ትንቢተ፡ኤርምያስ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1፤
1፤በብንያም፡አገር፡በዐናቶት፡ከነበሩ፡ካህናት፡የኾነ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡የኤርምያስ፡ቃል።
2፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዓሞጽ፡ልጅ፡በኢዮስያስ፡ዘመን፡በመንግሥቱ፡በዐሥራ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡የእግዚአብሔር፡ቃ ል፡መጣለት።
3፤በይሁዳም፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡ዘመን፥እስከይሁዳ፡ንጉሥ፡እስከኢዮስያስ፡ልጅ፡እስከ፡ሴዴ ቅያስ፡እስከ፡ዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ፍጻሜ፥ኢየሩሳሌም፡እስከተማረከችበት፡እስከ፡ዐምስተኛው፡ወር፡ድረስ ፡መጣ።
4፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
5፤በሆድ፡ሳልሠራኽ፡ዐውቄኻለኹ፥ከማሕፀንም፡ሳትወጣ፡ቀድሼኻለኹ፥ለአሕዛብም፡ነቢይ፡አድርጌኻለኹ።
6፤እኔም፦ወዮ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥እንሆ፥ብላቴና፡ነኝና፡እናገር፡ዘንድ፡አላውቅም፡አልኹ።
7፤እግዚአብሔር፡ግን፡እንዲህ፡አለኝ፦ወደምሰድ፟ኽ፡ዅሉ፡ዘንድ፡ትኼዳለኽና፥የማዝ፟ኽንም፡ዅሉ፡ትናገራለኽና ፦ብላቴና፡ነኝ፡አትበል።
8፤እኔ፡አድንኽ፡ዘንድ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡ከፊታቸው፡አትፍራ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
9፤እግዚአብሔርም፡እጁን፡ዘርግቶ፡አፌን፡ዳሰሰ፥እግዚአብሔርም፦እንሆ፥ቃሌን፡በአፍኽ፡ውስጥ፡አኑሬያለኹ፤
10፤እንሆ፦ትነቅልና፡ታፈርስ፡ዘንድ፥ታጠፋና፡ትገለብጥ፡ዘንድ፥ትሠራና፡ትተክል፡ዘንድ፡በአሕዛብና፡በመንግ ሥታት፡ላይ፡ዛሬ፡አድርጌኻለኹ፡አለኝ።
11፤ደግሞ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፦ኤርምያስ፡ሆይ፥ምን፡ታያለኽ፧እያለ፡ወደ፡እኔ፡መጣ።እኔም፦የለውዝ፡በትር፡ አያለኹ፡አልኹ።
12፤እግዚአብሔርም፦እፈጽመው፡ዘንድ፡በቃሌ፡እተጋለኹና፡መልካም፡አይተኻል፡አለኝ።
13፤ኹለተኛም፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፦ምን፡ታያለኽ፧እያለ፡ወደ፡እኔ፡መጣ።እኔም፦የሚፈላ፡አፍላል፡አያለ ኹ፥ፊቱም፡ከሰሜን፡ወገን፡ነው፡አልኹ።
14፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ከሰሜን፡ወገን፡ክፉ፡ነገር፡በምድሪቱ፡በተቀመጡ፡ዅሉ፡ላይ፡ይገለጣል።
15፤እንሆ፥እኔ፡በሰሜን፡ያሉትን፡የመንግሥታትን፡ወገኖች፡ዅሉ፡እጠራለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እነርሱም፡ይ መጣሉ፡እያንዳንዳቸውም፡በኢየሩሳሌም፡በር፡መግቢያ፡በዙሪያዋ፡በቅጥሯ፡ዅሉ፡ላይ፡በይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ ፡ላይ፡ዙፋናቸውን፡ያስቀምጣሉ።
16፤ስለ፡ክፋታቸውም፡ዅሉ፡እኔን፡ስለ፡ተዉ፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡ስላጠኑ፥ለእጃቸውም፡ሥራ፡ስለ፡ሰገዱ፥ፍ ርዴን፡በእነርሱ፡ላይ፡እናገራለኹ።
17፤አንተ፡ግን፡ወገብኽን፡ታጠቅ፥ተነሥም፥ያዘዝኹኽም፡ዅሉ፡ንገራቸው፤በፊታቸው፡እንዳላስፈራኽ፡አትፍራቸው ።
18፤እንሆ፥በምድሪቱ፡ዅሉ፡ላይ፡በይሁዳም፡ነገሥታት፡በአለቃዎቿና፡በካህናቷ፡ላይ፡በምድሪቱም፡ሕዝብ፡ላይ፡ እንደ፡ተመሸገ፡ከተማ፡እንደ፡ብረትም፡ዐምድ፡እንደ፡ናስም፡ቅጥር፡ዛሬ፡አድርጌኻለኹ።
19፤ከአንተ፡ጋራ፡ይዋጋሉ፥ነገር፡ግን፥አድንኽ፡ዘንድ፡እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡ድል፡አይነሡኽም፥ይላል፡እ ግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2፤
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤ኺድ፥በኢየሩሳሌም፡ዦሮ፡ጩኽ፥እንዲህም፡በል፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የብላቴንነትሽን፡ምሕረት፡የታ ጨሽበትንም፡ፍቅር፥በምድረ፡በዳ፡ዘር፡ባልተዘራበት፡ምድር፡እንደ፡ተከተልሽኝ፡ዐስቤያለኹ።
3፤እስራኤል፡ለእግዚአብሔር፡ቅዱስ፡ነበረ፥የቡቃያውም፡በኵራት፡ነበረ፤የበሉት፡እንደ፡በደለኛዎች፡ይቈጠራሉ ፥ክፉም፡ነገር፡ያገኛቸዋል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4፤የያዕቆብ፡ቤት፡የእስራኤልም፡ቤት፡ወገኖች፡ዅሉ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
5፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አባቶቻችኹ፡ከእኔ፡ዘንድ፡የራቁ፥ከንቱነትንም፡የተከተሉ፥ከንቱም፡የኾኑ፡ም ን፡ክፋት፡አግኝተውብኝ፡ነው፧
6፤እነርሱም፦ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣን፥በምድረ፡በዳም፡በባድማ፡ጕድጓድም፡ባለበት፡ምድር፥በውሃ፡ጥምና፡በሞት ፡ጥላ፡ምድር፥ማንም፡በማያልፍበትና፡ማንም፡በማይቀመጥበት፡ምድር፡የመራን፡እግዚአብሔር፡ወዴት፡አለ፧አላሉ ም።
7፤ፍሬዋንና፡በረከቷንም፡ትበሉ፡ዘንድ፡ወደ፡ፍሬያማ፡ምድር፡አገባዃችኹ፤ነገር፡ግን፥በገባችኹ፡ጊዜ፡ምድሬን ፡አረከሳችኹ፥ርስቴንም፡አጐሳቈላችኹ።
8፤ካህናቱም፦እግዚአብሔር፡ወዴት፡አለ፧አላሉም፥ባለኦሪቶችም፡አላወቁኝም፤ገዢዎችም፡ዐመፁብኝ፥ነቢያትም፡በ በዓል፡ትንቢት፡ተናገሩ፥የማይረባንም፡ነገር፡ተከተሉ።
9፤ስለዚህ፥ከእናንተ፡ጋራ፡እከራከራለኹ፥ከልጆቻችኹም፡ልጆች፡ጋራ፡እከራከራለኹ።
10፤ወደኪቲም፡ደሴቶች፡ዕለፉና፡ተመልከቱ፥ወደ፡ቄዳርም፡ላኩና፡እጅግ፡መርምሩ፥እንደዚህም፡ያለ፡ነገር፡ኾኖ ፡እንደ፡ኾነ፡እዩ።
11፤በእውኑ፡አማልክት፡ያልኾኑትን፡አማልክቱን፡የለወጣቸው፡አንድ፡ሕዝብ፡አለን፧ነገር፡ግን፡ሕዝቤ፡ክብሩን ፡ለማይረባ፡ነገር፡ለወጠ።
12፤ሰማያት፡ሆይ፥በዚህ፡ተደነቁ፥እጅግም፡ደንግጡና፡ተንቀጥቀጡ፡ይላል፡እግዚአብሔር።
13፤ሕዝቤ፡ኹለቱን፡ክፉ፡ነገሮች፡አድርገዋልና፤እኔን፡የሕያውን፡ውሃ፡ምንጭ፡ትተውኛል፥የተቀደዱትንም፡ጕድ ጓዶች፥ውሃውን፡ይይዙ፡ዘንድ፡የማይችሉትን፡ጕድጓዶች፥ለራሳቸው፡ቈፍረዋል።
14፤በእውኑ፡እስራኤል፡ባሪያ፡ነውን፧ወይስ፡የቤት፡ውላጅ፡ነውን፧ስለ፡ምን፡ብዝበዛ፡ኾነ፧
15፤የአንበሳ፡ደቦሎች፡በርሱ፡ላይ፡አገሡ፥ድምፃቸውንም፡ሰጡ፤ምድሩንም፡ባድማ፡አደረጉ፥ከተማዎቹም፡ተቃጠሉ ፡የሚቀመጥባቸውም፡የለም።
16፤የሜምፎስና፡የጣፍናስ፡ልጆች፡አስነወሩሽ፡አላገጡብሽም።
17፤ይህ፡ዅሉ፡የኾነብሽ፡እኔን፡ስለ፡ተውሽ፡አይደለምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፡አምላክሽ።
18፤አኹንስ፡የሺሖርን፡ውሃ፡ትጠጪ፡ዘንድ፡በግብጽ፡መንገድ፡ምን፡ጕዳይ፡አለሽ፧የኤፍራጥስንም፡ውሃ፡ትጠጪ፡ ዘንድ፡በአሶር፡መንገድ፡ምን፡ጕዳይ፡አለሽ፧
19፤ክፋትሽ፡ይገሥጽሻል፡ክዳትሽም፡ይዘልፍሻል፤አምላክሽንም፡እግዚአብሔርን፡የተውሽ፡እኔንም፡መፍራት፡የሌ ለብሽ፡ክፉና፡መራራ፡ነገር፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቂ፥ተመልከቺ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
20፤ከጥንት፡ዠምሮ፡ቀንበርሽን፡ሰብሬያለኹ፡እስራትሽንም፡ቈርጫለኹ፤አንቺም፦አላገለግልም፡አልሽ፥ነገር፡ግ ን፥ከፍ፡ባለው፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፡ከለምለምም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ለማመንዘር፡ተጋደምሽ።
21፤እኔ፡የተመረጠች፡ወይን፡ፍጹምም፡እውነተኛ፡ዘር፡አድርጌ፡ተክዬሽ፡ነበር፤አንቺ፡ግን፡ክፉ፡የእንግዳ፡ወ ይን፡ግንድ፡ኾነሽ፡እንዴት፡ተለወጥሽብኝ፧
22፤በእንዶድ፡ብትታጠቢም፥ለራስሽም፡ሳሙና፡ብታበዢ፥በእኔ፡ፊት፡በኀጢአትሽ፡ረክሰሻል፡ይላል፡ጌታ፡እግዚአ ብሔር።
23፤አንቺስ፦አልረከስኹም፥በዓሊምንም፡አልተከተልኹም፡እንዴት፡ትያለሽ፧በቈላ፡ያለውን፡መንገድሽን፡ተመልከ ቺ፥ያደረግሽውንም፡ዕወቂ፤በመንገድም፡ላይ፡እንደ፡ተለቀቀች፡እንደ፡ፈጣን፡ግመል፡ኾነሻል፤
24፤በምኞቷ፡ነፋስን፡እንደምታሸት፟፥በምድረ፡በዳ፡እንደ፡ለመደች፡እንደ፡ሜዳ፡አህያ፡ነሽ፤ከምኞቷ፡የሚመል ሳት፡ማን፡ነው፧የሚሿት፡ዅሉ፡አይደክሙም፥በወራቷ፡ያገኟታል።
25፤እግርሽን፡ከሻካራ፡መንገድ፡ጕረሮሽንም፡ከውሃ፡ጥም፡ከልክዪ፤አንቺ፡ግን፦እጨክናለኹ፥እንግዳዎችን፡ወድ ጃለኹና፥እከተላቸዋለኹም፡አልሽ።
26፤ሌባ፡በተያዘ፡ጊዜ፡እንደሚያፍር፡እንዲሁ፡የእስራኤል፡ቤት፥እነርሱና፡ንጉሦቻቸውም፡አለቃዎቻቸውም፡ካህ ናታቸውም፡ነቢያታቸውም፡ያፍራሉ።
27፤ግንዱን፦አንተ፡አባቴ፡ነኽ፤ድንጋዩንም፦አንተ፡ወለድኸኝ፡ይላሉ፤ፊታቸውንም፡ሳይኾን፡ዠርባቸውን፡ሰጡኝ ፥በመከራቸው፡ጊዜ፡ግን፦ተነሥተኽ፡አድነን፡ይላሉ።
28፤ለአንተ፡የሠራኻቸው፡አማልክትኽ፡ወዴት፡ናቸው፧ይሁዳ፡ሆይ፥አማልክትኽ፡እንደ፡ከተማዎችኽ፡ቍጥር፡እንዲ ሁ፡ናቸውና፥ይነሡ፡በመከራኽም፡ጊዜ፡ያድኑኽ።
29፤ከእኔ፡ጋራ፡የምትከራከሩ፡ለምንድር፡ነው፧ዅላችኹ፡ዐምፃችኹብኛል፡ይላል፡እግዚአብሔር።
30፤ልጆቻችኹን፡በከንቱ፡ቀሥፌአቸዋለኹ፤ተግሣጽን፡አልተቀበሉም፤ሰይፋችኹ፡እንደሚሰብር፡አንበሳ፡ነቢያታች ኹን፡በልቷል።
31፤ትውልድ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ተመልከቱ፦በእውኑ፡ለእስራኤል፡ምድረ፡በዳ፡ወይስ፡የጨለመች፡ምድር ፡ኾንኹባትን፧ሕዝቤስ፡ስለ፡ምን፦እኛ፡ፈርጥጠናል፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ወዳንተ፡አንመለስም፡ይላል፧
32፤በእውኑ፡ቈንዦ፡ጌጧን፡ወይስ፡ሙሽራ፡ዝርግፍ፡ጌጧን፡ትረሳለችን፧ሕዝቤ፡ግን፡የማይቈጠር፡ወራት፡ረስቶኛ ል።
33፤ፍቅርን፡ለመሻት፡መንገድሽን፡እንዴት፡ታቀኛለሽ! ስለዚህ፡ለክፉዎች፡ሴቶች፡እንኳ፡መንገድሽን፡አስተምረሻል።
34፤በእጆችሽም፡የንጹሓን፡ድኻዎች፡ደም፡ተገኝቷል፤በእነዚህ፡ዅሉ፡ላይ፡በግልጥ፡አገኘኹት፡እንጂ፡በስውር፡ ፈልጌ፡አላገኘኹትም።
35፤አንቺ፡ግን፦ንጹሕ፡ነኝ፤በእውነት፡ቍጣው፡ከእኔ፡ተመልሷል፡አልሽ።እንሆ፦ኀጢአት፡አልሠራኹም፡ብለሻልና ፥በፍርድ፡እከስ፟ሻለኹ።
36፤መንገድሽን፡ትለውጪ፡ዘንድ፡ለምን፡እጅግ፡ትሮጫለሽ፧አሶር፡እንዳሳፈረሽ፡ግብጽ፡ያሳፍርሻል።
37፤እግዚአብሔር፡የታመንሽባቸውን፡ጥሏልና፥በእነርሱም፡አይከናወንልሽምና፡እጅሽን፡በራስሽ፡ላይ፡አድርገሽ ፡ከዚያ፡ደግሞ፡ትወጫለሽ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3፤
1፤በሰው፡ዘንድ፦ሰው፡ሚስቱን፡ቢፈታ፥ከርሱም፡ዘንድ፡ኼዳ፡ሌላ፡ወንድ፡ብታገባ፥በእውኑ፡ደግሞ፡ወደ፡ርሱ፡ት መለሳለችን፧ያች፡ሴት፡እጅግ፡የረከሰች፡አይደለችምን፧ይባላል።አንቺ፡ከብዙ፡ውሽማዎች፡ጋራ፡አመንዝረሻል፥ ወደ፡እኔም፡ትመለሻለሽን፧ይላል፡እግዚአብሔር።
2፤ዐይንሽን፡አንሥተሽ፡ወደ፡ወናዎች፡ኰረብታዎች፡ተመልከቺ፤ያልተጋደምሽበት፡ስፍራ፡ወዴት፡አለ፧ዐረባዊ፡በ ምድረ፡በዳ፡እንደሚቀመጥ፡አንቺ፡በመንገድ፡ላይ፡ተቀምጠሽ፡ትጠብቂያቸው፡ነበር፤በግልሙትናሽና፡በኀጢአትሽ ፡ምድሪቱን፡አረከ፟ሽ።
3፤ስለዚህ፥ካፊያ፡ተከለከለ፥የዃለኛውም፡ዝናብ፡ጠፋ፤የጋለሞታም፡ሴት፡ፊት፡ነበረብሽ፥ታፍሪም፡ዘንድ፡እንቢ ፡ብለሻል።
4፤አኹንም፦አንተ፡አባቴ፡ሆይ፥የብላቴንነቴ፡ወዳጅ፡ነኽ፡ብለሽ፡አልጮኽሺልኝምን፧ለዘለዓለም፡ይቈጣልን፧
5፤እስከ፡ፍጻሜስ፡ድረስ፡ይጠብቀዋልን፧እንሆ፥እንዲህ፡ብለሽ፡ተናገርሽ፥እንደ፡ተቻለሽም፡መጠን፡ክፉን፡ነገ ር፡አደረግሽ።
6፤እግዚአብሔርም፡በንጉሡ፡በኢዮስያስ፡ዘመን፡እንዲህ፡አለኝ፦ከዳ፟ተኛዪቱ፡እስራኤል፡ያደረገችውን፡አየኽን ፧ወደረዘመው፡ተራራ፡ዅሉ፡ከለመለመ፡ዛፍም፡ዅሉ፡በታች፡ኼደች፡በዚያም፡ጋለሞተች።
7፤ይህንም፡ዅሉ፡ካደረገች፡በዃላ፦ወደ፡እኔ፡ትመለሳለች፡ብዬ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥አልተመለሰችም፤አታላይ፡እ ኅቷም፡ይሁዳ፡አየች።
8፤ከዳ፟ተኛዪቱም፡እስራኤል፡ስላመነዘረች፡ስለዚህ፡ፈትቻታለኹ፡የፍቿንም፡ወረቀት፡ሰጥቻታለኹ፤አታላይ፡እኅ ቷ፡ይሁዳ፡ግን፡እንዳልፈራች፡ርሷም፡ደግሞ፡ኼዳ፡እንደ፡ጋለሞተች፡አየኹ።
9፤በግልሙትናዋም፡በመቅለሏም፡ምድሪቱ፡ረከሰች፤ርሷም፡ከድንጋይና፡ከግንድ፡ጋራ፡አመነዘረች።
10፤በዚህም፡ዅሉ፡አታላዪቱ፡ይሁዳ፡በሐሰት፡እንጂ፡በፍጹም፡ልቧ፡ወደ፡እኔ፡አልተመለሰችም።
11፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ከአታላዪቱ፡ከይሁዳ፡ይልቅ፡ከዳ፟ተኛዪቱ፡እስራኤል፡ጸደቀች።
12፤ኺድና፡ይህን፡ቃል፡ወደ፡ሰሜን፡ተናገር፥እንዲህም፡በል፦ከዳ፟ተኛዪቱ፡እስራኤል፡ሆይ፥ተመለሽ፥ይላል፡እ ግዚአብሔር፤መሓሪ፡ነኝና፥ለዘለዓለምም፡አልቈጣምና፡በእናንተ፡ላይ፡ፊቴን፡አላደርግም፥ይላል፡እግዚአብሔር ።
13፤በአምላክሽ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡እንዳመፅሽ፥መንገድሽንም፡ከለመለመ፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ለእንግዳዎች፡እ ንደ፡ዘረጋሽ፥ቃሌንም፡እንዳልሰማሽ፡ኀጢአትሽን፡ብቻ፡ዕወቂ፡ይላል፡እግዚአብሔር።
14፤ከዳ፟ተኛዎች፡ልጆች፡ሆይ፥እኔ፡ባላችኹ፡ነኝና፡ተመለሱ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤አንዱንም፡ከአንዲት፡ከተማ ፡ኹለቱንም፡ካንድ፡ወገን፡እወስዳችዃለኹ፥ወደ፡ጽዮንም፡አመጣችዃለኹ፤
15፤እንደ፡ልቤም፡በግ፡ጠባቂዎችን፡እሰጣችዃለኹ፥በዕውቀትና፡በማስተዋልም፡ይጠብቋችዃል።
16፤በበዛችኹም፡ጊዜ፡በምድርም፡ላይ፡በረባችኹ፡ጊዜ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥በዚያ፡ዘመን፦የእግዚአብሔር፡የቃ ል፡ኪዳኑ፡ታቦት፡ብለው፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይጠሩም፤ልብ፡አያደርጉትም፥አያስቡትምም፥አይሹትምም፥ከእንግ ዲህ፡ወዲህም፡አይደረግም።
17፤በዚያም፡ዘመን፡ኢየሩሳሌምን፡የእግዚአብሔር፡ዙፋን፡ብለው፡ይጠሯታል፥አሕዛብም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሷ፡ይሰበሰ ባሉ፤ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ክፉውን፡እልከኛ፡ልባቸውን፡ተከትለው፡አይኼዱም።
18፤በዚያም፡ዘመን፡የይሁዳ፡ቤት፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ይኼዳል፤በአንድም፡ኾነው፡ከሰሜን፡ምድር፡ርስት፡አድር ጌ፡ለአባቶቻቸው፡ወደሰጠዃት፡ምድር፡ይመጣሉ።
19፤እኔ፡ግን፦ከወንዶች፡ልጆች፡ጋራ፡እንዴት፡አደርግሻለኹ፧ያማረችውንስ፡ምድር፡የከበረችውን፡የአሕዛብን፡ ሰራዊት፡ርስት፡እንዴት፡እሰጥሻለኹ፧ብዬ፡ነበር።ደግሞ፦አባቴ፡ብለሽ፡ትጠሪኛለሽ፥እኔንም፡ከመከተል፡አትመ ለሽም፡ብዬ፡ነበር።
20፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ሚስት፡ባሏን፡እንደምታታልል፡እንዲሁ፡አታለላችኹኝ፡ይላል፡እግዚአብሔር።
21፤የእስራኤል፡ልጆች፡መንገዳቸውን፡አጣ፟መ፟ዋልና፥አምላካቸውንም፡እግዚአብሔርን፡ረስተዋልና፥በወናዎች፡ ኰረብታዎች፡ላይ፡የልመናቸውና፡ልቅሷቸው፡ድምፅ፡ተሰማ።
22፤ከዳ፟ተኛዎች፡ልጆች፡ሆይ፥ተመለሱ፥ከዳ፟ተኛነታችኹንም፡እፈውሳለኹ።እንሆ፥አንተ፡አምላካችን፡እግዚአብ ሔር፡ነኽና፥ወዳንተ፡እንመጣለን።
23፤በእውነት፡የኰረብታዎችና፡የተራራዎች፡ፍጅት፡ከንቱ፡ናት፤በእውነት፡የእስራኤል፡መዳን፡በአምላካችን፡በ እግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው።
24፤ነገር፡ግን፥ከትንሽነታችን፡ዠምሮ፡የአባቶቻችን፡ድካም፥በጎቻቸውንና፡ላሞቻቸውን፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆ ቻቸውንም፥ዕፍረት፡በልቶባቸዋል።
25፤ከትንሽነታችን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እኛና፡አባቶቻችን፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኀጢአት ፡ሠርተናልና፥የአምላካችንንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰማንምና፡በዕፍረታችን፡እንጋደም፥ውርደታችንም፡ ይክደነን።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4፤
1፤እስራኤል፡ሆይ፥ብትመለስ፥ወደ፡እኔ፡ተመለስ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ርኵሰትኽንም፡ከፊቴ፡ብታስወግድ፥ባትና ወጥም፥
2፤ሕያው፡እግዚአብሔርን! ብለኽም፡በእውነትና፡በቅንነት፡በጽድቅም፡ብትምል፥አሕዛብ፡በርሱ፡ይባረካሉ፡በርሱም፡ይመካሉ።
3፤እግዚአብሔር፡ለይሁዳና፡ለኢየሩሳሌም፡ሰዎች፡እንዲህ፡ይላልና፦ጥጋቱን፡ዕርሻ፡ዕረሱ፥በሾኽም፡ላይ፡አትዝ ሩ።
4፤እናንተም፡የይሁዳ፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌምም፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ስለሥራችኹ፡ክፋት፡ቍጣዬ፡እንደ፡እሳት፡እንዳይ ወጣ፡የሚያጠፋውም፡ሳይኖር፡እንዳያቃጥል፥ለእግዚአብሔር፡ተገረዙ፥የልባችኹንም፡ሸለፈት፡አስወግዱ።
5፤በይሁዳ፡ዘንድ፡ተናገሩ፥በኢየሩሳሌምም፡ላይ፡አውሩና፦በአገሪቱ፡ላይ፡መለከት፡ንፉ፡በሉ፤ጮኻችኹም፦ዅላች ኹ፡ተሰብሰቡ፡ወደተመሸጉትም፡ከተማዎች፡እንግባ፡በሉ።
6፤ከሰሜን፡ክፉ፡ነገርንና፡ጽኑ፡ጥፋትን፡አመጣለኹና፡ወደ፡ጽዮን፡ዐላማን፡አንሡ፤ሽሹ፥አትዘግዩ።
7፤አንበሳ፡ከጭፍቅ፡ዱር፡ወጥቷል፥አሕዛብንም፡የሚዘርፍ፡ተነሥቷል፤ምድርሽን፡ባድማ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ከስፍራ ው፡ወጥቷል፥ከተማዎችሽም፡ሰው፡የሌለባቸው፡ፍርስራሾች፡ይኾናሉ።
8፤የእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡ከእኛ፡ዘንድ፡አልተመለሰምና፡ማቅ፡ልበሱ፥አልቅሱም፡ዋይም፡በሉ።
9፤በዚያም፡ቀን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የንጉሡና፡የመኳንንቱ፡ልብ፡ይጠፋል፥ካህናቱም፡ይደነቃሉ፡ነቢያቱም፡ይ ደነግጣሉ።
10፤እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ፥አንተ፡ሰይፍ፡እስከ፡ነፍስ፡ድረስ፡በደረሰ፡ጊዜ፦ሰላም፡ይኾንላችዃ ል፡ብለኽ፡ይህን፡ሕዝብና፡ኢየሩሳሌምን፡እጅግ፡አታለልኽ፡አልኹ።
11፤በዚያ፡ጊዜ፡ለዚህ፡ሕዝብና፡ለኢየሩሳሌም፦ለማበጠር፡ወይም፡ለማጥራት፡ሳይኾን፡የሚያቃጥል፡ነፋስ፡በምድ ረ፡በዳ፡ካሉ፡ከወናዎች፡ኰረብታዎች፡ወደወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ይመጣል፤
12፤ስለ፡እኔ፡ጽኑ፡የኾነ፡ነፋስ፡ከነዚህ፡ይመጣል፡ይባላል።አኹንም፡እኔ፡ደግሞ፡ፍርዴን፡በእነርሱ፡ላይ፡እ ናገራለኹ።
13፤እንሆ፥እንደ፡ደመና፡ይወጣል፥ሠረገላዎቹም፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፤ፈረሶቹም፡ከንስር፡ይልቅ፡ፈጣኖች፡ናቸ ው።ጠፍተናልና፥ወዮልን።
14፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ትድኚ፡ዘንድ፡ልብሽን፡ከክፉ፡ነገር፡ዕጠቢ።ክፉ፡ዐሳብ፡የሚኖርብሽ፡እስከ፡መቼ፡ድረስ ፡ነው፧
15፤የተናጋሪ፡ድምፅ፡ከዳን፡ዘንድ፡ይናገራልና፥ከኤፍሬምም፡ኰረብታዎች፡መከራን፡ያወራልና።
16፤ለአሕዛብ፡አሰሙና፦እንሆ፥ጠባቂዎች፡ከሩቅ፡አገር፡ይመጣሉ፤በይሁዳም፡ከተማዎች፡ላይ፡ይጮኻሉ፡ብላችኹ፡ በኢየሩሳሌም፡ላይ፡አውሩ።
17፤በእኔ፡ላይ፡ዐመፀኛ፡ኾናለችና፡በዙሪያዋ፡ከበ፟ው፡እንደ፡ዕርሻ፡ጠባቂዎች፡ኾነውባታል፥ይላል፡እግዚአብ ሔር።
18፤መንገድሽና፡ሥራሽ፡ይህን፡አድርጎብሻል፤ይህ፡ክፋትሽ፡መራር፡ነው፥ወደ፡ልብሽም፡ደርሷል።
19፤አንዠቴ! አንዠቴ! ልቤ፡በጣም፡ታሟ፟ል፥በውስጤም፡ልቤ፡ታውኮብኛል፤ነፍሴ፡ሆይ፥የመለከትን፡ድምፅና፡የሰልፍን፡ውካታ፡ሰምተሻ ልና፥ዝም፡እል፡ዘንድ፡አልችልም።
20፤መከራ፡በመከራ፡ላይ፡ተጠርቷል፤ምድርም፡ዅሉ፡ተበዝብዛለችና፤በድንገትም፡ድንኳኔ፡በቅጽበት፡ዐይንም፡መ ጋረጃዎቼ፡ጠፉ።
21፤ዐላማውን፡የምመለከት፥የመለከቱንስ፡ድምፅ፡የምሰማ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧
22፤ሕዝቤ፡ሰንፈዋልና፥አላወቁኝም፤ሰነፎች፡ልጆች፡ናቸው፥ማስተዋልም፡የላቸውም፤ክፉ፡ነገርን፡ለማድረግ፡ብ ልኀተኛዎች፡ናቸው፥በጎ፡ነገርን፡ማድረግ፡ግን፡አያውቁም።
23፤ምድሪቱን፡አየኹ፥እንሆም፥ባዶ፡ነበረች፡አንዳችም፡አልነበረባትም፤ሰማያትንም፡አየኹ፥ብርሃንም፡አልነበ ረባቸውም።
24፤ተራራዎችን፡አየኹ፥እንሆም፥ተንቀጠቀጡ፥ኰረብታዎችም፡ዅሉ፡ተናወጡ።
25፤አየኹ፥እንሆም፥ሰው፡አልነበረም፥የሰማይም፡ወፎች፡ዅሉ፡ሸሽተው፡ነበር።
26፤አየኹ፥እንሆም፥ፍሬያማ፡ዕርሻ፡ምድረ፡በዳ፡ኾነች፥ከተማዎችም፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ከጽኑ፡ቍጣው፡ የተነሣ፡ፈርሰው፡ነበር።
27፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ምድር፡ዅሉ፡ባድማ፟፡ትኾናለች፥ነገር፡ግን፥ፈጽሜ፡አላጠፋትም።
28፤ስለዚህ፥ምድር፡ታለቅሳለች፥በላይም፡ሰማይ፡ይጠቍራል፤ተናግሬያለኹና፥ዐስቤያለኹም፤አልጸጸትም፡ከርሱም ፡አልመለስም።
29፤ከፈረሰኛዎችና፡ከቀስተኛዎች፡ድምፅ፡የተነሣ፡ከተማ፡ዅሉ፡ሸሽታለች፤ወደችፍግ፡ዱርም፡ይገባሉ፡በቋጥኝ፡ ላይም፡ይወጣሉ፤ከተማ፡ዅሉ፡ተለቃ፟ለች፡የሚቀመጥባትም፡ሰው፡የለም።
30፤አንቺም፡የተበዘበዝሽ፡ሆይ፥ምን፡ታደርጊያለሽ፧ቀይ፡በለበስሽ፡ጊዜ፥በወርቅ፡አንባርም፡ባጌጥሽ፡ጊዜ፥ዐ ይንሽንም፡በኵል፡በተኳልሽ፡ጊዜ፥በከንቱ፡ታጌጫለሽ፤ውሽማዎችሽ፡አቃለሉሽ፥ነፍስሽን፡ይሿታል።
31፤እንደምታምጥ፡የበኵሯንም፡እንደምትወልድ፡ሴት፡ድምፅ፡ሰምቻለኹና፤የጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ድምፅ፡በድካም፡ይ ሰልላል፥እጆቿንም፡ትዘረጋለችና፦ተገድለው፡ከሞቱት፡የተነሣ፡ነፍሴ፡ዝላለችና፡ወዮልኝ! አለች።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5፤
1፤በኢየሩሳሌም፡መንገድ፡እየተመላለሳችኹ፡ሩጡ፥ተመልከቱም፥ዕወቁም፥በአደባባይዋም፡ፈልጉ፤ፍርድን፡የሚያደ ርገውን፡እውነትንም፡የሚሻውን፡ሰው፡ታገኙ፡እንደ፡ኾነ፡ይቅር፡እላታለኹ።
2፤እነርሱም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ቢሉ፡የሚምሉት፡በሐሰት፡ነው።
3፤አቤቱ፥ዐይንኽ፡እውነትን፡የምትመለከት፡አይደለችምን፧አንተ፡ቀሥፈኻቸዋል፥ነገር፡ግን፥አላዘኑም፥ቀጥቅጠ ኻቸውማል፥ነገር፡ግን፥ተግሣጽን፡እንቢ፡አሉ፤ፊታቸውን፡ከድንጋይ፡ይልቅ፡አጠንክረዋል፤ይመለሱ፡ዘንድ፡እን ቢ፡አሉ።
4፤እኔም፦የእግዚአብሔርን፡መንገድና፡የአምላካቸውን፡ሕግ፡አላወቁምና፡እነዚህ፡በእውነት፡ድኻዎችና፡ሰነፎች ፡ናቸው፤
5፤ወደ፡ታላላቆቹ፡እኼዳለኹ፡እናገራቸውማለኹ፤የእግዚአብሔርን፡መንገንድና፡የአምላካቸውን፡ሕግ፡ያውቃሉና፡ አልኹ።እነዚህ፡ግን፡ቀንበሩን፡በአንድነት፡ሰብረዋል፥እስራቱንም፡ቈርጠዋል።
6፤ስለዚህ፥ኀጢአታቸው፡በዝቷልና፥የክዳታቸውም፡ብዛት፡ጸንቷልና፤ስለዚህ፥አንበሳ፡ከዱር፡ወጥቶ፡ይሰብራቸዋ ል፥የበረሓም፡ተኵላ፡ያጠፋቸዋል፥ነብርም፡በከተማዎቻቸው፡ላይ፡ይተጋል፥ከዚያም፡የሚወጣ፡ዅሉ፡ይነጠቃል።
7፤በእነዚህ፡ነገሮች፡ይቅር፡የምልሽ፡እንዴት፡አድርጌ፡ነው፧ልጆችሽ፡ትተውኛል፡አማልክትም፡ባልኾኑ፡ምለዋል ፤ካጠገብዃቸውም፡በዃላ፡አመነዘሩ፡በጋለሞታዎቹም፡ቤት፡ተሰበሰቡ።
8፤እንደ፡ተቀለቡ፡ፈረሶች፡ኾኑ፤እያንዳንዳቸውም፡ከባልንጀራዎቻቸው፡ሚስቶች፡ዃላ፡አሽካኩ።
9፤በእውኑ፡ስለ፡እነዚህ፡ነገሮች፡አልቀሥፍምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ነፍሴስ፡እንደዚህ፡ባለ፡ሕዝብ፡ላይ፡አ ትበቀልምን፧
10፤ወደ፡ቅጥሯ፡ወጥታችኹ፡አፍርሱ፥ነገር፡ግን፥ፈጽማችኹ፡አታጥፉ፤ለእግዚአብሔር፡አይደሉምና፡ቅርንጫፏን፡ ውሰዱ።
11፤የእስራኤል፡ቤትና፡የይሁዳ፡ቤት፡በእኔ፡ላይ፡እጅግ፡ወንጅለዋል፡ይላል፡እግዚአብሔር።
12፤እነርሱም፦ርሱ፡አይደለም፥ክፉ፡ነገርም፡አይመጣብንም፡ሰይፍንና፡ራብንም፡አናይም፤ነቢያትም፡ነፋስ፡ይኾ ናሉ፥
13፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በእነርሱ፡ዘንድ፡የለም፥እንዲህም፡ይደረግባቸዋል፡ብለው፡እግዚአብሔርን፡ክደዋል ።
14፤ስለዚህም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚህ፡ቃል፡ተናግራችዃልና፥እንሆ፥በአፍኽ፡ውስ ጥ፡ቃሌን፡እሳት፡ይህንም፡ሕዝብ፡ዕንጨት፡አደርጋለኹ፥ትበላቸውማለች።
15፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንሆ፥ሕዝብን፡ከሩቅ፡አመጣባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ኀያል፡ጥንታዊ፡ሕዝብ ፡ነው፥ቋንቋቸውንም፡የማታውቀው፡የሚናገሩትንም፡የማታስተውለው፡ሕዝብ፡ነው።
16፤የፍላጻቸውም፡ሰገባ፡እንደ፡ተከፈተ፡መቃብር፡ነው፥ዅሉም፡ኀያላን፡ናቸው።
17፤መከርኽንና፡እንጀራኽን፡ይበላሉ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችኽንም፡ይበሏቸዋል፤በጎችኽንና፡ላሞችኽንም፡ይበ ላሉ፤ወይንኽንና፡በለስኽንም፡ይበላሉ፤የምትታመናቸውን፡የተመሸጉ፡ከተማዎችን፡በሰይፍ፡ይደበድባሉ።
18፤ነገር፡ግን፥በዚያ፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ፈጽሜ፡አላጠፋችኹም።
19፤እንዲህም፡ይኾናል፤እናንተ፦አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ስለ፡ምን፡አደረገብን፧ብትሉ፥ አንተ፦እንደ፡ተዋችኹኝ፡በአገራችኹም፡ሌላዎችን፡አማልክት፡እንዳመለካችኹ፥እንዲሁ፡ለእናንተ፡ባልኾነ፡አገ ር፡ለሌላዎች፡ሰዎች፡ትገዛላችኹ፡ትላቸዋለኽ።
20፤ይህን፡በያዕቆብ፡ቤት፡አውሩ፥በይሁዳም፡አሰሙ።
21፤እናንተ፡ሰነፎች፡ልበ፡ቢሶች፥ዐይን፡እያላችኹ፡የማታዩ፥ዦሮም፡እያላችኹ፡የማትሰሙ፡ሕዝብ፡ሆይ፥ይህን፡ ስሙ።
22፤በእውኑ፡እኔን፡አትፈሩምን፧ከፊቴስ፡አትደነግጡምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤እንዳያልፍ፡አሸዋን፡በዘለዓለ ም፡ትእዛዝ፡ለባሕር፡ዳርቻ፡አድርጌያለኹ፤ሞገዱም፡ቢናወጥ፡አያሸንፍም፥ቢጮኽም፡አያልፍበትም።
23፤ለዚህ፡ሕዝብ፡ግን፡የሸፈተና፡ያመፀ፡ልብ፡አላቸው፤ዐምፀዋል፥ኼደውማል።
24፤በልባቸውም፦የፊተኛውንና፡የዃለኛውን፡ዝናብ፡በጊዜው፡የሚሰጠውን፥ለመከርም፡የተመደቡትን፡ወራት፡የሚጠ ብቅልንን፡አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡እንፍራ፡አላሉም።
25፤በደላችኹ፡እነዚህን፡አስቀርታለች፥ኀጢአታችኹም፡መልካምን፡ነገር፡ከለከለቻችኹ።
26፤በሕዝቤ፡መካከል፡ክፉዎች፡ሰዎች፡ተገኝተዋል፤እንደ፡አጥማጆችም፡ያደባሉ፥ወጥመድንም፡ይዘረጋሉ፡ሰዎችን ም፡ያጠምዳሉ።
27፤ቀፎ፡ወፎችን፡እንደሚሞላ፥እንዲሁ፡ቤታቸው፡ሽንገላን፡ሞልታለች፤እንዲሁም፡ከብረዋል፡ባለጠጋዎችም፡ኾነ ዋል።
28፤ወፍረዋል፡ሰብተውማል፥ክፋታቸውንም፡ያለልክ፡አብዝተዋል፤የድኻ፡አደጎች፡ነገር፡መልካም፡እንዲኾን፡አል ተሟገቱላቸውም፥የችግረኛዎችንም፡ፍርድ፡አልፈረዱላቸውም።
29፤በእውኑ፡ስለ፡እነዚህ፡ነገሮች፡አልቀሥፍምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ነፍሴስ፡እንደዚህ፡ባለ፡ሕዝብ፡ላይ፡ አትበቀልምን፧
30፤የምታስደንቅና፡የምታስደነግጥ፡ነገር፡በምድር፡ላይ፡ኾናለች፤
31፤ነቢያት፡በሐሰት፡ትንቢት፡ይናገራሉ፥ካህናትም፡በእነዚህ፡እጅ፡ይገዛሉ፥ሕዝቤም፡እንዲህ፡ያለውን፡ነገር ፡ይወዳ፟ሉ፤በፍጻሜውስ፡ምን፡ታደርጋላችኹ፧
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6፤
1፤እናንተ፡የብንያም፡ልጆች፥ክፉ፡ነገር፡ታላቅም፡ጥፋት፡ከሰሜን፡ይጐበኛልና፥ከኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡ሽሹ፥በቴ ቁሔ፡መለከቱን፡ንፉ፥በቤትሐካሪም፡ላይ፡ምልክት፡አንሡ።
2፤የተዋበችውንና፡የተሰባቀለችውን፡የጽዮንን፡ልጅ፡አጐሰቍላለኹ።
3፤እረኛዎችና፡መንጋዎቻቸው፡ወደ፡ርሷ፡ይመጣሉ፥በዙሪያዋም፡ድንኳኖቻቸውን፡ይተክሉባታል፥እያንዳንዱም፡በስ ፍራው፡መንጋውን፡ያሰማራል።
4፤በርሷ፡ላይ፡ሰልፍ፡አዘጋጁ፥ተነሡ፥በቀትርም፡እንውጣ።ቀኑ፡መሽቷልና፥የማታውም፡ጥላ፡ረዝሟልና፥ወዮልን።
5፤ተነሡ፡በሌሊትም፡እንውጣ፥አዳራሾቿንም፡እናፍርስ።
6፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ዛፎቿን፡ቍረጡ፥በኢየሩሳሌምም፡ላይ፡ዐፈርን፡ደልድሉ፤ይህ ች፡ከተማ፡የምትቀሠፍ፡ናት፤መካከሏ፡ዅሉ፡ግፍ፡ብቻ፡ነው።
7፤በጕድጓድ፡ውሃ፡እንደሚፈልቅ፥እንዲሁ፡ክፋቷ፡ከርሷ፡ዘንድ፡ይፈልቃል፤ግፍና፡ቅሚያ፡በርሷ፡ዘንድ፡ይሰማል ፥ደዌና፡ቍስልም፡ዅልጊዜ፡በፊቴ፡አለ።
8፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ነፍሴ፡ከአንቺ፡እንዳትለይ፥አንቺንም፡ባድማና፡ወና፡እንዳላደርግሽ፥ተግሣጽን፡ተቀበዪ።
9፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰው፡ወይኑን፡እንደሚቃርም፥እንዲሁ፡ከእስራኤል፡የቀሩትን፡ፈጽሞ፡ይቃርሟቸ ዋል፤እጅኽንም፡እንደ፡ለቃሚ፡ወደ፡እንቅብ፡ዘርጋ።
10፤ይሰሙኝስ፡ዘንድ፡ለማን፡እናገራለኹ፧ለማንስ፡አስጠነቅቃለኹ፧እንሆ፥ዦሯቸው፡ያልተገረዘች፡ናት፡ለመስማ ትም፡አይችሉም፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ለስድብ፡ኾኖባቸዋል፥ደስም፡አያሠኛቸውም።
11፤ስለዚህ፥በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ተሞልቻለኹ፤ከመታገሥ፡ደክሜያለኹ፤በሜዳ፡በሕፃናት፡ላይ፡በጕልማሳዎችም፡ ጉባኤ፡ላይ፡በአንድነት፡አፍሰ፟ው፤ባል፡ከሚስቱ፡ጋራ፡ሽማግሌውም፡ከጐበዙ፡ጋራ፡ይያያዛልና።
12፤እጄን፡በምድር፡በሚኖሩ፡ላይ፡እዘረጋለኹና፥ቤቶቻቸው፡ዕርሻዎቻቸውም፡ሴቶቻቸውም፡በአንድነት፡ለሌላዎች ፡ይኾናሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
13፤ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ዅሉ፡ሥሥትን፡ያስባሉና፥ከነቢዩም፡ዠምሮ፡እስከ፡ካህኑ፡ድረስ፡ዅሉ ፡በተንኰል፡ያደርጋሉና።
14፤የሕዝቤንም፡ስብራት፡በጥቂቱ፡ይፈውሳሉ፤ሰላም፡ሳይኾን፦ሰላም፡ሰላም፡ይላሉ።
15፤ርኩስን፡ነገር፡ስለ፡ሠሩ፡ዐፍረዋልን፧ምንም፡አላፈሩም፥ዕፍረትንም፡አላወቁም፤ስለዚህ፥ከሚወድቁ፡ጋራ፡ ይወድቃሉ፤በጐበኘዃቸው፡ጊዜ፡ይዋረዳሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
16፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመንገድ፡ላይ፡ቁሙ፡ተመልከቱም፥የቀደመችውንም፡መንገድ፡ጠይቁ፤መልካሚቱ ፡መንገድ፡ወዴት፡እንደ፡ኾነች፡ዕወቁ፥በርሷም፡ላይ፡ኺዱ፥ለነፍሳችኹም፡ዕረፍት፡ታገኛላችኹ፤እነርሱ፡ግን፦ አንኼድባትም፡አሉ።
17፤እኔም፦የመለከቱን፡ድምፅ፡አድምጡ፡ብዬ፡ጠባቂዎችን፡ሾምኹባችኹ፤እነርሱ፡ግን፦አናደምጥም፡አሉ።
18፤አሕዛብ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ስሙ፤ማኅበር፡ሆይ፥እነዚያ፡የሚያገኛቸውን፡ዕወቁ።
19፤ምድር፡ሆይ፥ስሚ፤እንሆ፥ቃሌን፡ስላልሰሙ፥ሕጌንም፡ስለ፡ጣሉ፥በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡የዐሳባቸውን፡ፍሬ፥ክፉ ን፡ነገር፡አመጣባቸዋለኹ።
20፤ስለ፡ምንስ፡ከሳባ፡ዕጣንን፥ከሩቅም፡አገር፡ቀረፋን፡ታቀርቡልኛላችኹ፧የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹን፡አል ቀበለውም፡ሌላ፡መሥዋዕታችኹም፡ደስ፡አያሠኘኝም።
21፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከዚህ፡ሕዝብ፡ፊት፡ዕንቅፋቶችን፡አደርጋለኹ፤አባቶችና፡ል ጆች፡በአንድነት፡ይሰናከሉባቸዋል፥ጎረቤትና፡ባልንጀራም፡ይጠፋሉ።
22፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሕዝብ፡ከሰሜን፡አገር፡ይመጣል፥ታላቅ፡ሕዝብም፡ከምድር፡ዳርቻ፡ይነ ሣል።
23፤ቀስትንና፡ጦርን፡ይይዛሉ፤ጨካኞች፡ናቸው፥ምሕረትንም፡አያደርጉም፤ድምፃቸው፡እንደ፡ባሕር፡ይተማ፟ል፥በ ፈረሶችም፡ላይ፡ይቀመጣሉ፤የጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ለሰልፍ፡እንደ፡ተዘጋጀ፡ሰው፡እያንዳንዳቸው፡ባንቺ፡ላይ ፡ተሰለፉ።
24፤ወሬውን፡ሰምተናል፥እጃችን፡ደክማለች፤ምጥ፡ወላድን፡ሴት፡እንደሚይዛት፡ጭንቀት፡ይዞናል።
25፤የጠላት፡ሰይፍና፡ድንጋጤ፡ከበ፟ዋችዃልና፥ወደ፡ሜዳ፡አትውጡ፡በምንገድም፡ላይ፡አትኺዱ።
26፤የሕዝቤ፡ልጅ፡ሆይ፥ማቅ፡ልበሺ፡በዐመድም፡ውስጥ፡ተንከባለዪ፤አጥፊ፡በላያችን፡በድንገት፡ይመጣብናልና፥ ለአንድያ፡ልጅ፡እንደሚደረግ፡ልቅሶ፥መራራ፡ልቅሶ፡አልቅሺ።
27፤መንገዳቸውን፡እንድታውቅና፡እንድትፈትን፡በሕዝቤ፡መካከል፡ፈታኝ፡አድርጌኻለኹ።
28፤እነርሱ፡ዅሉ፡እጅግ፡ዐመፀኛዎች፡ናቸው፤በጠማማነት፡ይኼዳሉ፤ናስና፡ብረት፡ናቸው፤ዅሉ፡ርኵሰትን፡ያደር ጋሉ።
29፤ወናፍ፡አናፋ፡ርሳሱም፡በእሳት፡ቀለጠ፤አንጥረኛውም፡መልሶ፡በከንቱ፡ያቀልጠዋል፤ኀጢአተኛዎች፡አልተወገ ዱም።
30፤እግዚአብሔር፡ጥሏቸዋልና፥የተጣለ፡ብር፡ብለው፡ይጠሯቸዋል።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7፤
1፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤በእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡ቁም፥ይህንም፡ቃል፡እንዲህ፡ብለኽ፡ተናገር፦እግዚአብሔርን፡ልታመልኩ፡በእነዚህ ፡በሮች፡የምትገቡ፡ከይሁዳ፡ያላችኹ፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
3፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡አሳምሩ፡በዚህም፡ስፍራ፡አሳ ድራችዃለኹ።
4፤የእግዚአብሔር፡መቅደስ፥የእግዚአብሔር፡መቅደስ፥የእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ይህ፡ነው፡እያላችኹ፡በሐሰት፡ቃ ል፡አትታመኑ።
5፤መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡ፈጽማችኹ፡ብታሳምሩ፥በሰውና፡በጎረቤቱ፡መካከል፡ቅን፡ፍርድ፡ብትፈርዱ፥
6፤መጻተኛውንና፡ድኻ፡አደጉን፡መበለቲቱንም፡ባትገፉ፥በዚህም፡ስፍራ፡ንጹሕ፡ደምን፡ባታፈሱ፟፥ክፉም፡ሊኾንባ ችኹ፡እንግዳዎችን፡አማልክት፡ባትከተሉ፥
7፤ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡ለአባቶቻችኹ፡በሰጠዃቸው፡ምድር፡በዚህ፡ስፍራ፡አሳድራችዃለኹ።
8፤እንሆ፥በማትረቡበት፡በሐሰት፡ቃል፡ታምናችዃል።
9፤ትሰርቃላችኹ፥ትገድላላችኹ፥ታመነዝራላችኹ፥በሐሰትም፡ትምላላችኹ፥ለበዓልም፡ታጥናላችኹ፥የማታውቋቸውንም ፡እንግዳዎች፡አማልክት፡ትከተላላችኹ፤
