ትንቢተ፡ዳንኤል።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮአቄም፡በነገሠ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መ ጥቶ፡ከበባት።
2፤ጌታም፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡ኢዮአቄምን፡ከእግዚአብሔርም፡ቤት፡ዕቃ፡ከፍሎ፡በእጁ፡አሳልፎ፡ሰጠው፤ርሱም፡ወደ ሰናዖር፡ምድር፡ወደአምላኩ፡ቤት፡ወሰደው፥ዕቃውንም፡ወደአምላኩ፡ግምጃ፡ቤት፡አገባው።
3፤4፤ንጉሡም፡ነውር፡የሌለባቸውንና፡መልከ፡መልካሞቹን፥በጥበብ፡ዅሉ፡የሚያስተውሉትን፡ዕውቀትም፡የሞላባቸ ውን፡ብልኀተኛዎችና፡አስተዋዮች፡የኾኑትን፥በንጉሡም፡ቤት፡መቆም፡የሚችሉትን፡ብላቴናዎች፡ከእስራኤል፡ልጆ ች፡ከነገሥታቱና፡ከመሳፍንቱ፡ዘር፡ያመጣ፡ዘንድ፥የከለዳውያንንም፡ትምህርትና፡ቋንቋ፡ያስተምሯቸው፡ዘንድ፥ ለጃን፡ደረባዎች፡አለቃ፡ለአስፋኔዝ፡ነገረ።
5፤ንጉሡም፡ሦስት፡ዓመት፡ያሳድጓቸው፡ዘንድ፥ከዚያም፡በዃላ፡በንጉሡ፡ፊት፡ይቆሙ፡ዘንድ፥ከንጉሡ፡መብል፡ከሚ ጠጣውም፡ጠጅ፡በየዕለቱ፡ድርጓቸውን፡አዘዘላቸው።
6፤በእነዚህም፡መካከል፡ከይሁዳ፡ልጆች፡ዳንኤልና፡ዐናንያ፡ሚሳኤልና፡ዐዛርያ፡ነበሩ።
7፤የጃን፡ደረባዎቹም፡አለቃ፡ስም፡አወጣላቸው፤ዳንኤልን፡ብልጣሶር፥ዐናንያንም፡ሲድራቅ፥ሚሳኤልንም፡ሚሳቅ፥ ዐዛርያንም፡ዐብደናጎ፡ብሎ፡ጠራቸው።
8፤ዳንኤልም፡በንጉሡ፡መብልና፡በሚጠጣው፡ጠጅ፡እንዳይረክስ፡በልቡ፡ዐሰበ፤እንዳይረክስም፡የጃን፡ደረባዎቹን ፡አለቃ፡ለመነ።
9፤እግዚአብሔርም፡በጃን፡ደረባዎቹ፡አለቃ፡ፊት፡ለዳንኤል፡ሞገስንና፡ምሕረትን፡ሰጠው።
10፤የጃን፡ደረባዎቹም፡አለቃ፡ዳንኤልን፦መብሉንና፡መጠጡን፡ያዘዘላችኹን፡ጌታዬን፡ንጉሡን፡እፈራለኹ፤በዕድ ሜ፡እንደናንተ፡ካሉ፡ብላቴናዎች፡ይልቅ፡ፊታችኹ፡ከስቶ፡ያየ፡እንደ፡ኾነ፥ከንጉሡ፡ዘንድ፡በራሴ፡ታስፈርዱብ ኛላችኹ፡አለው።
11፤ዳንኤልም፡የጃንደርባዎቹ፡አለቃ፡በዳንኤልና፡በዐናንያ፡በሚሳኤልና፡በዐዛርያ፡ላይ፡የሾመውን፡ሜልዳርን ።
12፤እኛን፡ባሪያዎችኽን፡ዐሥር፡ቀን፡ያኽል፡ትፈትነን፡ዘንድ፥እለምንኻለኹ፤የምንበላውንም፡ጥራጥሬ፡የምንጠ ጣውንም፡ውሃ፡ይስጡን፤
13፤ከዚያም፡በዃላ፡የእኛን፡ፊትና፡ከንጉሡ፡መብል፡የሚበሉትን፡የብላቴናዎችን፡ፊት፡ተመልከት፤እንዳየኸውም ፡ዅሉ፡ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡የወደድኸውን፡አድርግ፡አለው።
14፤ይህንም፡ነገራቸውን፡ሰምቶ፡ዐሥር፡ቀን፡ፈተናቸው።
15፤ከዐሥር፡ቀንም፡በዃላ፡ከንጉሡ፡መብል፡ከበሉ፡ብላቴናዎች፡ዅሉ፡ይልቅ፡ፊታቸው፡አምሮ፡ሥጋቸውም፡ወፍሮ፡ ታየ።
16፤ሜልዳርም፡መብላቸውንና፡የሚጠጡትን፡ጠጅ፡አስቀርቶ፡ጥራጥሬውን፡ሰጣቸው።
17፤ለእነዚህም፡ለአራቱ፡ብላቴናዎች፡እግዚአብሔር፡በትምህርትና፡በጥበብ፡ዅሉ፡ዕውቀትንና፡ማስተዋልን፡ሰጣ ቸው፤ዳንኤልም፡በራእይና፡በሕልም፡ዅሉ፡አስተዋይ፡ነበረ።
18፤እነርሱም፡ይገቡ፡ዘንድ፥ንጉሡ፡ያዘዘው፡ቀን፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥የጃን፡ደረባዎቹ፡አለቃ፡ወደ፡ናቡከደነጾር ፡ዘንድ፡አገባቸው።
19፤ንጉሡም፡በተነጋገራቸው፡ጊዜ፡ከብላቴናዎቹ፡ዅሉ፡እንደ፡ዳንኤልና፡እንደ፡ዐናንያ፡እንደ፡ሚሳኤልና፡እን ደ፡ዐዛርያ፡ያለ፡አልተገኘም፤በንጉሡም፡ፊት፡ቆሙ።
20፤ንጉሡም፡በጠየቃቸው፡በጥበብና፡በማስተዋል፡ነገር፡ዅሉ፡በግዛቱ፡ዅሉ፡ከሚኖሩ፡የሕልም፡ተርጓሚዎችና፡አ ስማተኛዎች፡ዅሉ፡እነርሱ፡ዐሥር፡እጅ፡የበለጡ፡ኾነው፡አገኘባቸው።
21፤ዳንኤልም፡እስከንጉሡ፡እስከቂሮስ፡መዠመሪያ፡ዓመት፡ተቀመጠ።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ናቡከደነጾርም፡በነገሠ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡ናቡከደነጾር፡ሕልም፡ዐለመ፤መንፈሱም፡ታወከ፥እንቅልፉም፡ከር ሱ፡ራቀ።
2፤ለንጉሡም፡ሕልሙን፡እንዲነግሩት፡ንጉሡ፡የሕልም፡ተርጓሚዎቹንና፡አስማተኛዎቹን፡መተተኛዎቹንና፡ከለዳውያ ኑንም፡ይጠሩ፡ዘንድ፥አዘዘ፤እነርሱም፡ገብተው፡በንጉሡ፡ፊት፡ቆሙ።
3፤ንጉሡም፦ሕልም፡ዐልሜያለኹ፥ሕልሙንም፡ለማወቅ፡መንፈሴ፡ታውኳል፡አላቸው።
4፤ከለዳውያኑም፡ንጉሡን፡በሶርያ፡ቋንቋ፦ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ፤ለባሪያዎችኽ፡ሕልምኽን፡ንገር፥እኛ ም፡ፍቺውን፡እናሳይኻለን፡ብለው፡ተናገሩት።
5፤ንጉሡም፡መለሰ፡ከለዳውያኑንም፦ነገሩ፡ከእኔ፡ዘንድ፡ርቋል፤ሕልሙንና፡ፍቺውን፡ባታስታውቁኝ፥ትቈረጣላችኹ ፡ቤቶቻችኹም፡የጕድፍ፡መጣያ፡ይደረጋሉ።
6፤ሕልሙንና፡ፍቺውን፡ግን፡ብታሳዩ፥ከእኔ፡ዘንድ፡ስጦታና፡ዋጋ፡ብዙ፡ክብርም፡ትቀበላላችኹ፤ስለዚህም፡ሕልሙ ንና፡ፍቺውን፡አሳዩኝ፡አላቸው።
7፤ኹለተኛም፡ጊዜ፡መልሰው፦ንጉሡ፡ለባሪያዎቹ፡ሕልሙን፡ይንገር፥እኛም፡ፍቺውን፡እናሳያለን፡አሉት።
8፤ንጉሡ፡መልሶ፦ነገሩ፡ከእኔ፡ዘንድ፡እንደ፡ራቀ፡ታውቃላችኹና፡ጊዜውን፡እንድታስረዝሙ፡እኔ፡ዐውቃለኹ።
9፤ሕልሙንም፡ባታስታውቁኝ፡አንድ፡ፍርድ፡አለባችኹ፤ጊዜውን፡ለማሳለፍ፡የሐሰትንና፡የተንኰልን፡ቃል፡ልትነግ ሩኝ፡አዘጋጅታችዃል፤ስለዚህ፥ሕልሙን፡ንገሩኝ፥ፍቺውንም፡ማሳየት፡እንድትችሉ፡ዐውቃለኹ፡አለ።
10፤ከለዳውያኑም፡በንጉሡ፡ፊት፡መልሰው፦የንጉሡን፡ነገር፡ያሳይ፡ዘንድ፡የሚችል፡ሰው፡በምድር፡ላይ፡የለም፤ ከነገሥታትም፡ታላቅና፡ኀይለኛ፡የኾነ፡እንደዚህ፡ያለ፡ነገር፡የሕልም፡ተርጓሚንና፡አስማተኛን፡ከለዳዊንም፡ አልጠየቀም።
11፤ንጉሡም፡የሚጠይቀው፡ነገር፡የቸገረ፡ነው፤መኖሪያቸው፡ከሰው፡ጋራ፡ካልኾነ፡ከአማልክት፡በቀር፡በንጉሡ፡ ፊት፡የሚያሳየው፡ማንም፡የለም፡አሉ።
12፤ስለዚህም፡ንጉሡ፡ተበሳጨ፡እጅግም፡ተቈጣ፥የባቢሎንንም፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ያጠፉ፡ዘንድ፡አዘዘ።
13፤ትእዛዝም፡ወጣ፥ጠቢባንንም፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ዠመሩ፤ዳንኤልንና፡ባልንጀራዎቹንም፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ፈለጓቸ ው።
14፤የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡የባቢሎንን፡ጠቢባን፡ይገድል፡ዘንድ፡የወጣውን፡የንጉሡን፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡አ ርዮክን፡በፈሊጥና፡በማስተዋል፡ተናገረው፤
15፤ለንጉሡም፡አለቃ፡ለአርዮክ፡መልሶ፦የንጉሡ፡ትእዛዝ፡ስለ፡ምን፡ቸኰለ፧አለው።አርዮክም፡ነገሩን፡ለዳንኤ ል፡አስታወቀው።
16፤ዳንኤልም፡ገብቶ፡ፍቺውን፡ለንጉሡ፡የሚያስታውቅበት፡ጊዜ፡ይሰጠው፡ዘንድ፥ንጉሡን፡ለመነ።
17፤18፤የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።ዳንኤልም፡ባልንጀራዎቹም፡ከቀሩት፡ከባቢሎን፡ጠቢባን፡ጋራ፡ እንዳይሞቱ፡ስለዚህ፡ምስጢር፡ምሕረትን፡ከሰማይ፡አምላክ፡ይለምኑ፡ዘንድ፥ነገሩን፡ለባልንጀራዎቹ፡ለዐናንያ ና፡ለሚሳኤል፡ለዐዛርያ፡አስታወቃቸው።
19፤የዚያን፡ጊዜም፡ምስጢሩ፡በሌሊት፡ራእይ፡ለዳንኤል፡ተገለጠለት፤ዳንኤልም፡የሰማይን፡አምላክ፡አመሰገነ።
20፤ዳንኤልም፡ተናገረ፡እንዲህም፡አለ፦ጥበብና፡ኀይል፡ለርሱ፡ነውና፥የእግዚአብሔር፡ስም፡ከዘለዓለም፡እስከ ፡ዘለዓለም፡ይባረክ፤
21፤ጊዜያትንና፡ዘመናትን፡ይለውጣል፤ነገሥታትን፡ያፈልሳል፥ነገሥታትንም፡ያስነሣል፤ጥበብን፡ለጠቢባን፡ዕው ቀትንም፡ለአስተዋዮች፡ይሰጣል።
22፤የጠለቀውንና፡የተሰወረውን፡ይገልጣል፤በጨለማ፡ያለውን፡ያውቃል፥ብርሃንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነው።
23፤ጥበብንና፡ኀይልን፡የሰጠኸኝ፥እኛም፡የለመ፟ን፟ኽን፡ነገር፡አኹን፡ያስታወቅኸኝ፥አንተ፡የአባቶቼ፡አምላ ክ፡ሆይ፥የንጉሡን፡ነገር፡አስታውቀኸኛልና፥እገዛልኻለኹ፡አመሰግንኽማለኹ።
24፤ከዚህም፡በዃላ፡ዳንኤል፡ንጉሡ፡የባቢሎንን፡ጠቢባን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ወዳዘዘው፥ወደ፡አርዮክ፡ገባ፤በገባም ፡ጊዜ፦የባቢሎንን፡ጠቢባን፡አታጥፋ፤ወደ፡ንጉሡ፡አስገባኝ፥እኔም፡ፍቺውን፡ለንጉሡ፡አሳያለኹ፡አለው።
25፤የዚያን፡ጊዜም፡አርዮክ፡ዳንኤልን፡ፈጥኖ፡ወደ፡ንጉሡ፡አስገባውና፦ከይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡ያለውን፡ለንጉሡ ፡ፍቺውን፡የሚያስታውቀውን፡ሰው፡አግኝቻለኹ፡አለው።
26፤ንጉሡም፡መለሰ፡ብልጣሶርም፡የሚባለውን፡ዳንኤልን፦ያየኹትን፡ሕልምና፡ፍቺውን፡ታስታውቀኝ፡ዘንድ፡ትችላ ለኽን፧አለው።
27፤ዳንኤልም፡በንጉሡ፡ፊት፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ንጉሡ፡የጠየቀውን፡ምስጢር፡ጠቢባንና፡አስማተኛዎች፡የሕል ም፡ተርጓሚዎችና፡ቃላ፟ተኛዎች፡ለንጉሡ፡ያሳዩ፡ዘንድ፡አይችሉም፤
