፡ደረሰ፡ዐውቆ፥በዚህ፡ ዓለም፡ያሉትን፡ወገኖቹን፡የወደዳቸውን፡እስከ፡መጨረሻ፡ወደዳቸው።
2፤እራትም፡ሲበሉ፡ዲያብሎስ፡በስምዖን፡ልጅ፡በአስቆሮቱ፡በይሁዳ፡ልብ፡አሳልፎ፡እንዲሰጠው፡ዐሳብ፡ካገባ፡በ ዃላ፥
3፤ኢየሱስ፡አብ፡ዅሉን፡በልጁ፡እንደ፡ሰጠው፡ከእግዚአብሔርም፡እንደ፡ወጣ፡ወደ፡እግዚአብሔርም፡እንዲኼድ፡ዐ ውቆ፥
4፤ከእራት፡ተነሣ፡ልብሱንም፡አኖረ፥ማበሻም፡ጨርቅ፡ወስዶ፡ታጠቀ፤
5፤በዃላም፡በመታጠቢያው፡ውሃ፡ጨመረ፥የደቀ፡መዛሙርቱንም፡እግር፡ሊያጥብና፡በታጠቀበትም፡ማበሻ፡ጨርቅ፡ሊያ ብስ፡ዠመረ።
6፤ወደ፡ስምዖን፡ጴጥሮስም፡መጣ፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡የእኔን፡እግር፡ታጥባለኽን፧አለው።
7፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እኔ፡የማደርገውን፡አንተ፡አኹን፡አታውቅም፥በዃላ፡ግን፡ታስተውለዋለኽ፡አለው።
8፤ጴጥሮስም፦የእኔን፡እግር፡ለዘለዓለም፡አታጥብም፡አለው።ኢየሱስም፦ካላጠብኹኽ፥ከእኔ፡ጋራ፡ዕድል፡የለኽም ፡ብሎ፡መለሰለት።
9፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥እጄንና፡ራሴን፡ደግሞ፡እንጂ፡እግሬን፡ብቻ፡አይደለም፡አለው።
10፤ኢየሱስም፦የታጠበ፡እግሩን፡ከመታጠብ፡በቀር፡ሌላ፡አያስፈልገውም፥ዅለንተናው፡ግን፡ንጹሕ፡ነው፤እናንተ ም፡ንጹሓን፡ናችኹ፥ነገር፡ግን፥ዅላችኹ፡አይደላችኹም፡አለው።
11፤አሳልፎ፡የሚሰጠውን፡ያውቅ፡ነበርና፤ስለዚህ፦ዅላችኹ፡ንጹሓን፡አይደላችኹም፡አለው።
12፤እግራቸውንም፡ዐጥቦ፡ልብሱንም፡አንሥቶ፡ዳግመኛ፡ተቀመጠ፥እንዲህም፡አላቸው፦ያደረግኹላችኹን፡ታስተውላ ላችኹን፧
13፤እናንተ፡መምህርና፡ጌታ፡ትሉኛላችኹ፤እንዲሁ፡ነኝና፡መልካም፡ትላላችኹ።
14፤እንግዲህ፡እኔ፡ጌታና፡መምህር፡ስኾን፡እግራችኹን፡ካጠብኹ፥እናንተ፡ደግሞ፡ርስ፡በርሳችኹ፡እግራችኹን፡ ትተጣጠቡ፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ችዃል።
15፤እኔ፡ለእናንተ፡እንዳደረግኹ፡እናንተ፡ደግሞ፡ታደርጉ፡ዘንድ፡ምሳሌ፡ሰጥቻችዃለኹና።
16፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ባሪያ፡ከጌታው፡አይበልጥም።መልእክተኛም፡ከላከው፡አይበልጥም።
17፤ይህን፡ብታውቁ፥ብታደርጉትም፡ብፁዓን፡ናችኹ።
18፤ስለ፡ዅላችኹ፡አልናገርም፤እኔ፡የመረጥዃቸውን፡ዐውቃለኹ፤ነገር፡ግን፥መጽሐፍ፦እንጀራዬን፡የሚበላ፡በእ ኔ፡ላይ፡ተረከዙን፡አነሣብኝ፡ያለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ነው።
19፤በኾነ፡ጊዜ፡እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታምኑ፡ዘንድ፥ካኹን፡ዠምሬ፡አስቀድሞ፡ሳይኾን፡እነግራችዃለኹ።
20፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ማናቸውን፡የምልከውን፡የሚቀበል፡እኔን፡ይቀበላል፥እኔንም፡የሚቀበል፡የላ ከኝን፡ይቀበላል።
21፤ኢየሱስ፡ይህን፡ብሎ፡በመንፈሱ፡ታወከ፡መስክሮም፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡አንዱ፡አሳልፎ ፡ይሰጠኛል፡አለ።
22፤ደቀ፡መዛሙርቱ፡ስለ፡ማን፡እንደ፡ተናገረ፡አመንትተው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተያዩ።
23፤ኢየሱስም፡ይወደ፟ው፡የነበረ፥ከደቀ፡መዛሙርቱ፡አንዱ፥በኢየሱስ፡ደረት፡ላይ፡ተጠጋ፤
24፤ስለዚህ፥ስምዖን፡ጴጥሮስ፡ርሱን፡ጠቅሶ፦ስለማን፡እንደ፡ተናገረ፡ንገረን፡አለው።
25፤ርሱም፥በኢየሱስ፡ደረት፡እንዲህ፡ተጠግቶ፦ጌታ፡ሆይ፥ማን፡ነው፧አለው።
26፤ኢየሱስም፦እኔ፡ቍራሽ፡አጥቅሼ፡የምሰጠው፡ርሱ፡ነው፡ብሎ፡መለሰለት።ቍራሽም፡አጥቅሶ፡ለአስቆሮቱ፣ለስም ዖን፡ልጅ፣ለይሁዳ፡ሰጠው።
27፤ቍራሽም፡ከተቀበለ፡በዃላ፥ያን፡ጊዜ፡ሰይጣን፡ገባበት።እንግዲህ፡ኢየሱስ፦የምታደርገውን፡ቶሎ፡ብለኽ፡አ ድርግ፡አለው።
28፤ነገር፡ግን፥ከተቀመጡት፡ስለ፡ምን፡ይህን፡እንዳለው፡ማንም፡አላወቀም፤
29፤ይሁዳ፡ከረጢቱን፡የያዘ፡ስለ፡ኾነ፥ኢየሱስ፦ለበዓሉ፡የሚያስፈልገንን፡ግዛ፥ወይም፡ለድኻዎች፡ምጽዋት፡እ ንዲሰጥ፡ያለው፡ለአንዳንዱ፡መስሏቸው፡ነበርና።
30፤ርሱም፡ቍራሹን፡ከተቀበለ፡በዃላ፡ወዲያው፡ወጣ፤ሌሊትም፡ነበረ።
31፤ከወጣም፡በዃላ፡ኢየሱስ፡እንዲህ፡አለ፦አኹን፡የሰው፡ልጅ፡ከበረ፡እግዚአብሔርም፡ሰለ፡ርሱ፡ከበረ፤
32፤እግዚአብሔር፡ስለ፡ርሱ፡የከበረ፡ከኾነ፥እግዚአብሔር፡ደግሞ፡ርሱን፡ራሱን፡ያከብረዋል፡ወዲያውም፡ያከብ ረዋል።
33፤ልጆች፡ሆይ፥ገና፡ጥቂት፡ጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነኝ፤ትፈልጉኛላችኹ፤ለአይሁድም፦እኔ፡ወደምኼድበት፡እናን ተ፡ልትመጡ፡አይቻላችኹም፡እንዳልዃቸው፥አኹን፡ለእናንተ፡ደግሞ፡እላችዃለኹ፦
34፤ርስ፡በርሳችኹ፡ትዋደዱ፡ዘንድ፥እንደ፡ወደድዃችኹ፡እናንተ፡ደግሞ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ትዋደዱ፡ዘንድ፡ዐዲስ ፡ትእዛዝ፡እሰጣችዃለኹ።
35፤ርስ፡በርሳችኹ፡ፍቅር፡ቢኖራችኹ፥ደቀ፡መዛሙርቴ፡እንደ፡ኾናችኹ፡ሰዎች፡ዅሉ፡በዚህ፡ያውቃሉ።
36፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥ወዴት፡ትኼዳለኽ፧አለው።ኢየሱስም፦ወደምኼድበት፡አኹን፡ልትከተለኝ፡አትች ልም፥ነገር፡ግን፥በዃላ፡ትከተለኛለኽ፡ብሎ፡መለሰለት።
37፤ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥አኹን፡ልከተልኽ፡አለመቻሌ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧ነፍሴን፡ስንኳ፡ስለ፡አንተ፡እሰጣለ ኹ፡አለው።
38፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰለት፦ነፍስኽን፡ስለ፡እኔ፡ትሰጣለኽን፧እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥ሦስት፡ ጊዜ፡እስክትክደኝ፡ድረስ፡ዶሮ፡አይጮኽም።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14፤
1፤ልባችኹ፡አይታወክ፤በእግዚአብሔር፡እመኑ፥በእኔም፡ደግሞ፡እመኑ።
2፤በአባቴ፡ቤት፡ብዙ፡መኖሪያ፡አለ፤እንዲህስ፡ባይኾን፡ባልዃችኹ፡ነበር፤ስፍራ፡አዘጋጅላችኹ፡ዘንድ፡እኼዳለ ኹና፤
3፤ኼጄም፡ስፍራ፡ባዘጋጅላችኹ፥እኔ፡ባለኹበት፡እናንተ፡ደግሞ፡እንድትኾኑ፡ኹለተኛ፡እመጣለኹ፡ወደ፡እኔም፡እ ወስዳችዃለኹ።
4፤ወደምኼድበትም፡ታውቃላችኹ፥መንገዱንም፡ታውቃላችኹ።
5፤ቶማስም፦ጌታ፡ሆይ፥ወደምትኼድበት፡አናውቅም፤እንዴትስ፡መንገዱን፡እናውቃለን፧አለው።
6፤ኢየሱስም፦እኔ፡መንገድና፡እውነት፡ሕይወትም፡ነኝ፤በእኔ፡በቀር፡ወደ፡አብ፡የሚመጣ፡የለም።
7፤እኔንስ፡ብታውቁኝ፡አባቴን፡ደግሞ፡ባወቃችኹ፡ነበር።ካኹንም፡ዠምራችኹ፡ታውቁታላችኹ፡አይታችኹትማል፡አለ ው።
8፤ፊልጶስ፦ጌታ፡ሆይ፥አብን፡አሳየንና፡ይበቃናል፡አለው።
9፤ኢየሱስም፡አለው፦አንተ፡ፊልጶስ፥ይህን፡ያኽል፡ዘመን፡ከእናንተ፡ጋራ፡ስኖር፡አታውቀኝምን፧እኔን፡ያየ፡አ ብን፡አይቷል፤እንዴትስ፡አንተ፦አብን፡አሳየን፡ትላለኽ፧
10፤እኔ፡በአብ፡እንዳለኹ፡አብም፡በእኔ፡እንዳለ፡አታምንምን፧እኔ፡የምነግራችኹን፡ቃል፡ከራሴ፡አልናገረውም ፤ነገር፡ግን፥በእኔ፡የሚኖረው፡አብ፡ርሱ፡ሥራውን፡ይሠራል።
11፤እኔ፡በአብ፡እንዳለኹ፡አብም፡በእኔ፡እንዳለ፡እመኑኝ፤ባይኾንስ፡ስለ፡ራሱ፡ስለ፡ሥራው፡እመኑኝ።
12፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥በእኔ፡የሚያምን፡እኔ፡የማደርገውን፡ሥራ፡ርሱ፡ደግሞ፡ያደርጋል፤ከዚህም፡ የሚበልጥ፡ያደርጋል፥
13፤እኔ፡ወደ፡አብ፡እኼዳለኹና፤አብም፡ስለ፡ወልድ፡እንዲከበር፡በስሜ፡የምትለምኑትን፡ዅሉ፡አደርገዋለኹ።
14፤ማናቸውንም፡ነገር፡በስሜ፡ብትለምኑ፡እኔ፡አደርገዋለኹ።
15-16፤ብትወዱኝ፡ትእዛዜን፡ጠብቁ።እኔም፡አብን፡እለምናለኹ፡ለዘለዓለምም፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንዲኖር፡ሌላ፡አ ጽናኝ፡ይሰጣችዃል፤
17፤ርሱም፡ዓለም፡የማያየውና፡የማያውቀው፡ስለ፡ኾነ፡ሊቀበለው፡የማይቻለው፡የእውነት፡መንፈስ፡ነው፤ነገር፡ ግን፥ከእናንተ፡ዘንድ፡ስለሚኖር፡በውስጣችኹም፡ስለሚኾን፡እናንተ፡ታውቃላችኹ።
18፤ወላጆች፡እንደ፡ሌላቸው፡ልጆች፡አልተዋችኹም፤ወደ፡እናንተ፡እመጣለኹ።
19፤ገና፡ጥቂት፡ዘመን፡አለ፡ከዚህም፡በዃላ፡ዓለም፡አያየኝም፤እናንተ፡ግን፡ታዩኛላችኹ፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ እናንተ፡ደግሞ፡ሕያዋን፡ትኾናላችኹ።
20፤እኔ፡በአባቴ፡እንዳለኹ፡እናንተም፡በእኔ፡እንዳላችኹ፡እኔም፡በእናንተ፡እንዳለኹ፡በዚያን፡ቀን፡ታውቃላ ችኹ።
21፤ትእዛዜ፡በርሱ፡ዘንድ፡ያለችው፡የሚጠብቃትም፡የሚወደኝ፡ርሱ፡ነው፤የሚወደኝንም፡አባቴ፡ይወደዋል፡እኔም ፡እወደዋለኹ፡ራሴንም፡እገልጥለታለኹ።
22፤የአስቆሮቱ፡ያይደለ፡ይሁዳ፦ጌታ፡ሆይ፥ለዓለም፡ሳይኾን፡ራስኽን፡ለእኛ፡ልትገልጥ፡ያለኽ፡እንዴት፡ነው፧ አለው።
23፤ኢየሱስም፡መለሰ፥አለውም፦የሚወደኝ፡ቢኖር፡ቃሌን፡ይጠብቃል፤አባቴም፡ይወደዋል፡ወደ፡ርሱም፡እንመጣለን ፡በርሱም፡ዘንድ፡መኖሪያ፡እናደርጋለን።
24፤የማይወደኝ፡ቃሌን፡አይጠብቅም፤የምትሰሙትም፡ቃል፡የላከኝ፡የአብ፡ነው፡እንጂ፡የእኔ፡አይደለም።
25፤ከእናንተ፡ዘንድ፡ስኖር፡ይህን፡ነግሬያችዃለኹ፤
26፤አብ፡በስሜ፡የሚልከው፡ግን፡መንፈስ፡ቅዱስ፡የኾነው፡አጽናኝ፡ርሱ፡ዅሉን፡ያስተምራችዃል፥እኔም፡የነገር ዃችኹን፡ዅሉ፡ያሳስባችዃል።
27፤ሰላምን፡እተውላችዃለኹ፥ሰላሜን፡እሰጣችዃለኹ፤እኔ፡የምሰጣችኹ፡ዓለም፡እንደሚሰጥ፡አይደለም።ልባችኹ፡ አይታወክ፡አይፍራም።
28፤እኔ፡እኼዳለኹ፡ወደ፡እናንተም፡እመጣለኹ፡እንዳልዃችኹ፡ሰማችኹ።የምትወዱኝስ፡ብትኾኑ፡ከእኔ፡አብ፡ይበ ልጣልና፥ወደ፡አብ፡በመኼዴ፡ደስ፡ባላችኹ፡ነበር።
29፤ከኾነም፡በዃላ፡ታምኑ፡ዘንድ፡አኹን፡አስቀድሞ፡ሳይኾን፡ነግሬያችዃለኹ።
30፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ብዙ፡አልናገርም፥የዚህ፡ዓለም፡ገዢ፡ይመጣልና፤በእኔ፡ላይም፡አንዳች ፡የለውም፤
31፤ነገር፡ግን፥አብን፡እንድወድ፡ዓለም፡ሊያውቅ፥አብም፡እንዳዘዘኝ፥እንዲሁ፡አደርጋለኹ።ተነሡ፤ከዚህ፡እን ኺድ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15፤
1፤እውነተኛ፡የወይን፡ግንድ፡እኔ፡ነኝ፤ገበሬውም፡አባቴ፡ነው።
2፤ፍሬ፡የማያፈራውን፡በእኔ፡ያለውን፡ቅርንጫፍ፡ዅሉ፡ያስወግደዋል፤ፍሬ፡የሚያፈራውንም፡ዅሉ፡አብዝቶ፡እንዲ ያፈራ፡ያጠራዋል።
3፤እናንተ፡ስለነገርዃችኹ፡ቃል፡አኹን፡ንጹሓን፡ናችኹ፤
4፤በእኔ፡ኑሩ፡እኔም፡በእናንተ።ቅርንጫፍ፡በወይኑ፡ግንድ፡ባይኖር፡ከራሱ፡ፍሬ፡ሊያፈራ፡እንዳይቻለው፥እንዲ ሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡በእኔ፡ባትኖሩ፡አትችሉም።
5፤እኔ፡የወይን፡ግንድ፡ነኝ፡እናንተም፡ቅርንጫፎች፡ናችኹ።ያለእኔ፡ምንም፡ልታደርጉ፡አትችሉምና፡በእኔ፡የሚ ኖር፡እኔም፡በርሱ፥ርሱ፡ብዙ፡ፍሬ፡ያፈራል።
6፤በእኔ፡የማይኖር፡ቢኾን፡እንደ፡ቅርንጫፍ፡ወደ፡ውጭ፡ይጣላል፡ይደርቅማል፤እነርሱንም፡ሰብስበው፡ወደ፡እሳ ት፡ይጥሏቸዋል፥ያቃጥሏቸውማል።
7፤በእኔ፡ብትኖሩ፡ቃሎቼም፡በእናንተ፡ቢኖሩ፡የምትወዱትን፡ዅሉ፡ለምኑ፡ይኾንላችኹማል።
8፤ብዙ፡ፍሬ፡ብታፈሩና፡ደቀ፡መዛሙርቴ፡ብትኾኑ፡በዚህ፡አባቴ፡ይከበራል።
9፤አብ፡እንደ፡ወደደኝ፡እኔ፡ደግሞ፡ወደድዃችኹ፤በፍቅሬ፡ኑሩ።
10፤እኔ፡የአባቴን፡ትእዛዝ፡እንደ፡ጠበቅኹ፡በፍቅሩም፡እንደምኖር፥ትእዛዜን፡ብትጠብቁ፡በፍቅሬ፡ትኖራላችኹ ።
