ትንቢተ፡ኢሳይያስ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤በይሁዳ፡ነገሥታት፡በዖዝያንና፡በኢዮአታም፡በአካዝና፡በሕዝቅያስ፡ዘመን፡ስለ፡ይሁዳና፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ ያየው፡የዓሞጽ፡ልጅ፡የኢሳይያስ፡ራእይ።
2፤እግዚአብሔር፡ተናግሯልና፥ሰማያት፡ስሙ፥ምድርም፡አድምጪ፤ልጆችን፡ወለድኹ፡አሳደግኹም፥እነርሱም፡ዐመፁብ ኝ።
3፤በሬ፡የገዢውን፡አህያም፡የጌታውን፡ጋጣ፡ዐወቀ፤እስራኤል፡ግን፡አላወቀም፥ሕዝቤም፡አላስተዋለም።
4፤ኀጢአተኛ፡ወገንና፡በደል፡የተሞላበት፡ሕዝብ፥የክፉዎች፡ዘር፥ርኵሰትን፡የምታደርጉ፡ልጆች፡ሆይ፥ወዮላችኹ! እግዚአብሔርን፡ትተዋል፡የእስራኤልንም፡ቅዱስ፡አቃለ፟ዋል፥ወደ፡ዃላቸውም፡እየኼዱ፡ተለይተዋል።
5፤ደግሞስ፡ዐመፃ፡እየጨመራችኹ፡ለምን፡ገና፡ትቀሰፋላችኹ፧ራስ፡ዅሉ፡ለሕመም፥ልብም፡ዅሉ፡ለድካም፡ኾኗል።
6፤ከእግር፡ጫማ፡አንሥቶ፡እስከ፡ራስ፡ድረስ፡ጤና፡የለውም፤ቍስልና፡ዕበጥ፡የሚመግልም፡ነው፤አልፈረጠም፥አል ተጠገነም፥በዘይትም፡አልለዘበም።
7፤ምድራችኹ፡ባድማ፡ናት፤ከተማዎቻችኹ፡በእሳት፡ተቃጠሉ፤ዕርሻችኹንም፡በፊታችኹ፡ሌላዎች፡ይበሉታል፤ባዕድ፡ እንዳፈረሳት፡ምድር፡ባድማ፡ኾነች።
8፤የጽዮንም፡ሴት፡ልጅ፡በወይን፡ቦታ፡እንዳለ፡ዳስ፥በዱባ፡አትክልትም፡እንዳለ፡ጐዦ፥አንደ፡ተከበበችም፡ከተ ማ፡ኾና፡ቀረች።
9፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ዘርን፡ባያስቀርልን፡ኖሮ፥እንደ፡ሰዶም፡በኾንነ፡እንደ፡ገሞራም፡በመሰልነ፡ ነበር።
10፤እናንተ፡የሰዶም፡አለቃዎች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤እናንተ፡የገሞራ፡ሕዝብ፡ሆይ፥የአምላካችን ን፡ሕግ፡አድምጡ።
11፤የመሥዋዕታችኹ፡ብዛት፡ለእኔ፡ምን፡ይጠቅመኛል፧ይላል፡እግዚአብሔር፤የሚቃጠለውን፡የአውራ፡በግ፡መሥዋዕ ትንና፡የፍሪዳን፡ስብ፡ጠግቤያለኹ፤የበሬና፡የበግ፡ጠቦት፡የአውራ፡ፍየልም፡ደም፡ደስ፡አያሠኘኝም።
12፤በእኔ፡ፊት፡ልትታዩ፡ብትመጡ፡ይህን፡የመቅደሴን፡አደባባይ፡መርገጣችኹን፡ከእጃችኹ፡የሚሻ፡ማን፡ነው፧
13፤ምናምንቴውን፡ቍርባን፡ጨምራችኹ፡አታምጡ፤ዕጣን፡በእኔ፡ዘንድ፡አጸያፊ፡ነው፤መባቻችኹንና፡ሰንበታችኹን ፡በጉባኤ፡መሰብሰባችኹን፡አልወድ፟ም፤በደልንም፡የተቀደሰውንም፡ጉባኤ፡አልታገሥም።
14፤መባቻችኹንና፡በዓላቶቻችኹን፡ነፍሴ፡ጠልታለች፤ሸክም፡ኾነውብኛል፥ልታገሣቸውም፡ደክሜያለኹ።
15፤እጃችኹንም፡ወደ፡እኔ፡ብትዘረጉ፡ዐይኔን፡ከእናንተ፡እሰውራለኹ፥ልመናንም፡ብታበዙ፡አልሰማችኹም፤እጆቻ ችኹ፡ደም፡ተሞልተዋል።
16፤ታጠቡ፡ሰውነታችኹንም፡አንጹ፤የሥራችኹን፡ክፋት፡ከዐይኔ፡ፊት፡አስወግዱ፤ክፉ፡ማድረግን፡ተዉ፥
17፤መልካም፡መሥራትን፡ተማሩ፥ፍርድን፡ፈልጉ፥የተገፋውን፡አድኑ፥ለድኻ፡አደጉ፡ፍረዱለት፡ስለ፡መበለቲቱም፡ ተሟገቱ።
18፤ኑና፡እንዋቀስ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤ኀጢአታችኹ፡እንደ፡ዐለላ፡ብትኾን፡እንደ፡ዐመዳይ፡ትነጻለች፤እንደ ፡ደምም፡ብትቀላ፡እንደ፡ባዘቶ፡ትጠራለች።
19፤ዕሺ፡ብትሉ፡ለኔም፡ብትታዘዙ፥የምድርን፡በረከት፡ትበላላችኹ፤
20፤እምቢ፡ብትሉ፡ግን፡ብታምፁም፥ሰይፍ፡ይበላችዃል፤የእግዚአብሔር፡አፍ፡ይህን፡ተናግሯልና፦
21፤ፍርድ፡ሞልቶባት፡የነበረው፡የታመነችዪቱ፡ከተማ፡እንዴት፡ጋለሞታ፡ኾነች! ጽድቅ፡ዐድሮባት፡ነበር፥አኹን፡ግን፡ገዳዮች፡አሉባት።
22፤ብርሽ፡ወደ፡ዝገት፡ተለወጠ፤የወይን፡ጠጅሽ፡ከውሃ፡ጋራ፡ተደባለቀ።
23፤አለቃዎችሽ፡ዐመፀኛዎችና፡የሌቦች፡ባልንጀራዎች፡ኾኑ፤ዅሉ፡ጕቦ፡ይወዳ፟ሉ፥ዋጋም፡ለማግኘት፡ይሮጣሉ፤ለ ድኻ፡አደጉ፡አይፈርዱም፥የመበለቲቱም፡ሙግት፡ወደ፡እነርሱ፡አይደርስም።
24፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡ኀያል፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በጠላቶቼ፡ላይ፡ቍጣዬን፡እፈጽ ማለኹ፥የሚቋቋሙኝንም፡እበቀላለኹ።
25፤እጄንም፡ባንቺ፡ላይ፡አመጣለኹ፥ዝገትሽንም፡በጣም፡አነጻለኹ፥ቈርቈሮሽንም፡ዅሉ፡አወጣለኹ፤
26፤ፈራጆችሽንም፡እንደ፡ቀድሞ፡አማካሪዎችሽንም፡እንደ፡መዠመሪያው፡ጊዜ፡መልሼ፡አስነሣለኹ፤ከዚያም፡በዃላ ፡የጽድቅ፡ከተማ፡የታመነችም፡ከተማ፡ተብለሽ፡ትጠሪያለሽ።
27፤ጽዮን፡በፍርድ፡ከርሷም፡የሚመለሱ፡በጽድቅ፡ይድናሉ።
28፤በደለኛዎችና፡ኀጢአተኛዎች፡ግን፡በአንድነት፡ይሰበራሉ፥እግዚአብሔርንም፡የሚተዉ፡ይጠፋሉ።
29፤በወደዳችዃት፡የአድባር፡ዛፍ፡ታፍራላችኹና፥ስለ፡መረጣችዃትም፡አትክልት፡ዕፍረት፡ይይዛችዃልና፤
30፤ቅጠሏ፡እንደ፡ረገፈ፡ዛፍ፥ውሃም፡እንደሌለባት፡አትክልት፡ትኾናላችኹና።
31፤ኀይለኛውም፡እንደ፡ተልባ፡ጭረት፥ሥራውም፡እንደ፡ጠለሸት፡ይኾናል፤ዐብረውም፡ይቃጠላሉ፡እነርሱንም፡የሚ ያጠፋ፡የለም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ስለ፡ይሁዳና፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ያየው፡ቃል።
2፤በዘመኑም፡ፍጻሜ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ተራራ፡በተራራዎች፡ራስ፡ላይ፡ጸንቶ፡ይቆማል፥ከኰረብታዎችም፡በላይ ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፥አሕዛብም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ይሰበሰባሉ።
3፤ሕግ፡ከጽዮን፡የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ከኢየሩሳሌም፡ይወጣልና፥ብዙዎች፡አሕዛብ፡ኼደው፦ኑ፥ወደእግዚአብሔር ፡ተራራ፥ወደያዕቆብ፡አምላክ፡ቤት፡እንውጣ፤ርሱም፡መንገዱን፡ያስተምረናል፥በጐዳናውም፡እንኼዳለን፡ይላሉ።
4፤በአሕዛብም፡መካከል፡ይፈርዳል፥በብዙ፡አሕዛብም፡ላይ፡ይበይናል፤ሰይፋቸውንም፡ማረሻ፡ጦራቸውንም፡ማጭድ፡ ለማድረግ፡ይቀጠቅጣሉ፤ሕዝብም፡በሕዝብ፡ላይ፡ሰይፍ፡አያነሣም፥ሰልፍም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይማሩም።
5፤እናንተ፡የያዕቆብ፡ቤት፡ሆይ፥ኑ፥በእግዚአብሔር፡ብርሃን፡እንኺድ።
6፤ሕዝብኽን፡የያዕቆብን፡ቤት፡ትተኻልና፤ይኸውም፡የምሥራቅን፡ሰዎች፡ዐመል፡ስለ፡ተሞሉ፥እንደ፡ፍልስጥኤማው ያንም፡ሟርተኛዎች፡ስለ፡ኾኑ፥ከባዕድ፡ልጆችም፡ጋራ፡ስለ፡ተባበሩ፡ነው።
7፤ምድራቸው፡በብርና፡በወርቅ፡ተሞልታለች፥ለመዛግብቶቻቸውም፡ፍጻሜ፡የለውም፤ምድራቸውም፡ደግሞ፡በፈረሶች፡ ተሞልታለች፥ለሠረገላዎቻቸውም፡ፍጻሜ፡የለውም።
8፤ምድራቸው፡ደግሞ፡በጣዖታት፡ተሞልታለች፤ጣቶቻቸውም፡ላደረጉት፡ለእጃቸው፡ሥራ፡ይሰግዳሉ።
9፤ታናሹም፡ሰው፡ዝቅ፡ብሏል፥ጨዋውም፡ተዋርዷል፤ኀጢአታቸውንም፡ይቅር፡አትበላቸው።
10፤ከእግዚአብሔር፡ማስደንገጥና፡ከግርማው፡ክብር፡የተነሣ፡ወደድንጋይ፡ዋሻ፡ግባ፥በመሬትም፡ውስጥ፡ተሸሸግ ።
11፤ከፍ፡ያለችውም፡የሰው፡ዐይን፡ትዋረዳለች፥የሰዎችም፡ኵራት፡ትወድቃለች፥በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ብቻ ውን፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።
12፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡በትዕቢተኛውና፡በኵራተኛው፡ዅሉ፡ላይ፡ከፍ፡ባለውም፡ላይ፡ይኾናል፥ ርሱም፡ይዋረዳል፤
13፤ደግሞም፡በረዥሙ፡ከፍ፡ባለው፡በሊባኖስ፡ዝግባ፡ዅሉ፡ላይ፥በባሳንም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ላይ፥
14፤በረዥሙም፡ተራራ፡ዅሉ፡ላይ፥ከፍ፡ባለውም፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፥
15፤በረዥሙም፡ግንብ፡ዅሉ፡ላይ፥በተመሸገውም፡ቅጥር፡ዅሉ፡ላይ፥
16፤በተርሴስም፡መርከብ፡ዅሉ፡ላይ፥በሚያማምሩ፡ጣዖታትም፡ዅሉ፡ላይ፡ይኾናል።
17፤ሰውም፡ዅሉ፡ይዋረዳል፥የሰውም፡ኵራት፡ይወድቃል፥በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ብቻ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።
18፤ጣዖቶቻቸውም፡ዅሉ፡ፈጽመው፡ይጠፋሉ።
19፤እግዚአብሔርም፡ምድርን፡ያናውጥ፡ዘንድ፡በተነሣ፡ጊዜ፥ሰዎች፡ከማስደንገጡና፡ከግርማው፡ክብሩ፡የተነሣ፥ ወደድንጋይ፡ዋሻና፡ወደምድር፡ንቃቃት፡ውስጥ፡ይገባሉ።
20፤በዚያን፡ቀን፡ሰው፡ይሰግድላቸው፡ዘንድ፡ያበጇቸውን፡የብሩንና፡የወርቁን፡ጣዖቶቹን፡ለፍልፈልና፡ለሌሊት ፡ወፍ፡ይጥላል።
21፤እግዚአብሔርም፡ምድርን፡ያናውጥ፡ዘንድ፡በተነሣ፡ጊዜ፡ከማስደንገጡና፡ከግርማው፡ክብር፡የተነሣ፡ወደድን ጋይ፡ዋሻና፡ወደተሰነጠቁ፡አለቶች፡ውስጥ፡ይገባሉ።
22፤እስትንፋሱ፡በአፍንጫው፡ውስጥ፡ያለበትን፡ሰው፡ተዉት፤ርሱ፡ስለ፡ምን፡ይቈጠራል፧
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤እንሆ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ከኢየሩሳሌምና፡ከይሁዳ፡ድጋፍንና፡ብርታትን፥የእንጀራን፡ድጋፍ፡ዅሉ ፡የውሃውንም፡ድጋፍ፡ዅሉ፥
2፤ኀያሉንም፥ተዋጊውንም፥ፈራጁንም፥ነቢዩንም፥ሟርተኛውንም፥
3፤ሽማግሌውንም፥የዐምሳ፡አለቃውንም፥ከበርቴውንም፥አማካሪውንም፥ብልኁንም፡ሠራተኛ፥አስማት፡ዐዋቂውንም፡ይ ነቅላል።
4፤አለቃዎቻቸው፡እንዲኾኑ፡ብላቴናዎችን፡አስነሣባቸዋለኹ፥ሕፃናትም፡ይገዟቸዋል።
5፤ሕዝቡም፥ሰው፡በሰው፡ላይ፡ሰውም፡በባልንጀራው፡ላይ፥ይገፋፋል፤ብላቴናውም፡በሽማግሌው፡ላይ፡የተጠቃውም፡ በከበርቴው፡ላይ፡ይኰራል።
6፤ሰውም፡በአባቱ፡ቤት፡ውስጥ፡ወንድሙን፡ይዞ፦አንተ፡ልብስ፡አለኽ፡አለቃም፡ኹንልን፡ይህችም፡ባድማ፡ከእጅኽ ፡በታች፡ትኹን፡ሲለው፥
7፤በዚያ፡ቀን፡ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፦እኔ፡በቤቴ፡ውስጥ፡እንጀራ፡ወይም፡ልብስ፡የለኝምና፡ባለመድኀኒት፡አል ኾንም፤በሕዝቡም፡ላይ፡አለቃ፡አታደርጉኝም፡ይላል።
8፤የክብሩን፡ዐይን፡ያስቈጡ፡ዘንድ፡ምላሳቸውና፡ሥራቸው፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ነውና፥ኢየሩሳሌም፡ተፈታች፥ይ ሁዳም፡ወደቀ።
9፤የፊታቸውም፡ዕፍረት፡ይመሰክርባቸዋል፤እንደ፡ሰዶምም፡ኀጢአታቸውን፡ያወራሉ፥አይሰውሯትም።በራሳቸው፡ላይ ፡ክፉ፡ነገርን፡ሠርተዋልና፥ለነፍሳቸው፡ወዮ!
10፤የሥራቸውን፡ፍሬ፡ይበላሉና፡ጻድቁን፦መልካም፡ይኾንልኻል፡በሉት።
11፤እንደ፡እጁ፡ሥራ፡ፍዳው፡ይደረግበታልና፥ለበደለኛ፡ወዮ! ክፉም፡ደርሶበታል።
12፤ሕዝቤንስ፡አስገባሪዎቻቸው፡ይገፏቸዋል፥አስጨናቂዎችም፡ይሠለጥኑባቸዋል።ሕዝቤ፡ሆይ፥የመሯችኹ፡ያስቷች ዃል፡የምትኼዱበትንም፡መንገድ፡ያጠፋሉ።
13፤እግዚአብሔር፡ለፍርድ፡ተነሥቷል፡በሕዝቡም፡ላይ፡ሊፈርድ፡ቆሟል።
14፤እግዚአብሔር፡ከሕዝቡ፡ሽማግሌዎችና፡ከአለቃዎቻቸው፡ጋራ፡ይፋረዳል፤የወይኑን፡ቦታ፡የጨረሳችኹ፡እናንተ ፡ናችኹ፤ከድኻዎች፡የበዘበዛችኹት፡በቤታችኹ፡አለ፤
15፤ሕዝቤንም፡ለምን፡ታደቋ፟ቸዋላችኹ፧የድኻዎችንስ፡ፊት፡ለምን፡ትፈጫላችኹ፧ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአ ብሔር።
16፤ደግሞም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አለ፦የጽዮን፡ቈነዣዥት፡ኰርተዋልና፥ዐንገታቸውንም፡እያሰገጉ፡በዐይናቸ ውም፡እያጣቀሱ፥ፈንጠርም፡እያሉ፥በእግራቸውም፡እያቃጨሉ፡ይኼዳሉና፥
17፤ስለዚህ፥ጌታ፡የጽዮንን፡ቈነዣዥት፡ዐናት፡በቡሓነት፡ይመታል፥እግዚአብሔርም፡ኀፍረተ፡ሥጋቸውን፡ይገልጣ ል።
18፤በዚያም፡ቀን፡ጌታ፡የእግር፡አልቦውን፡ክብር፥መርበብንም፥ጨረቃ፡የሚመስለውንም፡ጌጥ፥የዦሮ፡እንጥልጥሉ ንም፥
19፤አንባሩንም፥መሸፈኛውንም፥ቀጸላውንም፥
20፤ሰንሰለቱንም፥መቀነቱንም፥የሽቱውንም፡ዕቃ፥
21፤ዐሸን፡ክታቡንም፥የእጅና፡የአፍንጫ፡ቀለበቱንም፥
22፤የዓመት፡በዓልንም፡ልብስ፥መጐናጸፊያውንም፥ልግም፡በገላውንም፥ከረጢቱንም፥
23፤መስተዋቱንም፥ከጥሩ፡በፍታ፡የተሠራውንም፡ልብስ፥ራስ፡ማሰሪያውንም፥ዐይነ፡ርግቡንም፡ያስወግዳል።
24፤እንዲህም፡ይኾናል፤በሽቱ፡ፋንታ፡ግማት፥በመታጠቂያውም፡ፋንታ፡ገመድ፥ጠጕርንም፡በመንቀስ፡ፋንታ፡ቡሓነ ት፥በመጐናጸፊያ፡ፋንታ፡ማቅ፥በውበትም፡ፋንታ፡ጠባሳ፡ይኾናል።
25፤ጕልማሳዎችሽ፡በሰይፍ፥ኀያላንሽም፡በውጊያ፡ይወድቃሉ።
26፤በሮቿ፡ያዝናሉ፡ያለቅሱማል፤ርሷም፡ብቻዋን፡በምድር፡ላይ፡ትቀመጣለች።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤በዚያም፡ቀን፡ሰባት፡ሴቶች።የገዛ፡እንጀራችንን፡እንበላለን፡የገዛ፡ልብሳችንንም፡እንለብሳለን፤ስምኽ፡ብ ቻ፡በእኛ፡ላይ፡ይጠራ፥መሰደባችንንም፡አርቅ፡ብለው፡አንዱን፡ወንድ፡ይይዙታል።
2፤በዚያም፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቍጥቋጥ፡ለጌጥና፡ለክብር፡ይኾናል፥ከእስራኤልም፡ወገን፡ላመለጡ፡ሰዎች፡የም ድሪቱን፡ፍሬ፡ለትምክሕትና፡ለውበት፡ይኾናል።
3፤4፤ጌታም፡የጽዮንን፡ቈነዣዥት፡እድፍ፡ባጠበ፡ጊዜ፥የኢየሩሳሌምንም፡ደም፡በፍርድ፡መንፈስና፡በሚያቃጥል፡ መንፈስ፡ከመካከሏ፡ባነጻ፡ጊዜ፥በጽዮን፡የቀረ፡በኢየሩሳሌምም፡የተረፈ፥በኢየሩሳሌም፡ለሕይወት፡የተጻፈ፡ዅ ሉ፥ቅዱስ፡ይባላል።
5፤እግዚአብሔርም፡በጽዮን፡ተራራ፡ላይ፡ባለ፡ማደሪያ፡ዅሉ፡በጉባኤያቸውም፡ላይ፡በቀን፡ዳመናንና፡ጢስን፡በሌ ሊትም፡የሚቃጠለውን፡የእሳት፡ብርሃን፡ይፈጥራል፤በክብርም፡ዅሉ፡ላይ፡መጋረጃ፡ይኾናል።
6፤በቀን፡ከሙቀት፡ለጥላ፥ከዐውሎ፡ነፋስና፡ከዝናብም፡ለመጠጊያና፡ለመሸሸጊያ፡ጐዦ፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤አኹን፡ስለ፡ወዳጄና፡ስለወይን፡ቦታው፡ለወዳጄ፡ቅኔ፡እቀኛለኹ።ለወዳጄ፡በፍሬያማው፡ኰረብታ፡ላይ፡የወይን ፡ቦታ፡ነበረው።
2፤በዙሪያው፡ቈፈረ፥ድንጋዮችንም፡ለቅሞ፡አወጣ፥ምርጥ፡የኾነውንም፡ዐረግ፡ተከለበት፥በመካከሉም፡ግንብ፡ሠራ ፥ደግሞም፡የመጥመቂያ፡ጕድጓድ፡ማሰበት፤ወይንንም፡ያፈራ፡ዘንድ፡ተማመነ፥ዳሩ፡ግን፡ሖምጣጣ፡ፍሬ፡አፈራ።
3፤አኹንም፡እናንተ፡በኢየሩሳሌም፡የምትኖሩ፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ሆይ፥በእኔና፡በወይኑ፡ቦታዬ፡መካከል፡እስኪ፡ፍ ረዱ።
4፤ለወይኔ፡ያላደረግኹለት፥ከዚህ፡ሌላ፡አደርግለት፡ዘንድ፡የሚገ፟ባ፟ኝ፡ምንድር፡ነው፧ወይንን፡ያፈራል፡ብዬ ፡ስተማመን፡ስለ፡ምን፡ሖምጣጣ፡ፍሬ፡አፈራ፧
5፤አኹንም፡በወይኔ፡ላይ፡የማደርገውን፡እነግራችዃለኹ፤ዐጥሩን፡እነቅላለኹ፥ለማሰማሪያም፡ይኾናል፤ቅጥሩንም ፡አፈርሳለኹ፥ለመራገጫም፡ይኾናል።
6፤ባድማ፡አደርገዋለኹ፤አይቈረጥም፥አይኰተኰትም፤ኵርንችትና፡ሾኽ፡ይበቅልበታል፤ዝናብንም፡እንዳያዘንቡበት ፡ዳመናዎችን፡አዛ፟ለኹ።
7፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ወይን፡ቦታ፡ርሱ፡የእስራኤል፡ቤት፡ነው፥የደስታውም፡አትክልት፡የይሁዳ፡ሰ ዎች፡ናቸው፤ፍርድን፡ተስፋ፡ያደርግ፡ነበር፥እንሆም፡ደም፡ማፍሰስ፡ኾነ፤ጽድቅንም፡ይተማመን፡ነበር፥እንሆም ፥ጩኸት፡ኾነ።
8፤ስፍራ፡እስከማይቀር፡ድረስ፡እናንተም፡በምድር፡ላይ፡ብቻችኹን፡እስክትቀመጡ፡ድረስ፥ቤትን፡ከቤት፡ጋራ፡ለ ሚያያይዙ፡ዕርሻንም፡ከዕርሻ፡ጋራ፡ለሚያቀራርቡ፡ወዮላቸው!
9፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በዦሮዬ፡እንዲህ፡አለ፦በእውነት፡ብዙ፡ታላቅና፡መልካም፡ቤት፡ባድማ፡ይኾናል ፥የሚቀመጥበትም፡አይገኝም።
10፤ከወይኑ፡ቦታ፡ዐሥር፡ጥማድ፡በሬ፡ካረሰው፡አንድ፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ብቻ፡ይወጣል፤አንድ፡የቆሮስ፡መስፈ ሪያ፡ዘር፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ብቻ፡ይሰጣል።
11፤ስካርን፡ለመከተል፡በጧት፡ለሚማልዱ፥የወይን፡ጠጅም፡እስኪያቃጥላቸው፡እስከ፡ሌሊት፡ድረስ፡ለሚዘገዩ፡ወ ዮላቸው!
12፤መሰንቆና፡በገና፡ከበሮና፡እንቢልታም፡የወይን፡ጠጅም፡በግብዣቸው፡አለ፤የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡ግን፡አል ተመለከቱም፥እጁም፡ያደረገችውን፡አላስተዋሉም።
13፤ስለዚህ፥ሕዝቤ፡ወደ፡ምርኮ፡ኼዱ፥ጌታን፡አላወቁትምና፤ከበርቴዎቻቸውም፡ተራቡ፥ሕዝባቸውም፡ተጠሙ።
14፤ሲኦልም፡ሆዷን፡አስፍታለች፥አፏንም፡ያለልክ፡ከፍታለች፤ከበርቴዎቻቸውና፡ዐዛውንቶቻቸው፡ባለጠጋዎቻቸው ም፡ደስተኛዎቻቸውም፡ወደ፡ርሷ፡ይወርዳሉ።
15፤ሰውም፡ይጐሰቍላል፥ሰውም፡ይዋረዳል፥የትዕቢተኛዎችም፡ዐይን፡ትዋረዳለች፤
16፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ግን፡በፍርድ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏል፥ቅዱሱም፡አምላክ፡በጽድቅ፡ተቀድሷል።
17፤የበግ፡ጠቦቶች፡በማሰማሪያቸው፡ውስጥ፡ይሰማራሉ፥እንግዳዎችም፡የሰቡትን፡ባድማ፡ይበላሉ።
18፤በደልን፡በምናምንቴ፡ገመድ፥ኀጢአትንም፡በሠረገላ፡ማሰሪያ፡ወደ፡ራሳቸው፡ለሚስቡ፦እናይ፡ዘንድ፡ይቸኵል ፥
19፤ሥራውንም፡ያፋጥን፤እናውቃትም፡ዘንድ፡የእስራኤል፡ቅዱስ፡ምክር፡ትቅረብ፥ትምጣ፡ለሚሉ፡ወዮላቸው!
20፤ክፉውን፡መልካም፡መልካሙን፡ክፉ፡ለሚሉ፥ጨለማውን፡ብርሃን፡ብርሃኑንም፡ጨለማ፡ለሚያደርጉ፥ጣፋጩን፡መራ ራ፡መራራውንም፡ጣፋጭ፡ለሚያደርጉ፡ወዮላቸው!
21፤በዐይናቸው፡ጥበበኛዎች፡በነፍሳቸውም፡አስተዋዮች፡ለኾኑ፡ወዮላቸው!
22፤የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጣት፡ኀያላን፡የሚያሰክረውንም፡ለማደባለቅ፡ጨካኞች፡ለኾኑ፤
23፤በደለኛውን፡ስለ፡ጕቦ፡ጻድቅ፡ለሚያደርጉ፥የጻድቁንም፡ጽድቅ፡ለሚያስወግዱበት፡ወዮላቸው!