28፤ነገር፡ግን፥ምስጢር፡የሚገልጥ፡አምላክ፡በሰማይ፡ውስጥ፡አለ፥ርሱም፡በዃለኛው፡ዘመን፡የሚኾነውን፡ለንጉ ሡ፡ለናቡከደነጾር፡አስታውቆታል።በዐልጋኽ፡ላይ፡የኾነው፡ሕልምና፡የራስኽ፡ራእይ፡ይህ፡ነው።
29፤አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡በዃላ፡የሚኾነው፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡በዐልጋኽ፡ላይ፡ታስብ፡ነበር፤ምስጢርንም ፡የሚገልጠው፡የሚኾነውን፡ነገር፡አስታውቆኻል።
30፤ነገር፡ግን፥ይህ፡ምስጢር፡ለእኔ፡መገለጡ፡ፍቺው፡ለንጉሡ፡ይታወቅ፡ዘንድ፥አንተም፡የልብኽን፡ዐሳብ፡ታው ቅ፡ዘንድ፡ነው፡እንጂ፡በዚህ፡ዓለም፡ካሉ፡ሰዎች፡ይልቅ፡በጥበብ፡ስለ፡በለጥኹ፡አይደለም።
31፤አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፥ታላቅ፡ምስል፡አየኽ፤ይህም፡ምስል፡ታላቅና፡ብልጭልጭታው፡የበዛ፡ነበረ፥በፊትኽም፡ቆ ሞ፡ነበር፤መልኩም፡ግሩም፡ነበረ።
32፤የዚህም፡ምስል፡ራስ፡ጥሩ፡ወርቅ፥ደረቱና፡ክንዶቹም፡ብር፥ሆዱና፡ወገቡም፡ናስ፥
33፤ጭኖቹም፡ብረት፥እግሮቹም፡እኩሉ፡ብረት፡እኩሉም፡ሸክላ፡ነበረ።
34፤እጅም፡ሳይነካው፡ድንጋይ፡ከተራራው፡ተፈንቅሎ፡ከብረትና፡ከሸክላ፡የኾነውን፡የምስሉን፡እግሮች፡ሲመታና ፡ሲፈጭ፡አየኽ።
35፤የዚያን፡ጊዜም፡ብረቱና፡ሸክላው፥ናሱና፡ብሩ፡ወርቁም፡በአንድነት፡ተፈጨ፥በመከርም፡ጊዜ፡በዐውድማ፡ላይ ፡እንዳለ፡እብቅ፡ኾነ፤ነፋስም፡ወሰደው፥ቦታውም፡አልታወቀም፤ምስሉንም፡የመታ፡ድንጋይ፡ታላቅ፡ተራራ፡ኾነ፡ ምድርንም፡ፈጽሞ፡ሞላ፡
36፤ሕልሙ፡ይህ፡ነው፤አኹንም፡ፍቺውን፡በንጉሡ፡ፊት፡እንናገራለን።
37፤አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፥የሰማይ፡አምላክ፡መንግሥትንና፡ኀይልን፥ብርታትንና፡ክብርን፡የሰጠኽ፡የነገሥታት፡ን ጉሥ፡አንተ፡ነኽ።
38፤በሚቀመጡበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡የሰው፡ልጆችንና፡የምድር፡አራዊትን፡የሰማይ፡ወፎችንም፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡ሰ ጥቶኻል፥ለዅሉም፡ገዢ፡አድርጎኻል፤አንተ፡የወርቁ፡ራስ፡ነኽ።
39፤ከአንተም፡በዃላ፡ከአንተ፡የሚያንስ፡ሌላ፡መንግሥት፡ይነሣል፤ከዚያም፡በዃላ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡የሚገዛ ፡ሌላ፡ሦስተኛ፡የናስ፡መንግሥት፡ይነሣል።
40፤አራተኛውም፡መንግሥት፡ዅሉን፡እንደሚቀጠቅጥና፡እንደሚያደቅ፟፡ብረት፡ይበረታል፤እነዚህንም፡ዅሉ፡እንደ ሚፈጭ፡ብረት፡ይቀጠቅጣል፡ይፈጭማል።
41፤እግሮቹና፡ጣቶቹም፡እኩሉ፡ሸክላ፡እኩሉም፡ብረት፡ኾኖ፡እንዳየኽ፥እንዲሁ፡የተከፋፈለ፡መንግሥት፡ይኾናል ፤ብረቱም፡ከሸክላው፡ጋራ፡ተደባልቆ፡እንዳየኹ፥የብረት፡ብርታት፡ለርሱ፡ይኾናል።
42፤የእግሮቹም፡ጣቶች፡እኩሉ፡ብረት፡እኩሉም፡ሸክላ፡እንደ፡ነበሩ፥እንዲሁ፡መንግሥቱ፡እኩሉ፡ብርቱ፡እኩሉ፡ ደካማ፡ይኾናል።
43፤ብረቱም፡ከሸክላው፡ጋራ፡ተደባልቆ፡እንዳየኽ፥እንዲሁ፡ከሰው፡ዘር፡ጋራ፡ይደባለቃሉ፤ነገር፡ግን፥ብረት፡ ከሸክላ፡ጋራ፡እንደማይጣበቅ፥እንዲሁ፡ርስ፡በርሳቸው፡አይጣበቁም።
44፤በእነዚያም፡ነገሥታት፡ዘመን፡የሰማይ፡አምላክ፡ለዘለዓለም፡የማይፈርስ፡መንግሥት፡ያስነሣል፤ለሌላ፡ሕዝ ብም፡የማይሰጥ፡መንግሥት፡ይኾናል፤እነዚያንም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ትፈጫቸዋለች፡ታጠፋቸውማለች፥ለዘለዓለምም ፡ትቆማለች።
45፤ድንጋዩም፡እጅ፡ሳይነካው፡ከተራራ፡ተፈንቅሎ፡ብረቱንና፡ናሱን፡ሸክላውንና፡ብሩን፡ወርቁንም፡ሲፈጨው፡እ ንዳየኽ፥እንዲሁ፡ከዚህ፡በዃላ፡የሚኾነውን፡ታላቁ፡አምላክ፡ለንጉሡ፡አስታውቆታል፤ሕልሙም፡እውነተኛ፡ፍቺው ም፡የታመነ፡ነው።
46፤የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡በግንባሩ፡ተደፍቶ፡ለዳንኤል፡ሰገደለት፥የእኽሉንም፡ቍርባን፡ዕጣኑ ንም፡ያቀርቡለት፡ዘንድ፡አዘዘ።
47፤ንጉሡም፡ዳንኤልን፦ይህን፡ምስጢር፡ትገልጥ፡ዘንድ፡ተችሎኻልና፥በእውነት፡አምላካችኹ፡የአማልክት፡አምላ ክ፥የነገሥታትም፡ጌታ፥ምስጢርም፡ገላጭ፡ነው፡ብሎ፡ተናገረው።
48፤ንጉሡም፡ዳንኤልን፡ከፍ፡ከፍ፡አደርገው፥ብዙም፡ታላቅ፡ስጦታ፡ሰጠው፥በባቢሎንም፡አውራጃ፡ዅሉ፡ላይ፡ሾመ ው፥በባቢሎንም፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ላይ፡ዋነኛ፡አለቃ፡አደረገው።
49፤ዳንኤልም፡ንጉሡን፡ለመነ፥ርሱም፡ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደናጎንም፡በባቢሎን፡አውራጃ፡ሥራ፡ላይ፡ሾማቸ ው፤ዳንኤል፡ግን፡በንጉሡ፡በር፡ነበረ።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ቁመቱ፡ስድሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ስድስት፡ክንድ፡የኾነውን፡የወርቁን፡ምስል፡አሠራ፤በባ ቢሎንም፡አውራጃ፡በዱራ፡ሜዳ፡አቆመው።
2፤ንጉሡም፡ናቡከደነጾር፡መኳንንትንና፡ሹማምቶችን፥አዛዦችንና፡ዐዛውንቶችን፥በጅሮንዶችንና፡አማካሪዎችን፥ መጋቢዎችንም፥አውራጃ፡ገዢዎችንም፡ዅሉ፡ይሰበስቡ፡ዘንድ፥ንጉሡም፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ምስል፡ምረቃ፡ይመ ጡ፡ዘንድ፡ላከ።
3፤በዚያን፡ጊዜም፡መኳንንቱና፡ሹማምቶቹ፥አዛዦቹና፡ዐዛውንቶቹ፥በጅሮንዶቹና፡አማካሪዎቹ፥መጋቢዎቹና፡አውራ ጃ፡ገዢዎቹ፡ዅሉ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ምስል፡ምረቃ፡ተሰበሰቡ፤ናቡከደነጾርም፡ባቆመው፡ምስል፡ፊት ፡ቆሙ።
4፤ዐዋጅ፡ነጋሪውም፡እየጮኸ፡እንዲህ፡አለ፦ወገኖችና፡አሕዛብ፡በልዩ፡ልዩ፡ቋንቋም፡የምትናገሩ፡ሆይ፥
5፤የመለከትንና፡የእንቢልታን፥የመሰንቆንና፡የክራርን፥የበገናንና፡የዋሽንትን፥የዘፈንንም፡ዅሉ፡ድምፅ፡በሰ ማችኹ፡ጊዜ፥ተደፍታችኹ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ለወርቁ፡ምስል፡እንድትሰግዱ፡ታዛ፟ችዃል።
6፤ተደፍቶም፡የማይሰግድ፡በዚያን፡ጊዜ፡በሚነድ፟፡እሳት፡እቶን፡ውስጥ፡ይጣላል።
7፤ስለዚህ፥በዚያን፡ጊዜ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡የመለከቱንና፡የእንቢልታውን፥የመሰንቆውንና፡የክራሩን፥የበገናውንና ፡የዘፈኑንም፡ዅሉ፡ድምፅ፡በሰሙ፡ጊዜ፥ወገኖችና፡አሕዛብ፡በልዩ፡ልዩ፡ቋንቋም፡የተናገሩ፡ዅሉ፡ተደፉ፥ንጉሡ ም፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ለወርቅ፡ምስል፡ሰገዱ።
8፤በዚያን፡ጊዜም፡ከለዳውያን፡ቀርበው፡አይሁድን፡ከሰሱ።
9፤ለንጉሡም፡ለናቡከደነጾር፡ተናገሩ፡እንዲህም፡አሉ።ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ።
10፤አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፦የመለከትንና፡የእንቢልታን፥የመሰንቆንና፡የክራርን፥የበገናንና፡የዋሽንትን፥የዘፈን ንም፡ዅሉ፡ድምፅ፡የሚሰማ፡ሰው፡ዅሉ፡ተደፍቶ፡ለወርቁ፡ምስል፡ይስገድ፤
11፤ተደፍቶም፡የማይሰግድ፡በሚነድ፟፡እሳት፡እቶን፡ውስጥ፡ይጣላል፡ብለኽ፡አዘዝኽ።
12፤በባቢሎን፡አውራጃ፡ሥራ፡ላይ፡የሾምኻቸው፡ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡የሚባሉ፡አይሁድ፡አሉ፤ንጉሥ፡ሆ ይ፥እነዚህ፡ሰዎች፡ትእዛዝኽን፡እንቢ፡ብለዋል፤አማልክትኽን፡አያመልኩም፥ላቆምኸውም፡ለወርቁ፡ምስል፡አይሰ ግዱም።
13፤ናቡከደነጾርም፡በብስጭትና፡በቍጣ፡ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደናጎንም፡ያመጡ፡ዘንድ፡አዘዘ፤እነዚህንም፡ ሰዎች፡ወደንጉሡ፡ፊት፡አመጧቸው።
14፤ናቡከደነጾርም፦ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡ሆይ፥አምላኬን፡አለማምለካችኹ፥ላቆምኹትም፡ለወርቁ፡ምስል ፡አለመስገዳችኹ፡እውነት፡ነውን፧
15፤አኹንም፡የመለከቱንና፡የእንቢልታውን፡የመሰንቆውንና፡የክራሩን፡የበገናውንና፡የዋሽንቱን፡የዘፈኑንም፡ ዅሉ፡ድምፅ፡በሰማችኹ፡ጊዜ፡ተደፍታችኹ፡ላሠራኹት፡ምስል፡ብትሰግዱ፡መልካም፡ነው፤ባትሰግዱ፡ግን፡በዚያ፡ጊ ዜ፡በሚነድ፟፡እሳት፡እቶን፡ውስጥ፡ትጣላላችኹ፤ከእጄስ፡የሚያድናችኹ፡አምላክ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ተናገራቸው።
16፤ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡መለሱ፡ንጉሡንም፦ናቡከደነጾር፡ሆይ፥በዚህ፡ነገር፡እንመልስልኽ፡ዘንድ፡አ ስፈላጊያችን፡አይደለም።
17፤የምናመልከው፡አምላካችን፡ከሚነደ፟ው፡ከእሳቱ፡እቶን፡ያድነን፡ዘንድ፡ይችላል፤ከእጅኽም፡ያድነናል፥ንጉ ሥ፡ሆይ!