11፤ደስታዬም፡በእናንተ፡እንዲኾን፡ደስታችኹም፡እንዲፈጸም፡ይህን፡ነግሬያችዃለኹ።
12፤እኔ፡እንደ፡ወደድዃችኹ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ትዋደዱ፡ዘንድ፡ትእዛዜ፡ይህች፡ናት።
13፤ነፍሱን፡ስለ፡ወዳጆቹ፡ከመስጠት፡ይልቅ፡ከዚህ፡የሚበልጥ፡ፍቅር፡ለማንም፡የለውም።
14፤እኔ፡ያዘዝዃችኹን፡ዅሉ፡ብታደርጉ፡እናንተ፡ወዳጆቼ፡ናችኹ።
15፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ባሪያዎች፡አልላችኹም፤ባሪያ፡ጌታው፡የሚያደርገውን፡አያውቅምና፤ወዳጆች፡ግን፡ብያች ዃለኹ፥ከአባቴ፡የሰማኹትን፡ዅሉ፡ለእናንተ፡አስታውቄያችዃለኹና።
16፤እኔ፡መረጥዃችኹ፡እንጂ፡እናንተ፡አልመረጣችኹኝም፤አብም፡በስሜ፡የምትለምኑትን፡ዅሉ፡እንዲሰጣችኹ፥ልት ኼዱና፡ፍሬ፡ልታፈሩ፡ፍሬያችኹም፡ሊኖር፡ሾምዃችኹ።
17፤ርስ፡በርሳችኹ፡እንድትዋደዱ፡ይህን፡አዛችዃለኹ።
18፤ዓለም፡ቢጠላችኹ፡ከእናንተ፡በፊት፡እኔን፡እንደ፡ጠላኝ፡ዕወቁ።
19፤ከዓለምስ፡ብትኾኑ፡ዓለም፡የራሱ፡የኾነውን፡ይወድ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥እኔ፡ከዓለም፡መረጥዃችኹ፡እንጂ፡ ከዓለም፡ስላይደላችኹ፡ስለዚህ፡ዓለም፡ይጠላችዃል።
20፤ባሪያ፡ከጌታው፡አይበልጥም፡ብዬ፡የነገርዃችኹን፡ቃል፡ዐስቡ።እኔን፡አሳደውኝ፡እንደ፡ኾኑ፡እናንተን፡ደ ግሞ፡ያሳድዷችዃል፤ቃሌን፡ጠብቀው፡እንደ፡ኾኑ፡ቃላችኹን፡ደግሞ፡ይጠብቃሉ።
21፤ዳሩ፡ግን፡የላከኝን፡አያውቁምና፡ይህን፡ዅሉ፡ሰለ፡ስሜ፡ያደርጉባችዃል።
22፤እኔ፡መጥቼ፡ባልነገርዃቸውስ፡ኀጢአት፡ባልኾነባቸውም፡ነበር፤አኹን፡ግን፡ለኀጢአታቸው፡ምክንያት፡የላቸ ውም።
23፤እኔን፡የሚጠላ፡አባቴን፡ደግሞ፡ይጠላል።
24፤ሌላ፡ሰው፡ያላደረገውን፡ሥራ፡በመካከላቸው፡ባላደረግኹ፥ኀጢአት፡ባልኾነባቸውም፡ነበር፤አኹን፡ግን፡እኔ ንም፡አባቴንም፡አይተውማል፡ጠልተውማል።
25፤ነገር፡ግን፥በሕጋቸው።በከንቱ፡ጠሉኝ፡ተብሎ፡የተጻፈው፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ነው።
26፤ዳሩ፡ግን፡እኔ፡ከአብ፡ዘንድ፡የምልክላችኹ፡አጽናኝ፡ርሱም፡ከአብ፡የሚወጣ፡የእውነት፡መንፈስ፡በመጣ፡ጊ ዜ፥ርሱ፡ስለ፡እኔ፡ይመሰክራል፤
27፤እናንተም፡ደግሞ፡ከመዠመሪያ፡ከእኔ፡ጋራ፡ኖራችዃልና፥ትመሰክራላችኹ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16፤
1፤እንዳትሰናከሉ፡ይህን፡ተናግሬያችዃለኹ።
2፤ከምኵራባቸው፡ያወጧችዃል፤ከዚህ፡በላይ፡ደግሞ፡የሚገድላችኹ፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡እንደሚያገለግል፡የሚመ ስልበት፡ጊዜ፡ይመጣል።
3፤ይህንም፡የሚያደርጉባችኹ፡አብንና፡እኔን፡ስላላወቁ፡ነው።
4፤ነገር፡ግን፥ጊዜው፡ሲደርስ፡እኔ፡እንደ፡ነገርዃችኹ፡ታስቡ፡ዘንድ፡ይህን፡ተናግሬያችዃለኹ።ከእንናንተም፡ ጋራ፡ስለ፡ነበርኹ፡በመዠመሪያ፡ይህን፡አልነገርዃችኹም።
5፤አኹን፡ግን፡ወደላከኝ፡እኼዳለኹ፡ከእናንተም፦ወዴት፡ትኼዳለኽ፧ብሎ፡የሚጠይቀኝ፡የለም።
6፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ስለ፡ተናገርዃችኹ፡ሐዘን፡በልባችኹ፡ሞልቷል።
7፤እኔ፡ግን፡እውነት፡እነግራችዃለኹ፤እኔ፡እንድኼድ፡ይሻላችዃል።እኔ፡ባልኼድ፡አጽናኙ፡ወደ፡እናንተ፡አይመ ጣምና፤እኔ፡ብኼድ፡ግን፡ርሱን፡እልክላችዃለኹ።
8፤ርሱም፡መጥቶ፡ስለ፡ኀጢአት፡ስለ፡ጽድቅም፡ስለ፡ፍርድም፡ዓለምን፡ይወቅሳል፤
9-10፤ስለ፡ኀጢአት፥በእኔ፡ስለማያምኑ፡ነው፤ስለ፡ጽድቅም፥ወደ፡አብ፡ስለምኼድ፡ከዚህም፡በዃላ፡ስለማታዩኝ፡ ነው፤
11፤ስለ፡ፍርድም፥የዚህ፡ዓለም፡ገዢ፡ስለ፡ተፈረደበት፡ነው።
12፤የምነግራችኹ፡ገና፡ብዙ፡አለኝ፥ነገር፡ግን፥አኹን፡ልትሸከሙት፡አትችሉም።
13፤ግን፡ርሱ፡የእውነት፡መንፈስ፡በመጣ፡ጊዜ፡ወደ፡እውነት፡ዅሉ፡ይመራችዃል፤የሚሰማውን፡ዅሉ፡ይናገራል፡እ ንጂ፡ከራሱ፡አይነግርምና፤የሚመጣውንም፡ይነግራችዃል።
14፤ርሱ፡ያከብረኛል፥ለእኔ፡ካለኝ፡ወስዶ፡ይነግራችዃልና።
15፤ለአብ፡ያለው፡ዅሉ፡የእኔ፡ነው፤ስለዚህ፦ለእኔ፡ካለኝ፡ወስዶ፡ይነግራችዃል፡አልኹ።
16፤ጥቂት፡ጊዜ፡አለ፥አታዩኝምም፤ደግሞም፡ጥቂት፡ጊዜ፡አለ፥ታዩኛላችኹም፥እኔ፡ወደ፡አብ፡እኼዳለኹና።
17፤ከደቀ፡መዛሙርቱም፡አንዳንዶቹ፡ርስ፡በርሳቸው፦ጥቂት፡ጊዜ፡አለ፥አታዩኝምም፤ደግሞም፡ጥቂት፡ጊዜ፡አለ፥ ታዩኛላችኹም፤ደግሞ፦ወደ፡አብ፡እኼዳለኹና፡የሚለን፡ይህ፡ምንድር፡ነው፧ተባባሉ።
18፤እንግዲህ፦ጥቂት፡የሚለው፡ይህ፡ምንድር፡ነው፧የሚናገረውን፡አናውቅም፡አሉ።
19፤ኢየሱስም፡ሊጠይቁት፡እንደ፡ወደዱ፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦ጥቂት፡ጊዜ፡አለ፥አታዩኝምም፤ደግሞም፡ጥቂት ፡ጊዜ፡አለ፥ታዩኛላችኹ፡ስላልኹ፥ስለዚህ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ትመራመራላችኹን፧
20፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥እናንተ፡ታለቅሳላችኹ፡ሙሾም፡ታወጣላችኹ፥ዓለም፡ግን፡ደስ፡ይለዋል፤እናን ተም፡ታዝናላችኹ፥ነገር፡ግን፥ሐዘናችኹ፡ወደ፡ደስታ፡ይለወጣል።
21፤ሴት፡በምትወልድበት፡ጊዜ፡ወራቷ፡ስለ፡ደረሰ፡ታዝናለች፤ነገር፡ግን፥ሕፃን፡ከወለደች፡በዃላ፥ሰው፡በዓለ ም፡ተወልዷልና፥ስለ፡ደስታዋ፡መከራዋን፡ዃላ፡አታስበውም።
22፤እንግዲህ፡እናንተ፡ደግሞ፡አኹን፡ታዝናላችኹ፤ነገር፡ግን፥እንደ፡ገና፡አያችዃለኹ፡ልባችኹም፡ደስ፡ይለዋ ል፥ደስታችኹንም፡የሚወስድባችኹ፡የለም።
23፤በዚያን፡ቀንም፡ከእኔ፡አንዳች፡አትለምኑም።እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥አብ፡በስሜ፡የምትለምኑትን፡ዅ ሉ፡ይሰጣችዃል።