24፤ስለዚህ፥የእሳት፡ወላፈን፡ቃርሚያን፡እንደሚበላ፥እብቅም፡በነበልባል፡ውስጥ፡እንደሚጠፋ፥እንዲሁ፡የእነ ርሱ፡ሥር፡የበሰበሰ፡ይኾናል፥ቡቃያቸውም፡እንደ፡ትቢያ፡ይበና፟ል፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ጥ ለዋልና፥የእስራኤልም፡ቅዱስ፡የተናገረውን፡ቃል፡አቃለ፟ዋልና።
25፤ስለዚህ፥የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ነዷ፟ል፥እጁንም፡በላያቸው፡ዘርግቶ፡መትቷቸዋል፤ተራራዎችም ፡ተንቀጠቀጡ፥ሬሳቸውም፡በአደባባይ፡መካከል፡እንደ፡ጕድፍ፡ኾኗል።በዚህም፡ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰች ም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።
26፤ለአሕዛብም፡በሩቅ፡ምልክትን፡ያቆማል፥ከምድርም፡ዳርቻ፡በፉጨት፡ይጠራቸዋል፤እንሆም፥እየተጣደፉ፡ፈጥነ ው፡ይመጣሉ።
27፤ደካማና፡ስንኵል፡የለባቸውም፥የሚያንቀላፋና፡የሚተኛም፡የለም፤የወገባቸውም፡መቀነት፡አይፈታም፥የጫማቸ ውም፡ማዘቢያ፡አይበጠስም።
28፤ፍላጻዎቻቸው፡ተስለዋል፥ቀስቶቻቸውም፡ዅሉ፡ተለጥጠዋል፤የፈረሶቻቸውም፡ኰቴ፡እንደ፡ቡላድ፡የሠረገላዎቻ ቸውም፡መንኰራኵር፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይቈጠራል።
29፤ጩኸታቸው፡እንደ፡አንበሳ፡ነው፥እንደ፡አንበሳ፡ደቦሎችም፡ያገሣሉ፤ንጥቂያንም፡ይዘው፡ያገሣሉ፥ይወስዱት ማል፥የሚያድንም፡የለም።
30፤በዚያም፡ቀን፡እንደ፡ባሕር፡መትመም፡ይተምሙባቸዋል፤ወደ፡ምድርም፡ቢመለከቱ፥እንሆ፥ጨለማና፡መከራ፡አለ ፤ብርሃንም፡በደመናዎቿ፡ውስጥ፡ጨልሟል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤ንጉሡ፡ዖዝያን፡በሞተበት፡ዓመት፡እግዚአብሔርን፡በረዥምና፡ከፍ፡ባለ፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀምጦ፡አየኹት፥የልብ ሱም፡ዘርፍ፡መቅደሱን፡ሞልቶት፡ነበር።
2፤ሱራፌልም፡ከርሱ፡በላይ፡ቆመው፡ነበር፥ለያንዳንዱም፡ስድስት፡ክንፍ፡ነበረው፤በኹለት፡ክንፍ፡ፊቱን፡ይሸፍ ን፡ነበር፥በኹለቱም፡ክንፍ፡እግሮቹን፡ይሸፍን፡ነበር፥በኹለቱም፡ክንፍ፡ይበር፡ነበር።
3፤አንዱም፡ለአንዱ፦ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ምድር፡ዅሉ፡ከክብሩ፡ተሞልታለች፡እያ ለ፡ይጮኽ፡ነበር።
4፤የመድረኩም፡መሠረት፡ከጯኺው፡ድምፅ፡የተነሣ፡ተናወጠ፥ቤቱንም፡ጢስ፡ሞላበት።
5፤እኔም፦ከንፈሮቼ፡የረከሱብኝ፡ሰው፡በመኾኔ፥ከንፈሮቻቸውም፡በረከሱባቸው፡ሕዝብ፡መካከል፡በመቀመጤ፡ዐይኖ ቼ፡የሰራዊትን፡ጌታ፡ንጉሡን፡እግዚአብሔርን፡ስለ፡አዩ፡ጠፍቻለኹና፡ወዮልኝ! አልኹ።
6፤ከሱራፌልም፡አንዱ፡እየበረረ፡ወደ፡እኔ፡መጣ፥በእጁም፡ከመሠዊያው፡በጕጠት፡የወሰደው፡ፍም፡ነበረ።
7፤አፌንም፡ዳሰሰበትና፦እንሆ፥ይህ፡ከንፈሮችኽን፡ነክቷል፤በደልኽም፡ከአንተ፡ተወገደ፥ኀጢአትኽም፡ተሰረየል ኽ፡አለኝ።
8፤የጌታንም፡ድምፅ፦ማንን፡እልካለኹ፧ማንስ፡ይኼድልናል፧ሲል፡ሰማኹ።እኔም፦እንሆኝ፥እኔን፡ላከኝ፡አልኹ።
9፤ርሱም፦ኺድ፥ይህን፡ሕዝብ፦መስማትን፡ትሰማላችኹ፡አታስተውሉምም፤ማየትንም፡ታያላችኹ፡አትመለከቱምም፡በላ ቸው።
10፤በዐይናቸው፡እንዳያዩ፥በዦሯቸውም፡እንዳይሰሙ፥በልባቸውም፡እንዳያስተውሉ፥ተመልሰውም፡እንዳይፈወሱ፥የ ዚህን፡ሕዝብ፡ልብ፡አደንድን፥ዦሯቸውንም፡አደንቍር፥ዐይናቸውንም፡ጨፍን፡አለኝ።
11፤እኔም፦ጌታ፡ሆይ፥እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ነው፧አልኹ።ርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ከተማዎች፡የሚኖርባቸውን፡ ዐጥተው፡እስኪፈርሱ፡ድረስ፥ቤቶችም፡ሰው፡አልቦ፡እስኪኾኑ፡ምድርም፡ፈጽሞ፡ባድማ፡ኾና፡እስክትቀር፡ድረስ፥
12፤እግዚአብሔርም፡ሰዎችን፡እስኪያርቅ፥በምድርም፡መካከል፡ውድማው፡መሬት፡እስኪበዛ፡ድረስ፡ነው።
13፤በርሷም፡ዘንድ፡ዐሥረኛ፡እጅ፡ቀርቶ፡እንደ፡ኾነ፡ርሱ፡ደግሞ፡ይቃጠላል፤በተቈረጡ፡ጊዜ፡ጕቶቻቸው፡እንደ ፡ቀሩ፡እንደ፡ግራርና፡እንደ፡ኮምበል፡ዛፍ፡ኾኖ፥ጕቶው፡የተቀደሰ፡ዘር፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዖዝያን፡ልጅ፡በኢዮአታም፡ልጅ፡በአካዝ፡ዘመን፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ረአሶን፡ የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ኢየሩሳሌምን፡ሊወጉ፡ወጡ፥ሊያሸንፏትም፡አልቻሉም።
2፤ለዳዊትም፡ቤት፦ሶርያ፡ከኤፍሬም፡ጋራ፡ተባብረዋል፡የሚል፡ወሬ፡ተነገረ፤የርሱም፡ልብ፡የሕዝቡም፡ልብ፡የዱ ር፡ዛፍ፡በነፋስ፡እንድትናወጥ፡ተናወጠ።
3፤እግዚአብሔርም፡ኢሳይያስን፡አለው፦አንተና፡ልጅኽ፡ያሱብ፡አካዝን፡ትገናኙት፡ዘንድ፡በልብስ፡ዐጣቢው፡ዕር ሻ፡መንገድ፡ወዳለው፡ወደ፡ላይኛው፡የኵሬ፡መስኖ፡ጫፍ፡ውጡ፤
4፤እንዲህም፡በለው፦ተጠበቅ፥ዝምም፡በል፤ስለ፡እነዚህ፡ስለሚጤሱ፡ስለ፡ኹለት፡የዕንጨት፡ጠለሸቶች፥ስለ፡ሶር ያና፡ስለ፡ረአሶን፡ስለ፡ሮሜልዩም፡ልጅ፡ቍጣ፡አትፍራ፥ልብኽም፡አይድከም።
5፤6፤ሶርያና፡ኤፍሬም፣የሮሜልዩም፡ልጅ፦ወደ፡ይሁዳ፡እንውጣ፡እናስጨንቀውም፥እንስበረውም፥የጣብኤልንም፡ል ጅ፡እናንግሥበት፡ብለው፡ክፋት፡ስለ፡መከሩብኽ፤
7፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ምክር፡አይጸናምና፥አይኾንም።
8፤የሶርያ፡ራስ፡ደማስቆ፡ነው፥የደማስቆም፡ራስ፡ረአሶን፡ነው፤በስድሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ውስጥ፡ኤፍሬም፡ይሰባ በራልና፥ሕዝብ፡አይኾንም፤
9፤የኤፍሬምም፡ራስ፡ሰማርያ፡ነው፥የሰማርያም፡ራስ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ነው።ባታምኑ፡አትጸኑም።
10፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡አካዝን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
11፤ከጥልቁ፡ወይም፡ከከፍታው፡ቢኾን፡ከአምላክኽ፡ከእግዚአብሔር፡ምልክትን፡ለምን።
12፤አካዝም፦አልለምንም፥እግዚአብሔርንም፡አልፈ፟ታተንም፡አለ።
13፤ርሱም፡አለ፦እናንተ፡የዳዊት፡ቤት፡ሆይ፥ስሙ፤በእውኑ፡ሰውን፡ማድከማችኹ፡ቀላል፡ነውን፧አምላኬን፡ደግሞ ፡የምታደክሙ፤
14፤ስለዚህ፥ጌታ፡ራሱ፡ምልክት፡ይሰጣችዃል፤እንሆ፥ድንግል፡ትፀንሳለች፥ወንድ፡ልጅም፡ትወልዳለች፥ስሙንም፡ ዐማኑኤል፡ብላ፡ትጠራዋለች።
15፤ክፉን፡ለመጥላት፡መልካሙንም፡ለመምረጥ፡ሲያውቅ፡ቅቤና፡ማር፡ይበላል።
16፤ሕፃኑ፡ክፉን፡ለመጥላት፡መልካሙን፡ለመምረጥ፡ሳያውቅ፡የፈራኻቸው፡የኹለቱ፡ነገሥታት፡አገር፡ባድማ፡ትኾ ናለች።
17፤እግዚአብሔርም፡ኤፍሬም፡ከይሁዳ፡ከተለየበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ያልመጣውን፡ዘመን፡በአንተና፡በሕዝብኽ፡በአባ ትኽም፡ቤት፡ላይ፡ያመጣል፤ርሱም፡የአሶር፡ንጉሥ፡መምጣት፡ነው።
18፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡በግብጽ፡ወንዝ፡ዳርቻ፡ያለውን፡ዝምብ፡በአሶርም፡አገር፡ያ ለውን፡ንብ፡በፉጨት፡ይጠራል።
19፤ይመጡማል፥እነርሱም፡ዅሉ፡በበረሓ፡ሸለቆ፡በድንጋይም፡ዋሻ፡ውስጥ፡በሾኽ፡ቍጥቋጦ፡ዅሉ፡ላይ፡በማሰማሪያ ውም፡ዅሉ፡ላይ፡ይሰፍራሉ።
20፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ከወንዙ፡ማዶ፡በተከራየው፡ምላጭ፡በአሶር፡ንጉሥ፡የራሱንና፡የእግሩን፡ጠጕር ፡ይላጨዋል፤ምላጩም፡ጢሙን፡ደግሞ፡ይበላል።
21፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ሰው፡አንዲት፡ጊደርን፡ኹለት፡በጎችንም፡ያሳድጋል፤
22፤ከሚሰጡት፡ወተት፡ብዛት፡የተነሣ፡ቅቤ፡ይበላል፤በአገሪቱም፡መካከል፡የቀረ፡ዅሉ፡ቅቤና፡ማር፡ይበላል።
23፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ሺሕ፡ብር፡የተገመተ፡ሺሕ፡የወይን፡ግንድ፡በነበረበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ለኵር ንችትና፡ለሾኽ፡ይኾናል።
24፤ኵርንችትና፡ሾኽ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥በፍላጻና፡በቀስት፡ወደዚያ፡ይገባሉ።
25፤በመቈፈሪያም፡ወደተቈፈሩ፡ኰረብታዎች፡ዅሉ፡ከኵርንችትና፡ሾኽ፡ፍርሀት፡የተነሣ፡ወደዚያ፡አትኼድም፤ነገ ር፡ግን፥የበሬ፡ማሰማሪያና፡የበግ፡መራገጫ፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤እግዚአብሔርም፦ታላቅ፡ሰሌዳ፡ወስደኽ፦ምርኮ፡ፈጠነ፥ብዝበዛ፡ቸኰለ፡ብለኽ፡በሰው፡ፊደል፡ጻፍበት።
2፤የታመኑትን፡ሰዎች፡ካህኑን፡ኦርዮንና፡የበራክዩን፡ልጅ፡ዘካርያስን፡ምስክሮች፡አድርግልኝ፡አለኝ።
3፤ወደ፡ነቢዪቱም፡ቀረብኹ፤ርሷም፡ፀነሰች፡ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች።
4፤እግዚአብሔርም፦ሕፃኑ፡አባቱንና፡እናቱን፡መጥራት፡ሳያውቅ፡የደማስቆን፡ሀብትና፡የሰማርያን፡ምርኮ፡በአሶ ር፡ንጉሥ፡ፊት፡ይወስዳልና፥ስሙን፦ምርኮ፡ፈጠነ፥ብዝበዛ፡ቸኰለ፡ብለኽ፡ጥራው፡አለኝ።
5፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡ተናገረኝ፡እንዲህም፡አለኝ።
6፤ይህ፡ሕዝብ፡በቀስታ፡የሚኼደውን፡የሰሊሖምን፡ውሃ፡ጠልቷልና፥ረአሶንንና፡የሮሜልዩንም፡ልጅ፡ወዷ፟ልና፥ስ ለዚህ፥
7፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡ብርቱና፡ብዙ፡የኾነውን፡የወንዝ፡ውሃ፥የአሶርን፡ንጉሥና፡ክብሩን፡ዅሉ፥ያመጣባቸዋል ፤መስኖውንም፡ዅሉ፡ሞልቶ፡ይወጣል፥በዳሩም፡ዅሉ፡ላይ፡ይፈሳ፟ል፤
8፤እየጐረፈም፡ወደ፡ይሁዳ፡ይገባል፤እያጥለቀለቀም፡ያልፋል፥እስከ፡ዐንገትም፡ይደርሳል፤ዐማኑኤል፡ሆይ፥የክ ንፉ፡መዘርጋት፡የአገርኽን፡ስፋት፡ትሞላለች።
9፤አሕዛብ፡ሆይ፥ዕወቁና፡ደንግጡ፤እናንተም፡ምድራችኹ፡የራቀ፡ዅሉ፥አድምጡ፤ታጠቁም፥ደንግጡ፤ታጠቁ፤ደንግጡ ።
10፤ተመካከሩ፥ምክራችኹም፡ይፈታል፤ቃሉን፡ተናገሩ፥ቃሉም፡አይጸናም፤እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ነውና።
11፤እግዚአብሔርም፡በጽኑ፡እጅ፡እንዲህ፡ተናገረኝ፥በዚህም፡ሕዝብ፡መንገድ፡አንዳልኼድ፡አስጠነቀቀኝ፥እንዲ ህም፡አለኝ።
12፤ይህ፡ሕዝብ፦ዱለት፡ነው፡በሚሉት፡ዅሉ፦ዱለት፡ነው፡አትበሉ፤መፈራታቸውንም፡አትፍሩ፥አትደንግጡ።
13፤ነገር፡ግን፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡ቀድሱት፤የሚያስፈራችኹና፡የሚያስደነግጣችኹም፡ርሱ፡ይኹን።
14፤ርሱም፡ለመቅደስ፡ይኾናል፤ነገር፡ግን፥ለኹለቱ፡ለእስራኤል፡ቤቶች፡ለዕንቅፋት፡ድንጋይና፡ለማሰናከያ፡አ ለት፥በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ለወጥመድና፡ለአሽክላ፡ይኾናል።
15፤ብዙዎችም፡በርሱ፡ይሰናከላሉ፥ይወድቁማል፥ይሰበሩማል፥ይጠመዱማል፥ይያዙማል።
16፤ምስክሩን፡እሰር፤በደቀ፡መዛሙርቴም፡መካከል፡ሕጉን፡ዐትም።
17፤ከያዕቆብም፡ቤት፡ፊቱን፡የመለሰውን፡እግዚአብሔርን፡እጠብቃለኹ፥እተማመንበትማለኹ።
18፤እንሆ፥እኔና፡እግዚአብሔር፡የሰጠኝ፡ልጆች፡ለእስራኤል፡በጽዮን፡ተራራ፡ከሚኖረው፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግ ዚአብሔር፡ዘንድ፡ምልክትና፡ተኣምራት፡ነን።
19፤እነርሱም፦የሚጮኹትንና፡ድምፃቸውን፡ዝቅ፡አድርገው፡የሚናገሩትን፡መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችን፡ጠ ይቁ፡ባሏችኹ፡ጊዜ፥ሕዝቡ፡ከአምላኩ፡መጠየቅ፡አይገ፟ባ፟ውምን፧ወይስ፡ለሕያዋን፡ሲሉ፡ሙታንን፡ይጠይቃሉን፧
20፤ወደ፡ሕግና፡ወደ፡ምስክር፡ኺዱ! እንዲህም፡ያለውን፡ቃል፡ባይናገሩ፡ንጋት፡አይበራላቸውም።
21፤እነርሱም፡ተጨንቀውና፡ተርበው፡ያልፋሉ፤በተራቡም፡ጊዜ፡ተቈጥተው፡ንጉሣቸውንና፡አምላካቸውን፡ይረግማሉ ፥ወደ፡ላይም፡ይመለከታሉ፤
22፤ወደ፡ምድርም፡ይመለከታሉ፥እንሆም፥መከራና፡ጨለማ፡የሚያስጨንቅም፡ጭጋግ፡አለ፤ወደ፡ድቅድቅም፡ጨለማ፡ይ ሰደዳሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤ነገር፡ግን፥ተጨንቃ፡ለነበረች፡ጨለማ፡አይኾንም።በመዠመሪያው፡ዘመን፡የዛብሎንንና፡የንፍታሌምን፡ምድር፡ አቃለለ፤በዃለኛው፡ዘመን፡ግን፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በባሕር፡መንገድ፡ያለውን፡የአሕዛብን፡ገሊላ፡ያከብራል።
2፤በጨለማ፡የኼደ፡ሕዝብ፡ብርሃን፡አየ፤በሞት፡ጥላ፡አገርም፡ለኖሩ፡ብርሃን፡ወጣላቸው።
3፤ሕዝብን፡አብዝተኻል፥ደስታንም፡ጨምረኽላቸዋል፤በመከር፡ደስ፡እንደሚላቸው፥ሰዎችም፡ምርኮን፡ሲካፈሉ፡ደስ ፡እንደሚላቸው፡በፊትኽ፡ደስ፡ይላቸዋል።
4፤በምድያም፡ጊዜ፡እንደ፡ኾነ፡የሸክሙን፡ቀንበር፡የጫንቃውንም፡በትር፡የአስጨናቂውንም፡ዘንግ፡ሰብረኻል።
5፤የሚረግጡ፡የሰልፈኛዎች፡ጫማ፡ዅሉ፥በደምም፡የተለወሰ፡ልብስ፡ለቃጠሎ፡ይኾናል፥እንደ፡እሳት፡ማቃጠያም፡ኾ ኖ፡ይቃጠላል።
6፤ሕፃን፡ተወልዶልናልና፥ወንድ፡ልጅም፡ተሰጥቶናልና፤አለቅነትም፡በጫንቃው፡ላይ፡ይኾናል፤ስሙም፡ድንቅ፡መካ ር፥ኀያል፡አምላክ፥የዘለዓለም፡አባት፥የሰላም፡አለቃ፡ተብሎ፡ይጠራል።
7፤ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡በፍርድና፡በጽድቅ፡ያጸናውና፡ይደግፈው፡ዘንድ፡በዳዊት፡ዙፋንና፡በ መንግሥቱ፡ላይ፡አለቅነቱ፡ይበዛል፥ለሰላሙም፡ፍጻሜ፡የለውም።የእግዚአብሔር፡ቅንአት፡ይህን፡ያደርጋል።
8፤ጌታ፡በያዕቆብ፡ላይ፡ቃልን፡ሰደደ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ወደቀ።
9፤10፤በትዕቢትና፡በልብ፡ኵራት፦ጡቡ፡ወድቋል፥ነገር፡ግን፥በተወቀረ፡ድንጋይ፡እንሠራለን፤የሾላ፡ዛፎች፡ተ ቈርጠዋል፥ነገር፡ግን፥ዝግባን፡እንተካባቸዋለን፡የሚሉ፡በኤፍሬምና፡በሰማርያ፡የሚኖሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ያውቃሉ ።
11፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ተራራ፡ላይ፡ተቋቋሚ፡ያስነሣበታል፥
12፤ጠላቶቹን፡ሶርያውያንንም፡ከምሥራቅ፥ፍልስጥኤማውያንንም፡ከምዕራብ፡ያንቀሳቅስበታል፤እስራኤልንም፡በተ ከፈተ፡አፍ፡ይበሉታል።በዚህም፡ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለ ች።
13፤ሕዝቡ፡ግን፡ወደቀሠፋቸው፡አልተመለሱም፥የሰራዊትንም፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡አልፈለጉም።
14፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ራስና፡ዥራትን፥የሰሌኑን፡ቅርንጫፍና፡እንግጫውን፡ባንድ፡ቀን፡ከእስራኤል፡ይቈር ጣል።
15፤ሽማግሌውና፡ከበርቴው፡ርሱ፡ራስ፡ነው፤በሐሰትም፡የሚያስተምር፡ነቢይ፡ርሱ፡ዥራት፡ነው።
16፤ይህን፡ሕዝብ፡የሚመሩ፡ያስቷቸዋል፤ተመሪዎቹም፡ይጠፋሉ።
17፤ሰው፡ዅሉ፡ዝንጉና፡ክፉ፡ሠሪ፡ነውና፥አፍም፡ዅሉ፡ስንፍናን፡ይናገራልና፥ስለዚህ፡ጌታ፡በጕልማሳዎቻቸው፡ ደስ፡አይለውም፥ለድኻ፡አደጎቻቸውና፡ለመበለቶቻቸውም፡አይራራም።በዚህም፡ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም ፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።
18፤ክፋት፡እንደ፡እሳት፡ይቃጠላል፤ኵርንችቱንና፡ሾኹን፡ይበላል፤ጭፍቅ፡የኾነውንም፡ዱር፡ያቃጥላል፥ጢሱም፡ ተትጐልጕሎ፡እንደ፡ዐምድ፡ይወጣል።
19፤በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ምድር፡ተቃጥላለች፤ሕዝቡም፡እሳት፡እንደሚበላው፡ዕንጨት፡ኾኗል፤ሰ ውም፡ለወንድሙ፡አይራራም።
20፤ሰው፡በቀኙ፡በኩል፡ይነቅላል፡ይራብማል፤በግራም፡በኩል፡ይበላል፡አይጠግብምም፤እያንዳንዱም፡የክንዱን፡ ሥጋ፡ይበላል፤
21፤ምናሴ፡ኤፍሬምን፡ኤፍሬምም፡ምናሴን፡ይበላል፤እነርሱ፡በአንድነት፡የይሁዳ፡ጠላቶች፡ይኾናሉ።በዚህም፡ዅ ሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤2፤መበለቶችም፡ቅሚያቸው፡እንዲኾኑ፥ድኻ፡አደጎችንም፡ብዝበዛቸው፡እንዲያደርጉ፥የድኻውን፡ፍርድ፡ያጣምሙ ፡ዘንድ፥የችግረኛውንም፡ሕዝቤን፡ፍርድ፡ያጐድሉ፡ዘንድ፡የግፍን፡ትእዛዛት፡ለሚያዙ፟፥ክፉንም፡ጽሕፈት፡ለሚ ጽፉ፡ወዮላቸው!
3፤በተጐበኛችኹበት፡ቀን፥መከራም፡ከሩቅ፡በሚመጣበት፡ዘመን፡ምን፡ታደርጉ፡ይኾን፧ለረድኤትስ፡ወደ፡ማን፡ትሸ ሻላችኹ፧ክብራችኹንስ፡ወዴት፡ትተዉታላችኹ፧
4፤ከእስረኛዎች፡በታች፡ይጐ፟ነበሳሉ፥ከተገደሉትም፡በታች፡ይወድቃሉ።በዚህም፡ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰ ችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።
5፤ለቍጣዬ፡በትር፡ለኾነ፥የመዓቴም፡ጨንገር፡በእጁ፡ላለ፟፡ለአሶር፡ወዮለት!