10፤መጣችኹም፥ስሜም፡በተጠራበት፡በዚህ፡ቤት፡በፊቴ፡ቆማችኹ፦ይህን፡አስጸያፊ፡የኾነ፡ነገርን፡ዅሉ፡አላደረ ግንም፡አላችኹ።
11፤ይህስ፡ስሜ፡የተጠራበት፡ቤት፡በዐይናችኹ፡የሌቦች፡ዋሻ፡ኾኗልን፧እንሆ፥እኔ፡አይቻለኹ፥ይላል፡እግዚአብ ሔር።
12፤ነገር፡ግን፥በቀድሞ፡ዘመን፡ስሜን፡ወዳሳደርኹበት፡በሴሎ፡ወደነበረው፡ስፍራዬ፡ኺዱ፥ከሕዝቤም፡ከእስራኤ ል፡ክፋት፡የተነሣ፡ያደረግኹበትን፡እዩ።
13፤አኹንም፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ስላደረጋችኹ፥በማለዳም፡ተነሥቼ፡በተናገርዃችኹ፡ጊዜ፡ስላልሰማችኹ፥በጠራዃ ችኹም፡ጊዜ፡ስላልመለሳችኹ፥
14፤ስለዚህ፥በሴሎ፡እንዳደረግኹ፡እንዲሁ፥ስሜ፡በተጠራበት፥በምትታመኑበት፡ቤት፥ለእናንተና፡ለአባቶቻችኹም ፡በሰጠዃችኹ፡ስፍራ፡አደርጋለኹ።
15፤የኤፍሬምንም፡ዘር፡ዅሉ፥ወንድሞቻችኹን፡ዅሉ፡እንደ፡ጣልኹ፥እንዲሁ፡ከፊቴ፡እጥላችዃለኹ።
16፤እንግዲህም፡አልሰማኽምና፡ስለዚህ፡ሕዝብ፡አትጸልይ፡ስለ፡እነርሱም፡ልመናና፡ጸሎት፡አታድርግ፤አትማልድ ላቸው።
17፤እነርሱስ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ውስጥና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ላይ፡የሚያደርጉትን፡አታይምን፧
18፤ያስቈጡኝ፡ዘንድ፥ለሰማይ፡ንግሥት፡ዕንጐቻ፡እንዲያደርጉ፡ለሌላዎችም፡አማልክት፡የመጠጥ፡ቍርባን፡እንዲ ያፈሱ፟፡ልጆች፡ዕንጨት፡ይሰበስባሉ፥አባቶችም፡እሳት፡ያነዳ፟ሉ፥ሴቶችም፡ዱቄት፡ይለውሳሉ።
19፤እኔን፡ያስቈጣሉን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ለፊታቸውስ፡ዕፍረት፡አይደለምን፧
20፤እንግዲህም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ቍጣዬና፡መዓቴ፡በዚህ፡ስፍራ፡ላይ፥በሰውና፡በእን ስሳ፡ላይ፥በዱር፡ዛፎችና፡በምድር፡ፍሬ፡ላይ፡ይፈሳ፟ል፤ይነዳ፟ል፥አይጠፋምም።
21፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለሌላ፡መሥዋዕታችኹ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹን፡ጨምሩ፥ሥጋውንም፡ብሉ።
22፤ከግብጽ፡ምድር፡ባወጣዃችኹ፡ቀን፡ስለሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡ስለ፡ሌላ፡መሥዋዕት፡ለአባቶቻችኹ፡አልተናገር ኹምና፥አላዘዝዃቸውምም።
23፤ነገር፡ግን፦ቃሌን፡ስሙ፥እኔም፡አምላክ፡እኾናችዃለኹ፡እናንተም፡ሕዝብ፡ትኾኑኛላችኹ፤መልካምም፡ይኾንላ ችኹ፡ዘንድ፡ባዘዝዃችኹ፡መንገድ፡ዅሉ፡ኺዱ፡ብዬ፡በዚህ፡ነገር፡አዘዝዃቸው።
24፤ነገር፡ግን፥በክፉ፡ልባቸው፡ዐሳብና፡እልከኝነት፡ኼዱ፡ወደ፡ፊትም፡ሳይኾን፡ወደ፡ዃላቸው፡ኼዱ፡እንጂ፡አ ልሰሙም፡ዦሯቸውንም፡አላዘነበሉም።
25፤አባቶቻችኹ፡ከግብጽ፡ምድር፡ከወጡበት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፥በየዕለቱ፡እየማለድኹ፡ባሪያዎቼን ፡ነቢያትን፡ዅሉ፡ልኬባችኹ፡ነበር።
26፤ነገር፡ግን፥ዐንገታቸውን፡አደነደኑ፡እንጂ፡አልሰሙኝም፡ዦሯቸውንም፡አላዘነበሉም፤አባቶቻቸውም፡ካደረጉ ት፡ይልቅ፡የባሰ፡አደረጉ።
27፤በዚህም፡ቃል፡ዅሉ፡ትነግራቸዋለኽ፥ነገር፡ግን፥አይሰሙኽም፤ትጠራቸውማለኽ፥ነገር፡ግን፥አይመልሱልኽም።
28፤አንተም፦የአምላኩን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ያልሰማ፥ተግሣጽንም፡ያልተቀበለ፡ሕዝብ፡ይህ፡ነው፤እውነት፡ ጠፍቷል፡ከአፋቸውም፡ተቈርጧል፡ትላቸዋለኽ።
29፤እግዚአብሔር፡የቍጣውን፡ትውልድ፡ጥሏልና፥ትቶታልምና፡ጠጕርሽን፡ቍረጪ፥ጣዪውም፥በወናዎች፡ኰረብታዎችም ፡ላይ፡አሙሺ።
30፤የይሁዳ፡ልጆች፡በፊቴ፡ክፉን፡ነገር፡ሠርተዋል፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ያረክሱትም፡ዘንድ፡ስሜ፡በተጠራበት ፡ቤት፡ርኵሰታቸውን፡አኑረዋል።
31፤እኔም፡ያላዘዝኹትንና፡በልቤ፡ያላሰብኹትን፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡ያቃጥሉ፡ዘንድ፡በሄኖ ም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ያለችውን፡የቶፌትን፡መስገጃዎች፡ሠረተዋል።
32፤ስለዚህ፥እንሆ፥ስፍራ፡ከማጣት፡የተነሣ፡በቶፌት፡ይቀበራሉና፡የዕርድ፡ሸለቆ፡ይባላል፡እንጂ፡ቶፌት፡ወይ ም፡የሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ዳግመኛ፡የማይባልበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
33፤የዚህም፡ሕዝብ፡ሬሳ፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡መብል፡ይኾናል፥የሚያስፈራራቸውም፡የለም።
34፤ምድሪቱም፡ባድማ፡ትኾናለችና፡ከይሁዳ፡ከተማዎችና፡ከኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡የእልልታን፡ድምፅና፡የደስታ ን፡ድምፅ፥የወንድ፡ሙሽራን፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራን፡ድምፅ፡አጠፋለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8፤
1፤በዚያን፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የይሁዳን፡ነገሥታት፡ዐጥንትና፡የመኳንንቶቹን፡ዐጥንት፥የካህናቱን፡ ዐጥንትና፡የነቢያቱን፡ዐጥንት፥የኢየሩሳሌምንም፡ሰዎች፡ዐጥንት፡ከመቃብራቸው፡ያወጣሉ።
2፤በወደዷቸውና፡ባመለኳቸው፥በተከተሏቸውና፡በፈለጓቸው፥በሰገዱላቸውም፡በፀሓይና፡በጨረቃ፡በሰማይም፡ሰራዊ ት፡ዅሉ፡ፊት፡ይዘረጓቸዋል፤አያከማቿቸውም፡አይቀብሯቸውምም፥በምድርም፡ፊት፡ላይ፡እንደ፡ጕድፍ፡ይኾናሉ።
3፤እኔም፡ባሳደድዃቸው፡ስፍራ፡ዅሉ፡የቀሩ፥ከዚች፡ክፉ፡ወገን፡የተረፉ፡ቅሬታዎች፡ዅሉ፥ከሕይወት፡ይልቅ፡ሞት ን፡ይመርጣሉ።
4፤እንዲህም፡ትላቸዋለኽ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የወደቁ፡አይነሡምን፧የሳተስ፡አይመለስምን፧
5፤እንግዲህ፡ይህ፡የኢየሩሳሌም፡ሕዝብ፡ዘወትር፡ስለ፡ምን፡ወደ፡ዃላው፡ይመለሳል፧ተንኰልን፡ይዟል፡ሊመለስም ፡እንቢ፡ብሏል።
6፤አደመጥኹ፡ሰማኹም፤ቅንን፡ነገር፡አልተናገሩም፤ማናቸውንም፦ምን፡አድርጌያለኹ፧ብሎ፡ከክፋቱ፡ንስሓ፡የገባ ፡የለም፤ወደ፡ሰልፍም፡እንደሚሮጥ፡ፈረስ፡እያንዳንዱ፡በየመንገዱ፡ይኼዳል።
7፤ሽመላ፡በሰማይ፡ጊዜዋን፡ዐውቃለች፤ዋኖስና፡ጨረባ፡ዋልያም፡የመምጣታቸውን፡ጊዜ፡ይጠብቃሉ፤ሕዝቤ፡ግን፡የ እግዚአብሔርን፡ፍርድ፡አላወቁም።
8፤እናንተስ።ጥበበኛዎች፡ነን፡የእግዚአብሔርም፡ሕግ፡ከእኛ፡ጋራ፡ነው፡እንዴት፡ትላላችኹ፧እንሆ፥የጸሓፊ፡ብ ርዕ፡ሐሰተኛ፡ነው፥በሐሰትም፡አድርጓል።
9፤ጥበበኛዎች፡ዐፍረዋል፥ደንግጠውማል፥ተማርከውማል፤እንሆ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ጥለዋል፤ምን፡ዐይነት፡ጥ በብ፡አላቸው፧
10፤ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ዅሉ፡ሥሥትን፡ያስባሉና፥ከነቢዩም፡ዠምሮ፡እስከ፡ካህኑ፡ድረስ፡ዅሉ ፡በተንኰል፡ያደርጋሉና፡ስለዚህ፡ሚስቶቻቸውን፡ለሌላዎች፥ዕርሻቸውንም፡ለሚወርሱባቸው፡እሰጣለኹ።
11፤የሕዝቤንም፡ሴት፡ልጅ፡ስብራት፡በጥቂቱ፡ይፈውሳሉ፤ሰላም፡ሳይኾን፦ሰለም፡ሰላም፡ይላሉ።
12፤አስጸያፊ፡ነገርን፡ስለ፡ሠሩ፡ዐፍረዋልን፧ምንም፡አላፈሩም፥ዕፍረትንም፡አላወቁም፤ስለዚህ፥ከሚወድቁ፡ጋ ራ፡ይወድቃሉ፤በጐበኘዃቸው፡ጊዜ፡ይዋረዳሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
13፤ፈጽሜ፡አጠፋችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በወይን፡ላይ፡ፍሬ፥በበለስ፡ዛፍ፡ላይ፡በለስ፡አይኾንም፥ቅጠል ም፡ይረግፋል፤የሚያልፉባቸውንም፡ሰጠዃቸው።
14፤ዝም፡ብለን፡ለምን፡እንቀመጣለን፧እግዚአብሔርን፡ስለ፡በደልን፡አምላካችን፡እግዚአብሔር፡አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም፡ውሃ፡አጠጥቶናልና፥ተሰብስባችኹ፡ወደተመሸጉ፡ከተማዎች፡እንግባ፥በዚያም፡እንጥፋ።
15፤ሰላምን፡በተስፋ፡ተጠባበቅን፥መልካምም፡አልተገኘም፤መጠገንን፡በተስፋ፡ተጠባበቅን፥እንሆም፥ድንጋጤ፡ኾ ነ።
16፤የፈረሰኛዎቹ፡ድምፅ፡ከዳን፡ተሰማ፤ከዐርበኛዎች፡ፈረሶች፡ማሽካካት፡የተነሣ፡ምድር፡ዅሉ፡ተንቀጠቀጠች፤ መጡም፡ምድሪቱንና፡በርሷም፡ያለውን፡ዅሉ፥ከተማዪቱንና፡የተቀመጡባትንም፡በሉ።
17፤እንሆ፥አስማት፡የማይከለክላቸውን፡እባቦችንና፡እፍኝቶችን፡እሰድ፟ባ፟ችዃለኹ፤እነርሱም፡ይነድፏችዃል።
18፤ሐዘኔ፡የማይጽናና፡ነው፥ልቤም፡በውስጤ፡ደክሟል።
19፤እንሆ፦እግዚአብሔር፡በጽዮን፡የለምን፧ወይስ፡ንጉሧ፡በርሷ፡ዘንድ፡የለምን፧የሚል፡የወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ጩ ኸት፡ድምፅ፡ከሩቅ፡አገር፡ተሰማ።በተቀረጹ፡ምስሎቻቸውና፡በባዕድ፡ከንቱነትስ፡ያስቈጡኝ፡ስለ፡ምንድር፡ነው ፧
20፤መከሩ፡ዐልፏል፥በጋው፡ኼዷል፥እኛም፡አልዳን፟ም።
21፤በሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ስብራት፡እኔ፡ተሰብሬያለኹ፡ጠቍሬማለኹ፤አድናቆትም፡ይዞኛል።
22፤በገለዓድ፡የሚቀባ፡መድኀኒት፡የለምን፧ወይስ፡በዚያ፡ሐኪም፡የለምን፧የወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ፈውስ፡ስለ፡ምን ፡አልኾነም፧
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9፤
1፤ተወግተው፡ስለ፡ሞቱ፡ስለሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ሰዎች፡ሌሊትና፡ቀን፡አለቅስ፡ዘንድ፡ራሴ፡ውሃ፥ዐይኔም፡የእንባ ፡ምንጭ፡በኾነልኝ!
2፤ዅሉም፡አመንዝራዎች፥የአታላዮች፡ጉባኤ፡ናቸውና፥ሕዝቤን፡እተዋቸው፡ዘንድ፡ከነርሱም፡እለይ፡ዘንድ፡በምድ ረ፡በዳ፡የመንገደኛዎች፡ማደሪያን፡ማን፡በሰጠኝ፧
3፤ምላሳቸውን፡ስለ፡ሐሰት፡እንደ፡ቀስት፡ገተሩ፤በምድር፡በረቱ፥ነገር፡ግን፥ለእውነት፡አይደለም፤ከክፋት፡ወ ደ፡ክፋት፡ይኼዳሉና፡እኔንም፡አላወቁምና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4፤ወንድምም፡ዅሉ፡ያሰናክላልና፥ባልንጀራም፡ዅሉ፡ያማልና፥እናንተ፡ዅሉ፡ከባልንጀራዎቻችኹ፡ተጠንቀቁ፥በወን ድሞቻችኹም፡አትታመኑ።
5፤ሰውም፡ዅሉ፡ባልንጀራውን፡ያታልላል፥በእውነትም፡አይናገርም፤ሐሰትን፡መናገርንም፡ምላሳቸው፡ተምሯል፥ክፉ ንም፡ለማድረግ፡ይደክማሉ።
6፤ማደሪያኽ፡በሽንገላ፡መካከል፡ነው፥ከሽንገላም፡የተነሣ፡እኔን፡ያውቁኝ፡ዘንድ፡እንቢ፡ብለዋል፥ይላል፡እግ ዚአብሔር።
7፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥አቀልጣቸዋለኹ፡እፈትናቸውማለኹ፤ስለሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ክፋት ፡ከዚህ፡ሌላ፡የማደርገው፡ምንድር፡ነው፧
8፤ምላሳቸው፡የተሳለ፡ፍላጻ፡ነው፤ሽንገላን፡ይናገራሉ፡ሰው፡ከባልንጀራው፡ጋራ፡በሰላም፡ይናገራል፥በልቡ፡ግ ን፡ያደባበታል።
9፤በእውኑ፡ስለዚህ፡ነገር፡አልቀሥፍምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ነፍሴስ፡እንደዚህ፡ባለ፡ሕዝብ፡ላይ፡አትበቀል ምን፧
10፤ለተራራዎች፡ልቅሶን፡ለምድረ፡በዳ፡ማሰማሪያዎችም፡ዋይታን፡አነሣለኹ፥ሰው፡እንዳያልፍባቸው፡በእሳት፡ተ ቃጥለዋልና።ሰዎችም፡የከብቱን፡ድምፅ፡አይሰሙም፤ከሰማይ፡ወፎች፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡ሸሽተው፡ኼደ ዋል።
11፤ኢየሩሳሌምንም፡የፍርስራሽ፡ክምር፡የቀበሮም፡ማደሪያ፡አደርጋታለኹ፥የይሁዳንም፡ከተማዎች፡ሰው፡የማይቀ መጥባት፡ባድማ፡አደርጋቸዋለኹ።
12፤ይህን፡የሚያስተውል፡ጠቢብ፡ሰው፡ማን፡ነው፧ያወራስ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡አፍ፡ለማን፡ተናገረ፧ሰው፡እ ንዳያልፍባት፡ምድርስ፡ስለ፡ምን፡ጠፋች፥እንደ፡ምድረ፡በዳስ፡ስለ፡ምን፡ተቃጠለች፧
13፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለ፦የሰጠዃቸውን፡ሕጌን፡ትተዋልና፥ቃሌንም፡አልሰሙምና፥
14፤ነገር፡ግን፥የልባቸውን፡ምኞትና፡አባቶቻቸው፡ያስተማሯቸውን፡በዓሊምን፡ተከትለዋልና፥
15፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህን፡ሕዝብ፡ሬትን፡አበላዋለኹ፡የሐ ሞትንም፡ውሃ፡አጠጣዋለኹ።
16፤እነርሱና፡አባቶቻቸውም፡ባላወቋቸው፡አሕዛብ፡መካከል፡እበትናቸዋለኹ፥እስካጠፋቸውም፡ድረስ፡በስተዃላቸ ው፡ሰይፍን፡እሰድ፟ባቸዋለኹ።
17፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲመጡ፡አልቃሾች፡ሴቶችን፡ጥሩ፤እንዲመጡም፡ወደ፡ብልኀተኛዎች፡ሴቶች፡ ላኩ፤
18፤ዐይኖቻችንም፡እንባ፡እንዲያፈሱ፟፡የዐይናችንም፡ሽፋሽፍቶች፡ውሃን፡እንዲያፈልቁ፡ፈጥነው፡ለእኛ፡ልቅሶ ውን፡ይያዙ።
19፤በጽዮን፦እንዴት፡ተበዘበዝን! ምድርንም፡ትተናልና፥ቤቶቻችንንም፡አፍርሰዋልና፥እንዴት፡ዐፈርን! የሚል፡የልቅሶ፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
20፤እናንተ፡ሴቶች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፥ዦሯችኹም፡የአፉን፡ቃል፡ትቀበል፥ለሴቶች፡ልጆቻችኹም፡ ልቅሶውን፥እያንዳንዳችኹም፡ለባልንጀራዎቻችኹ፡ዋይታውን፡አስተምሩ።
21፤ሕፃናቱን፡ከመንገድ፡ጕልማሳዎቹንም፡ከአደባባይ፡ያጠፉ፡ዘንድ፡ሞት፡ወደ፡መስኮታችን፡ደርሷል፡ወደ፡አዳ ራሻችንም፡ውስጥ፡ገብቷል።
22፤የሰውም፡ሬሳ፡እንደ፡ጕድፍ፡በዕርሻ፡ላይ፥ማንምም፡እንደማይሰበስበው፡ከዐጫጆች፡በዃላ፡እንደሚቀር፡ቃር ሚያ፡ይወድቃል።
23፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጠቢብ፡በጥበቡ፡አይመካ፥ኀያልም፡በኀይሉ፡አይመካ፥ባለጠጋም፡በብልጥግናው ፡አይመካ፤
24፤ነገር፡ግን፥የሚመካው።ምሕረትንና፡ፍርድን፡ጽድቅንም፡በምድር፡ላይ፡የማደርግ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡መኾኔ ን፡በማወቁና፡በማስተዋሉ፡በዚህ፡ይመካ፤ደስ፡የሚያሠኙኝ፡እነዚህ፡ናቸውና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
25-26፤አሕዛብ፡ዅሉ፡ያልተገረዙ፡ናቸውና፥የእስራኤልም፡ቤት፡ዅሉ፡ልባቸው፡ያልተገረዘ፡ነውና፥የተገረዙትን፡ ዅሉ፥ግብጽንና፡ይሁዳን፡ኤዶምያስንም፡የዐሞንንም፡ልጆች፡ሞዐብንም፡በምድረ፡በዳም፡የተቀመጡትን፡ጠጕራቸው ን፡በዙሪያ፡የተላጩትን፡ዅሉ፥ባለመገረዛቸው፡እነርሱን፡የምቀጣበት፡ዘመን፥እንሆ፥ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብ ሔር።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10፤
1፤እናንተ፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡በእናንተ፡ላይ፡የተናገረውን፡ቃል፡ስሙ።
2፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሕዛብን፡መንገድ፡አትማሩ፡ከሰማይ፡ምልክትም፡አትፍሩ፤አሕዛብ፡ይፈሩታል ና።
3፤የአሕዛብ፡ልማድ፡ከንቱ፡ነውና፤ዛፍ፡ከዱር፡ይቈረጣል፥በሠራተኛም፡እንጅ፡በመጥረቢያ፡ይሠራል።
4፤በብርና፡በወርቅ፡ያስጌጡታል፥እንዳይናወጥም፡በችንካርና፡በመዶሻ፡ይቸነክሩታል።
5፤እንደ፡ተቀረጸ፡ዐምድ፡ናቸው፥እነርሱም፡አይናገሩም፤መራመድም፡አይቻላቸውምና፥ይሸከሟቸዋል።ክፉ፡መሥራት ም፡አይቻላቸውምና፥ደግሞም፡መልካም፡ይሠሩ፡ዘንድ፡አይችሉምና፡አትፍሯቸው።
6፤አቤቱ፥እንደ፡አንተ፡ያለ፡የለም፤አንተ፡ታላቅ፡ነኽ፥ስምኽም፡በኀይል፡ታላቅ፡ነው።
7፤የአሕዛብ፡ንጉሥ፡ሆይ፥በአሕዛብ፡ጥበበኛዎች፡ዅሉ፡መካከል፡በመንግሥታቸውም፡ዅሉ፡እንደ፡አንተ፡ያለ፡ስለ ሌለ፥አንተን፡መፍራት፡ይገ፟ባ፟ልና፥አንተን፡የማይፈራ፡ማን፡ነው፧
8፤ባንድ፡ጊዜ፡ሰንፈዋል፥ደንቍረውማል፤ጣዖታት፡የሚያስተምሩት፡የዕንጨት፡ነገር፡ብቻ፡ነው።
9፤የሠራተኛና፡የአንጥረኛ፡እጅ፡ሥራ፡የኾነ፡ከተርሴስ፡ጥፍጥፍ፡ብር፡ከአፌዝም፡ወርቅ፡ይመጣል፤ልብሳቸውም፡ ሰማያዊና፡ቀይ፡ግምጃ፡ነው፥ዅሉም፡የብልኀተኛዎች፡ሥራ፡ናቸው።
10፤እግዚአብሔር፡ግን፡እውነተኛ፡አምላክ፡ነው፤ርሱም፡ሕያው፡አምላክና፡የዘለዓለም፡ንጉሥ፡ነው፤ከቍጣው፡የ ተነሣ፡ምድር፡ትንቀጠቀጣለች፤አሕዛብም፡መዓቱን፡አይችሉም።
11፤እናንተም፦ሰማይንና፡ምድርን፡ያልፈጠሩ፡እነዚህ፡አማልክት፡ከምድር፡ላይ፡ከሰማይም፡በታች፡ይጠፋሉ፡ትሏ ቸዋላችኹ።
12፤ምድርን፡በኀይሉ፡የፈጠረ፥ዓለሙን፡በጥበቡ፡የመሠረተ፡ሰማያትንም፡በማስተዋሉ፡የዘረጋ፡ርሱ፡ነው።
13፤ድምፁን፡ባሰማ፡ጊዜ፡ውሃዎች፡በሰማይ፡ይሰበሰባሉ፥ከምድርም፡ዳር፡ደመናትን፡ከፍ፡ያደርጋል፤ለዝናቡም፡ መብረቅን፡ያደርጋል፥ነፋስንም፡ከቤተ፡መዛግብቱ፡ያወጣል።
14፤ሰው፡ዅሉ፡ዕውቀት፡ዐጥቶ፡ሰንፏል፥አንጥረኛም፡ዅሉ፡ከቀረጸው፡ምስል፡የተነሣ፡አፍሯል፤ቀልጦ፡የተሠራ፡ ምስሉ፡ውሸት፡ነውና፥እስትንፋስም፡የላቸውምና።
15፤እነርሱ፡ምናምንቴና፡የቀልድ፡ሥራ፡ናቸው፤በተጐበኙ፡ጊዜ፡ይጠፋሉ።
16፤የያዕቆብ፡ዕድል፡ፈንታ፡እንደ፡እነዚህ፡አይደለም፤ርሱ፡የዅሉ፡ፈጣሪ፡ነውና፤እስራኤልም፡የርስቱ፡ነገድ ፡ነውና፤ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው።
17፤በምሽግ፡ውስጥ፡የተቀመጥሽ፡ሆይ፥ዕቃሽን፡ከመሬት፡ሰብስቢ፤
18፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥በምድሪቱ፡የሚኖሩትን፡እስኪሰማቸው፡ድረስ፡በዚህ፡ጊዜ፡እወነጭፋ ቸዋለኹ፥አስጨንቃቸውማለኹ።
19፤ስለ፡ስብራቴ፡ወዮልኝ! ቍስሌም፡ክፉ፡ነው፥እኔ፡ግን፦በእውነት፡የመከራ፡ቍስሌ፡ነው፥ርሱንም፡መሸከም፡ይገ፟ባ፟ኛል፡አልኹ።
20፤ድንኳኔ፡ተበዘበዘ፡አውታሬም፡ዅሉ፡ተቈረጠ፤ልጆቼም፡ከእኔ፡ወጥተው፡አይገኙም፤ድንኳኔንም፡ከእንግዲህ፡ ወዲህ፡የሚዘረጋ፡መጋረጃዎችንም፡የሚያነሣ፡የለም።
21፤እረኛዎች፡ሰንፈዋልና፥እግዚአብሔርን፡አልጠየቁትምና፡አልተከናወነላቸውም፥መንጋዎቻቸውም፡ዅሉ፡ተበትነ ዋል።
22፤የወሬን፡ድምፅ፡ስሙ፤እንሆም፥የይሁዳን፡ከተማዎች፡ባድማና፡የቀበሮ፡ማደሪያ፡ያደርጋቸው፡ዘንድ፡ከሰሜን ፡ምድር፡ጽኑ፡ሽብር፡መጥቷል።
23፤አቤቱ፥የሰው፡መንገድ፡ከራሱ፡እንዳይደለ፡ዐውቃለኹ፥አካኼዱንም፡ለማቅናት፡ከሚራመድ፡ሰው፡አይደለም።
24፤አቤቱ፥ቅጣኝ፤ነገር፡ግን፥እንዳታዋርደኝ፡በመጠን፡ይኹን፡እንጂ፡በቍጣ፡አይኹን።
25፤ያዕቆብን፡በልተውታልና፥ውጠውትማልና፥አጥፍተውትማልና፥ማደሪያውንም፡አፍርሰዋልና፥በማያውቁኽ፡አሕዛብ ፡ስምኽንም፡በማይጠሩ፡ወገኖች፡ላይ፡መዓትኽን፡አፍስ፟።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11፤
1፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤የዚህን፡ቃል፡ኪዳን፡ቃል፡ስማ፥ለይሁዳም፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ተናገር፥
3-4፤እንደዚህም፡በላቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከግብጽ፡አገር፡ከብረት፡ምድጃ፡ ባወጣዃቸው፡ቀን፡ለአባቶቻችኹ፡ያዘዝኹትን፡የዚህን፡ቃል፡ኪዳን፡ቃል፡የማይሰማ፡ሰው፡ርጉም፡ይኹን፤አልኹም ፦ቃሌን፡ስሙ፥ያዘዝዃችኹንም፡ዅሉ፡አድርጉ፤እንዲሁም፡እናንተ፡ሕዝብ፡ትኾኑኛላችኹ፡እኔም፡አምላክ፡እኾናች ዃለኹ።
5፤ይህም፡ዛሬ፡እንደ፡ኾነ፡ወተትና፡ማር፡የምታፈሰ፟ውን፡ምድር፡እሰጣቸው፡ዘንድ፡ለአባቶቻችኹ፡የማልኹትን፡ መሐላ፡አጸና፡ዘንድ፡ነው።እኔም፦አቤቱ፥አሜን፡ብዬ፡መለስኹለት።
6፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ይህችን፡ቃል፡ዅሉ፡በይሁዳ፡ከተማዎችና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ተናገር፥ እንዲህም፡በል፦የዚህን፡ቃል፡ኪዳን፡ቃል፡ስሙ፡አድርጉትም።
7፤አባቶቻችኹን፡ከግብጽ፡ምድር፡ካወጣኹበት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፥በማለዳ፡ተነሥቼ፡እያስጠነቀቅኹ ።ቃሌን፡ስሙ፡በማለት፡አስጠንቅቄያቸው፡ነበር።
8፤እነርሱ፡ዅሉ፡ግን፡በክፉ፡ልባቸው፡እልከኝነት፡ኼዱ፡እንጂ፥አልሰሙም፥ዦሯቸውንም፡አላዘነበሉም፤ስለዚህ፥ ያዘዝዃቸውን፡እነርሱም፡ያላደረጉትን፡የዚህን፡ቃል፡ኪዳን፡ቃል፡ዅሉ፡አመጣኹባቸው።
9፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦በይሁዳ፡ሰዎችና፡በኢየሩሳሌም፡በሚኖሩ፡ዘንድ፡ዐድማ፡ተገኝቷል።
10፤ቃሌንም፡ይሰሙ፡ዘንድ፡እንቢ፡ወዳሉ፡ወዳባቶቻቸው፡ኀጢአት፡ተመለሱ፥ያመልኳቸውም፡ዘንድ፡እንግዳዎችን፡ አማልክት፡ተከተሉ፤የእስራኤል፡ቤትና፡የይሁዳ፡ቤት፡ከአባቶቻቸው፡ጋራ፡ያደረግኹትን፡ቃል፡ኪዳን፡አፈረሱ።
11፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሊያመልጡት፡የማይችሉትን፡ክፉ፡ነገር፡አመጣባቸዋለኹ፥ወደ ፡እኔም፡ይጮኻሉ፤እኔም፡አልሰማቸውም።
12፤በይሁዳም፡ከተማዎችና፡በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩ፡ኼደው፡ወደሚያጥኑላቸው፡አማልክት፡ይጮኻሉ፤ነገር፡ግን፥በ መከራቸው፡ጊዜ፡ከቶ፡አያድኗቸውም።
13፤ይሁዳ፡ሆይ፥አማልክትኽ፡እንደ፡ከተማዎችኽ፡ቍጥር፡እንዲሁ፡ናቸው፤እንደ፡ኢየሩሳሌምም፡መንገዶች፡ቍጥር ፡ለነውረኛ፡ነገር፡መሠዊያ፥ርሱም፡ለበዓል፡ታጥኑበት፡ዘንድ፡መሠዊያ፥አድርጋችዃል።
14፤አንተም፡ስለዚህ፡ሕዝብ፡አትጸልይ፤ከመከራቸው፡የተነሣ፡ወደ፡እኔ፡በጮኹ፡ጊዜ፡አልሰማቸውምና፡ስለ፡እነ ርሱም፡ጩኸትና፡ልመና፡አታድርግ።
15፤ወዳጄ፡በቤቴ፡ውስጥ፡ምን፡አላት፧ስእለት፡ወይም፡የተቀደሰ፡ሥጋ፡ክፋትሽን፡ከአንቺ፡ያስወግዳልን፧ወይስ ፡በእነዚህ፡ታመልጫለሽን፧
16፤እግዚአብሔር፡ስምሽን፦በመልካም፡ፍሬ፡የተዋበች፡የለመለመች፡የወይራ፡ዛፍ፡ብሎ፡ጠራው፤በጽኑ፡ዐውሎ፡ነ ፋስ፡ጩኸት፡እሳትን፡አነደደባት፥ቅርንጫፎቿም፡ተሰብረዋል።
17፤ለበዓልም፡በማጠናቸው፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፡ለራሳቸው፡ስለሠሯት፡ስለእስራኤልና፡ስለይሁዳ፡ቤት፡ክፋት፡የተ ከለሽ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ክፉን፡ነገር፡ተናግሮብሻል።
18፤እግዚአብሔርም፡አስታወቀኝ፡እኔም፡ዐወቅኹ፤ሥራቸውንም፡ገለጥኽልኝ።
19፤እኔም፡ለመታረድ፡እንደሚነዳ፡እንደ፡የዋህ፡በግ፡ጠቦት፡ኾንኹ፤እነርሱም፦ዛፉን፡ከፍሬው፡ጋራ፡እንቍረጥ ፥ስሙም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡እንዳይታሰብ፡ከሕያዋን፡ምድር፡እናጥፋው፡ብለው፡ምክርን፡እንዳሰቡብኝ፡አላወቅ ኹም፡ነበር።
20፤ኵላሊትንና፡ልብን፡የምትፈትን፡በቅንም፡የምትፈርድ፡አቤቱ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥ክርክሬን፡ገልጬልኻለኹ ና፡በእነርሱ፡ላይ፡የሚኾን፡በቀልኽን፡ለይ።
21፤ስለዚህም፦በእጃችን፡እንዳትሞት፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ትንቢት፡አትናገር፡ብለው፡ነፍስኽን፡ስለሚሹ፡ስለ ዐናቶት፡ሰዎች፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እቀጣቸዋለኹ፤
22፤ጐበዛዝታቸው፡በሰይፍ፡ይሞታሉ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውም፡በራብ፡ይሞታሉ፤በምጐበኛቸውም፡ዓመት፡በዐ ናቶት፡ሰዎች፡ላይ፡ክፉ፡ነገር፡አመጣባቸዋለኹና፡ማንም፡ከነርሱ፡የሚቀር፡የለም።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12፤
1፤አቤቱ፥ከአንተ፡ጋራ፡በተሟገትኹ፡ጊዜ፡አንተ፡ጻድቅ፡ነኽ፤ነገር፡ግን፥ከአንተ፡ጋራ፡ስለ፡ፍርድ፡ልናገር። የኀጢአተኛዎች፡መንገድ፡ስለ፡ምን፡ይቃናል፧በደልንስ፡ለሚያደርጉ፡ዅሉ፡ስለ፡ምን፡ደኅንነት፡ይኾናል፧
2፤ተክለኻቸዋል፤ሥር፡ሰደ፟ዋል፤አድገዋል፡አፍርተውማል፤በአፋቸው፡አንተ፡ቅርብ፡ነኽ፥ከልባቸው፡ግን፡ሩቅ፡ ነኽ።
3፤አንተ፡ግን፥አቤቱ፥ዐውቀኸኛል፤አይተኸኛል፥ልቤንም፡በፊትኽ፡ፈትነኻል፤እንደ፡በጎች፡ለመታረድ፡ጐትተኽ፡ ለያቸው፥ለመታረድም፡ቀን፡አዘጋጃቸው።
4፤ምድሪቱ፡የምታለቅሰው፥የአገሩ፡ሣርስ፡ዅሉ፡የሚደርቀው፡እስከ፡መቼ፡ነው፧የተቀመጡባት፡ሰዎች፦ፍጻሜያችን ን፡አያይም፡ብለዋልና፥ስለ፡ክፋታቸው፡እንስሳዎችና፡ወፎች፡ጠፍተዋል።
5፤ከእግረኛዎች፡ጋራ፡በሮጥኽ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ቢያደክሙኽ፥ከፈረሶች፡ጋራ፡መታገል፡እንዴት፡ትችላለኽ፧በሰላም ም፡ምድር፡ታምነኽ፡ብትቀመጥ፥በዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡እንዴት፡ታደርጋለኽ፧
6፤ወንድሞችኽና፡የአባትኽ፡ቤት፡እነርሱ፡ጭምር፡አታለ፟ውኻልና፥በዃላኽም፡ጮኸዋልና፤በመልካምም፡ቢናገሩኽም ፡አትታመናቸው።
7፤ቤቴን፡ትቻለኹ፡ርስቴንም፡ጥያለኹ፥ነፍሴም፡የምትወዳ፟ትን፡በጠላቶቿ፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጥቻለኹ።
8፤ርስቴ፡በዱር፡እንዳለ፡አንበሳ፡ኾናብኛለች፤ድምፇን፡አንሥታብኛለች፤ስለዚህ፥ጠልቻታለኹ።
9፤ርስቴ፡እንደ፡ዝንጕርጕር፡አሞራ፡ኾነችብኝን፧አሞሮችስ፡በዙሪያዋና፡በላይዋ፡ኾነዋልን፧ኺዱ፥የምድር፡አራ ዊትን፡ዅሉ፡ሰብስቡ፥ይበሉም፡ዘንድ፡አምጧቸው።
10፤ብዙ፡እረኛዎች፡የወይኑን፡ቦታዬን፡አጥፍተዋል፥ዕድል፡ፈንታዬንም፡ረግጠዋል፤የአምሮቴን፡ዕድል፡ፈንታ፡ ምድረ፡በዳ፡አድርገውታል።
11፤ባድማ፡አድርገውታል፥ፈርሶም፡ወደ፡እኔ፡ያለቅሳል፤ምድር፡ዅሉ፡ባድማ፡ኾናለች፡በልቡም፡የሚያስባት፡የለ ም።
12፤በወናዎች፡ኰረብታዎች፡ዅሉ፡ላይ፡በዝባዦች፡መጥተዋል፥የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡ከምድር፡ዳር፡ዠምሮ፡እስከ ምድር፡ዳር፡ድረስ፡ይበላልና፤ለሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ሰላም፡የለም።
13፤ስንዴን፡ዘሩ፡ሾኽንም፡ዐጨዱ፤ደከሙ፥ምንም፡አልረባቸውም፤ስለእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡ከፍሬያችኹ፡ታፍራ ላችኹ።
14፤እግዚአብሔር፡ለሕዝቤ፡ለእስራኤል፡ያወረስኹትን፡ርስት፡ለሚነኩት፡ክፉዎች፡ጎረቤቶች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ይላ ልና፦እንሆ፥ከምድራቸው፡እነቅላቸዋለኹ፥የይሁዳንም፡ቤት፡ከመካከላቸው፡እነቅለዋለኹ።
15፤ከነቀልዃቸውም፡በዃላ፡መልሼ፡እምራቸዋለኹ፥እያንዳንዱንም፡ወደ፡ርስቱ፡እያንዳንዱንም፡ወደ፡ምድሩ፡እመ ልሳለኹ።
16፤በበዓል፡ይምሉ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡እንዳስተማሩ፡በስሜ፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ብለው፡ይምሉ፡ዘንድ፡የሕዝቤን፡መንገድ፡በትጋት፡ቢማሩ፥በዚያን፡ጊዜ፡በሕዝቤ፡መካከል፡ይመሠረታሉ።
17፤ባይሰሙኝ፡ግን፡ያንን፡ሕዝብ፡ፈጽሜ፡እነቅለዋለኹ፡አጠፋውማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13፤
1፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦ኺድ፥ከተልባ፡እግር፡የተሠራችን፡መታጠቂያ፡ለአንተ፡ግዛ፥ወገብኽንም፡ታጠ ቅባት፤በውሃውም፡ውስጥ፡አትንከራት።
2፤እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡መታጠቂያን፡ገዛኹ፡ወገቤንም፡ታጠቅኹባት።
3-4፤ኹለተኛም፡ጊዜ፦የገዛኻትን፡በወገብኽ፡ያለችውን፡መታጠቂያ፡ወስደኽ፡ተነሥ፥ወደ፡ኤፍራጥስም፡ኺድ፥በዚያ ም፡በተሰነጠቀ፡አለት፡ውስጥ፡ሸሽጋት፡የሚል፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መጣልኝ።
5፤እግዚአብሔርም፡እንዳዘዘኝ፡ኼድኹ፡በኤፍራጥስም፡አጠገብ፡ሸሸግዃት።
6፤ከብዙ፡ቀንም፡በዃላ፡እግዚአብሔር፦ተነሥተኽ፡ወደ፡ኤፍራጥስ፡ኺድ፥በዚያም፡ትሸሽጋት፡ዘንድ፡ያዘዝኹኽን፡ መታጠቂያ፡ከዚያ፡ውስጥ፡ውሰድ፡አለኝ።
7፤እኔም፡ወደ፡ኤፍራጥስ፡ኼድኹ፡ቈፈርኹም፥ከሸሸግኹበትም፡ስፍራ፡መታጠቂያዪቱን፡ወሰድኹ።እንሆም፥መታጠቂያ ዪቱ፡ተበላሽታ፡ነበር፥ለምንም፡አልረባችም።
8፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፤
9፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲሁ፡የይሁዳን፡ትዕቢት፡ታላቁንም፡የኢየሩሳሌምን፡ትዕቢት፡አበላሻለኹ።
10፤ቃሌን፡ይሰሙ፡ዘንድ፡እንቢ፡የሚሉ፥በልባቸውም፡እልከኝነት፡የሚኼዱ፥ያመልኳቸውና፡ይሰግዱላቸው፡ዘንድ፡ ሌላዎችን፡አማልክት፡የሚከተሉ፡እነዚህ፡ክፉ፡ሕዝብ፡አንዳች፡እንዳማትረባ፡እንደዚች፡መታጠቂያ፡ይኾናሉ።
11፤መታጠቂያ፡በሰው፡ወገብ፡ላይ፡እንደምትጣበቅ፥እንዲሁ፡ሕዝብና፡ስም፡ምስጋናና፡ክብር፡ይኾኑልኝ፡ዘንድ፡ የእስራኤልን፡ቤት፡ዅሉ፡የይሁዳንም፡ቤት፡ዅሉ፡ከእኔ፡ጋራ፡አጣብቄያለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ነገር፡ግን፥ አልሰሙም።
12፤ስለዚህ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ማድጋ፡ዅሉ፡የወይን፡ጠጅ፡ይሞላል፡ብለኽ፡ት ነግራቸዋለኽ፤እነርሱም፦ማድጋ፡ዅሉ፡የወይን፡ጠጅ፡እንዲሞላ፡በእውኑ፡እኛ፡አናውቅምን፧ይሉኻል።
13፤አንተም፡እንዲህ፡ትላቸዋለኽ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በዚች፡ምድር፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፥በዳዊ ት፡ዙፋን፡የሚቀመጡትን፡ነገሥታት፡ካህናቱንም፡ነቢያቱንም፡በኢየሩሳሌምም፡የተቀመጡትን፡ዅሉ፡በስካር፡እሞ ላቸዋለኹ።
14፤ሰውንም፡በሰው፡ላይ፥አባቶችንና፡ልጆችን፡ባንድ፡ላይ፥እቀጠቅጣለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤አጠፋቸዋለኹ፡ እንጂ፡አልራራም፥አላዝንም፥አልምርም።
15፤ስሙ፥አድምጡ፤እግዚአብሔር፡ተናግሯልና፥አትታበዩ።
16፤ሳትጨልም፡እግራችኹም፡በጨለመችው፡ተራራ፡ላይ፡ሳትሰናከል፥በተስፋ፡የምትጠባበቁትን፡ብርሃን፡ለሞት፡ጥ ላና፡ለድቅድቅ፡ጨለማ፡ሳይለውጠው፡ለአምላካችኹ፡ለእግዚአብሔር፡ክብርን፡ስጡ።
17፤ይህን፡ባትሰሙ፡ነፍሴ፡ስለ፡ትዕቢታችኹ፡በስውር፡ታለቅሳለች፤የእግዚአብሔርም፡መንጋ፡ተማርኳልና፥ዐይኔ ፡ታነባለች፥እንባንም፡ታፈሳ፟ለች።
18፤ለንጉሡና፡ለንጉሥ፡እናት፡ለእቴጌዪቱ፦የክብራችኹ፡አክሊል፡ከራሳችኹ፡ወርዷልና፥ተዋርዳችኹ፡ተቀመጡ፡በ ል።
19፤የደቡብ፡ከተማዎች፡ተዘግተዋል፥የሚከፍታቸውም፡የለም፤ይሁዳ፡ዅሉ፡ተማርኳል፥ፈጽሞ፡ተማርኳል።
20፤ዐይናችኹን፡አንሥታችኹ፡እነዚህን፡ከሰሜን፡የሚመጡትን፡ተመልከቱ፤ለአንቺ፡የተሰጠ፡መንጋ፥የተዋበ፡መን ጋሽ፥ወዴት፡አለ፧
21፤ወዳጆችሽ፡እንዲኾኑ፡ያስተማርሻቸውን፡በራስሽ፡ላይ፡አለቃዎች፡ባደረጋቸው፡ጊዜ፡ምን፡ትያለሽ፧እንደ፡ወ ላድ፡ሴት፡ምጥ፡አይዝሽምን፧
22፤በልብሽም፦እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ስለ፡ምን፡ደረሰብኝ፧ብትዪ፥ከኀጢአትሽ፡ብዛት፡የተነሣ፡የልብስሽ፡ዘርፍ ፡ተገልጧል፡ተረከዝሽም፡ተገፏ፟ል።
23፤በእውኑ፡ኢትዮጵያዊ፡መልኩን፡ወይስ፡ነብር፡ዝንጕርጕርነትን፡ይለውጥ፡ዘንድ፡ይችላልን፧በዚያን፡ጊዜ፡ክ ፋትን፡የለመዳችኹ፡እናንተ፡ደግሞ፡በጎ፡ለማድረግ፡ትችላላችኹ።
24፤ስለዚህ፥እንደሚያልፍ፡እብቅ፡በምድረ፡በዳ፡ነፋስ፡እበትናቸዋለኹ።
25፤ረስተሽኛልና፥በሐሰትም፡ታምነሻልና፥ዕጣሽ፡የለካኹልሽም፡ዕድል፡ፈንታ፡ይህ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር።
26፤ስለዚህም፡የልብስሽን፡ዘርፍ፡በፊትሽ፡እገልጣለኹ፡ዕፍረትሽም፡ይታያል።
27፤አስጸያፊ፡ሥራሽን፥ምንዝርናሽን፥ማሽካካትሽን፥የግልሙትናሽንም፡መዳራት፡በኰረብታዎች፡ላይ፡በሜዳም፡አ ይቻለኹ።ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ወዮልሽ! ለመንጻት፡እንቢ፡ብለሻል፤ይህስ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14፤
1፤ወደ፡ኤርምያስ፡ስለ፡ድርቅ፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤ይሁዳ፡አለቀሰች፥ደጆቿም፡ባዶ፡ኾኑ፡በምድርም፡ላይ፡ጨለሙ፤የኢየሩሳሌም፡ጩኸት፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏል።
3፤ታላላቆችም፡ብላቴናዎቻቸውን፡ወደ፡ውሃ፡ሰደዱ፤ወደ፡ጕድጓድ፡መጡ፡ውሃም፡አላገኙም፥ዕቃቸውንም፡ባዶውን፡ ይዘው፡ተመለሱ፤ዐፈሩም፡ተዋረዱም፡ራሳቸውንም፡ተከናነቡ።
4፤በምድር፡ላይ፡አልዘነበምና፡መሬቱ፡ስንጥቅጥቅ፡ስለ፡ኾነ፡ዐራሾች፡ዐፈሩ፥ራሳቸውንም፡ተከናነቡ።
5፤ዋላ፡ደግሞ፡በምድረ፡በዳ፡ወለደች፥ሣርም፡የለምና፡ግልገሏን፡ተወች።
6፤የሜዳ፡አህያዎችም፡በወና፡ኰረብታ፡ላይ፡ቆመዋል፥እንደ፡ቀበሮም፡ወደ፡ነፋስ፡አለከለኩ፤ልምላሜም፡የለምና ፡ዐይኖቻቸው፡ጠወለጉ።
7፤አቤቱ፥ኀጢአታችን፡ብዙ፡ነውና፥ባንተም፡ላይ፡ኀጢአት፡ሠርተናልና፥ኀጢአታችን፡ይመሰክርብናል፥ነገር፡ግን ፥ስለ፡ስምኽ፡ብለኽ፡አድርግ።
8፤አንተ፡የእስራኤል፡ተስፋ፡ሆይ፡በመከራም፡ጊዜ፡የምታድነው፥በምድር፡እንደ፡እንግዳ፥ወደ፡ማደሪያ፡ዘወር፡ እንደሚል፡መንገደኛ፡ስለ፡ምን፡ትኾናለኽ፧
9፤እንዳንቀላፋ፡ሰው፡ሰው፥ያድንም፡ዘንድ፡እንደማይችል፡ኀያል፡ስለ፡ምን፡ትኾናለኽ፧አንተ፡ግን፥አቤቱ፥በመ ካከላችን፡ነኽ፡እኛም፡በስምኽ፡ተጠርተናል፤አትተወን።
10፤እግዚአብሔር፡ለዚህ፡ሕዝብ፡እንዲህ፡ይላል፦መቅበዝበዝን፡ወደ፟ዋል፥እግራቸውንም፡አልከለከሉም፤ስለዚህ ፥እግዚአብሔር፡በእነርሱ፡ደስ፡አይለውም፥በደላቸውንም፡አኹን፡ያስባል፥ኀጢአታቸውንም፡ይቀጣል።
11፤እግዚአብሔርም፦ለዚህ፡ሕዝብ፡ስለ፡መልካም፡አትጸልይላቸው።
12፤በጾሙ፡ጊዜ፡ጸሎታቸውን፡አልሰማም፤የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ባቀረቡ፡ጊዜ፡አልቀበላ ቸውም፤በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡አጠፋቸዋለኹ፡አለኝ።
13፤እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! እንሆ፥ነቢያት።በእውነት፡ሰላምን፡በዚህ፡ስፍራ፡እሰጣችዃለኹ፡እንጂ፡ሰይፍን፡አታዩም፥ራብም፡አያገኛችኹም ፡ይሏቸዋል፡አልኹ።
14፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ነቢያቱ፡ውሸት፡በስሜ፡ትንቢት፡ይናገራሉ፤አላክዃቸውም፥አላዘዝዃቸውም፥ አልተናገርዃቸውም፤የውሸቱን፡ራእይ፡ሟርትንም፡ከንቱንም፡ነገር፡የልባቸውንም፡ሽንገላ፡ይሰብኩላችዃል።
15፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡በስሜ፡ትንቢት፡ስለሚናገሩ፡ነቢያት፦በዚች፡አገር፡ሰይፍና፡ራብ፡አይኾንም፡ስለሚ ሉ፡ስላላ፟ክዃቸው፡ነቢያት፡እንዲህ፡ይላል፦እነዚያ፡በሰይፍና፡በራብ፡ይጠፋሉ።
16፤ትንቢት፡የሚናገሩላቸውም፡ሰዎች፡ከራብና፡ከሰይፍ፡የተነሣ፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ይበተናሉ፤ክፋታቸው ንም፡አፈስ፟ባቸዋለኹ፡እነርሱንና፡ሚስቶቻቸውን፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡የሚቀብራቸው፡አይገኝም።