24፤እስከ፡አኹን፡በስሜ፡ምንም፡አልለመናችኹም፤ደስታችኹ፡ፍጹም፡እንዲኾን፡ለምኑ፡ትቀበሉማላችኹ።
25፤ይህን፡በምሳሌ፡ነግሬያችዃለኹ፤ነገር፡ግን፥ስለ፡አብ፡ለእናንተ፡በግልጥ፡የምናገርበት፡እንጂ፡ከዚያ፡ወ ዲያ፡በምሳሌ፡የማልናገርበት፡ሰዓት፡ይመጣል።
26፤በዚያን፡ቀን፡በስሜ፡ትለምናላችኹ፤እኔም፡ስለ፡እናንተ፡አብን፡እንድለምን፡የምላችኹ፡አይደለኹም፤
27፤እናንተ፡ስለ፡ወደዳችኹኝ፡ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡እኔ፡እንደ፡ወጣኹ፡ስላመናችኹ፡አብ፡ርሱ፡ራሱ፡ይወዳ ችዃልና።
28፤ከአብ፡ወጥቼ፡ወደ፡ዓለም፡መጥቻለኹ፤ደግሞ፡ዓለምን፡እተወዋለኹ፡ወደ፡አብም፡እኼዳለኹ።
29፤ደቀ፡መዛሙርቱ፦እንሆ፥አኹን፡በግልጥ፡ትናገራለኽ፡በምሳሌም፡ምንም፡አትነግርም።
30፤ዅሉን፡እንድታውቅ፥ማንምም፡ሊጠይቅኽ፡እንዳትፈልግ፡አኹን፡እናውቃለን፤ስለዚህ፥ከእግዚአብሔር፡እንደ፡ ወጣኽ፡እናምናለን፡አሉት።
31፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰላቸው።አኹን፡ታምናላችኹን፧
32፤እንሆ፥እያንዳንዳችኹ፡ወደ፡ቤት፡የምትበታተኑበት፡እኔንም፡ለብቻዬ፡የምትተዉበት፡ሰዓት፡ይመጣል፥አኹን ም፡ደርሷል፤ነገር፡ግን፥አብ፡ከእኔ፡ጋራ፡ስለ፡ኾነ፡ብቻዬን፡አይደለኹም።
33፤በእኔ፡ሳላችኹ፡ሰላም፡እንዲኾንላችኹ፡ይህን፡ተናግሬያችዃለኹ።በዓለም፡ሳላችኹ፡መከራ፡አለባችኹ፤ነገር ፡ግን፥አይዟችኹ፤እኔ፡ዓለምን፡አሸንፌዋለኹ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17፤
1-2፤ኢየሱስም፡ይህን፡ተናግሮ፡ወደ፡ሰማይ፡ዐይኖቹን፡አነሣና፡እንዲህ፡አለ፦አባት፡ሆይ፥ሰዓቱ፡ደርሷል፤ልጅ ኽ፡ያከብርኽ፡ዘንድ፥በሥጋም፡ዅሉ፡ላይ፡ሥልጣን፡እንደ፡ሰጠኸው፥ለሰጠኸው፡ዅሉ፡የዘለዓለምን፡ሕይወት፡ይሰ ጣቸው፡ዘንድ፡ልጅኽን፡አክብረው።
3፤እውነተኛ፡አምላክ፡ብቻ፡የኾንኽ፡አንተን፡የላክኸውንም፡ኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ያውቁ፡ዘንድ፡ይህች፡የዘለዓ ለም፡ሕይወት፡ናት።
4፤እኔ፡ላደርገው፡የሰጠኸኝን፡ሥራ፡ፈጽሜ፡በምድር፡አከበርኹኽ፤
5፤አኹንም፥አባት፡ሆይ፥ዓለም፡ሳይፈጠር፡ባንተ፡ዘንድ፡በነበረኝ፡ክብር፡አንተ፡በራስኽ፡ዘንድ፡አክብረኝ።
6፤ከዓለም፡ለሰጠኸኝ፡ሰዎች፡ስምኽን፡ገለጥኹላቸው።የአንተ፡ነበሩ፡ለኔም፡ሰጠኻቸው፤
7፤ቃልኽንም፡ጠብቀዋል።የሰጠኸኝ፡ዅሉ፡ከአንተ፡እንደ፡ኾነ፡አኹን፡ያውቃሉ፤
8፤የሰጠኸኝን፡ቃል፡ሰጥቻቸዋለኹና፤እነርሱም፡ተቀበሉት፥ከአንተም፡ዘንድ፡እንደ፡ወጣኹ፡በእውነት፡ዐወቁ፥አ ንተም፡እንደ፡ላክኸኝ፡አመኑ።
9፤እኔ፡ስለ፡እነዚህ፡እለምናለኹ፤ስለ፡ዓለም፡አልለምንም፡ስለሰጠኸኝ፡እንጂ፤የአንተ፡ናቸውና፤
10፤የእኔም፡የኾነ፡ዅሉ፡የአንተ፡ነው፡የአንተውም፡የእኔ፡ነው፤እኔም፡ስለ፡እነርሱ፡ከብሬያለኹ።
11፤ከዚህም፡በዃላ፡በዓለም፡አይደለኹም፥እነርሱም፡በዓለም፡ናቸው፥እኔም፡ወዳንተ፡እመጣለኹ።ቅዱስ፡አባት፡ ሆይ፥እነዚህን፡የሰጠኸኝን፡እንደ፡እኛ፡አንድ፡እንዲኾኑ፡በስምኽ፡ጠብቃቸው።
12፤ከነርሱ፡ጋራ፡በዓለም፡ሳለኹ፡የሰጠኸኝን፡በስምኽ፡እኔ፡እጠብቃቸው፡ነበር፤ጠበቅዃቸውም፡መጽሐፉም፡እን ዲፈጸም፡ከጥፋት፡ልጅ፡በቀር፡ከነርሱ፡ማንም፡አልጠፋም።
13፤አኹንም፡ወዳንተ፡እመጣለኹ፤በእነርሱም፡ዘንድ፡ደስታዬ፡የተፈጸመ፡እንዲኾንላቸው፡ይህን፡በዓለም፡እናገ ራለኹ።
14፤እኔ፡ቃልኽን፡ሰጥቻቸዋለኹ፤እኔም፡ከዓለም፡እንዳይደለኹ፡ከዓለም፡አይደሉምና፡ዓለም፡ጠላቸው።
15፤ከክፉ፡እንድትጠብቃቸው፡እንጂ፡ከዓለም፡እንድታወጣቸው፡አልለምንም።
16፤እኔ፡ከዓለም፡እንዳይደለኹ፡ከዓለም፡አይደሉም።
17፤በእውነትኽ፡ቀድሳቸው፤ቃልኽ፡እውነት፡ነው።
18፤ወደ፡ዓለም፡እንደ፡ላክኸኝ፡እንዲሁ፡እኔ፡ወደ፡ዓለም፡ላክዃቸው፤
19፤እነርሱም፡ደግሞ፡በእውነት፡የተቀደሱ፡እንዲኾኑ፡እኔ፡ራሴን፡ስለ፡እነርሱ፡እቀድሳለኹ።
20-21፤ዅሉም፡አንድ፡ይኾኑ፡ዘንድ፥ከቃላቸው፡የተነሣ፡በእኔ፡ስለሚያምኑ፡ደግሞ፡እንጂ፡ስለ፡እነዚህ፡ብቻ፡አ ልለምንም፤አንተ፡እንደ፡ላክኸኝ፡ዓለም፡ያምን፡ዘንድ፥አንተ፥አባት፡ሆይ፥በእኔ፡እንዳለኽ፡እኔም፡ባንተ፥እ ነርሱ፡ደግሞ፡በእኛ፡አንድ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡እለምናለኹ።
22-23፤እኛም፡አንድ፡እንደ፡ኾን፟፡አንድ፡ይኾኑ፡ዘንድ፤እኔም፡በእነርሱ፡አንተም፡በእኔ፡ስትኾን፥ባንድ፡ፍጹ ማን፡እንዲኾኑ፥የሰጠኸኝን፡ክብር፡እኔ፡ሰጥቻቸዋለኹ፤እንዲሁም፡ዓለም፡አንተ፡እንደ፡ላክኸኝ፡በወደድኸኝም ፡መጠን፡እነርሱን፡እንደ፡ወደድኻቸው፡ያውቃል።
24፤አባት፡ሆይ፥ዓለም፡ሳይፈጠር፡ስለ፡ወደድኸኝ፡የሰጠኸኝን፡ክብሬን፡እንዲያዩ፡እኔ፡ባለኹበት፡የሰጠኸኝ፡ እነርሱ፡ደግሞ፡ከእኔ፡ጋራ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡እወዳለኹ።
25፤ጻድቅ፡አባት፡ሆይ፥ዓለም፡አላወቀኽም፥እኔ፡ግን፡ዐወቅኹኽ፡እነዚህም፡አንተ፡እንደ፡ላክኸኝ፡ዐወቁ፤
26፤እኔንም፡የወደድኽባት፡ፍቅር፡በእነርሱ፡እንድትኾን፡እኔም፡በእነርሱ፥ስምኽን፡አስታወቅዃቸው፡አስታውቃ ቸውማለኹ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18፤
1፤ኢየሱስም፡ይህን፡ብሎ፡አትክልት፡ወዳለበት፡ስፍራ፡ወደቄድሮን፡ወንዝ፡ማዶ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወጣ፤ር ሱም፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡በዚያ፡ገቡ።
2፤ኢየሱስም፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡ብዙ፡ጊዜ፡ወደዚያ፡ስለ፡ተሰበሰቡ፡አሳልፎ፡የሰጠው፡ይሁዳ፡ደግሞ፡ስፍራውን፡ ያውቅ፡ነበር።