6፤ርሱንም፡በዝንጉ፡ሕዝብ፡ላይ፡እልካለኹ፥ምርኮውንና፡ብዝበዛውንም፡ይወስድ፡ዘንድ፡እንደ፡አደባባይም፡ጭቃ ፡የተረገጡ፡ያደርጋቸው፡ዘንድ፡በምቈጣቸው፡ሰዎች፡ላይ፡አዘ፟ዋለኹ።
7፤ርሱ፡እንዲሁ፡አያስብም፥በልቡም፡እንዲህ፡አይመስለውም፤ነገር፡ግን፥ማጥፋት፥ጥቂት፡ያይደሉትንም፡አሕዛብ ን፡መቍረጥ፡በልቡ፡አለ።
8፤እንዲህ፡ይላል፦መሳፍንቴ፡ዅሉ፡ነገሥታት፡አይደሉምን፧
9፤ካልኖ፡እንደ፡ከርከሚሽ፡አይደለችምን፧ሐማትስ፡እንደ፡አርፋድ፡አይደለችምን፧ሰማርያስ፡እንደ፡ደማስቆ፡አ ይደለችምን፧
10፤የተቀረጹ፡ምስሎቻቸው፡ከኢየሩሳሌምና፡ከሰማርያ፡ምስሎች፡የበለጡትን፡የጣዖቶችን፡መንግሥታት፡እጄ፡እን ዳገኘች፥
11፤በሰማርያና፡በጣዖቶቿም፡እንዳደረግኹ፥እንዲሁስ፡በኢየሩሳሌምና፡በጣዖቶቿ፡አላደርግምን፧
12፤ስለዚህ፥እንዲህ፡ይኾናል፤ጌታ፡ሥራውን፡ዅሉ፡በጽዮን፡ተራራና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡የአሶር ን፡ንጉሥ፡የኵሩ፡ልብ፡ፍሬን፡የዐይኑንም፡ከፍታ፡ትምክሕት፡ይጐበኛል።
13፤ርሱ፡እንዲህ፡ብሏልና፦አስተዋይ፡ነኝና፡በእጄ፡ኀይልና፡በጥበቤ፡አደረግኹት፤የአሕዛብን፡ድንበሮች፡አራ ቅኹ፥ሀብታቸውንም፡ዘረፍኹ፥እንደ፡ዠግናም፡ኾኜ፡በምድር፡የተቀመጡትን፡አዋረድኹ፤
14፤እጄም፡የአሕዛብን፡ኀይል፡እንደ፡ወፍ፡ቤት፡አገኘች፤የተተወም፡ዕንቍላል፡እንደሚሰበሰብ፡እንዲሁ፡እኔ፡ ምድርን፡ዅሉ፡ሰበሰብኹ፤ክንፉን፡የሚያራግብ፡አፉንም፡የሚከፍት፡የሚጮኽም፡የለም።
15፤በእውኑ፡መጥረቢያ፡በሚቈርጥበት፡ሰው፡ላይ፡ይመካልን፧ወይስ፡መጋዝ፡በሚስበው፡ላይ፡ይጓደዳልን፧ይህስ፥ በትር፡የሚያነሣውን፡እንደ፡መነቅነቅ፡ዘንግም፡ዕንጨት፡ያይደለውን፡እንደ፡ማንሣት፡ያኽል፡ነው።
16፤ስለዚህም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በወፍራሞች፡ላይ፡ክሳትን፡ይልካል፤ከክብሩም፡በታች፡ቃጠሎው፡እ ንደ፡እሳት፡መቃጠል፡ይነዳ፟ል።
17፤የእስራኤልም፡ብርሃን፡እንደ፡እሳት፡ቅዱስም፡እንደ፡ነበልባል፡ይኾናል፤ሾኹንና፡ኵርንችቱን፡ባንድ፡ቀን ፡ያቃጥላል፡ይበላውማል።
18፤ከነፍስም፡እስከ፡ሥጋ፡ድረስ፡የዱሩንና፡የሚያፈራውን፡ዕርሻ፡ክብር፡ይበላል፤ይህም፡የታመመ፡ሰው፡እንደ ሚሰለስል፡ይኾናል።
19፤የቀሩትም፡የዱር፡ዛፎች፡በቍጥር፡ጥቂት፡ይኾናሉ፥ታናሽ፡ብላቴናም፡ይጽፋቸው፡ዘንድ፡ይችላል።
20፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤የእስራኤል፡ቅሬታ፡ከያዕቆብም፡ቤት፡የዳኑት፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በመቷቸ ው፡ላይ፡አይደገፉም፤ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ቅዱስ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡በእውነት፡ይደገፋሉ።
21፤የያዕቆብም፡ቅሬታ፡ወደ፡ኀያል፡አምላክ፡ይምለሳሉ።
22፤እስራኤል፡ሆይ፥የሕዝብኽ፡ቍጥር፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡ቢኾን፡ቅሬታው፡ይመለሳል።ጽድቅ፡የተትረፈረፈበት ም፡ጥፋት፡ተወስኗል።
23፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ያለቀ፡የተቈረጠ፡ነገርን፡በምድር፡ዅሉ፡መካከል፡ይፈጽማል።
24፤ስለዚህ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በጽዮን፡የምትኖር፡ሕዝቤ፡ሆይ፥አሶር፡በበትር፡ቢ መታኽ፥ግብጽም፡እንዳደረገ፡ዘንጉን፡ቢያነሣብኽ፥አትፍራው።
25፤ቍጣዬ፡እስኪፈጸም፡መዓቴም፡እስኪያጠፋቸው፡ድረስ፡ጥቂት፡ጊዜ፡ቀርቷልና።
26፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ምድያምን፡በሔሬብ፡አለት፡በኩል፡እንደ፡መታው፡ጅራፍ፡ያነሣበታል፤በትሩ ም፡በባሕር፡ላይ፡ይኾናል፥በግብጽም፡እንዳደረገ፡ያነሣዋል።
27፤በዚያም፡ቀን፡ሸክሙ፡ከጫንቃኽ፡ቀንበሩም፡ከዐንገትኽ፡ላይ፡ይወርዳል፤ቀንበሩም፡ከውፍረት፡የተነሣ፡ይሰ በራል።
28፤ወደ፡አንጋይ፡መጥቷል፤በመጌዶን፡በኩል፡ዐልፏል፤በማክማስ፡ውስጥ፡ዕቃውን፡አኑሯል፤
29፤በመተላለፊያ፡ዐልፏል፤በጌባ፡ማደሪያው፡ነው፤ራማ፡ደንግጣለች፤የሳኦል፡ጊብዓ፡ኰብላ፟ለች።
30፤አንቺ፡የጋሊም፡ልጅ፡ሆይ፥በታላቅ፡ድምፅሽ፡ጩኺ፤ላይሳ፡ሆይ፥አድምጪ፤ዐናቶት፡ሆይ፥መልሽላት።
31፤መደቤና፡ሸሽታለች፤በግቤርም፡የሚኖሩ፡ቤተ፡ሰቦቻቸውን፡አሽሽተዋል።
32፤ዛሬ፡በኖብ፡ይቆማል፤በጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ተራራ፡በኢየሩሳሌም፡ኰረብታ፡ላይ፡እጁን፡ያንቀሳቅሳል።
33፤እንሆ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ቅርንጫፎቹን፡በሚያስፈራ፡ኀይል፡ይቈርጣል፤በቁመት፡የረዘሙትም፡ይ ቈረጣሉ፥ከፍ፡ያሉትም፡ይዋረዳሉ።
34፤ጭፍቅ፡የኾነውንም፡ዱር፡በብረት፡ይቈርጣል፥ሊባኖስም፡በኀያሉ፡እጅ፡ይወድቃል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤ከእሴይ፡ግንድ፡በትር፡ይወጣል፥ከሥሩም፡ቍጥቋጥ፡ያፈራል።
2፤የእግዚአብሔር፡መንፈስ፥የጥበብና፡የማስተዋል፡መንፈስ፥የምክርና፡የኀይል፡መንፈስ፥የዕውቀትና፡እግዚአብ ሔርን፡የመፍራት፡መንፈስ፡ያርፍበታል።
3፤እግዚአብሔርን፡በመፍራት፡ደስታውን፡ያያል።ዐይኑም፡እንደምታይ፡አይፈርድም፥ዦሮውም፡እንደምትሰማ፡አይበ ይንም፤
4፤ነገር፡ግን፥ለድኻዎች፡በጽድቅ፡ይፈርዳል፥ለምድርም፡የዋሆች፡በቅንነት፡ይበይናል፤በአፉም፡በትር፡ምድርን ፡ይመታል፥በከንፈሩም፡እስትንፋስ፡ክፉዎችን፡ይገድላል።
5፤የወገቡ፡መታጠቂያ፡ጽድቅ፥የጐኑም፡መቀነት፡ታማኝነት፡ይኾናል።
6፤ተኵላ፡ከበግ፡ጠቦት፡ጋራ፡ይቀመጣል፥ነብርም፡ከፍየል፡ጠቦት፡ጋራ፡ይተኛል፤ጥጃና፡የአንበሳ፡ደቦል፡ፍሪዳ ም፡በአንድነት፡ያርፋሉ፤ታናሽም፡ልጅ፡ይመራቸዋል።
7፤ላምና፡ድብ፡ዐብረው፡ይሰማራሉ፥ግልገሎቻቸውም፡በአንድነት፡ያርፋሉ፤አንበሳም፡እንደ፡በሬ፡ገለባ፡ይበላል ።
8፤የሚጠባውም፡ሕፃን፡በእባብ፡ጕድጓድ፡ላይ፡ይጫወታል፥ጡት፡የጣለውም፡ሕፃን፡በእፍኝት፡ቤት፡ላይ፡እጁን፡ይ ጭናል።
9፤በተቀደሰው፡ተራራዬ፡ዅሉ፡ላይ፡አይጐዱም፡አያጠፉምም፤ውሃ፡ባሕርን፡እንደሚከድን፡ምድር፡እግዚአብሔርን፡ በማወቅ፡ትሞላለችና።
10፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ለአሕዛብ፡ምልክት፡ሊኾን፡የቆመውን፡የእሴይን፡ሥር፡አሕዛብ፡ይፈልጉታል ፤ማረፊያውም፡የተከበረ፡ይኾናል።
11፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤የቀረውን፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ከአሶርና፡ከግብጽ፥ከጳትሮስና፡ከኢትዮጵያ፥ ከዔላምና፡ከሰናዖር፡ከሐማትም፥ከባሕርም፡ደሴቶች፡ይመልስ፡ዘንድ፡ጌታ፡እንደ፡ገና፡እጁን፡ይገልጣል።
12፤ለአሕዛብም፡ምልክትን፡ያቆማል፥ከእስራኤልም፡የተጣሉትን፡ይሰበስባል፥ከይሁዳም፡የተበተኑትን፡ከአራቱ፡ የምድር፡ማእዘኖች፡ያከማቻል።
13፤የኤፍሬምም፡ምቀኝነት፡ይርቃል፥ይሁዳንም፡የሚያስጨንቁ፡ይጠፋሉ፤ኤፍሬምም፡በይሁዳ፡አይቀናም፥ይሁዳም፡ ኤፍሬምን፡አያስጨንቅም።
14፤በምዕራብም፡በኩል፡በፍልስጥኤማውያን፡ጫንቃ፡ላይ፡እየበረሩ፡ይወርዳሉ፥የምሥራቅንም፡ልጆች፡በአንድነት ፡ይበዘብዛሉ፤በኤዶምያስና፡በሞዐብም፡ላይ፡እጃቸውን፡ይዘረጋሉ፥የዐሞንም፡ልጆች፡ለእነርሱ፡ይታዘዛሉ።
15፤እግዚአብሔርም፡የግብጽን፡ባሕር፡ያጠፋል፤በትኵሱም፡ነፋስ፡እጁን፡በወንዙ፡ላይ፡ያነሣል፥ሰባት፡ፈሳሾች ንም፡አድርጎ፡ይመታዋል፥ሰዎችም፡በጫማቸው፡እንዲሻገሩ፡ያደርጋቸዋል።
16፤ከግብጽም፡በወጣ፡ጊዜ፡ለእስራኤል፡እንደ፡ነበረ፥ለቀረው፡ለሕዝቡ፡ቅሬታ፡ከአሶር፡ጐዳና፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤በዚያም፡ቀን፦አቤቱ፥ተቈጥተኸኛልና፥ቍጣኽንም፡ከእኔ፡መልሰኻልና፥አጽናንተኸኛልምና፡አመሰግንኻለኹ።
2፤እንሆ፥አምላክ፡መድኀኒቴ፡ነው፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ኀይሌና፡ዝማሬዬ፡ነውና፥መድኀኒቴም፡ኾኗልና፥በርሱ፡ታ ምኜ፡አልፈራም፡ትላለኽ።
3፤ውሃውንም፡ከመድኀኒት፡ምንጮች፡በደስታ፡ትቀዳላችኹ።
4፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ትላላችኹ።እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥ስሙንም፡ጥሩ፤በአሕዛብ፡መካከል፡ሥራውን፡አስ ታውቁ፤ስሙ፡ከፍ፡ያለ፡እንደ፡ኾነ፡ተናገሩ።
5፤ታላቅ፡ሥራ፡ሠርቷልና፥ለእግዚአብሔር፡ተቀኙ፤ይህንም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡አስታውቁ።
6፤አንቺ፡በጽዮን፡የምትኖሪ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ቅዱስ፡በመካከልሽ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ደስ፡ይበልሽ፡እልልም፡ በዪ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ያየው፡ስለ፡ባቢሎን፡የተነገረ፡ሸክም።
2፤ምድረ፡በዳ፡በኾነ፡ተራራ፡ላይ፡ምልክትን፡አቁሙ፥ድምፅንም፡ከፍ፡አድርጉባቸው፤በአለቃዎችም፡ደጆች፡እንዲ ገቡ፡በእጅ፡ጥቀሱ።
3፤ቍጣዬን፡ይፈጽሙ፡ዘንድ፡ቅዱሳኔን፡አዝዣለኹ፥እኔ፡ኀያላኔንና፡በታላቅነቴ፡ደስ፡የሚላቸውን፡ጠርቻለኹ።
4፤በተራራዎች፡ላይ፡እንደ፡ታላቅ፡ሕዝብ፡ድምፅ፡የኾነ፡የብዙ፡ሰው፡ድምፅ፡አለ።የከተማቹት፡የአሕዛብ፡መንግ ሥታት፡የውካታ፡ጫጫታ፡አለ።የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሰራዊትን፡ለሰልፍ፡አሰልፏል።
5፤እግዚአብሔርና፡የቍጣው፡የጦር፡ዕቃ፡ምድርን፡ዅሉ፡ያጠፏት፡ዘንድ፡ከሩቅ፡አገር፡ከሰማይ፡ዳርቻ፡ይመጣሉ።
6፤የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቀርቧልና፥አልቅሱ፤ዅሉን፡ከሚችል፡አምላክ፡ዘንድ፡እንደሚመጣ፡ጥፋት፡ይመጣል።
7፤ስለዚህ፥እጅ፡ዅሉ፡ትዝላለች፥የሰውም፡ዅሉ፡ልብ፡ይቀልጣል።
8፤ይደነግጣሉ፤ምጥና፡ሕማም፡ይይዛቸዋል፥እንደምትወልድ፡ሴትም፡ያምጣሉ፤አንዱም፡በሌላው፡ይደነቃል፥ፊታቸው ም፡የነበልባል፡ፊት፡ነው።
9፤እንሆ፥ምድሪቱን፡ባድማ፡ሊያደርግ፥ኀጢአተኛዎቿንም፡ከርሷ፡ዘንድ፡ሊያጠፋ፡ጨካኝ፡ኾኖ፡በመዓትና፡በጽኑ፡ ቍጣ፡ተሞልቶ፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡ይመጣል።
10፤የሰማይም፡ከዋክብትና፡ሰራዊቱ፡ብርሃናቸውን፡አይሰጡም፥ፀሓይም፡በወጣች፡ጊዜ፡ትጨልማለች፥ጨረቃም፡በብ ርሃኑ፡አያበራም።
11፤ዓለሙን፡ስለ፡ክፋታቸው፡ክፉዎቹንም፡ስለ፡በደላቸው፡እቀጣለኹ፤የትዕቢተኛዎችንም፡ኵራት፡አዋርዳለኹ።
12፤የቀሩትም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ይልቅ፡የከበሩ፡ይኾናሉ፥ሰውም፡ከኦፊር፡ወርቅ፡ይልቅ፡የከበረ፡ይኾናል።
13፤ስለዚህ፥በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡መዓት፡በጽኑ፡ቍጣ፡ቀንም፡ሰማያትን፡አነቃንቃለኹ፥ምድርም፡ከስ ፍራዋ፡ትናወጣለች።
14፤እንደ፡ተባረረም፡ሚዳቋ፥ማንም፡እንደማይሰበስበው፡እንደ፡በግ፡መንጋ፥ሰው፡ዅሉ፡ወደ፡ወገኑ፡ይመለሳል፥ ዅሉም፡ወደ፡አገሩ፡ይሸሻል።
15፤የተገኘ፡ዅሉ፡የተወጋ፡ይኾናል፥የተያዘም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ይወድቃል።
16፤ሕፃናታቸውም፡በፊታቸው፡ይጨፈጨፋሉ፥ቤቶቻቸውም፡ይበዘበዛሉ፥ሚስቶቻቸውም፡ይነወራሉ።
17፤እንሆ፥ብር፡የማይሹትን፥ወርቅም፡የማያምራቸውን፡ሜዶናውያንን፡በላያቸው፡አስነሣለኹ።
18፤ፍላጻዎቻቸውም፡ጐበዞችን፡ይጨፈጭፋሉ፥የማሕፀንንም፡ፍሬ፡አይምሩም፥ዐይኖቻቸውም፡ለሕፃናት፡አይራሩም።
19፤እግዚአብሔርም፡ሰዶምንና፡ገሞራን፡ባፈረሰ፡ጊዜ፡እንደ፡ነበረው፥የመንግሥታት፡ክብር፡የከለዳውያንም፡ት ዕቢት፡ጌጥ፡ባቢሎን፡እንዲሁ፡ትኾናለች።
20፤ለዘለዓለም፡የሚቀመጥባት፡አይገኝም፥ከትውልድ፡እስከ፡ትውልድ፡ድረስ፡ሰው፡አይኖርባትም፤ዐረባውያንም፡ ድንኳንን፡በዚያ፡አይተክሉም፥እረኛዎችም፡መንጋዎቻቸውን፡በዚያ፡አያሳርፉም።
21፤በዚያም፡የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ያርፋሉ፥ጕጕቶችም፡በቤቶቻቸው፡ይሞላሉ፤ሰጐኖችም፡በዚያ፡ይኖራሉ፥በዚያ ም፡አጋንንት፡ይዘፍናሉ።
22፤ተኵላዎችም፡በግንቦቻቸው፥ቀበሮዎችም፡በሚያማምሩ፡አዳራሾቻቸው፡ይጮኻሉ፤ጊዜዋም፡ለመምጣት፡ቀርቧል፥ቀ ኗም፡አይዘገይም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤እግዚአብሔርም፡ያዕቆብን፡ይምረዋል፥እስራኤልንም፡ደግሞ፡ይመርጠዋል፥በአገራቸውም፡ያኖራቸዋል፤መጻተኛም ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይተባበራል፥ከያዕቆብም፡ቤት፡ጋራ፡ይጣበቃል።
2፤አሕዛብም፡ይዘው፡ወደ፡ስፍራቸው፡ያመጧቸዋል፥የእስራኤልም፡ቤት፡በእግዚአብሔር፡ምድር፡እንደ፡ሎሌዎችና፡ እንደ፡ገረዶች፡አድርገው፡ይገዟቸዋል፤የማረኳቸውን፡ይማርካሉ፥አስጨናቂዎችንም፡ይገዛሉ።
3፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡ከሐዘንኽና፡ከመከራኽ፡ከተገዛኽለትም፡ከጽኑ፡ባርነት፡ያሳር ፍኻል።
4፤ይህንም፡ምሳሌ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ላይ፡ታነሣለኽ፡እንዲህም፡ትላለኽ፦አስጨናቂ፡እንዴት፡ዐረፈ! አስገባሪም፡እንዴት፡ጸጥ፡አለ!
5፤6፤አሕዛብንም፡በመዓትና፡በማያቋርጥ፡መምታት፡የመታውን፥አሕዛብንም፡ባልተከለከለ፡መከራ፡በቍጣው፡የገዛ ውን፡የኃጥኣንን፡በትር፡የአለቃዎችንም፡ዘንግ፡እግዚአብሔር፡ሰብሯል።
7፤ምድርም፡ዅሉ፡ዐርፋ፡በጸጥታ፡ተቀምጣለች፡እልልም፡ብላለች።
8፤ጥድና፡የሊባኖስ፡ዝግባ፦አንተ፡ከተዋረድኽ፡ዠምሮ፡ማንም፡ይቈርጠን፡ዘንድ፡አልወጣብንም፡ብለው፡ባንተ፡ደ ስ፡አላቸው።
9፤ሲኦል፡በመምጣትኽ፡ልትገናኝኽ፡በታች፡ታወከች፤የሞቱትንም፥የምድርን፡ታላላቆች፡ዅሉ፥ለአንተ፡አንቀሳቀሰ ች፥የአሕዛብንም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡ከዙፋኖቻቸው፡አስነሣች።
10፤እነዚህ፡ዅሉ፦አንተ፡ደግሞ፡እንደ፡እኛ፡ደክመኻልን፧እኛንስ፡መስለኻልን፧ጌጥኽና፡የበገናኽ፡ድምፅ፡ወደ ፡ሲኦል፡ወረደ፤
11፤በበታችኽም፡ብል፡ተነጥፏል፥ትልም፡መደረቢያኽ፡ኾኗል፡ብለው፡ይመልሱልኻል።
12፤አንተ፡የንጋት፡ልጅ፡አጥቢያ፡ኮከብ፡ሆይ፥እንዴት፡ከሰማይ፡ወደቅኽ! አሕዛብንም፡ያዋረድኽ፡አንተ፡ሆይ፥እንዴት፡እስከ፡ምድር፡ድረስ፡ተቈረጥኽ!
13፤አንተን፡በልብኽ፦ወደ፡ሰማይ፡ዐርጋለኹ፥ዙፋኔንም፡ከእግዚአብሔር፡ከዋክብት፡በላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አደርጋለ ኹ፥በሰሜንም፡ዳርቻ፡በመሰብሰቢያ፡ተራራ፡ላይ፡እቀመጣለኹ፤
14፤ከዳመናዎች፡ከፍታ፡በላይ፡ዐርጋለኹ፥በልዑልም፡እመሰላለኹ፡አልኽ።
15፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ሲኦል፡ወደጕድጓዱም፡ጥልቅ፡ትወርዳለኽ።
16፤የሚያዩኽ፡ይመለከቱኻልና፦በእውኑ፡ምድርን፡ያንቀጠቀጠ፥መንግሥታትንም፡ያናወጠ፥
17፤ዓለሙን፡ዅሉ፡ባድማ፡ያደረገ፥ከተማዎችንም፡ያፈረሰ፥ምርኮኛዎቹንም፡ወደ፡ቤታቸው፡ያልሰደደ፡ሰው፡ይህ፡ ነውን፧ብለው፡ያስተውሉኻል።
18፤የአሕዛብ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በየቤታቸው፡በክብር፡አንቀላፍተዋል።
19፤አንተ፡ግን፡እንደ፡ተጠላ፡ቅርንጫፍ፡ከመቃብርኽ፡ተጥለኻል፤በሰይፍም፡የተወጉት፥ተገድለውም፡ወደጕድጓዱ ፡ድንጋዮች፡የወረዱት፡ከድነውኻል፤እንደ፡ተረገጠም፡ሬሳ፡ኾነኻል።
20፤ምድርኽን፡አጥፍተኻልና፥ሕዝብኽንም፡ገድለኻልና፥ከነርሱ፡ጋራ፡በመቃብር፡በአንድነት፡አትኾንም፤የክፉዎ ች፡ዘር፡ለዘለዓለም፡የተጠራ፡አይኾንም።
21፤እንዳይነሡም፥ምድርንም፡እንዳይወርሱ፥የዓለሙንም፡ፊት፡በከተማዎች፡እንዳይሞሉ፡ስላባቶቻቸው፡በደል፡ለ ልጆቹ፡ሞትን፡አዘጋጁላቸው።
22፤በእነርሱ፡ላይ፡እነሣለኹ፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ከባቢሎን፡ስምንና፡ቅሬታን፥ዘርንና፡ትው ልድንም፡እቈርጣለኹ፡ይላል፡እግዚአብሔር።
23፤የዣርት፡መኖሪያ፡የውሃም፡መቋሚያ፡አደርጋታለኹ፤በጥፋትም፡መጥረጊያ፡እጠርጋታለኹ፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር።
24፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ምሏል።እንደ፡ተናገርኹ፡በርግጥ፡ይኾናል፥እንደ፡ዐሰብኹም፡ እንዲሁ፡ይቆማል።
25፤አሶርን፡በምድሬ፡ላይ፡እሰብረዋለኹ፥በተራራዬም፡ላይ፡እረግጠዋለኹ፤ቀንበሩም፡ከነርሱ፡ላይ፡ይነሣል፥ሸ ክሙም፡ከጫንቃቸው፡ላይ፡ይወገዳል።
26፤በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡እግዚአብሔር፡ያሰበው፡ዐሳብ፡ይህ፡ነው፥በአሕዛብም፡ዅሉ፡ላይ፡የተዘረጋች፡እጅ፡ይህ ች፡ናት።
27፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ዐስቧል፤የሚያስጥለውስ፡ማን፡ነው፧እጁም፡ተዘርግታለች፤የሚመልሳት ስ፡ማን፡ነው፧
28፤ንጉሡ፡አካዝ፡በሞተበት፡ዓመት፡ይህ፡ሸክም፡ኾነ።
29፤ፍልስጥኤም፡ሆይ፥ከእባቡ፡ሥር፡እፍኝት፡ይወጣልና፥ፍሬውም፡የሚበር፟ና፡እሳት፡የሚመስል፡እባብ፡ይኾናል ና፥የመታሽ፡በትር፡ስለ፡ተሰበረ፡ዅላችኹም፡ደስ፡አይበላችኹ።
30፤የድኻዎችም፡የበኵር፡ልጆች፡ይሰማራሉ፥ችግረኛዎችም፡ተዘልለው፡ይተኛሉ፤ሥርኽንም፡በራብ፡እገድላለኹ፥ቅ ሬታኽም፡ይገደላል።
31፤አንተ፡በር፡ሆይ፥ወዮ፡በል፡አንቺም፡ከተማ፡ሆይ፥ጩኺ፤ፍልስጥኤም፡ሆይ፥ዅላችኹም፡ቀልጣችዃል፤ጢስ፡ከሰ ሜን፡ይመጣል፡ከጭፍራውም፡ተለይቶ፡የሚቀር፡የለም።
32፤ለሕዝቡም፡መልእክተኛዎች፡ምን፡ብሎ፡መመለስ፡ይገ፟ባ፟ል፧እግዚአብሔር፡ጽዮንን፡እንደ፡መሠረተ፥የሕዝቡ ም፡ችግረኛዎች፡በርሷ፡ውስጥ፡እንደሚጠጉ፡ነው።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤ስለ፡ሞዐብ፡የተነገረ፡ሸክም።የሞዐብ፡ዔር፡በሌሊት፡ፈርሶ፡ጠፋ፤ቂር፡የሚባልም፡የሞዐብ፡ምሽግ፡በሌሊት፡ ፈርሶ፡ጠፋ።
2፤ወደ፡ባይት፡ወደ፡ዲቦንም፡ወደኰረብታ፡መስገጃዎችም፡ለልቅሶ፡ወጥተዋል፤ሞዐብ፡በናባው፡በሜድባ፡ላይ፡ታለ ቅሳለች፤ራሳቸው፡ዅሉ፡ተነጭቷል፥ጢማቸውም፡ዅሉ፡ተላጭቷል።
3፤በየመንገዳቸውም፡በማቅ፡ታጥቀዋል፤በየሰገነቶቻቸውና፡በያደባባዮቻቸው፡እንባ፡እጅግ፡እያፈሰሱ፡ዅሉም፡አ ልቅሰዋል።
4፤ሐሴቦንና፡ኤልያሊ፡ጮኹ፤ድምፃቸው፡እስከ፡ያሀጽ፡ድረስ፡ይሰማል፤ስለዚህ፥የሞዐብ፡ሰልፈኛዎች፡ጮኹ፤ነፍሷ ፡በውስጧ፡ተንቀጠቀጠች።
5፤ልቤ፡ስለ፡ሞዐብ፡ጮኸ፤ከርሷም፡የሚሸሹ፡ወደ፡ዞዓር፡ወደ፡ዔግላት፡ሺሊሺያ፡ኰበለሉ፤በሉሒት፡ዐቀበት፡ላይ ፡እያለቀሱ፡ይወጣሉ፥በሖሮናይምም፡መንገድ፡የዋይታ፡ጩኸት፡ያነሣሉ።
6፤የኔምሬም፡ውሃዎች፡ይደርቃሉ፤ሣሩም፡ደርቋል፥ለጋውም፡ጠውልጓል፥ልምላሜውም፡ዅሉ፡የለም።
7፤ስለዚህ፥የሰበሰቡትን፡ሀብትና፡መዝገባቸውን፡ወደአሓያ፡ዛፍ፡ወንዝ፡ማዶ፡ይወስዱታል።
8፤ጩኸት፡የሞዐብን፡ዳርቻ፡ዅሉ፡ዞረ፤ልቅሶዋም፡ወደ፡ኤግላይምና፡ወደ፡ብኤርኢሊም፡ደረሰ።
9፤የዲሞንም፡ውሃ፡ደም፡ተሞልታለች፤በዲሞንም፡ላይ፡ሥቃይን፡እጨምራለኹ፥ከሞዐባውያንም፡በሚያመልጡ፥ከምድር ም፡በሚቀሩ፡ላይ፡አንበሳን፡አመጣለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤በምድርም፡ላይ፡ለሠለጠነው፡አለቃ፡የበግ፡ጠቦቶችን፡በምድረ፡በዳ፡ካለችው፡ከሴላ፡ወደጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ተ ራራ፡ስደዱ።
2፤እንደሚበር፟፡ወፍ፡እንደ፡ተበተኑም፡ጫጩቶች፡እንዲሁ፡የሞዐብ፡ሴቶች፡ልጆች፡በአርኖን፡መሻገሪያዎች፡ይኾ ናሉ።
3፤ምክርን፡ምከሪ፥ፍርድን፡አድርጊ፥በቀትር፡ጊዜ፡ጥላሽን፡እንደ፡ሌሊት፡አድርጊ፤የተሰደዱትን፡ሸሽጊ፥የሸሹ ትን፡አትግለጪ።
4፤ከሞዐብ፡የተሰደዱት፡ከአንቺ፡ጋራ፡ይቀመጡ፤ከሚያጠፋቸው፡ፊት፡መጋረጃ፡ኹኛቸው።የሚያስጨንቁ፡አልቀዋል፥ ጥፋትም፡ቀርቷል፤ይጨቍኑ፡የነበሩ፡ከምድር፡ጠፍተዋል።
5፤ዙፋንም፡በምሕረት፡ይቀናል፥በዚያም፡ላይ፡በዳዊት፡ድንኳን፡ፍርድን፡የሚሻ፡ጽድቅንም፡የሚያፈጥን፡ፈራጅ፡ በእውነት፡ይቀመጣል፡
6፤ስለሞዐብ፡ትዕቢት፡እጅግ፡ስለ፡መታበዩ፥ስለ፡ኵራቱና፡ስለ፡ትዕቢቱ፡ስለ፡ቍጣውም፡ሰምተናል፤ትምክሕቱ፡ከ ንቱ፡ነው።
7፤ስለዚህ፥ሞዐብ፡ስለ፡ሞዐብ፡ዋይ፡ይላል፤ዅሉም፡ዋይ፡ይላል፤ስለቂርሐራሴት፡መሠራት፡በጥልቅ፡ሐዘን፡ታለቅ ሳላችኹ።
8፤የሐሴቦን፡ዕርሻዎችና፡የሴባማ፡ወይን፡ግንዶች፡አዝነዋል።የአሕዛብ፡አለቃዎች፡የሰባበሯቸው፡ቅርንጫፎች፡ እስከ፡ኢያዜር፡ደርሰው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወጥተው፡ነበር፤ቍጥቋጦቹም፡ተዘርግተው፡ባሕርን፡ተሻግረው፡ነበር ።
9፤ስለዚህ፥በኢያዜር፡ልቅሶ፡ስለሴባማ፡ወይን፡ግንድ፡አለቅሳለኹ፤ሐሴቦንና፡ኤልያሊ፡ሆይ፥በዛፍሽ፡ፍሬና፡በ ወይንሽ፡መከር፡የጦር፡ጩኸት፡ወድቋልና፥በእንባዬ፡አረካሻለኹ።
10፤ደስታና፡ሐሤትም፡ከፍሬያማው፡ዕርሻ፡ተወስዷል፥በወይኑም፡ቦታዎች፡ዝማሬና፡እልልታ፡የለም፤በመጥመቂያም ፡ወይን፡የሚረግጥ፡የለም፤የረጋጮቹን፡እልልታ፡አጥፍቻለኹ።
11፤ስለዚህ፥ልቤ፡ስለ፡ሞዐብ፥አንዠቴም፡ስለ፡ቂርሔሬስ፡እንደ፡መሰንቆ፡ትጮኻለች።
12፤ሞዐብም፡መጥቶ፡በኰረብታ፡መስገጃ፡ላይ፡በደከመና፡ለጸሎት፡ወደ፡መቅደሱ፡በገባ፡ጊዜ፡አያሸንፍም፡
13፤እግዚአብሔር፡በሞዐብ፡ላይ፡በድሮ፡ዘመን፡የተናገረው፡ነገር፡ይህ፡ነው።
14፤አኹን፡ግን፡እግዚአብሔር፦በሦስት፡ዓመት፡ውስጥ፡እንደ፡ምንደኛ፡ዓመት፡የሞዐብ፡ክብርና፡የሕዝቡ፡ዅሉ፡ ብዛት፡ይዋረዳል፥ቅሬታውም፡እጅግ፡ያነሰና፡የተጠቃ፡ይኾናል፡ይላል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤ስለ፡ደማስቆ፡የተነገረ፡ሸክም፦እንሆ፥ደማስቆ፡ከተማ፡ከመኾን፡ተቋርጣለች፤ባድማና፡የፍርስራሽ፡ክምር፡ት ኾናለች።
2፤ከተማዎቿ፡ለዘለዓለም፡የተፈቱ፡ይኾናሉ፤ለመንጋ፡ማሰማሪያ፡ይኾናሉ፤መንጋዎች፡በዚያ፡ያርፋሉ፡የሚያስፈራ ቸውም፡የለም።
3፤ምሽግም፡ከኤፍሬም፥መንግሥትም፡ከደማስቆ፡ተወገደች፤የሶርያም፡ቅሬታ፡እንደ፡እስራኤል፡ልጆች፡ክብር፡ይኾ ናል፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
4፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤የያዕቆብ፡ክብር፡ይደክማል፡የሥጋውም፡ውፍረት፡ይከሳል።
5፤ዐጫጅ፡የቆመውን፡እኽል፡በእጁ፡ሰብስቦ፡ዛላውን፡እንደሚያጭድ፡ይኾናል፤በራፋይም፡ሸለቆ፡ቃርሚያ፡እንደሚ ለቅም፡እንዲሁ፡ይኾናል።
6፤ወይራ፡በተመታ፡ጊዜ፡ኹለት፡ወይም፡ሦስት፡ፍሬ፡በራሱ፡ላይ፡እንደሚቀር፥አራት፡ወይም፡ዐምስት፡በዛፊቱ፡ጫ ፍ፡እንደሚገኝ፥በርሱ፡ዘንድ፡ቃርሚያ፡ይቀራል፡ይላል፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር።
7፤በዚያ፡ቀን፡ሰው፡ወደ፡ፈጣሪው፡ይመለከታል፥ዐይኖቹም፡ወደእስራኤል፡ቅዱስ፡ያያሉ።
8፤እጁም፡የሠራችውን፡መሠዊያ፡አይመለከትም፤ጣቶቹም፡ወዳበጇቸው፥ወደማምለኪያ፡ዐጸዶች፡ወይም፡ወደፀሓይ፡ም ስሎች፥አያይም።
9፤በዚያም፡ቀን፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡የአሞራውያንና፡የኤውያውያን፡ከተማዎች፡እንደ፡ተፈቱ፥እንዲሁ፡ከተ ማዎችኽ፡ይፈታሉ፥ባድማም፡ይኾናሉ።
10፤የደኅንነትኽን፡አምላክ፡ረስተኻል፥የረድኤትኽንም፡ጌታ፡አላሰብኽም፤ስለዚህ፥ያማረውን፡ተክል፡ተክለኻል ፥እንግዳንም፡ዘር፡ዘርተኻል።
11፤በተከልኽበት፡ቀን፡ታበቅለዋለኽ፥በነጋውም፡ዘርኽን፡እንዲያብብ፡ታደርገዋለኽ፤ነገር፡ግን፥በሐዘንና፡በ ትካዜ፡ቀን፡መከሩ፡ይሸሻል።
12፤እንደ፡ባሕር፡ሞገድ፡ድምፅ፡ለሚተምሙ፡ለወገኖች፡ብዛት፥እንደ፡ኀይለኛም፡ውሃ፡ጩኸት፡ለሚጮኹ፡አሕዛብ፡ ወዮላቸው!