17፤እንደዚህም፡ብለኽ፡ትነግራቸዋለኽ፦የወገኔ፡ልጅ፡ድንግሊቱ፡በታላቅ፡ስብራትና፡እጅግ፡ክፉ፡በኾነ፡ቍስል ፡ተሰብራለችና፡ዐይኖቼ፡ሌሊትና፡ቀን፡ሳያቋርጡ፡እንባ፡ያፈሳሉ።
18፤ወደ፡ሜዳ፡ብወጣ፥እንሆ፥በሰይፍ፡የሞቱ፡አሉ፤ወደ፡ከተማም፡ብገባ፥እንሆ፥በራብ፡የከሱ፡አሉ፤ነቢዩና፡ካ ህኑም፡ወደማያውቋት፡አገር፡ኼደዋልና።
19፤በእውኑ፡ይሁዳን፡ፈጽመኽ፡ጥለኸዋልን፧ነፍስኽስ፡ጽዮንን፡ጠልታታለችን፧ስለ፡ምን፡መታኸን፧ፈውስስ፡ስለ ፡ምን፡የለንም፧ሰላምን፡በተስፋ፡ተጠባበቅን፥መልካምም፡አልተገኘም፤ፈውስን፡በተስፋ፡ተጠባበቅን፥እንሆም፥ ድንጋጤ፡ኾነ።
20፤አቤቱ፥ባንተ፡ላይ፡ኀጢአትን፡ሠርተናልና፥ክፋታችንንና፡የአባቶቻችንን፡በደል፡እናውቃለን።
21፤ስለ፡ስምኽ፡ብለኽ፡አትናቀን፥የክብርኽንም፡ዙፋን፡አታስነውር፤ከእኛ፡ጋራም፡ያደረግኸውን፡ቃል፡ኪዳንኽ ን፡ዐስብ፡እንጂ፡አታፍርስ።
22፤በእውኑ፡በአሕዛብ፡ጣዖታት፡መካከል፡ያዘንብ፡ዘንድ፡የሚችል፡ይገኛልን፧ወይስ፡ሰማይ፡ዝናብ፡ማፍሰስ፡ይ ችላልን፧አቤቱ፡አምላካችን፡ሆይ፥አንተ፡አይደለኽምን፧አንተ፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡አድርገኻልና፥ስለዚህ፡አን ተን፡በተስፋ፡እንጠባበቃለን።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15፤
1፤እግዚአብሔርም፡እንደዚህ፡አለኝ፦ሙሴና፡ሳሙኤል፡በፊቴ፡ቢቆሙም፥ልቤ፡ወደዚህ፡ሕዝብ፡አይዘነብልም፤ከፊቴ ፡ጣላቸው፤ይውጡ።
2፤እነርሱም፦ወዴት፡እንውጣ፡ቢሉኽ፥አንተ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለሞት፡የኾነ፡ወደ፡ሞት፥ለሰይፍም፡ የኾነ፡ወደ፡ሰይፍ፥ለራብም፡የኾነ፡ወደ፡ራብ፥ለምርኮም፡የኾነ፡ወደ፡ምርኮ፡ትላቸዋለኽ።
3፤ሰይፍን፡ለመግደል፡ውሻዎችንም፡ለመጐተት፡የሰማያትንም፡ወፎች፡የምድርንም፡አራዊት፡ለመብላትና፡ለማጥፋት ፥አራቱን፡ዐይነት፡ጥፋት፡አዝ፟ባቸዋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡የሕዝቅያስ፡ልጅ፡ምናሴ፡በኢየሩሳሌም፡ስላደረገው፡ዅሉ፡በምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡መካከ ል፡ለመከራ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ።
5፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥የሚራራልሽ፡ማን፡ነው፧የሚያዝንልሽስ፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ስለ፡ደኅንነትሽ፡ይጠይቅ፡ዘንድ ፡ፈቀቅ፡የሚል፡ማን፡ነው፧
6፤አንቺ፡እኔን፡ጥለሻል፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ወደ፡ዃላሽም፡ተመልሰሻል፤ስለዚህ፥እጄን፡ባንቺ፡ላይ፡ዘርግቼ ፡አጥፍቼሻለኹ፤ከይቅርታ፡ደክሜያለኹ።
7፤በአገርም፡ደጆች፡ውስጥ፡በመንሽ፡አበጥሬያቸዋለኹ፤የወላድ፡መካን፡አድርጌያቸዋለኹ፥ሕዝቤንም፡አጥፍቻለኹ ፤ከመንገዳቸውም፡አልተመለሱም።
8፤መበለቶቻቸውም፡ከባሕር፡አሸዋ፡ይልቅ፡በዝተውብኛል፤በብላቴናዎች፡እናት፡ላይ፡በቀትር፡ጊዜ፡አጥፊውን፡አ ምጥቻለኹ፤ጣርንና፡ድንጋጤን፡በድንገት፡አምጥቼባታለኹ።
9፤ሰባት፡የወለደች፡ደክማለች፥ነፍሷንም፡አውጥታለች፤ቀን፡ገና፡ሳለ፡ፀሓይዋ፡ገብታባታለች፤ዐፍራለች፡ተዋር ዳማለች፤የተረፉትንም፡በጠላቶቻቸው፡ፊት፡ለሰይፍ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
10፤እናቴ፡ሆይ፥ወዮልኝ! ለምድር፡ዅሉ፡የክርክርና፡የጥል፡ሰው፡የኾንኹትን፡ወለድሽኝ፡ለማንም፡አላበደርኹም፥ማንም፡ለእኔ፡አላበደረ ም፥ነገር፡ግን፥ዅሉ፡ይረግመኛል።
11፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አለ፦በእውነት፡ለደኅንነትኽ፡አጸናኻለኹ፤በእውነት፡በመከራና፡በጭንቅ፡ጊዜ፡ጠላ ትኽ፡እንዲለምንኽ፡አደርገዋለኹ።
12፤በእውኑ፡ብረትን፥የሰሜንን፡ብረት፥ናስንም፡የሚሰብር፡አለን፧
13፤በዳርቻኽ፡ዅሉ፡ስለ፡አለ፡ኀጢአትኽ፡ዅሉ፡ባለጠግነትኽንና፡መዝገብኽን፡ለመበዝበዝ፡በከንቱ፡እሰጣለኹ።
14፤የምታቃጥላችኹ፡እሳት፡ከቍጣዬ፡ትነዳ፟ለችና፡ከጠላቶችኽ፡ጋራ፡ወደማታውቀው፡ምድር፡አሳልፍኻለኹ።
15፤አቤቱ፥አንተ፡ታውቃለኽ፤ዐስበኝ፡ጐብኘኝም፡የሚያሳድዱኝንም፡ተበቀላቸው፡እንጂ፡አትታገሣቸው፤ስለ፡አን ተ፡ስድብን፡እንደ፡ታገሥኹ፡ዕወቅ።
16፤ቃልኽ፡ተገኝቷል፡እኔም፡በልቼዋለኹ፤አቤቱ፥የሰራዊት፡አምላክ፡ሆይ፥በስምኽ፡ተጠርቻለኹና፡ቃልኽ፡ሐሤት ና፡የልብ፡ደስታ፡ኾነኝ።
17፤በዋዘኛዎችና፡በደስተኛዎች፡ጉባኤ፡አልተቀመጥኹም፤ቍጣን፡ሞልተኽብኛልና፥በእጅኽ፡ፊት፡ለብቻዬ፡ተቀመጥ ኹ።
18፤ስለ፡ምን፡ሕመሜ፡አዘወተረኝ፧ቍስሌስ፡ስለ፡ምን፡የማይፈወስ፡ኾነ፧ስለ፡ምንስ፦አልሽርም፡አለ፧በእውኑ፡ እንደ፡ሐሰተኛ፡ምንጭ፥እንዳልታመነች፡ውሃ፡ትኾነኛለኽን፧
19፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ብትመለስ፡እመልስኻለኹ፡በፊቴም፡ትቆማለኽ፤የከበረውንም፡ከተዋረ ደው፡ብትለይ፡እንደ፡አፌ፡ትኾናለኽ፤እነርሱ፡ወዳንተ፡ይመለሳሉ፥አንተ፡ግን፡ወደ፡እነርሱ፡አትመለስም።
20፤ለዚህም፡ሕዝብ፡የተመሸገ፡የናስ፡ቅጥር፡አደርግኻለኹ፤ይዋጉኻል፡እኔ፡ግን፡ለማዳን፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና ፡አያሸንፉኽም።
21፤ከክፉ፡ሰዎችም፡እጅ፡እታደግኻለኹ፥ከጨካኞችም፡ጡጫ፡እቤዥኻለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16፤
1፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤በዚህ፡ስፍራ፡ሚስት፡አታግባ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችም፡አይኹኑልኽ።
3፤እግዚአብሔር፡በዚህ፡ስፍራ፡ስለተወለዱ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆች፥ስለወለዷቸውም፡ስለ፡እናቶቻቸው፥በዚችም ፡ምድር፡ስለወለዷቸው፡ስለ፡አባቶቻቸው፡እንዲህ፡ይላልና፦
4፤በክፉ፡ሞት፡ይሞታሉ፤አይለቀስላቸውም፡አይቀበሩምም፥በመሬትም፡ላይ፡እንደ፡ጕድፍ፡ይኾናሉ፤በሰይፍና፡በራ ብ፡ይጠፋሉ፥ሬሳቸውም፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡መብል፡ይኾናሉ።
5፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰላሜን፥ቸርነትና፡ምሕረትን፥ከዚህ፡ሕዝብ፡አስወግጃለኹና፡ልቅሶ፡ወዳለበት ፡ቤት፡አትግባ፥ታለቅስም፥ታዝንም፡ዘንድ፡አትኺድ።
6፤ታላላቆችና፡ታናናሾች፡በዚች፡ምድር፡ይሞታሉ፤አይቀበሩም፥ሰዎችም፡አያለቅሱላቸውም፥ስለ፡እነርሱም፡ገላን ፡አይነጩላቸውም፥ራስንም፡አይላጩላቸውም፤
7፤ሰዎችም፡ስለሞቱት፡ለማጽናናት፡የዕዝን፡እንጀራ፡አይቈርሱላቸውም፥ስለ፡አባታቸውና፡ስለ፡እናታቸውም፡የመ ጽናናት፡ጽዋ፡አያጠጧቸውም።
8፤ትበላና፡ትጠጣ፡ዘንድ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ለመቀመጥ፡ወደግብዣ፡ቤት፡አትግባ።
9፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥በዐይናችኹ፡ፊት፡በዘመናችኹም ፡የእልልታን፡ድምፅና፡የደስታን፡ድምፅ፡የወንድ፡ሙሽራን፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራን፡ድምፅ፡ከዚህ፡ስፍራ፡አስ ቀራለኹ።
10፤ለዚህም፡ሕዝብ፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡በተናገርኽ፡ጊዜ፦ይህን፡ዅሉ፡ታላቅ፡የኾነ፡ክፉ፡ነገርን፡ስለ፡ምን፡እ ግዚአብሔር፡ተናገረብን፧በደላችንስ፡ምንድር፡ነው፧በአምላካችንስ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡የሠራነው፡ኀጢአታች ን፡ምንድር፡ነው፧ቢሉኽ፥
11፤አንተ፡እንዲህ፡ትላቸዋለኽ፦አባቶቻችኹ፡እኔን፡ስለ፡ተዉ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ሌላዎችንም፡አማልክ ት፡ተከተሉ፡አመለኳቸውም፡ሰገዱላቸውም፥እነርሱም፡ትተውኛል፥ሕጌንም፡አልጠበቁም፤እናንተም፡ከአባቶቻችኹ፡ ይልቅ፡ክፉ፡አድርጋችዃል፤እንሆም፥ዅላችኹ፡እንደ፡ክፉ፡ልባችኹ፡እልከኝነት፡ኼዳችዃል፡እኔንም፡አልሰማችኹ ም።
13፤ስለዚህ፥ከዚች፡ምድር፡እናንተና፡አባቶቻችኹ፡ወዳላወቃችዃት፡ምድር፡እጥላችዃለኹ፤ምሕረትንም፡አላደርግ ላችኹምና፥በዚያ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡ቀንና፡ሌሊት፡ታመልካላችኹ።
14፤ስለዚህ፥እንሆ፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዳግመኛ፡የማይባልበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
15፤ነገር፡ግን፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከሰሜን፡ምድር፡ካሳደዳቸውም፡ምድር፡ዅሉ፡ያወጣ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ይባላል፤እኔም፡ለአባቶቻቸው፡ወደሰጠዃት፡ወደ፡ምድራቸው፡እመልሳቸዋለኹ።
16፤እንሆ፥ብዙ፡ዓሣ፡አጥማጆችን፡እሰዳ፟ለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እነርሱም፡ያጠምዷቸዋል፤ከዚያም፡በዃላ፡ ብዙ፡አዳኞችን፡እሰዳ፟ለኹ፥እነርሱም፡ከየተራራውና፡ከየኰረብታው፡ዅሉ፡ከየድንጋዩም፡ስንጣቂ፡ውስጥ፡ያድኗ ቸዋል።
17፤ዐይኔ፡በመንገዳቸው፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፤ከፊቴም፡አልተሰወሩም፥ኀጢአታቸውም፡ከዐይኔ፡አልተሸሸገም።
18፤ምድሬንም፡በተጠሉ፡በጣዖቶቻቸው፡ሬሳዎች፡አርክሰዋልና፥ርስቴንም፡አስጸያፊ፡በኾኑ፡ነገሮች፡ሞልተዋልና ፥አስቀድሜ፡የበደላቸውንና፡የኀጢአታቸውን፡ዕዳ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡እከፍላቸዋለኹ።
19፤አቤቱ፥ኀይሌ፥ዐምባዬ፥በመከራም፡ቀን፡መጠጊያዬ፡ሆይ፥ከምድር፡ዳርቻ፡አሕዛብ፡ወዳንተ፡መጥተው፦በእውነ ት፡አባቶቻችን፡ውሸትንና፡ከንቱን፡ነገር፡የማይረባቸውንም፡ወርሰዋል፡ይላሉ።
20፤በእውኑ፡ሰው፡አማልክት፡ያልኾኑትን፡ለራሱ፡አማልክትን፡አድርጎ፡ይሠራልን፧
21፤ስለዚህ፥እንሆ፥አስታውቃቸዋለኹ፥በዚች፡ጊዜ፡እጄንና፡ኀይሌን፡አስታውቃቸዋለኹ፤እነርሱም፡ስሜ፡እግዚአ ብሔር፡እንደ፡ኾነ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17፤
1፤የይሁዳ፡ኀጢአት፡በብረት፡ብርዕና፡በተሾለ፡እብነ፡አልማዝ፡ተጽፏል፤በልባቸው፡ጽላትና፡በመሠዊያቸው፡ቀን ዶች፡ተቀርጿል።
2፤ልጆቻቸውም፡ከለመለሙ፡ዛፎች፡በታችና፡በረዘሙት፡ኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉትን፡መሠዊያቸውንና፡የማምለኪያ፡ዐ ጸዳቸውን፡ያስባሉ።
3፤በሜዳ፡ያለው፡ተራራዬ፡ሆይ፥ባለጠግነትኽንና፡መዝገብኽን፡ዅሉ፡የኰረብታውን፡መስገጃዎችኽም፡ስለ፡ኀጢአት ፡በድንበሮችኽ፡ዅሉ፡ለመበዝበዝ፡እሰጣለኹ።
4፤አንተም፡የሰጠኹኽን፡ርስት፡ትለቃ፟ለኽ፡ለዘለዓለምም፡በማታውቃትም፡ምድር፡ለጠላቶቻችኹ፡ባሪያ፡አደርግኻ ለኹ፤ለዘለዓለም፡የሚነደ፟ውን፡እሳት፡በቍጣዬ፡አንድዳችዃልና።
5፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በሰው፡የሚታመን፡ሥጋ፡ለባሹንም፡ክንዱ፡የሚያደርግ፡ልቡም፡ከእግዚአብሔር፡ የሚመለስ፡ሰው፡ርጉም፡ነው።
6፤በምድረ፡በዳ፡እንዳለ፡ቍጥቋጦ፡ይኾናል፥መልካምም፡በመጣ፡ጊዜ፡አያይም፤ሰውም፡በሌለበት፥ጨው፡ባለበት፡ም ድር፡በምድረ፡በዳ፡በደረቅ፡ስፍራ፡ይቀመጣል።
7፤በእግዚአብሔር፡የታመነ፡እምነቱም፡እግዚአብሔር፡የኾነ፡ሰው፡ቡሩክ፡ነው።
8፤በውሃ፡አጠገብ፡እንደ፡ተተከለ፥በወንዝም፡ዳር፡ሥሩን፡እንደሚዘረጋ፡ሙቀትም፡ሲመጣ፡እንደማይፈራ፡ቅጠሉም ፡እንደሚለመልም፥በድርቅ፡ዓመትም፡እንደማይሠጋ፡ፍሬውንም፡እንደማያቋርጥ፡ዛፍ፡ይኾናል።
9፤የሰው፡ልብ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡ተንኰለኛ፡እጅግም፡ክፉ፡ነው፤ማንስ፡ያውቀዋል፧
10፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ለሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መንገዱ፥እንደ፡ሥራው፡ፍሬ፡እሰጥ፡ዘንድ፡ልብን፡እመረምራለኹ፡ኵ ላሊትንም፡እፈትናለኹ።
11፤ያልወለደችውን፡እንደምታቅፍ፡ቆቅ፥እንዲሁ፡በቅን፡ሳይኾን፡ባለጠግነትን፡የሚሰበስብ፡ሰው፡ነው፤በእኩሌ ታ፡ዘመኑ፡ይተወዋል፥በፍጻሜውም፡ሰነፍ፡ይኾናል።
12፤የመቅደሳችን፡ስፍራ፡ከጥንት፡ዠምሮ፡ከፍ፡ያለ፡የክብር፡ዙፋን፡ነው።
13፤አቤቱ፥የእስራኤል፡ተስፋ፡ሆይ፥የሚተዉኽ፡ዅሉ፡ያፍራሉ፤ከአንተም፡የሚለዩ፡የሕይወትን፡ውሃ፡ምንጭ፡እግ ዚአብሔርን፡ትተዋልና፥በምድር፡ላይ፡ይጻፋሉ።
14፤አቤቱ፥ፈውሰኝ፡እኔም፡እፈወሳለኹ፤አድነኝ፡እኔም፡እድናለኹ፤አንተ፡ምስጋናዬ፡ነኽና።
15፤እንሆ፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወዴት፡አለች፧አኹን፡ትምጣ፡ይሉኛል።
16፤እኔም፡አንተን፡ተከትዬ፡እረኛ፡ከመኾን፡አልቸኰልኹም፥የመከራንም፡ቀን፡አልወደድኹም፤አንተ፡ታውቃለኽ፤ ከከንፈሬ፡የወጣው፡በፊትኽ፡ነበረ።
17፤ለማስፈራራት፡አትኹንብኝ፤በመከራ፡ቀን፡አንተ፡መጠጊያዬ፡ነኽ።
18፤አሳዳጆቼ፡ይፈሩ፥እኔ፡ግን፡አልፈር፤እነርሱ፡ይደንግጡ፥እኔ፡ግን፡አልደንግጥ፤ክፉንም፡ቀን፡አምጣባቸው ፥በኹለት፡ዕጥፍ፡ጥፋት፡አጥፋቸው።
19፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦ኺድ፥የይሁዳም፡ነገሥታት፡በሚገቡበትና፡በሚወጡበት፡በሕዝቡ፡ልጆች፡በር ፡በኢየሩሳሌምም፡በሮች፡ዅሉ፡ቁም፤
20፤እንዲህም፡በላቸው፦በእነዚህ፡በሮች፡የምትገቡ፥እናንተ፡የይሁዳ፡ነገሥታት፥ይሁዳም፡ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም ፡የምትኖሩ፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
21፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለራሳችኹ፡ተጠንቀቁ፥በሰንበትም፡ቀን፡ሸክም፡አትሸከሙ፥በኢየሩሳሌምም፡በ ሮች፡አታግቡ፥
22፤ከቤቶቻችኹም፡በሰንበት፡ቀን፡ሸክምን፡አታውጡ፥ሥራንም፡ዅሉ፡አትሥሩበት፤አባቶቻችኹንም፡እንዳዘዝኹ፡የ ሰንበትን፡ቀን፡ቀድሱ።
23፤እነርሱ፡ግን፡አልሰሙም፡ዦሯቸውን፡አላዘነበሉም፥እንዳይሰሙና፡እንዳይገሠጹም፡ዐንገታቸውን፡አደነደኑ።
24፤እኔን፡ፈጽሞ፡ብትሰሙ፤ይላል፡እግዚአብሔር፥በሰንበትም፡ቀን፡በዚች፡ከተማ፡በሮች፡ሸክም፡ባታገቡ፥የሰን በትንም፡ቀን፡ብትቀድሱ፡ሥራንም፡ዅሉ፡ባትሠሩበት፥
25፤በዳዊት፡ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጡ፡ነገሥታትና፡መሳፍንት፡በሠረገላዎችና፡በፈረሶች፡ላይ፡እየተቀመጡ፡በዚች ፡ከተማ፡በሮች፡ይገባሉ፤እነርሱና፡መሳፍንቶቻቸው፡የይሁዳም፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌምም፡የሚቀመጡ፡ይገባሉ፥ይህ ችም፡ከተማ፡ለዘለዓለም፡የሰው፡መኖሪያ፡ትኾናለች።
26፤የሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕትን፡የእኽሉንም፡ቍርባን፡ዕጣኑንም፡የምስጋናውንም፡መሥዋዕት፡ይዘ ው፡ከይሁዳ፡ከተማዎች፡ከኢየሩሳሌምም፡ዙሪያ፡ከብንያምም፡አገር፡ከቈላውም፡ከደጋውም፡ከደቡብም፡ወደእግዚአ ብሔር፡ቤት፡ይመጣሉ።
27፤ነገር፡ግን፥የሰንበትን፡ቀን፡እንድትቀድሱ፥በሰንበትም፡ቀን፡ሸክምን፡ተሸክማችኹ፡በኢየሩሳሌም፡በሮች፡ እንዳትገቡ፡የነገርዃችኹን፡ባትሰሙኝ፥በበሮቿ፡ላይ፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥የኢየሩሳሌምንም፡አዳራሾች፡ትበላ ለች፥አትጠፋም።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18፤
1-2፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፥እንዲህም፡አለው፦ተነሥተኽ፡ወደሸክላ፡ሠሪው፡ቤት፡ው ረድ፥በዚያም፡ቃሌን፡አሰማኻለኹ።
3፤ወደሸክላ፡ሠሪው፡ቤትም፡ወረድኹ፥እንሆም፥ሥራውን፡በመንኰራኵር፡ላይ፡ይሠራ፡ነበር።
4፤ከጭቃም፡ይሠራው፡የነበረ፡ዕቃ፡በሸክላ፡ሠሪው፡እጅ፡ተበላሸ፥ሸክላ፡ሠሪውም፡እንደ፡ወደደ፡መልሶ፡ሌላ፡ዕ ቃ፡አድርጎ፡ሠራው።
5፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
6፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ይህ፡ሸክላ፡ሠሪ፡እንደሚሠራ፡በእውኑ፡እኔ፡በእናንተ፡ዘንድ፡መሥራት፡አይቻለኝምን ፧እንሆ፥ጭቃው፡በሸክላ፡ሠሪ፡እጅ፡እንዳለ፥እንዲሁ፡እናንተ፡በእኔ፡እጅ፡አላችኹ።
7፤ስለ፡ሕዝብ፡ስለ፡መንግሥትም፡እነቅል፡አፈርስም፡አጠፋም፡ዘንድ፡በተናገርኹ፡ጊዜ፥
8፤ይህ፡ስለ፡ርሱ፡የተናገርኹበት፡ሕዝብ፡ከክፋቱ፡ቢመለስ፥እኔ፡አደርግበት፡ዘንድ፡ካሰብኹት፡ክፉ፡ነገር፡እ ጸጸታለኹ።
9፤ስለ፡ሕዝቡም፡ስለ፡መንግሥትም፡እሠራውና፡እተክለው፡ዘንድ፡በተናገርኹ፡ጊዜ፥
10፤በፊቴ፡ክፉን፡ነገር፡ቢያደርግ፡ቃሌንም፡ባይሰማ፥እኔ፡አደርግለት፡ዘንድ፡ስለተናገርኹት፡መልካም፡ነገር ፡እጸጸታለኹ።
11፤አኹን፡እንግዲህ፡ለይሁዳ፡ሰዎችና፡በኢየሩሳሌም፡ለሚቀመጡ።እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ክፉ፡ነ ገር፡እፈጥርባችዃለኹ፥ዐሳብንም፡ዐስብባችዃለኹ፤አኹንም፡ዅላችኹ፡ከክፉ፡መንገዳችኹ፡ተመለሱ፥መንገዳችኹን ና፡ሥራችኹንም፡አቅኑ፡ብለኽ፡ተናገራቸው።
12፤እነርሱ፡ግን፦እንጨክናለን፤ዐሳባችንን፡ተከትለን፡እንኼዳለን፡ዅላችንም፡እንደ፡ክፉው፡ልባችን፡እልከኝ ነት፡እናደርጋለን፡አሉ።
13፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በአሕዛብ፡መካከል፦እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ማን፡ሰምቷል፧ብላችኹ፡ጠ ይቁ።የእስራኤል፡ድንግል፡በጣም፡የሚያስደነግጠውን፡ነገር፡አድርጋለች።
14፤በእውኑ፡የሊባኖስ፡በረዶ፡የምድረ፡በዳውን፡ድንጋይ፡ይተዋልን፧ወይስ፡ከሩቅ፡የምትመጣው፡ቀዝቃዛዪቱ፡ፈ ሳሽ፡ውሃ፡ትደርቃለችን፧
15፤ሕዝቤ፡ግን፡ረስተውኛል፡ለከንቱ፡ነገርም፡ዐጥነዋል፤ከመንገዱም፡ተሰናክለዋል፡ከቀድሞውም፡ጐዳና፡ርቀው ፡ወዳልተሠራው፡ወደ፡ጠማማው፡መንገድ፡ፈቀቅ፡ብለዋል።
16፤ምድራቸውን፡ለመደነቂያና፡ለዘለዓለም፡ማፏጫ፡አድርገዋል፤የሚያልፍባት፡ዅሉ፡ይደነቃል፥ራሱንም፡ያነቃን ቃል።
17፤በጠላት፡ፊት፡እንደ፡ምሥራቅ፡ነፋስ፡እበትናቸዋለኹ፥በጥፋታቸውም፡ቀን፡ዠርባዬን፡እንጂ፡ፊቴን፡አላሳያ ቸውም።
18፤እነርሱም፦ሕግ፡ከካህን፥ምክርም፡ከጠቢብ፥ቃልም፡ከነቢይ፡አይጠፋምና፡ኑ፥በኤርምያስ፡ላይ፡ዐሳብን፡እና ስብ።ኑ፥በምላስ፡እንምታው፥ቃሉንም፡ዅሉ፡አናድምጥ፡አሉ።
19፤አቤቱ፥አድምጠኝ፥የክርክሬንም፡ቃል፡ስማ።
20፤ለነፍሴ፡ጕድጓድ፡ቈፍረዋልና፥በእውኑ፡በመልካም፡ፋንታ፡ክፉ፡ይመለሳልን፧ስለ፡እነርሱ፡በመልካም፡እናገ ር፡ዘንድ፡ቍጣኽንም፡ከነርሱ፡እመልስ፡ዘንድ፡በፊትኽ፡እንደ፡ቆምኹ፡ዐስብ።
21፤ስለዚህ፥ልጆቻቸውን፡ለራብ፡ስጥ፥ለሰይፍም፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ስጣቸው፥ሚስቶቻቸውም፡የወላድ፡መካንና፡መበ ለቶች፡ይኹኑ፥ወንዶቻቸውም፡በሞት፡ይጥፉ፥ጕልማሳዎቻቸውም፡በሰልፍ፡ጊዜ፡በሰይፍ፡ይመቱ።
22፤ሊይዙኝ፡ጕድጓድ፡ቈፍረዋልና፥ለእግሮቼም፡ወጥመድ፡ሸሽገዋልና፥ድንገት፡በላያቸው፡ጭፍራ፡ባመጣኽ፡ጊዜ፡ ከቤታቸው፡ጩኸት፡ይሰማ።
23፤አንተ፡ግን፥አቤቱ፥ይገድሉኝ፡ዘንድ፡በላዬ፡የመከሩትን፡ምክር፡ዅሉ፡ታውቃለኽ፤በደላቸውን፡ይቅር፡አትበ ል፥ኀጢአታቸውንም፡ከፊትኽ፡አትደምስስ፤በፊትኽም፡ይውደቁ፥በቍጣኽ፡ጊዜ፡እንዲሁ፡አድርግባቸው።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19፤
1፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ኺድ፥ከሸክላ፡ሠሪ፡ገምቦ፡ግዛ፥ከሕዝቡም፡ሽማግሌዎችና፡ከካህናት፡ሽማግሌ ዎች፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤
2፤በካርሲት፡በር፡መግቢያ፡አጠገብ፡ወዳለው፡ወደሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ኺድ፥በዚያም፡የምነግርኽን፡ቃል፡ተናገር ፥
3፤እንዲህም፡በል፦የይሁዳ፡ነገሥታትና፡በኢየሩሳሌም፡የምትኖሩ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤የእስራኤል ፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሰማውን፡ሰው፡ዦሮ፡ጭው፡የሚያደርግ፡ክፉ፡ነገር፥ እንሆ፥በዚህ፡ስፍራ፡አመጣለኹ።
4፤ትተውኛልና፥ይህንም፡ስፍራ፡እንግዳ፡አድርገውታልና፥እነርሱና፡አባቶቻቸውም፡ለማያውቋቸው፡ለሌላዎች፡አማ ልክት፡ዐጥነዋልና፥የይሁዳም፡ነገሥታት፡ይህን፡ስፍራ፡በንጹሕ፡ደም፡ሞልተዋልና፥
5፤እኔም፡ያላዘዝኹትን፡ያልተናገርኹትንም፡ወደ፡ልቤም፡ያልገባውን፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡አድርገው፡ለበዓ ል፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡ያቃጥሉ፡ዘንድ፡የበዓልን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡ሠርተዋልና፥ስለዚህ፥
6፤እንሆ፥ይህ፡ስፍራ፡የዕርድ፡ሸለቆ፡ይባላል፡እንጂ፡ቶፌት፡ወይም፡የሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ዳግመኛ፡የማይባልበ ት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
7፤በዚህም፡ስፍራ፡የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌምን፡ምክር፡አፈርሳለኹ፥በጠላቶቻቸውም፡ፊት፡በሰይፍና፡ነፍሳቸውን ፡በሚሹት፡እጅ፡እጥላቸዋለኹ፥ሬሳቸውንም፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡መብል፡አድርጌ፡እሰጣለኹ።
8፤ይህችንም፡ከተማ፡ለመደነቂያና፡ለማፏጫ፡አደርጋታለኹ፤የሚያልፍባትም፡ዅሉ፡ስለተደረገባት፡መቅሠፍት፡ዅሉ ፡ይደነቃል፡ከንፈሩንም፡ይመጥጣል።
9፤የወንዶችና፡የሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ሥጋ፡አበላቸዋለኹ፥ዅሉም፡ጠላቶቻቸውንና፡ነፍሳቸውን፡የሚሹት፡በሚያስ ጨንቋቸው፡ጭንቀትና፡መከበብ፡የባልንጀራዎቻቸውን፡ሥጋ፡ይበላሉ።
10፤ገምቦውንም፡ከአንተ፡ጋራ፡በሚኼዱ፡ሰዎች፡ፊት፡ትሰብራለኽ፥
11፤እንዲህም፡ትላቸዋለኽ፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሸክላ፡ሠሪው፡ዕቃ፡እንደሚሰባበር ፡ደግሞም፡ይጠገን፡ዘንድ፡እንደማይቻል፥እንዲሁ፡ይህን፡ሕዝብና፡ይህችን፡ከተማ፡እሰብራለኹ፤የሚቀብሩበትም ፡ስፍራ፡ሌላ፡የለምና፡በቶፌት፡ይቀበራሉ።
12፤እንዲሁ፡በዚህ፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡አደርጋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ይህችንም፡ከተማ፡እንደ፡ቶፌ ት፡አደርጋለኹ።
13፤የረከሱትም፡የኢየሩሳሌም፡ቤቶችና፡የይሁዳ፡ነገሥታት፡ቤቶች፥እነዚያ፡በሰገነታቸው፡ላይ፡ለሰማይ፡ሰራዊ ት፡ዅሉ፡ያጠኑባቸው፡ለሌላዎችም፡አማልክት፡የመጠጥን፡ቍርባን፡ያፈሰሱባቸው፡ቤቶች፡ዅሉ፥እንደ፡ቶፌት፡ስፍ ራ፡ይኾናሉ።
14፤ኤርምያስም፡እግዚአብሔር፡ትንቢት፡ሊናገር፡ወደዚያ፡ልኮት፡ከነበረው፡ስፍራ፡ከቶፌት፡መጣ፥በእግዚአብሔ ርም፡ቤት፡አደባባይ፡ቆሞ፡ለሕዝብ፡ዅሉ፦
15፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ቃሌን፡እንዳይሰሙ፡ዐንገታቸውን፡አደንድነዋልና፥እን ሆ፥በዚች፡ከተማና፡በመንደሮቿ፡ዅሉ፡ላይ፡የተናገርኹባትን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አመጣለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20፤
1፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተሾመው፡አለቃ፡የካህኑ፡የኢሜር፡ልጅ፡ጳስኮር፡ኤርምያስ፡በዚህ፡ነገር፡ትንቢት፡ ሲናገር፡ሰማ።
2፤ጳስኮርም፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡መታው፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በነበረው፡በላይኛው፡በብንያም፡በር፡ባለው፡ በእግር፡ግንድ፡ውስጥ፡አኖረው።
3፤በነጋውም፡ጳስኮር፡ኤርምያስን፡ከግንድ፡ውስጥ፡አወጣው።ኤርምያስም፡እንዲህ፡አለው፦እግዚአብሔር፡ስምኽን ፦ማጎርሚሳቢብ፡እንጂ፡ጳስኮር፡ብሎ፡አይጠራኽም።
4፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ለራስኽና፡ለወዳጆችኽ፡ዅሉ፡ፍርሀት፡አደርግኻለኹ፤እነርሱም፡በጠላ ቶቻቸው፡ሰይፍ፡ይወድቃሉ፡ዐይኖችኽም፡ያያሉ፤ይሁዳንም፡ዅሉ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፥ርሱ ም፡ወደ፡ባቢሎን፡ያፈልሳቸዋል፡በሰይፍም፡ይገድላቸዋል።
5፤የዚችንም፡ከተማ፡ባለጠግነት፡ዅሉ፡ጥሪቷንም፡ዅሉ፡ክብሯንም፡ዅሉ፡የይሁዳንም፡ነገሥታት፡መዝገብ፡ዅሉ፡በ ጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፥እነርሱም፡ይበዘብዟቸዋል፡ይዘውም፡ወደ፡ባቢሎን፡ያፈልሷቸዋል።
6፤አንተም፥ጳስኮር፡ሆይ፥በቤትኽም፡የሚኖሩት፡ዅሉ፡ተማርካችኹ፡ትኼዳላችኹ፤አንተም፡በሐሰትም፡ትንቢት፡የተ ናገርኽላቸው፡ወዳጆችኽ፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡ትገባላችኹ፥በዚያም፡ትሞታላችኹ፥በዚያም፡ትቀበራላችኹ።
7፤አቤቱ፥አታለልኸኝ፡እኔም፡ተታለልኹ፥ከእኔም፡በረታኽ፡አሸነፍኽም፤ቀኑን፡ዅሉ፡መሳቂያ፡ኾኛለኹ፥ዅሉም፡ያ ላግጡብኛል።
8፤በተናገርኹ፡ቍጥር፡እጮኻለኹ፤ግፍና፡ጥፋት፡ብዬ፡እጮኻለኹ፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ቀኑን፡ዅሉ፡ስድብና፡ዋዛ ፡ኾኖብኛልና።
9፤እኔም፦የእግዚአብሔርን፡ስም፡አላነሣም፥ከእንግዲህ፡ወዲህም፡በስሙ፡አልናገርም፡ብል፥በዐጥንቶቼ፡ውስጥ፡ እንደ፡ገባ፡እንደሚነድ፟፡እሳት፡ያለ፡በልቤ፡ኾነብኝ፤ደከምኹ፥መሸከምም፡አልቻልኹም።
10፤የብዙ፡ሰዎችን፡ስድብ፡ሰምቻለኹ፥ማስፈራራትም፡ከቦ፟ኛል።መውደቄን፡የሚጠብቁ፡የሰላሜ፡ሰዎች፡ዅሉ፦ምና ልባት፡ይታለል፡እንደ፡ኾነ፥እናሸንፈውም፡እንደ፡ኾነ፥ርሱንም፡እንበቀል፡እንደ፡ኾነ፥ክሰሱት፡እኛም፡እንከ ሰ፟ዋለን፡ይላሉ።
11፤እግዚአብሔር፡ግን፡እንደ፡ኀያልና፡እንደ፡ጨካኝ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነው፤ስለዚህ፥አሳዳጆቼ፡ይሰናከላሉ፥አያሸ ንፉም፤አይከናወንላቸውምና፥በጽኑ፡ዕፍረት፡ያፍራሉ፤ለዘለዓለምም፡በማይረሳ፡ጕስቍልና፡ይጐሰቍላሉ።
12፤አቤቱ፥ጻድቅን፡የምትመረምር፡ኵላሊትንና፡ልብን፡የምትመለከት፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥ክርክሬን፡ገልጬልኻ ለኹና፡በቀልኽን፡በላያቸው፡ለይ።
13፤ለእግዚአብሔር፡ዘምሩ፡እግዚአብሔርንም፡አመስግኑ፤የችግረኛውን፡ነፍስ፡ከክፉ፡አድራጊዎች፡እጅ፡አድኗል ና።
14፤የተወለድኹባት፡ቀን፡የተረገመች፡ትኹን፤እናቴ፡እኔን፡የወለደችባት፡ቀን፡የተባረከች፡አትኹን።
15፤ወንድ፡ልጅ፡ተወልዶልኻል፡ብሎ፡ለአባቴ፡የምሥራች፡ነግሮ፡ደስ፡ያሠኘው፡ሰው፡የተረገመ፡ይኹን።
16፤ያም፡ሰው፡እግዚአብሔር፡ሳይጸጸት፡እንደ፡ገለበጣቸው፡ከተማዎች፡ይኹን፥በማለዳም፡ልቅሶን፡በቀትርም፡ጩ ኸትን፡ይስማ፤
17፤እናቴ፡መቃብር፡ትኾነኝ፡ዘንድ፡ማሕፀኗም፡ዘወትር፡ይዞኝ፡ያቈይ፡ዘንድ፡በማሕፀን፡ውስጥ፡አልገደለኝምና ።
18፤ድካምንና፡ጣርን፡አይ፡ዘንድ፡ዘመኔም፡በዕፍረት፡ታልቅ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡ከማሕፀን፡ወጣኹ፧
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21፤
1፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው።
2፤ይህም፡የኾነው፡ንጉሡ፡ሴዴቅያስ፦የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ይወጋናልና፥ስለ፡እኛ፥እባክኽ፥እግዚአብ ሔርን፡ጠይቅ፤ከእኛም፡ይመለስ፡ዘንድ፡ምናልባት፡እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡እንደ፡ተኣምራቱ፡ዅሉ፡ያደርግ፡ ይኾናል፡ብሎ፡የመልክያን፡ልጅ፡ጳስኮርንና፡ካህኑን፡የመዕሴያን፡ልጅ፡ሶፎንያስ፡ወደ፡ኤርምያስ፡በላከ፡ጊዜ ፡ነው።
3፤ኤርምያስም፡እንዲህ፡አላቸው፦ሴዴቅያስን፡እንዲህ፡በሉት፦
4፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የባቢሎንን፡ንጉሥ፡በቅጥርም፡ውጭ፡የከበቧችኹን ፡ከለዳውያንን፡የምትወጉበትን፡በእጃችኹ፡ያለውን፡ዕቃ፡ጦራችኹን፡እመልሰዋለኹ፥እነዚያንም፡ወደዚች፡ከተማ ፡ውስጥ፡እሰበስባቸዋለኹ።
5፤እኔም፡በተዘረጋች፡እጅና፡በብርቱ፡ክንድ፥በቍጣና፡በመዓት፡በታላቅም፡መቅሠፍት፡እወጋችዃለኹ።
6፤በዚችም፡ከተማ፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፡ሰዎችንና፡እንስሳዎችን፡እመታለኹ፥በጽኑም፡ቸነፈር፡ይሞታሉ።
7፤ከዚህ፡በዃላ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የይሁዳን፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስን፡ከቸነፈርና፡ከሰይፍ፡ከራብም፡በዚች፡ከተ ማ፡የቀሩትንም፡ባሪያዎቹንና፡ሕዝቡን፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፡በጠላቶቻቸውና፡ነፍሳቸውንም፡ በሚሹት፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፤ርሱም፡በሰይፍ፡ስለት፡ይመታቸዋል፤አያዝንላቸውም፥አይራራላቸውም፥አይ ምራቸውም።
8፤ለዚህም፡ሕዝብ፡እንዲህ፡በል፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በፊታችኹ፡የሕይወትን፡መንገድና፡የሞት ን፡መንገድ፡አድርጌያለኹ።
9፤በዚች፡ከተማ፡ውስጥ፡የሚዘገይ፥በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ይሞታል፤ወጥቶ፡ወደከበቧችኹ፡ወደ፡ከለዳውያ ን፡የሚገባ፡ግን፡በሕይወት፡ይኖራል፥ነፍሱም፡ምርኮ፡ትኾንለታለች።
10፤ለመልካም፡ሳይኾን፡ለክፉ፡ፊቴን፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡አድርጌያለኹና፤ለባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ትሰጣለች፥ር ሱም፡በእሳት፡ያቃጥላታል።
11፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
12፤የዳዊት፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሥራችኹ፡ክፋት፡ቍጣዬ፡እንደ፡እሳት፡እንዳይወጣና፡ ማንም፡ሳያጠፋው፡እንዳይነድ፟፥በማለዳ፡ፍርድን፡አድርጉ፡የተበዘበዘውንም፡ካስጨናቂው፡እጅ፡አድኑ።
13፤እንሆ፥በሸለቆው፡ውስጥ፡በሜዳ፡ላይም፡ባለው፡ዐምባ፡የምትቀመጪ፡ሆይ፥እኔ፡ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፤እናንተም፦ በእኛ፡ላይ፡የሚወርድ፡ወይም፡ወደ፡መኖሪያችን፡የሚገባ፡ማን፡ነው፧የምትሉ፡ሆይ፥እኔ፡በእናንተ፡ላይ፡ነኝ፤
14፤እንደ፡ሥራችኹም፡ፍሬ፡እቀጣችዃለኹ፤በዱሯም፡ውስጥ፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥በዙሪያዋም፡ያለውን፡ዅሉ፡ይበ ላል።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22፤
1፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አለ፦ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡ውረድ፡በዚያም፡ይህን፡ቃል፡ተናገር፥
2፤እንዲህም፡በል፦በዳዊት፡ዙፋን፡የምትቀመጥ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሆይ፥አንተና፡ባሪያዎችኽ፡በእነዚህም፡በሮች፡ የሚገባ፡ሕዝብኽ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
3፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ፍርድንና፡ጽድቅን፡አድርጉ፡የተበዘበዘውንም፡ካስጨናቂው፡እጅ፡አድኑ፤መጻተ ኛውንና፡ድኻ፡አደጉን፡መበለቲቱንም፡አትበድሉ፥አታምፁባቸውም፥በዚህም፡ስፍራ፡ንጹሕ፡ደምን፡አታፍስሱ።
4፤ይህንንም፡ነገር፡ብታደርጉ፥በዳዊት፡ዙፋን፡የሚቀመጡ፡ነገሥታት፥በሠረገላዎችና፡በፈረሶች፡ላይ፡ተቀምጠው ፥በዚህ፡ቤት፡በሮች፡ይገባሉ፤ርሱም፡ባሪያዎቹም፡ሕዝቡም፡እንዲሁ፡ይገባሉ።
5፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ቃል፡ባትሰሙ፥ይህ፡ቤት፡ወና፡እንዲኾን፡በራሴ፡ምያለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
6፤እግዚአብሔር፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡እንዲህ፡ይላልና፦አንተ፡በእኔ፡ዘንድ፡እንደ፡ገለዓድና፡እንደ፡ሊባኖ ስ፡ራስ፡ነኽ፥ነገር፡ግን፥በርግጥ፡ምድረ፡በዳ፡ማንም፡የማይቀመጥባቸውም፡ከተማዎች፡አደርግኻለኹ።
7፤መሣሪያም፡የሚይዙትን፡አጥፊዎች፡ባንተ፡ላይ፡አዘጋጃለኹ፥የተመረጡትንም፡የዝግባ፡ዛፎችኽን፡ይቈርጣሉ፥በ እሳትም፡ውስጥ፡ይጥሏቸዋል።
8፤ብዙ፡አሕዛብም፡በዚች፡ከተማ፡አጠገብ፡ያልፋሉ፥ዅሉም፡ባልንጀራዎቻቸውን፦እግዚአብሔር፡በዚች፡ታላቅ፡ከተ ማ፡ለምን፡እንዲህ፡አደርገ፧ይላሉ።
9፤እነርሱም፦የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ትተው፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ስለ፡ሰገዱ፡ስላመለኳ ቸውም፡ነዋ፡ብለው፡ይመልሳሉ።
10፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይመለስምና፥የተወለደባትንም፡አገር፡አያይምና፡ለሚወጣ፡እጅግ፡አልቅሱ፡እንጂ፡ለሞ ተ፡አታልቅሱ፡አትዘኑለትም።
11፤በአባቱ፡በኢዮስያስ፡ፋንታ፡ስለነገሠው፡ከዚህም፡ስፍራ፡ስለወጣው፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ስለኢዮስያስ፡ልጅ፡ ስለ፡ሰሎም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦
12፤እንግዲህም፡ወደዚህ፡አይመለስም፥በተማረከባት፡አገር፡ይሞታል፡እንጂ፤ይህችንም፡አገር፡ከእንግዲህ፡ወዲ ህ፡አያይም።
13፤ቤቱን፡በግፍ፡ሰገነቱንም፡በዐመፅ፡ለሚሠራ፥ባልንጀራውንም፡እንዲያው፡በከንቱ፡ለሚያሠራ፥ዋጋውንም፡ለማ ይሰጠው፤
14፤ለራሴ፡ሰፊ፡ቤት፡ትልቅም፡ሰገነት፡እሠራለኹ፡ለሚል፥መስኮትንም፡ለሚያወጣ፥በዝግባም፡ሥራ፡ለሚያሳጌጥ፥ በቀይ፡ቀለምም፡ለሚቀባው፡ወዮለት!