18፤ነገር፡ግን፥ንጉሥ፡ሆይ፥ርሱ፡ባያድነን፥አማልክትኽን፡እንዳናመልክ፡ላቆምኸውም፡ለወርቁ፡ምስል፡እንዳን ሰግድለት፡ዕወቅ፡አሉት።
19፤የዚያን፡ጊዜም፡ናቡከደነጾር፡በሲድራቅና፡በሚሳቅ፡በዐብደናጎም፡ላይ፡ቍጣ፡ሞላበት፥የፊቱም፡መልክ፡ተለ ወጠባቸው፤ርሱም፡ተናገረ፥የእቶንም፡እሳት፡ይነድ፟፡ከነበረው፡ይልቅ፡ሰባት፡ዕጥፍ፡አድርገው፡እንዲያነዱ፟ ት፡አዘዘ።
20፤ሲድራቅንና፡ሚሳቅንም፡ዐብደናጎንም፡ያስሩ፡ዘንድ፥ወደሚነድ፟ም፡ወደእቶን፡እሳት፡ይጥሏቸው፡ዘንድ፥በሰ ራዊቱ፡ውስጥ፡ከነበሩት፡ኀያላን፡አዘዘ።
21፤የዚያን፡ጊዜም፡እነዚህ፡ሰዎች፡ከሰናፊላቸውና፡ከቀሚሳቸው፡ከመጐናጸፊያቸውም፡ከቀረውም፡ልብሳቸው፡ጋራ ፡ታስረው፡በሚነድ፟፡በእቶን፡እሳት፡ውስጥ፡ተጣሉ።
22፤የንጉሡም፡ትእዛዝ፡አስቸኳይ፡ስለ፡ኾነ፡የእቶኑም፡እሳት፡እጅግ፡ስለሚነድ፟፥ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደ ናጎንም፡የጣሏቸውን፡ሰዎች፡የእሳቱ፡ወላፈን፡ገደላቸው።
23፤እነዚህም፡ሦስቱ፡ሰዎች፡ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡ታስረው፡በሚነደ፟ው፡በእቶኑ፡እሳት፡ውስጥ፡ወደቁ ።
24፤የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ተደነቀ፡ፈጥኖም፡ተነሣ፤አማካሪዎቹንም፦ሦስት፡ሰዎች፡አስረን፡በእ ሳት፡ውስጥ፡ጥለን፡አልነበረምን፧ብሎ፡ተናገራቸው።እነርሱም፦ንጉሥ፡ሆይ፥እውነት፡ነው፡ብለው፡ለንጉሡ፡መለ ሱለት።
25፤ርሱም፦እንሆ፥እኔ፡የተፈቱ፡በእሳቱም፡መካከል፡የሚመላለሱ፡አራት፡ሰዎች፡አያለኹ፤ምንም፡አላቈሰላቸውም ፤የአራተኛውም፡መልክ፡የአማልክትን፡ልጅ፡ይመስላል፡ብሎ፡መለሰ።
26፤የዚያን፡ጊዜም፡ናቡከደነጾር፡ወደሚነደ፟ው፡ወደእሳቱ፡እቶን፡በር፡ቀርቦ፦እናንተ፡የልዑል፡አምላክ፡ባሪ ያዎች፥ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፥ኑ፡ውጡ፡ብሎ፡ተናገራቸው።ሲድራቅና፡ሚሳቅም፡ዐብደናጎም፡ከእሳቱ፡መካ ከል፡ወጡ።
27፤መሳፍንቱና፡ሹማምቶቹም፡አዛዦቹና፡የንጉሡ፡አማካሪዎች፡ተሰብስበው፡እሳቱ፡በእነዚያ፡ሰዎች፡አካል፡ላይ ፡ኀይል፡እንዳልነበረው፥የራሳቸውም፡ጠጕር፡እንዳልተቃጠለች፥ሰናፊላቸውም፡እንዳልተለወጠ፥የእሳቱም፡ሽታ፡ እንዳልደረሰባቸው፡አዩ።
28፤ናቡከደነጾርም፡መልሶ፦መልአኩን፡የላከ፥ከአምላካቸውም፡በቀር፡ማንም፡አምላክ፡እንዳያመልኩ፡ለርሱም፡እ ንዳይሰግዱ፡ሰውነታቸውን፡አሳልፈው፡የሰጡትን፡የንጉሡንም፡ቃል፡የተላለፉትን፡በርሱ፡የታመኑትን፡ባሪያዎቹ ን፡ያዳነ፥የሲድራቅና፡የሚሳቅ፡የዐብደናጎም፡አምላክ፡ይባረክ።
29፤እኔም፡እንደዚህ፡የሚያድን፡ሌላ፡አምላክ፡የለምና፡በሲድራቅና፡በሚሳቅ፡በዐብደናጎም፡አምላክ፡ላይ፡የስ ድብን፡ነገር፡የሚናገር፡ወገንና፡ሕዝብ፡በልዩ፡ልዩም፡ቋንቋ፡የሚናገሩ፡ይቈረጣሉ፥ቤቶቻቸውም፡የጕድፍ፡መጣ ያ፡ይደረጋሉ፡ብዬ፡አዝዣለኹ፡አለ።
30፤የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደናጎንም፡በባቢሎን፡አውራጃ፡ውስጥ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረጋቸ ው።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ከንጉሡ፡ከናቡከደነጾር፡በምድር፡ዅሉ፡ወደሚቀመጡ፡ወገኖችና፡አሕዛብ፡በልዩ፡ልዩ፡ቋንቋም፡ወደሚናገሩ፡ዅ ሉ፥ሰላም፡ይብዛላችኹ።
2፤ልዑል፡አምላክ፡በፊቴ፡ያደረገውን፡ተኣምራቱንና፡ድንቁን፡አሳያችኹ፡ዘንድ፡ወድጃለኹ።
3፤ተኣምራቱ፡እንዴት፡ታላቅ፡ነው! ድንቁም፡እንዴት፡ጽኑ፡ነው! መንግሥቱም፡የዘለዓለም፡መንግሥት፡ነው፥ግዛቱም፡ለልጅ፡ልጅ፡ነው።
4፤እኔ፡ናቡከደነጾር፡በቤቴ፡ደስ፡ብሎኝ፡በአዳራሼም፡ተመችቶኝ፡ነበር።
5፤ሕልም፡ዐለምኹ፤ርሷም፡አስፈራችኝ፤በዐልጋዬም፡ላይ፡የነበረው፡ዐሳቤና፡የራሴ፡ራእይ፡አስጨነቁኝ።
6፤ስለዚህ፥የሕልሙን፡ፍቺ፡እንዲያስታውቁኝ፡የባቢሎን፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ወደ፡እኔ፡ይገቡ፡ዘንድ፡አዘዝኹ።
7፤የዚያን፡ጊዜም፡የሕልም፡ተርጓሚዎቹና፡አስማተኛዎቹ፡ከለዳውያኑና፡ቃላ፟ተኛዎቹ፡ገቡ፤ሕልሙንም፡በፊታቸው ፡ተናገርኹ፥ፍቺውን፡ግን፡አላስታወቁኝም።
8፤በመጨረሻም፡የቅዱሳን፡አማልክት፡መንፈስ፡ያለበት፡እንደ፡አምላኬ፡ስም፡ብልጣሶር፡የሚባለው፡ዳንኤል፡በፊ ቴ፡ገባ፤እኔም፡ሕልሙን፡ነገርኹት፡እንዲህም፡አልኹት።
9፤የሕልም፡ተርጓሚዎች፡አለቃ፡ብልጣሶር፡ሆይ፥የቅዱሳን፡አማልክት፡መንፈስ፡ባንተ፡ውስጥ፡እንዳለ፥ከምስጢር ም፡ዅሉ፡የሚያስቸግርኽ፡እንደሌለ፡ዐውቄያለኹና፡ያለምኹትን፡የሕልሜን፡ራእይ፡ፍቺውንም፡ንገረኝ።
10፤የራሴ፡ራእይ፡በዐልጋዬ፡ላይ፡ይህ፡ነበረ፤እንሆ፥በምድር፡መካከል፡ዛፍ፡አየኹ፥ቁመቱም፡እጅግ፡ረዥም፡ነ በረ።
11፤ዛፉም፡ትልቅ፡ኾነ፥በረታም፥ቁመቱም፡እስከ፡ሰማይ፡ደረሰ፥መልኩም፡እስከምድር፡ዅሉ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ታየ።
12፤ቅጠሉም፦የተዋበ፡ነበረ፡ፍሬውም፡ብዙ፡ነበረ፥ለዅሉም፡መብል፡ነበረበት፤ከጥላውም፡በታች፡የምድር፡አራዊ ት፡ያርፉበት፡ነበር፥በቅርንጫፎቹም፡ውስጥ፡የሰማይ፡ወፎች፡ይቀመጡ፡ነበር፥ሥጋ፡ለባሹም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ይበላ ፡ነበር።
13፤በዐልጋዬም፡ላይ፡በራሴ፡ራእይ፡አየኹ፤እንሆም፥አንድ፡ቅዱስ፡ጠባቂ፡ከሰማይ፡ወረደ።
14፤በታላቅ፡ድምፅም፡እየጮኸ፡እንዲህ፡አለ፦ዛፉን፡ቍረጡ፥ቅርንጫፎቹንም፡ጨፍጭፉ፥ቅጠሎቹንም፡አራግፉ፥ፍሬ ውንም፡በትኑ፤አራዊትም፡ከበታቹ፡ወፎቹም፡ከቅርንጫፉ፡ይሽሹ።
15፤ነገር፡ግን፥ጕቶውን፡በምድር፡ውስጥ፡ተዉት፥በመስክም፡ውስጥ፡በብረትና፡በናስ፡ማሰሪያ፡ታስሮ፡ይቈይ፤በ ሰማይም፡ጠል፡ይረስርስ፡ዕድል፡ፈንታውም፡በምድር፡ሣር፡ውስጥ፡ከአራዊት፡ጋራ፡ይኹን።
16፤ልቡም፡ከሰው፡ልብ፡ይለወጥ፥የአውሬም፡ልብ፡ይሰጠው፤ሰባት፡ዘመናትም፡ይለፉበት።
17፤ልዑሉ፡በሰዎች፡መንግሥት፡ላይ፡እንዲሠለጥን፥ለወደደውም፡እንዲሰጠው፥ከሰውም፡የተዋረደውን፡እንዲሾምበ ት፡ሕያዋን፡ያውቁ፡ዘንድ፥ይህ፡ነገር፡የጠባቂዎች፡ትእዛዝ፥ይህም፡ፍርድ፡የቅዱሳን፡ቃል፡ነው።
18፤እኔ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ይህን፡ሕልም፡ዐልሜያለኹ፤አንተም፥ብልጣሶር፥ፍቺውን፡አስታውቀኝ፥የመንግሥቴ ፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ፍቺውን፡ያስታውቁኝ፡ዘንድ፡አይችሉምና፤ነገር፡ግን፥የቅዱሳን፡አማልክት፡መንፈስ፡ባንተ፡ው ስጥ፡አለና፡አንተ፡ትችላለኽ።
19፤የዚያን፡ጊዜ፡ብልጣሶር፡የተባለው፡ዳንኤል፡አንድ፡ሰዓት፡ያኽል፡ዐሰበ፥ልቡም፡ታወከ።ንጉሡም፡መልሶ፦ብ ልጣሶር፡ሆይ፥ሕልሙና፡ፍቺው፡አያስቸግርኽ፡አለው።ብልጣሶርም፡መልሶ፡አለ፦ጌታዬ፡ሆይ፥ሕልሙ፡ለሚጠሉኽ፥ፍ ቺውም፡ለጠላቶችኽ፡ይኹን።
20፤ትልቅ፡የነበረው፡የበረታውም፥ቁመቱም፡እስከ፡ሰማይ፡የደረሰው፥መልኩም፡እስከ፡ምድር፡ዅሉ፡ድረስ፡የታየ ው፥
21፤ቅጠሉም፡አምሮ፡የነበረው፥ፍሬውም፡የበዛው፥ለዅሉም፡መብል፡የነበረበት፤በበታቹም፡የምድር፡አራዊት፡የተ ቀመጡ፥በቅርንጫፎቹም፡የሰማይ፡ወፎች፡ያደሩበት፡ያየኸው፡ዛፍ፤
22፤ንጉሥ፡ሆይ፥ርሱ፡ታላቅና፡ብርቱ፡የኾንኽ፡አንተ፡ነኽ፤ታላቅነትኽ፡በዝቷል፥እስከ፡ሰማይም፡ደርሷል፥ግዛ ትኽም፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ነው።
23፤ንጉሡም፡ከሰማይ፡የወረደውንና፦ዛፉን፡ቍረጡ፥አጥፉትም፤ነገር፡ግን፥ጕቶውን፡በምድር፡ውስጥ፡ተዉት፤በብ ረትና፡በናስ፡ማሰሪያ፡ታስሮ፡በመስክ፡ውስጥ፡ይቈይ፤በሰማይም፡ጠል፡ይረስርስ፥ሰባት፡ዘመናትም፡እስኪያልፉ በት፡ድረስ፡ዕድል፡ፈንታው፡ከምድር፡አራዊት፡ጋራ፡ይኹን፡ያለውን፡ቅዱስ፡ጠባቂ፡ማየቱ፤ንጉሥ፡ሆይ፥ፍቺው፡ ይህ፡ነው፤
24፤በጌታዬ፡በንጉሥ፡ላይ፡የወረደው፡የልዑሉ፡ትእዛዝ፡ነው፤
25፤ልዑሉም፡በሰዎች፡መንግሥት፡ላይ፡እንዲሠለጥን፥ለሚወደ፟ውም፡እንዲሰጠው፡እስክታውቅ፡ድረስ፡ከሰዎች፡ተ ለይተኽ፡ትሰደዳለኽ፥መኖሪያኽም፡ከምድር፡አራዊት፡ጋራ፡ይኾናል፥እንደ፡በሬም፡ሣር፡ትበላ፡ዘንድ፡ትገደዳለ ኽ፥በሰማይም፡ጠል፡ትረሰርሳለኽ፥ሰባት፡ዘመናትም፡ያልፉብኻል።
26፤የዛፉንም፡ጕቶ፡ይተዉት፡ዘንድ፡ማዘዙ፥ሥልጣን፡ከሰማያት፡እንደ፡ኾነ፡ካወቅኽ፡በዃላ፡መንግሥትኽ፡ይቈይ ልኻል።
27፤ንጉሥ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ምናልባት፡የደኅንነትኽ፡ዘመን፡ይረዝም፡እንደ፡ኾነ፡ምክሬ፡ደስ፡ያሠኝኽ፤ኀጢአትኽ ንም፡በጽድቅ፥በደልኽንም፡ለድኻዎች፡በመመጽወት፡አስቀር።
28፤ይህ፡ዅሉ፡በንጉሡ፡በናቡከደነጾር፡ላይ፡ደረሰ።
29፤ከዐሥራ፡ኹለት፡ወር፡በዃላ፡በባቢሎን፡ቤተ፡መንግሥት፡ሰገነት፡ላይ፡ይመላለስ፡ነበር።
30፤ንጉሡም፦ይህች፡እኔ፡በጕልበቴ፡ብርታት፡ለግርማዬ፡ክብር፡የመንግሥት፡መኖሪያ፡እንድትኾን፡ያሠራዃት፡ታ ላቂቱ፡ባቢሎን፡አይደለችምን፧ብሎ፡ተናገረ።
31፤ቃሉም፡ገና፡በንጉሡ፡አፍ፡ሳለ፡ድምፅ፡ከሰማይ፡ወደቀና፦ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ሆይ፦መንግሥት፡ከአንተ፡ዘ ንድ፡ዐለፈች፡ተብሎ፡ለአንተ፡ተነግሯል፤