13፤አሕዛብ፡እንደ፡ብዙ፡ውሃ፡ጩኸት፡ይጮኻሉ፤ርሱ፡ግን፡ይገሥጻቸዋል፥እነርሱም፡እየሸሹ፡ይርቃሉ፥በተራራም ፡ላይ፡እንዳለ፡እብቅ፡በነፋስ፡ፊት፥ዐውሎ፡ነፋስ፡እንደሚያዞረው፡ትቢያ፡ይበተናሉ።
14፤በመሸ፡ጊዜ፥እንሆ፥ድንጋጤ፡አለ፤ከማለዳም፡በፊት፡አይገኙም።የዘረፉን፡ሰዎች፡ዕድል፡ፈንታ፥የበዘበዙን ፡ዕጣ፡ይህ፡ነው።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤በኢትዮጵያ፡ወንዞች፡ማዶ፡ላለች፥ክንፍ፡ያላቸው፡መርከቦች፡ላሉባት፥
2፤መልእክተኛዎችን፡በባሕር፡ላይ፡የደንገል፡መርከቦችንም፡በውሃ፡ላይ፡ለምትልክ፡ምድር፡ወዮላት! እናንተ፡ፈጣኖች፡መልእክተኛዎች፡ሆይ፥ወደ፡ረዥምና፡ወደ፡ለስላሳ፡ሕዝብ፥ከመዠመሪያው፡አስደንጋጭ፡ወደ፡ኾ ነ፡ወገን፥ወደሚሰፍርና፡ወደሚረግጥ፥ወንዞችም፡ምድራቸውን፡ወደሚከፍሉት፡ሕዝብ፡ኺዱ።
3፤በዓለም፡የምትኖሩ፡ዅሉና፡በምድር፡የምትቀመጡ፡ሆይ፥ምልክት፡በተራራዎች፡ላይ፡በተነሣ፡ጊዜ፡እዩ፤መለከት ም፡በተነፋ፡ጊዜ፡ስሙ።
4፤እግዚአብሔር፦በፀሓይ፡ጮራ፡እንደ፡ደረቅ፡ትኵሳት፥በዐጨዳም፡ወራት፡እንደ፡ጠል፡ደመና፡ኾኜ፡በማደሪያዬ፡ በጸጥታ፡ተቀምጬ፡እመለከታለኹ፡ብሎኛልና።
5፤ርሱ፡ከመከር፡በፊት፡አበባ፡በረገፈ፡ጊዜ፡የወይንም፡ፍሬ፡ጨርቋ፡ሲይዝ፡የወይኑን፡ዘንግ፡በማጭድ፡ይቈርጣ ል፥ጫፎቹንም፡ይመለምላል፣ያስወግድማል።
6፤በተራራ፡ላይ፡ላሉ፡ነጣቂዎች፡ወፎች፥ለምድርም፡አውሬዎች፡በአንድነት፡ይቀራሉ፤ነጣቂዎችም፡ወፎች፡ይባጁባ ቸዋል፥የምድርም፡አውሬዎች፡ዅሉ፡ይከርሙባቸዋል።
7፤በዚያን፡ዘመን፡ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፥ከረዥምና፡ከለስላሳ፡ሕዝብ፥ከመዠመሪያው፡አስደንጋጭ፡ከኾ ነ፡ወገን፥ከሚሰፍርና፡ከሚረግጥ፥ወንዞችም፡ምድራቸውን፡ከሚከፍሉት፡ሕዝብ፡ዘንድ፡እጅ፡መንሻ፡የሰራዊት፡ጌ ታ፡የእግዚአብሔር፡ስም፡ወደሚገኝበት፡ስፍራ፡ወደጽዮን፡ተራራ፡ይቀርባል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤ስለ፡ግብጽ፡የተነገረ፡ሸክም፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡በፈጣን፡ደመና፡እይበረረ፡ወደ፡ግብጽ፡ይመጣል፤የግብጽ ም፡ጣዖታት፡በፊቱ፡ይርዳሉ፥የግብጽም፡ልብ፡በውስጧ፡ይቀልጣል።
2፤ግብጻውያንን፡በግብጻውያን፡ላይ፡አስነሣለኹ፤ወንድምም፡ወንድሙን፥ሰውም፡ባልንጀራውን፥ከተማም፡ከተማን፥ መንግሥትም፡መንግሥትን፡ይወጋል።
3፤የግብጽም፡መንፈስ፡በውስጧ፡ባዶ፡ይኾናል፥ምክራቸውንም፡አጠፋለኹ፤እነርሱም፡ጣዖቶቻቸውን፡በድግምት፡የሚ ጠነቍሉትንም፡መናፍስት፡ጠሪዎቻቸውንም፡ጠንቋዮቻቸውንም፡ይጠይቃሉ።
4፤ግብጻውያንንም፡በጨካኝ፡ጌታ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፤ጨካኝ፡ንጉሥም፡ይገዛቸዋል፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።
5፤ውሃዎችም፡ከባሕር፡ይደርቃሉ፥ወንዙም፡ያንሳል፡ደረቅም፡ይኾናል።
6፤ወንዞቹም፡ይገማሉ፥የግብጽም፡መስኖች፡ያንሳሉ፡ይደርቃሉም፤ደንገልና፡ቄጤማ፡ይጠወልጋሉ።
7፤በአባይ፡ወንዝ፡ዳር፡ያለው፡መስክ፡በአባይም፡ወንዝ፡አጠገብ፡የተዘራ፡ዕርሻ፡ዅሉ፡ይደርቃል፥ይበተንማል፥ አይገኝምም።
8፤ዓሣ፡አጥማጆቹ፡ያዝናሉ፥በአባይም፡ወንዝ፡መቃጥን፡የሚጥሉት፡ዅሉ፡ያለቅሳሉ፥በውሃዎችም፡ላይ፡መረብ፡የሚ ዘረጉት፡ይዝላሉ።
9፤የተበጠረውንም፡የተልባ፡እግር፡የሚሠሩ፥ነጩንም፡ልብስ፡የሚሠሩ፡ሸማኔዎች፡ያፍራሉ።
10፤ደገፋዎቿም፡ዅሉ፡ይሰባበራሉ፥የደመ፡ወዘኛዎችም፡ነፍስ፡ትተክዛለች።
11፤የጣኔዎስ፡አለቃዎች፡ፍጹም፡ሰነፎች፡ናቸው፤ፈርዖንን፡የሚመክሩ፡ጥበበኛዎች፡ምክራቸው፡ድንቍርና፡ኾነች ።ፈርዖንን፦እኛ፡የጥበበኛዎች፡ልጆች፡የቀደሙም፡ነገሥታት፡ልጆች፡ነን፡እንዴት፡ትሉታላችኹ፧
12፤አኹንሳ፡ጥበበኛዎችኽ፡የት፡አሉ፧አኹን፡ይንገሩኽ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በግብጽ፡ላይ፡ያሰበውን ፡ይወቁ።
13፤የጣኔዎስ፡አለቃዎች፡ሰነፎች፡ኾነዋል፥የሜምፎስም፡አለቃዎች፡ተሸንግለዋል፤የነገዶቿ፡የማእዘን፡ድንጋዮ ች፡የኾኑ፡ግብጽን፡አሳቱ።
14፤እግዚአብሔር፡የጠማምነትን፡መንፈስ፡በውስጧ፡ደባልቋል፤ሰካር፡በትፋቱ፡እንዲስት፡እንዲሁ፡ግብጽን፡በሥ ራዋ፡ዅሉ፡አሳቱ።
15፤ራስ፡ወይም፡ዥራት፡የሰሌን፡ቅርንጫፍ፡ወይም፡እንግጫ፡ቢኾን፡ሊሠራ፡የሚችል፡ሥራ፡ለግብጽ፡አይኾንላትም ።
16፤በዚያ፡ቀን፡ግብጻውያን፡እንደ፡ሴቶች፡ይኾናሉ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡በእነርሱ፡ላይ፡ከሚያንቀ ሳቅሳት፡ከእጁ፡መንቀሳቀስ፡የተነሣ፡ይሸበራሉ፡ይፈሩማል።
17፤የይሁዳም፡ምድር፡ግብጽን፡የምታስደነግጥ፡ትኾናለች፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ከመከረባት፡ምክር፡የ ተነሣ፡ወሬዋን፡የሚሰማ፡ዅሉ፡ይፈራል።
18፤በዚያ፡ቀን፡በግብጽ፡ምድር፡በከነዓን፡ቋንቋ፡የሚናገሩ፥በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔርም፡የሚምሉ፡ዐምስ ት፡ከተማዎች፡ይኾናሉ፤ከነዚህም፡አንዲቱ፡የጥፋት፡ከተማ፡ተብላ፡ትጠራለች።
19፤በዚያ፡ቀን፡በግብጽ፡ምድር፡መካከል፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፥በዳርቻዋም፡ለእግዚአብሔር፡ዐምድ፡ይኾናል ።
20፤ይህም፡ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡በግብጽ፡ምድር፡ምልክትና፡ምስክር፡ይኾናል፤ከሚያስጨንቋቸው፡የተ ነሣ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይጮኻሉና፥ርሱም፡መድኀኒትንና፡ኀያልን፡ሰዶ፟፡ያድናቸዋልና።
21፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡በግብጽ፡የታወቀ፡ይኾናል፥ግብጻውያንም፡እግዚአብሔርን፡ያውቃሉ፤በመሥዋዕት ና፡በቍርባን፡ያመልካሉ፥ለእግዚአብሔርም፡ስእለት፡ይሳላሉ፡ይፈጽሙትማል።
22፤እግዚአብሔርም፡ግብጽን፡ይመታታል፤ይመታታል፡ይፈውሳታልም፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ይመለሳሉ፡ርሱም፡ይለመ ናቸዋል፡ይፈውሳቸውማል።
23፤በዚያ፡ቀን፡ከግብጽ፡ወደ፡አሶር፡መንገድ፡ይኾናል፥አሶራዊውም፡ወደ፡ግብጽ፥ግብጻዊውም፡ወደ፡አሶር፡ይገ ባል፤ግብጻውያንም፡ከአሶራውያን፡ጋራ፡ይሰግዳሉ።
24፤25፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦ሕዝቤ፡ግብጽ፥የእጄም፡ሥራ፡አሶር፥ርስቴም፡እስራኤል፡የተባረከ፡ይኹን ፡ብሎ፡ይባርካቸዋልና፥በዚያ፡ቀን፡እስራኤል፡ለግብጽና፡ለአሶር፡ሦስተኛ፡ይኾናል፥በምድርም፡መካከል፡በረከ ት፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤የአሶር፡ንጉሥ፡ሳርጎን፡ተርታንን፡በሰደደ፡ጊዜ፥ርሱም፡ወደ፡አዛጦን፡በመጣ፡ጊዜ፥አዛጦንንም፡ወግቶ፡በያ ዛት፡ጊዜ፥
2፤በዚያ፡ዓመት፡እግዚአብሔር፡የዓሞጽን፡ልጅ፡ኢሳይያስን፦ኺድ፥ማቅኽን፡ከወገብኽ፡አውጣ፥ጫማኽንም፡ከእግር ኽ፡አውልቅ፡ብሎ፡ተናገረው።እንዲህም፡አደረገ፥ዕራቍቱንም፡ባዶ፡እግሩንም፡ኼደ።
3፤እግዚአብሔርም፡አለ፦ባሪያዬ፡ኢሳይያስ፡በግብጽና፡በኢትዮጵያ፡ላይ፡ሦስት፡ዓመት፡ለምልክትና፡ለተኣምራት ፡ሊኾን፡ዕራቍቱንና፡ባዶ፡እግሩን፡እንደ፡ኼደ፥
4፤እንዲሁ፡የአሶር፡ንጉሥ፡የግብጽንና፡የኢትዮጵያን፡ምርኮ፥ጐበዛዝቱንና፡ሽማግሌዎቹን፥ዕራቍታቸውንና፡ባዶ ፡እግራቸውን፡አድርጎ፥ገላቸውንም፡ገልጦ፥ለግብጽ፡ጕስቍልና፡ይነዳቸዋል።
5፤እነርሱም፡ከተስፋቸው፡ከኢትዮጵያ፡ከትምክሕታቸውም፡ከግብጽ፡የተነሣ፡ይፈራሉ፡ያፍሩማል፤
6፤በዚያም፡ቀን፡በዚች፡ባሕር፡ዳርቻ፡የሚቀመጡ፦እንሆ፥ከአሶር፡ንጉሥ፡እንድን፡ዘንድ፥ለርዳታ፡ወደ፡እነርሱ ፡የሸሸንበት፡ተስፋችን፡ይህ፡ነበረ፤እኛስ፡እንዴት፡እናመልጣለን፧ይላሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤በባሕር፡አጠገብ፡ስላለው፡ስለ፡ምድረ፡በዳ፡የተነገረ፡ሸክም።ዐውሎ፡ነፋስ፡ከደቡብ፡እንደሚወጣ፥እንዲሁ፡ ከሚያስፈራ፡አገር፡ከምድረ፡በዳ፡ይወጣል።
2፤ከባድ፡ራእይ፡ተነገረኝ፤ወንጀለኛው፡ይወነጅላል፥አጥፊውም፡ያጠፋል።ዔላም፡ሆይ፥ውጪ፤ሜዶን፡ሆይ፥ክበቢ፤ ትካዜውን፡ዅሉ፡አስቀርቻለኹ።
3፤ስለዚህ፥ወገቤ፡ሕመም፡ተሞላ፤እንደምትወልድ፡ሴት፡ምጥ፡ያዘኝ፤ከሕመሜ፡የተነሣ፡አልሰማም፥ከድንጋጤም፡የ ተነሣ፡አላይም።
4፤ልቤ፡ተንበደበደ፥ድንጋጤ፡አስፈራኝ፥ተስፋ፡ያደረግኹትም፡ድንግዝግዝታ፡መንቀጥቀጥ፡ኾነብኝ።
5፤ማዕዱን፡ያዘጋጃሉ፥ምንጣፉንም፡ይዘረጋሉ፥ይበሉማል፥ይጠጡማል፤እናንተ፡መሳፍንት፡ሆይ፥ተነሡ፥ጋሻውን፡አ ዘጋጁ።
6፤ጌታ፡እንዲህ፡ብሎኛልና፦ኺድ፥ጕበኛም፡አቁም፥የሚያየውንም፡ይናገር።
7፤በከብት፡የሚቀመጡትን፥ኹለት፡ኹለት፡እየኾኑ፡የሚኼዱት፡ፈረሰኛዎች፥በአህያዎች፡የሚቀመጡትንና፡በግመሎች ፡የሚቀመጡትን፡ባየ፡ጊዜ፡በጽኑ፡ትጋት፡አስተውሎ፡ተግቶም፡ያድምጥ።
8፤ያየውም፦ጌታ፡ሆይ፥ቀኑን፡ዅሉ፡ዘወትር፡በማማ፡ላይ፡ቆሜያለኹ፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡በመጠበቂያዬ፡ላይ፡ተተክያ ለኹ፥
9፤እንሆም፥በፈረሶች፡የሚቀመጡ፥ኹለት፡ኹለት፡ኹነው፡የሚኼዱ፡ፈረሰኛዎች፡ይመጣሉ፡ብሎ፡ጮኸ፤ርሱም፡መልሶ፦ ባቢሎን፡ወደቀች፡ወደቀች፥የተቀረጹም፡የአማልክቷ፡ምስሎች፡ዅሉ፡በምድር፡ላይ፡ተጥለው፡ደቀቁ፡አለ።
10፤እናንተ፡በዐውድማዬ፡ላይ፡የተወቃችኹ፡የዐውድማዬ፡ልጆች፡ሆይ፥ከእስራኤል፡አምላክ፡ከሰራዊት፡ጌታ፡እግ ዚአብሔር፡የሰማኹትን፡ነገርዃችኹ።
11፤ስለ፡ኤዶምያስ፡የተነገረ፡ሸክም።አንዱ፡ከሴይር።ጕበኛ፡ሆይ፥ሌሊቱ፡ምን፡ያኽል፡ነው፧ጕበኛ፡ሆይ፥ሌሊቱ ፡ምን፡ያኽል፡ነው፧ብሎ፡ጠራኝ።
12፤ጕበኛውም፦ይነጋል፡ድግሞም፡ይመሻል፤ትጠይቁ፡ዘንድ፡ብትወዱ፡ጠይቁ፤ተመልሳችኹም፡ኑ፡አለ።
13፤ስለ፡ዐረብ፡የተነገረ፡ሸክም።የድዳናውያን፡ነጋዴዎች፡ሆይ፥በዐረብ፡ዱር፡ውስጥ፡ታድራላችኹ።
14፤በቴማን፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ወደተጠሙት፡ሰዎች፡ውሃ፡አምጡ፡እንጀራ፡ይዛችኹ፡የሸሹትን፡ሰዎች፡ተቀበሏቸው።
15፤ከሰይፍ፥ከተመዘዘው፡ሰይፍ፥ከተለጠጠውም፡ቀስት፡ከጽኑም፡ሰልፍ፡ሸሽተዋልና።
16፤ጌታ፡እንዲህ፡ብሎኛልና፦እንደ፡ምንደኛ፡ዓመት፡ባንድ፡ዓመት፡ውስጥ፡የቄዳር፡ክብር፡ዅሉ፡ይጠፋል፤
17፤ከቀስተኛዎች፡ቍጥር፡የቀሩት፥የቄዳር፡ልጆች፡ኀያላን፥ያንሳሉ፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ተናግ ሯልና።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤ስለራእይ፡ሸለቆ፡የተነገረ፡ሸክም።እናንተ፡ዅላችኹ፡ወደ፡ሰገነት፡መውጣታችኹ፡ምን፡ኾናችዃል፧
2፤ጩኸትና፡ፍጅት፡የተሞላብሽ፡ከተማ፥ደስታ፡ያለሽ፡ከተማ፡ሆይ፥ባንቺ፡ውስጥ፡የተገደሉት፡በሰይፍ፡የተገደሉ ፡አይደሉም፥በሰልፍም፡የሞቱ፡አይደሉም።
3፤አለቃዎችሽ፡ዅሉ፡በአንድነት፡ሸሹ፥ያለቀስትም፡ተማረኩ፤ከሩቅ፡ሸሽተው፡ከአንቺ፡ዘንድ፡የተገኙት፡ዅሉ፡በ አንድነት፡ታሰሩ።
4፤ስለዚህ፦ፊታችኹን፡ከእኔ፡ዘንድ፡አርቁ፤መራራ፡ልቅሶ፡አለቅሳለኹ፤ስለ፡ሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ጥፋት፡ታጽናኑኝ ፡ዘንድ፡አትድከሙ፡አልኹ።
5፤ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የድንጋጤና፡የመረገጥ፡የድብልቅልቅም፡ቀን፥የቅጥርም፡መፍረስ፡ወደ ፡ተራራም፡መጮኽ፡በራእይ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ኾኗል።
6፤ዔላምም፡ከሠረገለኛዎችና፡ከፈረሰኛዎች፡ጋራ፡ኾኖ፡አፎቱን፡ተሸከመ፥ቂርም፡ጋሻውን፡ገለጠ።
7፤መልካሞቹንም፡ሸለቆዎችሽን፡ሠረገላዎች፡ሞሉባቸው፥ፈረሰኛዎችም፡መቆሚያቸውን፡በበር፡ላይ፡አደረጉ።
8፤የይሁዳንም፡መጋረጃ፡ገለጠ፤በዚያም፡ቀን፡በዱር፡ቤት፡የነበረውን፡የጦር፡ዕቃ፡ተመለከትኽ፥
9፤የዳዊትም፡ከተማ፡ፍራሾች፡እንደ፡በዙ፡አይታችዃል፥የታችኛውንም፡ኵሬ፡ውሃ፡አከማችታችዃል፥
10፤የኢየሩሳሌምን፡ቤቶች፡ቈጠራችኹ፡ቅጥሩንም፡ለማጥናት፡ቤቶችን፡አፈረሳችኹ።
11፤በአሮጌው፡ኵሬ፡ላለው፡ውሃ፡በኹለቱ፡ቅጥር፡መካከል፡መከማቻ፡ሠራችኹ፤ይህን፡ያደረገውን፡ግን፡አልተመለ ከታችኹም፥ቀድሞ፡የሠራውንም፡አላያችኹም።
12፤በዚያም፡ቀን፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ልቅሶና፡ወደ፡ዋይታ፡ራስን፡ወደ፡መንጨትና፡ማቅንም፡ወ ደ፡መልበስ፡ጠራ።
13፤እንሆም፥ሐሜትና፡ደስታ፡በሬውንና፡በጉንም፡ማረድ፡ሥጋንም፡መብላት፡የወይን፡ጠጅንም፡መጠጣት፡ኾነዋል፤ እናንተ፦ነገ፡እንሞታለንና፡እንብላ፡እንጠጣ፡ብላችዃል።
14፤ይህም፡ነገር፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ዦሮ፡ተሰማ፦እስክትሞቱ፡ድረስ፡ይህ፡በደል፡በእውነት፡አይ ሰረይላችኹም፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
15፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በቤቱ፡ውስጥ፡ወደ፡ተሾመው፡ወደዚህ፡አዛዥ፡ወደ፡ሳምናስ፡ ኺድ፥እንዲህም፡በለው፦
16፤መቃብር፡በዚህ፡ያስወቀርኽ፥ከፍ፡ባለው፡ስፍራ፡መቃብር፡ያሠ፟ራኽ፥በድንጋይም፡ውስጥ፡ለራስኽ፡መኖሪያ፡ ያሳነጽኽ፥በዚህ፡ምን፡አለኽ፧በዚህስ፡ባንተ፡ዘንድ፡ማን፡አለ፧
17፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡በኀይል፡ወርውሮ፡ይጥልኻል፥አጠንክሮም፡ይጨብጥኻል።
18፤ጠቅሎ፟ም፡ያንከባልልኻል፥ወደ፡ሰፊዪቱም፡ምድር፡እንደ፡ኳስ፡ይጥልኻል፤አንተ፡የጌታኽ፡ቤት፡ዕፍረት! በዚያ፡ትሞታለኽ፥በዚያም፡የክብርኽ፡ሠረገላዎች፡ይኾናሉ።
19፤ከአዛዥነት፡ሥራኽ፡አሳድድኻለኹ፥ከሹመትኽም፡ትሻራለኽ።
20፤በዚያም፡ቀን፡ባሪያዬን፡የኬልቅያስን፡ልጅ፡ኤልያቄምን፡እጠራለኹ፥
21፤መጐናጸፊያኽንም፡አለብሰዋለኹ፥በመታጠቂያኽም፡አስታጥቀዋለኹ፥ሹመትኽንም፡በእጁ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፤ በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ለይሁዳም፡ቤት፡አባት፡ይኾናል።
22፤የዳዊትንም፡ቤት፡መክፈቻ፡በጫንቃው፡ላይ፡አኖራለኹ፤ርሱም፡ይከፍታል፡የሚዘጋም፡የለም፡ርሱም፡ይዘጋል፡ የሚከፍትም፡የለም።
23፤በታመነም፡ስፍራ፡እንደ፡ችንካር፡እተክለዋለኹ፥ለአባቱም፡ቤት፡የክብር፡ዙፋን፡ይኾናል።
24፤የአባቱንም፡ቤት፡ክብር፡ዅሉ፡ልጆቹንም፡የልጅ፡ልጆቹንም፥ከጽዋ፡ዕቃ፡ዠምሮ፡እስከማድጋ፡ዕቃ፡ድረስ፥ታ ናናሹን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ይሰቅሉበታል።
25፤በዚያ፡ቀን፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥በታመነው፡ስፍራ፡የተከለው፡ችንካር፡ይወልቃል፡ተሰብሮ ም፡ይወድቃል፥በርሱም፡ላይ፡የተሰቀለው፡ሸክም፡ይጠፋል፡እግዚአብሔር፡ተናግሯልና።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤ስለ፡ጢሮስ፡የተነገረ፡ሸክም።የተርሴስ፡መርከቦች፡ሆይ፥አልቅሱ፤ፈርሷልና፥ቤት፡የለም፥መግባትም፡የለም፤ ከኪቲም፡አገር፡ዠምሮ፡ተገልጦላቸዋል።
2፤እናንተ፡በደሴት፡የምትኖሩ፡በባሕርም፡የምትሻገሩ፡የሲዶና፡ነጋዴዎች፡ንግድ፡የሞሉባችኹ፡ሆይ፥ጸጥ፡በሉ።
3፤የሺሖር፡ዘርና፡የአባይ፡ወንዝ፡መከር፡በብዙ፡ውሃዎች፡ላይ፡ገቢዋ፡ነበረ፤ርሷም፡የአሕዛብ፡መናገጃ፡ነበረ ች።
4፤ሲዶና፡ሆይ፥ባሕር፥የባሕር፡ምሽግ፦አላማጥኹም፥አልወለድኹም፤ጐበዛዝትንም፡አላሳደግኹም፥ደናግልንም፡አላ ሳደግኹም፡ብሎ፡ተናግሯልና፥ዕፈሪ።
5፤ወሬዋ፡ወደ፡ግብጽ፡በደረሰ፡ጊዜ፡በጢሮስ፡ወሬ፡ምጥ፡ይይዛቸዋል።
6፤ወደ፡ተርሴስ፡ተሻገሩ፤እናንተ፡በደሴት፡የምትኖሩ፡አልቅሱ።
7፤በቀድሞ፡ዘመን፡ተመሥርታ፡የነበረችው፥በዚያም፡እንደ፡እንግዳ፡ኾና፡ትኖር፡ዘንድ፡እግሮቿ፡ወደ፡ሩቅ፡ያፈ ለሷት፡የደስታችኹ፡ከተማ፡ይህች፡ናትን፧
8፤አክሊል፡ባስጫነች፡ከተማ፡በጢሮስ፡ላይ፡ይህን፡የወሰነ፡ማን፡ነው፧ነጋዴዎቿ፡አለቃዎች፡ናቸው፥በርሷም፡የ ሚሸጡና፡የሚለውጡ፡የምድር፡ክቡራን፡ናቸው።
9፤የክብርን፡ዅሉ፡ትዕቢት፡ይሽር፡ዘንድ፡የምድርንም፡ክቡራን፡ዅሉ፡ያስንቅ፡ዘንድ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብ ሔር፡ወስኖታል።
10፤የተርሴስ፡ልጅ፡ሆይ፥የሚከለክልሽ፡የለምና፡እንደ፡አባይ፡ወንዝ፡በአገርሽ፡ላይ፡ጐርፈሽ፡ዕለፊ።
11፤በባሕር፡ላይ፡እጁን፡ዘረጋ፡መንግሥታትንም፡አናወጠ፤ምሽጎቿንም፡ያጠፉ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ስለከነዓን ፡አገር፡አዘዘ።
12፤ርሱም፦አንቺ፡የተበደልሽ፡የሲዶና፡ድንግል፡ልጅ፡ሆይ፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ደስ፡አይበልሽ፤ተነሥተሽ፡ወደ ፡ኪቲም፡ተሻገሪ፥በዚያም፡ደግሞ፡አታርፊም፡አለ።
13፤እንሆ፥የከለዳውያን፡አገር! ይህ፡ሕዝብ፡ኾኖ፡አይገኝም፤አሶራውያን፡ለምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ሰጥተውታል፤ግንቦቻቸውን፡ሠሩ፥አዳራሾቿንም ፡አፈረሱ፥ባድማም፡አደረጓት።
14፤እናንተ፡የተርሴስ፡መርከቦች፡ሆይ፥ምሽጋችኹ፡ፈርሷልና፥ዋይ፡በሉ።
15፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ጢሮስ፡እንደ፡አንድ፡ንጉሥ፡ዘመን፡ሰባ፡ዓመት፡ያኽል፡የተረሳች፡ትኾናለ ች፤ከሰባ፡ዓመት፡በዃላ፡ግን፡ለጢሮስ፡በጋለሞታ፡ዘፈን፡እንደሚኾን፡እንዲሁ፡ይኾናል።
16፤አንቺ፡የተረሳሽ፡ጋለሞታ፡ሆይ፥መሰንቆ፡ያዢ፡በከተማ፡ላይም፡ዙሪ፤መታሰቢያም፡ይኾንልሽ፡ዘንድ፡ዜማን፡ አሳምሪ፡ዘፈንሽንም፡አብዢ።
17፤ከሰባ፡ዓመትም፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ጢሮስን፡ይጐበኛታል፥ወደ፡ዋጋዋም፡ትመለሳለች፥ደግሞም፡በምድር፡ፊ ት፡ላይ፡ከኾኑ፡ከዓለም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ጋራ፡ትገለሙታለች።
18፤ንግዷና፡ዋጋዋ፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ይኾናል፤ንግዷም፡በልተው፡ይጠግቡ፡ዘንድ፡ማለፊያም፡ልብስ፡ይ ለብሱ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለሚኖሩ፡ይኾናል፡እንጂ፡በዕቃ፡ቤትና፡በግምጃ፡ቤት፡ውስጥ፡አይከተትም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡ምድርን፡ባዶ፡ያደርጋታል፥ባድማም፡ያደርጋታል፥ይገለብጣትማል፥በርሷም፡የተቀመጡትን ፡ይበትናል።