15፤በዝግባ፡ዕንጨት፡ስለምትወዳደር፡በእውኑ፡ትነግሣለኽን፧በእውኑ፡አባትኽ፡አይበላምና፡አይጠጣም፡ነበርን ፧ፍርድንና፡ጽድቅንስ፡አያደርግም፡ነበርን፧በዚያም፡ጊዜ፡መልካም፡ኾኖለት፡ነበር።
16፤የድኻውንና፡የችግረኛውን፡ፍርድ፡ይፈርድ፡ነበር፥በዚያም፡ጊዜ፡መልካም፡ኾኖ፡ነበር።ይህ፡እኔን፡ማወቅ፡ አይደለምን፧ይላል፡እግዚአብሔር።
17፤ዐይንኽና፡ልብኽ፡ግን፡ለሥሥት፡ንጹሕ፡ደምንም፡ለማፍሰስ፡ዐመፅንና፡ግፍንም፡ለመሥራት፡ብቻ፡ነው።
18፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ስለኢዮስያስ፡ልጅ፡ስለ፡ኢዮአቄም፡እንዲህ፡ይላል፦ወንድሜ፡ሆይ ፥ወዮ! እያሉ፡አያለቅሱለትም፥ወይም፦ጌታ፡ሆይ፥ወዮ! እያሉ፡አያለቅሱለትም።
19፤አህያም፡እንደሚቀበር፡ይቀበራል፥ከኢየሩሳሌምም፡በር፡ወደ፡ውጭ፡ተጐትቶ፡ይጣላል።
20፤ውሽማዎችሽ፡ዅሉ፡ጠፍተዋልና፥ወደ፡ሊባኖስ፡ወጥተሽ፡ጩኺ፤በባሳን፡ላይ፡ድምፅሽን፡አንሺ፤በዓባሪምም፡ው ስጥ፡ኾነሽ፡ጩኺ።
21፤በደኅንነትሽ፡ጊዜ፡ተናገርኹሽ፤አንቺም፦አልሰማም፡አልሽ።ከሕፃንነትሽ፡ዠምሮ፡ቃሌን፡አለመስማትሽ፡መን ገድሽ፡ነው።
22፤በግ፡ጠባቂዎችሽን፡ዅሉ፡ነፋስ፡ይጠብቃቸዋል፥ውሽማዎችሽም፡ተማርከው፡ይኼዳሉ፤በዚያን፡ጊዜም፡ስለ፡ክፋ ትሽ፡ዅሉ፡ታፍሪያለሽ፡ትጐሳቈይማለሽ።
23፤አንቺ፡በሊባኖስ፡የምትቀመጪ፥በዝግባ፡ዛፍም፡ውስጥ፡ጐዦሽን፡የምትሠሪ፡ሆይ፥ምጥ፡እንደ፡ያዛት፡ሴት፡ሕ ማም፡በያዘሽ፡ጊዜ፡እንዴት፡ታጓሪያለሽ!
24፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮአቄም፡ልጅ፡ኢኮንያን፡የቀኝ፡እጄ፡ማኅተም፡ቢኾን፡ኖሮ፡እንኳ፥ ከዚያ፡እነቅልኽ፡ነበር፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
25፤ነፍስኽንም፡ለሚሹት፡ለምትፈራቸውም፡እጅ፥ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡ለከለዳውያንም፡እጅ፡እሰጥኻ ለኹ።
26፤አንተንም፡የወለደችኽንም፡እናትኽን፡ወዳልተወለዳችኹባት፡ወደ፡ሌላ፡አገር፡እጥላችዃለኹ፥በዚያም፡ትሞታ ላችኹ።
27፤ይመለሱባትም፡ዘንድ፡ነፍሳቸው፡ወደምትመኛት፡ወደዚያች፡ምድር፡አይመለሱም።
28፤በእውኑ፡ይህ፡ሰው፡ኢኮንያን፡የተናቀና፡የተሰበረ፡የሸክላ፡ዕቃ፡ነውን፧ወይስ፡ርሱ፡ለአንዳች፡የማይረባ ፡የሸክላ፡ዕቃ፡ነውን፧ርሱና፡ዘሩስ፡በማያውቋት፡ምድር፡ስለ፡ምን፡ተጥለው፡ወደቁ፧
29፤ምድር፡ሆይ፥ምድር፡ሆይ፥ምድር፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሚ።
30፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከዚህ፡ሰው፡ዘር፡የሚከናወን፡በዳዊትም፡ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጥ፡በይሁዳም፡ የሚነግሥ፡እንግዲህ፡አይገኝምና።መካን፡በዘመኑም፡የማይከናወንለት፡ሰው፡ብላችኹ፡ጻፉ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23፤
1፤የማሰማሪያዬን፡በጎች፡ለሚያጠፉና፡ለሚበትኑ፡እረኛዎች፡ወዮላቸው! ይላል፡እግዚአብሔር።
2፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፥ሕዝቤን፡ስለሚጠብቁ፡እረኛዎች፡እንዲህ፡ይላል፦በጎቼን፡በትና ችዃል፥አባራ፟ችዃቸውማል፥አልጐበኛችዃቸውምም፤እንሆ፥የሥራችኹን፡ክፋት፡እጐበኝባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብ ሔር።
3፤የመንጋዬም፡ቅሬታ፡ካባረርዃቸው፡ምድር፡ዅሉ፡ወደ፡በረታቸው፡ሰብስቤ፡እመልሳቸዋለኹ፤እነርሱም፡ያፈራሉ፥ ይበዙማል።
4፤የሚጠብቋቸውን፡እረኛዎች፡አስነሣላቸዋለኹ፥ዳግመኛም፡አይፈሩምና፡አይደነግጡም፥ከነሱም፡አንድ፡አይጐድል ም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
5፤እንሆ፥ለዳዊት፡ጻድቅ፡ቍጥቋጥ፡የማስነሣበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ርሱም፡እንደ፡ንጉሥ፡ይ ነግሣል፥ይከናወንለታልም፥በምድርም፡ፍርድንና፡ጽድቅን፡ያደርጋል።
6፤በዘመኑም፡ይሁዳ፡ይድናል፡እስራኤልም፡ተዘልሎ፡ይቀመጣል፥የሚጠራበትም፡ስም፦እግዚአብሔር፡ጽድቃችን፡ተብ ሎ፡ነው።
7፤ስለዚህ፥እንሆ፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዳግመኛ፡የማይባልበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
8፤ነገር፡ግን፦የእስራኤልን፡ቤት፡ዘር፡ከሰሜን፡አገርና፡ካሰደድዃቸውም፡አገር፡ዅሉ፡ያወጣና፡የመራ፡ሕያው፡ እግዚአብሔርን! ይባላል፤በምድራቸውም፡ይቀመጣሉ።
9፤ስለ፡ነቢያት፤ልቤ፡በውስጤ፡ተሰብሯል፡ዐጥንቶቼም፡ዅሉ፡ታውከዋል፤ከእግዚአብሔር፡የተነሣ፡ከቅዱስ፡ቃሉም ፡የተነሣ፡የወይን፡ጠጅ፡እንዳሸነፈው፡እንደ፡ሰካራም፡ሰው፡ኾኛለኹ።
10፤ምድር፡ከአመንዝራዎች፡ተሞልታለችና፥ከመርገምም፡የተነሣ፡ምድር፡አልቅሳለች፤የምድረ፡በዳ፡ማሰማሪያ፡ደ ርቋል፤አካኼዳቸው፡ክፉ፡ነው፥ብርታታቸውም፡ቅን፡አይደለም።
11፤ነቢዩና፡ካህኑም፡ረክሰዋልና፥በቤቴም፡ውስጥ፡ክፋታቸውን፡አግኝቻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
12፤ስለዚህ፥መንገዳቸው፡በጨለማ፡እንዳለች፡እንደ፡ድጥ፡ስፍራ፡ትኾንባቸዋለች፥እነርሱም፡ፍግምግም፡ብለው፡ ይወድቁባታል፤እኔም፡በምጐበኛቸው፡ዓመት፡ክፉ፡ነገርን፡አመጣባቸዋለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
13፤በሰማርያ፡ነቢያት፡ላይ፡ስንፍናን፡አይቻለኹ፤በበዓል፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ነበር፥ሕዝቤንም፡እስራኤል፡ያስ ቱ፡ነበር።
14፤በኢየሩሳሌምም፡ነቢያት፡ላይ፡የሚያስደነግጥን፡ነገር፡አይቻለኹ፤ያመነዝራሉ፡በሐሰትም፡ይኼዳሉ፤ማንም፡ ከክፋቱ፡እንዳይመለስ፡የክፉ፡አድራጊዎችን፡እጅ፡ያበረታሉ፤ዅሉም፡እንደ፡ሰዶም፡የሚኖሩባትም፡እንደ፡ገሞራ ፡ኾኑብኝ።
15፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከኢየሩሳሌም፡ነቢያት፡ዘንድ፡ርኵሰት፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ ወጥቷልና፥ሬትን፡አበላቸዋለኹ፥የሐሞትንም፡ውሃ፡አጠጣቸዋለኹ።
16፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትንቢት፡የሚናገሩላችኹን፡የነቢያትን፡ቃል፡አትሰሙ፤ከንቱ ነትን፡ያስተምሯችዃል፤ከእግዚአብሔር፡አፍ፡ሳይኾን፡ከገዛ፡ልባቸው፡የወጣውን፡ራእይ፡ይናገራሉ።
17፤ለሚንቁኝ፡ዅልጊዜ፦እግዚአብሔር፦ሰላም፡ይኾንላችዃል፡ብሏል፡ይላሉ፤በልቡም፡እልከኝነት፡ለሚኼድ፡ዅሉ፦ ክፉ፡ነገር፡አያገኛችኹም፡ይላሉ።
18፤ቃሉን፡ያይና፡ይሰማ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ምክር፡የቆመ፡ማን፡ነውና፧ቃሉንስ፡ያደመጠ፡የሰማስ፡ማን፡ነ ው፧
19፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ዐውሎ፡ነፋስ፥ርሱም፡ቍጣው፥የሚያገለባብጥ፡ዐውሎ፡ነፍስ፡ወጥቷል፤የዐመፀኛዎችን ፡ራስ፡ይገለባብጣል።
20፤የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡የልቡን፡ዐሳብ፡ሠርቶ፡እስኪፈጽም፡ድረስ፡አይመለስም፤በዃለኛው፡ዘመን፡ፈጽማችኹ፡ ታስተውሉታላችኹ።
21፤እኔ፡ሳል፟ካቸው፡እነዚህ፡ነቢያት፡ሮጡ፤እኔም፡ሳልነግራቸው፡ትንቢትን፡ተናገሩ።
22፤በምክሬ፡ግን፡ቢቆሙ፡ኖሮ፥ለሕዝቤ፡ቃሌን፡ባሰሙ፡ነበር፥ከክፉም፡መንገዳቸው፡ከሥራቸውም፡ክፋት፡በመለሷ ቸው፡ነበር።
23፤እኔ፡የቅርብ፡አምላክ፡ነኝ፡እንጂ፡የሩቅ፡አምላክ፡አይደለኹም።
24፤ሰው፡በስውር፡ቢሸሸግ፥እኔ፡አላየውምን፧ሰማይንና፡ምድርንስ፡የሞላኹ፡እኔ፡አይደለኹምን፧ይላል፡እግዚአ ብሔር።
25፤ዐለምኹ፥ዐለምኹ፡እያሉ፡በስሜ፡ሐሰትን፡የሚናገሩትን፡የነቢያትን፡ነገር፡ሰምቻለኹ።
26፤ትንቢትን፡በሐሰት፡በሚናገሩ፥የልባቸውንም፡ሽንገላ፡በሚናገሩ፡በነቢያት፡ልብ፡ይህ፡የሚኾነው፡እስከ፡መ ቼ፡ነው፧
27፤አባቶቻቸው፡ስለ፡በዓል፡ስሜን፡እንደ፡ረሱ፥እያንዳንዱ፡ለባልንጀራው፡በሚናገራት፡ሕልማቸው፡ሕዝቤ፡ስሜ ን፡ለማስረሳት፡ያስባሉ።
28፤የሚያልም፡ነቢይ፡ሕልምን፡ይናገር፤ቃሌም፡ያለበት፡ቃሌን፡በእውነት፡ይናገር።ገለባ፡ከስንዴ፡ጋራ፡ምን፡ አለው፧
29፤በእውኑ፡ቃሌ፡እንደ፡እሳት፥ድንጋዩንም፡እንደሚያደቅ፟፡መዶሻ፡አይደለችምን፧ይላል፡እግዚአብሔር።
30፤ስለዚህ፥እንሆ፥እያንዳንዱ፡ከባልንጀራው፡ዘንድ፡ቃሌን፡በሚሰርቁ፡ነቢያት፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔ ር።
31፤እንሆ፥ከምላሳቸው፡ትንቢትን፡አውጥተው።ርሱ፡ይላል፡በሚሉ፡ነቢያት፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
32፤እንሆ፥ሐሰትን፡በሚያልሙ፡በሚናገሩም፡በሐሰታቸውና፡በድፍረታቸውም፡ሕዝቤን፡በሚያስቱ፡በነቢያት፡ላይ፡ ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እኔም፡አልላክዃቸውም፡አላዘዝዃቸውምም፡ለእነዚህም፡ሕዝብ፡በማናቸውም፡አይረቧቸ ውም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
33፤ይህ፡ሕዝብ፡ወይም፡ነቢይ፡ወይም፡ካህን፦የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ቢጠይቅኽ፥አንተ፦ሸክ ሙ፡እናንተ፡ናችኹ፥እጥላችኹማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፡ትላቸዋለኽ።
34፤የእግዚአብሔር፡ሸክም፡የሚለውን፡ነቢይንና፡ካህንን፡ሕዝቡንም፡ያን፡ሰውና፡ቤቱን፡እቀጣለኹ።
35፤አንዱም፡አንዱ፡ለባልንጀራው፥አንዱም፡አንዱ፡ለወንድሙ፡እንዲህ፡ይበል፦እግዚአብሔር፡የመለሰው፡ምንድር ፡ነው፧እግዚአብሔርስ፡ምን፡ነገር፡ተናገረ፧
36፤ለሰው፡ዅሉ፡ቃል፡ሸክም፡ይኾንበታልና፥የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ይኾንበታልና፥የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ብላች ኹ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አትጥሩ፤የሰራዊትን፡ጌታ፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡የሕያውን፡አምላክ፡ቃል፡ ለውጣችዃልና።
37፤ለነቢዩ፦እግዚአብሔር፡ምን፡መለሰልኽ፧እግዚአብሔርስ፡የተናገረው፡ምንድር፡ነው፧ትላለኽ።
38፤ነገር፡ግን፦የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ብትሉ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፦የእግዚአብሔር፡ሸክም፡አት በሉ፡ብዬ፡ልኬባችዃለኹና፥እናንተም፡ይህን፡ቃል፦
39፤የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ብላችዃልና፥ስለዚህ፥እንሆ፥ፈጽሜ፡እረሳችዃለኹ፥እናንተንም፡ለእናንተና፡ለአባቶ ቻችኹም፡የሰጠዃትን፡ከተማ፡ከፊቴ፡እጥላለኹ።
40፤የዘለዓለምንም፡ስድብ፡ከቶም፡ተረስቶ፡የማይጠፋውን፡የዘለዓለምን፡ዕፍረት፡አመጣባችዃለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24፤
1፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የኢዮአቄምን፡ልጅ፡ኢኮንያንን፡የይሁዳንም፡አለቃዎች፡ጠ ራቢዎችንና፡ብረት፡ሠራተኛዎችን፡ከኢየሩሳሌም፡ማርኮ፡ወደ፡ባቢሎን፡ካፈለሳቸው፡በዃላ፥እግዚአብሔር፡አሳየ ኝ፥እንሆም፥በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ፊት፡ኹለት፡ቅርጫት፡በለስ፡ተቀምጠው፡ነበር።
2፤በአንደኛዪቱ፡ቅርጫት፡አስቀድሞ፡እንደ፡ደረሰ፡በለስ፡የሚመስል፡እጅግ፡መልካም፡በለስ፡ነበረባት፤በኹለተ ኛዪቱ፡ቅርጫት፡ከክፋቱ፡የተነሣ፡ይበላ፡ዘንድ፡የማይቻል፡እጅግ፡ክፉ፡በለስ፡ነበረባት።
3፤እግዚአብሔርም፦ኤርምያስ፡ሆይ፥የምታየው፡ምንድር፡ነው፧አለኝ።እኔም፦በለስን፡አያለኹ፤እጅግ፡መልካም፡የ ኾነ፡መልካም፡በለስ፥ከክፋቱም፡የተነሣ፡ይበላ፡ዘንድ፡የማይቻል፡እጅግ፡ክፉ፡የኾነ፡ክፉ፡በለስ፡ነው፡አልኹ ።
4፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
5፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንደዚህ፡እንደ፡መልካሙ፡በለስ፥እንዲሁ፡ከዚህ፡ስፍራ ፡ወደከለዳውያን፡ምድር፡የሰደድኹትን፡የይሁዳን፡ምርኮ፡ለበጎነት፡እመለከተዋለኹ።
6፤ዐይኔንም፡ለበጎነት፡በእነርሱ፡ላይ፡አደርጋለኹ፡ወደዚችም፡ምድር፡እመልሳቸዋለኹ፤እሠራቸዋለኹ፡እንጂ፡አ ላፈርሳቸውም፤እተክላቸዋለኹ፡እንጂ፡አልነቅላቸውም።
7፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡የሚያውቅ፡ልብ፡እሰጣቸዋለኹ፤በፍጹምም፡ልባቸው፡ወደ፡እኔ፡ይመለሳሉና ፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።
8፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ከክፋቱ፡የተነሣ፡ይበላ፡ዘንድ፡እንደማይቻል፡እንደ፡ክፉው፡በለስ፥እንዲሁ ፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስን፡አለቃዎቹንም፡በዚችም፡አገር፡የሚቀሩትን፡የኢየሩሳሌም፡ቅሬታ፡በግብጽም፡አ ገር፡የሚቀመጡትን፡እጥላቸዋለኹ።
9፤በማሳድዳቸውም፡ስፍራ፡ዅሉ፡ለስድብና፡ለምሳሌ፡ለማላገጫና፡ለርግማን፡ይኾኑ፡ዘንድ፡በምድር፡መንግሥታት፡ ዅሉ፡ለመበተን፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ።
10፤ለእነርሱና፡ለአባቶቻቸውም፡ከሰጠዃቸው፡ምድር፡እስኪጠፉ፡ድረስ፡በመካከላቸው፡ሰይፍንና፡ራብን፡ቸነፈር ንም፡እሰዳ፟ለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25፤
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፥በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡በመዠመ ሪያው፡ዓመት፥ስለይሁዳ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው።
2፤ይህንም፡ቃል፡ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ለይሁዳ፡ሕዝብ፡ዅሉና፡በኢየሩሳሌም፡ለተቀመጡ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረ ው፦
3፤ከይሁዳ፡ንጉሥ፡ከዓሞጽ፡ልጅ፡ከኢዮስያስ፡ከዐሥራ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ባሉት፡በእ ነዚህ፡በኻያ፡ሦስቱ፡ዓመታት፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡መጣ፥እኔም፡ማልጄ፡ተነሥቼ፡ተናገርዃችኹ፤ነገ ር፡ግን፥አልሰማችኹም።
4፤እግዚአብሔርም፡ማልዶ፡ተነሥቶ፡ባሪያዎቹን፡ነቢያትን፡ወደ፡እናንተ፡ላከ፤እናንተም፡አላደመጣችኹም፡ዦሯች ኹንም፡አላዘነበላችኹም።
5፤ርሱም፦ዅላችኹ፡እናንተ፡ከክፉ፡መንገዳችኹና፡ከሥራችኹ፡ክፋት፡ተመለሱ፤እግዚአብሔርም፡ከዘለዓለም፡ወደ፡ ዘለዓለም፡ለእናንተና፡ለአባቶቻችኹ፡በሰጣችኹ፡ምድር፡ተቀመጡ።
6፤ታመልኳቸውም፡ትሰግዱላቸውም፡ዘንድ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡አትከተሉ፥ክፉም፡እንዳላደርግባችኹ፡በእጃችኹ፡ ሥራ፡አታስቈጡኝ፡አለ።
7፤ለእናንተ፡ጕዳት፡እንዲኾን፡በእጃችኹ፡ሥራ፡ታስቈጡኝ፡ዘንድ፡አልሰማችኹኝም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
8፤ስለዚህ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ቃሌን፡አልሰማችኹምና፥እንሆ፥
9፤ልኬ፡የሰሜንን፡ወገኖች፡ዅሉ፡ባሪያዬንም፡የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾርን፡እወስዳለኹ፥በዚችም፡ምድር፡ በሚቀመጡባትም፡ሰዎች፡በዙሪያዋም፡ባሉ፡በእነዚህ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡አመጣቸዋለኹ፤ፈጽሜም፡አጠፋቸዋለኹ፥ ለመደነቂያና፡ለማፏጫም፡ለዘለዓለምም፡ባድማ፡አደርጋቸዋለኹ።
10፤ከነርሱም፡የእልልታን፡ድምፅና፡የደስታን፡ድምፅ፥የወንድ፡ሙሽራን፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራን፡ድምፅ፥የወፍ ጮንም፡ድምፅ፡የመብራትንም፡ብርሃን፡አስቀራለኹ።
11፤ይህችም፡ምድር፡ዅሉ፡ባድማና፡መደነቂያ፡ትኾናለች፤እነዚህም፡አሕዛብ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰባ፡ዓመት፡ይገ ዛሉ።
12፤ሰባው፡ዓመትም፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥የባቢሎንን፡ንጉሥና፡ያንን፡ሕዝብ፡ስለ፡ኀጢአታቸው፡እቀጣለኹ፥ይላል፡እ ግዚአብሔር፥የከለዳውያንንም፡ምድር፡ለዘለዓለም፡ባድማ፡አደርጋታለኹ።
13፤በርሷም፡ላይ፡የተናገርኹትን፡ቃሌን፡ዅሉ፥ማለት፡ኤርምያስ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡ትንቢት፡የተናገረውን፡ በዚች፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡ዅሉ፥በዚያች፡ምድር፡አመጣለኹ።
14፤ብዙ፡አሕዛብና፡ታላላቆች፡ነገሥታት፡እነርሱን፡ያስገዟቸዋል፤እኔም፡እንደ፡አደራረጋቸውና፡እንደ፡እጃቸ ው፡ሥራ፡እከፍላቸዋለኹ።
15፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦የዚህን፡ቍጣ፡የወይን፡ጠጅ፡ጽዋ፡ከእጄ፡ውሰድ፡አን ተንም፡የምሰድ፟ባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡አጠጣቸው።
16፤ከምሰድ፟ባቸውም፡ሰይፍ፡የተነሣ፡ይጠጣሉ፡ይወላገዱማል፡ያብዳሉም።
17፤ከእግዚአብሔርም፡እጅ፡ጽዋውን፡ወሰድኹ፥እግዚአብሔርም፡እኔን፡የሰደደባቸውን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡አጠጣዃቸው ።
18፤ዛሬ፡እንደኾነው፡ዅሉ፡ባድማና፡መደነቂያ፡ማፏጫም፡ርግማንም፡ኣደርጋቸው፡ዘንድ፡ኢየሩሳሌምንና፡የይሁዳ ን፡ከተማዎች፡ነገሥታቷንም፡አለቃዎቿንም፡አጠጣዃቸው።
19፤የግብጽንም፡ንጉሥ፡ፈርዖንን፡ባሪያዎቹንም፡አለቃዎቹንም፡ሕዝቡንም፡ዅሉ፥
20፤የተደባለቀውንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፥የዖፅ፡ምድር፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥የፍልስጥኤም፡ምድር፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፡ አስቀሎናንም፡ጋዛንም፡ዐቃሮንንም፡የአዞጦንንም፡ቅሬታ፥
21፤ኤዶምያስንም፥ሞዐብንም፥የዐሞንም፡ልጆች፥
22፤የጤሮስን፡ነገሥታትም፡ዅሉ፥የሲዶናን፡ነገሥታት፡ዅሉ፥በባሕር፡ማዶ፡ያለች፡የደሴት፡ነገሥታትንም፥
23፤ድዳንንም፥ቴማንንም፥ቡዝንም፥ጠጕራቸውንም፡የሚቈርጡትን፡ዅሉ፥
24፤የዐረብ፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥በምድረ፡በዳ፡የሚቀመጡ፡የድብልቅ፡ሕዝብ፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥
25፤የዘምሪ፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥የዔላም፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥
26፤የሜዶን፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥የቀረቡና፡የራቁ፥አንዱ፡ከሌላው፡ጋራ፡ያሉ፡የሰሜን፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥በም ድር፡ፊት፡ላይ፡ያሉ፡የዓለም፡መንግሥታትንም፡ዅሉ፡አጠጣዃቸው፤የሼሻክም፡ንጉሥ፡ከነርሱ፡በዃላ፡ይጠጣል።
27፤አንተም፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመካከላችኹ፡ከምሰደ፟ው፡ሰ ይፍ፡የተነሣ፡ጠጡ፥ስከሩም፥አስታውኩም፡ውደቁም፥ከእንግዲህም፡ወዲህ፡አትነሡም፡በላቸው።
28፤ይጠጡም፡ዘንድ፡ጽዋውን፡ከእጅኽ፡ለመቀበል፡እንቢ፡ቢሉ፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ፈ ጽማችኹ፡ትጠጣላችኹ፡በላቸው።
29፤እንሆ፥ስሜ፡የተጠራባትን፡ከተማ፡አስጨንቃት፡ዘንድ፡እዠምራለኹ፤በእውኑ፡እናንተ፡ያልተቀጣችኹ፡ትኾናላ ችኹን፧በምድር፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ሰይፍን፡እጠራለኹና፡ያለቅጣት፡አትቀሩም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአ ብሔር።
30፤ስለዚህ፥ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ትንቢት፡ትናገርባቸዋለኽ፥እንዲህም፡ትላቸዋለኽ፦እግዚአብሔር፡በላይ፡ኾኖ፡ይ ጮኻል፥በቅዱስ፡ማደሪያውም፡ኾኖ፡ድምፁን፡ያሰማል፤በበረቱ፡ላይ፡እጅግ፡ይጮኻል፥ወይንም፡እንደሚጠምቁ፡በም ድር፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ይጮኻል።
31፤እግዚአብሔር፡ከአሕዛብ፡ጋራ፡ክርክር፡አለውና፡ድምፅ፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ይደርሳል፤ከሥጋ፡ለባሽ ፡ዅሉ፡ጋራ፡ይፋረዳል፥ኀጢአተኛዎችንም፡ለሰይፍ፡አሳልፎ፡ይሰጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
32፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ክፉ፡ነገር፡ከሕዝብ፡ወደ፡ሕዝብ፡ይወጣል፥ጽኑም፡ዐ ውሎ፡ነፍስ፡ከምድር፡ዳርቻ፡ይነሣል።
33፤በዚያም፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ግዳዩች፡ከምድር፡ዳር፡ዠምሮ፡እስከምድር፡ዳር፡ድረስ፡ይኾናሉ፤አይለቀስላ ቸውም፤በምድር፡ላይ፡እንደ፡ጕድፍ፡ይኾናሉ፡እንጂ፡አይከማቹም፡አይቀበሩምም።
34፤ትታረዱና፡ትበተኑ፡ዘንድ፡ቀናችኹ፡ደርሷልና፥እንደ፡ተወደደም፡የሸክላ፡ዕቃ፡ትወድቃላችኹና፡እናንተ፡እ ረኛዎች፥አልቅሱ፡ጩኹም፤እናንተ፡የመንጋ፡አውራዎች፥በዐመድ፡ውስጥ፡ተንከባለሉ።
35፤ሽሽትም፡ከእረኛዎች፡ማምለጥም፡ከመንጋ፡አውራዎች፡ይጠፋል።
36፤እግዚአብሔር፡ማሰማሪያቸውን፡አጥፍቷልና፥የእረኛዎች፡ጩኸት፡ድምፅ፡የመንጋ፡አውራዎችም፡ልቅሶ፡ኾኗል።
37፤ከእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡የተነሣ፡የሰላም፡በረት፡ፈርሷል።
38፤እንደ፡አንበሳ፡መደቡን፡ለቋ፟ል፤ካስጨናቂውም፡ሰይፍና፡ከጽኑ፡ቍጣው፡የተነሣ፡ምድራቸው፡ባድማ፡ኾናለች ና።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26፤
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡ይህ፡ቃል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡መጣ።
2፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ቁም፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ውስጥ፡ይሰግዱ፡ ዘንድ፡ለሚመጡት፡ለይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ትነግራቸው፡ዘንድ፡ያዘዝኹኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ተናገራቸው፤አንዲትም፡ ቃል፡አታጕድል።
3፤ምናልባት፡ይሰሙ፥ከክፉ፡መንገዳቸውም፡ይመለሱ፡ይኾናል፤እኔም፡ስለሥራቸው፡ክፋት፡ያሰብኹባቸውን፡ክፉ፡ነ ገር፡እተዋለኹ።
4፤እንዲህም፡በላቸው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በፊታችኹ፡በሰጠዃት፡ሕጌ፡ትኼዱ፡ዘንድ፡ባትሰሙኝ፥
5፤ያልሰማችኹትን፡በማለዳ፡ተነሥቼ፡ወደ፡እናንተ፡የላክዃቸውን፡የባሪያዎቼን፡የነቢያትን፡ቃል፡ባትሰሙ፥
6፤ይህን፡ቤት፡እንደ፡ሴሎ፡አደርገዋለኹ፥ይህችንም፡ከተማ፡ለምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ርግማን፡አደርጋታለኹ።
7፤ካህናቱም፡ነቢያቱም፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ኤርምያስ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ይህን፡ቃል፡ሲናገር፡ሰሙ።
8፤ኤርምያስም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡ይናገር፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ያዘዘውን፡ነገር፡ዅሉ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ካህናትና፡ነ ቢያት፡ሕዝቡም፡ዅሉ፦ሞትን፡ትሞታለኽ።
9፤በእግዚአብሔር፡ስም፦ይህ፡ቤት፡እንደ፡ሴሎ፡ይኾናል፥ይህችም፡ከተማ፡ባድማና፡ወና፡ትኾናለች፡ብለኽ፡ስለ፡ ምን፡ትንቢት፡ተናገርኽ፧ብለው፡ያዙት።ሕዝቡም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡በኤርምያስ፡ላይ፡ተሰብስበ ው፡ነበር።
10፤የይሁዳም፡አለቃዎች፡ይህን፡በሰሙ፡ጊዜ፡ከንጉሥ፡ቤት፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወጡ፥በዐዲሱም፡በእግዚአብ ሔር፡ቤት፡ደጅ፡መግቢያ፡ተቀመጡ።
11፤ካህናቱና፡ነቢያቱም፡ለአለቃዎቹና፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፦በዦሯችኹ፡እንደ፡ሰማችኹ፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡ትንቢት፡ ተናግሯልና፥ይህ፡ሰው፡ሞት፡የሚገ፟ባ፟ው፡ነው፡ብለው፡ተናገሩ።
12፤ኤርምያስም፡ለአለቃዎችና፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦በሰማችኹት፡ቃል፡ዅሉ፡በዚች፡ቤትና፡በዚ ች፡ከተማ፡ላይ፡ትንቢት፡እናገር፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ልኮኛል።
13፤አኹንም፡መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡አሳምሩ፥የአምላካችኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤እግዚአብሔርም ፡የተናገረባችኹን፡ክፉ፡ነገር፡ይተዋል።
14፤እኔ፡ግን፥እንሆ፥በእጃችኹ፡ነኝ፤በዐይናችኹ፡መልካምና፡ቅን፡የመሰለውን፡አድርጉብኝ።
15፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡በዦሯችኹ፡እናገር፡ዘንድ፡በእውነት፡እግዚአብሔር፡ወደ፡እናንተ፡ልኮኛልና ፥ብትገድሉኝ፡ንጹሕ፡ደምን፡በራሳችኹና፡በዚች፡ከተማ፡በሚኖሩባትም፡ላይ፡እንድታመጡ፡በርግጥ፡ዕወቁ።
16፤አለቃዎቹና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ለካህናትና፡ለነቢያት፦ይህ፡ሰው፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ተናግሮና ልና፥ሞት፡አይገ፟ባ፟ውም፡አሉ።
17፤ከአገሩ፡ሽማግሌዎችም፡ሰዎች፡ተነሥተው፡ለሕዝቡ፡ጉባኤ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ብለው፡ተናገሩ።
18፤ሞሬታዊው፡ሚክያስ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሕዝቅያስ፡ዘመን፡ነቢይ፡ነበረ፤ለይሁዳም፡ሕዝብ፡ዅሉ፦የሰራዊት፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጽዮን፡እንደ፡ዕርሻ፡ትታረሳለች፥ኢየሩሳሌም፡የፍርስራሽ፡ክምር፡ትኾናለች ፥የቤቱም፡ተራራ፡እንደ፡ዱር፡ከፍታ፡ይኾናል፡ብሎ፡ተናገረ።
19፤በእውኑ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ገደሉትን፧በእውኑ፡እግዚአብሔርን፡አልፈሩምን፧ወደ፡እ ግዚአብሔርስ፡አልተማለሉምን፧እግዚአብሔርስ፡የተናገረባቸውን፡ክፉ፡ነገር፡አይተውምን፧እኛም፡በነፍሳችን፡ ላይ፡ታላቅ፡ክፋት፡እናደርጋለን።
20፤ደግሞም፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ትንቢት፡የተናገረ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፤ርሱም፡የቂርያትይዓሪም፡ሰው፥የሸማ ያ፡ልጅ፥ኦርዮ፡ይባል፡ነበር፤በዚችም፡ከተማ፡በዚችም፡ምድር፡ላይ፡እንደ፡ኤርምያስ፡ቃል፡ዅሉ፡ትንቢት፡ተና ገረ።
21፤ንጉሡም፡ኢዮአቄም፡ኀያላኑም፡ዅሉ፡አለቃዎቹም፡ዅሉ፡ቃሉን፡በሰሙ፡ጊዜ፡ንጉሡ፡ሊገድለው፡ፈለገ፤ኦርዮም ፡ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፡ፈርቶ፡ሸሸ፡ወደ፡ግብጽም፡ገባ።
22፤ንጉሡም፡ኢዮአቄም፡የዓክቦርን፡ልጅ፡ኤልናታንን፡ከርሱም፡ጋራ፡ሌላዎችን፡ሰዎች፡ወደ፡ግብጽ፡ላካቸው፤
23፤ከግብጽም፡ኦርዮን፡አውጥተው፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ኢዮአቄም፡ይዘውት፡መጡ፤ርሱም፡በሰይፍ፡ገደለው፡ሬሳውን ም፡ክቡራን፡ባልኾኑ፡ሰዎች፡መቃብር፡ጣለው።
24፤ነገር፡ግን፥በሕዝቡ፡እጅ፡እንዳይሰጥና፡እንዳይገድሉት፡የሳፋን፡ልጅ፡የአኪቃም፡እጅ፡ከኤርምያስ፡ጋራ፡ ነበረች።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27፤
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡ይህ፡ቃል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ ኤርምያስ፡መጣ።
2፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦እስራትና፡ቀንበር፡ሥራ፡በዐንገትኽም፡ላይ፡አድርግ፤
3፤ወደይሁዳ፡ንጉሥም፡ወደ፡ሴዴቅያስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በመጡት፡መልእክተኛዎች፡እጅ፡ወደኤዶምያስ፡ንጉሥ፡ወ ደሞዐብም፡ንጉሥ፡ወደዐሞንም፡ልጆች፡ንጉሥ፡ወደጢሮስም፡ንጉሥ፡ወደሲዶናም፡ንጉሥ፡ላካቸው።
4፤ለጌታዎቻቸውም፡እንዲነግሩ፡እንዲህ፡ብለኽ፡እዘዛቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦ለጌታዎቻችኹ፡እንዲህ፡በሉ።
5፤ምድሪቱን፡በምድርም፡ፊት፡ላይ፡ያሉትን፡ሰዎችንና፡እንስሳዎችን፡በታላቅ፡ኀይሌና፡በተዘረጋችው፡ክንዴ፡ፈ ጥሬያለኹ፤ለዐይኔም፡መልካም፡ለኾነው፡እሰጣታለኹ።
6፤አኹንም፡እነዚህን፡ምድሮች፡ዅሉ፡ለባሪያዬ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጥቻለኹ፤ይገ ዙለትም፡ዘንድ፡የምድረ፡በዳ፡አራዊትን፡ደግሞ፡ሰጥቼዋለኹ።
7፤የገዛ፡ራሱም፡ምድር፡ጊዜ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ለርሱና፡ለልጅ፡ለልጅ፡ልጁም፡ይገዛሉ፤በዚያን፡ ጊዜም፡ብዙ፡አሕዛብና፡ታላላቆች፡ነገሥታት፡ርሱን፡ያስገዙታል።
8፤ለባቢሎን፡ንጉሥም፡ለናቡከደነጾር፡የማይገዛውን፥ከባቢሎንም፡ንጉሥ፡ቀንበር፡በታች፡ዐንገቱን፡ዝቅ፡የማያ ደርገውን፡ሕዝብና፡መንግሥት፥ያን፡ሕዝብ፡በእጁ፡እስካጠፋው፡ድረስ፥በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡እቀጣለኹ ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
9፤እናንተ፡ግን፦ለባቢሎን፡ንጉሥ፡አትገዙም፡የሚሏችኹን፡ነቢያታችኹንና፡ሟርተኛዎቻችኹን፥ሕልም፡ዐላሚዎቻች ኹንና፡ቃላ፟ተኛዎቻችኹን፡መተተኛዎቻችኹንም፡አትስሙ፤
10፤ከምድራችኹ፡እንዲያርቋችኹ፥እኔም፡እንዳሳድዳችኹ፡እናንተም፡እንድትጠፉ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ይናገሩላች ዃልና።
11፤ነገር፡ግን፥ከባቢሎን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡በታች፡ዐንገቱን፡ዝቅ፡የሚያደርገውንና፡የሚገዛለትን፡ሕዝብ፡በአ ገሩ፡ላይ፡እተወዋለኹ፤እነርሱም፡ያርሷታል፡ይቀመጡባትማል።
12፤ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሴዴቅያስም፡በዚህ፡ቃል፡ተናገርኹ፦ከባቢሎን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡በታች፡ዐንገታችኹን፡ዝቅ ፡አድርጉ፥ለርሱና፡ለሕዝቡም፡ተገዙላቸው፥በሕይወትም፡ኑሩ።
13፤ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ይገዛ፡ዘንድ፡እንቢ፡ስለ፡አለ፡ሕዝብ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገረ፥አንተና፡ሕዝብኽ፡ በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ለምን፡ትሞታላችኹ፧
14፤ሐሰተኛን፡ትንቢት፡ይናገሩላችዃልና።ለባቢሎን፡ንጉሥ፡አትገዙም፡የሚሏችኹን፡የነቢያትን፡ቃል፡አትስሙ።
15፤እኔ፡አልላክዃቸውምና፤ነገር፡ግን፥እኔ፡እንዳሳድዳችኹ፥እናንተና፡ትንቢት፡የሚናገሩላችኹ፡ነቢያትም፡እ ንድትጠፉ፡በስሜ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ይናገራሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
16፤ለካህናትም፡ለዚህም፡ሕዝብ፡እንዲህ፡ብዬ፡ተናገርኹ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሐሰተኛውን፡ትንቢት፡ ይናገሩላችዃልና፦የእግዚአብሔር፡ቤት፡ዕቃ፡በቅርብ፡ጊዜ፡ከባቢሎን፡ይመለሳል፡የሚሏችኹን፡የነቢያታችኹን፡ ቃል፡አትስሙ።
17፤እነርሱም፡አትስሙ፤ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ተገዙ፡በሕይወትም፡ኑሩ።ይህችስ፡ከተማ፡ስለ፡ምን፡ባድማ፡ትኾናለች ፧
18፤እነርሱ፡ግን፡ነቢያት፡ቢኾኑ፥የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በእነርሱ፡ዘንድ፡ቢገኝ፥በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በይ ሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡በኢየሩሳሌምም፡የቀረችው፡ዕቃ፡ወደ፡ባቢሎን፡እንዳትኼድ፡ወደሰራዊት፡ጌታ፡ወደ፡እግዚአብ ሔር፡ይማለሉ።
19-20፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የኢዮአቄምን፡ልጅ፡ኢኮንያንንና፡የይሁዳንና፡የኢየሩ ሳሌምን፡ከበርቴዎች፡ዅሉ፡ማርኮ፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ባፈለሳቸው፡ጊዜ፡ስላልወሰዳቸው፡ዐምዶች፡ስለ ፡ኵሬውም፡ስለ፡መቀመጫዎቹም፡በዚችም፡ከተማ፡ስለቀረች፡ዕቃ፡ዅሉ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይ ላልና፤
21፤በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡በኢየሩሳሌምም፡ስለቀረችው፡ዕቃ፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራ ዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
22፤ወደ፡ባቢሎን፡ትወሰዳለች፡እስከምጐበኛትም፡ቀን፡ድረስ፡በዚያ፡ትኖራለች፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በዚያን፡ ጊዜም፡አወጣታለኹ፡ወደዚህም፡ስፍራ፡እመልሳታለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28፤
1፤በዚያም፡ዓመት፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡በአራተኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ነ ቢዩ፡የገባዖን፡ሰው፡የዓዙር፡ልጅ፡ሐናንያ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በካህናትና፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፡እንዲህ፡ብ ሎ፡ተናገረኝ።
2፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ይናገራል።የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡ሰ ብሬያለኹ።
3፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ከዚች፡ስፍራ፡ወደ፡ባቢሎን፡የወሰዳትን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዕቃ፡ዅሉ፡ በኹለት፡ዓመት፡ውስጥ፡ወደዚች፡ስፍራ፡እመልሳታለኹ፤
4፤ወደ፡ባቢሎንም፡የኼዱትን፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የኢዮአቄምን፡ልጅ፡ኢኮንያንንና፡የይሁዳን፡ምርኮ፡ዅሉ፡ወደዚ ች፡ስፍራ፡እመልሳቸዋለኹ፤የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡እሰብራለኹና።
5፤ነቢዩ፡ኤርምያስም፡በካህናቱና፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በቆሙት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፡ለነቢዩ፡ለሐናንያ፡ተናገረ ።
6፤ነቢዩም፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡አለ፦አሜን፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ያድርግ፤የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዕቃ፡ምርኮ ውንም፡ዅሉ፡ከባቢሎን፡ወደዚህ፡ስፍራ፡በመመለስ፡እግዚአብሔር፡የተናገርኸውን፡ትንቢት፡ይፈጽም።
7፤ነገር፡ግን፥በዦሮኽና፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ዦሮ፡የምናገረውን፡ይህን፡ቃል፡ስማ፤
8፤ከጥንት፡ከእኔና፡ከአንተ፡በፊት፡የነበሩ፡ነቢያት፡በብዙ፡አገርና፡በታላላቅ፡መንግሥታት፡ላይ፡ስለ፡ሰልፍ ና፡ስለ፡ክፉ፡ነገር፡ስለ፡ቸነፈርም፡ትንቢት፡ተናገሩ።
9፤ስለ፡ሰላም፡የተናገረ፡ነቢይ፥የነቢዩ፡ቃል፡በኾነ፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡በእውነት፡የሰደደው፡ነቢይ፡እንደ፡ ኾነ፡ይታወቃል።
10፤ነቢዩም፡ሐናንያ፡ቀንበሩን፡ከነቢዩ፡ከኤርምያስ፡ዐንገት፡ወስዶ፡ሰበረው።
11፤ሐናንያም፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲሁ፡በኹለት፡ዓመት፡ውስጥ፡የባቢሎንን፡ ንጉሥ፡የናቡከደነጾርን፡ቀንበር፡ከአሕዛብ፡ዅሉ፡ዐንገት፡እሰብራለኹ፡አለ።ነቢዩም፡ኤርምያስ፡መንገዱን፡ኼ ደ።
12፤ነቢዩም፡ሐናንያ፡ቀንበሩን፡ከነቢዩ፡ከኤርምያስ፡ዐንገት፡ከሰበረ፡በዃላ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ኤር ምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
13፤ኺድ፥ለሐናንያ፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገረው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አንተ፡የዕንጨትን፡ቀንበር፡ሰብረ ኻል፥እኔ፡ግን፡በርሱ፡ፋንታ፡የብረትን፡ቀንበር፡እሠራለኹ።
14፤የእስራኤልም፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡ ይገዙለት፡ዘንድ፡የብረትን፡ቀንበር፡በእነዚህ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ዐንገት፡ላይ፡አድርጌያለኹ፤እነርሱም፡ይገዙለ ታል፥የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ደግሞ፡ሰጥቼዋለኹ።
15፤ነቢዩም፡ኤርምያስ፡ነቢዩን፡ሐናንያን፦ሐናንያ፡ሆይ፥ስማ፤ይህ፡ሕዝብ፡በሐሰት፡እንዲታመን፡አድርገኻል፡ እንጂ፡እግዚአብሔር፡አላ፟ከኽም።
16፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከምድር፡ላይ፡እሰድ፟ኻለኹ፤በእግዚአብሔር፡ላይ፡ዐመፅን፡ ተናግረኻልና፥በዚህ፡ዓመት፡ትሞታለኽ፡አለው።
17፤ነቢዩም፡ሐናንያ፡በዚያው፡ዓመት፡በሰባተኛው፡ወር፡ሞተ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29፤
1፤ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ወደተረፉት፡የምርኮ፡ሽማግሌዎች፥ወደ፡ካህናቱም፥ወደ፡ነቢያቱም፥ናቡከደነጾር፡ከኢየሩሳ ሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ማርኮ፡ወዳፈለሰውም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ከኢየሩሳሌም፡የላከው፡የደብዳቤው፡ቃል፡ይህ፡ነው።
2፤ይህም፡የኾነው፡ንጉሡ፡ኢኮንያን፣እናቱም፡እቴጌዪቱ፣ጃን፡ደረባዎቹም፣የይሁዳና፡የኢየሩሳሌምም፡አለቃዎች ፣ጠራቢዎችና፡ብረት፡ሠራተኛዎችም፡ከኢየሩሳሌም፡ከወጡ፡በዃላ፡ነው።
3፤ኤርምያስ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡ወደ፡ባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ናቡከደነጾር፡ወደ፡ባቢሎን፡በላካቸው፡በሳ ፋን፡ልጅ፡በኤልዓሣና፡በኬልቅያስ፡ልጅ፡በገማርያ፡እጅ፡ደብዳቤውን፡እንዲህ፡ሲል፡ላከው።
4፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ላስማረክዃቸው፡ምርኮኛዎች ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ይላል፦
5፤ቤት፡ሠርታችኹ፡ተቀመጡ፥አታክልትም፡ተክላችኹ፡ፍሬዋን፡ብሉ፤
6፤ተጋቡ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ውለዱ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችኹንም፡አጋቡ፥እነርሱም፡ወንዶችንና፡ሴ ቶችን፡ልጆች፡ይውለዱ፤ከዚያም፡ተባዙ፡ጥቂቶችም፡አትኹኑ።
7፤በርሷ፡ሰላም፡ሰላም፡ይኾንላችዃልና፥ወደ፡ርሷ፡ላስማርክዃችኹ፡ከተማ፡ሰላምን፡ፈልጉ፥ስለ፡ርሷም፡ወደ፡እ ግዚአብሔር፡ጸልዩ።
8፤የእስራኤልም፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በመካከላችኹ፡ያሉት፡ነቢያታችኹና፡ ሟርተኛዎቻችኹ፡አያታሏ፟ችኹ፥እናንተም፡የምታልሙትን፡ሕልም፡አትስሙ።
9፤በስሜ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ይናገሩላችዃልና፤እኔም፡አላ፟ክዃቸውም።
10፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ሰባው፡ዓመት፡በባቢሎን፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡እጐበኛችዃለኹ፥ወደዚህም፡ስፍራ ፡እመልሳችኹ፡ዘንድ፡መልካሚቱን፡ቃሌን፡እፈጽምላችዃለኹ።
11፤ለእናንተ፡የማስባትን፡ዐሳብ፡እኔ፡ዐውቃለኹ፤ፍጻሜና፡ተስፋ፡እሰጣችኹ፡ዘንድ፡የሰላም፡ዐሳብ፡ነው፡እን ጂ፡የክፉ፡ነገር፡አይደለም።
12፤እናንተም፡ትጠሩኛላችኹ፥ኼዳችኹም፡ወደ፡እኔ፡ትጸልያላችኹ፥እኔም፡እሰማችዃለኹ።
13፤እናንተ፡ትሹኛላችኹ፥በፍጹም፡ልባችኹም፡ከሻችኹኝ፡ታገኙኛላችኹ።
14፤ከእናንተም፡ዘንድ፡እገኛለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ምርኳችኹንም፡እመልሳለኹ፥ከአሕዛብም፡ዅሉ፡ዘንድ፡እ ናንተንም፡ካሳደድኹበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡እሰበስባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እናንተንም፡ለምርኮ፡ወዳፈለስኹ በት፡ስፍራ፡እመልሳችዃለኹ።
15፤እናንተም፦እግዚአብሔር፡በባቢሎን፡ነቢያትን፡አስነሥቶልናል፡ብላችዃልና፤
16፤እግዚአብሔር፡በዳዊት፡ዙፋን፡ስለተቀመጠ፡ንጉሥ፡ከእናንተም፡ጋራ፡ስላልተማረኩት፡ወንድሞቻችኹ፥በዚች፡ ከተማ፡ስለሚኖሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፥እንዲህ፡ይላልና፦
17፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሰይፍንና፡ራብን፡ቸነፈርንም፡እሰድ፟ባቸዋለኹ፥ከክ ፋቱም፡የተነሣ፡ይበላ፡ዘንድ፡እንደማይቻል፡እንደ፡ክፉ፡በለስ፡አደርጋቸዋለኹ።
18፤በሰይፍም፡በራብም፡በቸነፈርም፡አሳዳድዳቸዋለኹ፥ባሳደድኹባቸውም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ዘንድ፡ለጥላቻና፡ለመደ ነቂያ፡ለማፏጫም፡ለመሰደቢያም፡እንዲኾኑ፡በምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ዘንድ፡ለመበተን፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ ።
19፤ይህም፡የኾነው፡ቃሌን፡ስላልሰሙ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በማለዳ፡ተነሥቼ፡ባሪያዎቼን፡ነቢያትን፡ወደ ፡እነርሱ፡ሰድጃለኹና፤እናንተ፡ግን፡አልሰማችኹም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
20፤ስለዚህ፥ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡የሰደድዃችኹ፡ምርኮኛዎች፡ዅሉ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
21፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በስሜ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ስለሚናገሩላችኹ፡ስለቆላያ ፡ልጅ፡ስለ፡አክአብና፡ስለመዕሴያ፡ልጅ፡ስለ፡ሴዴቅያስ፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነ ጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፥በዐይኖቻችኹም፡ፊት፡ይገድላቸዋል።
22፤ከነርሱም፡የተነሣ፡በባቢሎን፡ያሉ፡የይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡ዅሉ፦የባቢሎን፡ንጉሥ፡በእሳት፡እንደ፡ጠበሳቸው ፡እንደ፡ሴዴቅያስና፡እንደ፡አክአብ፡እግዚአብሔር፡ያድርግኽ፡የምትባል፡ርግማንን፡ያነሣሉ፤እኔም፡ዐውቃለኹ ፡ምስክርም፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
23፤በእስራኤል፡ዘንድ፡ስንፍና፡አድርገዋልና፥ከባልንጀራዎቻቸውም፡ሚስቶች፡ጋራ፡አመንዝረዋልና፥ያላዘዝዃቸ ውንም፡ቃል፡በስሜ፡በሐሰት፡ተናግረዋልና።
24፤ለኔሔላማዊው፡ለሸማያ፡እንዲህ፡በል፦
25፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በኢየሩሳሌም፡ወዳለው፡ሕዝብ፡ዅሉ፥ወ ደ፡ካህኑም፡ወደመዕሴያ፡ልጅ፡ወደ፡ሶፎንያስ፥ወደ፡ካህናቱም፡ዅሉ፡ደብዳቤዎችን፡በስምኽ፡እንዲህ፡ስትል፡ል ከኻል።
26፤እያበደ፡ትንቢት፡የሚናገርን፡ሰው፡ዅሉ፡በእግር፡ግንድና፡በዛንጅር፡ታኖረው፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ቤት ፡አለቃ፡እንድትኾን፡እግዚአብሔር፡በካህኑ፡በዮዳዔ፡ፋንታ፡ካህን፡አድርጎኻል።
27፤አኹንስ፡ትንቢት፡ተናጋሪውን፡የዓናቶቱን፡ሰው፡ኤርምያስን፡ስለ፡ምን፡አትዘልፈውም፧
28፤ርሱ፦ምርኮው፡የረዘመው፡ነውና፥ቤት፡ሠርታችኹ፡ተቀመጡ፥አታክልትንም፡ተክላችኹ፡ፍሬዋን፡ብሉ፡ብሎ፡ወደ ፡እኛ፡ወደ፡ባቢሎን፡ልኳልና።
29፤ካህኑም፡ሶፎንያስ፡ይህን፡ደብዳቤ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡ዦሮ፡አነበበው።
30፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
31፤እግዚአብሔር፡ስለ፡ኔሔላማዊው፡ስለ፡ሸማያ፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ወደ፡ምርኮኛዎች፡ዅሉ፡ላክ።እኔ፡ሳል ፟ከው፡ሸማያ፡ትንቢት፡ተናግሮላችዃልና፥በሐሰትም፡እንድትታመኑ፡አድርጓችዃልና፤
32፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ኔሔላማዊውን፡ሸማያንና፡ዘሩን፡እቀጣለኹ፤እኔም፡የማደርግ ላችኹን፡መልካሙን፡ነገር፡የሚያይ፡ሰው፡በመካከላችኹ፡አይኖርላችኹም፡
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30፤
1፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የነገርኹኽን፡ቃል፡ዅሉ፡በመጽሐፍ፡ጻፍ።
3፤እንሆ፥የሕዝቤን፡የእስራኤልንና፡የይሁዳን፡ምርኮ፡የምመልስባት፡ዘመን፡ይመጣልና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ለ አባቶቻቸውም፡ወደሰጠዃት፡ምድር፡እመልሳቸዋለኹ፥እነርሱም፡ይገዟታል።
4፤እግዚአብሔር፡ስለ፡እስራኤልና፡ስለ፡ይሁዳ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
5፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦የሚያስፈራ፡ድምፅ፡ሰምተናል፤የፍርሀት፡ነው፡እንጂ፡የሰላም፡አይደለም።
6፤ጠይቁ፥ወንድ፡ይወልድ፡እንደ፡ኾነ፡ተመልከቱ፤ስለ፡ምን፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡ወላድ፡እጁን፡በወገቡ፡ላይ፡አድ ርጎ፡ፊቱም፡ዅሉ፡ወደ፡ጥቍረት፡ተለውጦ፡አየኹ፧
7፤ወዮ! ያ፡ቀን፡ታላቅ፡ነውና፥ርሱንም፡የሚመስል፡የለምና፤ያ፡የያዕቆብ፡መከራ፡ዘመን፡ነው፥ነገር፡ግን፥ከርሱ፡ይድ ናል።
8፤በዚያ፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ቀንበርን፡ከዐንገትኽ፡እሰብራለኹ፥እስ ራትኽንም፡እበጥሳለኹ፥ከእንግዲህ፡ወዲህም፡ለሌላ፡አትገዛም፤
9፤ለአምላካቸው፡ለእግዚአብሔርም፡ለማስነሣላቸው፡ለንጉሣቸው፡ለዳዊትም፡ይገዛሉ፡እንጂ፡ሌላዎች፡አሕዛብ፡እ ንደ፡ገና፡አይገዟቸውም።
10፤እንሆ፥አንተን፡ከሩቅ፡ዘርኽንም፡ከምርኮ፡አገር፡አድናለኹና፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡ሆይ፥አትፍራ፥ይላል፡እግ ዚአብሔር፥አንተም፡እስራኤል፡ሆይ፥አትደንግጥ፤ያዕቆብም፡ይመለሳል፡ያርፍማል፡ተዘልሎም፡ይቀመጣል፤ማንም፡ አያስፈራውም።
11፤አድንኽ፡ዘንድ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤አንተንም፡የበተንኹባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡ፈ ጽሜ፡አጠፋለኹ፥አንተን፡ግን፡ፈጽሜ፡አላጠፋኽም፤በመጠን፡እቀጣኻለኹ፥ያለቅጣትም፡ከቶ፡አልተውኽም።
12፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስብራትኽ፡የማይፈወስ፡ቍስልኽም፡ክፉ፡ነው።
13፤ትጠገን፡ዘንድ፡ክርክርኽን፡የሚፈርድልኽ፡የለም፥ቍስልኽንም፡የሚፈውስ፡መድኀኒት፡የለኽም።
14፤ውሽማዎችኽ፡ዅሉ፡ረስተውኻል፡አይፈልጉኽምም፤በደልኽ፡ታላቅ፡ስለ፡ኾነ፥ኀጢአትኽም፡ስለ፡በዛ፥በጠላት፡ ማቍሰልና፡በጨካኝ፡ቅጣት፡አቍስዬኻለኹና።
15፤ሕመምኽ፡የማይፈወስ፡ኾኗልና፥ስለ፡ስብራትኽ፡ለምን፡ትጮኻለኽ፧በደልኽ፡ታላቅ፡ስለ፡ኾነ፡ኀጢአትኽም፡ስ ለ፡በዛ፥ይህን፡አድርጌብኻለኹ።
16፤ስለዚህ፥የሚውጡኽ፡ዅሉ፡ይዋጣሉ፥ጠላቶችኽም፡ዅላቸው፡ይማረካሉ፤የዘረፉኽም፡ይዘረፋሉ፥የበዘበዙኽንም፡ ዅሉ፡ለመበዝበዝ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
17፤እኔ፡ጤናኽን፡እመልስልኻለኹ፡ቍስልኽንም፡እፈውሳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ማንም፡የማይሻት፥የተጣለች፡ ጽዮን፡ብለው፡ጠርተውሻልና።
18፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የያዕቆብን፡ድንኳን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ለማደሪያውም፡እራራለኹ፤ከ ተማዪቱም፡በጕብታዋ፡ላይ፡ትሠራለች፥አዳራሹም፡እንደ፡ዱሮው፡የሰው፡መኖሪያ፡ይኾናል።
19፤ከርሱም፡ዘንድ፡የምስጋናና፡የዘፋኞች፡ድምፅ፡ይወጣል፤እኔም፡አበዛቸዋለኹ፡አያንሱምም፥እኔም፡አከብራቸ ዋለኹ፡ታናሽም፡አይኾኑም።
20፤ልጆቻቸውም፡እንደ፡ቀድሞ፡ይኾናሉ፥ማኅበራቸውም፡በፊቴ፡ጸንቶ፡ይኖራል፤የሚያስጨንቋቸውንም፡ዅሉ፡እቀጣ ለኹ።
21፤አለቃቸው፡ከነርሱ፡ውስጥ፡ይኾናል፥ገዣቸውም፡ከመካከላቸው፡ይወጣል፤እኔ፡አቀርበዋለኹ፡ርሱም፡ይቀርባል ፤ይህስ፡ባይኾን፡ወደ፡እኔ፡ለመቅረብ፡የሚደፍር፡ማን፡ነው፧ይላል፡እግዚአብሔር።
22፤እናንተም፡ሕዝብ፡ትኾኑኛላችኹ፡እኔም፡አምላክ፡እኾናችዃለኹ።
23፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ዐውሎ፡ነፋስ፥ርሱም፡ቍጣው፥የሚያገለባብጥ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ወጥቷል፤የዐመፀኛዎችን ም፡ራስ፡ይገለባብጣል።
24፤የእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡የልቡን፡ዐሳብ፡ሠርቶ፡እስኪፈጽም፡ድረስ፡አይመለስም፡በዃለኛው፡ዘመን፡ታስተ ውሉታላችኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31፤
1፤በዚያን፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ለእስራኤል፡ወገኖች፡ዅሉ፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡እነርሱም፡ሕዝብ፡ይ ኾኑኛል።
2፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤል፡ማረፊያ፡ሊሻ፡በኼደ፡ጊዜ፡ከሰይፍ፡የተረፈው፡ሕዝብ፡በምድረ፡በዳ ፡ሞገስ፡አገኘ።
3፤እግዚአብሔርም፡ከሩቅ፡ተገለጠልኝ፡እንዲህም፡አለኝ፦በዘለዓለም፡ፍቅር፡ወድጄሻለኹ፤ስለዚህ፥በቸርነት፡ሳ ብኹሽ።
4፤የእስራኤል፡ድንግል፡ሆይ፥እንደ፡ገና፡እሠራሻለኹ፡አንቺም፡ትሠሪያለሽ፤እንደ፡ገናም፡ከበሮሽን፡አንሥተሽ ፡ከዘፋኞች፡ጋራ፡ወደ፡ዘፈን፡ትወጫለሽ።
5፤እንደ፡ገናም፡በሰማርያ፡ተራራዎች፡ላይ፡የወይን፡ቦታዎችን፡ትተክሊያለሽ፤አትክልተኛዎች፡ይተክላሉ፡በፍሬ ውም፡ደስ፡ይላቸዋል።
6፤በኤፍሬምም፡ተራራዎች፡ላይ፡ያሉ፡ጠባቂዎች፦ተነሡ፥ወደ፡ጽዮን፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንው ጣ፡ብለው፡የሚጮኹበት፡ቀን፡ይመጣልና።
7፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ስለ፡ያዕቆብ፡ደስ፡ይበላችኹ፡ስለ፡አሕዛብም፡አለቃዎች፡እልል፡በሉ፤አውሩ ፥አመስግኑ።እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡የእስራኤልን፡ቅሬታ፡አድኗል፡በሉ።
8፤እንሆ፥ከሰሜን፡አገር፡አመጣቸዋለኹ፥ከምድርም፡ዳርቻ፡እሰበስባቸዋለኹ፥በመካከላቸውም፡ዕውሩና፡ዐንካሳው ፡ያረገዘችና፡የወለደችም፡በአንድነት፤ታላቅ፡ጉባኤ፡ኾነው፡ወደዚህ፡ይመለሳሉ።
9፤በልቅሶ፡ወጡ፡እኔም፡በማጽናናት፡አመጣቸዋለኹ፤በወንዝ፡ዳር፡በቅን፡መንገድ፡አስኬዳቸዋለኹ፥በርሱም፡አይ ሰናከሉም፤እኔ፡ለእስራኤል፡አባት፡ነኝና፥ኤፍሬምም፡በኵሬ፡ነውና።
10፤አሕዛብ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፥በሩቅም፡ላሉ፡ደሴቶች፡አውሩና፦እስራኤልን፡የበተነ፡ርሱ፡ይሰ በስበዋል፥እረኛም፡መንጋውን፡እንደሚጠብቅ፡ይጠብቀዋል፡በሉ።
11፤እግዚአብሔር፡ያዕቆብን፡ተቤዥቶታል፥ከበረቱበትም፡እጅ፡አድኖታል።
12፤ይመጣሉ፡በጽዮንም፡ተራራ፡እልል፡ይላሉ፤ወደእግዚአብሔርም፡በጎነት፥ወደ፡እኽልና፡ወደ፡ወይን፡ጠጅ፡ወደ ፡ዘይትም፥ወደ፡በጎችና፡ወደ፡ላሞች፡ይሰበሰባሉ፤ነፍሳቸውም፡እንደ፡ረካች፡ገነት፡ትኾናለች፥ከእንግዲህም፡ ወዲህ፡አያዝኑም።
13፤በዚያን፡ጊዜም፡ድንግሊቱ፡በዘፈን፡ደስ፡ይላታል፥ጐበዛዝቱና፡ሽማግሌዎቹም፡ባንድ፡ላይ፡ደስ፡ይላቸዋል፤ ልቅሷቸውንም፡ወደ፡ደስታ፡እመልሳለኹ፥አጽናናቸውማለኹ፥ከሐዘናቸውም፡ደስ፡አሠኛቸዋለኹ።
14፤የካህናቱንም፡ነፍስ፡በብዛት፡አረካታለኹ፡ሕዝቤም፡በጎነቴን፡ይጠግባል።
15፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የዋይታና፡የመራራ፡ልቅሶ፡ድምፅ፡በራማ፡ተሰማ፤ራሔል፡ስለ፡ልጆቿ፡አለቀሰ ች፤የሉምና፡ስለ፡ልጆቿ፡መጽናናትን፡እንቢ፡አለች።
16፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ድምፅሽን፡ከልቅሶ፡ዐይንሽንም፡ከእንባ፡ከልክዪ፤ለሥራሽ፡ዋጋ፡ይኾናልና፥ ከጠላትም፡ምድር፡ይመለሳሉ።
17፤ለፍጻሜሽም፡ተስፋ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ልጆችሽም፡ወደ፡ዳርቻቸው፡ይመለሳሉ።
18፤ኤፍሬም፦ቀጣኸኝ፡እኔም፡እንዳልተገራ፡ወይፈን፡ተቀጣኹ፤አንተ፡እግዚአብሔር፡አምላኬ፡ነኽና፥መልሰኝ፡እ ኔም፡እመለሳለኹ።
19፤ከተመለስኹ፡በዃላ፡ተጸጸትኹ፥ከተገሠጽኹም፡በዃላ፡ጭኔን፡ጸፋኹ፤የብላቴንነቴንም፡ስድብ፡ተሸክሜያለኹና ፡ዐፈርኹ፥ተዋረድኹም፡ብሎ፡ሲያለቅስ፡ሰማኹ።
20፤በእውነት፡ኤፍሬም፡ለእኔ፡የከበረ፡ልጅ፡ነውን፧ወይስ፡የተወደደ፡ሕፃን፡ነውን፧በርሱ፡ላይ፡በተናገርኹ፡ ቍጥር፡ዐስበዋለኹ፤ስለዚህ፥አንዠቴ፡ታወከችለት፥ርኅራኄም፡እራራለታለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
21፤ለራስሽ፡የመንገድ፡ምልክት፡አድርጊ፥መንገድንም፡የሚመሩ፡ዐምዶችን፡ትከዪ፥ልብሽንም፡ወደኼድሽበት፡መን ገድ፡ወደ፡ጥርጊያው፡አቅኚ፤አንቺ፡የእስራኤል፡ድንግል፡ሆይ፥ተመለሺ፥ወደ፡እነዚህም፡ወደ፡ከተማዎችሽ፡ተመ ለሺ።
22፤አንቺ፡ከዳ፟ተኛ፡ልጅ፡ሆይ፥እስከ፡መቼ፡ትቅበዘበዣለሽ፧እግዚአብሔር፡በምድር፡ላይ፡ዐዲስ፡ነገርን፡ፈጥ ሯልና፥ሴት፡ወንድን፡ትከባ፟ለች።
23፤የእስራኤል፡አምላክ፣የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ምርኳቸውን፡በመለስኹ፡ጊዜ፡በይሁዳ፡ አገር፡በከተማዎቿ።የጽድቅ፡ማደሪያ፡ሆይ፥የቅድስና፡ተራራ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ይባርክኽ፡የሚልን፡ነገር፡እ ንደ፡ገና፡ይናገራሉ።
24፤በይሁዳ፡ከተማዎችና፡በአገሩ፡ዅሉ፡ከገበሬዎችና፡መንጋን፡ይዘው፡ከሚዞሩ፡ጋራ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ይገኛሉ።
25፤የደከመችውን፡ነፍስ፡አርክቻለኹና፥ያዘነችውንም፡ነፍስ፡ዅሉ፡አጥግቤያለኹና።
26፤ከዚህም፡በዃላ፡ነቃኹ፡ተመለከትኹም፥እንቅልፌም፡ጣፋጭ፡ኾነልኝ።
27፤የእስራኤልን፡ቤትና፡የይሁዳን፡ቤት፡በሰው፡ዘርና፡በእንስሳ፡ዘር፡የምዘራበት፡ዘመን፥እንሆ፥ይመጣል፥ይ ላል፡እግዚአብሔር።
28፤እንዲህም፡ይኾናል፤አፈርሳቸውና፡ክፉ፡አድርግባቸው፡ዘንድ፡እንደ፡ተጋኹባቸው፥እንዲሁ፡እሠራቸውና፡እተ ክላቸው፡ዘንድ፡እተጋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
29፤በዚያ፡ዘመን፡ሰው፡ዳግመኛ፡እንዲህ፡አይልም፦አባቶች፡ጨርቋ፡የወይን፡ፍሬ፡በሉ፥የልጆችም፡ጥርሶች፡ጠረ ሱ፤
30፤ነገር፡ግን፥ሰው፡ዅሉ፡በገዛ፡በደሉ፡ይሞታል፤መራራውን፡የወይን፡ፍሬ፡የሚበላ፡ዅሉ፡ጥርሶቹ፡ይጠርሳሉ።
31፤እንሆ፥ከእስራኤል፡ቤትና፡ከይሁዳ፡ቤት፡ጋራ፡ዐዲስ፡ቃል፡ኪዳን፡የምገባበት፡ወራት፡ይመጣል፥ይላል፡እግ ዚአብሔር፤
32፤ከግብጽ፡አገር፡አወጣቸው፡ዘንድ፡እጃቸውን፡በያዝኹበት፡ቀን፡ከአባቶቻቸው፡ጋራ፡እንደ፡ገባኹት፡ያለ፡ቃ ል፡ኪዳን፡አይደለም፤እነርሱ፡በኪዳኔ፡አልጸኑምና፥እኔም፡ቸል፡አልዃቸው፥ይላል፡እግዚአብሔር።
33፤ከነዚያ፡ወራት፡በዃላ፡ከእስራኤል፡ቤት፡ጋራ፡የምገባው፡ቃል፡ኪዳን፡ይህ፡ነውና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ሕ ጌን፡በልቡናቸው፡አኖራለኹ፥በልባቸውም፡እጽፈዋለኹ፤እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛ ል።
34፤እያንዳንዱ፡ሰው፡ባልንጀራውን፥እያንዳንዱም፡ወንድሙን፦እግዚአብሔርን፡ዕወቅ፡ብሎ፡አያስተምርም፤ከታና ሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ዅሉ፡ያውቁኛልና፥ይላል፡እግዚአብሔር።በደላቸውን፡እምራቸዋለኹና፥ኀጢአታቸ ውንም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አላስብምና።
35፤ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡የሚባል፥ፀሓይን፡በቀን፡የጨረቃንና፡የከዋክብትን፡ሥርዐት፡በሌሊት፡ብርሃን፡አድር ጎ፡የሚሰጥ፥እንዲተሙ፟ም፡የባሕርን፡ሞገዶች፡የሚያናውጥ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
36፤ይህ፡ሕግ፡ከፊቴ፡ቢወገድ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥በዚያን፡ጊዜ፡ደግሞ፡የእስራኤል፡ዘር፡በፊቴ፡ሕዝብ፡እን ዳይኾን፡ለዘለዓለም፡ይቀራል።
37፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰማይ፡በላይ፡ቢከነዳ፥የምድርም፡መሠረት፡በታች፡ቢመረመር፥በዚያን፡ጊዜ፡ ስላደረጉት፡ነገር፡ዅሉ፡የእስራኤልን፡ዘር፡ዅሉ፡እጥላለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
38፤ከሐናንኤል፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከማእዘኑ፡በር፡ድረስ፡ከተማ፡ለእግዚአብሔር፡የሚሠራበት፡ዘመን፥እንሆ፥ይ መጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
39፤የተለካበትም፡ገመድ፡ወደጋሬብ፡ኰረብታ፡በቀጥታ፡ወደ፡ፊት፡ይኼዳል፥ወደ፡ጎዓም፡ይዞራል።
40፤የሬሳም፡ሸለቆ፡ዅሉ፡የዐመድም፡ዕርሻ፡ዅሉ፡እስከቄድሮን፡ወንዝ፡ድረስ፡በምሥራቅ፡በኩል፡እስካለው፡እስ ከፈረስ፡በር፡ማእዘን፡ድረስ፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ይኾናል፤ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ለዘለዓለም፡አይነቀል ም፡አይፈርስምም።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32፤
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡በዐሥረኛው፡ዓመት፥በናቡከደነጾር፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፥ከእግዚአብሔር ፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው።
2፤በዚያን፡ጊዜም፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡ኢየሩሳሌምን፡ከቦ፟፡ነበር፤ነቢዩም፡ኤርምያስ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡ ቤት፡በነበረው፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ታስሮ፡ነበር።
3፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡እንዲህ፡ብሎ፡አስጠብቆት፡ነበርና፦ስለ፡ምን፡እንዲህ፡ብለኽ፡ትንቢት፡ትናገራለ ኽ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህችን፡ከተማ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፡ርሱም፡ይ ይዛታል፤
4፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡በእውነት፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ዐልፎ፡ይሰጣል፥አፍ፡ለአፍም፡ይናገረዋል፥ዐ ይኑም፡ዐይኑን፡ያያል፡እንጂ፡ከከለዳውያን፡እጅ፡አያመልጥም፤
5፤ርሱም፡ሴዴቅያስን፡ወደ፡ባቢሎን፡ያፈልሰዋል፥እኔም፡እስክጐበኘው፡ድረስ፡በዚያ፡ይኖራል፥ይላል፡እግዚአብ ሔር፤ከከለዳውያን፡ጋራ፡ብትዋጉ፡ምንም፡አትረቡም።
6፤ኤርምያስም፡እንዲህ፡አለ፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
7፤እንሆ፥የአጎትኽ፡የሰሎም፡ልጅ፡ዐናምኤል፡ወዳንተ፡መጥቶ፦ትገዛው፡ዘንድ፡መቤዠቱ፡የአንተ፡ነውና፥በዐናቶ ት፡ያለውን፡ዕርሻዬን፡ግዛ፡ይልኻል።
8፤እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡የአጎቴ፡ልጅ፡ዐናምኤል፡እኔ፡ወዳለኹበት፡ወደግዞቱ፡ቤት፡አደባባይ፡መጥቶ፦በብ ንያም፡አገር፡በዐናቶት፡ያለውን፡ዕርሻዬን፥እባክኽ፥ግዛ፤ርስቱ፡የአንተ፡ነውና፥መቤዠቱም፡የአንተ፡ነውና፤ ለአንተ፡ግዛው፡አለኝ።ይህም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቅኹ።
9፤በዐናቶትም፡ያለውን፡ዕርሻ፡ከአጎቴ፡ልጅ፡ከዐናምኤል፡ገዛኹ፥ዐሥራ፡ሰባት፡ሰቅል፡ብርም፡መዘንኹለት።
10፤በውሉም፡ወረቀት፡ላይ፡ፈረምኹ፡ዐተምኹትም፥ምስክሮችንም፡ጠርቼ፡ብሩን፡በሚዛን፡መዘንኹለት።
11፤የታተመውንና፡የተከፈተውን፡የውል፡ወረቀት፡ወሰድኹ፤
12፤የአጎቴም፡ልጅ፡ዐናምኤል፥የውሉንም፡ወረቀት፡የፈረሙ፡ምስክሮች፥በግዞትም፡ቤት፡አደባባይ፡የተቀመጡ፡አ ይሁድ፡ዅሉ፡እያዩ፡የውሉን፡ወረቀት፡ለመሕሤያ፡ልጅ፡ለኔርያ፡ልጅ፡ለባሮክ፡ሰጠኹት።
13፤በፊታቸውም፡እንዲህ፡ብዬ፡ባሮክን፡አዘዝኹት፦
14፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ብዙ፡ቀን፡ይጠበቁ፡ዘንድ፡የታተመውን ና፡የተከፈተውን፡ይህን፡የውል፡ወረቀት፡ወስደኽ፡በሸክላ፡ዕቃ፡ውስጥ፡አኑራቸው።
15፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ሰዎች፡በዚች፡ምድር፡ቤትንና፡ዕርሻ ን፡የወይን፡ቦታንም፡እንደ፡ገና፡ይገዛሉ።
16፤ለኔርያ፡ልጅ፡ለባሮክም፡የውሉን፡ወረቀት፡ከሰጠኹት፡በዃላ፥እንዲህ፡ብዬ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለይኹ።
17፤አቤቱ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥እንሆ፥አንተ፡ሰማይንና፡ምድርን፡በታላቅ፡ኀይልኽና፡በተዘረጋች፡ክንድኽ ፡ፈጥረኻል፥ከአንተም፡የሚያቅት፡ነገር፡የለም።
18፤ለብዙ፡ሺሕ፡ምሕረት፡ታደርጋለኽ፥የአባቶችንም፡በደል፡ከነርሱ፡በዃላ፡በልጆቻቸው፡ብብት፡ትመልሳለኽ፤ስ ምኽ፡ታላቅና፡ኀያል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው።
19፤በምክር፡ታላቅ፡በሥራም፡ብርቱ፡ነኽ፤ለዅሉም፡እንደ፡መንገዱና፡እንደ፡ሥራው፡ፍሬ፡ትሰጥ፡ዘንድ፡ዐይኖች ኽ፡በአዳም፡ልጆች፡መንገድ፡ዅሉ፡ተገልጠዋል።
20፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ምልክትንና፡ድንቅን፡ነገር፡በግብጽ፡ምድር፡ደግሞም፡በእስራኤልና፡በሌላዎች፡ሰዎች ፡መካከል፡አድርገኻል፥እንደ፡ዛሬም፡ለአንተ፡ስም፡አድርገኻል።
21፤በምልክትና፡በድንቅ፡ነገር፥በብርቱ፡እጅና፡በተዘረጋች፡ክንድ፡በታላቅም፡ግርማ፡ሕዝብኽን፡እስራኤልን፡ ከግብጽ፡ምድር፡አወጣኽ።
22፤ትሰጣቸውም፡ዘንድ፡ለአባቶቻቸው፡የማልኽላቸውን፡ምድር፥ወተትና፡ማርንም፡የምታፈሰ፟ውን፡ምድር፥ሰጠኻቸ ው፤
23፤እነርሱም፡ገብተው፡ወረሷት፤ነገር፡ግን፥ቃልኽን፡አልሰሙም፥በሕግኽም፡አልኼዱም፤ያደርጉም፡ዘንድ፡ካዘዝ ኻቸው፡ዅሉ፡ምንም፡አላደረጉም፤ስለዚህ፥ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አመጣኽባቸው።
24፤እንሆ፥የዐፈር፡ድልድል፥ሊይዟትም፡እስከ፡ከተማዪቱ፡ድረስ፡ቀርበዋል፤ከሰይፍና፡ከራብ፡ከቸነፈርም፡የተ ነሣ፡ከተማዪቱ፡ለሚዋጓት፡ለከለዳውያን፡እጅ፡ተሰጥታለች፥የተናገርኸውም፡ኾኗል፤እንሆም፥አንተ፡ታየዋለኽ።
25፤አንተም፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፦ዕርሻውን፡በብር፡ግዛ፡ምስክሮችንም፡ጥራ፡አልኸኝ፤ከተማዪቱ፡ግን፡ለከ ለዳውያን፡እጅ፡ተሰጥታለች።
26፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
27፤እንሆ፥እኔ፡የሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤
28፤በእውኑ፡እኔን፡የሚያቅተኝ፡ነገር፡አለን፧ስለዚህ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህችን፡ከተማ፡ ለከለዳውያን፡እጅና፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፥ርሱም፡ይይዛታል።
29፤ይህችን፡ከተማ፡የሚወጉ፡ከለዳውያን፡መጥተው፡በእሳት፡ያነዷ፟ታል፥ያስቈጡኝም፡ዘንድ፡በሰገነታቸው፡ላይ ፡ለበዓል፡ካጠኑባቸው፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡የመጠጥን፡ቍርባን፡ካፈሰሱባቸው፡ቤቶች፡ጋራ፡ያቃጥሏታል።
30፤የእስራኤል፡ልጆችና፡የይሁዳ፡ልጆች፡ከታናሽነታቸው፡ዠምሮ፡በፊቴ፡ክፉ፡ነገርን፡ብቻ፡አድርገዋልና፤የእ ስራኤልም፡ልጆች፡እኔን፡በእጃቸው፡ሥራ፡ከማስቈጣት፡በቀር፡ሌላ፡ሥራ፡አላደረጉምና።
31፤ከፊቴ፡አስወግዳት፡ዘንድ፡ይህች፡ከተማ፡ከሠሯት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ቍጣዬንና፡መዓቴን፡ለማ ነሣሣት፡ኾናለችና፤
32፤ይህም፡እኔን፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፥እነርሱና፡ነገሥታታቸው፡አለቃዎቻቸውም፡ካህናታቸውም፡ነቢያታቸውም፡የይ ሁዳም፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌምም፡የሚንኖሩ፥ስላደረጉት፡ስለእስራኤል፡ልጆችና፡ስለይሁዳ፡ልጆች፡ክፋት፡ዅሉ፡ነ ው።
33፤ፊታቸውንም፡ሳይኾን፡ዠርባቸውን፡ወደ፡እኔ፡መለሱ፤እኔም፡በማለዳ፡ተነሥቼ፡ሳሰተምራቸው፡ተግሣጽን፡ይቀ በሉ፡ዘንድ፡አልሰሙም።
34፤ያረክሱትም፡ዘንድ፡ስሜ፡በተጠራበት፡ቤት፡ውስጥ፡ርኵሰታቸውን፡አኖሩ።
35፤ይሁዳን፡ወደ፡ኀጢአት፡እንዲያገቡት፥ይህንን፡ርኵሰት፡ያደርጉ፡ዘንድ፥እኔ፡ያላዘዝኹትንና፡በልቤ፡ያላሰ ብኹትን፡ነገር፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡ለሞሎክ፡በእሳት፡ያሳልፉ፡ዘንድ፡በሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ ያሉትን፡የበዓልን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡ሠሩ።
36፤አኹን፡እንግዲህ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡አንተ፡ስለ፡ርሷ፦በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ለባ ቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ተሰጥታለች፡ስለምትላት፡ከተማ፡እንዲህ፡ይላል፦
37፤እንሆ፥በቍጣዬና፡በመዓቴ፡በታላቅም፡መቅሠፍቴ፡እነርሱን፡ካሳደድኹባት፡አገር፡ዅሉ፡እሰበስባቸዋለኹ፥ወ ደዚህም፡ስፍራ፡እመልሳቸዋለኹ፥ተዘልለውም፡እንዲኖሩ፡አደርጋለኹ፤
38፤እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።
39፤ለእነርሱም፡ከነርሱም፡በዃላ፡ለልጆቻቸው፡መልካም፡ይኾንላቸው፡ዘንድ፡ለዘለዓለም፡እንዲፈሩኝ፡አንድ፡ል ብና፡አንድ፡መንገድ፡እሰጣቸዋለኹ።
40፤ለእነርሱም፡ከማደርገው፡በጎነት፡አልመለስም፡ስል፥ከነርሱ፡ጋራ፡የዘለዓለምን፡ቃል፡ኪዳን፡እገባለኹ፤ከ እኔም፡ዘንድ፡ፈቀቅ፡እንዳይሉ፡መፈራቴን፡በልባቸው፡ውስጥ፡አኖራለኹ።
41፤ለእነርሱም፡መልካምን፡በማድረግ፡ደስ፡ይለኛል፡በእውነትም፡በፍጹም፡ልቤና፡በፍጹም፡ነፍሴ፡በዚች፡ምድር ፡እተክላቸዋለኹ።
42፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ይህን፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡እንዳመጣኹ፥እንዲሁ፡ የተናገርኹላቸውን፡በጎነት፡ዅሉ፡አመጣላቸዋለኹ።
43፤እናንተም፦ያለሰውና፡ያለእንስሳ፡ያለች፡ባድማ፡ናት፥ለከለዳውያንም፡እጅ፡ተሰጥታለች፡በምትሏት፡ምድር፡ ዕርሻን፡ይገዛሉ።
44፤ምርኮኛዎቻቸውንም፡እመልሳለኹና፡በብንያም፡አገር፡በኢየሩሳሌምም፡ዙሪያ፡ባሉ፡ስፍራዎች፥በይሁዳም፡ከተ ማዎች፡በደጋውም፡ባሉ፡ከተማዎች፡በቈላውም፡ባሉ፡ከተማዎች፡በደቡብም፡ባሉ፡ከተማዎች፥ሰዎች፡ዕርሻውን፡በብ ር፡ይገዛሉ፡በውሉም፡ወረቀት፡ፈርመው፡ያትማሉ፡ምስክሮችንም፡ይጠራሉ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33፤
1፤ኤርምያስ፡ገና፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ታስሮ፡ሳለ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኹለተኛ፡ጊዜ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ ለት፦
2፤ስሙ፡እግዚአብሔር፡የኾነ፥ያደረገው፡እግዚአብሔር፥ያጸናውም፡ዘንድ፡የሠራው፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል ፦
3፤ወደ፡እኔ፡ጩኽ፥እኔም፡እመልስልኻለኹ፤አንተም፡የማታውቀውን፡ታላቅና፡ኀይለኛ፡ነገርን፡አሳይኻለኹ።
4፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ለዐፈር፡ድልድልና፡ለምሽግ፡ስለ፡ፈረሱ፡ስለዚች፡ከተማ፡ቤቶች፥ስለይሁ ዳም፡ነገሥታት፡ቤቶች፡እንዲህ፡ይላልና፦
5፤ከለዳውያን፡ለመዋጋት፡መጥተዋል፤ነገር፡ግን፥በቍጣዬና፡በመዓቴ፡በገደልዃቸው፡ሰዎች፡ሬሳዎች፡ሊሞሏቸው፡ ነው፥ስለ፡ክፋታቸው፡ዅሉ፡ፊቴን፡ከዚች፡ከተማ፡ሰውሬያለኹና።
6፤እንሆ፥ፈውስንና፡መድኀኒትን፡አመጣላታለኹ፥እፈውሳቸውማለኹ፤የሰላምንና፡የእውነትን፡ብዛት፡እገልጥላቸዋ ለኹ።
7፤የይሁዳን፡ምርኮና፡የእስራኤልንም፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ቀድሞም፡እንደ፡ነበሩ፡አድርጌ፡እሠራቸዋለኹ።
8፤እኔንም፡ከበደሉበት፡ኀጢአት፡ዅሉ፡አነጻቸዋለኹ፡እኔንም፡የበደሉኝን፡ያመፀብኝንም፡ኀጢአታቸውን፡ዅሉ፡ይ ቅር፡እላለኹ።
9፤ይህችም፡ከተማ፡እኔ፡የምሠራላቸውን፡በጎነት፡ዅሉ፡በሚሰሙ፡እኔም፡ስላመጣኹላቸው፡በጎነትና፡ሰላም፡ዅሉ፡ በሚፈሩና፡በሚደነግጡ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ፊት፡ለደስታ፡ስም፡ለምስጋናም፡ለክብርም፡ትኾናለች።
10፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፦ያለሰውና፡ያለእንስሳ፡ያለች፡ባድማ፡ናት፡በምትሏት፡በዚች፡ስፍራ ፥የሚቀመጥባቸው፡በሌላ፥ያለሰውና፡ያለእንስሳ፡ባድማ፡በኾኑ፡በይሁዳ፡ከተማዎችና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፥
11፤የሐሤት፡ድምፅና፡የደስታ፡ድምፅ፥የወንድ፡ሙሽራ፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራ፡ድምፅ፦እግዚአብሔር፡ቸር፡ነውና ፥ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፡ነውና፥የሰራዊትን፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፡የሚሉ፡ድምፅ፥ወደእግዚአብሔርም ፡ቤት፡የምስጋናን፡መሥዋዕት፡የሚያመጡት፡ድምፅ፡እንደ፡ገና፡ይሰማል።የምድርን፡ምርኮ፡ቀድሞ፡እንደ፡ነበረ ፡አድርጌ፡እመልሳለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
12፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ባድማ፡ኾኖ፥ያለሰውና፡ያለእንስሳ፡ባለው፡በዚህ፡ስፍራ፡በ ከተማዎችም፡ዅሉ፡መንጋዎቻቸውን፡የሚያሳርፉት፡የእረኛዎች፡መኖሪያ፡ይኾናል።
13፤በደጋው፡ላይ፡ባሉ፡ከተማዎች፡በቈላውም፡ባሉ፡ከተማዎች፡በደቡብም፡ባሉ፡ከተማዎች፥በብንያምም፡አገር፡በ ኢየሩሳሌምም፡ዙሪያ፡ባሉ፡ስፍራዎች፥በይሁዳም፡ከተማዎች፡መንጋዎቹ፡በተቈጣጣሪው፡እጅ፡እንደ፡ገና፡ያልፋሉ ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
14፤እንሆ፥ስለእስራኤል፡ቤትና፡ስለይሁዳ፡ቤት፡የተናገርኹትን፡መልካም፡ቃል፡የምፈጽምበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ ይላል፡እግዚአብሔር።
15፤በዚያም፡ዘመን፡በዚያም፡ጊዜ፡ለዳዊት፡የጽድቅን፡ቍጥቋጥ፡አበቅልለታለኹ፤ርሱም፡ፍርድንና፡ጽድቅን፡በም ድር፡ያደርጋል።
16፤በዚያም፡ዘመን፡ይሁዳ፡ይድናል፡ኢየሩሳሌምም፡ተዘልላ፡ትቀመጣለች፤የምትጠራበትም፡ስም፦እግዚአብሔር፡ጽ ድቃችን፡ተብሎ፡ነው።
17፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በእስራኤል፡ቤት፡ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጥ፡ሰው፡ከዳዊት፡ዘንድ፡አይታጣም፤
18፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡የሚያቀርብ፡የእኽሉንም፡ቍርባን፡የሚያቃጥል፡ዅልጊዜም፡የሚሠዋ፡ሰው፡ከሌዋው ያን፡ካህናት፡ዘንድ፡በእኔ፡ፊት፡አይታጣም።
19፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
20፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ቀንና፡ሌሊት፡በወራቱ፡እንዳይኾን፡የቀን፡ቃል፡ኪዳኔንና፡የሌሊት፡ቃል፡ኪ ዳኔን፡ማፍረስ፡ብትችሉ፥
21፤በዙፋኑ፡ላይ፡የሚነግሥ፡ልጅ፡እንዳይኾንለት፡ከባሪያዬ፡ከዳዊት፡ጋራ፥ከአገልጋዮቼም፡ከሌዋውያን፡ካህና ት፡ጋራ፡ያለው፡ቃል፡ኪዳኔ፡ደግሞ፡ይፈርሳል።
22፤የሰማይን፡ሰራዊት፡መቍጠር፡የባሕርንም፡አሸዋ፡መስፈር፡እንደማይቻል፥እንዲሁ፡የባሪያዬን፡የዳዊትን፡ዘ ርና፡የሚያገለግሉኝን፡ሌዋውያንን፡አበዛለኹ።
23፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
24፤ይህ፡ሕዝብ፦እግዚአብሔር፡የመረጣቸውን፡ኹለቱን፡ወገን፡ጥሏቸዋል፡ያለውን፡ነገር፡አትመለከትምን፧እንዲ ሁ፡በፊታቸው፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ሕዝብ፡እንዳይኾን፡ሕዝቤን፡አቃለ፟ዋል።
25፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የቀንና፡የሌሊት፡ቃል፡ኪዳኔን፡የሰማይንና፡የምድርንም፡ሥርዐት፡ያላጸናኹ ፡እንደ፡ኾነ፥
26፤እኔም፡ደግሞ፡በአብርሃምና፡በይሥሐቅ፡በያዕቆብም፡ዘር፡ላይ፡ገዢዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ከዘሩ፡እንዳልወስድ ፥የያዕቆብንና፡የባሪያዬን፡የዳዊትን፡ዘር፡እጥላለኹ፤ምርኳቸውን፡እመልሳለኹና፥እምራቸውማለኹና።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34፤
1፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ከእጁም፡ግዛት፡በታች፡ያሉ፡የምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡አሕ ዛብም፡ዅሉ፡ኢየሩሳሌምንና፡ከተማዎቿን፡ዅሉ፡ይወጉ፡በነበረ፡ጊዜ፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የ መጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኺድ፡ለይሁዳም፡ንጉሥ፡ለሴዴቅያስ፡ተናገር፡እንዲህም፡ በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህችን፡ከተማ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፥በእሳ ትም፡ያቃጥላታል፤
3፤አንተም፡በርግጥ፡ትያዛለኽ፡በእጅም፡አልፈኽ፡ትሰጣለኽ፡እንጂ፡ከእጁ፡አታመልጥም፤ዐይንኽም፡የባቢሎንን፡ ንጉሥ፡ዐይን፡ታያለች፥ርሱም፡ከአንተ፡ጋራ፡አፍ፡ለአፍ፡ይናገራል፥ወደ፡ባቢሎንም፡ትገባለኽ።
4፤ነገር፡ግን፥የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ፤እግዚአብሔር፡ስለ፡አንተ፡እንዲህ ፡ይላል፦በሰይፍ፡አትሞትም፥በሰላም፡ትሞታለኽ፡እንጂ፤