32፤ልዑሉም፡በሰዎች፡መንግሥት፡ላይ፡እንዲሠለጥን፥ለሚወደ፟ውም፡እንዲሰጠው፡እስክታውቅ፡ድረስ፡ከሰዎች፡ተ ለይተኽ፡ትሰደዳለኽ፥መኖሪያኽም፡ከምድር፡አራዊት፡ጋራ፡ይኾናል፤እንደ፡በሬም፡ሣር፡ትበላ፡ዘንድ፡ትገደዳለ ኽ፥ሰባት፡ዘመናትም፡ያልፉብኻል፡አለው።
33፤በዚያም፡ሰዓት፡ነገሩ፡በናቡከደነጾር፡ላይ፡ደረሰ፤ጠጕሩም፡እንደ፡ንስር፥ጥፍሩም፡እንደ፡ወፎች፡እስኪረ ዝም፡ድረስ፡ከሰዎች፡ተለይቶ፡ተሰደደ፥እንደ፡በሬም፡ሣር፡በላ፥አካሉም፡በሰማይ፡ጠል፡ረሰረሰ።
34፤ዘመኑም፡ከተፈጸመ፡በዃላ፡እኔ፡ናቡከደነጾር፡ዐይኔን፡ወደ፡ሰማይ፡አነሣኹ፥አእምሮዬም፡ተመለሰልኝ፤ልዑ ሉንም፡ባረክኹ፥ለዘለዓለምም፡የሚኖረውን፡አመሰገንኹ፡አከበርኹትም፤ግዛቱ፡የዘለዓለም፡ግዛት፡ነውና፥መንግ ሥቱም፡ለልጅ፡ልጅ፡ነውና።
35፤በምድርም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡እንደ፡ምናምን፡ይቈጠራሉ፤በሰማይም፡ሰራዊት፡በምድርም፡ላይ፡በሚኖሩ፡መካከል፡ እንደ፡ፈቃዱ፡ያደርጋል፤እጁንም፡የሚከለክላት፡ወይም፦ምን፡ታደርጋለኽ፧የሚለው፡የለም።
36፤በዚያን፡ጊዜም፡አእምሮዬ፡ተመለሰልኝ፥ለመንግሥቴም፡ክብር፡ግርማዬና፡ውበቴ፡ወደ፡እኔ፡ተመለሰ፤አማካሪ ዎቼና፡መኳንንቶቼም፡ፈለጉኝ፥በመንግሥቴም፡ውስጥ፡ጸናኹ፥ብዙም፡ክብር፡ተጨመረልኝ።
37፤አኹንም፡እኔ፡ናቡከደነጾር፡የሰማይን፡ንጉሥ፡አመሰግናለኹ፥ታላቅም፡አደርገዋለኹ፥አከብረውማለኹ።ሥራው ፡ዅሉ፡እውነት፥መንገዱም፡ፍርድ፡ነውና፥በትዕቢትም፡የሚኼዱትን፡ያዋርድ፡ዘንድ፡ይችላልና።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤ንጉሡ፡ብልጣሶር፡ለሺሕ፡መኳንንቶቹ፡ትልቅ፡ግብዣ፡አደረገ፥በሺሑም፡ፊት፡የወይን፡ጠጅ፡ይጠጣ፡ነበር።
2፤ብልጣሶርም፡የወይን፡ጠጅ፡በቀመሰ፡ጊዜ፡ንጉሡና፡መኳንንቶቹ፣ሚስቶቹና፡ቁባቶቹ፡ይጠጡባቸው፡ዘንድ፦አባቴ ፡ናቡከደነጾር፡በኢየሩሳሌም፡ከነበረው፡መቅደስ፡ያመጣቸውን፡የወርቁንና፡የብሩን፡ዕቃዎች፡አምጡ፡ብሎ፡አዘ ዘ።
3፤የዚያን፡ጊዜም፡በኢየሩሳሌም፡ከነበረው፡ከእግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅደስ፡የመጡትን፡የወርቁን፡ዕቃዎች፡አመጡ ፤ንጉሡና፡መኳንንቶቹም፡ሚስቶቹና፡ቁባቶቹም፡ጠጡባቸው።
4፤የወይን፡ጠጅም፡እየጠጡ፡ከወርቅና፡ከብር፣ከናስና፡ከብረት፣ከዕንጨትና፡ከድንጋይ፡የተሠሩትን፡አማልክት፡ አመሰገኑ።
5፤በዚያም፡ሰዓት፡የሰው፡እጅ፡ጣቶች፡ወጥተው፡በንጉሡ፡ቤት፡በተለሰነው፡ግንብ፡ላይ፡በመቅረዙ፡አንጻር፡ጻፉ ፤ንጉሡም፡የሚጽፉትን፡ጣቶች፡አየ።
6፤የዚያን፡ጊዜም፡የንጉሡ፡ፊት፡ተለወጠበት፥ዐሳቡም፡አስቸገረው፥የወገቡም፡ዥማቶች፡ተፈቱ፥ጕልበቶቹም፡ተብ ረከረኩ።
7፤ንጉሡም፡አስማተኛዎቹንና፡ከለዳውያኑን፣ቃላ፟ተኛዎቹንም፡ያገቡ፡ዘንድ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ፤ንጉሡም፡የባ ቢሎንን፡ጠቢባን፦ይህን፡ጽሕፈት፡ያነበበ፥ፍቺውንም፡ያሳየኝ፡ሐምራዊ፡ግምጃ፡ይለብሳል፥የወርቅም፡ማርዳ፡በ ዐንገቱ፡ዙሪያ፡ይኾንለታል፥በመንግሥትም፡ላይ፡ሦስተኛ፡ገዢ፡ይኾናል፡ብሎ፡ተናገረ።
8፤የዚያን፡ጊዜም፡የንጉሡ፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ገቡ፤ነገር፡ግን፥ጽሕፈቱን፡ያነቡ፟፥ፍቺውንም፡ለንጉሡ፡ያስታውቁ፡ ዘንድ፡አልቻሉም።
9፤ንጉሡም፡ብልጣሶር፡እጅግ፡ደነገጠ፥ፊቱም፡ተለወጠበት፥መኳንንቶቹም፡ተደናገጡ።
10፤ንግሥቲቱም፡ስለንጉሡና፡ስለመኳንንቱ፡ቃል፡ወደግብዣ፡ቤት፡ገባች፤ንግሥቲቱም፡ተናገረች፥እንዲህም፡አለ ች፦ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ፤ዐሳብኽ፡አያስቸግርኽ፥ፊትኽም፡አይለወጥ።
11፤የቅዱሳን፡አማልክት፡መንፈስ፡ያለበት፡ሰው፡በመንግሥትኽ፡ውስጥ፡አለ፤በአባትኽም፡ዘመን፡እንደ፡አማልክ ት፡ጥበብ፡ያለ፡ጥበብና፡ማስተዋል፡ዕውቀትም፡ተገኘበት፤አባትኽ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡የሕልም፡ተርጓሚዎችና ፡የአስማተኛዎች፣የከለዳውያንና፡የቃላ፟ተኛዎች፡አለቃ፡አደረገው።
12፤መልካም፡መንፈስ፣ዕውቀትም፣ማስተዋልም፣ሕልምንም፡መተርጐም፥እንቆቅልሽንም፡መግለጥ፥የተቋጠረውንም፡መ ፍታት፡ንጉሡ፡ስሙን፡ብልጣሶር፡ብሎ፡በሰየመው፡በዳንኤል፡ዘንድ፡ተገኝቷልና።አኹንም፡ዳንኤል፡ይጠራ፥ርሱም ፡ፍቺውን፡ያሳያል።
13፤የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡ወደንጉሡ፡ፊት፡ገባ፤ንጉሡም፡ተናገረው፥ዳንኤልንም፡እንዲህ፡አለው፦ንጉሡ፡አባ ቴ፡ከይሁዳ፡ከማረካቸው፣ከይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡የኾንኽ፡ዳንኤል፡አንተ፡ነኽን፧
14፤የአማልክት፡መንፈስ፡እንዳለብኽ፥ዕውቀትና፡ማስተዋልም፣መልካምም፡ጥበብ፡እንደ፡ተገኘብኽ፡ስለ፡አንተ፡ ሰምቻለኹ።
15፤አኹንም፡ይህን፡ጽሕፈት፡ያነቡ፟፡ዘንድ፥ፍቺውንም፡ያስታውቁኝ፡ዘንድ፥ጠቢባንና፡አስማተኛዎች፡ወደ፡እኔ ፡ገብተው፡ነበር፤ነገር፡ግን፥የነገሩን፡ፍቺ፡ያሳዩ፡ዘንድ፡አልቻሉም።
16፤አንተ፡ግን፡ፍቺን፡ትሰጥ፡ዘንድ፥የተቋጠረንም፡ትፈታ፡ዘንድ፡እንድትችል፡ሰምቻለኹ፤አኹንም፡ጽሕፈቱን፡ ታነብ፟፡ዘንድ፥ፍቺውንም፡ታስታውቀኝ፡ዘንድ፡ብትችል፥ሐምራዊ፡ግምጃ፡ትለብሳለኽ፥የወርቅም፡ማርዳ፡በዐንገ ትኽ፡ዙሪያ፡ይኾንልኻል፥አንተም፡በመንግሥት፡ላይ፡ሦስተኛ፡ገዢ፡ትኾናለኽ።
17፤የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡መለሰ፥በንጉሡም፡ፊት፡እንዲህ፡አለ፦ስጦታኽ፡ለአንተ፡ይኹን፥በረከትኽንም፡ለሌ ላ፡ስጥ፤ነገር፡ግን፥ጽሕፈቱን፡ለንጉሡ፡አነባ፟ለኹ፥ፍቺውንም፡አስታውቃለኹ።
18፤ንጉሥ፡ሆይ፥ልዑል፡አምላክ፡ለአባትኽ፡ለናቡከደነጾር፡መንግሥትንና፡ታላቅነትን፣ክብርንና፡ግርማን፡ሰጠ ው።
19፤ስለሰጠው፡ታላቅነት፡ወገኖችና፡አሕዛብ፣በልዩ፡ልዩም፡ቋንቋ፡የሚናገሩ፡ዅሉ፡በፊቱ፡ይንቀጠቀጡና፡ይፈሩ ፡ነበር፤የፈቀደውን፡ይገድል፥የፈቀደውንም፡በሕይወት፡ያኖር፡ነበር፤የፈቀደውንም፡ያነሣ፥የፈቀደውንም፡ያዋ ርድ፡ነበር።
20፤ልቡ፡ግን፡በታበየ፥በኵራትም፡ያደርግ፡ዘንድ፡መንፈሱ፡በጠነከረ፡ጊዜ፥ከመንግሥቱ፡ዙፋን፡ተዋረደ፥ክብሩ ም፡ተለየው።
21፤ልዑል፡አምላክም፡በሰዎች፡መንግሥት፡ላይ፡እንዲሠለጥን፥የሚወደ፟ውንም፡እንዲሾምበት፡እስኪያውቅ፡ድረስ ፡ከሰው፡ልጆች፡ተይለቶ፡ተሰደደ፤ልቡም፡እንደ፡አውሬ፡ልብ፡ኾነ፥መኖሪያውም፡ከምድረ፡በዳ፡አህያዎች፡ጋራ፡ ነበረ፤እንደ፡በሬ፡ሣር፡በላ፥አካሉም፡በሰማይ፡ጠል፡ረሰረሰ።
22፤ብልጣሶር፡ሆይ፥አንተ፡ልጁ፡ስትኾን፡ይህን፡ዅሉ፡እያወቅኽ፡በሰማይ፡ጌታ፡ላይ፡ኰራኽ፡እንጂ፡ልብኽን፡አ ላዋረድኽም።
23፤የመቅደሱንም፡ዕቃዎች፡በፊትኽ፡አመጡ፥አንተም፣መኳንንትኽም፣ሚስቶችኽም፣ቁባቶችኽም፡የወይን፡ጠጅ፡ጠጣ ችኹባቸው፤ከብርና፡ከወርቅም፣ከናስና፡ከብረትም፣ከዕንጨትና፡ከድንጋይም፡የተሠሩትን፥የማያዩትንም፥የማይሰ ሙትንም፥የማያውቁትንም፡አማልክት፡አመሰገንኽ፤ትንፋሽኽንና፡መንገድኽን፡ዅሉ፡በእጁ፡የያዘውን፡አምላክ፡አ ላከበርኸውም።
24፤ስለዚህም፡እነዚህ፡የእጅ፡ጣቶች፡ከርሱ፡ዘንድ፡ተልከዋል፤ይህም፡ጽሕፈት፡ተጽፏል።
25፤የተጻፈውም፡ጽሕፈት፦ማኔ፡ቴቄል፡ፋሬስ፡ይላል።
26፤የነገሩም፡ፍቺ፡ይህ፡ነው፤ማኔ፡ማለት፥እግዚአብሔር፡መንግሥትኽን፡ቈጠረው፥ፈጸመውም፡ማለት፡ነው።
27፤ቴቄል፡ማለት፥በሚዛን፡ተመዘንኽ፥ቀለ፟ኽም፡ተገኘኽ፡ማለት፡ነው።
28፤ፋሬስ፡ማለት፥መንግሥትኽ፡ተከፈለ፥ለሜዶንና፡ለፋርስ፡ሰዎችም፡ተሰጠ፡ማለት፡ነው።
29፤የዚያን፡ጊዜም፡ብልጣሶር፡ለዳንኤል፡ሐምራዊ፡ግምጃ፡እንዲያለብሱት፥የወርቅ፡ማርዳም፡በዐንገቱ፡ዙሪያ፡ እንዲያደርጉለት፡አዘዘ፤በመንግሥትም፡ላይ፡ሦስተኛ፡ገዢ፡እንዲኾን፡ዐዋጅ፡አስነገረ።
30፤በዚያ፡ሌሊት፡የከለዳውያን፡ንጉሥ፡ብልጣሶር፡ተገደለ።
31፤ሜዶናዊውም፡ዳርዮስ፡መንግሥቱን፡ወሰደ፤ዕድሜውም፡ስድሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ነበረ።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤ዳርዮስም፡በመንግሥቱ፡ዅሉ፡ዘንድ፡እንዲኾኑ፡መቶ፡ኻያ፡መሳፍንት፡በመንግሥቱ፡ላይ፡ይሾም፡ዘንድ፡ወደደ።
2፤መሳፍንቱም፡ሒሳቡን፡ያመጡላቸው፡ዘንድ፥ንጉሡም፡እንዳይጐ፟ዳ፥ሦስት፡አለቃዎች፡በላያቸው፡አደረገ፤ከነር ሱም፡አንደኛው፡ዳንኤል፡ነበረ።
3፤ዳንኤልም፡መልካም፡መንፈስ፡ስለ፡አለው፥ከአለቃዎችና፡ከመሳፍንት፡በለጠ፤ንጉሡም፡በመንግሥቱ፡ዅሉ፡ላይ፡ ይሾመው፡ዘንድ፡ዐሰበ።
4፤የዚያን፡ጊዜም፡አለቃዎችና፡መሳፍንቱ፡ስለ፡መንግሥቱ፡በዳንኤል፡ላይ፡ሰበብ፡ይፈልጉ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥ የታመነ፡ነበረና፥ስሕተትና፡በደልም፡አልተገኘበትምና፥በርሱ፡ላይ፡ሰበብና፡በደል፡ያገኙበት፡ዘንድ፡አልቻሉ ም።
5፤እነዚያም፡ሰዎች፦ከአምላኩ፡ሕግ፡በቀር፥በዚህ፡በዳንኤል፡ላይ፡ሌላ፡ሰበብ፡አናገኝበትም፡አሉ።