2፤እንደ፡ሕዝቡም፡እንዲሁ፡ካህኑ፥እንደ፡ባሪያውም፡እንዲሁ፡ጌታው፥እንደ፡ባሪያዪቱም፡እንዲሁ፡እመቤቷ፥እን ደሚገዛም፡እንዲሁ፡የሚሸጠው፥እንደ፡አበዳሪውም፡እንዲሁ፡ተበዳሪው፥እንደ፡ዕዳ፡አስከፋዩም፡እንዲሁ፡ዕዳ፡ ከፋዩ፡ይኾናል።
3፤ምድር፡መፈታትን፡ትፈታለች፥ፈጽማም፡ትበላሻለች፤እግዚአብሔር፡ይህን፡ቃል፡ተናግሯልና።
4፤ምድርም፡አለቀሰች፥ረገፈችም፤ዓለም፡ደከመች፥ረገፈችም፤የምድርም፡ሕዝብ፡ታላላቆች፡ደከሙ።
5፤ምድርም፡ከሚቀመጡባት፡በታች፡ረክሳለች፥ሕጉን፡ተላልፈዋልና፥ሥርዐቱንም፡ለውጠዋልና፥የዘለዓለሙንም፡ቃል ፡ኪዳን፡አፍርሰዋልና።
6፤ስለዚህ፥መርገም፡ምድርን፡ትበላለች፥በርሷም፡የተቀመጡ፡ይቀጣሉ፤ስለዚህ፥የምድር፡ሰዎች፡ይቃጠላሉ፥ጥቂት ፡ሰዎችም፡ይቀራሉ።
7፤የወይን፡ጠጅ፡አለቀሰች፥የወይን፡ንግድ፡ደከመች፥ልባቸው፡ደስ፡ያለው፡ዅሉ፡ተከዙ።
8፤የከበሮው፡ሐሤት፡ቀርቷል፥የደስተኛዎች፡ድምፅ፡ዝም፡ብሏል፥የመሰንቆ፡ደስታ፡ቀርቷል።
9፤እየዘፈኑም፡የወይን፡ጠጅን፡አይጠጡትም፥የሚያሰክርም፡መጠጥ፡ለሚጠጡት፡መራራ፡ይኾናል።
10፤ባድማ፡የኾነችው፡ከተማ፡ፈረሰች፤ቤት፡ዅሉ፡ማንም፡እንዳይገባበት፡ተዘጋ።
11፤ስለወይኑም፡ጠጅ፡በአደባባይ፡ጩኸት፡ይኾናል፤ደስታ፡ዅሉ፡ጨልሟል፥የምድርም፡ሐሤት፡ፈርሷል።
12፤ከተማዪቱም፡ባድማ፡ኾናለች፥በሯም፡በጥፋት፡ተመትቷል።
13፤የወይራን፡ዛፍ፡እንደ፡መምታት፥ከወይንም፡መከር፡በዃላ፡ቃርሚያውን፡እንደ፡መልቀም፥እንዲሁ፡በምድር፡መ ካከል፡በአሕዛብም፡መካከል፡ይኾናል።
14፤እነዚህ፡ድምፃቸውን፡ያነሣሉ፥እልልም፡ይላሉ፥ስለእግዚአብሔር፡ክብርም፡ከባሕር፡ይጣራሉ።
15፤ስለዚህ፥እግዚአብሔርን፡በምሥራቅ፥የእስራኤልንም፡አምላክ፡የእግዚአብሔርንም፡ስም፡በባሕር፡ደሴቶች፡አ ክብሩ።
16፤ለጻድቁ፡ክብር፡ይኹን፡የሚለውን፡ዝማሬ፡ከምድር፡ዳርቻ፡ሰምተናል።እኔ፡ግን፦ከሳኹ፥ከሳኹ፥ወዮልኝ! ወንጀለኛዎች፡ወንጅለዋል፤ወንጀለኛዎች፡እጅግ፡ወንጅለዋል፡አልኹ።
17፤በምድር፡ላይ፡የምትኖር፡ሆይ፥ፍርሀትና፡ገደል፡ወጥመድም፡ባንተ፡ላይ፡አሉ።
18፤የሰማይ፡መስኮቶች፡ተከፍተዋልና፥የምድርም፡መሠረት፡ተናውጣለችና፥ከፍርሀት፡ድምፅ፡የሸሸ፡በገደል፡ይወ ድቃል፥ከገደልም፡የወጣ፡በወጥመድ፡ይያዛል።
19፤ምድር፡ተሰባበረች፥ምድር፡ፈጽማ፡ደቀቀች፥ምድር፡ተነዋወጠች።
20፤ምድር፡እንደ፡ሰካር፡ሰው፡ትንገዳገዳለች፥እንደ፡ዳስም፡ትወዛወዛለች፤መተላለፏ፡ይከብድባታል፥ትወድቅማ ለች፥ደግማም፡አትነሣም።
21፤በዚያም፡ቀን፡እንደዚህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡በከፍታ፡ያለውን፡ሰራዊት፡በከፍታ፡ላይ፥በምድርም፡ያሉት ን፡ነገሥታት፡በምድር፡ላይ፡ይቀጣቸዋል።
22፤ግዞተኛዎች፡በጕድጓድ፡እንደሚከማቹ፡በአንድነት፡ይከማቻሉ፥በግዞት፡ቤትም፡ውስጥ፡ተዘግተው፡ይኖራሉ፥ከ ብዙ፡ቀንም፡በዃላ፡ይጐበኛሉ።
23፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡በጽዮን፡ተራራና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ይነግሣልና፥በሽማግሌዎቹም፡ፊት፡ክ ብር፡ይኾናልና፥ጨረቃ፡ይታወካል፡ፀሓይም፡ያፍራል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤አቤቱ፥አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፤ድንቅን፡ነገር፡የዱሮ፡ምክርን፡በታማኝነትና፡በእውነት፡አድርገኻልና፥ከፍ፡ከ ፍ፡አደርግኻለኹ፥ስምኽንም፡አመሰግናለኹ።
2፤ከተማዪቱን፡የድንጋይ፡ክምር፥የተመሸገችውን፡ከተማ፡ውድማ፡እንድትኾን፥የኃጥኣንንም፡አዳራሽ፡ከተማ፡እን ዳትኾን፡አድርገኻል፤ከቶ፡አትሠራም።
3፤ስለዚህ፥ኀያላኑ፡ወገኖች፡ያከብሩኻል፥የጨካኞች፡አሕዛብ፡ከተማም፡ትፈራኻለች።
4፤የጨካኞችም፡ቍጣ፡እስትንፋስ፡ቅጥርን፡እንደሚመታ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡በኾነ፡ጊዜ፥ለድኻው፡መጠጊያ፥ለችግረኛው ፡በጭንቁ፡ጊዜ፡መጠጊያ፥ከውሽንፍር፡መሸሸጊያ፡ከሙቀትም፡ጥላ፡ኾነኻል።
5፤እንደ፡ሙቀት፡በደረቅ፡ስፍራ፡የኃጥኣንን፡ጩኸት፡ዝም፡ታሠኛለኽ፤ሙቀትም፡በደመና፡ጥላ፡እንዲበርድ፡እንዲ ሁ፡የጨካኞች፡ዝማሬ፡ይዋረዳል።
6፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ለሕዝብ፡ዅሉ፡በዚህ፡ተራራ፡ላይ፡ታላቅ፡የሰባ፡ግብዣ፥ያረጀ፡የወይን፡ጠጅ ፥ቅልጥም፡የሞላባቸው፡የሰቡ፡ነገሮች፥የጥሩና፡ያረጀ፡የወይን፡ጠጅ፡ግብዣ፡ያደርጋል።
7፤በዚህም፡ተራራ፡ላይ፡በወገኖች፡ዅሉ፡ላይ፡የተጣለውን፡መጋረጃ፥በአሕዛብም፡ዅሉ፡ላይ፡የተዘረጋውን፡መሸፈ ኛ፡ያጠፋል።
8፤ሞትን፡ለዘለዓለም፡ይውጣል፥ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ከፊት፡ዅሉ፡እንባን፡ያብሳል፥የሕዝቡን፡ስድብ፡ከምድር፡ ዅሉ፡ላይ፡ያስወግዳል፤እግዚአብሔር፡ተናግሯልና።
9፤በዚያም፡ቀን፦እንሆ፥አምላካችን፡ይህ፡ነው፤ተስፋ፡አድርገነዋል፥ያድነንማል፤እግዚአብሔር፡ይህ፡ነው፤ጠብ ቀነዋል፤በማዳኑ፡ደስ፡ይለናል፡ሐሤትም፡እናደርጋለን፡ይባላል።
10፤የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በዚህ፡ተራራ፡ላይ፡ታርፋለች፥ጭድም፡በጭቃ፡ውስጥ፡እንደሚረገጥ፡እንዲሁ፡ሞዐብ፡ በስፍራው፡ይረገጣል።
11፤ዋናተኛም፡ሲዋኝ፡እጁን፡እንደሚዘረጋ፥እንዲሁ፡በመካከሉ፡እጁን፡ይዘረጋል፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ት ዕቢቱን፡ከእጁ፡ተንኰል፡ጋራ፡ያዋርዳል።
12፤የተመሸገውንም፡ከፍ፡ከፍ፡ያለውንም፡ቅጥርኽን፡ዝቅ፡ያደርገዋል፥ያዋርደውማል፥ወደ፡መሬትም፡እስከ፡ዐፈ ር፡ድረስ፡ይጥለዋል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤በዚያም፡ቀን፡ይህ፡ቅኔ፡በይሁዳ፡ምድር፡ይዘመራል።የጸናች፡ከተማ፡አለችን፤ለቅጥርና፡ለምሽግ፡መድኀኒትን ፡ያኖርባታል።
2፤እውነትን፡የሚጠብቅ፡ጻድቅ፡ሕዝብ፡ይገባ፡ዘንድ፡በሮችን፡ክፈቱ።
3፤ባንተ፡ታምናለችና፡ባንተ፡ለምትደገፍ፡ነፍስ፡ፈጽመኽ፡በሰላም፡ትጠብቃታለኽ።
4፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡የዘለዓለም፡ዐምባ፡ነውና፥ለዘለዓለም፡በእግዚአብሔር፡ታመኑ።
5፤በከፍታ፡የሚኖሩትን፡ሰዎች፡ዝቅ፡ያደርጋል፤ከፍ፡ያለችውን፡ከተማ፡ያዋርዳል፥እስከ፡መሬትም፡ድረስ፡ያዋር ዳታል፥እስከ፡ዐፈርም፡ድረስ፡ይጥላታል።
6፤እግር፥የድኻ፡እግርም፡የችግረኛም፡አረጋገጥ፥ትረግጣታለች።
7፤የጻድቃን፡መንገድ፡ቅን፡ናት፤አንተ፡ቅን፡የኾንኽ፡የጻድቃንን፡መንገድ፡ታቃናለኽ።
8፤አቤቱ፥በፍርድኽ፡መንገድ፡ተስፋ፡አድርገንኻል፥ስምኽም፡መታሰቢያኽም፡የነፍሳችን፡ምኞት፡ነው።
9፤ፍርድኽን፡በምድር፡ባደረግኽ፡ጊዜ፡በዓለም፡የሚኖሩት፡ጽድቅን፡ይማራሉና፡ነፍሴ፡በሌሊት፡ትናፍቅኻለች፥መ ንፈሴም፡በውስጤ፡ወዳንተ፡ትገሠግሣለች።
10፤ለኀጢአተኛ፡ሞገስ፡ቢደረግለት፡ጽድቅን፡አይማርም፤በቅኖች፡ምድር፡ክፉን፡ነገር፡ያደርጋል፥የእግዚአብሔ ርንም፡ግርማ፡አያይም።
11፤አቤቱ፥እጅኽ፡ከፍ፡ከፍ፡አለች፡አላዩምም፤ነገር፡ግን፥በሕዝብኽ፡ላይ፡ያለኽን፡ቅንአት፡አይተው፡ያፍራሉ ፤እሳትም፡ጠላቶችኽን፡ትበላለች።
12፤አቤቱ፥ሥራችንን፡ዅሉ፡ሠርተኽልናልና፥ሰላምን፡ትሰጠናለኽ።
13፤አቤቱ፡አምላካችን፡ሆይ፥ከአንተ፡በቀር፡ሌላዎች፡ጌታዎች፡ገዝተውናል፤ነገር፡ግን፥ባንተ፡ብቻ፡ስምኽን፡ እናስባለን።
14፤እነርሱ፡ሞተዋል፥በሕይወት፡አይኖሩም፤ጠፍተዋል፥አይነሡም፤ስለዚህ፥አንተ፡ጐብኝተኻቸዋል፥አጥፍተኻቸው ማል፥መታሰቢያቸውንም፡ዅሉ፡ምንም፡ምን፡አድርገኻል።
15፤ሕዝብን፡አበዛኽ፥አቤቱ፥ሕዝብን፡አበዛኽ፤አንተም፡ተከበርኽ፥የአገሪቱንም፡ዳርቻ፡ዅሉ፡አሰፋኽ።
16፤አቤቱ፥በመከራ፡ጊዜ፡ፈለጉኽ፥በገሰጽኻቸውም፡ጊዜ፡ልመናቸውን፡ወዳንተ፡አፈሰሱ።
17፤የፀነሰች፡ሴት፡ለመውለድ፡ስትቀርብ፡እንደምትጨነቅና፡በምጥ፡እንደምትጮኽ፥አቤቱ፥እንዲሁ፡በፊትኽ፡ኾነ ናል።
18፤እኛ፡ፀንሰናል፡ምጥም፡ይዞናል፥ነፋስንም፡እንደምንወልድ፡ኾነናል፤በምድርም፡ደኅንነት፡አላደረግነም፤በ ዓለምም፡የሚኖሩ፡ይወድቃሉ።
19፤ሙታንኽ፡ሕያዋን፡ይኾናሉ፥ሬሳዎችም፡ይነሣሉ።በምድር፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ጠልኽ፡የብርሃን፡ጠል፡ነውና፥ምድ ርም፡ሙታንን፡ታወጣለችና፡ንቁ፡ዘምሩም።
20፤ሕዝቤ፡ሆይ፥ና፡ወደ፡ቤትኽም፡ግባ፥ደጅኽን፡በዃላኽ፡ዝጋ፡ቍጣ፡እስኪያልፍ፡ድረስ፡ጥቂት፡ጊዜ፡ተሸሸግ።
21፤በምድር፡በሚኖሩት፡ላይ፡በበደላቸው፡ምክንያት፡ቍጣውን፡ያመጣባቸው፡ዘንድ፥እንሆ፥እግዚአብሔር፡ከስፍራ ው፡ይወጣል፤ምድርም፡ደሟን፡ትገልጣለች፥ሙታኗንም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አትከድንም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ፈጣኑን፡እባብ፡ሌዋታንን፡ጠማማውንም፡እባብ፡ሌዋታንን፡በጠንካራ፡በታላቅም፡ በብርቱም፡ሰይፍ፡ይቀጣል፥በባሕርም፡ውስጥ፡ያለውን፡ዘንዶ፡ይገድላል።
2፤በዚያም፡ቀን፡ለተወደደው፡የወይን፡ቦታ፡ተቀኙለት።
3፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ጠባቂው፡ነኝ፤ዅልጊዜ፡አጠጣዋለኹ፤ማንም፡እንዳይጐዳው፡በሌሊትና፡በቀን፡እጠብቀዋለኹ ።
4፤አልቈጣም፤ሾኽና፡ኵርንችት፡በእኔ፡ላይ፡ምነው፡በሰልፍ፡በነበሩ! በእነርሱ፡ላይ፡ተራምጄ፡በአንድነት፡ባቃጠልዃቸው፡ነበር።
5፤ወይም፡ጕልበቴን፡ይያዝ፥ከእኔ፡ጋራ፡ሰላም፡ያድርግ፤ከእኔ፡ጋራ፡ሰላም፡ያድርግ።
6፤በሚመጣው፡ዘመን፡ያዕቆብ፡ሥር፡ይሰዳ፟ል፥እስራኤልም፡ያብባል፡ይጨበጭብማል፤በፍሬያቸውም፡የዓለሙን፡ፊት ፡ይሞላሉ።
7፤በእውኑ፡የመቱትን፡እንደ፡መታ፡እንዲሁ፡ርሱን፡መታውን፧ወይስ፡እነርሱ፡እንደ፡ተገደሉበት፡መገደል፡ርሱ፡ ተገድሏልን፧
8፤ነዳቸው፡ሰደዳቸው፡ቀሠፋቸው፤የምሥራቅ፡ነፋስ፡እንደሚነፍስበት፡ቀን፡በጠንካራ፡ዐውሎ፡አስወገዳቸው።
9፤ስለዚህም፡የማምለኪያ፡ዐጸዶችና፡የፀሓይ፡ምስሎች፡ዳግመኛ፡እንዳይነሡ፡የመሠዊያውን፡ድንጋይ፡ዅሉ፡እንደ ፡ደቀቀ፡እንደ፡ኖራ፡ድንጋይ፡ባደረገ፡ጊዜ፥እንዲሁ፡የያዕቆብ፡በደል፡ይሰረያል፥ይህም፡ኀጢአትን፡የማስወገ ድ፡ፍሬ፡ዅሉ፡ነው።
10፤የተመሸገችው፡ከተማ፡ብቻዋን፡ኾነች፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ኾና፡የተፈታችና፡የተተወች፡መኖሪያ፡ናት፤በዚያ ም፡ጥጃ፡ይሰማራል፡በዚያም፡ይተኛል፡ቅርንጫፏንም፡ይበላል።
11፤ጫፎቿ፡በደረቁ፡ጊዜ፡ይሰበራሉ፥ሴቶችም፡መጥተው፡ያቃጥሏቸዋል፤የማያስተውል፡ሕዝብ፡ነውና፥ስለዚህ፡ፈጣ ሪው፡አይራራለትም፡ሠሪውም፡ምሕረት፡አያደርግለትም።
12፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡ከወንዝ፡ፈሳሽ፡ዠምሮ፡እስከግብጽ፡ወንዝ፡ድረስ፡እኽሉን፡ ይወቃል፥እናንተም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥አንድ፡ባንድ፡ትሰበሰባላችኹ።
13፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ታላቅ፡መለከት፡ይነፋል፥በአሶርም፡የጠፉ፥በግብጽ፡ምድርም፡የተሰደዱ፡ይ መጣሉ፥በተቀደሰውም፡ተራራ፡በኢየሩሳሌም፡ለእግዚአብሔር፡ይሰግዳሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤ለኤፍሬም፡ሰካሮች፡ትዕቢት፡አክሊል፥በወይን፡ጠጅ፡ለተሸነፉ፡በወፍራም፡ሸለቋቸው፡ራስ፡ላይ፡ላለችም፡ለረ ገፈች፡ለክብሩ፡ጌጥ፡አበባ፡ወዮ!
2፤እንሆ፥በጌታ፡ዘንድ፡ኀያል፡ብርቱ፡የኾነ፡አለ።እንደ፡በረዶ፡ወጨፎ፥እንደሚያጠፋም፡ዐውሎ፡ነፋስ፥እንደሚ ያጥለቀልቅም፡እንደ፡ታላቅ፡ውሃ፡ፈሳሽ፡በጠነከረ፡እጅ፡ወደ፡ምድር፡ይጥላል።
3፤የኤፍሬም፡ሰካሮች፡ትዕቢት፡አክሊል፡በእግር፡ይረገጣል፤
4፤በወፍራሙ፡ሸለቆ፡ራስ፡ላይ፡ያለች፡የረገፈች፡የክብሩ፡ጌጥ፡አበባ፡ከመከር፡በፊት፡አስቀድማ፡እንደምትበስ ል፡በለስ፡ትኾናለች፤ሰው፡ባያት፡ጊዜ፡በእጁ፡እንዳለች፡ይበላታል።
5፤በዚያ፡ቀን፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለቀሩት፡ሕዝቡ፡የክብር፡ዘውድና፡የጌጥ፡አክሊል፡ይኾናል፤
6፤በፍርድ፡ወንበር፡ላይ፡ለሚቀመጥም፡የፍርድ፡መንፈስ፥ሰልፉን፡ወደ፡በር፡ለሚመልሱም፡ኀይል፡ይኾናል።
7፤እነዚህም፡ደግሞ፡ከወይን፡ጠጅ፡የተነሣ፡ይስታሉ፥ከሚያሰክርም፡መጠጥ፡የተነሣ፡ይፋንናሉ፤ካህኑና፡ነቢዩ፡ ከሚያሰክር፡መጠጥ፡የተነሣ፡ይስታሉ፥በወይን፡ጠጅም፡ይዋጣሉ፥ከሚያሰክርም፡መጠጥ፡የተነሣ፡ይፋንናሉ፤በራእ ይ፡ይስታሉ፥በፍርድም፡ይሰናከላሉ።
8፤ማእዱ፡ዅሉ፡ትፋትንና፡ርኵሰትን፡ተሞልቷታል፤ንጹሕ፡ስፍራ፡እንኳ፡የለም።
9፤ዕውቀትን፡ለማን፡ያስተምረዋል፧ወይስ፡ወሬ፡ማስተዋልን፡ለማን፡ይሰጣል፧ወተትን፡ለተዉ፡ወይስ፡ጡትን፡ለጣ ሉ፡ነውን፧
10፤ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ጥቂት፡በዚህ፡ጥቂት፡በዚያ ፡ነው።
11፤በባዕድ፡አፍ፡በልዩም፡ልሳን፡ለዚህ፡ሕዝብ፡ይናገራል፤ርሱም፦ዕረፍት፡ይህች፡ናት፥
12፤የደከመውን፡አሳርፉ፤ይህችም፡ማረፊያ፡ናት፡አላቸው፤እነርሱ፡ግን፡መስማትን፡እንቢ፡አሉ።
13፤ስለዚህ፥ኼደው፡ወደ፡ዃላ፡እንዲወድቁ፥እንዲሰበሩም፥ተጠምደውም፡እንዲያ፟ዙ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ትእዛ ዝ፡በትእዛዝ፥ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ጥቂት፡በዚህ፡ጥቂት፡በዚያ፡ይኾንላ ቸዋል።
14፤ስለዚህ፥በኢየሩሳሌም፡ያለውን፡ሕዝብ፡የምትገዙ፡ፌዘኛዎች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
15፤እናንተም፦ከሞት፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አድርገናል፥ከሲኦልም፡ጋራ፡ተማምለናል፤ሐሰትን፡መሸሸጊያችን፡አድር ገናልና፥በሐሰትም፡ተሰውረናልና፥የሚትረፈረፍ፡መቅሠፍት፡ባለፈ፡ጊዜ፡አይደርስብንም፡ስላላችኹ፥
16፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በጽዮን፡ድንጋይን፡ለመሠረት፡አስቀምጣለኹ፤የተፈተነ ውን፥የከበረውን፥መሠረቱ፡የጸናውን፡የማእዘን፡ድንጋይ፤የሚያምን፡አያፍርም።
17፤ለገመድ፡ፍርድን፡ለቱንቢም፡ጽድቅን፡አደርጋለኹ፤በረዶውም፡የሐሰትን፡መሸሸጊያ፡ይጠርጋል፥ውሃዎችም፡መ ሰወሪያውን፡ያሰጥማሉ።
18፤ከሞትም፡ጋራ፡ያደረጋችኹት፡ቃል፡ኪዳን፡ይፈርሳል፥ከሲኦልም፡ጋራ፡የተማማላችኹት፡መሐላ፡አይጸናም፤የሚ ትረፈረፍ፡መቅሠፍት፡ባለፈ፡ጊዜ፡ትረገጡበታላችኹ።
19፤ባለፈም፡ጊዜ፡ይወስዳችዃል፤ማለዳ፡ማለዳ፡ቀንና፡ሌሊት፡ያልፋል፤ወሬውንም፡ማስተዋል፡ድንጋጤ፡ይኾናል።
20፤ሰው፡በርሱ፡ላይ፡ተዘርግቶ፡ቢተኛ፡ዐልጋው፡ዐጪር፡ነው፤ሰውም፡ሰውነቱን፡መሸፈን፡ቢወድ፟፡መጐናጸፊያ፡ ጠባብ፡ነው።
21፤እግዚአብሔርም፡ሥራውን፡ማለት፡እንግዳ፡ሥራውን፡ይሠራ፡ዘንድ፥አድራጎቱንም፡ማለት፡ያልታወቀውን፡አድራ ጎቱን፡ያደርግ፡ዘንድ፡በፐራሲም፡ተራራ፡እንደ፡ነበረ፡ይነሣል፥በገባዖንም፡ሸለቆ፡እንደ፡ነበረ፡ይቈጣል።
22፤አኹንም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡የሚጸናውን፡የጥፋት፡ትእዛዝ፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ሰምቻለ ኹና፥እስራት፡እንዳይጸናባችኹ፡አታፊዙ።
23፤አድምጡ፥ድምፄንም፡ስሙ፤ልብ፡አድርጉ፥ንግግሬንም፡ስሙ።
24፤በእውኑ፡ገበሬ፡ሊዘራ፡ዅልጊዜ፡ያርሳልን፧ወይስ፡ዅልጊዜ፡ዕርሻውን፡ይገለግላልን፧
25፤ጓሉንስ፡ይከሰክሳልን፧ዕርሻውን፡ባስተካከለ፡ጊዜ፡ጥቍሩን፡አዝሙድ፥ከሙኑንም፥ስንዴውንም፡በተርታ፥ገብ ሱንም፡በስፍራው፥ዐጃንም፡በደረጃው፡የሚዘራ፡አይደለምን፧
26፤ይህንም፡ብልኀት፡አምላኩ፡ያስታውቀዋል፡ያስተምረውማል።
27፤ጥቍሩ፡አዝሙድ፡በተሳለች፡መኼጃ፡አያኼድም፥የሠረገላም፡መንኰራኵር፡በከሙን፡ላይ፡አይዞርም፤ነገር፡ግን ፥ጥቍሩ፡አዝሙድ፡በሽመል፥ከሙኑም፡በበትር፡ይወቃል።
28፤የእንጀራ፡እኽል፡ይደቃ፟ልን፧ለዘለዓለም፡አያኼደውም፤የሠረገላውን፡መንኰራኵርና፡ፈረሶቹን፡ምንም፡ቢያ ስኬድበት፡አያደቀ፟ውም።
29፤ይህም፡ደግሞ፡ድንቅ፡ምክር፡ከሚመክር፡በግብሩም፡ማለፊያ፡ከኾነው፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ወጥቷ ል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤ዳዊት፡ለሰፈረባት፡ከተማ፡ለአርኤል፡ወዮላት! ዓመት፡በዓመት፡ላይ፡ጨምሩ፥በዓላትም፡ይመለሱ።
2፤አርኤልንም፡አስጨንቃለኹ፥ልቅሶና፡ዋይታም፡ይኾንባታል፤እንደ፡አርኤልም፡ትኾንልኛለች።
3፤በዙሪያሽም፡እሰፍራለኹ፥በቅጥርም፡ከብቤ፡አስጨንቅሻለኹ፥ዐምባም፡በላይሽ፡አቆማለኹ።
4፤ትዋረጂማለሽ፥በመሬትም፡ላይ፡ኾነሽ፡ትናገሪያለሽ፥ቃልሽም፡ዝቅ፡ብሎ፡ከዐፈር፡ይወጣል፤ድምፅሽም፡ከመሬት ፡እንደሚወጣ፡እንደ፡መናፍስት፡ጠሪ፡ድምፅ፡ይኾናል፥ቃልሽም፡ከዐፈር፡ወጥቶ፡ይጮኻል።
5፤ነገር፡ግን፥የጠላቶችሽ፡ብዛት፡እንደ፡ደቀቀ፡ትቢያ፥የጨካኞችም፡ብዛት፡እንደሚያልፍ፡ገለባ፡ይኾናል።
6፤ድንገትም፡ፈጥኖ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በነጐድጓድ፥በምድርም፡መናወጥ፥በታላቅም፡ድምፅ፥በዐውሎ፡ ነፋስም፥በወጨፎም፥በምትበላም፡በእሳት፡ነበልባል፡ይጐበኛታል።
7፤በአርኤልም፡ላይ፡የሚዋጉ፥ርሷንና፡ምሽጓንም፡የሚወጉ፡የሚያስጨንቋትም፥የአሕዛብ፡ዅሉ፡ብዛት፡እንደ፡ሕል ምና፡እንደ፡ሌሊት፡ራእይ፡ይኾናል።
8፤ተርቦም፡እንደሚያልም፡ሰው፡ይኾናል፤በሕልሙም፥እንሆ፥ይበላል፥ነገር፡ግን፥ይነቃል፡ሰውነቱም፡ባዶ፡ነው፤ ተጠምቶም፡እንደሚያልም፡ሰው፡ይኾናል፤በሕልሙም፥እንሆ፥ይጠጣል፥ነገር፡ግን፥ይነቃል፥እንሆም፥ይዝላል፡ሰው ነቱም፡አምሮት፡አለው፤እንዲሁ፡የጽዮንን፡ተራራ፡የሚወጉ፡የአሕዛብ፡ዅሉ፡ብዛት፡ይኾናል።
9፤ተደነቁ፡ደንግጡም፤ተጨፈኑም፡ዕውሮችም፡ኹኑ፤በወይን፡ጠጅ፡አይኹን፡እንጂ፡ሰከሩ፤በሚያሰክር፡መጠጥ፡አይ ኹን፡እንጂ፡ተንገደገዱ።
10፤እግዚአብሔር፡የእንቅልፍ፡መንፈስ፡አፍሶ፟ባችዃል፡ዐይኖቻችኹን፡ነቢያትንም፡ጨፍኖባችዃል፡ራሶቻችኹን፡ ባለራእዮችን፡ሸፍኖባችዃል።
11፤ራእዩም፡ዅሉ፡እንደ፡ታተመ፡መጽሐፍ፡ቃል፡ኾኖባችዃል፤ማንበብንም፡ለሚያውቅ፦ይህን፡አንብ፟፡ብለው፡በሰ ጡት፡ጊዜ፡ርሱ፦ታትሟልና፥አልችልም፡ይላቸዋል፤
12፤ደግሞም፡መጽሐፉን፡ማንበብን፡ለማያውቅ፦ይህን፡አንብ፟፡ብለው፡በሰጡት፡ጊዜ፡ርሱ፦ማንበብ፡አላውቅም፡ይ ላቸዋል።
13፤ጌታም፦ይህ፡ሕዝብ፡በአፉ፡ወደ፡እኔ፡ይቀርባልና፥በከንፈሮቹም፡ያከብረኛልና፥ልቡ፡ግን፡ከእኔ፡የራቀ፡ነ ውና፥በሰዎች፡ሥርዐትና፡ትምህርት፡ብቻ፡ይፈራኛልና፥
14፤ስለዚህ፥እንሆ፥ድንቅ፡ነገርን፡በዚህ፡ሕዝብ፡መካከል፥ድንቅ፡ነገርን፡ተኣምራትንም፥እንደ፡ገና፡አደርጋ ለኹ፤የጥበበኛዎችም፡ጥበብ፡ትጠፋለች፥የአስተዋዮችም፡ማስተዋል፡ትሰወራለች።
15፤ምክራቸውን፡ጥልቅ፡አድርገው፡ከእግዚአብሔር፡ለሚሰውሩ፥ሥራቸውንም፡በጨለማ፡ውስጥ፡አድርገው።ማን፡ያየ ናል፧ወይስ፡ማን፡ያውቀናል፧ለሚሉ፡ወዮላቸው!