3፤ስለዚህ፥ይሁዳ፡ጭፍራዎችንና፥ከካህናት፡አለቃዎች፣ከፈሪሳውያንም፡ሎሌዎችን፡ተቀብሎ፥በችቦና፡በፋና፣በጋ ሻ፡ጦርም፡ወደዚያ፡መጣ።
4፤ኢየሱስም፥የሚመጣበትን፡ዅሉ፡ዐውቆ፡ወጣና፦ማንን፡ትፈልጋላችኹ፡አላቸው።
5፤የናዝሬቱን፡ኢየሱስን፡ብለው፡መለሱለት።ኢየሱስ፦እኔ፡ነኝ፡አላቸው።አሳልፎ፡የሰጠውም፡ይሁዳ፡ደግሞ፡ከነ ርሱ፡ጋራ፡ቆሞ፡ነበር።
6፤እንግዲህ፦እኔ፡ነኝ፡ባላቸው፡ጊዜ፥ወደ፡ዃላ፡አፈግፍገው፡በምድር፡ወደቁ።
7፤ደግሞም፦ማንን፡ትፈልጋላችኹ፧ብሎ፡ጠየቃቸው።እነርሱም፦የናዝሬቱን፡ኢየሱስን፡አሉት።
8፤ኢየሱስ፡መልሶ፦እኔ፡ነኝ፡አልዃችኹ፤እንግዲህ፡እኔን፡ትፈልጉ፡እንደ፡ኾናችኹ፡እነዚህ፡ይኺዱ፡ተዉአቸው፡ አለ፤
9፤ይህም፦ከነዚህ፡ከሰጠኸኝ፡አንዱን፡ስንኳ፡አላጠፋኹም፡ያለው፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ነው።
10፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፡ሰይፍ፡ስለ፡ነበረው፡መዘዘው፥የሊቀ፡ካህናቱንም፡ባሪያ፡መቶ፟፡ቀኝ፡ዦሮውን፡ቈረጠ፤ የባሪያውም፡ስም፡ማልኮስ፡ነበረ።
11፤ኢየሱስም፡ጴጥሮስን፦ሰይፍኽን፡ወደ፡ሰገባው፡ክተተው፤አብ፡የሰጠኝን፡ጽዋ፡አልጠጣትምን፧አለው።
12፤እንግዲህ፡የሻለቃውና፡ጭፍራዎቹ፡የአይሁድም፡ሎሌዎች፡ኢየሱስን፡ይዘው፡አሰሩት፥
13፤አስቀድመውም፡ወደ፡ሐና፡ወሰዱት፤በዚያች፡ዓመት፡ሊቀ፡ካህናት፡ለነበረው፡ለቀያፋ፡ዐማቱ፡ነበርና።
14፤ቀያፋም፦አንድ፡ሰው፡ስለ፡ሕዝብ፡ይሞት፡ዘንድ፡ይሻላል፡ብሎ፡ለአይሁድ፡የመከራቸው፡ነበረ።
15፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፡ሌላውም፡ደቀ፡መዝሙር፡ኢየሱስን፡ተከተሉ።ያም፡ደቀ፡መዝሙር፡በሊቀ፡ካህናቱ፡ዘንድ፡ የታወቀ፡ነበረ፥ወደሊቀ፡ካህናቱም፡ግቢ፡ከኢየሱስ፡ጋራ፡ገባ፤
16፤ጴጥሮስ፡ግን፡በውጭ፡በበሩ፡ቆሞ፡ነበር።እንግዲህ፡በሊቀ፡ካህናቱ፡ዘንድ፡የታወቀው፡ሌላው፡ደቀ፡መዝሙር ፡ወጣ፥ለበረኛዪቱም፡ነግሮ፡ጴጥሮስን፡አስገባው።
17፤በረኛ፡የነበረችዪቱም፡ገረድ፡ጴጥሮስን፦አንተ፡ደግሞ፡ከዚህ፡ሰው፡ደቀ፡መዛሙርት፡አንዱ፡አይደለኽምን፧ አለችው።ርሱ፦አይደለኹም፡አለ።
18፤ብርድ፡ነበረና፡ባሪያዎችና፡ሎሌዎች፡የፍም፡እሳት፡አንድደው፡ቆሙ፡ይሞቁም፡ነበር፤ጴጥሮስም፡ደግሞ፡ከነ ርሱ፡ጋራ፡ቆሞ፡ይሞቅ፡ነበር።
19፤ሊቀ፡ካህናቱም፡ኢየሱስን፡ስለ፡ደቀ፡መዛሙርቱና፡ስለ፡ትምህርቱ፡ጠየቀው።
20፤ኢየስስም፡መልሶ፦እኔ፡በግልጥ፡ለዓለም፡ተናገርኹ፤አይሁድ፡ዅሉ፡በሚሰበሰቡበት፡በምኵራብና፡በመቅደስ፡ እኔ፡ዅልጊዜ፡አስተማርኹ፥በስውርም፡ምንም፡አልተናገርኹም።
21፤ስለምን፡ትጠይቀኛለኽ፧ለእነርሱ፡የተናገርኹትን፡የሰሙትን፡ጠይቅ፤እንሆ፥እነዚህ፡እኔ፡የነገርኹትን፡ያ ውቃሉ፡አለው።
22፤ይህንም፡ሲል፡በዚያ፡ቆሞ፡የነበረው፡ከሎሌዎች፡አንዱ፦ለሊቀ፡ካህናቱ፡እንዲህ፡ትመልሳለኽን፧ብሎ፡ኢየሱ ስን፡በጥፊ፡መታው።
23፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ክፉ፡ተናግሬ፡እንደ፡ኾንኹ፡ስለ፡ክፉ፡መስክር፤መልካም፡ተናግሬ፡እንደ፡ኾንኹ፡ግን፡ሰ ለ፡ምን፡ትመታኛለኽ፧አለው።
24፤ስለዚህ፥ሐና፥እንደ፡ታሰረ፥ወደ፡ሊቀ፡ካህናቱ፣ወደ፡ቀያፋ፡ሰደደው።
25፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፡ቆሞ፡እሳት፡ይሞቅ፡ነበር።እንግዲህ፦አንተ፡ደግሞ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡አይደለኽምን፧አ ሉት።ርሱም፦አይደለኹም፡ብሎ፡ካደ።
26፤ጴጥሮስ፡ዦሮውን፡የቈረጠው፡ዘመድ፡የኾነ፡ከሊቀ፡ካህናቱ፡ባሪያዎች፡አንዱ፦በአትክልቱ፡ከርሱ፡ጋራ፡እኔ ፡አይቼኽ፡አልነበረምን፧አለው።
27፤ጴጥሮስም፡እንደ፡ገና፡ካደ፥ወዲያውም፡ዶሮ፡ጮኸ።
28፤ኢየሱስንም፡ከቀያፋ፡ወደገዢው፡ግቢ፡ወሰዱት፤ማለዳም፡ነበረ፤እነርሱም፡የፋሲካ፡በግ፡ይበሉ፡ዘንድ፡እን ጂ፡እንዳይረክሱ፡ወደገዢው፡ግቢ፡አልገቡም።
29፤ስለዚህ፥ጲላጦስ፡ወደ፡ውጭ፣ወደ፡እነርሱ፡ወጥቶ፦ይህን፡ሰው፡ስለ፡ምን፡ትከሱታላችኹ፡አላቸው።
30፤እነርሱም፡መልሰው፦ይህስ፡ክፉ፡አድራጊ፡ባይኾን፡ወዳንተ፡አሳልፈን፡ባልሰጠነውም፡ነበር፡አሉት።
31፤ጲላጦስም፦እናንተ፡ወስዳችኹ፡እንደ፡ሕጋችኹ፡ፍረዱበት፡አላቸው።አይሁድም፦ለእኛስ፡ማንንም፡ልንገድል፡ አልተፈቀደልንም፡አሉት፤
32፤ኢየሱስ፡በምን፡ዐይነት፡ሞት፡ሊሞት፡እንዳለው፡ሲያመለክት፡የተናገረው፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ነው።
33፤ጲላጦስም፡እንደ፡ገና፡ወደገዢው፡ግቢ፡ገባና፡ኢየሱስን፡ጠርቶ፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡አንተ፡ነኽን፧አለው።
34፤ኢየሱስም፡መልሶ፦አንተ፡ይህን፡የምትለው፡ከራስኽ፡ነውን፡ወይስ፡ሌላዎች፡ስለ፡እኔ፡ነገሩኽን፧አለው።
35፤ጲላጦስ፡መልሶ፦እኔ፡አይሁዳዊ፡ነኝን፧ወገኖችኽና፡የካህናት፡አለቃዎች፡ለእኔ፡አሳልፈው፡ሰጡኽ፤ምን፡አ ድርገኻል፧አለው።
36፤ኢየሱስም፡መልሶ፦መንግሥቴ፡ከዚህ፡ዓለም፡አይደለችም፤መንግሥቴስ፡ከዚህ፡ዓለም፡ብትኾን፥ወደ፡አይሁድ፡ እንዳልሰጥ፡ሎሌዎቼ፡ይዋጉልኝ፡ነበር፤አኹን፡ግን፡መንግሥቴ፡ከዚህ፡አይደለችም፡አለው።
37፤ጲላጦስም፦እንግዲያ፡ንጉሥ፡ነኽን፧አለው።ኢየሱስም፡መልሶ፦እኔ፡ንጉሥ፡እንደ፡ኾንኹ፡አንተ፡ትላለኽ።እ ኔ፡ለእውነት፡ልመሰክር፡ስለዚህ፡ተወልጃለኹ፡ስለዚህም፡ወደ፡ዓለም፡መጥቻለኹ፤ከእውነት፡የኾነ፡ዅሉ፡ድምፄ ን፡ይሰማል፡አለው።
38፤ጲላጦስ፦እውነት፡ምንድር፡ነው፧አለው።ይህንም፡ብሎ፡ዳግመኛ፡ወደ፡አይሁድ፡ወጥቶ፦እኔስ፡አንዲት፡በደል ፡ስንኳ፡አላገኘኹበትም።
39፤ነገር፡ግን፥በፋሲካ፡አንድ፡ልፈታላችኹ፡ልማድ፡አላችኹ፤እንግዲህ፡የአይሁድን፡ንጉሥ፡ልፈታላችኹ፡ትወዳ ላችኹን፧አላቸው።