5፤ከአንተ፡በፊት፡እንደ፡ነበሩ፡እንደ፡ዱሮ፡ነገሥታት፡እንደ፡አባቶችኽ፡መቃጠል፥እንዲሁ፡ያቃጥሉኻልና፦ወየ ው! ጌታ፡ሆይ፡እያሉ፡ያለቅሱልኻል፤እኔ፡ቃልን፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
6-7፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡ኢየሩሳሌምንና፡የቀሩትን፡የይሁዳን፡ከተማዎች፡ዅሉ፥ከተመሸጉት፡ከይሁዳ፡ከ ተማዎች፡የተረፉትን፡ለኪሶንና፡ዓዜቃን፡በወጋ፡ጊዜ፥ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሴ ዴቅያስ፡በኢየሩሳሌም፡ነገረው።
8-9፤ሰው፡ዅሉ፡ዕብራዊ፡የኾነውን፡ወንድ፡ባሪያውንና፡ዕብራዊት፡የኾነች፡ሴት፡ባሪያውን፡ሐራነት፡እንዲያወጣ ፥አይሁዳዊ፡ወንድሙንም፡ማንም፡እንዳይገዛ፥ስለ፡ሐራነታቸው፡ዐዋጅ፡እንዲነገር፡ንጉሡ፡ሴዴቅያስ፡በኢየሩሳ ሌም፡ከነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ካደረገ፡በዃላ፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ ቃል፡ይህ፡ነው፦
10፤ሰው፡ዅሉ፡ወንድ፡ባሪያውንና፡ሴት፡ባሪያውን፡ሐራነት፡እንዲያወጣ፡ከእንግዲህ፡ወዲህም፡ማንም፡እንዳይገ ዛቸው፡ወደቃል፡ኪዳኑ፡የገቡ፡አለቃዎች፡ዅሉና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ሰሙ፥ሐራነትም፡አወጧቸው።
11፤ነገር፡ግን፥ከዚያ፡በዃላ፡ተመልሰው፡ሐራነት፡ያወጧቸውን፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎቻቸውን፡አስመለሱ፥ወ ንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎችም፡አድርገው፡ገዟቸው።
12፤ስለዚህ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
13፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አባቶቻችኹን፡ከባርነት፡ቤት፡ከግብጽ፡አገር፡ባወጣዃ ቸው፡ቀን፡ከነርሱ፡ጋራ፡እንዲህ፡ብዬ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረግኹ።
14፤ሰባት፡ዓመት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥የተሸጠላችኹን፡ስድስትም፡ዓመት፡የተገዛላችኹን፡ዕብራዊ፡ወንድማችኹን፡እ ያንዳንዳችኹ፡ሐራነት፡ታወጡታላችኹ፥እያንዳንዱም፡ያወጣዋል፤አባቶቻችኹ፡ግን፡አልሰሙኝም፡ዦሯቸውንም፡አላ ዘነበሉም።
15፤እናንተም፡ዛሬ፡ተመልሳችኹ፡ሰው፡ዅሉ፡ባልንጀራውን፡ሐራነት፡ለማውጣት፡ዐዋጅ፡በመንገር፡ለዐይኔ፡ደስ፡ የሚያሠኝን፡ነገር፡አድርጋችኹ፡ነበር፥በስሜም፡በሚጠራበት፡ቤት፡ውስጥ፡በፊቴ፡ቃል፡ኪዳን፡አድርጋችኹ፡ነበ ር።
16፤ነገር፡ግን፥ተመልሳችኹ፡ስሜን፡አስነቀፋችኹ፥እያንዳንዳችኹም፡በፈቃዳቸው፡እንዲኼዱ፡ሐራነት፡ያወጣችዃ ቸውን፡ወንድና፡ሴት፡ባሪያዎቻችኹን፡አስመለሳችኹ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎችም፡እንዲኾኑላችኹ፡ገዛችዃቸው ።
17፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰው፡ዅሉ፡ለወንድሙና፡ለባልንጀራው፡የሐራነት፡ዐዋጅ፡ለመንገር፡ እኔን፡አልሰማችኹም፤እንሆ፥እኔ፡ለሰይፍና፡ለቸነፈር፡ለራብም፡የሐራነት፡ዐዋጅ፡እናገርባችዃለኹ፥ይላል፡እ ግዚአብሔር፤በምድርም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡መካከል፡እንድትበተኑ፡አደርጋችዃለኹ።
18፤ቃል፡ኪዳኔንም፡የተላለፉትን፡ሰዎች፥እንቦሳውንም፡ቈርጠው፡በቍራጩ፡መካከል፡ባለፉ፡ጊዜ፡በፊቴ፡ያደረጉ ትን፡የቃል፡ኪዳንን፡ቃል፡ያልፈጸሙትን፥
19፤የይሁዳን፡አለቃዎችና፡የኢየሩሳሌምን፡አለቃዎች፡ጃን፡ደረባዎችን፡ካህናትንም፡በእንቦሳም፡ቍራጭ፡መካከ ል፡ያለፉትን፡የአገሩን፡ሕዝብ፡ዅሉ፥
20፤ለጠላቶቻቸው፡እጅ፡ነፍሳቸውንም፡ለሚሿት፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፤ሬሳቸውም፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡ አራዊት፡መብል፡ይኾናል።
21፤የይሁዳንም፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስንና፡አለቃዎቹን፡ለጠላቶቻቸው፡እጅ፡ነፍሳቸውንም፡ለሚሿት፡እጅ፡ከእናንተም ፡ለተመለሱት፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
22፤እንሆ፥አዛ፟ለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ወደዚችም፡ከተማ፡እመልሳቸዋለኹ፤ርሷንም፡ይወጋሉ፡ይይዟትማል፡በ እሳትም፡ያቃጥሏታል፤የይሁዳንም፡ከተማዎች፡ሰው፡የሌለበት፡ባድማ፡አደርጋቸዋለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35፤
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡ዘመን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይ ህ፡ነው፦
2፤ወደሬካባውያን፡ቤት፡ኼደኽ፡ተናገራቸው፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ከጓዳዎቹ፡ወደ፡አንዲቱ፡አግባቸው፡የወይ ን፡ጠጅም፡አጠጣቸው።
3፤የከባስንን፡ልጅ፡የኤርምያስን፡ልጅ፡ያእዛንያን፡ወንድሞቹንም፡ልጆቹንም፡ዅሉ፡የሬካባውያንን፡ወገን፡ዅሉ ፡ወሰድዃቸው፤
4፤ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡በበረኛው፡በሰሎም፡ልጅ፡በመዕሴያ፡ጓዳ፡በላይ፡ባለው፡በአለቃዎች፡ጓዳ፡አጠገብ፡ ወዳለው፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደጌዴልያ፡ልጅ፡ወደሐናን፡ልጆች፡ጓዳ፡አገባዃቸው።
5፤በሬካባውያንም፡ልጆች፡ፊት፡የወይን፡ጠጅ፡የሞላባቸውን፡ማድጋዎችንና፡ጽዋዎችን፡አኑሬ፦የወይኑን፡ጠጅ፡ጠ ጡ፡አልዃቸው።
6፤እነርሱ፡ግን፡እንዲህ፡አሉ፦የወይኑን፡ጠጅ፡አንጠጣም፥አባታችን፡የሬካብ፡ልጅ፡ኢዮናዳብ፡እንዲህ፡ብሎ፡አ ዞ፟ናልና።እናንተና፡ልጆቻችኹ፡ለዘለዓለም፡የወይን፡ጠጅ፡አትጠጡ።
7፤በምትኖሩባት፡ምድር፡ላይ፡ብዙ፡ዘመን፡እንድትኖሩ፥በዕድሜያችኹ፡ሙሉ፡በድንኳን፡ውስጥ፡ተቀመጡ፡እንጂ፡ቤ ትን፡አትሥሩ፥ዘርንም፡አትዝሩ፥ወይንም፡አትትከሉ፥አንዳችም፡አይኹንላችኹ።
8፤እኛም፡የአባታችንን፡የሬካብ፡ልጅ፡የኢዮናዳብን፡ቃል፡ባዘዘን፡ነገር፡ዅሉ፡ታዘ፟ናል፤እኛም፡ሚስቶቻችንም ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችንም፡ዕድሜያችንን፡ሙሉ፡የወይን፡ጠጅ፡አልጠጣንም፤
9፤የምንቀመጥበትንም፡ቤት፡አልሠራንም፤የወይን፡ቦታና፡ዕርሻ፡ዘርም፡የለንም፤
10፤በድንኳንም፡ውስጥ፡ተቀምጠናል፥ታዘ፟ናል፥አባታችንም፡ኢዮናዳብ፡ያዘዘንን፡ዅሉ፡አድርገናል።
11፤ነገር፡ግን፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወደዚች፡ምድር፡በመጣ፡ጊዜ፦ኑ፡ከከለዳውያን፡ሰራዊትና፡ከሶ ርያ፡ሰራዊት፡ፊት፡የተነሣ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንኺድ፡አልን፤እንዲሁም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጥን።
12፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
13፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኺድና፡ለይሁዳ፡ሰዎችና፡በኢየሩሳሌም ፡ለሚቀመጡ፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦ቃሌን፡ትሰሙ፡ዘንድ፡ተግሣጽን፡አትቀበሉምን፧ይላል፡እግዚአብሔር።
14፤የሬካብ፡ልጅ፡ኢዮናዳብ፡ልጆቹ፡የወይን፡ጠጅ፡እንዳይጠጡ፡ያዘዛቸው፡ቃል፡ተፈጸመ፤ለአባታቸውም፡ትእዛዝ ፡ታዘ፟ዋልና፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡አይጠጡም፤እኔም፡በማለዳ፡ተነሥቼ፡ተናግሬያችዃለኹ፤ተናገርኹ፥ኾኖም፡አል ሰማችኹኝም።
15፤ደግሞም፦እያንዳንዳችኹ፡ከክፉ፡መንገዳችኹ፡ተመለሱ፥ሥራችኹንም፡አሳምሩ፥ታመልኳቸውም፡ዘንድ፡ሌላዎችን ፡አማልክት፡አትከተሉ፥ለእናንተና፡ለአባቶቻችኹም፡በሰጠኹት፡ምድር፡ትቀመጣላችኹ፡እያልኹ፡በማለዳ፡ተነሥቼ ፡ባሪያዎቼን፡ነቢያትን፡ዅሉ፡ልኬባችኹ፡ነበር፤እናንተ፡ግን፡ዦሯችኹን፡አላዘነበላችኹም፡እኔንም፡አልሰማች ኹኝም።
16፤የሬካብ፡ልጅ፡የኢዮናዳብ፡ልጆች፡አባታቸው፡ያዘዛቸውን፡ትእዛዝ፡ፈጽመዋልና፥ይህ፡ሕዝብ፡ግን፡አልሰማኝ ምና፤
17፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፣የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በተናገርዃቸው፡ጊ ዜ፡አልሰሙምና፥በጠራዃቸውም፡ጊዜ፡አልመለሱልኝምና፡የተናገርኹባቸውን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡በይሁዳ፡ላይ፡በኢ የሩሳሌምም፡በሚቀመጡ፡ዅሉ፡ላይ፡አመጣባቸዋለኹ።
18፤ኤርምያስም፡ሬካባውያንን፡እንዲህ፡አላቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ለአባታችኹ፡ለኢዮናዳብ፡ትእዛዝ፡ታዛ፟ችዃልና፥ትእዛዙንም፡ዅሉ፡ጠብቃችዃልና፥ያዘዛችኹንም፡ፈጽማች ዃልና፤
19፤ስለዚህ፥በፊቴ፡የሚቆም፡ሰው፡ከሬካብ፡ልጅ፡ከኢዮናዳብ፡ወገን፡ለዘለዓለም፡አይታጣም።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36፤
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፡ይህ፡ቃል፡ከእግዚአብሔር ፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ፦
2፤አንድ፡የመጽሐፍ፡ክርታስ፡ውሰድ፥ለአንተም፡ከተናገርኹበት፡ቀን፡ከኢዮስያስ፡ዘመን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድ ረስ፡በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ላይ፡በአሕዛብም፡ዅሉ፡ላይ፡የተናገርኹኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ጻፍበት።
3፤ምናልባት፡የይሁዳ፡ቤት፦እኔ፡አደርግባቸዋለኹ፡ያልኹትንና፡ያሰብኹትን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ይሰሙ፡ይኾናል፥ ከክፉ፡መንገዳቸው፡ይመለሱ፡ዘንድ፡እኔም፡በደላቸውንና፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡እል፡ዘንድ።
4፤ኤርምያስም፡የኔርያን፡ልጀ፡ባሮክን፡ጠራ፥ባሮክም፡እግዚአብሔር፡ለርሱ፡የተናገረውን፡ቃል፡ዅሉ፡ከኤርምያ ስ፡አፍ፡በመጽሐፉ፡ክርታስ፡ጻፈ።
5፤ኤርምያስም፡ባሮክን፡እንዲህ፡ሲል፡አዘዘው፦እኔ፡ተግዤያለኹ፤ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እገባ፡ዘንድ፡አልችል ም።
6፤አንተ፡ግን፡ኺድ፥ከአፌም፡የጻፍኸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡በጾም፡ቀን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በሕዝቡ፡ዦ ሮ፡በክርታሱ፡አንብ፟፤ደግሞም፡ከከተማዎቻቸው፡በሚወጡ፡በይሁዳ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዦሮ፡አንበ፟ው።
7፤እግዚአብሔር፡በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡የተናገረው፡ቍጣውና፡መዓቱ፡ታላቅ፡ነውና፥ምናልባት፡ጸሎታቸው፡በእግዚአ ብሔር፡ፊት፡ትወድቅ፡ይኾናል፥ዅሉም፡ከክፉ፡መንገዱ፡ይመለስ፡ይኾናል።
8፤የኔርያም፡ልጅ፡ባሮክ፡ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረገ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የእግዚአብሔርን፡ ቃል፡በመጽሐፉ፡አነበበ።
9፤እንዲህም፡ኾነ፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡በዘጠነኛው፡ወር፡በኢየ ሩሳሌም፡የተቀመጡ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ከይሁዳም፡ከተማዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡የመጡ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊ ት፡ለመጾም፡ዐዋጅ፡ነገሩ።
10፤ባሮክም፡የኤርምያስን፡ቃል፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በላይኛው፡አደባባይ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በዐዲሱ፡በር ፡መግቢያ፡ባለው፡በጸሓፊው፡በሳፋን፡ልጅ፡በገማርያ፡ጓዳ፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ዦሮ፡በመጽሐፉ፡አነበበ።
11፤የሳፋንም፡ልጅ፡የገማርያ፡ልጅ፡ሚክያስ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ዅሉ፡ከመጽሐፉ፡በሰማ፡ጊዜ፥
12፤ወደንጉሡ፡ቤት፡ወደጸሓፊው፡ጓዳ፡ወረደ፤እንሆም፥አለቃዎች፡ዅሉ፥ጸሓፊው፡ኤሊሳማ፥የሸማያ፡ልጅ፡ድላያ፥ የዓክቦር፡ልጅ፡ኤልናታን፥የሳፋን፡ልጅ፡ገማርያ፥የሐናንያ፡ልጅ፡ሴዴቅያስ፡አለቃዎቹም፡ዅሉ፡በዚያ፡ተቀምጠ ው፡ነበር።
13፤ሚክያስም፡ባሮክ፡በሕዝቡ፡ዦሮ፡በመጽሐፉ፡ባነበበ፡ጊዜ፡የሰማውን፡ቃል፡ዅሉ፡ነገራቸው።
14፤አለቃዎቹም፡ዅሉ፦በሕዝቡ፡ዦሮ፡ያነበብኸውን፡ክርታስ፡በእጅኽ፡ይዘኽ፡ና፡የሚል፡መልእክት፡በኵሲ፡ልጅ፡ በሰሌምያ፡ልጅ፡በናታንያ፡ልጅ፡በይሁዲ፡እጅ፡ወደ፡ባሮክ፡ላኩ።የኔርያም፡ልጅ፡ባሮክ፡ክርታሱን፡በእጁ፡ይዞ ፡ወደ፡እነርሱ፡መጣ።
15፤እነርሱም፦እስኪ፡ተቀመጥ፥በዦሯችንም፡አንብ፟፡አሉት።ባሮክም፡በዦሯቸው፡አነበበው።
16፤ቃሉንም፡ዅሉ፡በሰሙ፡ጊዜ፡ፈርተው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተመካከሩ፥ባሮክንም፦ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡በርግጥ፡ለንጉ ሡ፡እንናገራለን፡አሉት።
17፤ባሮክንም፦ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ከአፉ፡እንዴት፡እንደ፡ጻፍኸው፡ንገረን፡ብለው፡ጠየቁት።
18፤ባሮክም፦ይህን፡ቃል፡ከአፉ፡ይነግረኝ፡ነበር፥እኔም፡በመጽሐፉ፡ላይ፡በቀለም፡እጽፍ፡ነበር፡ብሎ፡መለሰላ ቸው።
19፤አለቃዎቹም፡ባሮክን፦አንተና፡ኤርምያስ፡ኺዱ፥ተሸሸጉ፥ወዴትም፡እንደ፡ኾናችኹ፡ማንም፡አይወቅ፡አሉት።
20፤ወደ፡ንጉሡም፡ወደ፡አደባባይ፡ገቡ፥ክርታሱንም፡በጸሓፊው፡በኤሊሳማ፡ጓዳ፡አኑረውት፡ነበር፤ቃሉንም፡ዅሉ ፡በንጉሡ፡ዦሮ፡ተናገሩ።
21፤ንጉሡም፡ክርታሱን፡ያመጣ፡ዘንድ፡ይሁዲን፡ላከ፥ርሱም፡ከጸሓፊው፡ከኤሊሳማ፡ጓዳ፡ወሰደው፤ይሁዲም፡በንጉ ሡና፡በንጉሡ፡አጠገብ፡በቆሙት፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ዦሮ፡አነበበው።
22፤ንጉሡም፡በዘጠነኛው፡ወር፡በክረምት፡ቤት፡ተቀምጦ፡ነበር፥በፊቱም፡በምድጃ፡ውስጥ፡እሳት፡ይነድ፟፡ነበር ።
23፤ይሁዲም፡ሦስት፡ወይም፡አራት፡ዐምድ፡ያኽል፡ባነበበ፡ቍጥር፥ንጉሡ፡በካራ፡ቀደደው፤ክርታሱም፡በምድጃ፡ው ስጥ፡ባለው፡እሳት፡ፈጽሞ፡እስኪቃጠል፡ድረስ፡በምድጃ፡ውስጥ፡ወዳለው፡እሳት፡ጣለው።
24፤ንጉሡም፡ይህንም፡ቃል፡ዅሉ፡የሰሙ፡ባሪያዎቹ፡ዅሉ፡አልፈሩም፡ልብሳቸውንም፡አልቀደዱም።
25፤ነገር፡ግን፥ኤልናታንና፡ድላያ፡ገማርያም፡ክርታሱን፡እንዳያቃጥል፡ንጉሡን፡ለመኑት፥ርሱ፡ግን፡አልሰማቸ ውም።
26፤ንጉሡም፡ጸሓፊውን፡ባሮክንና፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡ይይዙ፡ዘንድ፡የንጉሡን፡ልጅ፡ይረሕምኤልንና፡የዓዝር ኤልን፡ልጅ፡ሰራያን፡የዓብድኤልንም፡ልጅ፡ሰሌምያን፡አዘዘ፥እግዚአብሔር፡ግን፡ሰወራቸው።
27፤ንጉሡም፡ክርታሱንና፡ባሮክ፡ከኤርምያስ፡አፍ፡የጻፈውን፡ቃል፡ካቃጠለ፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
28፤ዳግመኛም፡ሌላ፡ክርታስ፡ውሰድ፥የይሁዳም፡ንጉሥ፡ኢዮአቄም፡ባቃጠለው፡ክርታስ፡ላይ፡የነበረውን፡የቀድሞ ውን፡ቃል፡ዅሉ፡ጻፍበት።
29፤የይሁዳንም፡ንጉሥ፡ኢዮአቄምን፡እንዲህ፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አንተ፦የባቢሎን፡ንጉሥ፡በ ርግጥ፡ይመጣል፡ይህችንም፡አገር፡ያፈርሳታል፡ከሰውና፡ከእንስሳም፡ባዶ፡ያደርጋታል፡ብለኽ፡ለምን፡ጻፍኽበት ፧ብለኽ፡ይህን፡ክርታስ፡አቃጥለኻል።
30፤ስለዚህም፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ስለ፡ኢዮአቄም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዳዊት፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀማጭ፡ አይኖርለትም፥ሬሳውም፡በቀን፡ለትኵሳት፡በሌሊትም፡ለውርጭ፡ይጣላል።
31፤ስለ፡ኀጢአታቸውም፡ርሱንና፡ዘሩን፡ባሪያዎቹንም፡እቀጣለኹ፤እነርሱም፡አልሰሙምና፡የተናገርኹባቸውን፡ክ ፉ፡ነገር፡ዅሉ፡በእነርሱ፡ላይና፡በኢየሩሳሌም፡በሚቀመጡ፡በይሁዳም፡ሰዎች፡ላይ፡አመጣለኹ።
ኤርምያስም፡ሌላ፡ክርታስ፡ወሰደ፡ለኔርያም፡ልጅ፡ለጸሓፊው፡ለባሮክ፡ሰጠው፤ርሱም፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮአቄም ፡በእሳት፡ያቃጠለውን፡የመጽሐፉን፡ቃል፡ዅሉ፡ከኤርምያስ፡አፍ፡ጻፈበት፥ደግሞም፡እንደ፡ቀድሞው፡ያለ፡ቃል፡ ብዙ፡ቃል፡ተጨመረበት።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡37።______________
ምዕራፍ፡37፤
1፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በይሁዳ፡ያነገሠው፡የኢዮስያስ፡ልጅ፡ሴዴቅያስ፡በኢዮአቄም፡ልጅ፡በኢኮን ያን፡ፋንታ፡ነገሠ።
2፤ርሱም፡ኾነ፡ባሪያዎቹ፡የአገሩም፡ሕዝብ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡እጅ፡የተናገረውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አ ልሰሙም።
3፤ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፦ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡እኛ፡ጸልይ፡ብሎ፡የሰሌምያን፡ልጅ፡ዮካልንና ፡ካህኑን፡የመዕሴያን፡ልጅ፡ሶፎንያስን፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡ላከ።
4፤ርሱንም፡በግዞት፡ቤት፡ገና፡አላገቡትም፡ነበርና፥ኤርምያስ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ይወጣና፡ይገባ፡ነበር።
5፤የፈርዖንም፡ሰራዊት፡ከግብጽ፡ወጣ፤ኢየሩሳሌምንም፡ከበ፟ዋት፡የነበሩ፡ከለዳውያን፡ይህን፡ወሬ፡በሰሙ፡ጊዜ ፡ከኢየሩሳሌም፡ተመለሱ።
6፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
7፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከእኔ፡ትጠይቁ፡ዘንድ፡የላካችኹን፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡እ ንዲህ፡በሉት፦እንሆ፥ሊረዳችኹ፡የወጣው፡የፈርዖን፡ሰራዊት፡ወደ፡አገሩ፡ወደ፡ግብጽ፡ይመለሳል።
8፤ከለዳውያንም፡ተመልሰው፡ይህችን፡ከተማ፡ይዋጓታል፡ይይዟትማል፡በእሳትም፡ያቃጥሏታል።
9፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አይኼዱምና፦ከለዳውያን፡በርግጥ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ይኼዳሉ፡ብላችኹ፡ራሳችኹን፡ አታታልሉ።
10፤እናንተም፡የሚዋጉትን፡የከለዳውያንን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ብትመቱት፡ኖሮ፥ከነርሱም፡የተወጉት፡ብቻ፡ቢቀሩ፡ኖ ሮ፥ዅሉ፡እያንዳንዱ፡በድንኳኑ፡ተነሥቶ፡ይህችን፡ከተማ፡በእሳት፡ባቃጠሏት፡ነበር።
11፤የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ከፈርዖን፡ሰራዊት፡ፊት፡የተነሣ፡ከኢየሩሳሌም፡በተመለሰ፡ጊዜ፥
12፤ኤርምያስ፡በሕዝቡ፡መካከል፡የርስቱን፡ዕድል፡ፈንታ፡ከዚያ፡ይቀበል፡ዘንድ፡ወደብንያም፡አገር፡ሊኼድ፡ከ ኢየሩሳሌም፡ወጣ።
13፤በብንያምም፡በር፡በነበረ፡ጊዜ፡የሐናንያ፡ልጅ፡የሰሌምያ፡ልጅ፡የሪያ፡የተባለ፡የዘበኛዎች፡አለቃ፡በዚያ ፡ነበረ፤ርሱም፦ወደ፡ከለዳውያን፡መኰብለልኽ፡ነው፡ብሎ፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡ያዘው።
14፤ኤርምያስም፦ሐሰት፡ነው፤ወደ፡ከለዳውያን፡መኰብለሌ፡አይደለም፡አለ፤ርሱ፡ግን፡አልሰማውም፥የሪያም፡ኤር ምያስን፡ይዞ፡ወደ፡አለቃዎች፡አመጣው።
15፤አለቃዎችም፡ተቈጥተው፡ኤርምያስን፡መቱት፥የጸሓፊውንም፡የዮናታንን፡ቤት፡የግዞት፡ቤት፡አድርገውት፡ነበ ርና፥በዚያ፡አኖሩት።
16፤ኤርምያስም፡ወደጕድጓድ፡ቤት፡ወደ፡ጓዳዎቹ፡ገባ፤ኤርምያስም፡በዚያ፡ብዙ፡ቀን፡ከተቀመጠ፡በዃላ፥
17፤ንጉሡ፡ሴዴቅያስ፡ልኮ፡አስመጣው፥ንጉሡም፡በቤቱ።በእውኑ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የኾነ፡ቃል፡አለን፧ብሎ ፡በቈይታ፡ጠየቀው።ኤርምያስም፦አዎን፡አለ።ደግሞም፦በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አልፈኽ፡ትሰጣለኽ፡አለ።
18፤ኤርምያስም፡ደግሞ፡ንጉሡን፡ሴዴቅያስን፡እንዲህ፡አለው፦በግዞት፡ቤት፡የጣላችኹኝ፡አንተን፡ወይስ፡ባሪያ ዎችኽን፡ወይስ፡ሕዝብኽን፡ምን፡በድያችኹ፡ነው፧
19፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡በእናንተና፡በዚች፡አገር፡አይመጣባችኹም፡ብለው፡ትንቢት፡ይናገሩላችኹ፡የነበሩ፡ነቢያ ታችኹ፡ወዴት፡አሉ፧
20፤ንጉሡ፡ጌታዬ፡ሆይ፥እንድትሰማኝ፡አኹን፡እለምንኻለኹ፤እባክኽ፥ልመናዬ፡ወዳንተ፡ይድረስ፤በዚያ፡እንዳል ሞት፡ወደጸሓፊው፡ወደዮናታን፡ቤት፡አትመልሰኝ።
21፤ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፡አዘዘ፥ኤርምያስንም፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡አኖሩት፥እንጀራም፡ዅሉ፡ከከተማ፡እስኪ ጠፋ፡ድረስ፡ዕለት፡ዕለት፡አንድ፡አንድ፡እንጀራ፡ከጋጋሪዎች፡መንገድ፡ይሰጡት፡ነበር።እንዲሁም፡ኤርምያስ፡ በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ተቀምጦ፡ነበር።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡38።______________
ምዕራፍ፡38፤
1፤ኤርምያስም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡የተናገረውን፡ቃል፡የማታን፡ልጅ፡ስፋጥያስ፥የጳስኮርም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፥የሰሌም ያም፡ልጅ፡ዮካል፥የመልክያም፡ልጅ፡ጳስኮር፡ሰሙ።
2፤ኤርምያስ፡እንዲህ፡ብሏልና፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚች፡ከተማ፡የሚቀመጥ፡በሰይፍና፡በራብ፡በቸነ ፈርም፡ይሞታል፤ወደ፡ከለዳውያን፡ግን፡የሚወጣ፡በሕይወት፡ይኖራል፥ነፍሱም፡እንደ፡ምርኮ፡ትኾንለታለች፥በሕ ይወትም፡ይኖራል።
3፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ይህች፡ከተማ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡እጅ፡በርግጥ፡ትሰጣለች፥ርሱም፡ይ ይዛታል።
4፤አለቃዎቹም፡ንጉሡን፦ይህን፡የመሰለውን፡ቃል፡ሲነግራቸው፡በዚች፡ከተማ፡የቀሩትን፡የሰልፈኛዎቹን፡እጅ፡የ ሕዝቡንም፡ዅሉ፡እጅ፡ያደክማልና፥ይህ፡ሰው፡እንዲገደል፡እንለምንኻለን፤ይህ፡ሰው፡ክፋትን፡እንጂ፡ለዚህ፡ሕ ዝብ፡ሰላምን፡አይመኝለትምና፡አሉት።
5፤ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፦ንጉሡ፡በእናንተ፡ላይ፡ምንም፡ሊያደርግ፡አይችልምና፥እንሆ፥በእጃችኹ፡ነው፡አለ።
6፤ኤርምያስንም፡ወሰዱት፡በግዞት፡ቤቱም፡አደባባይ፡ወደነበረው፡ወደንጉሡ፡ልጅ፡ወደመልክያ፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡ ጣሉት፤ኤርምያስንም፡በገመድ፡አወረዱት።በጕድጓድም፡ውስጥ፡ጭቃ፡እንጂ፡ውሃ፡አልነበረበትም፤ኤርምያስም፡ወ ደ፡ጭቃው፡ውስጥ፡ገባ።
7፤በንጉሡም፡ቤት፡የነበረው፡ጃን፡ደረባ፡ኢትዮጵያዊው፡አቢሜሌክ፡ኤርምያስን፡በጕድጓዱ፡ውስጥ፡እንዳኖሩት፡ ሰማ።ንጉሡም፡በብንያም፡በር፡ተቀምጦ፡ነበር።
8፤አቢሜሌክም፡ከንጉሡ፡ቤት፡ወጥቶ፡ንጉሡን፡እንዲህ፡አለው፦
9፤ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥እነዚህ፡ሰዎች፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡በጕድጓድ፡ውስጥ፡በመጣላቸው፡በርሱ፡ላይ፡በማድረ ጋቸው፡ዅሉ፡ክፉ፡አድርገዋል፤በከተማዪቱም፡ውስጥ፡እንጀራ፡ስለሌለ፡በዚያ፡በራብ፡ይሞታል።
10፤ንጉሡም፡ኢትዮጵያዊውን፡አቢሜሌክም፦ከአንተ፡ጋራ፡ሠላሳ፡ሰዎች፡ከዚህ፡ውሰድ፥ነቢዩም፡ኤርምያስ፡ሳይሞ ት፡ከጕድጓድ፡አውጣው፡ብሎ፡አዘዘው።
11፤አቢሜሌክም፡ከርሱ፡ጋራ፡ሰዎችን፡ይዞ፡ኼደ፥ከቤተ፡መዛግብቱም፡በታች፡ወደነበረው፡ወደንጉሥ፡ቤት፡ገባ፥ ከዚያም፡አሮጌ፡ጨርቅና፡ዕላቂ፡ልብስ፡ወሰደ፥ወደ፡ኤርምያስም፡ወደ፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡በገመድ፡አወረደው።
12፤ኢትዮጵያዊውም፡አቢሜሌክ፡ኤርምያስን፦ይህን፡አሮጌ፡ጨርቅና፡ዕላቂውን፡ልብስ፡በብብትኽ፡ከገመዱ፡በታች ፡አድርግ፡አለው፤ኤርምያስም፡እንዲሁ፡አደረገ።
13፤ኤርምያስንም፡በገመዱ፡ጐተቱት፡ከጕድጓድም፡አወጡት፥ኤርምያስም፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ተቀመጠ።
14፤ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፡ልኮ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደነበረው፡ወደ፡ሦስተኛው፡መግቢያ፡ወደ፡ርሱ፡ነቢዩን፡ኤ ርምያስን፡አስመጣው፤ንጉሡም፡ኤርምያስን፦አንዲት፡ነገር፡እጠይቅኻለኹ፤ምንም፡አትሸሽገኝ፡አለው።
15፤ኤርምያስም፡ሴዴቅያስን፦ብነግርኽ፡በእውኑ፡አትገድለኝምን፧ብመክርኽም፡አትሰማኝም፡አለው።
16፤ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፦ይህችን፡ነፍስ፡የፈጠረልን፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! አልገድልኽም፥ነፍስኽንም፡ለሚሹ፡ለእነዚህ፡ሰዎች፡እጅ፡አሳልፌ፡አልሰጥኽም፡ብሎ፡በቈይታ፡ለኤርምያስ፡ማለ ።
17፤ኤርምያስም፡ሴዴቅያስን፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደባቢሎ ን፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ብትወጣ፥ነፍስኽ፡በሕይወት፡ትኖራለች፡ይህችም፡ከተማ፡በእሳት፡አትቃጠልም፤አንተም፡ቤ ትኽም፡በሕይወት፡ትኖራላችኹ።
18፤ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ባትወጣ፡ግን፥ይህች፡ከተማ፡በከለዳውያን፡እጅ፡ትሰጣለች፥በእሳትም፡ያቃጥ ሏታል፡አንተም፡ከእጃቸው፡አታመልጥም፡አለው።
19፤ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፡ኤርምያስን፦ወደ፡ከለዳውያን፡በኰበለሉት፡በአይሁድ፡እጅ፡አሳልፈው፡ይሰጡኛል፡እነር ሱም፡ያፌዙብኛል፡ብዬ፡እፈራለኹ፡አለው።
20፤ኤርምያስም፡እንዲህ፡አለው፦አሳልፈው፡አይሰጡኽም።እኔ፡የምነግርኽን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እባክኽ፥ስ ማ፤ይቀናኻል፥ነፍስኽም፡በሕይወት፡ትኖራለች።
21፤ትወጣ፡ዘንድ፡እንቢ፡ብትል፡ግን፥እግዚአብሔር፡ያሳየኝ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
22፤እንሆ፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡የቀሩትን፡ሴቶች፡ዅሉ፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ያወጣሉ፤እነዚያም፡ሴቶ ች፦ባለሟሎችኽ፡አታ፟ለ፟ውኻል፡አሸንፈውኽማል፤እግሮችኽ፡ግን፡አኹን፡በጭቃ፡ውስጥ፡ከገቡ፡እነርሱ፡ከአንተ ፡ወደ፡ዃላ፡ተመልሰዋል፡ይላሉ።
23፤ሚስቶችኽንና፡ልጆችኽንም፡ዅሉ፡ወደ፡ከለዳውያን፡ያወጣሉ፤አንተም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ትያዛለኽ፡እን ጂ፡ከእጃቸው፡አታመልጥም፤ይህችም፡ከተማ፡በእሳት፡ትቃጠላለች።
24፤ሴዴቅያስም፡ኤርምያስን፡እንዲህ፡አለው፦ይህን፡ቃል፡ማንም፡አይወቅ፥አንተም፡አትሞትም።
25፤አለቃዎቹ፡ግን፡እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡እንደ፡ተነጋገርኹ፡ቢሰሙ፥ወዳንተም፡መጥተው፦ለንጉሡ፡ያልኸውን፡ንገ ረን፡አትሸሽገንም፥እኛም፡አንገድልኽም፤ደግሞ፡ንጉሡ፡ያለኽን፡ንገረን፡ቢሉኽ፥አንተ፦
26፤በዚያ፡እሞት፡ዘንድ፡ወደዮናታን፡ቤት፡አትመልሰኝ፡ብዬ፡በንጉሡ፡ፊት፡ለመንኹ፡በላቸው።
27፤አለቃዎቹም፡ዅሉ፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጥተው፡ጠየቁ፥ንጉሡም፡እንዳዘዘው፡እንደዚህ፡ቃል፡ዅሉ፡ነገራቸው።ነ ገሩም፡አልተሰማምና፡ከርሱ፡ጋራ፡መነጋገርን፡ተው።
28፤ኢየሩሳሌም፡እስከተያዘችበት፡ቀን፡ድረስ፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ተቀመጠ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡39።______________
ምዕራፍ፡39፤
1፤ኢየሩሳሌምም፡በተያዘች፡ጊዜ፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡የባቢሎን፡ ንጉሥ፡ናቡከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጥተው፡ከበቧት፤
2፤በሴዴቅያስም፡በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡በአራተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዘጠነኛው፡ቀን፡ከተማዪቱ፡ተሰበረች።
3፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ዅሉ፥ኤርጌል፡ሳራስር፥ሳምጋርናቦ፥ሠርሰኪም፥ራፌስ፥ኤርጌል፡ሳራስር፥ራብማ ግ፥ከቀሩት፡ከባቢሎን፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ጋራ፡ገብተው፡በመካከለኛው፡በር፡ውስጥ፡ተቀመጡ።
4፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡ሰልፈኛዎቹም፡ዅሉ፡ባይዋቸው፡ጊዜ፡ኰበለሉ፥በሌሊትም፡በንጉሡ፡አትክልት፡መንገ ድ፡በኹለቱ፡ቅጥር፡መካከል፡ከነበረው፡ደጅ፡ከከተማዪቱ፡ወጡ፤በዐረባም፡መንገድ፡ወጡ።
5፤የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ተከታተላቸው፥ሴዴቅያስንም፡በኢያሪኮ፡ሜዳ፡አገኙት፤ይዘውም፡በሐማት፡ምድር፡ወዳ ለችው፡ወደ፡ሪብላ፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ናቡከደነጾር፡አመጡት፡ርሱም፡ፍርድን፡በርሱ፡ላይ፡ተናገረ።
6፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የሴዴቅያስን፡ልጆች፡በዐይኑ፡ፊት፡በሪብላ፡ገደላቸው፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የይሁዳን፡ከ በርቴዎች፡ዅሉ፡ገደለ።
7፤የሴዴቅያስንም፡ዐይን፡አወጣ፥ወደ፡ባቢሎንም፡ይወስደው፡ዘንድ፡በሰንሰለት፡አሰረው።
8፤ከለዳውያንም፡የንጉሡንና፡የሕዝቡን፡ቤቶች፡በእሳት፡አቃጠሉ፥የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡አፈረሱ።
9፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በከተማዪቱ፡የቀሩትን፡ሕዝብ፡ወደ፡ርሱም፡የኰበለሉትን፡ሰዎች፡የቀረውን ም፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ወደ፡ባቢሎን፡ማረካቸው።
10፤አንዳች፡ከሌላቸው፡ከሕዝቡ፡ድኻዎች፡ግን፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በይሁዳ፡አገር፡ተዋቸው፥የወይ ኑን፡ቦታና፡ዕርሻውን፡በዚያን፡ጊዜ፡ሰጣቸው።
11-12፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ስለ፡ኤርምያስ፦ውሰደውና፡በመልካም፡ተመልከተው፥የሚሻውንም፡ነገር፡ አድርግለት፡እንጂ፡ክፉን፡ነገር፡አታድርግበት፡ብሎ፡የዘበኛዎቹን፡አለቃ፡ናቡዘረዳንን፡አዘዘ።
13፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ላከ፥ናቡሽዝባንም፡ራፋስቂስም፡ኤርጌል፡ሳራስርም፡ራብማግም፡የባቢሎን ም፡ንጉሥ፡ዋና፡ዋና፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ላኩ፤
14፤ኤርምያስንም፡ከግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡አወጡት፥ወደ፡ቤቱም፡ይወስደው፡ዘንድ፡ለሳፋን፡ልጅ፡ለአኪቃም፡ል ጅ፡ለጎዶልያስ፡ሰጡት፤እንዲህም፡በሕዝብ፡መካከል፡ተቀመጠ።
15፤በግዞትም፡ቤት፡አደባባይ፡ታስሮ፡ሳለ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ፦
16፤ኺድ፡ለኢትዮጵያዊውም፡ለአቢሜሌክ፡እንዲህ፡በለው፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እ ንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ለበጎነት፡ሳይኾን፡ለክፋት፡ቃሌን፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡አመጣለኹ፤በዚያም፡ቀን፡በፊትኽ ፡ይፈጸማል።
17፤በዚያ፡ቀን፡አድንኻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በምትፈራቸው፡ሰዎች፡እጅ፡አልሰጥኽም።
18፤ፈጽሜ፡አድንኻለኹ፡ነፍስኽም፡እንደ፡ምርኮ፡ትኾንልኻለች፡እንጂ፡በሰይፍ፡አትወድቅም፥በእኔ፡ታምነኻልና ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡40።______________
ምዕራፍ፡40፤
1፤ወደ፡ባቢሎን፡በተማረኩት፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡መካከል፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በ ሰንሰለት፡አስሮ፡በወሰደው፡ጊዜ፡ከራማ፡ከለቀቀው፡በዃላ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል ፡ይህ፡ነው።
2፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ኤርምያስን፡ወሰደው፡እንዲህም፡አለው፦አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ክፉ፡ነገር፡በ ዚህ፡ስፍራ፡ላይ፡ተናገረ፤
3፤እግዚአብሔርም፡አመጣው፡እንደ፡ተናገረውም፡አደረገ፤በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ኀጢአት፡ሠርታችዃልና፥ቃሉንም ፡አልሰማችኹምና፡ይህ፡ነገር፡ኾነባችኹ።
4፤አኹንም፥እንሆ፥በእጅኽ፡ካለችው፡ሰንሰለት፡ዛሬ፡ፈታኹኽ።ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ባቢሎን፡መምጣት፡መልካም፡መስ ሎ፡ቢታይኽ፥ና፥እኔም፡በመልካም፡አይኻለኹ፤ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ባቢሎን፡መምጣት፡መልካም፡መስሎ፡ባይታይኽ፡ግ ን፥ተቀመጥ፤እንሆ፥አገሪቱ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ናት፤ትኼድ፡ዘንድ፡መልካም፡መስሎ፡ወደሚታይኽ፡ደስ፡ወደሚያሠኝኽ ም፡ስፍራ፡ኺድ።
5፤ርሱም፡ገና፡ሳይመለስ።የባቢሎን፡ንጉሥ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ላይ፡ወደሾመው፡ወደሳፋን፡ልጅ፡ወደአኪቃም፡ል ጅ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ተመለስ፥ከርሱም፡ጋራ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ተቀመጥ፤ወይም፡ትኼድ፡ዘንድ፡ደስ፡ወደሚያሠኝኽ ፡ስፍራ፡ኺድ፡አለው።የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ሥንቅና፡ስጦታ፡ሰጥቶ፡አሰናበተው።
6፤ኤርምያስም፡የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ወዳለበት፡ወደ፡ምጽጳ፡ኼደ፥ከርሱም፡ጋራ፡በአገሩ፡ውስጥ፡በቀሩት፡ ሕዝብ፡መካከል፡ተቀመጠ።
7፤በየሜዳውም፡የነበሩት፡የጭፍራ፡አለቃዎችና፡ሰዎቻቸው፡ዅሉ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን ፡በምድር፡ላይ፡እንደ፡ሾመ፥ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ልጆችንም፥ወደ፡ባቢሎን፡ያልተማረኩትን፡የምድርን፡ድኻዎች ፥እንዳስጠበቀ፡በሰሙ፡ጊዜ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፥
8፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናንና፡ዮናታን፥የተንሑሜትም፡ልጅ፡ሰራያ፥የነጦፋዊውም፡የዮፌ፡ልጆች፡የማዕካታዊውም፡ ልጅ፡ያእዛንያ፡ከሰዎቻቸው፡ጋራ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ወደ፡ምጽጳ፡መጡ።
9፤የሳፋንም፡ልጅ፡የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ለእነርሱና፡ለሰዎቻቸው፡እንዲህ፡ብሎ፡ማለ።ለከለዳውያን፡ትገዙ ፡ዘንድ፡አትፍሩ፤በምድር፡ተቀመጡ፡ለባቢሎንም፡ንጉሥ፡ተገዙ፥መልካምም፡ይኾንላችዃል።
10፤እኔም፥እንሆ፥ወደ፡እኛ፡በሚመጡት፡ከለዳውያን፡ፊት፡እቆም፡ዘንድ፡በምጽጳ፡እኖራለኹ፤እናንተ፡ግን፡ወይ ንንና፡የበጋ፡ፍሬ፡ዘይትንም፡አከማቹ፥በየዕቃችኹም፡ውስጥ፡ክተቱ፥በያዛችዃቸውም፡ከተማዎቻችኹ፡ተቀመጡ።
11፤በሞዐብም፡በዐሞንም፡ልጆች፡መካከል፡በኤዶምያስም፡በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡የነበሩ፡አይሁድ፡ዅሉ፡የባቢሎን ፡ንጉሥ፡የይሁዳን፡ቅሬታ፡እንዳስቀረ፥የሳፋንንም፡ልጅ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን፡በላያቸው፡እንደ፡ሾመ ው፡በሰሙ፡ጊዜ፥
12፤አይሁድ፡ዅሉ፡ከተሰደዱበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ተመለሱ፥ወደይሁዳም፡አገር፡ጎዶልያስ፡ወዳለበት፡ወደ፡ምጽጳ፡መ ጡ፥ወይንና፡የበጋንም፡ፍሬ፡እጅግ፡ብዙ፡አከማቹ።
13፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡በየሜዳውም፡የነበሩ፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ወደ፡ምጽጳ፡መጥተ ው፦
14፤የዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፡በዓሊስ፡ይገድልኽ፡ዘንድ፡የናታንያን፡ልጅ፡እስማኤልን፡እንደ፡ሰደደ፡ታውቃለኽን ፧አሉት።የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ግን፡አላመናቸውም።
15፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፦እባክኽ፥ልኺድ፤ማንም፡ሳያውቅ፡የናታንያን፡ልጅ፡እስማኤልን፡ልግደለው፤ወዳንተ ፡የተሰበሰቡ፡አይሁድ፡ዅሉ፡እንዲበተኑ፡የይሁዳም፡ቅሬታ፡እንዲጠፋ፡ነፍስኽን፡ስለ፡ምን፡ይገድላል፧ብሎ፡በ ምጽጳ፡በቈይታ፡ለጎዶልያስ፡ተናገረ።