6፤የዚያን፡ጊዜም፡አለቃዎቹና፡መሳፍንቱ፡ወደ፡ንጉሡ፡ተሰብስበው፡እንዲህ፡አሉት፦ንጉሥ፡ዳርዮስ፡ሆይ፥ሺሕ፡ ዓመት፡ንገሥ።
7፤የመንግሥቱ፡አለቃዎች፡ዅሉ፣ሹማምቶችና፡መሳፍንት፣አማካሪዎችና፡አዛዦች፦ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡በቀር፡ማን ም፡እስከ፡ሠላሳ፡ቀን፡ድረስ፡ልመና፡ከአምላክ፡ወይም፡ከሰው፡ቢለምን፥በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡ይጣ፟ል ፥የሚል፡የንጉሥ፡ሕግና፡ብርቱ፡ትእዛዝ፡ይወጣ፡ዘንድ፡ተማከሩ።
8፤አኹንም፥ንጉሥ፡ሆይ፥እንደማይለወጠው፡እንደ፡ሜዶንና፡እንደ፡ፋርስ፡ሕግ፥እንዳይለወጥ፡ትእዛዙን፡አጽና፥ ጽሕፈቱንም፡ጻፍ።
9፤ንጉሡም፡ዳርዮስ፡ጽሕፈቱንና፡ትእዛዙን፡ጻፈ።
10፤ዳንኤልም፡ጽሕፈቱ፡እንደ፡ተጻፈ፡ባወቀ፡ጊዜ፥ወደ፡ቤቱ፡ገባ፤የዕልፍኙም፡መስኮቶች፡ወደኢየሩሳሌም፡አን ጻር፡ተከፍተው፡ነበር፤ቀድሞም፡ያደርግ፡እንደ፡ነበረ፥በየዕለቱ፡ሦስት፡ጊዜ፡በጕልበቱ፡ተንበርክኮ፡በአምላ ኩ፡ፊት፡ጸለየ፥አመሰገነም።
11፤እነዚያም፥ሰዎች፡ተሰብስበው፥ዳንኤል፡በአምላኩ፡ፊት፡ሲጸልይና፡ሲለምን፡አገኙት።
12፤ወደ፡ንጉሡም፡ቀርበው፥ስለንጉሡ፡ትእዛዝ፦ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡በቀር፡እስከ፡ሠላሳ፡ቀን፡ድረስ፡ከአምላ ክ፡ወይም፡ከሰው፡የሚለምን፡ሰው፡ዅሉ፡በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡እንዲጣል፡ትእዛዝ፡አልጻፍኽምን፧አሉት ።ንጉሡም፡መልሶ፦ነገሩ፡እንደማይለወጠው፡እንደ፡ሜዶንና፡እንደ፡ፋርስ፡ሕግ፡እውነት፡ነው፡አላቸው።
13፤የዚያን፡ጊዜም፡በንጉሡ፡ፊት፡መልሰው፦ንጉሥ፡ሆይ፥ከይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡የኾነው፡ዳንኤል፡በየዕለቱ፡ሦስ ት፡ጊዜ፡ልመናውን፡ይለምናል፡እንጂ፥አንተንና፡የጻፍኸውን፡ትእዛዝ፡አይቀበልም፡አሉት።
14፤ንጉሡም፡ይህን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡በጣም፡ዐዘነ፥ያድነውም፡ዘንድ፡ልቡን፡ወደ፡ዳንኤል፡አደረገ፤ሊያድነው ም፡ፀሓይ፡እስኪገባ፡ድረስ፡ደከመ።
15፤የዚያን፡ጊዜም፡እነዚያ፡ሰዎች፡ወደ፡ንጉሡ፡ተሰብስበው፡ንጉሡን፦ንጉሥ፡ሆይ፥ንጉሡ፡ያጸናው፡ትእዛዝ፡ወ ይም፡ሥርዐት፡ይለወጥ፡ዘንድ፡እንዳይገ፟ባ፟፡የሜዶንና፡የፋርስ፡ሕግ፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቅ፡አሉት።
16፤የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡አዘዘ፥ዳንኤልንም፡አምጥተው፡በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ጣሉት፤ንጉሡም፡ተናገረ፥ዳን ኤልንም፦ዅልጊዜ፡የምታመልከው፡አምላክኽ፡ርሱ፡ያድንኽ፡አለው።
17፤ድንጋይም፡አምጥተው፡በጕድጓዱ፡አፍ፡ላይ፡ገጠሙበት፤ንጉሡም፡በዳንኤል፡ላይ፡የተደረገው፡እንዳይለወጥ፡ በቀለበቱና፡በመኳንንቱ፡ቀለበት፡አተመው።
18፤ንጉሡም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ፥ሳይበላም፡ዐደረ፤መብልም፡አላመጡለትም፥እንቅልፉም፡ከርሱ፡ራቀ።
19፤በነጋውም፡ንጉሡ፡ማልዶ፡ተነሣ፥ፈጥኖም፡ወዳንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ኼደ።
20፤ወደ፡ጕድጓዱም፡ወደ፡ዳንኤል፡በቀረበ፡ጊዜ፥በሐዘን፡ቃል፡ጠራው፤ንጉሡም፡ተናገረ፥ዳንኤልንም፦የሕያው፡ አምላክ፡ባሪያ፡ዳንኤል፡ሆይ፥ዅልጊዜ፡የምታመልከው፡አምላክኽ፡ከአንበሳዎች፡ያድንኽ፡ዘንድ፡ችሏልን፧አለው ።
21፤ዳንኤልም፡ንጉሡን፦ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ።
22፤በፊቱ፡ቅንነት፡ተገኝቶብኛልና፥ባንተም፡ፊት፡ደግሞ፥ንጉሥ፡ሆይ፥አልበደልኹምና፥አምላኬ፡መልአኩን፡ልኮ ፡የአንበሳዎችን፡አፍ፡ዘጋ፥እነርሱም፡አልጐዱኝም፡አለው።
23፤የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡እጅግ፡ደስ፡አለው፥ዳንኤልንም፡ከጕድጓዱ፡ያወጡት፡ዘንድ፡አዘዘ፤ዳንኤልም፡ከጕድ ጓድ፡ወጣ፥በአምላኩም፡ታምኖ፡ነበርና፥አንዳች፡ጕዳት፡አልተገኘበትም።
24፤ንጉሡም፡አዘዘ፥ዳንኤልንም፡የከሰሱ፡እነዚያን፡ሰዎች፡አመጧቸው፥እነርሱንና፡ልጆቻቸውንም፣ሚስቶቻቸውን ም፡በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ጣሏቸው፤ወደጕድጓዱም፡መጨረሻ፡ሳይደርሱ፡አንበሳዎች፡ያዟቸው፥ዐጥንታቸውንም፡ዅ ሉ፡ሰባበሩ።
25፤የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሥ፡ዳርዮስ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ወደሚኖሩ፡ወገኖችና፡አሕዛብ፥በልዩ፡ልዩም፡ቋንቋ፡ወ ደሚናገሩ፡ዅሉ፡ጻፈ፥እንዲህም፡አለ፦ሰላም፡ይብዛላችኹ።
26፤በመንግሥቴ፡ግዛት፡ዅሉ፡ያሉ፡ሰዎች፡በዳንኤል፡አምላክ፡ፊት፡እንዲፈሩና፡እንዲንቀጠቀጡ፡አዝዣለኹ፤ርሱ ፡ሕያው፡አምላክ፡ለዘለዓለም፡የሚኖር፡ነውና፤መንግሥቱም፡የማይጠፋ፡ነው፥ግዛቱም፡እስከ፡መጨረሻ፡ድረስ፡ይ ኖራል።
27፤ያድናል፥ይታደግማል፤በሰማይና፡በምድርም፡ተኣምራትንና፡ድንቅን፡ይሠራል፤ዳንኤልንም፡ከአንበሳዎች፡አፍ ፡አድኖታል።
28፤ይህም፡ዳንኤል፡በዳርዮስ፡መንግሥትና፡በፋርሳዊው፡በቂሮስ፡መንግሥት፡ኑሮው፡ተቃናለት።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤በባቢሎን፡ንጉሥ፡በብልጣሶር፡በመዠመሪያው፡ዓመት፡ዳንኤል፡በዐልጋው፡ላይ፡ሕልምንና፡የራሱን፡ራእይ፡አየ ፤ከዚያም፡በዃላ፡ሕልሙን፡ጻፈ፥ዋነኛውንም፡ነገር፡ተናገረ።
2፤ዳንኤልም፡ተናገረ፡እንዲህም፡አለ፦በሌሊት፡በራእይ፡አየኹ፤እንሆም፥አራቱ፡የሰማይ፡ነፋሳት፡በታላቁ፡ባሕ ር፡ላይ፡ይጋጩ፡ነበር።
3፤አራትም፡ታላላቅ፡አራዊት፡ከባሕር፡ወጡ፥እያንዳንዲቱም፡ልዩ፡ልዩ፡ነበረች።
4፤መዠመሪያዪቱ፡አንበሳ፡ትመስል፡ነበር፥የንስርም፡ክንፍ፡ነበራት፤ክንፎቿም፡ከርሷ፡እስኪነቀሉ፡ድረስ፡አይ ፡ነበር፥ከምድርም፡ከፍ፡ከፍ፡ተደረገች፥እንደ፡ሰውም፡በኹለት፡እግር፡እንድትቆም፡ተደረገች፥የሰውም፡ልብ፡ ተሰጣት።
5፤እንሆም፥ኹለተኛዪቱ፡ድብ፡የምትመስል፡ሌላ፡አውሬ፡ነበረች፥ባንድ፡ወገንም፡ቆመች፥ሦስትም፡የጐድን፡ዐጥን ቶች፡በአፏ፡ውስጥ፡በጥርሷ፡መካከል፡ነበሩ፤እንደዚህም፦ተነሥተሽ፡እጅግ፡ሥጋ፡ብዪ፡ተባለላት።
6፤ከዚህም፡በዃላ፥እንሆ፥ነብር፡የምትመስል፡በዠርባዋም፡ላይ፡አራት፡የወፍ፡ክንፎች፡የነበሯት፡ሌላ፡አውሬ፡ አየኹ፤ለአውሬዪቱም፡አራት፡ራሶች፡ነበሯት፥ግዛትም፡ተሰጣት።
7፤ከዚህም፡በዃላ፡በሌሊት፡ራእይ፡አየኹ፤እንሆም፥የምታስፈራና፡የምታስደነግጥ፡እጅግም፡የበረታች፥ታላላቅም ፡የብረት፡ጥርሶች፡የነበሯት፡አራተኛ፡አውሬ፡ነበረች፤ትበላና፡ታደቅ፟፡ነበር፥የቀረውንም፡በእግሯ፡ትረግጥ ፡ነበር፤ከርሷም፡በፊት፡ከነበሩት፡አራዊት፡ዅሉ፡የተለየች፡ነበረች፤ዐሥር፡ቀንዶችም፡ነበሯት።
8፤ቀንዶችንም፡ተመለከትኹ፤እንሆም፥በመካከላቸው፡ሌላ፡ትንሽ፡ቀንድ፡ወጣ፥በፊቱም፡ከቀደሙት፡ቀንዶች፡ሦስት ፡ተነቃቀሉ፤እንሆም፥በዚያ፡ቀንድ፡እንደ፡ሰው፡ዐይኖች፡የነበሩ፡ዐይኖች፡በትዕቢትም፡የሚናገር፡አፍ፡ነበሩ በት።
9፤ዙፋኖችም፡እስኪዘረጉ፡ድረስ፡አየኹ፥በዘመናት፡የሸመገለውም፡ተቀመጠ፤ልብሱም፡እንደ፡በረዶ፡ነጭ፥የራሱም ፡ጠጕር፡እንደ፡ጥሩ፡ጥጥ፡ነበረ፤ዙፋኑም፡የእሳት፡ነበልባል፡ነበረ፥መንኰራኵሮቹም፡የሚነድ፟፡እሳት፡ነበሩ ።
10፤የእሳትም፡ፈሳሽ፡ከፊቱ፡ይፈልቅና፡ይወጣ፡ነበር፤ሺሕ፡ጊዜ፡ሺሕ፡ያገለግሉት፡ነበር፥እልፍ፡አእላፋትም፡ በፊቱ፡ቆመው፡ነበር፤ፍርድም፡ኾነ፥መጻሕፍትም፡ተገለጡ።
11፤የዚያን፡ጊዜም፡ቀንዱ፡ይናገረው፡ከነበረው፡ከታላቁ፡ቃል፡ድምፅ፡የተነሣ፡አየኹ፤አውሬዪቱም፡እስክትገደ ል፥አካሏም፡እስኪጠፋ፡ድረስ፥በእሳትም፡ለመቃጠል፡እስክትሰጥ፡ድረስ፡አየኹ።
12፤ከቀሩትም፡አራዊት፡ግዛታቸው፡ተወሰደ፤የሕይወታቸው፡ዕድሜ፡ግን፡እስከ፡ዘመንና፡እስከ፡ጊዜ፡ድረስ፡ረዘ መ።
13፤በሌሊት፡ራእይ፡አየኹ፤እንሆም፥የሰው፡ልጅ፡የሚመስል፡ከሰማይ፡ደመናት፡ጋራ፡መጣ፡በዘመናት፡ወደሸመገለ ውም፡ደረሰ፤ወደ፡ፊቱም፡አቀረቡት።
14፤ወገኖችና፡አሕዛብ፡በልዩ፡ልዩ፡ቋንቋም፡የሚናገሩ፡ዅሉ፡ይገዙለት፡ዘንድ፡ግዛትና፡ክብር፡መንግሥትም፡ተ ሰጠው፤ግዛቱም፡የማያልፍ፡የዘለዓለም፡ግዛት፡ነው፥መንግሥቱም፡የማይጠፋ፡ነው።
15፤በእኔም፡በዳንኤል፡በሥጋዬ፡ውስጥ፡መንፈሴ፡ደነገጠች፥የራሴም፡ራእይ፡አስቸገረኝ።
16፤በዚያም፡ከቆሙት፡ወደ፡አንዱ፡ቀርቤ፡ስለዚህ፡ዅሉ፡እውነቱን፡ጠየቅኹት፤ርሱም፡ነገረኝ፥የነገሩንም፡ፍቺ ፡አስታወቀኝ።
17፤እነዚህ፡አራቱ፡ታላላቅ፡አራዊት፡ከምድር፡የሚነሡ፡አራት፡ነገሥታት፡ናቸው።
18፤ነገር፡ግን፥የልዑሉ፡ቅዱሳን፡መንግሥቱን፡ይወስዳሉ፥እስከ፡ዘለዓለም፡ዓለምም፡መንግሥቱን፡ይወርሳሉ።
19፤ከዚህም፡በዃላ፡ከቀሩት፡ዅሉ፡ተለይታ፡እጅግ፡ስለምታስፈራው፥ጥርሶቿም፡የብረት፡ጥፍራዎቿም፡የናስ፡ስለ ኾኑት፥ስለምትበላውና፡ስለምታደቀ፟ው፡የቀረውንም፡በእግሯ፡ስለምትረግጠው፡ስለ፡አራተኛዪቱ፡አውሬ፥