40፤ዅሉም፡ደግመው፦በርባንን፡እንጂ፡ይህን፡አይደለም፡እያሉ፡ጮኹ።በርባን፡ግን፡ወንበዴ፡ነበረ።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19፤
1፤በዚያን፡ጊዜም፡ጲላጦስ፡ኢየሱስን፡ይዞ፡ገረፈው።
2፤ወታደሮችም፡ከሾኽ፡አክሊል፡ጐንጕነው፡በራሱ፡ላይ፡አኖሩ፡ቀይ፡ልብስም፡አለበሱት፤
3፤እየቀረቡም፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፡ይሉት፡ነበር፤
4፤በጥፊም፡ይመቱት፡ነበር።ጲላጦስም፡ደግሞ፡ወደ፡ውጭ፡ወጥቶ፦እንሆ፥አንዲት፡በደል፡ስንኳ፡እንዳላገኘኹበት ፡ታውቁ፡ዘንድ፡ርሱን፡ወደ፡ውጭ፡አወጣላችዃለኹ፡አላቸው።
5፤ኢየሱስም፡የሾኽ፡አክሊል፡ደፍቶ፡ቀይ፡ልብስም፡ለብሶ፡ወደ፡ውጭ፡ወጣ።
6፤ጲላጦስም፦እንሆ፥ሰውዬው፡አላቸው።የካህናት፡አለቃዎችና፡ሎሌዎች፡ባዩትም፡ጊዜ፦ስቀለው፡ስቀለው፡እያሉ፡ ጮኹ።ጲላጦስም፦እኔስ፡አንዲት፡በደል፡ስንኳ፡አላገኘኹበትምና፡እናንተ፡ወስዳችኹ፡ስቀሉት፡አላቸው።
7፤አይሁድም፡መልሰው፦እኛ፡ሕግ፡አለን፥እንደ፡ሕጋችንም፡ሊሞት፡ይገ፟ባ፟ዋል፥ራሱን፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡አ ድርጓልና፥አሉት።
8፤ስለዚህ፥ጲላጦስ፡ይህን፡ነገር፡በሰማ፡ጊዜ፥እጅግ፡ፈራ፤
9፤ተመልሶም፡ወደገዢው፡ግቢ፡ገባና፡ኢየሱስን፦አንተ፡ከወዴት፡ነኽ፧አለው።ኢየሱስ፡ግን፡አንድ፡እንኳ፡አልመ ለሰለትም።
10፤ስለዚህ፥ጲላጦስ፦አትነግረኝምን፧ልሰቅልኽ፡ሥልጣን፡እንዳለኝ፡ወይም፡ልፈታኽ፡ሥልጣን፡እንዳለኝ፡አታው ቅምን፧አለው።
11፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ከላይ፡ካልተሰጠኽ፡በቀር፥በእኔ፡ላይ፡ምንም፡ሥልጣን፡ባልነበረኽም፤ስለዚህ፥ለአንተ፡ አሳልፎ፡የሰጠኝ፥ኀጢአቱ፡የባሰ፡ነው፡አለው።
12፤ከዚህ፡በዃላ፡ጲላጦስ፡ሊፈታው፡ፈለገ፤ነገር፡ግን፥አይሁድ፦ይህንስ፡ብትፈታው፡የቄሳር፡ወዳጅ፡አይደለኽ ም፤ራሱን፡ንጉሥ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡የቄሳር፡ተቃዋሚ፡ነው፡እያሉ፡ጮኹ።
13፤ጲላጦስም፡ይህን፡ነገር፡ሰምቶ፡ኢየሱስን፡ወደ፡ውጭ፡አወጣው፥በዕብራይስጥም፡ገበታ፡በተባለው፡ጸፍጸፍ፡ በሚሉት፡ስፍራ፡በፍርድ፡ወንበር፡ተቀመጠ።
14፤ለፋሲካም፡የማዘጋጀት፡ቀን፡ነበረ፤ስድስት፡ሰዓትም፡የሚያኽል፡ነበረ፤አይሁድንም፦እንሆ፥ንጉሣችኹ፡አላ ቸው።
15፤እነርሱ፡ግን፦አስወግደው፥አስወግደው፥ስቀለው፡እያሉ፡ጮኹ።ጲላጦስም፦ንጉሣችኹን፡ልስቀለውን፧አላቸው። የካህናት፡አለቃዎችም፦ከቄሳር፡በቀር፡ሌላ፡ንጉሥ፡የለንም፡ብለው፡መለሱለት።
16፤ስለዚህ፥በዚያን፡ጊዜ፡እንዲሰቀል፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
17፤ኢየሱስንም፡ይዘው፡ወሰዱት፤መስቀሉንም፡ተሸክሞ፡በዕብራይስጥ፡ጎልጎታ፡ወደተባለው፡የራስ፡ቅል፡ስፍራ፡ ወደሚሉት፡ወጣ።
18፤በዚያም፡ሰቀሉት፥ከርሱም፡ጋራ፡ሌላዎች፡ኹለት፥አንዱን፡በዚህ፡አንዱን፡በዚያ፡ኢየሱስንም፡በመካከላቸው ፡ሰቀሉ።
19፤ጲላጦስም፡ደግሞ፡ጽሕፈት፡ጽፎ፡በመስቀሉ፡ላይ፡አኖረው፤ጽሕፈቱም፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡የናዝሬቱ፡ኢየሱስ፡ የሚል፡ነበረ።
20፤ኢየሱስም፡የተሰቀለበት፡ስፍራ፡ለከተማ፡ቅርብ፡ነበረና፡ከአይሁድ፡ብዙዎች፡ይህን፡ጽሕፈት፡አነበቡት፤በ ዕብራይስጥና፡በሮማይስጥ፡በግሪክም፡ተጽፎ፡ነበር።
21፤ስለዚህ፥የአይሁድ፡ካህናት፡አለቃዎች፡ጲላጦስን፦ርሱ፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነኝ፡እንዳለ፡እንጂ፥የአይሁድ፡ ንጉሥ፡ብለኽ፡አትጻፍ፡አሉት።
22፤ጲላጦስም፦የጻፍኹትን፡ጽፌያለኹ፡ብሎ፡መለሰ።
23፤ጭፍራዎችም፡ኢየሱስን፡በሰቀሉት፡ጊዜ፡ልብሶቹን፡ወስደው፡ለያንዳንዱ፡ጭፍራ፡አንድ፡ክፍል፡ኾኖ፡በአራት ፡ከፋፈሉት፤እጀ፡ጠባቡን፡ደግሞ፡ወሰዱ።እጀ፡ጠባቡም፡ከላይ፡ዠምሮ፡ወጥ፟፡ኾኖ፡የተሠራ፡ነበረ፡እንጂ፡የተ ሰፋ፡አልነበረም።
24፤ስለዚህ፥ርስ፡በርሳቸው፦ለማን፡እንዲኾን፡በርሱ፡ዕጣ፡እንጣጣልበት፡እንጂ፥አንቅደደው፡ተባባሉ።ይህም፦ ልብሴን፡ርስ፡በርሳቸው፡ተከፋፈሉ፡በእጀ፡ጠባቤም፡ዕጣ፡ተጣጣሉበት፡የሚለው፡የመጽሐፍ፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ ፡ነው።
25፤ጭፍራዎችም፡እንዲህ፡አደረጉ።ነገር፡ግን፥በኢየሱስ፡መስቀል፡አጠገብ፡እናቱ፥የእናቱም፡እኅት፥የቀለዮጳ ም፡ሚስት፡ማርያም፥መግደላዊትም፡ማርያም፡ቆመው፡ነበር።
26፤ኢየሱስም፡እናቱን፡ይወደ፟ው፡የነበረውንም፡ደቀ፡መዝሙር፡በአጠገቡ፡ቆሞ፡ባየ፡ጊዜ፡እናቱን፦አንቺ፡ሴት ፥እንሆ፥ልጅሽ፡አላት።
27፤ከዚህ፡በዃላ፡ደቀ፡መዝሙሩን፦እናትኽ፡እንሇት፡አለው።ከዚህም፡ሰዓት፡ዠምሮ፡ደቀ፡መዝሙሩ፡ወደ፡ቤቱ፡ወ ሰዳት።
28፤ከዚህ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡አኹን፡ዅሉ፡እንደተፈጸመ፡ዐውቆ፥የመጽሐፉ፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፦ተጠማኹ፡አለ።
29፤በዚያም፡ሖምጣጤ፡የሞላበት፡ዕቃ፡ተቀምጦ፡ነበር፤እነርሱም፡ሖምጣጤውን፡በሰፍነግ፡ሞልተው፡በሁሶፕም፡አ ድርገው፡ወደ፡አፉ፡አቀረቡለት።
30፤ኢየሱስም፡ሖምጣጤውን፡ከተቀበለ፡በዃላ፦ተፈጸመ፡አለ፥ራሱንም፡አዘንብሎ፡ነፍሱን፡አሳልፎ፡ሰጠ።
31፤አይሁድም፡የማዘጋጀት፡ቀን፡ስለ፡ኾነ፡ያ፡ሰንበት፡ትልቅ፡ነበረና፡ሥጋቸው፡በሰንበት፡በመስቀል፡ላይ፡እ ንዳይኖር፥ጭናቸውን፡ሰብረው፡እንዲያወርዷቸው፡ጲላጦስን፡ለመኑት።
32፤ጭፍራዎችም፡መጥተው፡የፊተኛውን፡ጭን፡ከርሱም፡ጋራ፡የተሰቀለውን፡የሌላውን፡ጭን፡ሰበሩ፤
33፤ወደ፡ኢየሱስ፡በመጡ፡ጊዜ፡ግን፡ርሱ፡ፈጽሞ፡እንደ፡ሞተ፡አይተው፡ጭኑን፡አልሰበሩም፤
34፤ነገር፡ግን፥ከጭፍራዎች፡አንዱ፡ጐኑን፡በጦር፡ወጋው፤ወዲያውም፡ደምና፡ውሃ፡ወጣ።