16፤የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ግን፡የቃሬያን፡ልጅ፡ዮሐናንን፦በእስማኤል፡ላይ፡ሐሰት፡ተናግረኻልና፥ይህን፡ ነገር፡አታድርግ፡አለው።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡41።______________
ምዕራፍ፡41፤
1፤በሰባተኛውም፡ወር፡ከመንግሥት፡ወገንና፡ከንጉሡ፡ዋና፡ዋና፡አለቃዎች፡አንዱ፡የኤሊሳማ፡ልጅ፡የናታንያ፡ል ጅ፡እስማኤል፡ከዐሥር፡ሰዎች፡ጋራ፡ወደ፡ምጽጳ፡ወደአኪቃም፡ልጅ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡መጣ፤በዚያም፡በምጽጳ፡ባን ድ፡ላይ፡እንጀራ፡በሉ።
2፤የናታንያም፡ልጅ፡እስማኤል፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ዐሥሩ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡የሳፋንን፡ልጅ፡የአኪቃምን፡ ልጅ፡ጎዶልያስን፡በሰይፍ፡መቱ፥የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በአገሩ፡ላይ፡የሾመውን፡ገደሉ።
3፤እስማኤልም፡ከጎዶልያስ፡ጋራ፡በምጽጳ፡የነበሩትን፡አይሁድ፡ዅሉ፥በዚያም፡የተገኙትን፡የከለዳውያንን፡ሰል ፈኛዎች፡ዅሉ፡ገደላቸው።
4፤ጎዶልያስን፡ከገደለ፡በዃላ፡ማንም፡ሳያውቅ፡በኹለተኛው፡ቀን፥
5፤ጢማቸውን፡ላጭተው፡ልብሳቸውንም፡ቀደ፟ው፡ገላቸውንም፡ነጭተው፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ያቀርቡ፡ዘንድ፡የእ ኽል፡ቍርባንና፡ዕጣን፡በእጃቸው፡እየያዙ፥ሰማንያ፡ሰዎች፡ከሴኬምና፡ከሴሎ፡ከሰማርያም፡መጡ።
6፤የናታንያም፡ልጅ፡እስማኤል፡ከምጽጳ፡ወጥቶ፡እያለቀሰ፡ሊገናኛቸው፡ኼደ፤በተገናኛቸውም፡ጊዜ፦ወደአኪቃም፡ ልጅ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ኑ፡አላቸው።
7፤ወደከተማም፡መካከል፡በመጡ፡ጊዜ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡ሰዎች፡ገደሏቸው፥በጕድ ጓድም፡መካከል፡ጣሏቸው።
8፤በመካከላቸውም፡እስማኤልን፦በሜዳ፡የተሸሸገ፡ስንዴና፡ገብስ፡ዘይትና፡ማርም፡አለንና፡አትግደለን፡የሚሉት ፡ዐሥር፡ሰዎች፡ተገኙ።ርሱም፡ተዋቸው፥ከወንድሞቻቸውም፡ጋራ፡አልገደላቸውም።
9፤እስማኤልም፡ከጎዶልያስ፡ጋራ፡የገደላቸውን፡የሰዎች፡ሬሳ፡ዅሉ፡የጣለበት፡ጕድጓድ፡ንጉሡ፡አሣ፡የእስራኤል ን፡ንጉሥ፡ባኦስን፡ስለ፡ፈራ፡የሠራው፡ጕድጓድ፡ነበረ፤የናታንያም፡ልጅ፡እስማኤል፡የገደላቸውን፡ሞላበት።
10፤እስማኤልም፡በምጽጳ፡የነበረውን፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ዅሉ፥የንጉሡን፡ሴቶች፡ልጆች፡የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ና ቡዘረዳን፡ለአኪቃም፡ልጅ፡ለጎዶልያስ፡የሰጠውን፡በምጽጳ፡የቀሩትን፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ማረካቸው፤የናታንያም፡ልጅ ፡እስማኤል፡ማርኮ፡ወደዐሞን፡ልጆች፡ይኼድ፡ዘንድ፡ተነሣ።
11፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ያደረ ገውን፡ክፋት፡ዅሉ፡በሰሙ፡ጊዜ፥
12፤ሰዎቹን፡ዅሉ፡ይዘው፡ከናታንያ፡ልጅ፡ከእስማኤል፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ኼዱ፥በገባዖንም፡ባለው፡በታላቁ፡ውሃ፡አጠ ገብ፡አገኙት።
13፤ከእስማኤልም፡ጋራ፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የቃሬያን፡ልጅ፡ዮሐናንን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩትን፡የጭፍራ፡ አለቃዎችን፡ዅሉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ደስ፡አላቸው።
14፤እስማኤልም፡ከምጽጳ፡የማረካቸው፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ዘወር፡ብለው፡ተመለሱ፥ወደቃሬያም፡ልጅ፡ወደ፡ዮሐናን፡ኼዱ ።
15፤የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ግን፡ከስምንት፡ሰዎች፡ጋራ፡ከዮሐናን፡አመለጠ፡ወደዐሞንም፡ልጆች፡ኼደ።
16፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን፡ በምጽጳ፡ከገደለው፡በዃላ፡ከናታንያ፡ልጅ፡ከእስማኤል፡ያስመለሷቸውን፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ዅሉ፥ከገባዖን፡ያስ መለሷቸውን፡ሰልፈኛዎች፥ሴቶችንም፥ልጆችንም፥ጃን፡ደረባዎችንም፥ወሰዱ፤
17፤ተነሥተውም፡ወደ፡ግብጽ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡በቤተ፡ልሔም፡አጠገብ፡ባለው፡በጌሮት፡ከመዓም፡ተቀመጡ፤
18፤እስማኤል፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡በአገሩ፡ላይ፡የሾመውን፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን፡ስለ፡ገደለው፡ከለዳው ያንን፡ፈርተዋልና።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡42።______________
ምዕራፍ፡42፤
1፤የጭፍራ፡አለቃዎችም፡ዅሉ፡የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡የሆሻያም፡ልጅ፡ያእዛንያ፡ሕዝብም፡ዅሉ፡ከታናሹ፡ዠምሮ ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ቀረቡ፥
2-3፤ነቢዩንም፡ኤርምያስን፦ዐይኖችኽ፡እንዳዩን፡ከብዙ፡ጥቂት፡ቀርተናልና፥ልመናችን፥እባክኽ፥በፊትኽ፡ትድረ ስ፤አምላክኽም፡እግዚአብሔር፡የምንኼድበትን፡መንገድና፡የምናደርገውን፡ነገር፡ያሳየን፡ዘንድ፡ስለ፡እኛ፥ስ ለዚህ፡ቅሬታ፡ዅሉ፥ወደ፡አምላክኽ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልይ፡አሉት።
4፤ነቢዩም፡ኤርምያስ፦ሰምቻችዃለኹ፤እንሆ፥እንደ፡ቃላችኹ፡ወደ፡አምላካችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እጸልያለኹ፤ እግዚአብሔርም፡የሚመልስላችኹን፡ዅሉ፡እነግራችዃለኹ፥ከእናንተም፡ምንም፡አልሸሽግም፡አላቸው።
5፤ኤርምያስንም፦አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ባንተ፡እጅ፡ወደ፡እኛ፡የላከውን፡ነገር፡ዅሉ፡ባናደርግ፥እግዚአብሔ ር፡በመካከላችን፡እውነተኛና፡ታማኝ፡ምስክር፡ይኹን።
6፤የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡በመስማታችን፡መልካም፡እንዲኾንልን፥መልካም፡ወይም፡ክፉ፡ቢኾን፥አ ንተን፡ወደ፡ርሱ፡የምንልክኽ፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እንሰማለን፡አሉት።
7፤ከዐሥር፡ቀን፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ።
8፤የቃሬያንም፡ልጅ፡ዮሐናንን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩትን፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላ ቁ፡ድረስ፡ሕዝቡንም፡ዅሉ፡ጠራ፥እንዲህም፡አላቸው፦
9፤ጸሎታችኹን፡በፊቱ፡አቀርብ፡ዘንድ፡ወደ፡ርሱ፡የላካችኹኝ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላ ል፦
10፤ስላደረግኹባችኹ፡ክፉ፡ነገር፡ተጸጽቻለኹና፡በዚች፡ምድር፡ብትቀመጡ፡እሠራችዃለኹ፡እንጂ፡አላፈርሳችኹም ፥እተክላችዃለኹ፡እንጂ፡አልነቅላችኹም።
11፤ከምትፈሩት፡ከባቢሎን፡ንጉሥ፡አትፍሩ፤አድናችኹ፡ዘንድ፡ከእጁም፡አስጥላችኹ፡ዘንድ፡እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ ፡ነኝና፡አትፍሩ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
12፤ርሱ፡እንዲምራችኹ፡ወደ፡አገራችኹም፡እንዲመልሳችኹ፡እኔ፡እምራችዃለኹ።
13፤እናንተ፡ግን፦በዚች፡ምድር፡አንቀመጥም፡ብትሉ፡የአምላካችኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ባትሰሙ፥
14፤እናንተም፦አይደለም፤ሰልፍ፡ወደማናይባት፡የመለከትም፡ድምፅ፡ወደማንሰማባት፡ወደማንራብባትም፡ወደግብጽ ፡ምድር፡እንኼዳለን፡በዚያም፡እንቀመጣለን፡ብትሉ፥
15፤እናንተ፡የይሁዳ፡ቅሬታ፡ሆይ፥አኹን፡እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊ ት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡ግብጽ፡ትገቡ፡ዘንድ፡በዚያም፡ትቀመጡ፡ዘንድ፡ፊታችኹን፡ብታቀኑ ፥
16፤የምትፈሩት፡ሰይፍ፡በዚያ፡በግብጽ፡ምድር፡ያገኛችዃል፥ስለ፡ርሱም፡የምትደነግጡበት፡ራብ፡በዚያ፡በግብጽ ፡ይደርስባችዃል፥በዚያም፡ትሞታላችኹ።
17፤ወደ፡ግብጽም፡ይገቡ፡ዘንድ፡በዚያም፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ፊታቸውን፡በሚያቀኑ፡ሰዎች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ይኾንባቸ ዋል፤በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ይሞታሉ፤እኔም፡ከማመጣባቸው፡ክፉ፡ነገር፡ማንም፡አይቀርም፥ማንም፡አያመ ልጥም።
18፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ቍጣዬና፡መዓቴ፡በኢየሩሳሌም፡በሚኖ ሩ፡ላይ፡እንደ፡ፈሰሰ፥እንዲሁ፡ወደ፡ግብጽ፡በገባችኹ፡ጊዜ፡መዓቴ፡ይፈስ፟ባችዃል፤እናንተም፡ለጥላቻና፡ለመ ደነቂያ፡ለመረገሚያና፡ለመሰደቢያ፡ትኾናላችኹ፥ይህንም፡ስፍራ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታዩትም።
19፤እናንተ፡የይሁዳ፡ቅሬታ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፦ወደ፡ግብጽ፡አትግቡ፡ብሎ፡ተናግሮባችዃልና፥ዛሬ፡እንዳስጠነ ቀቅዃችኹ፡በርግጥ፡ዕወቁ።
20፤እናንተ፦ስለ፡እኛ፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልይ፥አምላካችንም፡እግዚአብሔር፡የሚናገርኽን ፡ዅሉ፡ንገረን፡እኛም፡እናደርገዋለን፡ብላችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡አምላካችኹ፡ልካችኹኝ፡ነበርና፥ራሳ ችኹን፡አታላ፟ችዃል።
21፤እኔም፡ዛሬ፡ነግሬያችዃለኹ፥ወደ፡እናንተም፡በላከኝ፡ነገር፡ዅሉ፡የአምላካችኹን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ አልሰማችኹም።
22፤አኹንም፡ኼዳችኹ፡እንድትቀመጡ፡በወደዳችኹበት፡ስፍራ፡በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡እንድትሞቱ፡በርግጥ ፡ዕወቁ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡43።______________
ምዕራፍ፡43፤
1፤የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ዅሉ፥ለእነርሱ፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡የላከውን፡ይህን፡ቃል፡ዅ ሉ፥ኤርምያስ፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡መናገርን፡በፈጸመ፡ጊዜ፥
2፤የሆሻያ፡ልጅ፡ዐዛርያስ፡የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡ትዕቢተኛዎችም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ኤርምያስን፦ሐሰት፡ተናግረኻ ል፤አምላካችን፡እግዚአብሔር፦በዚያ፡ትቀመጡ፡ዘንድ፡ወደ፡ግብጽ፡አትግቡ፡ብሎ፡አላ፟ከኽም፤
3፤ነገር፡ግን፥ከለዳውያን፡እንዲገድሉን፡ወደ፡ባቢሎንም፡እንዲማርኩን፡በእጃቸው፡አሳልፈኽ፡ትሰጠን፡ዘንድ፡ የኔርያ፡ልጅ፡ባሮክ፡በላያችን፡ላይ፡አነሣሥቶኻል፡አሉት።
4፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡የጭፍራ፡አለቃዎችም፡ዅሉ፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡በይሁዳ፡ምድር፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡የእግዚአ ብሔርን፡ቃል፡አልሰሙም።
5፤የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡የጭፍራ፡አለቃዎችም፡ዅሉ፡በይሁዳ፡ምድር፡ለመቀመጥ፡ከተሰደዱባቸው፡ከአሕዛብ፡ዅ ሉ፡የተመለሱትን፡የይሁዳን፡ቅሬታ፡ዅሉ፥
6፤ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ልጆችንም፡የንጉሡንም፡ሴቶች፡ልጆች፥የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ከሳፋን፡ልጅ፡ ከአኪቃም፡ልጅ፡ከጎዶልያስ፡ጋራ፡የተዋቸውን፡ሰዎች፡ዅሉ፥ነቢዩንም፡ኤርምያስን፡የኔርያንም፡ልጅ፡ባሮክን፡ ወሰዱ፤
7፤የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡አልሰሙምና፡ወደግብጽ፡ምድር፡ገቡ፥እስከ፡ጣፍናስ፡ድረስ፡መጡ።
8፤በጣፍናስም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
9፤ታላላቆችን፡ድንጋዮች፡በእጅኽ፡ውሰድ፥የይሁዳም፡ሰዎች፡እያዩ፡በጣፍናስ፡ባለው፡በፈርዖን፡ቤት፡ደጅ፡መግ ቢያ፡ሸሽጋቸው፤
10፤እንዲህም፡በላቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ልኬ፡ባሪያ ዬን፡የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡አመጣለኹ፥ዙፋኑንም፡እኔ፡በሸሸግዃቸው፡በእነዚህ፡ድንጋዮች፡ላይ፡አ ኖራለኹ፤ርሱም፡ማለፊያውን፡ድንኳኑን፡በላያቸው፡ይዘረጋል።
11፤መጥቶም፡የግብጽን፡ምድር፡ይመታል፥ለሞትም፡የሚኾነውን፡ለሞት፥ለምርኮም፡የሚኾነውን፡ለምርኮ፥ለሰይፍም ፡የሚኾነውን፡ለሰይፍ፡አሳልፎ፡ይሰጣል።
12፤በግብጽም፡አማልክት፡ቤቶች፡እሳትን፡ያነዳ፟ል፡ያቃጥላቸውማል፡ይማርካቸውማል፤እረኛም፡ደበሎውን፡እንደ ሚደርብ፡እንዲሁ፡የግብጽን፡አገር፡ይደርባል፤ከዚያም፡በሰላም፡ይወጣል።
13፤በግብጽም፡ምድር፡ያለውን፡የሄልዮቱን፡ከተማ፡ሐውልቶች፡ይሰብራል፥የግብጽንም፡አማልክት፡ቤቶች፡በእሳት ፡ያቃጥላል።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡44።______________
ምዕራፍ፡44፤
1፤በግብጽ፡ምድር፡በሚግዶልና፡በጣፍናስ፡በሜምፎስም፡በጳትሮስም፡አገር፡ስለተቀመጡ፡አይሁድ፡ዅሉ፡ወደ፡ኤር ምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ ፡ያመጣኹትን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አይታችዃል፤እንሆ፥ዛሬ፡ባድማ፡ኾነዋል፥የሚቀመጥባቸውም፡የለም።
3፤ይህም፡የኾነው፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፡ስላደረጉት፡ክፋት፥ለማያውቋቸውም፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ያጥኑ፡ዘንድ፡ያ መልኳቸውም፡ዘንድ፡ስለ፡ኼዱ፡ነው።
4፤በማለዳም፡ተነሥቼ፡ባሪያዎቼን፡ነቢያትን፡ዅሉ፡ሰደድኹባችኹና፦እንደዚህ፡እንደ፡ጠላኹት፡ያለ፡ርኩስ፡ነገ ር፡አታድርጉ፡አልዃችኹ።
5፤ነገር፡ግን፥አልሰሙም፡ከክፋታቸውም፡ተመልሰው፡ለሌላዎች፡አማልክት፡እንዳያጥኑ፡ዦሯቸውን፡አላዘነበሉም።
6፤ስለዚህ፥መዓቴና፡ቍጣዬ፡ፈሰሱ፥በይሁዳም፡ከተማዎችና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ነደዱ፤ዛሬም፡እንደኾነው፡ ፈረሱ፡ባድማም፡ኾኑ።
7፤አኹንም፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከይሁዳ፡ወገን፡ቅሬታ፡እን ዳይቀርላችኹ፥ወንድንና፡ሴትን፥ብላቴናንና፡ሕፃንን፡ከመካከላችኹ፡ታጠፉ፡ዘንድ፡ይህን፡ታላቅ፡ክፋት፡በራሳ ችኹ፡ላይ፡ለምን፡ታደርጋላችኹ፧
8፤ሰውነታችኹንም፡ታጠፉ፡ዘንድ፡በምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡መረገሚያና፡መሰደቢያ፡ትኾኑ፡ዘንድ፥ለመቀ መጥ፡በገባችኹባት፡በግብጽ፡ምድር፡ለሌላዎች፡አማልክት፡በማጠናችኹ፡በእጃችኹ፡ሥራ፡ለምን፡ታስቈጡኛላችኹ፧
9፤በእውኑ፡በይሁዳ፡ምድርና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ያደረጉትን፡የአባቶቻችኹን፡ክፋት፥የይሁዳንም፡ነገሥታ ት፡ክፋት፥የሚስቶቻቸውንም፡ክፋት፥የእናንተንም፡ክፋት፥የሚስቶቻችኹንም፡ክፋት፡ረስታችኹታልን፧
10፤እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡አልተዋረዱም፡አልፈሩምም፥በእናንተና፡በአባቶቻችኹም፡ፊት፡ባኖርኹት፡ሕጌና፡ሥርዐቴ ፡አልኼዱም።
11፤ስለዚህም፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይሁዳን፡ዅሉ፡አጠፋ ፡ዘንድ፡ፊቴን፡ለክፋት፡በላያችኹ፡አደርጋለኹ።
12፤ወደ፡ግብጽም፡ይገቡ፡ዘንድ፡በዚያም፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ፊታቸውን፡ያቀኑትን፡የይሁዳን፡ቅሬታ፡እወስዳለኹ፥ ዅሉም፡ይጠፋሉ፥በግብጽም፡ምድር፡ይወድቃሉ፤በሰይፍና፡በራብ፡ይጠፋሉ፤ከታናሹም፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ ፡በሰይፍና፡በራብ፡ይሞታሉ፤ለጥላቻና፡ለመደነቂያ፡ለመረገሚያና፡ለመሰደቢያ፡ይኾናሉ።
13፤ኢየሩሳሌምንም፡እንደ፡ቀጣኹ፥እንዲሁ፡በግብጽ፡ምድር፡የሚኖሩትን፡በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡እቀጣለ ኹ።
14፤በዚያ፡ለመቀመጥ፡ወደግብጽ፡ምድር፡ከኼዱ፥ወደይሁዳ፡አገር፡ተመልሰው፡በዚያ፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ከሚወዱ፡ከ ይሁዳ፡ቅሬታ፡ወገን፡የሚያመልጥና፡የሚቀር፡ወደዚያም፡የሚመለስ፡የለም፤ከሚያመልጥም፡በቀር፡ማንም፡አይመለ ስም።
15፤ሚስቶቻቸውም፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ማጠናቸውን፡ያወቁ፡ሰዎች፡ዅሉ፡በዚያም፡የቆሙ፡ሴቶች፡ዅሉ፥በግብጽ፡ ምድር፡በጳትሮስ፡የተቀመጡ፡ሕዝብ፡ዅሉ፥ታላቅ፡ጉባኤ፡ኾነው፡ለኤርምያስ፡መለሱለት፡እንዲህም፡አሉ።
16፤አንተ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡የነገርኸንን፡ቃል፡አንሰማኽም።
17፤ነገር፡ግን፥እኛና፡አባቶቻችን፡ነገሥታታችንም፡አለቃዎቻችንም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡በኢየሩሳሌም፡አደባባ ይ፡እናደርገው፡እንደ፡ነበረ፥ለሰማይ፡ንግሥት፡እናጥን፡ዘንድ፡የመጠጥንም፡ቍርባን፡እናፈስ፟ላት፡ዘንድ፡ከ አፋችን፡የወጣውን፡ቃል፡ዅሉ፡በርግጥ፡እናደርጋለን፤በዚያን፡ጊዜም፡እንጀራ፡እንጠግብ፡ነበር፥መልካምም፡ይ ኾንልን፡ክፉም፡አናይም፡ነበር።
18፤ለሰማይ፡ንግሥት፡ማጠንን፥ለርሷም፡የመጠጥን፡ቍርባን፡ማፍሰስን፡ከተውን፡ወዲህ፡ግን፥እኛ፡በዅሉ፡ነገር ፡ተቸግረናል፥በሰይፍና፡በራብ፡አልቀናል።
19፤እኛስ፡ለሰማይ፡ንግሥት፡ባጠን፟ላት፡የመጠጥንም፡ቍርባን፡ባፈሰስንላት፡ጊዜ፥በእውኑ፡ያለባሎቻችን፡ምስ ሏን፡ለማብጀት፡ዕንጐቻ፡አድርገንላት፡ኖሯልን፧የመጠጥንም፡ቍርባን፡አፍሰ፟ንላት፡ኖሯልን፧
20፤ኤርምያስም፡ይህን፡ቃል፡ለመለሱለት፡ሕዝብ፡ዅሉ፥ለወንዶቹና፡ለሴቶቹ፡ለሕዝቡም፡ዅሉ፥መለሰላቸው፡እንዲ ህም፡አለ።
21፤እናንተና፡አባቶቻችኹ፡ነገሥታታችኹም፡አለቃዎቻችኹም፡የምድርም፡ሕዝብ፡በይሁዳ፡ከተማዎችና፡በኢየሩሳሌ ም፡አደባባይ፡ያጠናችኹትን፡ዕጣን፡እግዚአብሔር፡ያሰበው፡በልቡም፡ያኖረው፡አይደለምን፧
22፤እግዚአብሔርም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡የሥራችኹን፡ክፋትና፡ያደረጋችኹትን፡ርኵሰት፡ይታገሥ፡ዘንድ፡አልቻለ ም፤ስለዚህ፥ምድራችኹ፡ባድማ፣መደነቂያም፣መረገሚያም፡ኾናለች፥ዛሬም፡እንደ፡ኾነ፡የሚኖርባት፡የለም።
23፤ስላጠናችኹ፥በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ስለ፡በደላችኹ፥የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ስላልሰማችኹ፥በሕጉና፡በሥር ዐቱም፡በምስክሩም፡ስላልኼዳችኹ፥ስለዚህ፡ዛሬ፡እንደ፡ኾነ፡ይህች፡ክፉ፡ነገር፡አግኝታችዃለች።
24፤ኤርምያስም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡ለሴቶቹም፡ዅሉ፡እንዲህ፡አለ፦በግብጽ፡ምድር፡የምትኖሩ፡ይሁዳ፡ዅሉ፥የእግዚአ ብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
25፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተና፡ሚስቶቻችኹ፡በአፋችኹ።ለሰ ማይ፡ንግሥት፡እናጥን፡ዘንድ፡የመጠጥንም፡ቍርባን፡እናፈስ፟ላት፡ዘንድ፡የተሳልነውን፡ስእለታችንን፡በርግጥ ፡እንፈጽማለን፡አላችኹ፡በእጃችኹም፡አደረጋችኹት፤እንግዲህ፡ስእለታችኹን፡አጽኑ፡ስእለታችኹንም፡ፈጽሙ።
26፤እናንተ፡በግብጽ፡ምድር፡የምትኖሩ፡ይሁዳ፡ዅሉ፥ስለዚህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ ፡በሚኖር፡በይሁዳ፡ሰው፡ዅሉ፡አፍ፡ስሜ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ።ሕያው፡እግዚአብሔርን! ተብሎ፡እንዳይጠራ፥እንሆ፥በታላቅ፡ስሜ፡ምያለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
27፤እንሆ፥ለመልካም፡ሳይኾን፡ለክፋት፡እተጋባቸዋለኹ፤በግብጽም፡ምድር፡ያሉት፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ዅሉ፡እስኪጠ ፉ፡ድረስ፡በሰይፍና፡በራብ፡ያልቃሉ።
28፤ከሰይፍም፡የሚያመልጡ፡ጥቂት፡ሰዎች፡ኾነው፡ከግብጽ፡ምድር፡ወደይሁዳ፡ምድር፡ይመለሳሉ፤ሊቀመጡም፡ወደግ ብጽ፡ምድር፡የገቡት፡የይሁዳ፡ቅሬታ፡ዅሉ፡ከእኔ፡ወይም፡ከነርሱ፡የማናችን፡ቃል፡እንዲጸና፡ያውቃሉ።
29፤ቃሌም፡በላያችኹ፡ለክፋት፡እንዲጸና፡ታውቁ፡ዘንድ፡በዚች፡ስፍራ፡እንድቀጣችኹ፡ምልክታችኹ፡ይህ፡ነው፥ይ ላል፡እግዚአብሔር።
30፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የይሁዳን፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስን፡ጠላቱ፡ለኾነው፡ነፍሱንም፡ለፈለገው፡ለባቢሎ ን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡እንደ፡ሰጠኹት፥እንዲሁ፥እንሆ፥የግብጹን፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ሖፍራን፡ ለጠላቶቹ፡ነፍሱንም፡ለሚፈልጉ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡45።______________
ምዕራፍ፡45፤
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፡የኔርያ፡ልጅ፡ባሮክ፡እነዚህን፡ቃሎች፡ከ ኤርምያስ፡አፍ፡በመጽሐፍ፡በጻፋቸው፡ጊዜ፥ነቢዩ፡ኤርምያስ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤ባሮክ፡ሆይ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይልኻል።
3፤አንተ፦እግዚአብሔር፡በሕመሜ፡ላይ፡ሐዘንን፡ጨምሮብኛልና፥ወዮልኝ! በልቅሶዬ፡ጩኸት፡ደክሜያለኹ፥ዕረፍትንም፡አላገኘኹም፡ብለኻል።
4፤እንዲህ፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የሠራኹትን፡አፈርሳለኹ፥የተከልኹትንም፡እነቅላለኹ፤ ይኸውም፡በምድር፡ዅሉ፡ነው።
5፤ለራስኽ፡ታላቅን፡ነገር፡ትፈልጋለኽን፧በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፥እንሆ፥ክፉ፡ነገርን፡አመጣለኹና፡አትፈልገ ው፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ነገር፡ግን፥በኼድኽበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ነፍስኽን፡እንደ፡ምርኮ፡አድርጌ፡እሰጥኻለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡46።______________
ምዕራፍ፡46፤
1፤ስለ፡አሕዛብ፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤ስለ፡ግብጽ፤በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡አጠገብ፡በከርከሚሽ፡ስለነበረው፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአ ቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ስለመታው፡ስለግብጽ፡ንጉሥ፡ስለፈርዖን፡ኒካዑ፡ሰራ ዊት።
3፤ጋሻ፡ጦር፡አዘጋጁ፡ወደ፡ሰልፍም፡ቅረቡ።
4፤ፈረሰኛዎች፡ሆይ፥ፈረሶችን፡ለጕሙና፡ውጡ፥ራስ፡ቍርንም፡ደፍታችኹ፡ቁሙ፤ጦርንም፡ሰንግሉ፡ጥሩርንም፡ልበሱ ።
5፤ፈርተው፡ወደ፡ዃላ፡ሲመለሱ፥ኀያላናቸውም፡ሲደበደቡ፡ወደ፡ዃላቸውም፡ሳይመለከቱ፡ፈጥነው፡ሲሸሹ፡ለምን፡አ የኹ፧በዚህና፡በዚያ፡ድንጋጤ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
6፤ፈጣኑ፡አያመልጥም፡ኀያሉም፡አይድንም፤በሰሜን፡በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡በኩል፡ተሰናክለው፡ወደቁ።
7፤ይህ፡እንደ፡ግብጽ፡ወንዝ፡የሚነሣ፥ውሃውም፡እንደ፡ወንዝ፡የሚናወጥ፡ማን፡ነው፧
8፤ግብጽ፡እንደ፡ግብጽ፡ወንዝ፡ይነሣል፡ውሃውም፡እንደ፡ወንዙ፡ይናወጣል፤ርሱም፦እነሣለኹ፡ምድርንም፡ዅሉ፡እ ከድናለኹ፤ከተማዎችንና፡የሚኖሩባቸውን፡አጠፋለኹ፡ብሏል።
9፤ፈረሶች፡ሆይ፥ውጡ፤ሠረገላዎችም፡ሆይ፥ንጐዱ፤ጋሻም፡የሚያነግቡ፡የኢትዮጵያና፡የፋጥ፡ኀያላን፥ቀስትንም፡ ይዘው፡የሚስቡ፡የሉድ፡ኀያላን፡ይውጡ።
10፤ያ፡ቀን፡ጠላቶቹን፡የሚበቀልበት፡የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡የበቀል፡ቀን፡ነው፤ሰይፍ፡በልቶ፡ይጠግ ባል፡በደማቸውም፡ይሰክራል፥ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡በሰሜን፡ምድር፡በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡አጠገብ፡መሥ ዋዕት፡አለውና።
11፤ድንግሊቱ፡የግብጽ፡ልጅ፡ሆይ፥ወደ፡ገለዓድ፡ውጪ፥የሚቀባንም፡መድኀኒት፡ውሰጂ፤መድኀኒትን፡ያበዛሽው፡በ ከንቱ፡ነው፤መዳን፡የለሽም።
12፤ኀያሉ፡በኀያሉ፡ላይ፡ተሰናክሎ፡ኹለቱ፡በአንድነት፡ወድቀዋልና፥አሕዛብ፡ጕስቍልናሽን፡ሰምተዋል፥ልቅሶሽ ም፡ምድርን፡ሞልቷታል።
13፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡እንዲመጣና፡የግብጽን፡ምድር፡እንዲመታ፡እግዚአብሔር፡ለነቢዩ፡ለኤርምያ ስ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
14፤በግብጽ፡ተናገሩ፥በሚግዶልም፡አሰሙ፥በሜምፎስና፡በጣፍናስ፡አሰሙ፤ሰይፍ፡በዙሪያኽ፡ያለውን፡በልቷልና፦ ተነሥ፡ተዘጋጅም፡በሉ።
15፤ኀይለኛዎችኽ፡ስለ፡ምን፡ተወገዱ፧እግዚአብሔር፡ስላደከማቸው፡አልቆሙም።
16፤ብዛታቸውም፡ተሰናከለ፥ሰውም፡አንዱ፡በአንዱ፡ላይ፡ወደቀ፤እነርሱም፦ተነሡ፥ከሚያስጨንቅ፡ሰይፍ፡ፊት፡ወ ደ፡ወገናችን፡ወደተወለድንባት፡ምድር፡እንመለስ፡አሉ።
17፤በዚያም፡የግብሥ፡ንጉሥ፡ፈርዖንን፦ሰዓቱን፡የሚያሳልፍ፡ጕረኛ፡ብለው፡ጠሩት።
18፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በተራራዎች፡መካከል፡እንዳለ፡እንደ፡ታቦር፥በባሕርም፡አጠገብ፡እንዳለ፡እንደ፡ቀርሜ ሎስ፥እንዲሁ፡በእውነት፡ይመጣል፥ይላል፡ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የተባለው፡ንጉሥ።
19፤አንቺ፡በግብጽ፡የምትቀመጪ፡ልጅ፡ሆይ፥ሜምፎስ፡ባድማ፡ትኾናለችና፥ትቃጠልማለችና፥የሚቀመጥባትም፡አይገ ኝምና፡ለምርኮ፡የሚኾን፡ዕቃ፡አዘጋጂ።
20፤ግብጽ፡የተዋበች፡ጊደር፡ናት፤ጥፋት፡ግን፡ይመጣል፥ከሰሜን፡በኩል፡ይመጣባታል።
21፤በርሷም፡ያሉ፡የተቀጠሩ፡ሠራተኛዎች፡እንደ፡ሰቡ፡ወይፈኖች፡ናቸው፤የጥፋታቸው፡ቀንና፡የመጐብኘታቸው፡ጊ ዜ፡መጥቶባቸዋልና፥ተመለሱ፥በአንድነትም፡ሸሹ፥አልቆሙምም።
22፤ከሰራዊትም፡ጋራ፡ይኼዳሉና፥ድምፅ፡እንደ፡እባብ፡ይተማ፟ል፤እንደ፡ዕንጨት፡ቈራጮችም፡በምሣር፡ይመጡባታ ል።
23፤ይቈጠሩ፡ዘንድ፡የማይቻሉትን፡የዱሯን፡ዛፎች፡ይቈርጣሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ከአንበጣ፡ይልቅ፡በዝተዋል ና፥ቍጥርም፡የላቸውምና።
24፤የግብጽ፡ልጅ፡ታፍራለች፤በሰሜን፡ሕዝብ፡እጅ፡ዐልፋ፡ትሰጣለች።
25፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የኖእ፡ዐሞንን፥ፈርዖንንም፥ግ ብጽንም፥አማልክቷንና፡ነገሥታቷንም፥ፈርዖንና፡በርሱም፡የሚታመኑትን፡እቀጣለኹ፤
26፤ነፍሳቸውንም፡በሚፈልጉ፡ሰዎች፡እጅ፥በባቢሎንም፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፥በባሪያዎቹም፡እጅ፡አሳልፌ ፡እሰጣቸዋለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡እንደ፡ቀድሞው፡ዘመን፡የሰው፡መኖሪያ፡ትኾናለች፥ይላል፡እግዚአብሔር።
27፤ነገር፡ግን፥አንተ፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡ሆይ፥አትፍራ፥አንተም፡እስራኤል፡ሆይ፥አትደንግጥ፤እንሆ፥አንተን፡ ከሩቅ፡ዘርኽንም፡ከተማረከባት፡ምድር፡አድናለኹ፤ያዕቆብም፡ተመልሶ፡ያርፋል፡ተዘልሎም፡ይቀመጣል፥ማንም፡አ ያስፈራውምም።
28፤አንተ፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡ሆይ፥እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡አትፍራ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤አንተንም፡ያሰደድ ኹባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡ፈጽሜ፡አጠፋለኹና፥አንተን፡ግን፡ፈጽሜ፡አላጠፋኽም፤በመጠን፡እቀጣኻለኹ፥ያለቅጣ ትም፡አልተውኽም።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡47።______________
ምዕራፍ፡47፤
1፤ፈርዖንም፡ጋዛን፡ሳይመታ፡ስለ፡ፍልስጥኤማውያን፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ቃል ፡ይህ፡ነው፦
2፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ውሃ፡ከሰሜን፡ይነሣል፡የሚያጥለቀልቅም፡ፈሳሽ፡ይኾናል፤በአገሪቱና፡ በመላዋ፡ዅሉ፥በከተማዪቱና፡በሚኖሩባት፡ላይ፡ይጐርፋል፤ሰዎቹም፡ይጮኻሉ፥በምድርም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ያለቅሳሉ ።
3፤ከኀይለኛዎች፡ፈረሶች፡ከኰቴያቸው፡መጠብጠብ፡ድምፅ፥ከሠረገላዎቹም፡መሸከርከር፥ከመንኰራኵሮቹም፡መትመም ፡የተነሣ፡አባቶች፡በእጃቸው፡ድካም፡ምክንያት፡ፊታቸውን፡መልሰው፡ወደ፡ልጆቻቸው፡አይመለከቱም።
4፤ይህም፡የሚኾነው፡ፍልስጥኤማውያንን፡ዅሉ፡ያጠፋ፡ዘንድ፡የቀሩትንም፡ረዳቶች፡ዅሉ፡ከጢሮስና፡ከሲዶና፡ይቈ ርጥ፡ዘንድ፡ስለሚመጣው፡ቀን፡ነው፤እግዚአብሔር፡ፍልስጥኤማውያንና፡የከፍቶርን፡ደሴት፡ቅሬታ፡ያጠፋልና።
5፤ቡሓነት፡በጋዛ፡ላይ፡መጥቷል፤አስቀሎና፡ጠፋች፤የዔናቅ፡ቅሬታዎች፡ሆይ! እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ገላችኹን፡ትነጫላችኹ፧
6፤አንተ፡የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡ሆይ፥ዝም፡የማትለው፡እስከ፡መቼ፡ነው፧ወደ፡ሰገባኽ፡ግባ፡ጸጥ፡ብለኽም፡ዕረ ፍ።
7፤እግዚአብሔር፡በአስቀሎናና፡በባሕር፡ዳር፡ላይ፡ትእዛዝ፡ሰጥቷልና፥በዚያም፡አዘጋጅቶታልና፥እንዴት፡ዝም፡ ትላለኽ፧
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡48።______________
ምዕራፍ፡48፤
1፤ስለ፡ሞዐብ፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ናባው፡ጠፍታለችና፡ወዮላት! ቂርያታይም፡ዐፍራለች፡ተይዛማለች፤ሚሥጋብ፡ዐፍራለች፡ደንግጣማለች።
2፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡የሞዐብ፡ትምክሕት፡የለም፤በሐሴቦን፡ላይ፦ኑ፥ሕዝብ፡እንዳትኾን፡እናጥፋት፡ብለው፡ክፉ ፡ነገር፡ዐስበውባታል።መድሜን፡ሆይ፥አንቺ፡ደግሞ፡ትጠፊያለሽ፡ሰይፍም፡ያሳድድሻል።
3፤መፍረስና፡ታላቅ፡ጥፋት፡የሚል፡የጩኸት፡ቃል፡ከሖሮናይም፡ተሰማ።
4፤ሞዐብ፡ጠፍታለች፥ልጆቿም፡ጩኸትን፡አሰምተዋል።
5፤በሉሒት፡ዐቀበት፡ልቅሶ፡እያለቀሱ፡ይወጣሉና፥በሖሮናይምም፡ቍልቍለት፡የጥፋትንና፡የመባባትን፡ጩኸት፡ሰም ተዋል።
6፤ሸሽታችኹ፡ራሳችኹን፡አድኑ፤በምድረ፡በዳ፡እንዳለ፡ቍጥቋጦ፡ኹኑ።
7፤በሥራሽና፡በመዝገብሽ፡ታምነሻልና፥አንቺ፡ደግሞ፡ትያዢያለሽ፤ካሞሽም፡ከካህናቱና፡ከአለቃዎቹ፡ጋራ፡በአን ድነት፡ይማረካል።
8፤እግዚአብሔርም፡እንደ፡ተናገረ፥አጥፊ፡ወደ፡ከተማ፡ዅሉ፡ይመጣል፡አንዲትም፡ከተማ፡አትድንም፤ሸለቆውም፡ይ ጠፋል፡ሜዳውም፡ይበላሻል።
9፤በራ፟፡እንድትወጣ፡ለሞዐብ፡ክንፍ፡ስጧት፤ከተማዎቿም፡ባድማና፡ወና፡ይኾናሉ።
10፤የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡በቸልታ፡የሚያደርግ፡ርጉም፡ይኹን፥ሰይፉንም፡ከደም፡የሚከለክል፡ርጉም፡ይኹን።
11፤ሞዐብ፡ከታናሽነቱ፡ዠምሮ፡ቅምጥል፡ነበረ፥በአምቡላውም፡ላይ፡ዐርፏል፥ከዕቃውም፡ወደ፡ዕቃ፡አልተገላበጠ ም፥ወደ፡ምርኮም፡አልኼደም፤ስለዚህ፥ቃናው፡በርሱ፡ውስጥ፡ቀርቷል፥መዐዛውም፡አልተለወጠም።
12፤ስለዚህ፥እንሆ፥የሚያገላብጡትን፡የምልክበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እነርሱም፡ያገላብጡታ ል፤ጋኖቹንም፡ባዶ፡ያደርጋሉ፥መስቴዎቹንም፡ይሰብራሉ።
13፤የእስራኤልም፡ቤት፡ይታመንባት፡ከነበረው፡ከቤቴል፡እንዳፈረ፥እንዲሁ፡ሞዐብ፡ከካሞሽ፡ያፍራል።
14፤እናንተ፦እኛ፡ኀያላን፡በሰልፍም፡ጽኑዓን፡ነን፡እንዴት፡ትላላችኹ፧
15፤ሞዐብ፡ፈርሷል፥ከተማዎቹም፡ጠፍተዋል፥የተመረጡትም፡ጕልማሳዎች፡ወደ፡መታረድ፡ወርደዋል፥ይላል፡ስሙ፡የ ሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የኾነ፡ንጉሥ።
16፤የሞዐብ፡ጥፋት፡ሊመጣ፡ቀርቧል፡መከራውም፡እጅግ፡ይፈጥናል።
17፤በዙሪያው፡ያላችኹ፡ዅሉ፡ስሙንም፡የምታውቁ፡ዅሉ፦ብርቱው፡በትር፥የከበረው፡ሽመል፥እንዴት፡ተሰበረ! ብላችኹ፡አልቅሱለት።
18፤በዲቦን፡የምትኖሪ፡ሆይ፥ሞዐብን፡የሚያጠፋ፡ወጥቶብሻልና፥ዐምባሽንም፡ሰብሯልና፥ከክብርሽ፡ውረጂ፥በጥማ ትም፡ተቀመጪ።
19፤በዐሮዔር፡የምትኖሪ፡ሆይ፥በመንገድ፡አጠገብ፡ቆመሽ፡ተመልከቺ፤የሸሸውንና፡ያመለጠችውን፦ምን፡ኾኗል፧ብ ለሽ፡ጠይቂ።
20፤ሞዐብም፡ፈርሷልና፥ዐፈረ፤አልቅሱ፡ጩኹም፤ሞዐብ፡እንደ፡ተዘረፈ፡በአርኖን፡አጠገብ፡አውሩ።
21፤በሜዳ፡ላይ፥በሖሎን፥በያሳ፥በሜፍዓት፡ላይ፥
22፤በዲቦን፥በናባው፥በቤት፡ዲብላታይም፡ላይ፥
23፤በቂርያታይም፥በቤትጋሙል፥
24፤በቤትምዖን፡ላይ፥በቂርዮት፥በባሶራ፥በሞዐብም፡ምድር፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ቅርብና፡ሩቅ፡በኾኑ፡ላይ፡ፍርድ፡ መጥቷል።
25፤የሞዐብ፡ቀንድ፡ተቈረጠ፡ክንዱም፡ተሰበረ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
26፤በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኰርቷልና፥አስክሩት፤ሞዐብም፡በጥፋቱ፡ላይ፡ይንከባለላል፥ደግሞም፡መሳቂያ፡ይኾናል ።
27፤እስራኤል፡ለአንተ፡መሳቂያ፡አልኾነምን፧ወይስ፡በሌባዎች፡መካከል፡ተገኝቷልን፧ስለ፡ርሱ፡በተናገርኽ፡ጊ ዜ፡ራስኽን፡ትነቀንቃለኽ።
28፤እናንተ፡በሞዐብ፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ከተማዎችን፡ትታችኹ፡በአለት፡ውስጥ፡ተቀመጡ፥በገደል፡አፋፍም፡ቤቷን፡ እንደምትሠራ፡እንደ፡ርግብ፡ኹኑ።
29፤እጅግ፡እንደ፡ታበየ፡ስለሞዐብ፡ትዕቢት፡ስለ፡ትምክሕቱም፡ስለ፡ኵራቱም፡ስለ፡መጓደዱም፡ስለልቡም፡ትዕቢ ት፡ሰምተናል።
30፤ቍጣው፡ምንም፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ፉከራው፡ምንም፡አልሠራም።
31፤ስለዚህ፥ለሞዐብ፡አለቅሳለኹ፥ለሞዐብም፡ዅሉ፡እጮኻለኹ፤ለቂርሔሬስ፡ሰዎች፡አለቅሳለኹ።
32፤አንቺ፡የሴባማ፡ወይን፡ሆይ፥ከኢያዜር፡ልቅሶ፡ይልቅ፡ለአንቺ፡አለቅሳለኹ፤ቅርንጫፎችሽ፡ባሕርን፡ተሻግረ ዋል፥ወደኢያዜርም፡ባሕር፡ደርሰዋል፤አጥፊው፡በሰብልሽና፡በወይንሽ፡ላይ፡መጥቷል።
33፤ሐሤትና፡ደስታ፡ከፍሬያማው፡ዕርሻና፡ከሞዐብ፡ምድር፡ጠፍተዋል፤ጠጁን፡ከመጥመቂያው፡አጥፍቻለኹ፤ጠማቂው ም፡በእልልታ፡አይጠምቅም፥እልልታቸውም፡እልልታ፡አይኾንም።
34፤ከሐሴቦን፡ጩኸት፡እስከ፡ኤልያሊና፡እስከ፡ያሀጽ፡ድረስ፡ድምፃቸውን፡ሰጥተዋል፤ከዞዓር፡እስከ፡ሖሮናይም ና፡እስከ፡ዔግላት፡ሺሊሺያ፡ድረስ፡ይደርሳል፤የኔምሬም፡ውሃ፡ደግሞ፡ይደርቃል።
35፤በኰረብታው፡መስገጃ፡ላይ፡የሚሠዋውን፡ለአማልክቱም፡የሚያጥነውን፡ከሞዐብ፡አጠፋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔ ር።
36፤ያተረፈው፡ትርፉ፡ጠፍቶበታልና፤ስለዚህ፥ልቤ፡ለሞዐብ፡እንደ፡እንቢልታ፡ይጮኻል፥ልቤም፡ለቂርሔሬስ፡ሰዎ ች፡እንደ፡እንቢልታ፡ይጮኻል።
37፤ራስ፡ዅሉ፡መላጣ፡ጢምም፡ዅሉ፡የተላጨ፡ነውና፤በእጅም፡ዅሉ፡ላይ፡ክትፋት፡በወገብም፡ላይ፡ማቅ፡አለና።
38፤ሞዐብን፡እንደማይወደድ፡ዕቃ፡ሰብሬያለኹና፡በሞዐብ፡ሰገነት፡ዅሉ፡ላይ፡በአደባባዩም፡ላይ፡በዅሉም፡ቦታ ፡ልቅሶ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
39፤እንዴት፡ተገለበጠ! በዕፍረትም፡የተነሣ፡ሞዐብ፡ዠርባውን፡እንዴት፡መለሰ! ብላችኹ፡አልቅሱ።ሞዐብም፡በዙሪያው፡ላሉት፡ዅሉ፡መሳቂያና፡ድንጋጤ፡ይኾናል።
40፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥እንደ፡ንስር፡ይበራ፟ል፡ክንፉንም፡በሞዐብ፡ላይ፡ይዘረጋል።
41፤ከተማዎቹ፡ተይዘዋል፥ዐምባዎቹም፡ተወስደዋል፥በዚያም፡ቀን፡የሞዐብ፡ኀያላን፡ልብ፡ምጥ፡እንደ፡ያዛት፡ሴ ት፡ልብ፡ይኾናል።
42፤ሞዐብም፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኰርቷልና፥ሕዝብ፡ከመኾን፡ይጠፋል።
43፤በሞዐብ፡የምትኖር፡ሆይ፥ፍርሀትና፡ጕድጓድ፡ወጥመድም፡ባንተ፡ላይ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
44፤በሞዐብ፡ላይ፡የመጐብኘትን፡ዓመት፡አመጣበታለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በፍርሀት፡የሸሸ፡በጕድጓድ፡ውስ ጥ፡ይወድቃል፥ከጕድጓድም፡የወጣ፡በወጥመድ፡ይያዛል።
45፤የሸሹ፡ደክመው፡ከሐሴቦን፡ጥላ፡በታች፡ቆመዋል፤እሳት፡ከሐሴቦን፡ነበልባልም፡ከሴዎን፡ወጥቷል፡የሞዐብን ም፡ማእዘን፡የሤትንም፡ልጆች፡ዐናት፡በልቷል።
46፤ሞዐብ፡ሆይ፥ወዮልኽ! የካሞሽ፡ወገን፡ጠፍቷል፤ወንዶች፡ልጆችኽ፡ተማርከዋልና፥ሴቶች፡ልጆችኽም፡ወደ፡ምርኮ፡ኼደዋልና።
47፤ነገር፡ግን፥በዃለኛው፡ዘመን፡የሞዐብን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።የሞዐብ፡ፍርድ፡እስከዚ ህ፡ድረስ፡ነው።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡49።______________
ምዕራፍ፡49፤