16፤ይህ፡የእናንተ፡ጠማምነት፡ነው፤እንደ፡ሸክላ፡ሠሪ፡ጭቃ፡የምትቈጠሩ፡አይደላችኹምን፧በእውኑ፡ሥራ፡ሠሪው ን፦አልሠራኸኝም፡ይለዋልን፧ወይስ፡የተደረገው፡አድራጊውን፦አታስተውልም፡ይለዋልን፧
17፤ሊባኖስ፡እንደ፡ፍሬያማ፡ዕርሻ፡ሊለወጥ፡ፍሬያማውም፡ዕርሻ፡እንደ፡ዱር፡ሊቈጠር፡ጥቂት፡ዘመን፡የቀረ፡አ ይደለምን፧
18፤በዚያም፡ቀን፡ደንቈሮዎች፡የመጽሐፍን፡ቃል፡ይሰማሉ፥የዕውሮችም፡ዐይኖች፡ከጭጋግና፡ከጨለማ፡ተለይተው፡ ያያሉ።
19፤የዋሃን፡ደስታቸውን፡በእግዚአብሔር፡ያበዛሉ፥በሰዎች፡መካከል፡ያሉ፡ችግረኛዎችም፡ሐሤትን፡በእስራኤል፡ ቅዱስ፡ያደርጋሉ።
20፤ጨካኙ፡ሰው፡አልቋልና፥ፌዘኛውም፡ጠፍቷልና፥ለኀጢአትም፡የደፈጡ፡ዅሉ፡ይቈረጣሉና፤
21፤እነዚህም፡ሰውን፡በነገር፡በደለኛ፡የሚያደርጉ፥በበርም፡ለሚገሥጸው፡አሽክላ፡የሚያኖሩ፥ጻድቁንም፡በከን ቱ፡ነገር፡የሚያስቱ፡ናቸው።
22፤ስለዚህ፥አብርሃምን፡የተቤዠ፡እግዚአብሔር፥ስለያዕቆብ፡ቤት፡እንዲህ፡ይላል፦ያዕቆብ፡አኹን፡አያፍርም፥ ፊቱም፡አኹን፡አይለወጥም።
23፤ነገር፡ግን፥የእጄን፡ሥራ፡ልጆቹን፡በመካከሉ፡ባያቸው፡ጊዜ፡ስሜን፡ይቀድሳሉ፤የያዕቆብንም፡ቅዱስ፡ይቀድ ሳሉ፥የእስራኤልንም፡አምላክ፡ይፈራሉ።
24፤በመንፈስም፡የሳቱ፡ማስተዋልን፡ያውቃሉ፥የሚያጕረመርሙም፡ትምህርትን፡ይቀበላሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤ለዐመፀኛዎች፡ልጆች፡ወዮላቸው! ይላል፡እግዚአብሔር፤ከእኔ፡ዘንድ፡ያልኾነን፡ምክር፡ይመክራሉ፥ኀጢአትንም፡በኀጢአት፡ላይ፡ይጨምሩ፡ዘንድ፡ ከመንፈሴ፡ዘንድ፡ያልኾነውን፡ቃል፡ኪዳን፡ያደርጋሉ።
2፤ከአፌም፡ነገርን፡ሳይጠይቁ፡በፈርዖን፡ኀይል፡ይጸኑ፡ዘንድ፡በግብጽም፡ጥላ፡ይታመኑ፡ዘንድ፡ወደ፡ግብጽ፡እ ንዲወርዱ፡ይኼዳሉ።
3፤ስለዚህ፥የፈርዖን፡ኀይል፡ዕፍረት፥በግብጽም፡ጥላ፡መታመን፡ስድብ፡ይኾንባችዃል።
4፤አለቃዎች፡ምንም፡በጣኔዎስ፡ቢኾኑ፥መልክተኛዎችም፡ምንም፡ወደ፡ሓኔስ፡ቢደርሱ፥
5፤ዅላቸው፡ይጠቅሟቸው፡ዘንድ፡ስለማይችሉ፥ዕፍረትና፡ስድብ፡እንጂ፡ረድኤትና፡ረብ፡ስለማይኾኑ፡ሕዝብ፡ያፍራ ሉ።
6፤በደቡብ፡ስላሉ፡እንስሳዎች፡የተነገረ፡ሸክም።ተባትና፡እንስት፡አንበሳ፡እፍኝትም፡ነዘር፡እባብም፡በሚወጡ ባት፡በመከራና፡በጭንቀት፡ምድር፡በኩል፡ብልጥግናቸውን፡በአህያዎች፡ጫንቃ፡ላይ፡መዛግብቶቻቸውንም፡በግመሎ ች፡ሻኛ፡ላይ፡እየጫኑ፡ወደማይጠቅሟቸው፡ሕዝብ፡ይኼዳሉ።
7፤የግብጽ፡ርዳታ፡ከንቱና፡ምናምን፡ነው፤ስለዚህ፥ስሙን፦በቤት፡የሚቀመጥ፡ረዓብ፡ብዬ፡ጠርቼዋለኹ።
8፤አኹንም፡ኺድ፥ለሚመጣውም፡ዘመን፡ለዘለዓለም፡እንዲኾን፡በሰሌዳ፡ላይ፡በመጽሐፍም፡ውስጥ፡ጻፍላቸው።
9፤ዐመፀኛ፡ወገንና፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ለመስማት፡የማይወዱ፡የሐሰት፡ልጆች፡ናቸውና፤
10፤ባለራእዮችን፦አትመልከቱ፡ይላሉ፥ነቢያትንም፦ጣፋጩንና፡አታላዩን፡ነገር፡እንጂ፡ቅኑን፡ነገር፡አትንገሩ ን፡ከመንገድ፡ፈቀቅ፡በሉ፥
11፤ከጐዳናውም፡ዘወር፡በሉ፥የእስራኤልንም፡ቅዱስ፡ከእኛ፡ዘንድ፡አስወግዱ፡ይሏቸዋል።
12፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡ቅዱስ፡እንዲህ፡ይላል፦ይህችን፡ቃል፡አቃላ፟ችዃልና፥በግፍና፡በጠማምነት፡ታምናችዃ ልና፥በርሱም፡ተደግፋችዃልና፥
13፤ስለዚህ፥ይህ፡በደል፡አዘብዝቦ፡ለመፍረስ፡እንደ፡ቀረበ፥አፈራረሱም፡ፈጥኖ፡ድንገት፡እንደሚመጣ፡እንደ፡ ረዥም፡ቅጥር፡ይኾንባችዃል።
14፤የሸክለኛ፡ማድጋ፡እንደሚሰበር፡ይሰብረዋል፥ሳይራራም፡ያደቀ፟ዋል፤ከስባሪውም፡እሳት፡ከማንደጃ፡የሚወስ ዱበት፡ወይም፡ውሃ፡ከጕድጓድ፡የሚቀዱበት፡ገል፡አይገኝም።
15፤የእስራኤል፡ቅዱስ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በመመለስና፡በማረፍ፡ትድናላችኹ፤በጸጥታና፡በመ ታመን፡ኀይል፡ይኾንላችዃል፤እናንተም፡እንቢ፡አላችኹ፥
16፤ነገር፡ግን፦በፈረስ፡ላይ፡ተቀምጠን፡እንሸሻለን፡እንጂ፡እንዲህ፡አይኾንም፡አላችኹ፥ስለዚህም፡ትሸሻላች ኹ፤ደግሞም፦በፈጣን፡ፈረስ፡ላይ፡እንቀመጣለን፡አላችኹ፥ስለዚህም፡የሚያሳድዷችኹ፡ፈጣኖች፡ይኾናሉ።
17፤ካንድ፡ሰው፡ዛቻ፡የተነሣ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ይሸሻሉ፤እናንተም፡በተራራ፡ራስ፡ላይ፡እንዳለ፡ምሰሶ፥በኰረብታም ፡ላይ፡እንዳለ፡ምልክት፡ኾናችኹ፡እስክትቀሩ፡ድረስ፥ከዐምስት፡ሰዎች፡ዛቻ፡የተነሣ፡ትሸሻላችኹ።
18፤እግዚአብሔርም፡የፍርድ፡አምላክ፡ነውና፥ስለዚህ፡እግዚአብሔር፡ይራራላችኹ፡ዘንድ፡ይታገሣል፥ይምራችኹም ፡ዘንድ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፤ርሱን፡በመተማመን፡የሚጠባበቁ፡ዅሉ፡ብፁዓን፡ናቸው።
19፤በኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡በጽዮን፡የምትኖሩ፡ሕዝብ፡ሆይ፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታለቅስም፤በጩኸትም፡ድምፅ፡ይ ራራልኻል፥በሰማኽም፡ጊዜ፡ይመልስልኻል።
20፤ጌታም፡የጭንቀትን፡እንጀራና፡የመከራን፡ውሃ፡ቢሰጥኽም፡አስተማሪኽ፡እንግዲህ፡ከአንተ፡አይሰወርም፤ዐይ ኖችኽ፡ግን፡አስተማሪኽን፡ያያሉ፥
21፤ወደ፡ቀኝም፡ወደ፡ግራም፡ፈቀቅ፡ብትል፡ዦሮዎችኽ፡በዃላኽ፦መንገዱ፡ይህች፡ናት፡በርሷም፡ኺድ፡የሚለውን፡ ቃል፡ይሰማሉ።
22፤በብርም፡የተለበጡትን፡የተቀረጹትን፡ምስሎችኽን፡በወርቅም፡የተለበጡትን፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎችኽ ን፡ታረክሳለኽ፤እንደ፡ርኩስም፡ነገር፡ትጥላቸዋለኽ፦ወግዱ፡ትላቸውማለኽ።
23፤በምድርም፡ለተዘራው፡ዘርኽ፡ዝናብ፡ይሰጣል፥ከምድርም፡ፍሬ፡የሚወጣ፡እንጀራ፡ወፍራምና፡ብዙ፡ይኾናል።በ ዚያም፡ቀን፡ከብቶችኽ፡በሰፊ፡መስክ፡ይሰማራሉ፤
24፤መሬትንም፡የሚያርሱ፡በሬዎችና፡አህያዎች፡በመንሽና፡በወንፊት፡የነጻውን፡ጨው፡ጨው፡የሚለውን፡ገፈራ፡ይ በላሉ።
25፤በታላቅም፡እልቂት፡ቀን፡ግንቦች፡በወደቁ፡ጊዜ፡በረዥሙ፡ተራራ፡ዅሉ፡ከፍ፡ባለውም፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፡ወ ንዞችና፡የውሃ፡ፈሳሾች፡ይኾናሉ።
26፤እግዚአብሔርም፡የሕዝቡን፡ስብራት፡በጠገነ፡ዕለት፥መቅሠፍቱ፡የቈሰለውንም፡በፈወሰ፡ዕለት፥የጨረቃ፡ብር ሃን፡እንደ፡ፀሓይ፡ብርሃን፥የፀሓይም፡ብርሃን፡እንደ፡ሰባት፡ቀን፡ብርሃን፡ሰባት፡ዕጥፍ፡ይኾናል።
27፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ስም፡ከሚነድ፟፡ቍጣ፡ከሚትጐለጐልም፡ጢስ፡ጋራ፡ከሩቅ፡ይመጣል፤ከንፈሮቹም፡ቍጣን ፡የሞሉ፡ናቸው፥ምላሱም፡እንደምትበላ፡እሳት፡ናት፤
28፤እስትንፋሱም፡አሕዛብን፡በአጥፊ፡ወንፊት፡ሊነፋቸው፡እንደሚያጥለቀልቅ፡እስከ፡ዐንገትም፡እንደሚደርስ፡ ወንዝ፡ነው፥በሕዝብም፡መንጋጋ፡የሚያስት፡ልጓም፡ይኾናል።
29፤ዝማሬ፡በተቀደሰች፡የዐውደ፡ዓመት፡ሌሊት፡እንደሚኾን፡ዝማሬ፡ይኾንላችዃል፤ወደእግዚአብሔርም፡ተራራ፡ወ ደእስራኤል፡ዐምባ፡ይመጣ፡ዘንድ፡እንቢልታ፡ይዞ፡እንደሚኼድ፡ሰው፡የልብ፡ደስታ፡ይኾንላችዃል።
30፤እግዚአብሔርም፡ክቡር፡ድምፁን፡ያሰማል፥የክንዱንም፡መውረድ፡በሚነድ፟፡ቍጣውና፡በምትበላ፡እሳት፡ነበል ባል፡በዐውሎ፡ነፋስም፡በወጨፎም፡በበረዶ፡ጠጠርም፡ይገልጣል።
31፤አሶርም፡በበትር፡ከመታው፡ከእግዚአብሔር፡ድምፅ፡የተነሣ፡ይደነግጣል።
32፤እግዚአብሔር፡በላዩ፡በሚያወርድበት፡የታዘዘበቱ፡የበትር፡ድብደባ፡ዅሉ፡በከበሮና፡በመሰንቆ፡ይኾናል፤በ ጦርነትም፡ክንዱን፡አንሥቶ፡ይዋጋቸዋል።
33፤ከቀድሞም፡ዠምሮ፡የማቃጠያ፡ስፍራ፡ተዘጋጅታለች፥ለንጉሥም፡ተበጅታለች፤ጥልቅና፡ሰፊም፡አድርጓታል፤እሳ ትና፡ብዙ፡ማገዶ፡ተከምሯል፤የእግዚአብሔርም፡እስትንፋስ፡እንደ፡ዲን፡ፈሳሽ፡ያቃጥለዋል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31።
1፤ስለ፡ርዳታ፡ወደ፡ግብጽ፡ለሚወርዱ፡በፈረሶችም፡ለሚደገፉ፥ስለ፡ብዛታቸውም፡በሠረገላዎች፥እጅግ፡ብርቱዎች ም፡ስለ፡ኾኑ፡በፈረሰኛዎች፡ለሚታመኑ፥ወደእስራኤልም፡ቅዱስ፡ለማይመለከቱ፡እግዚአብሔርንም፡ለማይፈልጉ፡ወ ዮላቸው!
2፤ርሱ፡ግን፡ደግሞ፡ጠቢብ፡ነው፥ክፉንም፡ነገር፡ያመጣል፥ቃሉንም፡አይመልስም፥በክፉም፡አድራጊዎች፡ቤት፡ላይ ፡በደልንም፡በሚሠሩ፡ረዳት፡ላይ፡ይነሣል።
3፤ግብጻውያን፡ሰዎች፡እንጂ፡አምላክ፡አይደሉም፥ፈረሶቻቸውም፡ሥጋ፡እንጂ፡መንፈስ፡አይደሉም፤እግዚአብሔርም ፡እጁን፡በዘረጋ፡ጊዜ፥ረጂው፡ይሰናከላል፡ተረጂውም፡ይወድቃል፥ዅሉም፡ባንድ፡ላይ፡ይጠፋሉ።
4፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይለኛልና፦አንበሳ፡ወይም፡የአንበሳ፡ደቦል፡በንጥቂያው፡ላይ፡ሲያገሣ፥ብዙ፡እረኛ ዎች፡ቢከማቹበት፡ከቃላቸው፡እንደማይፈራ፡ከድምፃቸውም፡እንደማይዋረድ፥እንዲሁ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔ ር፡በጽዮን፡ተራራና፡በኰረብታዋ፡ላይ፡ይዋጋ፡ዘንድ፡ይወርዳል።
5፤እንደሚበር፟፡ወፍ፡እንዲሁ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ይጋርዳታል፤ይከልላታል፥ይታደጋታ ል፥ዐልፎም፡ያድናታል።
6፤እናንተ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥አጥብቃችኹ፡ወደዐመፃችኹበት፡ተመለሱ።
7፤በዚያም፡ቀን፡እያንዳንዳቸው፡እጆቻቸው፡ለኀጢአት፡የሠሩላቸውን፡የብሩንና፡የወርቁን፡ጣዖቶቻቸውን፡ይጥላ ሉ።
8፤አሶርም፡የሰው፡ባልኾነ፡ሰይፍ፡ይወድቃል፥የሰውም፡ያልኾነ፡ሰይፍ፡ይበላዋል፤ከሰይፍም፡ይሸሻሉ፡ጐበዛዝቱ ም፡ገባሮች፡ይኾናሉ።
9፤ዐምባው፡ከፍርሀት፡የተነሣ፡ያልፋል፥መሳፍንቱም፡ከዐላማው፡የተነሣ፡ይደነግጣሉ፥ይላል፡እሳቱ፡በጽዮን፡እ ቶኑም፡በኢየሩሳሌም፡የኾነ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32።
1፤እንሆ፥ንጉሥ፡በጽድቅ፡ይነግሣል፥መሳፍንትም፡በፍርድ፡ይገዛሉ።
2፤ሰውም፡ከነፋስ፡እንደ፡መሸሸጊያ፡ከዐውሎ፡ነፋስም፡እንደ፡መጠጊያ፥በጥም፡ቦታም፡እንደ፡ወንዝ፡ፈሳሽ፥በበ ረሓም፡አገር፡እንደ፡ትልቅ፡ድንጋይ፡ጥላ፡ይኾናል።
3፤የሚያዩትም፡ሰዎች፡ዐይኖች፡አይጨፈኑም፥የሚሰሙትም፡ዦሮዎች፡ያደምጣሉ።
4፤ጥንቃቄ፡የሌላቸው፡ሰዎች፡ልብ፡ዕውቀትን፡ታስተውላለች፥የተብታቦችም፡ምላስ፡ደኅና፡አድርጋ፡ትናገራለች።
5፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ሰነፍ፡ከበርቴ፡ተብሎ፡አይጠራም፥ንፉግም፡ለጋስ፡አይባልም።
6፤ሰነፍ፡ግን፡ስንፍናን፡ይናገራል፥ልቡም፡ዝንጉነትን፡ይፈጽም፡ዘንድ፡በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ስሕተትን፡ይና ገር፡ዘንድ፡የተራበችውንም፡ሰውነት፡ባዶ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ከተጠማም፡ሰው፡መጠጥን፡ይቈርጥ፡ዘንድ፡በደልን፡ ይሠራል።
7፤የንፉግም፡ዕቃ፡ክፉ፡ናት፤ችግረኛ፡ቅን፡ነገርን፡በተናገረ፡ጊዜ፡እንኳ፡ርሱ፡በሐሰት፡ቃል፡ድኻውን፡ያጠፋ ፡ዘንድ፡ክፉን፡ዐሳብ፡ያስባል።
8፤ከበርቴ፡ሰው፡ግን፡ለመከበር፡ያስባል፥በመከበርም፡ጸንቶ፡ይኖራል።
9፤እናንተ፡ዓለመኛዎች፡ሴቶች፡ሆይ፥ተነሡ፡ድምፄንም፡ስሙ፤እናንተ፡ተማምናችኹ፡የምትቀመጡ፡ሴቶች፡ልጆች፡ሆ ይ፥ንግግሬን፡አድምጡ።
10፤እናንተ፡ተማምናችኹ፡የምትቀመጡ፡ሴቶች፡ሆይ፥ወይንን፡መቍረጥ፡ይጠፋልና፥ፍሬም፡ማከማቸት፡አይመጣምና፡ ከዓመትና፡ከጥቂት፡ቀን፡በዃላ፡ትንቀጠቀጣላችኹ።
11፤እናንተ፡ዓለመኛዎች፡ሴቶች፡ሆይ፥ተጠንቀቁ፤ተማምናችኹም፡የምትቀመጡ፡ሆይ፥ተንቀጥቀጡ፤ልብሳችኹን፡አው ልቁ፥ዕራቍታችኹን፡ኹኑ፥ወገባችኹንም፡በማቅ፡ታጠቁ።
12፤ስለተወደደችውም፡ዕርሻ፡ስለሚያፈራውም፡ወይን፡ደረታችኹን፡ድቁ።
13፤በሕዝቤ፡ምድር፡ላይ፥በደስታ፡ከተማ፡ባሉት፡በደስታ፡ቤቶች፡ዅሉ፡ላይ፡ሾኽና፡ኵርንችት፡ይወጣባቸዋል፤
14፤አዳራሹ፡ወና፡ትኾናለችና፥የብዙ፡ሰውም፡ከተማ፡ትለቀቃለችና፥ዐምባውና፡ግንቡም፡ለዘለዓለም፡ዋሻ፥የምድ ረ፡በዳም፡አህያ፡ደስታ፥የመንጋዎችም፡ማሰማሪያ፡ይኾናልና።
15፤ይህም፥መንፈስ፡ከላይ፡እስኪፈስ፟ልን፥ምድረ፡በዳውም፡ፍሬያማ፡ዕርሻ፡እስኪኾን፥ፍሬያማውም፡ዕርሻ፡ዱር ፡ተብሎ፡እስኪቈጠር፡ድረስ፡ይኾናል።
16፤ከዚያ፡በዃላ፡ፍርድ፡በምድረ፡በዳ፡ይኖራል፥ጽድቅም፡በፍሬያማው፡ዕርሻ፡ያድራል።
17፤የጽድቅም፡ሥራ፡ሰላም፥የጽድቅም፡ፍሬ፡ለዘለዓለም፡ጸጥታና፡መታመን፡ይኾናል።
18፤ሕዝቤም፡በሰላም፡ማደሪያ፡በታመነም፡ቤት፡በጸጥተኛ፡ማረፊያ፡ይቀመጣል።
19፤በረዶ፡ግን፡በዱር፡ላይ፡ይወርዳል፥ከተማም፡ፈጽማ፡ትዋረዳለች።
20፤እናንተ፡የበሬና፡የአህያ፡እግር፡እየነዳችኹ፡በውሃ፡ዅሉ፡አጠገብ፡የምትዘሩ፡ብፁዓን፡ናችኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33።
1፤አንተ፡ሳትጠፋ፡የምታጠፋ፥ባንተም፡ላይ፡ወንጀል፡ሳይደረግ፡ወንጀል፡የምታደርግ፡ወዮልኽ! ማጥፋትን፡በተውኽ፡ጊዜ፡ትጠፋለኽ፤መወንጀልንም፡በተውኽ፡ጊዜ፡ይወነጅሉኻል።
2፤አቤቱ፥ማረን፤አንተን፡ተማምነናል፤ጧት፡ጧት፡ክንድ፡በመከራም፡ጊዜ፡ማዳን፡ኹነን።
3፤ከፍጅት፡ድምፅ፡ወገኖች፡ሸሹ፥በመነሣትኽም፡አሕዛብ፡ተበተኑ።
4፤አንበጣ፡እንደሚሰበስብ፡ምርኳችኹ፡ትሰበሰባለች፥ኵብኵባም፡እንደሚዘል፟፡ሰዎች፡ይዘሉ፟በታል።
5፤እግዚአብሔር፡በአርያም፡ተቀምጧልና፥ከፍ፡ከፍ፡አለ፤ጽዮንን፡በፍርድና፡በጽድቅ፡ሞላት።
6፤የዘመንኽም፡ጸጥታ፥የመድኀኒት፡ብዛት፥ጥበብና፡ዕውቀት፡ይኾናል፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡መዝገቡ፡ነው።
7፤እንሆ፥ኀይለኛዎቻቸው፡በሜዳ፡ይጮኻሉ፤የሰላም፡መልእክተኛዎች፡መራራ፡ልቅሶ፡ያለቅሳሉ።
8፤መንገዶች፡ባድማ፡ኾኑ፥ተላላፊም፡ቀረ፤ርሱም፡ቃል፡ኪዳንን፡አፈረሰ፡ከተማዎችንም፡ናቀ፡ሰውንም፡አልተመለ ከተም።
9፤ምድሪቱ፡አለቀሰች፡ከሳችም፤ሊባኖስ፡ዐፈረ፡ጠወለገም፤ሳሮን፡እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ኾነ፤ባሳንና፡ቀርሜሎስ፡ ቅጠላቸውን፡አረገፉ።
10፤አኹን፡እነሣለኹ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤አኹን፡እከበራለኹ፤አኹን፡ከፍ፡ከፍ፡እላለኹ።
11፤ገለባን፡ትፀንሳላችኹ፥እብቅንም፡ትወልዳላችኹ፤እስትንፋሳችኹ፡የምትበላችኹ፡እሳት፡ናት።
12፤አሕዛብም፡እንደ፡ተቃጠለ፡ኖራ፥ተቈርጦም፡በእሳት፡እንደ፡ተቃጠለ፡ሾኽ፡ይኾናሉ።
13፤እናንተ፡በሩቅ፡ያላችኹ፡የሠራኹትን፡ስሙ፥እናንተም፡በቅርብ፡ያላችኹ፡ኀይሌን፡ዕወቁ።
14፤በጽዮን፡ያሉ፡ኀጢአተኛዎች፡ፈሩ፤መንቀጥቀጥ፡ዝንጉዎቹን፡ያዘ፤ከምትበላ፡እሳት፡ጋራ፡መኖርን፡የሚችል፡ ከእኛ፡ማን፡አለ፧ለዘለዓለምም፡ከምትነድ፟፡እሳት፡ጋራ፡መኖርን፡የሚችል፡ከእኛ፡ማን፡አለ፧
15፤በጽድቅ፡የሚኼድ፡ቅን፡ነገርንም፡የሚናገር፥በሽንገላ፡የሚገኝ፡ትርፍን፡የሚንቅ፥መማለጃን፡ከመጨበጥ፡እ ጁን፡የሚያራግፍ፥ደም፡ማፍሰስን፡ከመስማት፡ዦሮዎቹን፡የሚያደነቍር፥ክፋትንም፡ከማየት፡ዐይኖቹን፡የሚጨፍን ፡ነው።
16፤ርሱ፡ከፍ፡ባለ፡ስፍራ፡ይቀመጣል፤ጠንካራ፡ዐምባ፡መጠጊያው፡ይኾናል፤እንጀራም፡ይሰጠዋል፥ውሃውም፡የታመ ነች፡ትኾናለች።
17፤ዐይኖችኽ፡ንጉሥን፡በውበቱ፡ያዩታል፤እነርሱም፡በሩቅ፡ያለች፡ምድርን፡ያይዋታል።
18፤ልብኽም፦ጸሓፊ፡ወዴት፡አለ፧መዛኝስ፡ወዴት፡አለ፧ግንቦቹንስ፡የቈጠረ፡ወዴት፡አለ፧ብሎ፡የሚያስፈራ፡ነገ ር፡ያስባል።
19፤ጨካኝን፡ሕዝብ፥ቋንቋው፡ለማስተዋል፡ጥልቅ፡የኾነውንና፡አንደበቱ፡ለማስተዋል፡ጸያፍ፡የኾነውን፡ሕዝብ፥ አታይም።
20፤የበዓላችንን፡ከተማ፡ጽዮንን፡ተመልከት፤ዐይኖችኽ፡የሰላም፡ማደሪያ፥ካስማውም፡ለዘለዓለም፡የማይነቀል፡ አውታሩም፡ዅሉ፡የማይበጠስ፥የማይወገድ፡ድንኳን፡የኾነውን፡ኢየሩሳሌምን፡ያያሉ።
21፤እግዚአብሔር፡በዚያ፡የሰፉ፡ወንዞችና፡የመስኖች፡ስፍራ፡ኾኖ፡ከእኛ፡ጋራ፡በግርማ፡ይኾናል፤የሚቀዘፉ፡መ ርከቦች፡አይገቡባትም፥ታላላቆችም፡መርከቦች፡አያልፉባትም።
22፤እግዚአብሔር፡ፈራጃችን፡ነው፥እግዚአብሔር፡ሕግን፡ሰጪያችን፡ነው፥እግዚአብሔር፡ንጉሣችን፡ነው፤ርሱ፡ያ ድነናል።
23፤ገመዶችኽ፡ላልተዋል፥ደቀላቸውንም፡አላጸኑም፥ሸራውንም፡መዘርጋት፡አልቻሉም።በዚያም፡ጊዜ፡የብዙ፡ምርኮ ፡ብዝበዛ፡ተከፈለ፤ዐንካሳዎች፡እንኳ፡ብዝበዛውን፡በዘበዙ።
24፤በዚያም፡የሚቀመጥ፦ታምሜያለኹ፡አይልም፥በርሷም፡ለሚቀመጡ፡ሰዎች፡በደላቸው፡ይቅር፡ይባልላቸዋል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34።
1፤እናንተ፡አሕዛብ፡ሆይ፥ቅረቡ፥ስሙ፤እናንተ፡ወገኖች፡ሆይ፥አድምጡ፤ምድርና፡መላ፟ዋ፥ዓለምና፡ከርሷ፡የሚወ ጣ፡ዅሉ፡ይስሙ።
2፤የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡መዓቱም፡በሰራዊታቸው፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፤ፈጽሞ፡አጠፋቸው፥ለመታረ ድም፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
3፤ከነርሱም፡የተገደሉት፡ይጣላሉ፥የሬሳቸውም፡ግማት፡ይሸታል፥ተራራዎችም፡ከደማቸው፡የተነሣ፡ይርሳሉ።
4፤የሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ይበሰብሳሉ፥ሰማያትም፡እንደ፡መጽሐፍ፡ጥቅል፟፡ይጠቀለላሉ፥ከወይንና፡ከበለስም፡ ቅጠል፡እንደሚረግፍ፡ሰራዊታቸው፡ዅሉ፡ይረግፋል።
5፤ሰይፌ፡በሰማይ፡ኾና፡እስክትረካ፡ድረስ፡ጠጥታለች፤እንሆ፥በኤዶምያስና፡በረገምኹት፡ሕዝብ፡ላይ፡ለፍርድ፡ ትወርዳለች።
6፤እግዚአብሔር፡መሥዋዕት፡በባሶራ፥ታላቅም፡ዕርድ፡በኤዶምያስ፡ምድር፡አለውና፡የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡በደም ፡ተሞልታለች፥በስብም፥በበግ፡ጠቦትና፡በፍየል፡ደምም፥በአውራም፡በግ፡ኵላሊት፡ስብ፡ወፍራለች።
7፤ጐሽ፡ከነርሱ፡ጋራ፥ወይፈኖችም፡ከኰርማዎች፡ጋራ፡ይወድቃሉ፤ምድራቸውም፡በደም፡ትረካለች፥ዐፈራቸውም፡በስ ብ፡ትወፍራለች።
8፤የእግዚአብሔር፡የበቀሉ፡ቀን፥ስለጽዮንም፡ክርክር፡የብድራት፡ዓመት፡ነው።
9፤የኤዶምያስም፡ፈሳሾች፡ዝፍት፡ኾነው፡ይለወጣሉ፥ዐፈሯም፡ዲን፡ይኾናል፥መሬቷም፡የሚቃጠል፡ዝፍት፡ትኾናለች ።
10፤በሌሊትና፡በቀንም፡አትጠፋም፥ጢሷም፡ለዘለዓለም፡ይወጣል፤ከትውልድ፡እስከ፡ትውልድም፡ድረስ፡ባድማ፡ኾና ፡ትኖራለች፤ለዘለዓለም፡ዓለም፡ማንም፡አያልፍባትም።
11፤ጭልፊትና፡ዣርት፡ግን፡ይወርሷታል፤ጕጕትና፡ቍራም፡ይኖሩባታል፤በላይዋም፡የመፍረስ፡ገመድና፡የባዶነት፡ ቱንቢ፡ይዘረጋባታል።