20፤በራሷም፡ላይ፡ስለነበሩ፡ስለ፡ዐሥር፡ቀንዶች፥በዃላም፡ስለ፡ወጣው፥በፊቱም፡ሦስቱ፡ስለ፡ወደቁ፥ዐይኖችና ፡ትዕቢት፡የተናገረ፡አፍ፡ስለ፡ነበሩት፥መልኩም፡ከሌላዎች፡ስለ፡በለጠ፡ስለ፡ሌላው፡ቀንድ፡እውነቱን፡ለማወ ቅ፡ፈቀድኹ።
21፤እንሆም፥ያ፡ቀንድ፡ከቅዱሳን፡ጋራ፡ሲዋጋ፡አየኹ፥
22፤በዘመናት፡የሸመገለው፡እስኪመጣ፡ድረስ፥ፍርድም፡ለልዑሉ፡ቅዱሳን፡እስኪሰጥ፡ድረስ፥ቅዱሳኑም፡መንግሥቱ ን፡የሚወስዱበት፡ዘመን፡እስኪመጣ፡ድረስ፡አሸነፋቸውም።
23፤እንዲህም፡አለ፦አራተኛዪቱ፡አውሬ፡በምድር፡ላይ፡አራተኛ፡መንግሥት፡ትኾናለች፤ርሱም፡ከመንግሥታት፡ዅሉ ፡የተለየ፡ይኾናል፥ምድሪቱንም፡ዅሉ፡ይበላል፥ይረግጣታል፡ያደቃ፟ትማል።
24፤ዐሥሩም፡ቀንዶች፡ከዚያ፡መንግሥት፡የሚነሡ፡ዐሥር፡ነገሥታት፡ናቸው፤ከነርሱም፡በዃላ፡ሌላ፡ይነሣል፥ርሱ ም፡ከፊተኛዎች፡የተለየ፡ይኾናል፥ሦስቱንም፡ነገሥታት፡ያዋርዳል።
25፤በልዑሉም፡ላይ፡ቃልን፡ይናገራል፥የልዑልንም፡ቅዱሳን፡ይሰባብራል፥ዘመናትንና፡ሕግን፡ይለውጥ፡ዘንድ፡ያ ስባል፤እስከ፡ዘመንና፡እስከ፡ዘመናት፡እስከ፡እኩሌታ፡ዘመንም፡በእጁ፡ይሰጣሉ።
26፤ነገር፡ግን፥ፍርድ፡ይኾናል፥እስከ፡ፍጻሜም፡ድረስ፡ያፈርሱትና፡ያጠፉት፡ዘንድ፡ግዛቱን፡ያስወግዱታል።
27፤መንግሥትም፡ግዛትም፡ከሰማይም፡ዅሉ፡በታች፡ያሉ፡የመንግሥታት፡ታላቅነት፡ለልዑሉ፡ቅዱሳን፡ሕዝብ፡ይሰጣ ል፤መንግሥቱ፡የዘለዓለም፡መንግሥት፡ነው፥ግዛቶችም፡ዅሉ፡ይገዙለታል፡ይታዘዙለትማል።
28፤የነገሩም፡ፍጻሜ፡እስከዚህ፡ድረስ፡ነው።እኔም፡ዳንኤል፡በዐሳቤ፡እጅግ፡ተቸገርኹ፥ፊቴም፡ተለወጠብኝ፤ዳ ሩ፡ግን፡ነገሩን፡በልቤ፡ጠብቄያለኹ።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤በመዠመሪያ፡ከተገለጠልኝ፡ራእይ፡በዃላ፥ንጉሡ፡ብልጣሶር፡በነገሠ፡በሦስተኛው፡ዓመት፥ለእኔ፡ለዳንኤል፡ራ እይ፡ተገለጠልኝ።
2፤በራእዩም፡አየኹ፤ባየኹም፡ጊዜ፡በዔላም፡አውራጃ፡ባለው፡በሱሳ፡ግንብ፡ነበርኹ፤በራእዩም፡አየኹ፡በኡባል፡ ወንዝም፡አጠገብ፡ነበርኹ።
3፤ዐይኔን፡አንሥቼ፡አየኹ፤እንሆም፥ኹለት፡ቀንዶች፡የነበሩት፡አንድ፡አውራ፡በግ፡በወንዙ፡ፊት፡ቆሞ፡ነበር፥ ኹለቱም፡ቀንዶቹ፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ፡ነበር፤አንዱ፡ግን፡ከኹለተኛው፡ከፍ፡ያለ፡ነበረ፥ታላቁም፡ወደ፡ዃላው፡ወጥ ቶ፡ነበር።
4፤አውራውም፡በግ፡ወደ፡ምዕራብ፡ወደ፡ሰሜንም፡ወደ፡ደቡብም፡በቀንዱ፡ሲጐሽም፡አየኹ፤አራዊትም፡ዅሉ፡ይቋቋሙ ት፡ዘንድ፡አልቻሉም፥ከእጁም፡የሚያድን፡አልነበረም፤እንደ፡ፈቃዱም፡አደረገ፥ራሱንም፡ታላቅ፡አደረገ።
5፤እኔም፡ስመለከት፥እንሆ፥ከምዕራብ፡ወገን፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡በምድር፡ዅሉ፡ፊት፡ላይ፡ወጣ፥ምድርንም፡አ ልነካም፤ለፍየሉም፡በዐይኖቹ፡መካከል፡አንድ፡ታላቅ፡ቀንድ፡ነበረው።
6፤ኹለትም፡ቀንድ፡ወዳለው፡በወንዝም፡ፊት፡ቆሞ፡ወዳየኹት፡አውራ፡በግ፡መጣ፥በኀይሉም፡ቍጣ፡ፈጥኖ፡ወደ፡ርሱ ፡ሮጠ።
7፤ወደ፡አውራውም፡በግ፡ሲቀርብ፡አየኹት፤ርሱም፡ተመረረበት፥አውራውንም፡በግ፡መታ፥ኹለቱንም፡ቀንዶች፡ሰበረ ፤አውራውም፡በግ፡ሊቋቋመው፡ኀይል፡አልነበረውም፥ርሱም፡በምድር፡ላይ፡ጥሎ፡ረገጠው፤አውራውንም፡በግ፡ከእጁ ፡ያድነው፡ዘንድ፡የሚችል፡አልነበረም።
8፤አውራውም፡ፍየል፡ራሱን፡እጅግ፡ታላቅ፡አደረገ፤በበረታም፡ጊዜ፡ታላቁ፡ቀንዱ፡ተሰበረ፥ወደ፡አራቱም፡የሰማ ይ፡ነፋሳት፡የሚመለከቱ፡አራት፡ቀንዶች፡ከበታቹ፡ወጡ።
9፤ከነርሱም፡ከአንደኛው፡አንድ፡ታናሽ፡ቀንድ፡ወጣ፥ወደ፡ደቡብም፡ወደ፡ምሥራቅም፡ወደ፡መልካሚቱም፡ምድር፡እ ጅግ፡ከፍ፡አለ።
10፤እስከሰማይም፡ሰራዊት፡ድረስ፡ከፍ፡አለ፤ከሰራዊትና፡ከከዋክብትም፡ዐያሌዎችን፡ወደ፡ምድር፡ጣለ፥ረገጣቸ ውም።
11፤እስከሰራዊትም፡አለቃ፡ድረስ፡ራሱን፡ታላቅ፡አደረገ፤ከርሱም፡የተነሣ፡የዘወትሩ፡መሥዋዕት፡ተሻረ፥የመቅ ደሱም፡ስፍራ፡ፈረሰ።
12፤ሰራዊቱም፡ከኀጢአት፡የተነሣ፡ከዘወትሩ፡መሥዋዕት፡ጋራ፡ተሰጠው፤ርሱም፡እውነትን፡ወደ፡ምድሩ፡ጣለ፥አደ ረገም፡ተከናወነም።
13፤ከቅዱሳኑም፡አንዱ፡ሲናገር፡ሰማኹ፤ለተናገረው፡ለቅዱሱም፡ኹለተኛው፡ቅዱስ፦ስለዘወትሩ፡መሥዋዕት፥መቅደ ሱና፡ሰራዊቱም፡ይረገጡ፡ዘንድ፡ስለሚሰጥና፡ስለሚያጠፋ፡ኀጢአት፡የኾነው፡ራእይ፡እስከ፡መቼ፡ይኾናል፧አለው ።
14፤ርሱም፦እስከ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ማታና፡ጧት፡ድረስ፡ነው፤ከዚያም፡በዃላ፡መቅደሱ፡ይነጻል፡አለኝ።
15፤እኔም፡ዳንኤል፡ራእዩን፡ባየኹ፡ጊዜ፡ማስተዋሉን፡ፈለግኹ፤እንሆም፥የሰው፡ምስያ፡በፊቴ፡ቆሞ፡ነበር።
16፤በኡባልም፡ወንዝ፡መካከል፦ገብርኤል፡ሆይ፥ራእዩን፡ለዚህ፡ሰው፡አስታውቀው፡ብሎ፡የሚጮኸውን፡የሰውን፡ድ ምፅ፡ሰማኹ።
17፤እኔም፡ወደ፡ቆምኹበት፡ቀረበ፤በመጣም፡ጊዜ፡ፈርቼ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ራእዩ፡ለ ፍጻሜ፡ዘመን፡እንደ፡ኾነ፡አስተውል፡አለኝ።
18፤ሲናገረኝም፡ደንግጬ፡በምድር፡ላይ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ፤ርሱም፡ዳሰሰኝ፡ቀጥ፡አድርጎም፡አቆመኝ።
19፤እንዲህም፡አለኝ፦እንሆ፥በመቅሠፍቱ፡በመጨረሻ፡ዘመን፡የሚኾነውን፡አስታውቅኻለኹ፤ይህ፡ለተወሰነው፡ለፍ ጻሜ፡ዘመን፡ነውና።
20፤ባየኸው፡በአውራው፡በግ፡ላይ፡የነበሩ፡ኹለቱ፡ቀንዶች፡እነርሱ፡የሜዶንና፡የፋርስ፡ነገሥታት፡ናቸው።
21፤አውራውም፡ፍየል፡የግሪክ፡ንጉሥ፡ነው፤በዐይኖቹም፡መካከል፡ያለው፡ታላቁ፡ቀንድ፡መዠመሪያው፡ንጉሥ፡ነው ።
22፤ርሱም፡በተሰበረ፡ጊዜ፡በርሱ፡ፋንታ፡አራቱ፡እንደ፡ተነሡ፥እንዲሁ፡ከወገኑ፡አራት፡መንግሥታት፡ይነሣሉ፥ ነገር፡ግን፥በኀይል፡አይተካከሉትም።
23፤በመንግሥታቸውም፡መጨረሻ፥ኀጢአታቸው፡በተሞላች፡ጊዜ፥እንቆቅልሽን፡የሚያስተውል፡ፊተ፡ጨካኝ፡ንጉሥ፡ይ ነሣል።
24፤ኀይሉም፡ይበረታል፥ነገር፡ግን፥በራሱ፡ኀይል፡አይደለም፤በድንቅም፡ያጠፋል፥ያደርግማል፥ይከናወንማል፤ኀ ያላንንና፡የቅዱሳንን፡ሕዝብ፡ያጠፋል።
25፤በመታለሉ፡ተንኰልን፡በእጁ፡ያከናውናል፤በልቡም፡ይታበያል፥ታምነውም፡የሚኖሩትን፡ብዙዎችን፡ያጠፋል፤በ አለቃዎቹም፡አለቃ፡ላይ፡ይቋቋማል፤ያለ፡እጅም፡ይሰበራል።
26፤የተነገረውም፡የማታውና፡የጧቱ፡ራእይ፡እውነተኛ፡ነው፤ነገር፡ግን፥ከብዙ፡ዘመን፡በዃላ፡ስለሚኾን፡ራእዩ ን፡ዝጋ።
27፤እኔም፡ዳንኤል፡ተኛኹ፥ዐያሌም፡ቀን፡ታመምኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡ተነሥቼ፡የንጉሡን፡ሥራ፡እሠራ፡ነበር፤ስለ ፡ራእዩም፡አደንቅ፡ነበር፥የሚያስተውለው፡ግን፡አልነበረም።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤በከለዳውያን፡መንግሥት፡ላይ፡በነገሠ፥ከሜዶን፡ዘር፡በነበረ፡በአሕሻዊሮስ፡ልጅ፡በዳርዮስ፡በመዠመሪያ፡ዓ መት፥
2፤በነገሠ፡በመዠመሪያው፡ዓመት፡እኔ፡ዳንኤል፡የኢየሩሳሌም፡መፍረስ፡የሚፈጸምበትን፡ሰባውን፡ዓመት፥እግዚአ ብሔር፡በቃሉ፡ለነቢዩ፡ለኤርምያስ፡የተናገረውን፡የዓመቱን፡ቍጥር፡በመጽሐፍ፡አስተዋልኹ።
3፤ማቅ፡ለብሼ፡በዐመድም፡ላይ፡ኾኜ፡ስጾም፡እጸልይና፡እለምን፡ዘንድ፡ፊቴን፡ወደ፡ጌታ፡ወደ፡አምላክ፡አቀናኹ ።
4፤ወደ፡አምላኬም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለይኹ፥ተናዝዤም፡እንዲህ፡አልኹ፦ጌታ፡ሆይ፥ከሚወዱኽና፡ትእዛዝኽን፡ ከሚፈጽሙ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረትን፡የምትጠብቅ፡ታላቅና፡የምታስፈራ፡አምላክ፡ሆይ፥
5፤ኀጢአትን፡ሠርተናል፥በድለንማል፥ክፋትንም፡አድርገናል፥ዐምፀንማል፥ከትእዛዝኽና፡ከፍርድኽም፡ፈቀቅ፡ብለ ናል፤
6፤በስምኽም፡ለነገሥታታችንና፡ለአለቃዎቻችን፡ለአባቶቻችንም፡ለአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የተናገሩትን፡ባሪያዎች ኽን፡ነቢያትን፡አልሰማንም።
7፤ጌታ፡ሆይ፥ጽድቅ፡ለአንተ፡ነው፤እንደ፡ዛሬም፡ለእኛ፡ለይሁዳ፡ሰዎችና፡በኢየሩሳሌም፡ለሚቀመጡ፡ለእስራኤል ም፡ዅሉ፡በቅርብና፡በሩቅም፡ላሉት፡አንተን፡በበደሉበት፡በበደላቸው፡ምክንያት፡በበተንኽበት፡አገር፡ዅሉ፡የ ፊት፡ዕፍረት፡ነው።
8፤ጌታ፡ሆይ፥ባንተ፡ላይ፡ኀጢአት፡ስለ፡ሠራን፡ለእኛና፡ለነገሥታታችን፡ለአለቃዎቻችንና፡ለአባቶቻችንም፡የፊ ት፡ዕፍረት፡ነው።
9፤10፤በርሱ፡ላይ፡ምንም፡እንኳ፡ያመፅን፡ብንኾን፥በባሪያዎቹም፡በነቢያት፡እጅ፡በፊታችን፡ባኖረው፡በሕጉ፡ እንኼድ፡ዘንድ፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ምንም፡እንኳ፡ባንሰማ፥ለጌታ፡ለአምላካችን፡ምሕረትና ፡ይቅርታ፡ነው።
11፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ሕግኽን፡ተላልፈዋል፥ቃልኽንም፡እንዳይሰሙ፡ፈቀቅ፡ብለዋል፤በርሱ፡ላይ፡ኀጢአት፡ሠርተ ናልና፥በእግዚአብሔር፡ባሪያ፡በሙሴ፡ሕግ፡የተጻፈው፡መሐላና፡ርግማን፡ፈሰሰብን።
12፤እጅግ፡ክፉ፡ነገርንም፡በእኛ፡ላይ፡በማምጣቱ፡በላያችንና፡በእኛ፡ዘንድ፡በተሾሙት፡ፈራጆቻችን፡ላይ፡የተ ናገረውን፡ቃል፡አጸና፤በኢየሩሳሌምም፡ላይ፡እንደተደረገው፡ያለ፡ነገር፡ከቶ፡ከሰማይ፡ዅሉ፡በታች፡አልተደረ ገም።