1፤ስለዐሞን፡ልጆች፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለእስራኤል፡ልጆች፡የሉትምን፧ወይስ፡ወራሽ፡የለውምን፧ስለ ፡ምን፡ሚልኮም፡ጋድን፡ወረሰ፧ሕዝቡስ፡በከተማዎቹ፡ላይ፡ስለ፡ምን፡ተቀመጠ፧
2፤ስለዚህ፥እንሆ፥በዐሞን፡ልጆች፡ከተማ፡በረባት፡ላይ፡የሰልፍ፡ውካታን፡የማሰማበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤የፍርስራሽ፡ክምርም፡ትኾናለች፥ሴቶች፡ልጆቿም፡በእሳት፡ይቃጠላሉ፥እስራኤልም፡የወረሱትን፡ይ ወርሳል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
3፤ሐሴቦን፡ሆይ፥ጋይ፡ፈርሳለችና፡አልቅሺላት፡እናንተም፡የረባት፡ሴቶች፡ልጆች፡ሆይ፥ሚልኮም፡ካህናቱና፡አለ ቃዎቹም፡በአንድነት፡ይማረካሉና፡ጩኹ፥ማቅም፡ታጠቁ፥አልቅሱም፥በቅጥሮችም፡መካከል፡ተሯሯጡ።
4፤ማን፡ይመጣብኛል፡ብለሽ፡በመዝገብሽ፡የታመንሽ፡አንቺ፡ከዳ፟ተኛ፡ልጅ፡ሆይ፥በሸለቆዎችሽ፥ውሃ፡በሚያረካቸ ው፡ሸለቆዎችሽ፥ስለ፡ምን፡ትመኪያለሽ፧
5፤እንሆ፥በዙሪያሽ፡ካሉት፡ዅሉ፡ዘንድ፡ፍርሀትን፡አመጣብሻለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤እያንዳ ንዳችኹም፡በፊታችኹ፡ወዳለው፡ስፍራ፡ትሰደዳላችኹ፥የሚሸሹትንም፡የሚሰበስብ፡የለም።
6፤ነገር፡ግን፥ከዚያ፡በዃላ፡የዐሞንን፡ልጆች፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
7፤ስለ፡ኤዶምያስ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእውኑ፡በቴማን፡ጥበብ፡የለምን፧ከብልኀተኛ ዎችስ፡ምክር፡ጠፍቷልን፧
8፤ጥበባቸውስ፡አልቋልን፧እናንተ፡በድዳን፡የምትኖሩ፡ሆይ፥የዔሳውን፡ጥፋት፥የምጐበኝበትን፡ጊዜ፥አመጣበታለ ኹና፡ሽሹ፥ወደ፡ዃላ፡ተመለሱ፥በጥልቅም፡ውስጥ፡ተቀመጡ።
9፤ወይን፡ለቃሚዎች፡ቢመጡብኽ፥ቃርሚያውን፡አይተውልኽምን፧ሌባዎችስ፡በሌሊት፡ቢመጡ፥የሚያጠፉት፡እስኪበቃቸ ው፡ድረስ፡አይደለምን፧
10፤እኔ፡ግን፡ዔሳውን፡ዐራቈትኹት፥የተሸሸጉትንም፡ስፍራዎች፡ገለጥኹ፥ይሸሸግም፡ዘንድ፡አይችልም፤ዘሩም፡ወ ንድሞቹም፡ጎረቤቶቹም፡ጠፍተዋል፡ርሱም፡የለም።
11፤ድኻ፡አደጎችኽን፡ተው፥እኔም፡በሕይወት፡አኖራቸዋለኹ፤መበለቶችኽም፡በእኔ፡ይታመኑ።
12፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ጽዋውን፡ያልተገባቸው፡ሰዎች፡ጠጥተውታል፤አንተም፡ሳትቀጣ፡ትቀራ ለኽን፧በርግጥ፡ትጠጣለኽ፡እንጂ፡ያለቅጣት፡አትቀርም።
13፤ባሶራ፡መደነቂያና፡መሰደቢያ፡መረገሚያም፡እንድትኾን፡በራሴ፡ምያለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ከተማዎቿም፡ ዅሉ፡ለዘለዓለም፡ባድማ፡ይኾናሉ።
14፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወሬ፡ሰምቻለኹ፡በአሕዛብም፡መካከል።ተሰብሰቡ፥በርሷም፡ላይ፡ኑ፡ለሰልፍም፡ተነሡ ፡የሚል፡መልእክተኛ፡ተልኳል።
15፤እንሆ፥በአሕዛብ፡ዘንድ፡የተጠቃኽ፥በሰዎችም፡ዘንድ፡የተናቅኽ፡አድርጌኻለኹ።
16፤በአለት፡ንቃቃት፡ውስጥ፡የምትቀመጥ፥የተራራውን፡ከፍታ፡የምትይዝ፡ሆይ፥ድፍረትኽና፡የልብኽ፡ኵራት፡አታ ለ፟ውኻል።ቤትኽን፡ምንም፡እንደ፡ንስር፡ከፍ፡ብታደርግ፥ከዚያ፡አወርድኻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
17፤ኤዶምያስም፡መደነቂያ፡ትኾናለች፥የሚያልፍባትም፡ዅሉ፡ይደነቃል፥ስለመጣባትም፡መቅሠፍት፡ዅሉ፡ያፏጭባታ ል።
18፤ሰዶምና፡ገሞራ፡በእነርሱም፡አጠገብ፡የነበሩት፡ከተማዎች፡እንደ፡ተገለበጡ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እንዲሁ ፡በዚያ፡ሰው፡አይቀመጥም፡የሰው፡ልጅም፡አይኖርባትም።
19፤እንሆ፥ከርሷ፡ዘንድ፡በቶሎ፡አባርራቸዋለኹና፡በጠነከረው፡ዐምባ፡ላይ፡ከዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡ውስጥ፡እንደ ፡አንበሳ፡ይወጣል፤የተመረጠውንም፡በርሷ፡ላይ፡እሾመዋለኹ፤እንደ፡እኔ፡ያለ፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ለእኔ፡ጊዜ፡ የሚወስን፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ፊቴን፡የሚቃወም፡እረኛ፡ማን፡ነው፧
20፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡በኤዶምያስ፡ላይ፡የመከረባትን፡ምክር፥በቴማንም፡በሚኖሩ፡ሰዎች፡ላይ፡ያሰባትን፡ ዐሳብ፡ስሙ፤በእውነት፡የመንጋ፡ትንንሾች፡ይጐተታሉ፤በእውነት፡ማደሪያቸውን፡ባድማ፡ያደርግባቸዋል።
21፤ከመውደቃቸው፡ድምፅ፡የተነሣ፡ምድር፡ተናወጠች፥የጩኸታቸውም፡ድምፅ፡በቀይ፡ባሕር፡ተሰማ።
22፤እንሆ፥እንደ፡ንስር፡ወጥቶ፡ይበራል፡ክንፉንም፡በባሶራ፡ላይ፡ይዘረጋል፥በዚያም፡ቀን፡የኤዶምያስ፡ኀያላ ን፡ልብ፡ምጥ፡እንደ፡ያዛት፡ሴት፡ልብ፡ይኾናል።
23፤ስለ፡ደማስቆ፤ክፉ፡ወሬ፡ሰምተዋልና፥ሐማትና፡አርፋድ፡ዐፈሩ፥ቀለጡም፤በባሕርም፡ላይ፡ሐዘን፡አለ፥ታርፍ ም፡ዘንድ፡አትችልም።
24፤ደማስቆ፡ደከመች፡ትሸሽም፡ዘንድ፡ዘወር፡አለች፡እንቅጥቅጥም፡ያዛት፥እንደ፡ወላድም፡ሴት፡ጣርና፡ምጥ፡ያ ዛት።
25፤የተመሰገነችው፡ከተማ፥የደስታዬ፡ከተማ፥ሳትለቀቅ፡እንዴት፡ቀረች፧
26፤ስለዚህ፥ጐበዛዝቷ፡በአደባባይዋ፡ላይ፡ይወድቃሉ፥በዚያም፡ቀን፡ሰልፈኛዎች፡ዅሉ፡ይጠፋሉ፥ይላል፡የሰራዊ ት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
27፤በደማስቆም፡ቅጥር፡ላይ፡እሳት፡አነዳ፟ለኹ፡የወልደ፡አዴርንም፡አዳራሾች፡ትበላለች።
28፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ስለ፡መታ፡ስለቄዳርና፡ስለአሶር፡መንግሥታት፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላ ል፦ተነሡ፡ወደ፡ቄዳርም፡ውጡ፥የምሥራቅንም፡ልጆች፡አጥፉ።
29፤ድንኳናቸውንና፡መንጋቸውን፡ይወስዳሉ፤መጋረጃዎቻቸውንና፡ዕቃቸውን፡ዅሉ፡ግመሎቻቸውንም፡ለራሳቸው፡ይወ ስዳሉ፥በዙሪያቸውም፡ዅሉ፡ጥፋትን፡ጥሩባቸው።
30፤እናንተ፡በአሶር፡የምትኖሩ፡ሆይ፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ተማክሮባችዃልና፥ዐሳብም፡ዐስቦባችዃል ና፥ሽሹ፥ወደ፡ሩቅም፡ኺዱ፥በጥልቅም፡ውስጥ፡ተቀመጡ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
31፤ተነሡ፥ዕርፊት፡ወዳለበት፡ተዘልሎም፡ወደተቀመጠው፥ደጅና፡መወርወሪያ፡ወደሌለው፡ብቻውንም፡ወደተቀመጠው ፡ሕዝብ፡ውጡ።
32፤ግመሎቻቸው፡ይበዘበዛሉ፡የእንስሳዎቻቸውም፡ብዛት፡ይማረካል፤ጠጕራቸውንም፡በዙሪያ፡የሚላጩትን፡ሰዎች፡ ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እበትናቸዋለኹ፤ከዳርቻቸውም፡ዅሉ፡ጥፋት፡አመጣባቸዋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
33፤አሶርም፡የቀበሮ፡መኖሪያና፡የዘለዓለም፡ባድማ፡ትኾናለች፤በዚያም፡ሰው፡አይኖርም፥የሰው፡ልጅም፡አይቀመ ጥባትም።
34፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡ስለ፡ዔላም፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡የእግ ዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
35፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ዋና፡የኀይላቸው፡መሣሪያ፡የኾነውን፡የዔላምን፡ቀስ ት፡እሰብራለኹ።
36፤ከአራቱም፡ከሰማይ፡ማእዘናት፡አራቱን፡ነፋሳት፡በዔላም፡ላይ፡አመጣለኹ፥ወደ፡እነዚያም፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እ በትናቸዋለኹ፤ከዔላም፡የተሰደዱ፡ሰዎች፡የማይደርሱበት፡ሕዝብ፡አይገኝም።
37፤በጠላቶቻቸውና፡ነፍሳቸውን፡በሚሿት፡ፊት፡ዔላምን፡አስደነግጣለኹ፤ክፉ፡ነገርን፡ርሱም፡ጽኑ፡ቍጣዬን፡አ መጣባቸዋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እስካጠፋቸውም፡ድረስ፡በዃላቸው፡ሰይፍ፡እሰድ፟ባቸዋለኹ፤
38፤ዙፋኔንም፡በዔላም፡አኖራለኹ፥ከዚያም፡ንጉሡንና፡አለቃዎቹን፡አጠፋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
39፤ነገር፡ግን፥በዃለኛው፡ዘመን፡የዔላምን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡50።______________
ምዕራፍ፡50፤
1፤እግዚአብሔር፡ስለከለዳውያን፡ምድር፡ስለ፡ባቢሎን፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2፤በአሕዛብ፡መካከል፡ተናገሩ፡አውሩም፥ዐላማውንም፡አንሡ፤አውሩ፥አትደብቁ።ባቢሎን፡ተወሰደች፥ቤል፡ዐፈረ፥ ሜሮዳክ፡ደነገጠ፤ምስሎቿ፡ዐፈሩ፥ጣዖታቷ፡ደነገጡ፡በሉ።
3፤ሕዝብ፡ከሰሜን፡ወጥቶባታል፡ምድሯንም፡ባድማ፡ያደርጋል፥የሚቀመጥባትም፡አይገኝም፤ከሰው፡ዠምሮ፡እስከ፡እ ንስሳ፡ድረስ፡ሸሽተው፡ኼደዋል።
4፤በዚያም፡ወራት፡በዚያም፡ጊዜ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡ልጆችና፡የይሁዳ፡ልጆች፡በአንድነት፡ኾነው ፡ይመጣሉ፥እያለቀሱም፡መንገዳቸውን፡ይኼዳሉ፥አምላካቸውንም፡እግዚአብሔርን፡ይፈልጋሉ።
5፤ፊታቸውንም፡ወደዚያ፡አቅንተው፦ኑ፥ከቶ፡በማይረሳ፡በዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ተጠጉ፡ብለ ው፡ስለ፡ጽዮን፡መንገድ፡ይጠይቃሉ።
6፤ሕዝቤ፡የጠፉ፡በጎች፡ኾነዋል፤እረኛዎቻቸው፡አሳቷቸው፥በተራራዎችም፡ላይ፡የተቅበዘበዙ፡አደረጓቸው፤ከተራ ራ፡ወደ፡ኰረብታ፡ዐለፉ፥በረታቸውንም፡ረሱ።
7፤ያገኟቸው፡ዅሉ፡በሏቸው፥ጠላቶቻቸውም፦በጽድቅ፡ማደሪያ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፥በአባቶቻቸው፡ተስፋ፡በእግዚ አብሔር፡ላይ፡ኀጢአት፡ስለ፡ሠሩ፡እኛ፡አልበደልንም፡አሉ።
8፤ከባቢሎን፡መካከል፡ሽሹ፥ከከለዳውያንም፡ድር፡ውጡ፥በመንጋዎችም፡ፊት፡እንደ፡አውራ፡ፍየሎች፡ኹኑ።
9፤እንሆ፥ከሰሜን፡ምድር፡የታላላቅ፡አሕዛብን፡ጉባኤ፡አስነሣለኹ፡በባቢሎንም፡ላይ፡አመጣቸዋለኹ፤በርሷም፡ላ ይ፡ይሰለፋሉ፥ከዚያም፡ትወሰዳለች፤ፍላጻዎቻቸውም፡ባዶውን፡እንደማይመለስ፡እንደ፡ብልኅ፡ዠግና፡ፍላጻ፡ናቸ ው።
10፤የከላውዴዎንም፡ምድር፡ትበዘበዛለች፥የሚበዘብዟትም፡ዅሉ፡ይጠግባሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
11፤ርስቴን፡የምትበዘብዙ፡እናንተ፡ሆይ፥ደስ፡ብሏችዃልና፥ሐሤትንም፡አድርጋችዃልና፥በመስክ፡ላይም፡እንዳለ ች፡ጊደር፡ኾናችኹ፡ተቀናጥታችዃልና፥እንደ፡ብርቱዎችም፡ፈረሶች፡አሽካክታችዃልና፥
12፤እናታችኹ፡እጅግ፡ታፍራለች፥የወለደቻችኹም፡ትጐሰቍላለች፤እንሆ፥በአሕዛብ፡መካከል፡ዃለኛዪቱ፡ትኾናለች ፤ምድረ፡በዳና፡ደረቅ፡ምድር፡በረሓም፡ትኾናለች።
13፤ከእግዚአብሔር፡ቍጣ፡የተነሣ፡ባድማ፡ትኾናለች፡እንጂ፡ሰው፡አይቀመጥባትም፤በባቢሎንም፡በኩል፡የሚያልፍ ፡ዅሉ፡ይደነቃል፡በመጣባትም፡መቅሠፍት፡ዅሉ፡ያፏጫል።
14፤እናንተ፡ቀስትን፡የምትገትሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፥በባቢሎን፡ላይ፡በዙሪያዋ፡ተሰለፉ፤በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኀጢአ ት፡ሠርታለችና፡ወርውሩባት፡ፍላጻዎችንም፡አትንፈጉ።
15፤የእግዚአብሔር፡በቀል፡ነውና፥በዙሪያዋ፡ጩኹባት፤እጇን፡ሰጠች፤ግንቦቿ፡ወደቁ፡ቅጥሮቿም፡ፈረሱ፤ርሷን፡ ተበቀሉ፡እንደ፡ሠራችውም፡ሥሩባት።
16፤ዘሪውንና፡በመከር፡ጊዜ፡ማጭድ፡የሚይዘውን፡ከባቢሎን፡አጥፉ፤ከሚያስጨንቅ፡ሰይፍ፡ፊት፡እያንዳንዱ፡ወደ ፡ወገኑ፡ይመለሳል፡እያንዳንዱም፡ወደ፡አገሩ፡ይሸሻል።
17፤እስራኤል፡የባዘነ፡በግ፡ነው፤አንበሳዎች፡አሳደዱት፤መዠመሪያ፡የአሶር፡ንጉሥ፡በላው፥በመጨረሻም፡የባቢ ሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ዐጥንቱን፡ቈረጠመው።
18፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፣የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሶርን፡ንጉሥ፡እንደ፡ቀጣ ኹ፡እንዲሁ፥እንሆ፥የባቢሎንን፡ንጉሥና፡ምድሩን፡እቀጣለኹ።
19፤እስራኤልንም፡ወደ፡ማሰማሪያው፡እመልሳለኹ፥በቀርሜሎስና፡በባሳንም፡ላይ፡ይሰማራል፥ሰውነቱም፡በኤፍሬም ፡ተራራና፡በገለዓድ፡ላይ፡ትጠግባለች።
20፤እነዚህን፡ያስቀረዃቸውን፡ይቅር፡እላቸዋለኹና፡በዚያን፡ወራት፡በዚያም፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የእ ስራኤል፡በደል፡የይሁዳም፡ኀጢአት፡ይፈለጋል፡ምንም፡አይገኝም።
21፤በምራታይም፡ምድር፡ላይ፡በፋቁድም፡በሚኖሩት፡ላይ፡ውጣ፤ግደላቸው፡ፈጽመኽም፡አጥፋቸው፥ይላል፡እግዚአብ ሔር፥እንዳዘዝኹኽም፡ዅሉ፡አድርግ።
22፤የሰልፍና፡የታላቅ፡ጥፋት፡ውካታ፡በምድር፡ላይ፡አለ።
23፤የምድር፡ዅሉ፡መዶሻ፡እንዴት፡ደቀቀ፥እንዴትስ፡ተሰበረ! ባቢሎንስ፡በአሕዛብ፡መካከል፡እንዴት፡ባድማ፡ኾነች!
24፤ባቢሎን፡ሆይ፥አጥምጄብሻለኹ፥አንቺም፡ሳታውቂ፡ተይዘሻል፤ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ስለ፡ተዋጋሽ፡ተገኝተሻል ፥ተይዘሽማል።
25፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በከለዳውያን፡ምድር፡ይሠራ፡ዘንድ፡ሥራ፡አለውና፥እግዚአብሔር፡ዕቃ፡ቤቱን ፡ከፍቶ፡የቍጣውን፡ዕቃ፡ጦር፡አውጥቷል።
26፤ከየበኩሉ፡በርሷ፡ላይ፡ውጡ፥ጐተራዎቿንም፡ክፈቱ፤እንደ፡ክምርም፡አድርጓት፥ፈጽማችኹም፡አጥፏት፥አንዳች ም፡አታስቀሩላት።
27፤ወይፈኖቿን፡ዅሉ፡ዕረዱ፥ወደ፡መታረድም፡ይውረዱ፤ቀናቸው፣የመጐብኘታቸው፡ጊዜ፡ደርሷልና፥ወዮላቸው!
28፤የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡በቀል፡የመቅደሱንም፡በቀል፡በጽዮን፡ይነግሩ፡ዘንድ፥ሸሽተው፡ከባቢሎን ፡አገር፡ያመለጡት፡ሰዎች፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
29፤ቀስትን፡የሚገትሩትን፡ቀስተኛዎችን፡ዅሉ፡በባቢሎን፡ላይ፡ጥሯቸው፤በዙሪያዋ፡ስፈሩባት፡አንድም፡አያምል ጥ፤በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኰርታለችና፥እንደ፡ሥራዋ፡መጠን፡መልሱላት፥እንዳደረገችም ፡ዅሉ፡አድርጉባት።
30፤ስለዚህ፥ጐበዛዝቷ፡በአደባባይዋ፡ላይ፡ይወድቃሉ፥በዚያም፡ቀን፡ሰልፈኛዎቿ፡ዅሉ፡ይጠፋሉ፥ይላል፡እግዚአ ብሔር።
31፤ትዕቢተኛው፡ሆይ፥የመጐብኘትኽ፡ጊዜ፥ቀንኽ፡ደርሷልና፥እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እ ግዚአብሔር።
32፤ትዕቢተኛው፡ተሰናክሎ፡ይወድቃል፡የሚያነሣውም፡የለም፤በከተማዎቹም፡ውስጥ፡እሳት፡አነዳ፟ለኹ፥በዙሪያው ም፡ያለውን፡ዅሉ፡ትበላለች።
33፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤል፡ልጆችና፡የይሁዳ፡ልጆች፡በአንድነት፡ተገፍተዋ ል፥የማረኳቸውም፡ዅሉ፡በኀይል፡ይይዟቸዋል፥ይለቋ፟ቸውም፡ዘንድ፡እንቢ፡ብለዋል።
34፤ተቤዢያቸው፡ብርቱ፡ነው፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው፤ምድርንም፡ያሳርፍ፡ዘንድ፥በባቢሎንም ፡የሚኖሩትን፡ያውክ፡ዘንድ፥ሙግታቸውን፡ፈጽሞ፡ይሟገታል።
35፤ሰይፍ፡በከለዳውያንና፡በባቢሎን፡በሚኖሩ፡ላይ፥በአለቃዎቿና፡በጥበበኛዎቿ፡ላይ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔ ር።
36፤ሰይፍ፡በሚጓደዱት፡ላይ፡አለ፡ሰነፎችም፡ይኾናሉ፥ሰይፍም፡በኀያላኗ፡ላይ፡አለ፡እነርሱም፡ይደነግጣሉ።
37፤ሰይፍ፡በፈረሶቻቸውና፡በሠረገላዎቻቸው፡ላይ፡በመካከሏም፡ባሉት፡በልዩ፡በልዩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ላይ፡አለ፥እ ነርሱም፡እንደ፡ሴቶች፡ይኾናሉ፤ሰይፍም፡በመዝገቧ፡ላይ፡አለ፡ለብዝበዛም፡ይኾናል።
38፤ርሷ፡የተቀረጹ፡ምስሎች፡ምድር፡ናት፥እነርሱም፡በጣዖታት፡ይመካሉና፥ድርቅ፡በውሃዎቿ፡ላይ፡ይኾናል፥እነ ርሱም፡ይደርቃሉ።
39፤ስለዚህ፥የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ከተኵላዎች፡ጋራ፡ይቀመጡባታል፥ሰጐኖችም፡ይቀመጡባታል፤ሰውም፡ከዚያ፡ወ ዲያ፡ለዘለዓለም፡አይቀመጥባትም፥እስከልጅ፡ልጅም፡ድረስ፡የሚኖርባት፡የለም።
40፤ሰዶምንና፡ገሞራን፡በአጠገባቸውም፡የነበሩትን፡ከከተማዎች፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ገለበጣቸው፥ይላል፡እግ ዚአብሔር፥እንዲሁ፡ሰው፡በዚያ፡አይቀመጥም፡የሰውም፡ልጅ፡አይኖርባትም።
41፤እንሆ፥ሕዝብ፡ከሰሜን፡ይመጣል፤ታላቅ፡ሕዝብና፡ብዙ፡ነገሥታትም፡ከምድር፡ዳርቻ፡ይነሣሉ።
42፤ቀስትንና፡ጦርን፡ይይዛሉ፤ጨካኞች፡ናቸው፥ምሕረትም፡አያደርጉም፤ድምፃቸው፡እንደ፡ባሕር፡ይተማ፟ል፥በፈ ረሶችም፡ላይ፡ይቀመጣሉ።የባቢሎን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ለሰልፍ፡እንደ፡ተዘጋጀ፡ሰው፡እያንዳንዳቸው፡ባንቺ፡ላይ ፡ተሰለፉ።
43፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወሬያቸውን፡ሰምቷል፥እጁም፡ደክማለች፥ጭንቀትም፡ይዞታል፥ምጥ፡ወላድ፡ሴትን፡እንደሚይ ዛት፡ጭንቀት፡ይዞታል።
44፤እንሆ፥ከርሷ፡ዘንድ፡በቶሎ፡አባርራቸዋለኹና፥በጠነከረው፡ዐምባ፡ላይ፡ከዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡ውስጥ፡እንደ ፡አንበሳ፡ይወጣል፤የተመረጠውንም፡በርሷ፡ላይ፡እሾመዋለኹ፤እንደ፡እኔ፡ያለ፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ለእኔ፡ጊዜ፡ የሚወስን፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ፊቴን፡የሚቃወም፡እረኛ፡ማን፡ነው፧
45፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡በባቢሎን፡ላይ፡የመከረባትን፡ምክር፥በከለዳውያንም፡ምድር፡ላይ፡ያሰባትን፡ዐሳብ ፡ስሙ፤በእውነት፡የመንጋ፡ትናንሾች፡ይጐተታሉ፤በእውነት፡ማደሪያቸውን፡ባድማ፡ያደርግባቸዋል።
46፤ከባቢሎን፡መያዝ፡ድምፅ፡የተነሣ፡ምድር፡ተናወጠች፥ጩኸትም፡በአሕዛብ፡መካከል፡ዘንድ፡ተሰማ።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡51።______________
ምዕራፍ፡51፤
1፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በባቢሎን፡ላይና፡በከለዳውያን፡ምድር፡በሚኖሩት፡ላይ፡አጥፊውን፡ነፋ ስ፡አስነሣለኹ።
2፤በባቢሎንም፡ላይ፡የሚያዘሩትን፡ሰዎች፡እሰዳ፟ለኹ፤እነርሱም፡ያዘሯታል፥ምድሯንም፡ባዶ፡ያደርጋሉ፤በመከራ ም፡ቀን፡በዙሪያዋ፡ይከቧ፟ታል።
3፤በወርዋሪው፡ላይ፡በጥሩርም፡በሚነሣው፡ላይ፡ቀስተኛው፡ቀስቱን፡ይገትር፤ለጐበዛዝቷ፡አትዘኑ፡ሰራዊቷንም፡ ዅሉ፡አጥፉ።
4፤በከለዳውያንም፡ምድር፡ተገድለው፥በሜዳዋም፡ላይ፡ተወግተው፡ይወድቃሉ።
5፤ምድራቸው፡በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡በተሠራው፡በደል፡ምንም፡እንኳ፡የተሞላች፡ብትኾን፥እስራኤልም፡ኾነ፡ይ ሁዳ፡በአምላኩ፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አልተጣለም።
6፤ከባቢሎን፡ውስጥ፡ሽሹ፥እያንዳንዳችኹም፡ነፍሳችኹን፡አድኑ፤በበደሏ፡አትጥፉ፥የእግዚአብሔር፡በቀል፡ጊዜ፡ ነውና፥ርሱም፡ብድራቷን፡ይከፍላታልና።
7፤ባቢሎን፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ውስጥ፡ምድርን፡ዅሉ፡ያሰከረች፡የወርቅ፡ጽዋ፡ነበረች፥አሕዛብም፡ከጠጇ፡ጠጥ ተዋል፤ስለዚህ፥አሕዛብ፡አብደዋል።
8፤ባቢሎን፡በድንገት፡ወድቃ፡ጠፍታለች፤አልቅሱላት፥ትፈወስም፡እንደ፡ኾነ፡ለቍስሏ፡መድኀኒት፡ውሰዱላት።
9፤ባቢሎንን፡ፈወስናት፥ርሷ፡ግን፡አልተፈወሰችም፤ፍርዷ፡እስከ፡ሰማይ፡ደርሷልና፥እስከ፡ደመናም፡ድረስ፡ከፍ ፡ከፍ፡ብሏልና፥ትታችዃት፡እያንዳንዳችን፡ወደ፡አገራችን፡እንኺድ።
10፤እግዚአብሔር፡ጽድቃችንን፡አውጥቷል፤ኑ፥በጽዮን፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡እንናገር።
11፤ፍላጻዎችን፡ሳሉ፡ጋሻዎችንም፡አዘጋጁ፤እግዚአብሔር፡ያጠፋት፡ዘንድ፡ዐሳቡ፡በባቢሎን፡ላይ፡ነውና፥የሜዶ ንን፡ነገሥታት፡መንፈስ፡አስነሥቷል፤የእግዚአብሔር፡በቀል፡የመቅደሱ፡በቀል፡ነውና።
12፤በባቢሎን፡ቅጥር፡ዐላማውን፡አንሡበት፥ጥበቃን፡አጽኑ፥ተመልካቾችን፡አቁሙ፥ድብቅ፡ጦር፡አዘጋጁ።እግዚአ ብሔር፡በባቢሎን፡በሚኖሩት፡ላይ፡የተናገረውን፡ዐስቧልና፥አድርጓልምና።
13፤አንቺ፡በብዙ፡ውሃ፡አጠገብ፡የተቀመጥሽ፥በመዝገብም፡የበለጠግሽ፡ሆይ፥እንደ፡ሥሥትሽ፡መጠን፡ፍጻሜሽ፡ደ ርሷል።
14፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ሲል፡በራሱ፡ምሏል፦በእውነት፡ሰዎችን፡እንደ፡አንበጣ፡እሞላብሻለ ኹ፥እነርሱም፡ጩኸት፡ያነሡብሻል።
15፤ምድርን፡በኀይሉ፡የፈጠረ፥ዓለሙን፡በጥበቡ፡የመሠረተ፥ሰማያትንም፡በማስተዋሉ፡የዘረጋ፡ርሱ፡ነው።
16፤ድምፁን፡ባሰማ፡ጊዜ፡ውሃዎች፡በሰማይ፡ይታወካሉ፥ከምድርም፡ዳር፡ደመናትን፡ከፍ፡ያደርጋል፤ለዝናብም፡መ ብረቅን፡ያደርጋል፥ነፍስንም፡ከቤተ፡መዛግብቱ፡ያወጣል።
17፤ሰው፡ዅሉ፡ዕውቀት፡ዐጥቶ፡ሰንፏል፥አንጥረኛም፡ዅሉ፡ከቀረጸው፡ምስል፡የተነሣ፡አፍሯል፤ቀልጦ፡የተሠራ፡ ምስሉ፡ውሸት፡ነውና፥እስትንፋስም፡የላቸውምና።
18፤እነርሱም፡ምናምንቴና፡የቀልድ፡ሥራ፡ናቸው፤በተጐበኙ፡ጊዜ፡ይጠፋሉ።
19፤የያዕቆብ፡ዕድል፡ፈንታ፡እንደ፡እነዚህ፡አይደለም፥ርሱ፡የዅሉ፡ፈጣሪ፡ነውና፤እስራኤልም፡የርስቱ፡ነገድ ፡ነው፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው።
20፤አንቺ፡መዶሻዬና፡የጦር፡መሣሪያዬ፡ነሽ፤ባንቺ፡አሕዛብን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡መንግሥታትን፡አጠፋለኹ ፤
21፤ባንቺ፡ፈረሱንና፡ፈረሰኛውን፡እሰባብራለኹ፤
22፤ባንቺም፡ሠረገላውንና፡በላዩ፡የሚቀመጠውን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡ወንድንና፡ሴትን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺ ም፡ሽማግሌውንና፡ብላቴናውን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡ጕልማሳውንና፡ቈንዦዪቱን፡እሰባብራለኹ፤
23፤ባንቺም፡እረኛውንና፡መንጋውን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡አራሹንና፡ጥማጁን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡አለቃዎ ችንና፡ሹማምቶችን፡እሰባብራለኹ።
24፤በጽዮን፡በዐይናችኹ፡ፊት፡ስለሠሩት፡ክፋታቸው፡ዅሉ፡በባቢሎንና፡በከለዳውያን፡ምድር፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ ፡ፍዳቸውን፡እከፍላለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
25፤አንተ፡ምድርን፡ዅሉ፡የምታጠፋ፡አጥፊ፡ተራራ፡ሆይ፥እንሆ፥እኔ፡ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እ ጄንም፡እዘረጋብኻለኹ፥ከድንጋዮችም፡ላይ፡አንከባልልኻለኹ፥የተቃጠለም፡ተራራ፡አደርግኻለኹ።
26፤ከአንተም፡ለማእዘንና፡ለመሠረት፡የሚኾን፡ድንጋይ፡አይወስዱም፥ለዘለዓለምም፡ባድማ፡ትኾናለኽ፥ይላል፡እ ግዚአብሔር።
27፤በምድር፡ላይ፡ዐላማን፡አንሡ፡በአሕዛብም፡መካከል፡መለከት፡ንፉ፥አሕዛብንም፡አዘጋጁባት፤የአራራትንና፡ የሚኒን፡የአስከናዝንም፡መንግሥታት፡ሰብስቡባት፡አለቃንም፡በላይዋ፡አቁሙ፤እንደ፡ጠጕራም፡ኵብኵባ፡ፈረሶች ን፡በላይዋ፡አውጡ።
28፤አሕዛብን፡የሚዶንንም፡ነገሥታት፡አለቃዎችንም፡ሹማምቶችንም፡ዅሉ፡የግዛታቸውንም፡ምድር፡ዅሉ፡አዘጋጁባ ት።
29፤ማንም፡እንዳይቀመጥባት፡የባቢሎንን፡ምድር፡ባድማ፡ያደርጋት፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡ዐሳብ፡በባቢሎን፡ላ ይ፡ጸንቷልና፥ምድር፡ተናውጣለች፡ታመመችም።
30፤የባቢሎን፡ኀያላን፡መዋጋትን፡ትተዋል፡በዐምባዎቻቸውም፡ውስጥ፡ተቀምጠዋል፤ኀይላቸውም፡ጠፍቷል፡እንደ፡ ሴቶችም፡ኾነዋል፤ማደሪያዎቿም፡ነደ፟ዋል፡መወርወሪያዎቿም፡ተሰብረዋል።
31-32፤ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ድረስ፡ከተማው፡እንደ፡ተያዘች፡መልካሞቿም፡እንደ፡ተያዙ፥ቅጥሯም፡በእሳት፡እንደ፡ ተቃጠለ፥ሰልፈኛዎችም፡እንደ፡ደነገጡ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ይነግር፡ዘንድ፡ወሬኛው፡ወሬኛውን፡መልእክተኛውም፡ መልእክተኛውን፡ሊገናኝ፡ይሮጣል።
33፤የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ዐውድማ፡እንደ፡ተረገጠ፡ጊዜ፥እንዲ ሁ፡የባቢሎን፡ልጅ፡ናት፤ጥቂት፡ቈይታ፡የመከር፡ጊዜ፡ይደርስባታል።
34፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በላኝ፥ከፋፈለኝም፥እንደ፡ባዶ፡ዕቃም፡አደረገኝ፥እንደ፡ዘንዶም፡ዋጠኝ፥ ከሚጣፍጠውም፡ምግቤ፡ሆዱን፡ሞላ፥እኔንም፡ጣለኝ።
35፤በጽዮን፡የምትቀመጥ፦በእኔና፡በሥጋዬ፡የተደረገ፡ግፍ፡በባቢሎን፡ላይ፡ይኹን፡ትላለች፤ኢየሩሳሌምም፦ደሜ ፡በከለዳውያን፡ምድር፡በሚኖሩት፡ላይ፡ይኹን፡ትላለች።
36፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እሟገትልሻለኹ፡በቀልሽንም፡እበቀልልሻለኹ፤ባሕሯንም፡ድር ቅ፡አደርገዋለኹ፡ምንጯንም፡አደርቀዋለኹ።
37፤ባቢሎንም፡የድንጋይ፡ቍልልና፡የቀበሮ፡ማደሪያ፡መደነቂያም፡ማፏጫም፡ትኾናለች፥የሚቀመጥባትም፡ሰው፡አይ ገኝም።
38፤በአንድነትም፡እንደ፡አንበሳዎች፡ያገሣሉ፥እንደ፡አንበሳም፡ደቦሎች፡ያጕረመርማሉ።
39፤በሞቃቸው፡ጊዜ፡ደስ፡እንዲላቸው፡ለዘለዓለምም፡አንቀላፍተው፡እንዳይነቁ፡የመጠጥ፡ግብዣ፡አደርግላቸዋለ ኹ፡አሰክራቸውማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
40፤እንደ፡ጠቦቶችና፡እንደ፡አውራ፡በጎች፡እንደ፡አውራ፡ፍየሎችም፡ወደ፡መታረድ፡አወርዳቸዋለኹ።
41፤ሼሻክ፡እንዴት፡ተያዘች! የምድርም፡ዅሉ፡ምስጋና፡እንዴት፡ተወሰደች! ባቢሎንም፡በአሕዛብ፡መካከል፡መደነቂያ፡እንዴት፡ኾነች!
42፤ባሕር፡በባቢሎን፡ላይ፡ወጣ፡በሞገዱም፡ብዛት፡ተከደነች።
43፤ከተማዎቿ፡ባድማና፡ደረቅ፡ምድር፡ምድረ፡በዳም፥ሰውም፡የማይቀመጥበት፡የሰውም፡ልጅ፡የማያልፍበት፡ምድር ፡ኾኑ።
44፤በባቢሎንም፡ውስጥ፡ቤልን፡እቀጣለኹ፡የዋጠውንም፡ከአፉ፡አስተፋዋለኹ፤አሕዛብም፡ከዚያ፡ወዲያ፡ወደ፡ርሱ ፡አይሰበሰቡም፥የባቢሎንም፡ቅጥር፡ይወድቃል።
45፤ሕዝቤ፡ሆይ፥ከመካከሏ፡ውጡ፡እያንዳንዳችኹም፡ከእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡ራሳችኹን፡አድኑ።
46፤በምድርም፡ከሚሰማ፡ወሬ፡የተነሣ፡አትፍሩ፡ልባችኹም፡የዛለ፡አይኹን፤ባንድ፡ዓመት፡ወሬ፡ይመጣል፥ከዚያም ፡በዃላ፡በሌላው፡ዓመት፡ወሬ፥በምድርም፡ላይ፡ግፍ፡ይመጣል፥አለቃም፡በአለቃ፡ላይ፡ይነሣል።
47፤ስለዚህ፥እንሆ፥የተቀረጹትን፡የባቢሎን፡ምስሎች፡የምቀጣበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ምድሯም፡ዅሉ፡ታፍራለች፤ተ ወግተውም፡የሞቱት፡ዅሉ፡በመካከሏ፡ይወድቃሉ።
48፤አጥፊዎች፡ከሰሜን፡ይመጡባታልና፥ሰማይና፡ምድር፡በእነርሱም፡ያለው፡ዅሉ፡ስለ፡ባቢሎን፡እልል፡ይላሉ፥ይ ላል፡እግዚአብሔር።
49፤ባቢሎንም፡ከእስራኤል፡ተወግተው፡የሞቱት፡እንዲወድቁ፡እንዳደረገች፥እንዲሁ፡በባቢሎን፡ከምድሩ፡ዅሉ፡ተ ወግተው፡የሞቱት፡ይወድቃሉ።
50፤ከሰይፍ፡ያመለጣችኹ፡ሆይ፥ኺዱ፥አትቁሙ፤እግዚአብሔርን፡ከሩቅ፡ዐስቡ፥ኢየሩሳሌምንም፡በልባችኹ፡ዐስቡ።
51፤ስድብን፡ስለ፡ሰማን፡ዐፍረናል፤ባዕዳን፡ሰዎችም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅደስ፡ገብተዋልና፥ነውር፡ፊታ ችንን፡ከድኖታል።
52፤ስለዚህ፥እንሆ፥የተቀረጹትን፡ምስሎቿ፡የምቀጣበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፡በምድሯም፡ላይ፡ ዅሉ፡የተወጉት፡ያንቋርራሉ።
53፤ባቢሎን፡ምንም፡ወደ፡ሰማይ፡ብትወጣ፥የኀይሏንም፡ከፍታ፡ብታጸና፥ከእኔ፡ዘንድ፡አጥፊዎች፡ይመጡባታል፥ይ ላል፡እግዚአብሔር።
54፤ከባቢሎን፡ጩኸት፥ከከለዳውያንም፡ምድር፡የታላቅ፡ጥፋት፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
55፤እግዚአብሔር፡ባቢሎንን፡አጥፍቷታልና፥ከርሷም፡ታላቁን፡ድምፅ፡ዝም፡አሠኝቷልና፤ሞገዳቸውም፡እንደ፡ብዙ ፡ውሃዎች፡ይተማ፟ል፥የድምፃቸውም፡ጩኸት፡ተሰምቷል።
56፤አጥፊው፡በባቢሎን፡ላይ፡መጥቶባታልና፥ኀያላኗ፡ተያዙ፥ቀስታቸውም፡ተሰባበረ፤እግዚአብሔር፡ፍዳን፡የሚከ ፍል፡አምላክ፡ነውና፥ፍዳንም፡በርግጥ፡ይከፍላል።
57፤መሳፍንቷንና፡ጥበበኛዎቿንም፥አለቃዎቿንና፡ሹማምቷን፡ኀያላኗንም፡አሰክራለኹ፥ለዘለዓለምም፡አንቀላፍተ ው፡አይነቁም፥ይላል፡ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የተባለው፡ንጉሥ።
58፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰፊው፡የባቢሎን፡ቅጥር፡ፈጽሞ፡ይፈርሳል፡ረዣዥሞችም፡በሮ ቿ፡በእሳት፡ይቃጠላሉ፤የወገኖችም፡ድካም፡ከንቱ፡ትኾናለች፥የአሕዛብም፡ሥራ፡ለእሳት፡ትኾናለች፤እነርሱም፡ ይደክማሉ።
59፤የመሕሤያ፡ልጅ፡የኔርያ፡ልጅ፡ሰራያ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡በነገሠ፡በአራተኛው፡ዓመት፡ከርሱ፡ጋራ፡ ወደ፡ባቢሎን፡በኼደ፡ጊዜ፡ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ያዘዘው፡ቃል፡ይህ፡ነው።ሰራያም፡የቤት፡አዛዥ፡ነበረ።
60፤በባቢሎንም፡ላይ፡የሚመጣውን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፥ስለ፡ባቢሎን፡የተጻፈውን፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፥ኤርምያስ፡በ መጽሐፍ፡ላይ፡ጻፈው።
61፤ኤርምያስም፡ሰራያን፡እንዲህ፡አለው፦ወደ፡ባቢሎን፡በገባኽ፡ጊዜ፡እይ፥ይህንም፡ቃል፡ዅሉ፡አንብ፟ና፦
62፤አቤቱ፥ከሰው፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡ማንም፡እንዳይቀመጥባት፥ለዘለዓለምም፡ባድማ፡እንድትኾን፡ታ ጠፋት፡ዘንድ፡በዚች፡ስፍራ፡ላይ፡ተናግረኻል፡በል።
63፤ይህንም፡መጽሐፍ፡ማንበብ፡ከፈጸምኽ፡በዃላ፥ድንጋይን፡እሰርበት፡በኤፍራጥስም፡ውስጥ፡ጣለው፤
64፤አንተም፦እኔ፡ከማመጣባት፡ክፉ፡ነገር፡የተነሣ፡እንዲሁ፡ባቢሎን፡ትሰጥማለች፡አትነሣምም፡በል።የኤርምያ ስ፡ቃል፡እስከዚህ፡ድረስ፡ነው።
_______________ትንቢተ፡ኤርምያስ፥ምዕራፍ፡52።______________
ምዕራፍ፡52፤
1፤ሴዴቅያስ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡አንድ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡አንድ፡ዓመት ፡ነገሠ፤እናቱም፡ዐሚጣል፡የተባለች፡የሊብና፡ሰው፡የኤርምያስ፡ልጅ፡ነበረች።
2፤ኢዮአቄምም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
3፤ከፊቱም፡አውጥቶ፡እስኪጥላቸው፡ድረስ፡ይህ፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ላይ፡ኾኗልና፤ሴ ዴቅያስም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ላይ፡ዐመፀ።
4፤ሴዴቅያስም፡በነገሠ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡ ከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡መጥተው፡ከበቧት፡በዙሪያዋም፡ዕርድ፡አደረገ።
5፤ከተማዪቱም፡እስከ፡ንጉሡ፡እስከ፡ሴዴቅያስ፡እስከ፡ዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ተከባ፟፡ነበር።
6፤በአራተኛውም፡ወር፡በዘጠነኛው፡ቀን፡በከተማዪቱ፡ራብ፡ጸንቶ፡ነበር፥ለአገሩም፡ሰዎች፡እንጀራ፡ታጣ።
7፤ከተማዪቱም፡ተሰበረች፥ሰልፈኛዎችም፡ዅሉ፡ሸሹ፥በኹለቱም፡ቅጥር፡መካከል፡ባለው፡በር፡ወደንጉሡ፡አትክልት ፡በሚወስደው፡መንገድ፡በሌሊት፡ከከተማዪቱ፡ወጡ።ከለዳውያንም፡በከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ነበሩ፤በዐረባም፡መንገድ ፡ኼዱ።
8፤የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ንጉሡን፡ተከታተሉት፥በኢያሪኮም፡ሜዳ፡ሴዴቅያስን፡ያዙ፤ሰራዊቱም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ዘ ንድ፡ተበትነው፡ነበር።
9፤ንጉሡንም፡ይዘው፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለባት፡በሐማት፡ምድር፡ወዳለችው፡ወደ፡ሪብላ፡አመጡት፤ርሱም፡ፍርድ ን፡በርሱ፡ላይ፡ተናገረ።
10፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የሴዴቅያስን፡ልጆች፡በፊቱ፡ገደላቸው፥የይሁዳንም፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ደግሞ፡በሪብላ፡ገ ደላቸው።
11፤የሴዴቅያስንም፡ዐይኖች፡አወጣ፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በሰንሰለት፡አሰረው፡ወደ፡ባቢሎንም፡ወሰደው፥እስኪሞ ትም፡ድረስ፡በግዞት፡ቤት፡አኖረው።
12፤በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡በዐሥራ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ፊት፡የቆመው፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ።
13፤የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡አቃጠለ፤የኢየሩሳሌምንም፡ቤቶች፡ዅሉ፥ታላላቆችን፡ቤቶች፡ዅሉ፥ በእሳት፡አቃጠለ።
14፤ከዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ጋራ፡የነበረው፡የከለዳውያን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡የኢየሩሳሌምን፡ቅጥር፡ዅሉ፡ዙሪያዋን፡ አፈረሱ።
15፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡የሕዝቡን፡ድኻዎች፥በከተማም፡ውስጥ፡የቀረውን፡ሕዝብ፥ሸሽተውም፡ወደባ ቢሎን፡ንጉሥ፡የተጠጉትን፥የሕዝቡንም፡ቅሬታ፡አፈለሰ።
16፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፥ከአገሩ፡ድኻዎች፥ወይን፡ተካዮችና፡ዐራሾች፡እንዲኾኑ፥አስቀረ።
17፤ከለዳውያንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበሩትን፡የናስ፡ዐምዶች፡በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የነበሩትን፡መቀመ ጫዎችና፡የናሱን፡ኵሬ፡ሰባበሩ፥ናሱንም፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዱ።
18፤ምንቸቶቹንና፡መጫሪያዎችንም፡መኰስተሪያዎችንና፡ድስቶችን፡ጭልፋዎችንም፡የሚያገለግሉበትንም፡የናስ፡ዕ ቃ፡ዅሉ፡ወሰዱ።
19፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ጽዋዎቹንና፡ማንደጃዎቹን፡ድስቶቹንና፡ምንቸቶችን፡መቅረዞችንና፡ጭልፋዎቹን፡መንቀ ሎችንም፥የወርቁን፡ዕቃ፡በወርቅ፥የብሩንም፡ዕቃ፡በብር፡አድርጎ፥ወሰደ።
20፤ንጉሡ፡ሰሎሞንም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ያሠራቸውን፡ኹለቱን፡ዐምዶች፥አንዱንም፡ኵሬ፥ከመቀመጫዎቹም፡በታ ች፡የነበሩትን፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡የናስ፡በሬዎች፡ወሰደ፤ለእነዚህ፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ናስ፡ሚዛን፡አልነበረም።
21፤ዐምዶቹም፥የአንዱ፡ዐምድ፡ቁመት፡ዐሥራ፡ስምንት፡ክንድ፡ነበረ፥የዙሪያውም፡መጠን፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ ነበረ፤ውፍረቱም፡አራት፡ጣት፡ያኽል፡ነበረ፥ባዶም፡ነበረ።
22፤የናሱም፡ጕልላት፡በላዩ፡ነበረ፤የአንዱም፡ጕልላት፡ቁመት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥በጕልላቱም፡ላይ፡በዙሪ ያው፡ዅሉ፡ከናስ፡የተሠሩ፡መረበብና፡ሮማኖች፡ነበሩበት፤በኹለተኛውም፡ዐምድ፡ደግሞ፡እንደዚህ፡ያለ፡ነገርና ፡ሮማኖች፡ነበሩበት።
23፤በስተውጭም፡ዘጠና፡ስድስት፡ሮማኖች፡ነበሩ።በመረበቡም፡ዙሪያ፡የነበሩ፡ሮማኖች፡ዅሉ፡አንድ፡መቶ፡ነበሩ ።
24፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ታላቁን፡ካህን፡ሰራያን፡ኹለተኛውንም፡ካህን፡ሶፎንያስን፡ሦስቱንም፡በረኛዎች፡ወሰ ደ፤
25፤ከከተማዪቱም፡በሰልፈኛዎች፡ላይ፡ተሾመው፡ከነበሩት፡አንዱን፡ጃን፡ደረባ፥በከተማዪቱም፡ከሚገኙት፡በንጉ ሡ፡ፊት፡ከሚቆሙት፡ሰባቱን፡ሰዎች፥የአገሩንም፡ሕዝብ፡የሚያሰልፈውን፡የሰራዊቱን፡አለቃ፡ጸሓፊ፥በከተማዪቱ ም፡ከተገኙት፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡ስድሳ፡ሰዎች፡ወሰደ።
26፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወስዶ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለበት፡ወደ፡ሪብላ፡አመጣቸው።
27፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡መታቸው፥በሐማትም፡ምድር፡ባለችው፡በሪብላ፡ገደላቸው።እንዲሁ፡ይሁዳ፡ከአገሩ፡ተማረ ከ።
28፤ናቡከደነጾር፡የማረከው፡ሕዝብ፡ይህ፡ነው፤በሰባተኛው፡ዓመት፡ሦስት፡ሺሕ፡ኻያ፡ሦስት፡አይሁድ፤
29፤ናቡከደነጾርም፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡ስምንት፡መቶ፡ሠላሳ፡ኹለት፡ነፍስ፡ከኢየሩሳሌም፡ማርኳል፤
30፤በናቡከደነጾር፡በኻያ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ከአይሁድ፡ሰባት፡መቶ፡አርባ፡ዐ ምስት፡ነፍስ፡ማርኳል፤ሰዎች፡ዅሉ፡አራት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።
31፤እንዲህም፡ኾነ፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ዮአኪን፡በተማረከ፡በሠላሳ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ወር፡ከ ወሩም፡በኻያ፡ዐምስተኛው፡ቀን፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ዮርማሮዴክ፡በነገሠ፡በአንደኛው፡ዓመት፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡ የዮአኪንን፡ራስ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረገ፡ከወህኒም፡አወጣው፤
32፤በመልካምም፡ተናገረው፥ዙፋኑንም፡ከርሱ፡ጋራ፡በባቢሎን፡ከነበሩት፡ነገሥታት፡ዙፋን፡በላይ፡አደረገለት።
33፤በወህኒም፡ውስጥ፡ለብሶት፡የነበረውን፡ልብስ፡ለወጠለት፥ዮአኪንም፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡በፊቴ፡ዅልጊዜ ፡እንጀራ፡ይበላ፡ነበር።
34፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡እስኪሞት፡ድረስ፡የዘወትር፡ቀለብ፡ዕለት፡ዕለት፡ይሰጠው፡ነበ ር፨

http://www.gzamargna.net