12፤መሳፍንቷን፡ወደ፡መንግሥት፡ይጠራሉ፥ነገር፡ግን፥ማንም፡አይገኝባትም፤አለቃዎቿም፡ዅሉ፡ምናምኖች፡ይኾና ሉ።
13፤በአዳራሾቿም፡ሾኽ፡በቅጥሮቿም፡ሳማን፡አሜከላ፡ይበቅሉባታል፤የቀበሮም፡ማደሪያና፡የሰጐን፡ስፍራ፡ትኾና ለች።
14፤የምድረ፡በዳም፡አራዊት፡ከተኵላዎች፡ጋራ፡ይገናኛሉ፥አጋንንትም፡ርስ፡በርሳቸው፡ይጠራራሉ፤ጅንም፡በዚያ ፡ትኖራለች፥ለርሷም፡ማረፊያ፡ታገኛለች።
15፤በዚያም፡ዋሊያ፡ቤቷን፡ትሠራለች፡ዕንቍላልም፡ትጥላለች፡ትቀፈቅፈውማለች፡ልጆቿንም፡በጥላዋ፡ትሰበስባለ ች፤በዚያም፡ደግሞ፡አሞራዎች፡እያንዳንዳቸው፡ከባልንጀራዎቻቸው፡ጋራ፡ይሰበሰባሉ።
16፤በእግዚአብሔር፡መጽሐፍ፡ፈልጉ፥አንቡ፟ም፤አፌ፡አዟ፟ልና፥መንፈሱም፡ሰብስቧቸዋልና፥ከነዚህ፡አንዲት፡አ ትጠፋም፥ባልንጀራውንም፡የሚያጣ፡የለም።
17፤ርሱም፡ዕጣ፡ጣለባቸው፥እጁም፡በገመድ፡ከፈለችላቸው፤ለዘለዓለም፡ይገዟታል፥ከትውልድም፡እስከ፡ትውልድ፡ ድረስ፡ይቀመጡባታል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35።
1፤ምድረ፡በዳውና፡ደረቁ፡ምድር፡ደስ፡ይላቸዋል፥በረሓውም፡ሐሤት፡ያደርጋል፡እንደ፡ጽጌ፡ረዳም፡ያብባል።
2፤እጅግ፡ያብባል፡በደስታና፡በዝማሬ፡ሐሤትን፡ያደርጋል፤የሊባኖስ፡ክብር፥የቀርሜሎስና፡የሳሮን፡ግርማ፡ይሰ ጠዋል፤የእግዚአብሔርንም፡ክብር፡የአምላካችንንም፡ግርማ፡ያያሉ።
3፤የደከሙትን፡እጆች፡አበርቱ፥የላሉትንም፡ጕልበቶች፡አጽኑ።
4፤ፈሪ፡ልብ፡ላላቸው፦እንሆ፥አምላካችኹ፡በበቀል፡በእግዚአብሔርም፡ብድራት፡ይመጣልና፥መጥቶም፡ያድናችዃልና ፥በርቱ፥አትፍሩ፡በሏቸው።
5፤በዚያን፡ጊዜም፡የዕውሮች፡ዐይን፡ይገለጣል፤የደንቈሮዎችም፡ዦሮ፡ይከፈታል።
6፤በዚያን፡ጊዜ፡ዐንካሳ፡እንደ፡ሚዳቋ፡ይዘላ፟ል፥የድዳም፡ምላስ፡ይዘምራል፤በምድረ፡በዳ፡ውሃ፥በበረሓም፡ፈ ሳሽ፡ይፈልቃልና።
7፤ደረቂቱ፡ምድር፡ኵሬ፥የጥማት፡መሬት፡የውሃ፡ምንጭ፡ትኾናለች፤ቀበሮ፡የተኛበት፡መኖሪያ፡ልምላሜና፡ሸምበቆ ፡ደንገልም፡ይኾንበታል።
8፤በዚያም፡ጐዳናና፡መንገድ፡ይኾናል፡ርሱም፡የተቀደሰ፡መንገድ፡ይባላል፤ንጹሓንም፡ያልኾኑ፡አያልፉበትም፥ለ ንጹሓን፡ግን፡ይኾናል፤ተላላፊዎችና፡ሰነፎች፡እንኳ፡አይስቱበትም።
9፤አንበሳም፡አይኖርበትም፥ነጣቂ፡አውሬም፡አይወጣበትም፥ከዚያም፡አይገኙም፤የዳኑት፡ግን፡በዚያ፡ይኼዳሉ፤
10፤እግዚአብሔርም፡የተቤዣቸው፡ይመለሳሉ፡እየዘመሩም፡ወደ፡ጽዮን፡ይመጣሉ፤የዘለዓለም፡ደስታ፡በራሳቸው፡ላ ይ፡ይኾናል፤ሐሤትንና፡ደስታን፡ያገኛሉ፥ሐዘንና፡ትካዜም፡ይሸሻሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በንጉሡ፡በሕዝቅያስ፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ዓመት፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ወደ፡ይሁዳ፡ወደ ተመሸጉት፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወጥቶ፡ወሰዳቸው።
2፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ራፋስቂስን፡ከብዙ፡ሰራዊት፡ጋራ፡ከለኪሶ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ ላከ፥ርሱም፡በዐጣቢው፡ዕርሻ፡መንገድ፡ባለችው፡በላይኛዪቱ፡ኵሬ፡መስኖ፡አጠገብ፡ቆመ።
3፤የቤቱም፡አዛዥ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ጸሓፊውም፡ሳምናስ፡ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፡ወደ፡ ርሱ፡ወጡ።
4፤ራፋስቂስም፡አላቸው፦ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ታላቁ፡የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡የ ምትታመንበት፡መተማመኛ፡ምንድር፡ነው፧
5፤እኔ፦ለሰልፍ፡የኾነው፡ምክርኽና፡ኀያልኽ፡ከንቱ፡ነገር፡ነው፡አልኹ፤አኹንም፡በእኔ፡ላይ፡ያመፅኸው፡በማን ፡ተማምነኽ፡ነው፧
6፤እንሆ፥በዚህ፡በተቀጠቀጠ፡በሸምበቆ፡በትር፡በግብጽ፡ትታመናለኽ፤ሰው፡ቢመረኰዘው፡ተሰብሮ፡በእጁ፡ይገባል ፥ያቈስለውማል፤የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ለሚታመኑበት፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው።
7፤አንተም፦በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡እንታመናለን፡ብትለኝ፥ሕዝቅያስ፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፦በዚህ፡መ ሠዊያ፡ፊት፡ስገዱ፡ብሎ፡የኰረብታ፡መስገጃዎቹንና፡መሠዊያዎቹን፡ይስፈረሰ፡ይህ፡አይደለምን፧
8፤አኹን፡እንግዲህ፡ከጌታዬ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ጋራ፡ተወራረድ፥የሚቀመጡባቸውንም፡ሰዎች፡ማግኘት፡ቢቻልኽ፡እኔ ፡ኹለት፡ሺሕ፡ፈረሶች፡እሰጥኻለኹ።
9፤ስለ፡ሠረገላዎችና፡ስለ፡ፈረሰኛዎች፡በግብጽ፡ስትታመን፥ከጌታዬ፡ባሪያዎች፡የሚያንሰውን፡የአንዱን፡አለቃ ፡ፊት፡ትቃወም፡ዘንድ፡እንዴት፡ይቻልኻል፧
10፤አኹንም፡በእውኑ፡ያለእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ይህን፡አገር፡አጠፋ፡ዘንድ፡ወጥቻለኹን፧እግዚአብሔር፦ወደዚ ህ፡አገር፡ወጥተኽ፡አጥፋው፡አለኝ።
11፤ኤልያቄምና፡ሳምናስ፡ዮአስም፡ራፋስቂስን፦እኛ፡እንሰማለንና፡እባክኽ፥በሶርያ፡ቋንቋ፡ለባሪያዎችኽ፡ተና ገር፤በቅጥርም፡ላይ፡ባለው፡ሕዝብ፡ዦሮ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡አትናገረን፡አሉት።
12፤ራፋስቂስ፡ግን፦ጌታዬ፡ይህን፡ቃል፡እናገር፡ዘንድ፡ወዳንተና፡ወደ፡ጌታኽ፡ልኮኛልን፧ከእናንተ፡ጋራ፡ኵሳ ቸውን፡ይበሉ፡ዘንድ፡ሽንታቸውንም፡ይጠጡ፡ዘንድ፡በቅጥር፡ላይ፡ወደተቀመጡት፡ሰዎች፡አይደለምን፧አላቸው።
13፤ራፋስቂስም፡ቆሞ፡በታላቅ፡ድምፅ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡እንዲህ፡ብሎ፡ጮኸ።የታላቁን፡የአሶርን፡ንጉሥ፡ቃል፡ ስሙ።
14፤ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦ያድናችኹ፡ዘንድ፡አይችልምና፡ሕዝቅያስ፡አያታላ፟ችኹ፤
15፤ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡በርግጥ፡ያድነናል፡ይህችም፡ከተማ፡በአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አትሰጥም፡ብሎ፡በእግ ዚአብሔር፡እንድትታመኑ፡አያድርጋችኹ።
16፤ሕዝቅያስንም፡አትስሙ፤የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ከእኔ፡ጋራ፡ታረቁ፡ወደ፡እኔም፡ውጡ፤እያንዳንዳች ኹም፡ከወይናችኹና፡ከበለሳችኹ፡ብሉ፥ከጕድጓዳችኹም፡ውሃ፡ጠጡ፤
17፤ይህም፡መጥቼ፡ምድራችኹን፡ወደምትመስለው፡ምድር፥እኽልና፡የወይን፡ጠጅ፥እንጀራና፡ወይን፡ወዳለበት፡ምድ ር፡እስካፈልሳችኹ፡ድረስ፡ነው።
18፤ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡ያድነናል፡ብሎ፡እንዳያታልላችኹ፡ተጠንቀቁ።በእውኑ፡የአሕዛብ፡አማልክት፡አገ ሮቻቸውን፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አድነዋቸዋልን፧
19፤የሐማትና፡የአርፋድ፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧የሴፈርዋይም፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧ሰማርያን፡ከእጄ፡አድነ ዋታልን፧
20፤እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ከእጄ፡ያድን፡ዘንድ፡ከነዚህ፡አገሮች፡አማልክት፡ዅሉ፡አገሩን፡ከእጄ፡ያዳነ ፡ማን፡ነው፧
21፤እነርሱም፡ዝም፡አሉ፥አንዳችም፡አልመለሱለትም፤ንጉሡ፡እንዳይመልሱለት፡አዞ፟፡ነበርና።
22፤የቤቱ፡አዛዥ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ጸሓፊውም፡ሳምናስ፡ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፡ልብሳ ቸውን፡ቀደ፟ው፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጡ፥የራፋስቂስንም፡ቃል፡ነገሩት።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡37።______________
ምዕራፍ፡37።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ንጉሡ፡ሕዝቅያስ፡ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀደደ፥ማቅም፡ለበሰ፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት ፡ገባ።
2፤የቤቱንም፡አዛዥ፡ኤልያቄምን፡ጸሓፊውንም፡ሳምናስን፡የካህናቱንም፡ሽማግሌዎች፡ማቅ፡ለብሰው፡ወደ፡ነቢዩ፡ ወደዓሞጽ፡ልጅ፡ወደ፡ኢሳይያስ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ላካቸው።
3፤እነርሱም፦ሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ቀን፡የመከራና፡የተግሣጽ፡የዘለፋም፡ቀን፡ነው፤ልጆች፡የሚወለዱ በት፡ጊዜ፡ደርሷል፡ለመውለድም፡ኀይል፡የለም።
4፤ምናልባት፡በሕያው፡አምላክ፡ላይ፡ይገዳደር፡ዘንድ፡ጌታው፡የአሶር፡ንጉሥ፡የላከውን፡የራፋስቂስን፡ቃል፡አ ምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ይሰማ፡እንደ፡ኾነ፥አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ስለሰማው፡ቃል፡ይገሥጸው፡እንደ፡ኾነ፥ስ ለዚህ፡ለቀረው፡ቅሬታ፡ጸልይ፡አሉት።
5፤እንዲሁ፡የንጉሡ፡የሕዝቅያስ፡ባሪያዎች፡ወደ፡ኢሳይያስ፡መጡ።
6፤ኢሳይያስም፦ለጌታችኹ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሶር፡ንጉሥ፡ባሪያዎች፡ስለ፡ሰደቡኝ፥ስለሰማኸው፡ ቃል፡አትፍራ።
7፤እንሆ፥በላዩ፡መንፈስን፡እሰዳ፟ለኹ፥ወሬንም፡ይሰማል፥ወደ፡ምድሩም፡ይመለሳል፤በምድሩም፡በሰይፍ፡እንዲወ ድቅ፡አደርጋለኹ፡በሉት፡አላቸው።
8፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ከለኪሶ፡እንደ፡ራቀ፡ሰምቶ፡ነበርና፥ራፋስቂስ፡ተመልሶ፡በልብና፡ሲዋጋ፡አገኘው።
9፤ርሱም፦የኢትዮጵያ፡ንጉሥ፡ቲርሐቅ፡ሊዋጋኽ፡መጥቷል፡የሚል፡ወሬ፡ሰማ።በሰማም፡ጊዜ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መልእ ክተኛዎችን፡ላከ፥
10፤እንዲህ፡ሲል፦ለይሁዳ፡ንጉሠ፡ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ኢየሩሳሌም፡በአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አ ትሰጥም፡ብሎ፡የምትታመንበት፡አምላክኽ፡አያታል፟ኽ።
11፤እንሆ፥የአሶር፡ነገሥታት፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ያደረጉትን፥እንዴትስ፡እንዳጠፏቸው፡ሰምተኻል፤አንተስ፡ት ድናለኽን፧
12፤አባቶቼ፡ያጠፏቸውን፡ጎዛንን፥ካራንን፥ራፊስን፥በተላሳር፡የነበሩትንም፡የዔዴንን፡ልጆች፡የአሕዛብ፡አማ ልክት፡አዳኗቸውን፧
13፤የሐማት፡ንጉሥ፥የአርፋድ፡ንጉሥ፥የሴፈርዋይም፡ከተማ፡ንጉሥ፥የሄናና፡የዒዋ፡ንጉሥ፡ወዴት፡አሉ፧
14፤ሕዝቅያስም፡ደብዳቤውን፡ከመልእክተኛዎች፡እጅ፡ተቀብሎ፡አነበበው፤ሕዝቅያስም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወ ጥቶ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዘረጋው።
15፤ሕዝቅያስም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ጸለየ።
16፤አቤቱ፥በኪሩቤል፡ላይ፡የምትቀመጥ፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡ብቻኽን፡የምድር፡መ ንግሥታት፡ዅሉ፡አምላክ፡ነኽ፤ሰማይንና፡ምድርን፡ፈጥረኻል።
17፤አቤቱ፥ዦሮኽን፡አዘንብልና፡ስማ፤አቤቱ፥ዐይንኽን፡ክፈትና፡እይ፤በሕያው፡አምላክ፡ላይ፡ይገዳደር፡ዘንድ ፡የላከውን፡የሰናክሬም፡ቃል፡ስማ።
18፤አቤቱ፥በእውነት፡የአሶር፡ነገሥታት፡ዓለሙን፡ዅሉ፡አገሮቻቸውንም፡አፍርሰዋል፥
19፤አማልክታቸውንም፡በእሳት፡ላይ፡ጥለዋል፤የዕንጨትና፡የድንጋይ፡የሰው፡እጅ፡ሥራ፡ነበሩ፡እንጂ፡አማልክት ፡አልነበሩምና፡ስለዚህ፡አጥፍተዋቸዋል።
20፤እንግዲህም፡አምላካችን፡አቤቱ፥የምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡አንተ፡ብቻ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኽ፡ያውቁ ፡ዘንድ፡ከእጁ፡አድነን።
21፤የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡እንዲህ፡ብሎ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ላከ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ስለአሶር፡ንጉሥ፡ስለ፡ሰናክሬም፡ወደ፡እኔ፡ለምነኻልና፥
22፤እግዚአብሔር፡ስለ፡ርሱ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦ድንግሊቱ፡የጽዮን፡ልጅ፡ቀላል፡አድርጋኻለች፥በንቀ ትም፡ሥቃብኻለች፤የኢየሩሳሌም፡ልጅ፡ራሷን፡ነቅንቃብኻለች።
23፤የተገዳደርኸው፡የሰደብኸውስ፡ማን፡ነው፧ቃልኽንስ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደረግኽበት፡ዐይንኽንስ፡ወደ፡ላይ፡ያነሣ ኽበት፡ማን፡ነው፧በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡ነው።
24፤አንተም፦በሠረገላዬ፡ብዛት፡ወደተራራዎች፡ከፍታ፥ወደሊባኖስ፡ጥግ፡ላይ፡ወጥቻለኹ፤ረዣዥሞቹንም፡ዝግባዎ ች፡የተመረጡትንም፡ጥዶች፡እቈርጣለኹ፥ወደከፍታውም፡ዳርቻ፡ወደቀርሜሎስ፡ዱር፡እገባለኹ።
25፤ቈፈርኹም፡ውሃም፡ጠጣኹ፡የግብጽንም፡ወንዞች፡ዅሉ፡በእግሬ፡ጫማ፡አደርቃለኹ፡ብለኽ፡በባሪያዎችኽ፡እጅ፡ በጌታ፡ላይ፡ተገዳደርኽ።
26፤እኔ፡ጥንቱን፡እንደ፡ሠራኹት፥ቀድሞውንም፡እንዳደረግኹት፡አልሰማኽምን፧አኹንም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች ፡የፍርስራሽ፡ክምር፡እስኪኾኑ፡ድረስ፡እንድታፈርስ፡አደረግኹኽ።
27፤ስለዚህ፥የሚኖሩባቸው፡ሰዎች፡እጃቸው፡ዝሏል፥ደንግጠውም፡ታውከዋል፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ሣር፥እንደ፡ለመ ለመም፡ቡቃያ፥በሰገነትም፡ላይ፡እንዳለ፡ሣር፥ሳይሸት፡ዋግ፡እንደ፡መታው፡እኽል፡ኾነዋል።
28፤እኔ፡ግን፡መቀመጫኽንና፡መውጫኽን፡መግቢያኽንም፡በእኔም፡ላይ፡የተቈጣኸውን፡ቍጣ፡ዐውቄያለኹ።
29፤ቍጣኽና፡ትዕቢትኽ፡ወደ፡ዦሮዬ፡ደርሷልና፥ስለዚህ፡ስናጋዬን፡በአፍንጫኽ፡ልጓሜንም፡በከንፈርኽ፡አደርጋ ለኹ፥በመጣኽበትም፡መንገድ፡እመልስኻለኹ።
30፤ይህም፡ምልክት፡ይኾንኻል፤በዚህ፡ዓመት፡የገቦውን፥በኹለተኛውም፡ዓመት፡ከገቦው፡የበቀለውን፡ትበላላችኹ ፤በሦስተኛውም፡ዓመት፡ትዘራላችኹ፡ታጭዱማላችኹ፥ወይንም፡ትተክላላችኹ፡ፍሬውንም፡ትበላላችኹ።
31፤ያመለጠው፡የይሁዳ፡ቤት፡ቅሬታ፡ሥሩን፡ወደ፡ታች፡ይሰዳ፟ል፥ወደ፡ላይም፡ያፈራል።
32፤ከኢየሩሳሌም፡ቅሬታ፡ከጽዮንም፡ተራራ፡ያመለጡት፡ይወጣሉና፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቅንአት፡ይህ ን፡ያደርጋል።
33፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡ስለአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ወደዚች፡ከተማ፡አይመጣም፥ፍላጻንም፡አይወረው ርባትም፥በጋሻም፡አይመጣባትም፥የዐፈርንም፡ድልድል፡አይደለድልባትም።
34፤በመጣበት፡መንገድ፡በዚያው፡ይመለሳል፥ወደዚችም፡ከተማ፡አይመጣም፡ይላል፡እግዚአብሔር።
35፤ስለ፡እኔም፡ስለ፡ባሪያዬም፡ስለ፡ዳዊት፡ይህችን፡ከተማ፡አድናት፡ዘንድ፡እጋርዳታለኹ።
36፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ወጣ፥ከአሶራውያንም፡ሰፈር፡መቶ፡ሰማንያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ገደለ፤ማለዳም፡በተነ ሡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ዅሉ፡በድኖች፡ነበሩ።
37፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ተነሥቶ፡ኼደ፥ተመልሶም፡በነነዌ፡ተቀመጠ።
38፤በአምላኩም፡በናሳራክ፡ቤት፡ሲሰግድ፡ልጆቹ፡አድራሜሌክና፡ሳራሳር፡በሰይፍ፡ገደሉት፤ወደአራራትም፡አገር ፡ኰበለሉ።ልጁም፡አስራዶን፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡38።______________
ምዕራፍ፡38።
1፤በዚያም፡ወራት፡ሕዝቅያስ፡ለሞት፡እስኪደርስ፡ታመመ።ነቢዩም፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ርሱ፡መጥቶ፦እ ግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትሞታለኽ፡እንጂ፡በሕይወት፡አትኖርምና፡ቤትኽን፡አስተካክል፡አለው።
2፤ሕዝቅያስም፡ፊቱን፡ወደ፡ግድግዳው፡መልሶ፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ፦
3፤አቤቱ፥በፊትኽ፡በእውነትና፡በፍጹም፡ልብ፡እንደ፡ኼድኹ፡ደስ፡የሚያሠኝኽንም፡እንዳደረግኹ፡ታስብ፡ዘንድ፡ እለምንኻለኹ።ሕዝቅያስም፡እጅግ፡አድርጎ፡አለቀሰ።
4፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኢሳይያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
5፤ኺድ፥ሕዝቅያስን፡እንዲህ፡በለው፦የአባትኽ፡የዳዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጸሎትኽን፡ሰም ቻለኹ፥እንባኽንም፡አይቻለኹ፤እንሆ፥በዕድሜኽ፡ላይ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡እጨምራለኹ።