13፤በሙሴም፡ሕግ፡እንደ፡ተጻፈ፡ይህ፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡መጣብን፤ከኀጢአታችንም፡እንመለስ፡እውነትኽንም፡እና ስብ፡ዘንድ፡ወደአምላካችን፡ወደእግዚአብሔር፡ፊት፡አልለመንንም።
14፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡ክፉ፡ነገሩን፡ጠብቆ፡በእኛ፡ላይ፡አመጣ፤አምላካችን፡እግዚአብሔር፡በሚሠራው፡ሥ ራ፡ዅሉ፡ጻድቅ፡ነውና፥እኛም፡ቃሉን፡አልሰማንምና።
15፤አኹንም፡ሕዝብኽን፡ከግብጽ፡ምድር፡በበረታች፡እጅ፡ያወጣኽ፥እንደ፡ዛሬም፡ቀን፡ዝና፡ለአንተ፡ያገኘኽ፡ጌ ታ፡አምላካችን፡ሆይ፥ኀጢአትን፡ሠርተናል፥ክፋትንም፡አድርገናል።
16፤ጌታ፡ሆይ፥ስለ፡ኀጢአታችንና፡ስላባቶቻችን፡በደል፡ኢየሩሳሌምና፡ሕዝብኽ፡በዙሪያችን፡ላሉት፡ዅሉ፡መሰደ ቢያ፡ኾነዋልና፥እንደ፡ጽድቅኽ፡ዅሉ፡ቍጣኽና፡መዓትኽ፡ከከተማኽ፡ከኢየሩሳሌም፡ከቅዱስ፡ተራራኽ፡እንዲመለስ ፡እለምንኻለኹ።
17፤አኹንም፥አምላካችን፡ሆይ፥የባሪያኽን፡ጸሎትና፡ልመናውን፡ስማ፤ጌታ፡ሆይ፥በፈረሰው፡በመቅደስኽ፡ላይ፡ስ ለ፡አንተ፡ስትል፡ፊትኽን፡አብራ።
18፤አምላኬ፡ሆይ፥በፊትኽ፡የምንለምን፡ስለ፡ብዙ፡ምሕረትኽ፡ነው፡እንጂ፡ስለ፡ጽድቃችን፡አይደለምና፡ዦሮኽን ፡አዘንብለኽ፡ስማ፤ዐይንኽን፡ገልጠኽ፡ጥፋታችንና፡ስምኽ፡የተጠራባትን፡ከተማ፡ተመልከት።
19፤አቤቱ፥ስማ፤አቤቱ፥ይቅር፡በል፤አቤቱ፥አድምጥና፡አድርግ፤አምላኬ፡ሆይ፥ስምኽ፡በከተማኽና፡በሕዝብኽ፡ላ ይ፡ተጠርቷልና፥ስለ፡ራስኽ፡አትዘግይ።
20፤እኔም፡ገና፡ስናገር፡ስጸልይ፥በኀጢአቴና፡በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ኀጢአት፡ስናዘዝ፥በአምላኬም፡በእግዚአ ብሔር፡ፊት፡ስለተቀደሰው፡ስለአምላኬ፡ተራራ፡ስለምን፥
21፤ገናም፡በጸሎት፡ስናገር፡አስቀድሜ፡በራእይ፡አይቼው፡የነበረው፡ሰው፡ገብርኤል፥እንሆ፥እየበረረ፡መጣ፤በ ማታም፡መሥዋዕት፡ጊዜ፡ዳሰሰኝ።
22፤አስተማረኝም፥ተናገረኝም፡እንዲህም፡አለ፦ዳንኤል፡ሆይ፥ጥበብንና፡ማስተዋልን፡እሰጥኽ፡ዘንድ፡አኹን፡መ ጥቻለኹ።
23፤አንተ፡እጅግ፡የተወደድኽ፡ነኽና፥በልመናኽ፡መዠመሪያ፡ላይ፡ትእዛዝ፡ወጥቷል፥እኔም፡እነግርኽ፡ዘንድ፡መ ጥቻለኹ፤አኹንም፡ነገሩን፡መርምር፥ራእዩንም፡አስተውል።
24፤ዐመፃን፡ይጨርስ፥ኀጢአትንም፡ይፈጽም፥በደልንም፡ያስተሰርይ፥የዘለዓለምን፡ጽድቅ፡ያገባ፥ራእይንና፡ትን ቢትን፡ያትም፥ቅዱሰ፡ቅዱሳኑንም፡ይቀባ፡ዘንድ፡በሕዝብኽና፡በቅድስት፡ከተማኽ፡ላይ፡ሰባ፡ሱባዔ፡ተቀጥሯል።
25፤ስለዚህ፥ዕወቅ፡አስተውልም፤ኢየሩሳሌምን፡መጠገንና፡መሥራት፡ትእዛዙ፡ከሚወጣበት፡ዠምሮ፡እስከ፡አለቃው ፡እስከ፡መሲሕ፡ድረስ፡ሰባት፡ሱባዔና፡ስድሳ፡ኹለት፡ሱባዔ፡ይኾናል፤ርሷም፡በጭንቀት፡ዘመን፡ከጐዳናና፡ከቅ ጥር፡ጋራ፡ትሠራለች።
26፤ከስድሳ፡ኹለት፡ጊዜ፡ሰባትም፡በዃላ፡መሲሕ፡ይገደላል፥በርሱም፡ዘንድ፡ምንም፡የለም፤የሚመጣውም፡አለቃ፡ ሕዝብ፡ከተማዪቱንና፡መቅደሱን፡ያጠፋሉ፤ፍጻሜውም፡በጐርፍ፡ይኾናል፥እስከ፡መጨረሻም፡ድረስ፡ጦርነት፡ይኾና ል፤ጥፋትም፡ተቀጥሯል።
27፤ርሱም፡ከብዙ፡ሰዎች፡ጋራ፡ጽኑ፡ቃል፡ኪዳን፡ላንድ፡ሱባዔ፡ያደርጋል፤በሱባዔውም፡እኩሌታ፡መሥዋዕቱንና፡ ቍርባኑን፡ያስቀራል፤በርኵሰትም፡ጫፍ፡ላይ፡አጥፊው፡ይመጣል፤እስከተቈረጠውም፡ፍጻሜ፡ድረስ፡መቅሠፍት፡በአ ጥፊው፡ላይ፡ይፈሳ፟ል።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤በፋርስ፡ንጉሥ፡በቂሮስ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡ብልጣሶር፡ለተባለው፡ለዳንኤል፡ነገር፡ተገለጠለት፤ነገሩም፡እ ውነት፡ነበረ፥ርሱም፡ታላቅ፡ጦርነት፡ነው፤ነገሩንም፡አስተዋለ፥በራእዩም፡ውስጥ፡ማስተዋል፡ተሰጠው።
2፤በዚያም፡ወራት፡እኔ፡ዳንኤል፡ሦስት፡ሳምንት፡ሙሉ፡ሳዝን፡ነበር።
3፤ማለፊያ፡እንጀራም፡አልበላኹም፥ሥጋና፡ጠጅም፡በአፌ፡አልገባም፥ሦስቱም፡ሳምንት፡እስኪፈጸም፡ድረስ፡ዘይት ፡አልተቀባኹም።
4፤ከመዠመሪያውም፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡ጤግሮስ፡በተባለው፡በታላቁ፡ወንዝ፡አጠገብ፡ሳለኹ፥ዐይኔን፡አ ነሣኹ፥
5፤እንሆም፥በፍታ፡የለበሰውን፡ጥሩም፡የአፌዝን፡ወርቅ፡በወገቡ፡ላይ፡የታጠቀውን፡ሰው፡አየኹ።
6፤አካሉም፡እንደ፡ቢረሌ፡ይመስል፡ነበር፥ፊቱም፡እንደ፡መብረቅ፡ምስያ፡ነበረ፥ዐይኖቹም፡እንደሚንበለበል፡ፋ ና፥ክንዶቹና፡እግሮቹም፡እንደ፡ጋለ፡ናስ፥የቃሉም፡ድምፅ፡እንደ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ድምፅ፡ነበረ።
7፤እኔም፡ዳንኤል፡ብቻዬን፡ራእዩን፡አየኹ፥ከእኔ፡ጋራ፡የነበሩ፡ሰዎች፡ግን፡ራእዩን፡አላዩም፤ነገር፡ግን፥ጽ ኑ፡መንቀጥቀጥ፡ወደቀባቸው፥ሊሸሸጉም፡ሸሹ።
8፤እኔም፡ብቻዬን፡ቀረኹ፡ይህንም፡ታላቅ፡ራእይ፡አየኹ፤ኀይልም፡አልቀረልኝም፥ደም፡ግባቴም፡ወደ፡ማሸብሸብ፡ ተለወጠብኝ፥ኀይልም፡ዐጣኹ።
9፤የቃሉንም፡ድምፅ፡ሰማኹ፤የቃሉንም፡ድምፅ፡በሰማኹ፡ጊዜ፡ደንግጬ፡በምድር፡ላይ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ።
10፤እንሆም፥አንዲት፡እጅ፡ዳሰሰችኝ፥በጕልበቴና፡በእጄም፡አቆመችኝ።
11፤ርሱም፦እጅግ፡የተወደድኽ፡ሰው፡ዳንኤል፡ሆይ፥እኔ፡ዛሬ፡ወዳንተ፡ተልኬያለኹና፡የምነግርኽን፡ቃል፡አስተ ውል፥ቀጥ፡ብለኽም፡ቁም፡አለኝ።ይህንም፡ቃል፡ባለኝ፡ጊዜ፡እየተንቀጠቀጥኹ፡ቆምኹ።
12፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ዳንኤል፡ሆይ፥አትፍራ፤ልብኽ፡ያስተውል፡ዘንድ፥ሰውነትኽም፡በአምላክኽ፡ፊት፡ይዋ ረድ፡ዘንድ፡ካደረግኽበት፡ከመዠመሪያው፡ቀን፡ዠምሮ፡ቃልኽ፡ተሰምቷል፤እኔም፡ስለ፡ቃልኽ፡መጥቻለኹ።
13፤የፋርስ፡መንግሥት፡አለቃ፡ግን፡ኻያ፡አንድ፡ቀን፡ተቋቋመኝ፤እንሆም፥ከዋነኛዎቹ፡አለቃዎች፡አንዱ፡ሚካኤ ል፡ሊረዳኝ፡መጣ፤እኔም፡ከፋርስ፡ነገሥታት፡ጋራ፡በዚያ፡ተውኹት።
14፤ራእዩም፡ገና፡ለብዙ፡ዘመን፡ነውና፥በዃለኛው፡ዘመን፡ለሕዝብኽ፡የሚኾነውን፡አስታውቅኽ፡ዘንድ፡አኹን፡መ ጥቻለኹ።
15፤ይህንም፡ቃል፡በተናገረኝ፡ጊዜ፡ፊቴን፡ወደ፡ምድር፡አቀረቀርኹ፥ዲዳም፡ኾንኹ።
16፤እንሆም፥የሰው፡ልጅ፡የሚመስል፡ከንፈሬን፡ዳሰሰኝ፤የዚያን፡ጊዜም፡አፌን፡ከፍቼ፡ተናገርኹ፡በፊቴም፡ቆሞ ፡የነበረውን፦ጌታዬ፡ሆይ፥ከራእዩ፡የተነሣ፡ሕመሜ፡መጣብኝ፥ኀይልም፡ዐጣኹ።
17፤ይህ፡የጌታዬ፡ባሪያ፡ከዚህ፡ከጌታዬ፡ጋራ፡ይናገር፡ዘንድ፡እንዴት፡ይችላል፧አኹንም፡ኀይል፡ዐጣኹ፥እስት ንፋስም፡አልቀረልኝም፡አልኹት።
18፤ደግሞ፡ሰው፡የሚመስል፡ዳሰሰኝ፥አበረታኝም።
19፤ርሱም፦እጅግ፡የተወደድኽ፡ሰው፡ሆይ፥አትፍራ፤ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፤በርታ፥ጽና፡አለኝ።በተናገረኝም፡ጊ ዜ፡በረታኹና፦አበርትተኸኛልና፥ጌታዬ፡ይናገር፡አልኹ።
20፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ወዳንተ፡የመጣኹት፡ስለ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፥ታውቃለኽን፧አኹንም፡ከፋርስ፡አለቃ፡ጋ ራ፡እዋጋ፡ዘንድ፡እመለሳለኹ፤እኔም፡ስወጣ፥እንሆ፤የግሪክ፡አለቃ፡ይመጣል።
21፤ነገር፡ግን፥በእውነት፡ጽሑፍ፡የተጻፈውን፡እነግርኻለኹ፤በዚህም፡ነገር፡ከአለቃችኹ፡ከሚካኤል፡በቀር፡ማ ንም፡የሚያጸናኝ፡የለም።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤እኔም፡በሜዶናዊ፡በዳርዮስ፡መዠመሪያ፡ዓመት፡አጸናውና፡አበረታው፡ዘንድ፡ቆሜ፡ነበር።
2፤አኹንም፡እውነትን፡አሳይኻለኹ።እንሆ፥ሦስት፡ነገሥታት፡ደግሞ፡በፋርስ፡ይነሣሉ፤አራተኛውም፡ከዅሉ፡ይልቅ ፡እጅግ፡ባለጠጋ፡ይኾናል፤በባለጠግነቱም፡በበረታ፡ጊዜ፡በግሪክ፡መንግሥት፡ላይ፡ዅሉን፡ያስነሣል።
3፤ኀያልም፡ንጉሥ፡ይነሣል፥በትልቅ፡አገዛዝም፡ይገዛል፥እንደ፡ፈቃዱም፡ያደርጋል።
4፤ርሱም፡በተነሣ፡ጊዜ፡መንግሥቱ፡ይሰበራል፤እስከ፡አራቱ፡የሰማይ፡ነፋሳት፡ይከፋፈላል።ለዘሩ፡ግን፡አይከፋ ፈልም፥እንደ፡ገዛበትም፡አገዛዝ፡አይኾንም፤መንግሥቱ፡ይነቀላልና፤ከነዚህም፡ለሌላዎች፡ይኾናልና።
5፤የደቡብም፡ንጉሥ፡ከአለቃዎቹም፡አንዱ፡ይበረታሉ፤ርሱም፡ይበረታበታል፡ይሠለጥንማል፤ግዛቱም፡ታላቅ፡ግዛት ፡ይኾናል።
6፤ከዘመናትም፡በዃላ፡ይጋጠማሉ፤የደቡብም፡ንጉሥ፡ሴት፡ልጅ፡ቃል፡ኪዳን፡ለማድረግ፡ወደሰሜን፡ንጉሥ፡ትመጣለ ች፤የክንዷ፡ኀይል፡ግን፡አይጸናም፥ርሱና፡ክንዱም፡አይጸናም፤ርሷና፡ርሷን፡ያመጡ፡የወለዳትም፡በዚያም፡ዘመ ን፡ያጸናት፡ዐልፈው፡ይሰጣሉ።
7፤ነገር፡ግን፥ከሥሯ፡ቍጥቋጥ፡አንዱ፡በስፍራው፡ይነሣል፤ወደ፡ሰራዊቱም፡ይመጣል፥ወደሰሜንም፡ንጉሥ፡ዐምባ፡ ይገባል፥በላያቸውም፡ያደርጋል፥ያሸንፍማል።
8፤አማልክታቸውንና፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎቻቸውን፡ከብርና፡ከወርቅም፡የተሠሩትን፡የከበሩትን፡ዕቃዎች፡ ወደ፡ግብጽ፡ይማርካል፤እስከ፡ጥቂትም፡ዓመት፡ድረስ፡ከሰሜን፡ንጉሥ፡ጋራ፡ሳይዋጋ፡ይቀመጣል።
9፤ይህም፡ወደደቡብ፡ንጉሥ፡መንግሥት፡ይገባል፥ነገር፡ግን፥ወደገዛ፡ምድሩ፡ይመለሳል።