35፤ያየውም፡መስክሯል፤ምስክሩም፡እውነት፡ነው፤እናንተም፡ደግሞ፡ታምኑ፡ዘንድ፡ርሱ፡እውነት፡እንዲናገር፡ያ ውቃል።
36፤ይህ፡የኾነ፦ከርሱ፡ዐጥንት፡አይሰበርም፡የሚል፡የመጽሐፉ፡ቃል፡እንዲፈጸም፡ነው።
37፤ደግሞም፡ሌላው፡መጽሐፍ፦የወጉትን፡ያዩታል፡ይላል።
38፤ከዚህም፡በዃላ፡አይሁድን፡ስለ፡ፈራ፡በስውር፡የኢየሱስ፡ደቀ፡መዝሙር፡የነበረ፡የአርማትያስ፡ዮሴፍ፡የኢ የሱስን፡ሥጋ፡ሊወስድ፡ጲላጦስን፡ለመነ፤ጲላጦስም፡ፈቀደለት።ስለዚህም፡መጥቶ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ወሰደ።
39፤ደግሞም፡አስቀድሞ፡በሌሊት፡ወደ፡ኢየሱስ፡መጥቶ፡የነበረ፡ኒቆዲሞስ፡መቶ፡ንጥር፡የሚያኽል፡የከርቤና፡የ ሬት፡ቅልቅል፡ይዞ፡መጣ።
40፤የኢየሱስንም፡ሥጋ፡ወስደው፥እንደ፡አይሁድ፡አገናነዝ፡ልማድ፥ከሽቱ፡ጋራ፡በተልባ፡እግር፡ልብስ፡ከፈኑት ።
41፤በተሰቀለበትም፡ስፍራ፡አትክልት፡ነበረ፥በአትክልቱም፡ማንም፡ገና፡ያልተቀበረበት፡ዐዲስ፡መቃብር፡ነበረ ።
42፤ስለዚህ፥መቃብሩ፡ቅርብ፡ነበረና፥ስለ፡አይሁድ፡ማዘጋጀት፡ቀን፡ኢየሱስን፡በዚያ፡አኖሩት።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20፤
1፤ከሳምንቱም፡በፊተኛው፡ቀን፥መግደላዊት፡ማርያም፥ገና፡ጨለማ፡ሳለ፡ማለዳ፡ወደ፡መቃብር፡መጣች፤ድንጋዩም፡ ከመቃብሩ፡ተፈንቅሎ፡አየች።
2፤እየሮጠችም፡ወደ፡ስምዖን፡ጴጥሮስና፥ኢየሱስ፡ይወደ፟ው፡ወደ፡ነበረው፣ወደ፡ሌላው፡ደቀ፡መዝሙር፡መጥታ፦ጌ ታን፡ከመቃብር፡ወስደውታል፥ወዴትም፡እንዳኖሩት፡አናውቅም፡አለቻቸው።
3፤ስለዚህ፥ጴጥሮስና፡ሌላው፡ደቀ፡መዝሙር፡ወጥተው፡ወደ፡መቃብሩ፡ኼዱ።
4፤ኹለቱም፡ዐብረው፡ሮጡ፤ሌላው፡ደቀ፡መዝሙርም፡ከጴጥሮስ፡ይልቅ፡ፈጥኖ፡ወደ፡ፊት፡ሮጠና፡አስቀድሞ፡ከመቃብ ሩ፡ደረሰ፤
5፤ዝቅም፡ብሎ፡ቢመለከት፡የተልባ፡እግሩን፡ልብስ፡ተቀምጦ፡አየ፥ነገር፡ግን፥አልገባም።
6፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፡ተከትሎት፡መጣ፡ወደ፡መቃብሩም፡ገባ፤የተልባ፡እግሩን፡ልብስ፡ተቀምጦ፡አየ፥
7፤ደግሞም፡በራሱ፡የነበረውን፡ጨርቅ፡ለብቻው፡ባንድ፡ስፍራ፡ተጠምጥሞ፡እንደ፡ነበረ፡እንጂ፡ከተልባ፡እግሩ፡ ልብስ፡ጋራ፡ተቀምጦ፡እንዳልነበረ፡አየ።
8፤በዚያን፡ጊዜ፡አስቀድሞ፡ወደ፡መቃብር፡የመጣውም፡ሌላው፡ደቀ፡መዝሙር፡ደግሞ፡ገባ፥አየም፥አመነም፤
9፤ከሙታን፡ይነሣ፡ዘንድ፡እንዲገባው፡የሚለውን፡የመጽሐፉን፡ቃል፡ገና፡አላወቁም፡ነበርና።
10፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ወደ፡ቤታቸው፡ደግሞ፡ኼዱ።
11፤ማርያም፡ግን፡እያለቀሰች፡ከመቃብሩ፡በስተውጭ፡ቆማ፡ነበር።ስታለቅስም፡ወደ፡መቃብር፡ዝቅ፡ብላ፡ተመለከ ተች፤
12፤ኹለት፡መላእክትም፡ነጭ፡ልብስ፡ለብሰው፡የኢየሱስ፡ሥጋ፡ተኝቶበት፡በነበረው፡አንዱ፡በራስጌ፡ሌላውም፡በ እግርጌ፡ተቀምጠው፡አየች።
13፤እነርሱም፦አንቺ፡ሴት፥ስለ፡ምን፡ታለቅሻለሽ፧አሏት።ርሷም፦ጌታዬን፡ወስደውታል፡ወዴትም፡እንዳኖሩት፡አ ላውቅም፡አለቻቸው።
14፤ይህንም፡ብላ፡ወደ፡ዃላ፡ዘወር፡ስትል፡ኢየሱስን፡ቆሞ፡አየችው፤ኢየሱስም፡እንደ፡ኾነ፡አላወቀችም።
15፤ኢየሱስም፦አንቺ፡ሴት፥ስለ፡ምን፡ታለቅሻለሽ፧ማንንስ፡ትፈልጊያለሽ፧አላት።ርሷም፡የአትክልት፡ጠባቂ፡መ ስሏት፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡ወስደኸው፡እንደ፡ኾንኽ፡ወዴት፡እንዳኖርኸው፡ንገረኝ፡እኔም፡እወስደዋለኹ፡አለችው ።
16፤ኢየሱስም፦ማርያም፡አላት።ርሷ፡ዘወር፡ብላ፡በዕብራይስጥ፦ረቡኒ፡አለችው፤ትርጓሜውም፦መምህር፡ሆይ፡ማለ ት፡ነው።
17፤ኢየሱስም፦ገና፡ወደ፡አባቴ፡አላረግኹምና፡አትንኪኝ፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ወንድሞቼ፡ኼደሽ፦እኔ፡ወደ፡አባቴ ና፡ወደ፡አባታችኹ፡ወደ፡አምላኬና፡ወደ፡አምላካችኹ፡ዐርጋለኹ፡ብለሽ፡ንገሪያቸው፡አላት።
18፤መግደላዊት፡ማርያም፡መጥታ፡ጌታን፡እንዳየች፡ይህንም፡እንዳላት፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ነገረች።
19፤ያም፡ቀን፡ርሱም፡ከሳምንቱ፡ፊተኛው፡በመሸ፡ጊዜ፥ደቀ፡መዛሙርቱ፡ተሰብስበው፡በነበሩበት፥አይሁድን፡ስለ ፡ፈሩ፡ደጆቹ፡ተዘግተው፡ሳሉ፥ኢየሱስ፡መጣ፤በመካከላቸውም፡ቆሞ፦ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን፡አላቸው።
20፤ይህንም፡ብሎ፡እጆቹንም፡ጐኑንም፡አሳያቸው።ደቀ፡መዛሙርቱም፡ጌታን፡ባዩ፡ጊዜ፡ደስ፡አላቸው።
21፤ኢየሱስም፡ዳግመኛ፦ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን፤አብ፡እንደ፡ላከኝ፡እኔ፡ደግሞ፡እልካችዃለኹ፡አላቸው።
22፤ይህንም፡ብሎ፡እፍ፡አለባቸውና፦መንፈስ፡ቅዱስን፡ተቀበሉ።
23፤ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡ያላችዃቸው፡ዅሉ፡ይቀርላቸዋል፤የያዛችኹባቸው፡ተይዞባቸዋል፡አላቸው።
24፤ነገር፡ግን፥ከዐሥራ፡ኹለቱ፡አንዱ፡ዲዲሞስ፡የሚሉት፡ቶማስ፡ኢየሱስ፡በመጣ፡ጊዜ፡ከነርሱ፡ጋራ፡አልነበረ ም።
25፤ሌላዎቹም፡ደቀ፡መዛሙርቱ፦ጌታን፡አይተነዋል፡አሉት።ርሱ፡ግን፦የችንካሩን፡ምልክት፡በእጆቹ፡ካላየኹ፡ጣ ቴንም፡በችንካሩ፡ምልክት፡ካላገባኹ፡እጄንም፡በጐኑ፡ካላገባኹ፡አላምንም፡አላቸው።
26፤ከስምንት፡ቀን፡በዃላም፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ደግመው፡በውስጥ፡ነበሩ፥ቶማስም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ነበረ።ደጆች፡ተ ዘግተው፡ሳሉ፡ኢየሱስ፡መጣ፤በመካከላቸውም፡ቆሞ፦ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን፡አላቸው።