10፤ልጆቹም፡ይዋጋሉ፤ብዙ፡ሰራዊትንና፡ሕዝብን፡ይሰበስባል፤ርሱም፡ይመጣል፥ይጐርፍማል፥ያልፍማል፤ተመልሶም ፡እስከ፡ዐምባው፡ድረስ፡ይዋጋል።
11፤የደቡብም፡ንጉሥ፡ይቈጣል፡ወጥቶም፡ከሰሜን፡ንጉሥ፡ጋራ፡ይዋጋል፤ብዙ፡ሕዝብንም፡ለሰልፍ፡ያቆማል፥ሕዝቡ ም፡ዐልፎ፡በእጁ፡ይሰጣል።
12፤ሕዝቡም፡በተወሰደ፡ጊዜ፡ልቡ፡ይታበያል፤አእላፋትንም፡ይጥላል፥ነገር፡ግን፥አያሸንፍም።
13፤የሰሜንም፡ንጉሥ፡ይመለሳል፥ከቀደመውም፡የበለጠ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ለሰልፍ፡ያቆማል፤በዘመናትና፡በዓመታትም፡ ፍጻሜ፡ከታላቅ፡ሰራዊትና፡ከብዙ፡ሀብት፡ጋራ፡ይመጣል።
14፤በዚያም፡ዘመን፡ብዙ፡ሰዎች፡በደቡብ፡ንጉሥ፡ላይ፡ይነሣሉ፤ከሕዝብኽም፡መካከል፡የዐመፅ፡ልጆች፡ራእዩን፡ ያጸኑ፡ዘንድ፡ይነሣሉ፤ነገር፡ግን፥ይወድቃሉ።
15፤የሰሜንም፡ንጉሥ፡ይመጣል፥ዐፈርንም፡ይደለድላል፥የተመሸገችንም፡ከተማ፡ይወስዳል፤የደቡብም፡ሰራዊት፡የ ተመረጡትም፡ሕዝቡ፡አይቆሙም፤ለመቋቋምም፡ኀይል፡የላቸውም።
16፤በርሱም፡ላይ፡የሚመጣው፡ግን፡እንደ፡ፈቃዱ፡ያደርጋል፥በፊቱም፡የሚቆም፡የለም፤በመልካሚቱም፡ምድር፡ይቆ ማል፥በእጁም፡ውስጥ፡ጥፋት፡ይኾናል።
17፤ከመንግሥቱም፡ዅሉ፡ኀይል፡ጋራ፡ይመጣ፡ዘንድ፡ፊቱን፡ያቀናል፥ከርሱም፡ጋራ፡አንድነትን፡ያደርጋል፤ያረክ ሳትም፡ዘንድ፡ሴትን፡ልጅ፡ይሰጠዋል፤ርሷም፡አትጸናም፡ለርሱም፡አትኾንም።
18፤ከዚህም፡በዃላ፡ፊቱን፡ወደ፡ደሴቶች፡ይመልሳል፥ብዙዎችንም፡ይወስዳል፤አንድ፡አለቃ፡ግን፡ስድቡን፡ይሽራ ል፥ስድቡንም፡በራሱ፡ላይ፡ይመልሳል።
19፤ፊቱንም፡ወደገዛ፡ምድሩ፡ዐምባዎች፡ይመልሳል፤ተሰናክሎም፡ይወድቃል፥አይገኝምም።
20፤የዚያን፡ጊዜም፡በመንግሥቱ፡ክብር፡መካከል፡አስገባሪውን፡የሚያሳልፍ፡በስፍራው፡ይነሣል፤ነገር፡ግን፥በ ቍጣው፡ሳይኾን፡በሰልፍም፡ሳይኾን፡በጥቂት፡ቀን፡ይሰበራል።
21፤በርሱም፡ስፍራ፡የተጠቃ፡ሰው፡ይነሣል፡የመንግሥቱንም፡ክብር፡አይሰጡትም፤በቀስታ፡መጥቶ፡መንግሥቱን፡በ ማታለል፡ይገዛል።
22፤የሚጐርፍም፡ሰራዊት፡ከፊቱ፡ይወሰዳል፥ርሱና፡የቃል፡ኪዳኑ፡አለቃ፡ይሰበራሉ።
23፤ከርሱም፡ጋራ፡ከተወዳጀ፡በዃላ፥በተንኰል፡ያደርጋል፤ከጥቂትም፡ሕዝብ፡ጋራ፡ወጥቶ፡ይበረታል።
24፤በቀስታ፡ከአገር፡ዅሉ፡ወደለመለመችው፡ክፍል፡ይገባል፤አባቶቹና፡የአባቶቹ፡አባቶች፡ያላደረጉትንም፡ያደ ርጋል፤ብዝበዛውንና፡ምርኮውንም፣ሀብቱንም፡በመካከላቸው፡ይበትናል፤በምሽጎችም፡ላይ፡እስከ፡ጊዜው፡ድረስ፡ ዐሳቡን፡ይፈጥራል።
25፤በታላቅም፡ሰራዊት፡ኾኖ፡ኀይሉንና፡ልቡን፡በደቡብ፡ንጉሥ፡ላይ፡ያስነሣል፤የደቡብም፡ንጉሥ፡በታላቅና፡በ ብዙ፡ሰራዊት፡ኾኖ፡በሰልፍ፡ይዋጋል፤ነገር፡ግን፥ዐሳብ፡በርሱ፡ላይ፡ይፈጥራሉና፥አይጸናም።
26፤መብሉንም፡የሚበሉ፡ሰዎች፡ይሰብሩታል፤ሰራዊቱም፡ይጐርፋል፤ብዙዎችም፡ተገድለው፡ይወድቃሉ።
27፤እነዚህም፡ኹለት፡ነገሥታት፡ክፋትን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡በልባቸው፡ያስባሉ፥ባንድ፡ገበታም፡ተቀምጠው፡ሐሰት ፡ይናገራሉ፤ነገር፡ግን፥ፍጻሜው፡እስከተወሰነው፡ጊዜ፡ነውና፥አይከናወንላቸውም።
28፤ከብዙም፡ሀብት፡ጋራ፡ወደ፡ምድሩ፡ይመለሳል፥ልቡም፡በተቀደሰ፡ቃል፡ኪዳን፡ላይ፡ይኾናል፤ፈቃዱንም፡ያደር ጋል፥ወደገዛ፡ምድሩም፡ይመለሳል።
29፤በተወሰነውም፡ጊዜ፡ይመለሳል፥ወደ፡ደቡብም፡ይመጣል፤ነገር፡ግን፥ዃለኛው፡እንደ፡ፊተኛው፡አይኾንም።
30፤የኪቲም፡መርከቦች፡ይመጡበታልና፥ስለዚህ፡ዐዝኖ፡ይመለሳል፥በቅዱሱም፡ቃል፡ኪዳን፡ላይ፡ይቈጣል፥ፈቃዱን ም፡ያደርጋል፤ተመልሶም፡ቅዱሱን፡ቃል፡ኪዳን፡የተዉትን፡ሰዎች፡ይመለከታል።
31፤ከርሱም፡ጋራ፡ሰራዊቶች፡ይቆማሉ፥መቅደሱንም፣ግንቡንም፡ያረክሳሉ፥የዘወትሩንም፡መሥዋዕት፡ያስቀራሉ፥የ ጥፋትንም፡ርኵሰት፡ያቆማሉ።
32፤ቃል፡ኪዳኑን፡የሚበድሉትንም፡በማታለል፡ያስታል፤ነገር፡ግን፥አምላካቸውን፡የሚያውቁ፡ሕዝብ፡ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም።
33፤በሕዝቡም፡መካከል፡ያሉ፡ጥበበኛዎች፡ብዙ፡ሰዎችን፡ያስተምራሉ፤ነገር፡ግን፥በሰይፍና፡በእሳት፡ነበልባል ፡በምርኮና፡በመበዝበዝ፡ብዙ፡ዘመን፡ይወድቃሉ።
34፤በወደቁም፡ጊዜ፡በጥቂት፡ርዳታ፡ይረ፟ዳ፟ሉ፤ብዙ፡ሰዎችም፡በግብዝነት፡ወደ፡እነርሱ፡ተባብረው፡ይሰበሰባ ሉ።
35፤እስከተወሰነውም፡ዘመን፡ይኾናልና፥ከጥበበኛዎቹ፡ዐያሌዎቹ፡እስከ፡ፍጻሜ፡ዘመን፡ይነጥሩና፡ይጠሩ፣ይነጡ ም፡ዘንድ፡ይወድቃሉ።
36፤ንጉሡም፡እንደ፡ፈቃዱ፡ያደርጋል፤ራሱንም፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል፥በአማልክት፡ዅሉ፡ላይ፡ራሱን፡ታላቅ፡ያደ ርጋል፥በአማልክትም፡አምላክ፡ላይ፡በትዕቢት፡ይናገራል፤ቍጣም፡እስኪፈጸም፡ድረስ፡ይከናወንለታል፥የተወሰነ ው፡ይደረጋልና።
37፤የአባቶቹንም፡አማልክት፡የሴቶችንም፡ምኞት፡አይመለከትም፤ራሱንም፡በዅሉ፡ላይ፡ታላቅ፡ያደርጋልና፥አማል ክትን፡ዅሉ፡አይመለከትም።
38፤በእነዚህ፡ፋንታ፡ግን፡የዐምባዎቹን፡አምላክ፡ያከብራል፤አባቶቹም፡ያላወቁትን፡አምላክ፡በወርቅና፡በብር ፡በዕንቍና፡በከበረ፡ነገር፡ያከብረዋል።
39፤በእንግዳም፡አምላክ፡ርዳታ፡በጽኑ፡ዐምባ፡ላይ፡ያደርጋል፤ለሚያውቁት፡ክብር፡ያበዛላቸዋል፥በብዙም፡ላይ ፡ያስገዛቸዋል፥ምድርንም፡በዋጋ፡ይከፍላል።
40፤በፍጻሜ፡ዘመንም፡የደቡብ፡ንጉሥ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይዋጋል፤የሰሜንም፡ንጉሥ፡ከሠረገላዎችና፡ከፈረሰኛዎች፡ከ ብዙም፡መርከቦች፡ጋራ፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይመጣበታል፤ወደ፡አገሮችም፡ይገባል፥ይጐርፍማል፥ያልፍማል።
41፤ወደ፡መልካሚቱም፡ምድር፡ይገባል፥ብዙ፡አገሮችም፡ይወድቃሉ፤ነገር፡ግን፥ኤዶምያስና፡ሞዐብ፡ከዐሞንም፡ል ጆች፡የበለጡት፡ከእጁ፡ይድናሉ።
42፤እጁን፡በአገሮች፡ላይ፡ይዘረጋል፥የግብጽም፡ምድር፡አታመልጥም።
43፤በወርቅና፡በብርም፡መዝገብ፡ላይ፥በከበረችም፡በግብጽ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ላይ፡ይሠለጥናል፤የልብያና፡የኢትዮጵያ ፡ሰዎችም፡ይከተሉታል።
44፤ከምሥራቅና፡ከሰሜን፡ግን፡ወሬ፡ያውከዋል፤ብዙ፡ሰዎችንም፡ይገድል፡ዘንድና፡ፈጽሞ፡ያጠፋ፡ዘንድ፡በታላቅ ፡ቍጣ፡ይወጣል።
45፤ንጉሣዊ፡ድንኳኑንም፡በባሕርና፡በከበረው፡በቅዱስ፡ተራራ፡መካከል፡ይተክላል፤ወደ፡ፍጻሜው፡ግን፡ይመጣል ፥ማንም፡አይረዳውም።
_______________ትንቢተ፡ዳንኤል፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤በዚያም፡ዘመን፡ስለሕዝብኽ፡ልጆች፡የሚቆመው፡ታላቁ፡አለቃ፡ሚካኤል፡ይነሣል፤ሕዝብም፡ከኾነ፡ዠምሮ፡እስከ ዚያ፡ዘመን፡ድረስ፡እንደ፡ርሱ፡ያለ፡ያልኾነ፡የመከራ፡ዘመን፡ይኾናል፤በዚያም፡ዘመን፡በመጽሐፉ፡ተጽፎ፡የተ ገኘው፡ሕዝብኽ፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ይድናል።
2፤በምድርም፡ትቢያ፡ውስጥ፡ካንቀላፉቱ፡ብዙዎች፡ይነቃሉ፤እኩሌቶቹ፡ወደዘለዓለም፡ሕይወት፥እኩሌቶቹም፡ወደ፡ ዕፍረትና፡ወደዘለዓለም፡ጕስቍልና።
3፤ጥበበኛዎቹም፡እንደሰማይ፡ጸዳል፥ብዙ፡ሰዎችንም፡ወደ፡ጽድቅ፡የሚመልሱ፡እንደ፡ከዋክብት፡ለዘለዓለም፡ይደ ምቃሉ።
4፤ዳንኤል፡ሆይ፥አንተ፡ግን፡እስከ፡ፍጻሜ፡ዘመን፡ድረስ፡ቃሉን፡ዝጋ፥መጽሐፉንም፡ዐትም፤ብዙ፡ሰዎች፡ይመረም ራሉ፥ዕውቀትም፡ይበዛል።
5፤እኔም፡ዳንኤል፡አየኹ፤እንሆም፥ኹለት፡ሌላዎች፡ቆመው፡ነበር፥አንዱ፡በዚህ፡በወንዙ፡ዳር፥ሌላውም፡በዚያ፡ በወንዙ፡ዳር።
6፤አንዱም፡ከወንዙ፡ውሃ፡በላይ፡የነበረውን፡በፍታም፡የለበሰውን፦የዚህ፡ድንቅ፡ፍጻሜ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧አለ ው።
7፤ከወንዙም፡ውሃ፡በላይ፡የነበረው፡በፍታም፡የለበሰው፡ሰው፡ቀኝና፡ግራ፡እጁን፡ወደ፡ሰማይ፡አንሥቶ፦ለዘመን ና፡ለዘመናት፡ለዘመንም፡እኩሌታ፡ነው፤የተቀደሰውም፡ሕዝብ፡ኀይል፡መበተን፡በተጨረሰ፡ጊዜ፡ይህ፡ዅሉ፡ይፈጸ ማል፡ብሎ፡ለዘለዓለም፡ሕያው፡ኾኖ፡በሚኖረው፡ሲምል፡ሰማኹ።
8፤ሰማኹም፥ነገር፡ግን፥አላስተዋልኹም፤የዚያን፡ጊዜም፦ጌታዬ፡ሆይ፥የዚህ፡ዅሉ፡ፍጻሜ፡ምንድር፡ነው፧አልኹ።
9፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ዳንኤል፡ሆይ፥ቃሉ፡እስከ፡ፍጻሜ፡ዘመን፡ድረስ፡የተዘጋና፡የታተመ፡ነውና፥ኺድ፤
10፤ብዙ፡ሰዎች፡ሰውነታቸውን፡ያጠራሉ፥ያነጡማል፥ይነጥሩማል፤ክፉዎች፡ግን፡ክፋትን፡ያደርጋሉ፤ክፉዎችም፡ዅ ሉ፡አያስተውሉም፥ጥበበኛዎች፡ግን፡ያስተውላሉ።
11፤የዘወትሩም፡መሥዋዕት፡ከቀረ፡ዠምሮ፥የጥፋትም፡ርኵሰት፡ከቆመ፡ዠምሮ፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዘጠና፡ቀን፡ይኾ ናል።
12፤የሚታገሥ፥እስከ፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ቀንም፡የሚደርስ፡ምስጉን፡ነው።
13፤አንተ፡ግን፡እስከ፡ፍጻሜው፡ድረስ፡ኺድ፤አንተም፡ታርፋለኽ፥በቀኑም፡መጨረሻ፡በዕጣ፡ክፍልኽ፡ትቆማለኽ፨

http://www.gzamargna.net