27፤ከዚያም፡በዃላ፡ቶማስን፦ጣትኽን፡ወደዚህ፡አምጣና፡እጆቼን፡እይ፤እጅኽንም፡አምጣና፡በጐኔ፡አግባው፤ያመ ንኽ፡እንጂ፡ያላመንኽ፡አትኹን፡አለው።
28፤ቶማስም፦ጌታዬ፡አምላኬም፡ብሎ፡መለሰለት።
29፤ኢየሱስም፦ስላየኸኝ፡አምነኻል፤ሳያዩ፡የሚያምኑ፡ብፁዓን፡ናቸው፡አለው።
30፤ኢየሱስም፡በዚህ፡መጽሐፍ፡ያልተጻፈ፡ሌላ፡ብዙ፡ምልክት፡በደቀ፡መዛሙርቱ፡ፊት፡አደረገ፤
31፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፡ርሱ፡ክርስቶስ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡እንደ፡ኾነ፡ታምኑ፡ዘንድ፥አምናችኹም፡በስሙ፡ ሕይወት፡ይኾንላችኹ፡ዘንድ፡ይህ፡ተጽፏል።
_______________የዮሐንስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21፤
1፤ከዚህ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡በጥብርያዶስ፡ባሕር፡አጠገብ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንደ፡ገና፡ተገለጠላቸው፤
2፤እንዲህም፡ተገለጠ።ስምዖን፡ጴጥሮስና፡ዲዲሞስ፡የሚባለው፡ቶማስ፡ከገሊላ፡ቃና፡የኾነ፡ናትናኤልም፡የዘብዴ ዎስም፡ልጆች፡ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ሌላዎች፡ኹለት፡በአንድነት፡ነበሩ።
3፤ስምዖን፡ጴጥሮስ፦ዓሣ፡ላጠምድ፡እኼዳለኹ፡አላቸው።እነርሱም፦እኛም፡ከአንተ፡ጋራ፡እንመጣለን፡አሉት።ወጥ ተውም፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡ገቡ፡በዚያችም፡ሌሊት፡ምንም፡አላጠመዱም።
4፤በነጋም፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡በባሕር፡ዳር፡ቆመ፤ደቀ፡መዛሙርቱ፡ግን፡ኢየሱስ፡መኾኑን፡አላወቁም።
5፤ኢየሱስም፦ልጆች፡ሆይ፥አንዳች፡የሚበላ፡አላችኹን፧አላቸው።የለንም፡ብለው፡መለሱለት።
6፤ርሱም፦መረቡን፡በታንኳዪቱ፡በስተቀኝ፡ጣሉት፡ታገኙማላችኹ፡አላቸው።ስለዚህ፡ጣሉት፤በዚህም፡ጊዜ፡ከዓሣው ፡ብዛት፡የተነሣ፡ሊጐትቱት፡አቃታቸው።
7፤ኢየሱስ፡ይወደ፟ው፡የነበረውም፡ደቀ፡መዝሙር፡ጴጥሮስን፦ጌታ፡እኮ፡ነው፡አለው።ስለዚህ፡ስምዖን፡ጴጥሮስ፡ ጌታ፡መኾኑን፡በሰማ፡ጊዜ፡ዕራቍቱን፡ነበረና፥ልብሱን፡ታጥቆ፡ወደ፡ባሕር፡ራሱን፡ጣለ።
8፤ሌላዎቹ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ግን፡ከምድር፡ኹለት፡መቶ፡ክንድ፡ያኽል፡እንጂ፡እጅግ፡አልራቁም፡ነበርና፥ዓሣ፡የ ሞላውን፡መረብ፡እየሳቡ፡በጀልባ፡መጡ።
9፤ወደ፡ምድርም፡በወጡ፡ጊዜ፡ፍምና፡ዓሣ፡በላዩ፡ተቀምጦ፡እንጀራም፡አዩ።
10፤ኢየሱስም፦አኹን፡ካጠመዳችኹት፡ዓሣ፡አምጡ፡አላቸው።
11፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፡ወደ፡ጀልባዪቱ፡ገብቶ፡መቶ፡ዐምሳ፡ሦስት፡ታላላቅ፡ዓሣዎች፡ሞልቶ፡የነበረውን፡መረብ ፡ወደ፡ምድር፡ጐተተ፤ይህንም፡ያኽል፡ብዙ፡ሲኾን፡መረቡ፡አልተቀደደም።
12፤ኢየሱስም፦ኑ፥ምሳ፡ብሉ፡አላቸው።ከደቀ፡መዛሙርቱ፡አንድ፡ስንኳ፦አንተ፡ማን፡ነኽ፧ብሎ፡ሊመረምረው፡የደ ፈረ፡አልነበረም፤ጌታ፡መኾኑን፡ዐውቀው፡ነበርና።
13፤ኢየሱስም፡መጣና፡እንጀራ፡አንሥቶ፡ሰጣቸው፥እንዲሁም፡ዓሣውን።
14፤ኢየሱስ፡ከሙታን፡ከተነሣ፡በዃላ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሲገለጥላቸው፡ይህ፡ሦስተኛው፡ጊዜ፡ነበረ።
15፤ምሳ፡ከበሉ፡በዃላም፡ኢየሱስ፡ስምዖን፡ጴጥሮስን፦የዮና፡ልጅ፡ስምዖን፡ሆይ፥ከነዚህ፡ይልቅ፡ትወደኛለኽን ፧አለው፦አዎን፡ጌታ፡ሆይ፥እንድወድኽ፡አንተ፡ታውቃለኽ፡አለው፦ግልገሎቼን፡አሰማራ፡አለው።
16፤ደግሞ፡ኹለተኛ፦የዮና፡ልጅ፡ስምዖን፡ሆይ፥ትወደኛለኽን፧አለው፦አዎን፡ጌታ፡ሆይ፥እንድወድኽ፡አንተ፡ታው ቃለኽ፡አለው፦ጠቦቶቼን፡ጠብቅ፡አለው።
17፤ሦስተኛ፡ጊዜ፦የዮና፡ልጅ፡ስምዖን፡ሆይ፥ትወደኛለኽን፧አለው።ሦስተኛ፦ትወደኛለኽን፧ስለ፡አለው፡ጴጥሮስ ፡ዐዘነና፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡ዅሉን፡ታውቃለኽ፤እንድወድኽ፡አንተ፡ታውቃለኽ፡አለው።ኢየሱስም፦በጎቼን፡አሰማ ራ።
18፤እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥አንተ፡ጕልማሳ፡ሳለኽ፡ወገብኽን፡በገዛ፡ራስኽ፡ታጥቀኽ፡ወደምትወደ፟ው፡ትኼ ድ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥በሸመገልኽ፡ጊዜ፡እጆችኽን፡ትዘረጋለኽ፥ሌላውም፡ያስታጥቅኻል፡ወደማትወደ፟ውም፡ይወ ስድኻል፡አለው።
19፤በምን፡ዐይነት፡ሞት፡እግዚአብሔርን፡ያከብር፡ዘንድ፡እንዳለው፡ሲያመለክት፡ይህን፡አለ።ይህንም፡ብሎ፦ተ ከተለኝ፡አለው።
20፤ጴጥሮስም፡ዘወር፡ብሎ፡ኢየሱስ፡ይወደ፟ው፡የነበረውን፡ደቀ፡መዝሙር፡ሲከተለው፡አየ፤ርሱም፡ደግሞ፡በእራ ት፡ጊዜ፡በደረቱ፡ተጠግቶ፦ጌታ፡ሆይ፥አሳልፎ፡የሚሰጥኽ፡ማን፡ነው፧ያለው፡ነበረ።
21፤ጴጥሮስም፡ይህን፡አይቶ፡ኢየሱስን፦ጌታ፡ሆይ፥ይህስ፡እንዴት፡ይኾናል፧አለው።
22፤ኢየሱስም፦እስክመጣ፡ድረስ፡ይኖር፡ዘንድ፡ብወድስ፥ምን፡አግዶኽ፧አንተ፡ተከተለኝ፡አለው።
23፤ስለዚህ፦ያ፡ደቀ፡መዝሙር፡አይሞትም፡የሚለው፡ይህ፡ነገር፡ወደ፡ወንድሞች፡ወጣ፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፦እስ ክመጣ፡ድረስ፡ይኖር፡ዘንድ፡ብወድስ፡ምን፡አግዶኽ፧አለው፡እንጂ፡አይሞትም፡አላለውም።
24፤ስለ፡እነዚህም፡የመሰከረ፡ይህንንም፡ጽፎ፡ያለ፡ይህ፡ደቀ፡መዝሙር፡ነው፥ምስክሩም፡እውነት፡እንደ፡ኾነ፡ እናውቃለን።
25፤ኢየሱስም፡ያደረገው፡ብዙ፡ሌላ፡ነገር፡ደግሞ፡አለ፤ዅሉ፡በያንዳንዱ፡ቢጻፍ፡ለተጻፉት፡መጻሕፍት፡ዓለም፡ ራሱ፡ባልበቃቸውም፡ይመስለኛል፨

http://www.gzamargna.net