6፤አንተንና፡ይህችንም፡ከተማ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡እታደጋለኹ፥ይህችንም፡ከተማ፡እጋርዳታለኹ።
7፤እግዚአብሔርም፡የተገረውን፡ነገር፡እንዲፈጽመው፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምልክቱ፡ይህ፡ይኾንልኻል።
8፤እንሆ፥በአካዝ፡የጥላ፡ስፍረ፡ሰዓት፡ላይ፡ከፀሓይ፡ጋራ፡የወረደውን፡በደረጃዎች፡ያለውን፡ጥላ፡ዐሥር፡ደረ ጃ፡ወደ፡ዃላ፡እንዲመለስ፡አደርጋለኹ።ፀሓይም፡በጥላ፡ስፍረ፡ሰዓት፡ላይ፡የወረደበት፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ዃ ላ፡ተመለሰ።
9፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፡ታሞ፟፡ከደዌው፡በተፈወሰ፡ጊዜ፡የጻፈው፡ጽሕፈት፡ይህ፡ነው፦
10፤እኔ፦በሕይወት፡ዘመኔ፡መካከል፡ወደሲኦል፡በሮች፡እገባለኹ፤የቀረው፡ዘመኔ፡ጐደለብኝ፡አልኹ።
11፤ደግሞም፦በሕያዋን፡ምድር፡እግዚአብሔርን፡አላይም፤በዓለምም፡ከሚኖሩ፡ጋራ፡ሰውን፡እንግዲህ፡አልመለከት ም፡አልኹ።
12፤ማደሪያዬ፡ተነቀለች፥እንደ፡እረኛ፡ድንኳንም፡ከእኔ፡ዘንድ፡ተወገደች፤ሕይወቴንም፡እንደ፡ሸማኔ፡ጠቀለል ኹ፥ርሱም፡ከመጠቅለያው፡ይቈርጠኛል፤ከማለዳም፡ዠምሮ፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡ታጠፋኛለኽ።
13፤እስኪነጋ፡ድረስ፡ቈይቼ፡ነበር፤ርሱ፡እንደ፡አንበሳ፡ዐጥንቴን፡ዅሉ፡ሰበረ፤ከማለዳ፡ዠምሮ፡እስከ፡ማታ፡ ድረስ፡ታጠፋኛለኽ።
14፤እንደ፡ጨረባና፡እንደ፡ሽመላ፡ተንጫጫኹ፥እንደ፡ርግብም፡አጕረመረምኹ፤ዐይኖቼ፡ወደ፡ላይ፡ከማየት፡ደከሙ ፦ጌታ፡ሆይ፥ተጨንቄያለኹና፡መከታ፡ኹነኝ።
15፤ምን፡እላለኹ፧ርሱ፡ተናግሮኛል፥ርሱ፡ራሱም፡ይህን፡አድርጓል፤በዘመኔ፡ዅሉ፡ስለነፍሴ፡ምሬት፡ቀስ፡ብዬ፡ እኼዳለኹ።
16፤ጌታ፡ሆይ፥በዚህ፡ነገር፡ሰዎች፡በሕይወት፡ይኖራሉ፥በዚህም፡ዅሉ፡የመንፈሴ፡ሕይወት፡ነው፤አንተም፡ፈወስ ኸኝ፡ወደ፡ሕይወትም፡መለስኸኝ።
17፤እንሆ፥ታላቅ፡ምሬት፡ለደኅንነቴ፡ኾነ፤አንተም፡ነፍሴን፡ከጥፋት፡ጕድጓድ፡አዳንኻት፥ኀጢአቴንም፡ዅሉ፡ወ ደ፡ዃላኽ፡ጣልኽ።
18፤ሲኦል፡አያመሰግንኽምና፥ሞትም፡አያከብርኽምና፤ወደ፡ጕድጓዱ፡የሚወርዱ፡እውነትኽን፡ተስፋ፡አያደርጉም።
19፤እኔ፡ዛሬ፡እንደማደርግ፡ሕያዋን፡እነርሱ፡ያመሰግኑኻል፤አባት፡ለልጆች፡እውነትኽን፡ያስታውቃል።
20፤እግዚአብሔር፡ያድነኛል፤ስለዚህ፥በዕድሜያችን፡ዘመን፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ቅኔዎችን፡አውታር፡ባለ ው፡ዕቃ፡እንዘምራለን።
21፤ኢሳይያስም፦የበለስ፡ጥፍጥፍ፡አምጥተው፡በዕባጩ፡ላይ፡ይለብጡት፥ርሱም፡ይፈወሳል፡ብሎ፡ነበር።
22፤ሕዝቅያስም፦ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እወጣ፡ዘንድ፡ምልክቱ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ነበር።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡39።______________
ምዕራፍ፡39።
1፤በዚያም፡ወራት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የባልዳን፡ልጅ፡መሮዳክ፡ባልዳን፡ሕዝቅያስ፡ታሞ፟፡እንደ፡ተፈወሰ፡ሰምቶ ፡ነበርና፥ደብዳቤና፡እጅ፡መንሻ፡ላከለት።
2፤ሕዝቅያስም፡ደስ፡አለው፥ግምጃ፡ቤቱንም፥ብሩንና፡ወርቁንም፥ቅመሙንና፡የከበረውንም፡ዘይት፥መሣሪያም፡ያለ በትን፡ቤት፡ዅሉ፥በቤተ፡መዛግብቱም፡የተገኘውን፡ዅሉ፡አሳያቸው፤በቤቱና፡በግዛቱ፡ዅሉ፡ካለው፡ሕዝቅያስ፡ያ ላሳያቸው፡የለም።
3፤ነቢዩም፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጥቶ፦እነዚህ፡ሰዎች፡ምን፡አሉ፧ከወዴትስ፡መጡልኽ፧አለው ።ሕዝቅያስም፦ከሩቅ፡አገር፡ከባቢሎን፡መጡልኝ፡አለው።
4፤ርሱም፦በቤትኽ፡ያዩት፡ምንድር፡ነው፧አለው፤ሕዝቅያስም፦በቤቴ፡ያለውን፡ዅሉ፡አይተዋል፤በቤተ፡መዛግብቴ፡ ካለው፡ያላሳየዃቸው፡የለም፡አለው።
5፤ኢሳይያስም፡ሕዝቅያስን፦የሰራዊትን፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ።
6፤እንሆ፥በቤትኽ፡ያለው፡ዅሉ፥አባቶችኽም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያከማቹት፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡የሚፈልስበት፡ወ ራት፡ይመጣል፤ምንም፡አይቀርም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
7፤ከአንተም፡ከሚወጡት፡ከምትወልዳቸው፡ልጆችኽ፡ማርከው፡ይወስዳሉ፤በባቢሎንም፡ንጉሥ፡ቤት፡ውስጥ፡ጃን፡ደረ ባዎች፡ይኾናሉ፡አለው።
8፤ሕዝቅያስም፡ኢሳይያስን፦የተናገርኸው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መልካም፡ነው፡አለው።ደግሞም፦በዘመኔ፡ሰላምና ፡እውነት፡ይኹን፡አለ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡40።______________
ምዕራፍ፡40።
1፤አጽናኑ፥ሕዝቤን፡አጽናኑ፡ይላል፡አምላካችኹ።
2፤ለኢየሩሳሌም፡ልብ፡ተናገሩ፡የተቀጠረችበት፡ወራት፡እንደ፡ተፈጸመ፥ኀጢአቷም፡እንደ፡ተሰረየ፥ከእግዚአብሔ ርም፡እጅ፡ስለ፡ኀጢአቷ፡ዅሉ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡እንደ፡ተቀበለች፡ወደ፡ርሷ፡ጩኹ።
3፤የዐዋጅ፡ነጋሪ፡ቃል።የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡በምድረ፡በዳ፡ጥረጉ፥ለአምላካችንም፡ጐዳና፡በበረሓ፡አስተ ካከሉ።
4፤ሸለቆው፡ዅሉ፡ከፍ፡ይላል፥ተራራውና፡ኰረብታውም፡ዅሉ፡ዝቅ፡ይላል፤ጠማማውም፡ይቃናል፥ስርጓጕጡም፡ሜዳ፡ይ ኾናል፤
5፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ይገለጣል፥ሥጋ፡ለባሹም፡ዅሉ፡በአንድነት፡ያየዋል፥የእግዚአብሔር፡አፍ፡ይህን፡ተ ናግሯልና።
6፤ጩኽ፡የሚል፡ሰው፡ቃል፤ምን፡ብዬ፡ልጩኽ፧አልኹ።ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ሣር፡ነው፥ክብሩም፡ዅሉ፡እንደ፡ምድረ፡በ ዳ፡አበባ፡ነው።
7፤የእግዚአብሔር፡እስትንፋስ፡ይነፍስበታልና፥ሣሩ፡ይደርቃል፡አበባውም፡ይረግፋል፤በእውነት፡ሕዝቡ፡ሣር፡ነ ው።
8፤ሣሩ፡ይደርቃል፡አበባውም፡ይረግፋል፥የአምላካችን፡ቃል፡ግን፡ለዘለዓለም፡ጸንታ፡ትኖራለች።
9፤የምሥራች፡የምትነግሪ፡ጽዮን፡ሆይ፥ከፍ፡ወዳለው፡ተራራ፡ውጪ፡የምሥራች፡የምትነግሪ፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ድም ፅሽን፡በኀይል፡አንሺ፤አንሺ፥አትፍሪ፤ለይሁዳም፡ከተማዎች፦እንሆ፥አምላካችኹ! ብለሽ፡ንገሪ።
10፤እንሆ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኀያል፡ይመጣል፡ክንዱም፡ስለ፡ርሱ፡ይገዛል፤እንሆ፥ዋጋው፡ከርሱ፡ጋራ፡ ደመ፡ወዙም፡በፊቱ፡ነው።
11፤መንጋውን፡እንደ፡እረኛ፡ያሰማራል፥ጠቦቶቹን፡በክንዱ፡ሰብስቦ፡በብብቱ፡ይሸከማል፥የሚያጠቡትንም፡በቀስ ታ፡ይመራል።
12፤ውሃዎችን፡በዕፍኙ፡የሰፈረ፥ሰማይንም፡በስንዝር፡የለካ፥የምድርንም፡ዐፈር፡በመስፈሪያ፡ሰብስቦ፡የያዘ፥ ተራራዎችን፡በሚዛን፡ኰረብታዎችንም፡በሚዛኖች፡የመዘነ፡ማን፡ነው፧
13፤የእግዚአብሔርን፡መንፈስ፡ያዘዘ፥ወይስ፡አማካሪ፡ኾኖ፡ያስተማረው፡ማን፡ነው፧
14፤ወይስ፡ከማን፡ጋራ፡ተመካከረ፧ወይስ፡ማን፡መከረው፧የፍርድንም፡መንገድ፡ማን፡አስተማረው፧ዕውቀትንስ፡ማ ን፡አስተማረው፧የማስተዋልንስ፡መንገድ፡ማን፡አሳየው፧
15፤እንሆ፥አሕዛብ፡በገንቦ፡እንዳለች፡ጠብታ፡ናቸው፥በሚዛንም፡እንዳለ፡ትንሽ፡ትቢያ፡ተቈጥረዋል፤እንሆ፥ደ ሴቶችን፡እንደ፡ቀላል፡ነገር፡ያነሣል።
16፤ሊባኖስ፡ለማንደጃ፡እንስሳዎቿም፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አይበቁም።
17፤አሕዛብ፡ዅሉ፡በፊቱ፡እንዳልነበሩ፡ናቸው፤ከምናምን፡እንደሚያንሱ፥እንደ፡ከንቱ፡ነገርም፡ይቈጥራቸዋል።
18፤እንግዲህ፡እግዚአብሔርን፡በማን፡ትመስሉታላችኹ፧ወይስ፡በምን፡ምሳሌ፡ታስተያዩታላችኹ፧
19፤የተቀረጸውንስ፡ምስል፡ሠራተኛ፡ሠርቶታል፥አንጥረኛም፡በወርቅ፡ለብጦታል፥የብሩንም፡ሰንሰለት፡አፍሶ፟ለ ታል።
20፤ለዚህ፡መባዕ፡ገንዘቡ፡ያልበቃው፡ድኻ፡የማይነቅዘውን፡ዕንጨት፡ይመርጣል፤ምስሉም፡እንዳይናወጥ፡ያቆመው ፡ዘንድ፡ብልኅ፡ሠራተኛን፡ይፈልጋል።
21፤አላወቃችኹምን፧ወይስ፡አልሰማችኹምን፧ከጥንትስ፡አልተወራላችኹምን፧ወይስ፡ምድር፡ከተመሠረተች፡ዠምሮ፡ አላስተዋላችኹምን፧
22፤ርሱ፡በምድር፡ክበብ፡ላይ፡ይቀምጣል፥በርሷም፡የሚኖሩት፡እንደ፡አንበጣ፡ናቸው፤ሰማያትን፡እንደ፡መጋረጃ ፡የሚዘረጋቸው፡እንደ፡ድንኳንም፡ለመኖሪያ፡የሚዘረጋቸው፥
23፤አለቃዎችንም፡እንዳልነበሩ፥የምድርንም፡ፈራጆች፡እንደ፡ከንቱ፡ነገር፡የሚያደርጋቸው፡ርሱ፡ነው።
24፤ገና፡እንደ፡ተተከሉና፡እንደ፡ተዘሩ፥በምድርም፡ሥር፡ገና፡እንደ፡ሰደዱ፡ወዲያውኑ፡ነፈሰባቸው፥እነርሱም ፡ደረቁ፥ዐውሎ፡ነፋስም፡እንደ፡እብቅ፡ጠረጋቸው።
25፤እንግዲህ፡እተካከለው፡ዘንድ፡በማን፡መሰላችኹኝ፧ይላል፡ቅዱሱ።
26፤ዐይናችኹን፡ወደ፡ላይ፡አንሥታችኹ፡ተመልከቱ፤እነዚህን፡የፈጠረ፡ማን፡ነው፧ሰራዊታቸውን፡በቍጥር፡የሚያ ወጣ፡ርሱ፡ነው፥ዅሉንም፡በየስማቸው፡ይጠራቸዋል፤በኀይሉ፡ብዛትና፡በችሎቱ፡ብርታት፡አንድስ፡እንኳ፡አይታጣ ውም።
27፤ያዕቆብ፡ሆይ፥እስራኤልም፡ሆይ፦መንገዴ፡ከእግዚአብሔር፡ተሰውራለች፡ፍርዴም፡ከአምላኬ፡ዐልፋለች፡ለምን ፡ትላለኽ፧ለምንስ፡እንዲህ፡ትናገራለኽ፧
28፤አላወቅኽምን፧አልሰማኽምን፧እግዚአብሔር፡የዘለዓለም፡አምላክ፥የምድርም፡ዳርቻ፡ፈጣሪ፡ነው፤አይደክምም ፥አይታክትም፥ማስተዋሉም፡አይመረመርም።
29፤ለደካማ፡ኀይልን፡ይሰጣል፥ጕልበት፡ለሌለውም፡ብርታትን፡ይጨምራል።
30፤ብላቴናዎች፡ይደክማሉ፡ይታክቱማል፥ጐበዛዝቱም፡ፈጽሞ፡ይወድቃሉ፤
31፤እግዚአብሔርን፡በመተማመን፡የሚጠባበቁ፡ግን፡ኀይላቸውን፡ያድሳሉ፤እንደ፡ንስር፡በክንፍ፡ይወጣሉ፤ይሮጣ ሉ፥አይታክቱም፤ይኼዳሉ፥አይደክሙም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡41።______________
ምዕራፍ፡41።
1፤ደሴቶች፡ሆይ፥በፊቴ፡ዝም፡በሉ፤አሕዛብም፡ኀይላቸውን፡ያድሱ፤ይቅረቡም፡በዚያን፡ጊዜም፡ይናገሩ፤ለፍርድ፡ ለአንድነት፡እንቅረብ።
2፤ከምሥራቅ፡አንዱን፡ያስነሣ፡በጽድቅም፡ወደ፡እግሩ፡የተጠራው፡ማን፡ነው፧አሕዛብንም፡አሳልፎ፡በፊቱ፡ሰጠው ፥ነገሥታትንም፡አስገዛለት፤ለሰይፉ፡እንደ፡ትቢያ፡ለቀስቱም፡እንደ፡ተጠረገ፡እብቅ፡አድርጎ፡ሰጣቸው።
3፤አሳደዳቸው፥እግሮቹም፡አስቀድመው፡ባልኼዱባት፡መንገድ፡በደኅንነት፡ዐለፈ።
4፤ይህን፡የሠራና፡ያደረገ፥ትውልድንም፡ከጥንት፡የጠራ፡ማን፡ነው፧እኔ፡እግዚአብሔር፥ፊተኛው፡በዃለኛዎችም፡ ዘንድ፡የምኖር፡እኔ፡ነኝ።
5፤ደሴቶች፡አይተው፡ፈሩ፥የምድርም፡ዳርቻዎች፡ተንቀጠቀጡ፤ቀረቡም፡ደረሱም።
6፤ዅሉም፡እያንዳንዱ፡ባልንጀራውን፡ይረዳው፡ነበር፥ወንድሙንም፦አይዞኽ፡ይለው፡ነበር።
7፤ዐናጢውም፡አንጥረኛውን፥በመዶሻም፡የሚያሣሣውን፡መስፍ፡መችውን፡አጽናና፥ስለማጣበቅ፡ሥራውም፦መልካም፡ነ ው፡አለ፤እንዳይንቀሳቀስም፡በችንካር፡አጋጠመው።
8፤ባሪያዬ፡እስራኤል፥የመረጥኹኽ፡ያዕቆብ፥የወዳጄ፡የአብርሃም፡ዘር፡ሆይ፥
9፤አንተ፡ከምድር፡ዳርቻ፡የያዝኹኽ፡ከማእዘኗም፡የጠራኹኽና፦አንተ፡ባሪያዬ፡ነኽ፥መርጬኻለኹ፡አልጥልኽም፡ያ ልኹኽ፡ሆይ፥
10፤እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡አትፍራ፤እኔ፡አምላክኽ፡ነኝና፡አትደንግጥ፤አበረታኻለኹ፥እረዳኽማለኹ፥በጽድ ቄም፡ቀኝ፡ደግፌ፡እይዝኻለኹ።
11፤እንሆ፥የሚቈጡኽ፡ዅሉ፡ያፍራሉ፥ይዋረዱማል፤የሚከራከሩኽም፡እንዳልነበሩ፡ይኾናሉ፥ይጠፉማል።
12፤የሚያጣሉኽንም፡ትሻቸዋለኽ፡አታገኛቸውምም፥የሚዋጉኽም፡እንዳልነበሩና፡እንደ፡ምናምን፡ይኾናሉ።
13፤እኔ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፦አትፍራ፥እረዳኻለኹ፡ብዬ፡ቀኝኽን፡እይዛለኹና።
14፤አንተ፡ትል፡ያዕቆብ፡የእስራኤልም፡ሰዎች፡ሆይ፥አትፍሩ፤እረዳኻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የሚቤዥኽም፡የ እስራኤል፡ቅዱስ፡ነው።
15፤እንሆ፥እንደ፡ተሳለች፡እንደ፡ዐዲስ፡ባለጥርስ፡ማኼጃ፡አድርጌኻለኹ፤ተራራዎችንም፡ታኼዳለኽ፡ታደቃ፟ቸው ማለኽ፥ኰረብታዎችንም፡እንደ፡ገለባ፡ታደርጋቸዋለኽ።
16፤ታበጥራቸዋለኽ፥ነፋስም፡ይጠርጋቸዋል፥ዐውሎ፡ነፋስም፡ይበትናቸዋል፤አንተም፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይልኻ ል፥በእስራኤልም፡ቅዱስ፡ትመካለኽ።
17፤ድኻዎችና፡ምስኪኖችም፡ውሃ፡ይሻሉ፡አያገኙምም፥ምላሳቸውም፡በጥማት፡ደርቋል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡እሰማቸ ዋለኹ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እኔ፡አልተዋቸውም።
18፤በወናዎቹ፡ኰረብታዎች፡ላይ፡ወንዞችን፥በሸለቆዎችም፡መካከል፡ምንጮችን፡እከፍታለኹ፤ምድረ፡በዳውን፡ለው ሃ፡መቆሚያ፥የጥማትንም፡ምድር፡ለውሃ፡መፍለቂያ፡አደርጋለኹ።
19፤20፤የእግዚአብሔር፡እጅ፡ይህን፡እንደ፡ሠራች፥የእስራኤልም፡ቅዱስ፡እንደ፡ፈጠረው፡ያዩ፡ዘንድ፡ያውቁም፡ ዘንድ፡ያስቡም፡ዘንድ፡በአንድነትም፡ያስተውሉ፡ዘንድ፥በምድረ፡በዳ፡ዝግባውንና፡ግራሩን፡ባርሰነቱንና፡የዘ ይቱን፡ዛፍ፡አበቅላለኹ፥በበረሓውም፡ጥዱንና፡አስታውን፡ወይራውንም፡በአንድነት፡አኖራለኹ።
21፤ክርክራችኹን፡አቅርቡ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ማስረጃችኹን፡አምጡ፥ይላል፡የያዕቆብ፡ንጉሥ።
22፤ያምጡ፥የሚኾነውንም፡ይንገሩን፤ልብም፡እናደርግ፡ዘንድ፡ፍጻሜያቸውንም፡እናውቅ፡ዘንድ፥የቀደሙት፡ነገሮ ች፡ምን፡እንደ፡ኾኑ፡ተናገሩ፥የሚመጡትንም፡አሳዩን።
23፤አማልክትም፡መኾናችኹን፡እናውቅ፡ዘንድ፡በዃላ፡የሚመጡትን፡ተናገሩ፤እንደነግጥም፡ዘንድ፡በአንድነትም፡ እናይ፡ዘንድ፡መልካሙን፡ወይም፡ክፉውን፡አድርጉ።
24፤እንሆ፥እንዳልነበረ፡ናችኹ፥ሥራችኹም፡ከንቱ፡ነው፤የሚመርጣችኹም፡አስጸያፊ፡ነው።
25፤አንዱን፡ከሰሜን፡አነሣኹ፡መጥቷልም፤አንዱም፡ከፀሓይ፡መውጫ፡ስሜን፡የሚጠራ፡ይመጣል፤በጭቃ፡ላይ፡እንደ ሚመጣ፡ሰው፡ዐፈርም፡እንደሚረግጥ፡ሸክለኛ፡በአለቃዎች፡ላይ፡ይመጣል።
26፤እናውቅ፡ዘንድ፡ከጥንት፡የተናገረው፦እውነት፡ነው፡እንልም፡ዘንድ፡ቀድሞ፡የተናገረው፡ማን፡ነው፧የሚናገ ር፡የለም፥የሚገልጥም፡የለም፥ቃላችኹንም፡የሚሰማ፡የለም።
27፤በመዠመሪያ፡ለጽዮን፦እንሇቸው፡እላለኹ፤ለኢየሩሳሌምም፡የምሥራች፡ነጋሪን፡እሰጣለኹ።
28፤ብመለከት፡ማንም፡አልነበረም፤ብጠይቃቸውም፡የሚመልስልኝ፡አማካሪ፡በመካከላቸው፡የለም።
29፤እንሆ፥እነርሱ፡ዅሉ፡ከንቱዎች፡ናቸው፥ሥራቸውም፡ምንም፡ምን፡ናት፤ቀልጠው፡የተሠሩት፡ምስሎቻቸውም፡ነፋ ስና፡ኢምንት፡ናቸው።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡42።______________
ምዕራፍ፡42።
1፤እንሆ፥ደግፌ፡የያዝኹት፡ባሪያዬ፤ነፍሴ፡ደስ፡የተሠኘችበት፡ምርጤ፤በርሱ፡ላይ፡መንፈሴን፡አድርጌያለኹ፥ር ሱም፡ለአሕዛብ፡ፍርድን፡ያወጣል።
2፤አይጮኽም፡ቃሉንም፡አያነሣም፥ድምፁንም፡በሜዳ፡አያሰማም።
3፤የተቀጠቀጠን፡ሸምበቆ፡አይሰብርም፥የሚጤስንም፡ክር፡አያጠፋም፤በእውነት፡ፍርድን፡ያወጣል።
4፤በምድርም፡ፍርድን፡እስኪያደርግ፡ድረስ፡ይበራል፡እንጂ፡አይጠፋም፤አሕዛብም፡በስሙ፡ይታመናሉ።
5፤ሰማያትን፡የፈጠረ፡የዘረጋቸውም፥ምድርንና፡በውስጧ፡ያለውን፡ያጸና፥በርሷ፡ላይ፡ለሚኖሩ፡ሕዝብ፡እስትንፋ ስን፥ለሚኼዱባትም፡መንፈስን፡የሚሰጥ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
6፤7፤እኔ፡እግዚአብሔር፡በጽድቅ፡ጠርቼኻለኹ፥እጅኽንም፡እይዛለኹ፡እጠብቅኽማለኹ፥የዕውሩንም፡ዐይን፡ትከፍ ት፡ዘንድ፡የተጋዘውንም፡ከግዞት፡ቤት፡በጨለማም፡የተቀመጡትን፡ከወህኒ፡ቤት፡ታወጣ፡ዘንድ፡ለሕዝብ፡ቃል፡ኪ ዳን፡ለአሕዛብም፡ብርሃን፡አድርጌ፡እሰጥኻለኹ።
8፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤ስሜ፡ይህ፡ነው፤ክብሬን፡ለሌላ፥ምስጋናዬንም፡ለተቀረጹ፡ምስሎች፡አልሰጥም።
9፤እንሆ፥የቀድሞው፡ነገር፡ተፈጸመ፥ዐዲስ፡ነገርንም፡እናገራለኹ፤አስቀድሞም፡ሳይበቅል፡ርሱን፡አስታውቃችዃ ለኹ።
10፤ወደ፡ባሕር፡የምትወርዱ፡በርሷም፡ውስጥ፡ያላችኹ፡ዅሉ፥ደሴቶችና፡በእነርሱም፡ላይ፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ለእግ ዚአብሔር፡ዐዲስ፡መዝሙር፥ከምድርም፡ዳርቻ፡ምስጋናውን፡ዘምሩ።
11፤ምድረ፡በዳውና፡ከተማዎቹ፡የቄዳርም፡ሰዎች፡የሚቀመጡባቸው፡መንደሮች፡ድምፃቸውን፡ያንሡ፤በሴላ፡የሚኖሩ ፡እልል፡ይበሉ፥በተራራዎችም፡ራስ፡ላይ፡ኾነው፡ይጩኹ።
12፤ለእግዚአብሔር፡ክብርን፡ይስጡ፥ምስጋናውንም፡በደሴቶች፡ይናገሩ።
13፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ኀያል፡ይወጣል፡እንደ፡ሰልፈኛም፡ቅንአትን፡ያስነሣል፤ይጮኻል፡ድምፁንም፡ያሰማል፡ በጠላቶቹም፡ላይ፡ይበረታል።
14፤ከድሮ፡ዘመን፡ዠምሮ፡ዝም፡ብያለኹ፥ዝም፡ብዬም፡ታግሻለኹ፤አኹን፡ምጥ፡እንደ፡ያዛት፡ሴት፡እጮኻለኹ፤አጠ ፋለኹ፡በአንድነትም፡እጨርሳለኹ።
15፤ተራራዎችንና፡ኰረብታዎችን፡አፈርሳለኹ፥ቡቃያዎቻቸውንም፡ዅሉ፡አደርቃለኹ፤ወንዞችንም፡ደሴቶች፡አደርጋ ለኹ፥ኵሬዎችንም፡አደርቃለኹ።
16፤ዕውሮችንም፡በማያውቋት፡መንገድ፡አመጣቸዋለኹ፥በማያውቋትም፡ጐዳና፡እመራቸዋለኹ፤በፊታቸውም፡ጨለማውን ፡ብርሃን፡አደርጋለኹ፥ጠማማውንም፡አቀናለኹ።ይህን፡አደርግላቸዋለኹ፥አልተዋቸውምም።
17፤በተቀረጹትም፡ምስሎች፡የሚታመኑ፥ቀልጠው፡የተሠሩትንም፡ምስሎች፦አምላኮቻችን፡ናችኹ፡የሚሉ፡ወደ፡ዃላቸ ው፡ይመለሳሉ፡ፈጽመውም፡ያፍራሉ።
18፤እናንተ፡ደንቈሮዎች፥ስሙ፤እናንተም፡ዕውሮች፥ታዩ፡ዘንድ፡ተመልከቱ።
19፤ከባሪያዬ፡በቀር፡ዕውር፡ማን፡ነው፧እንደምልከው፡መልእክተኛዬስ፡በቀር፡ደንቈሮ፡የኾነ፡ማን፡ነው፧እንደ ፡ፍጹሙ፡ወይስ፡እንደእግዚአብሔር፡ባሪያ፡ዕውር፡የኾነ፡ማን፡ነው፧
20፤ብዙ፡ነገርን፡ታያላችኹ፥ነገር፡ግን፥አትጠባበቁትም፤ዦሯችኹም፡ተከፍተዋል፥ነገር፡ግን፥አትሰሙም።
21፤እግዚአብሔር፡ስለ፡ጽድቁ፡ሕጉን፡ታላቅ፡ያደርግና፡ያከብር፡ዘንድ፡ወደደ።
22፤ይህ፡ግን፡የተበዘበዘና፡የተዘረፈ፡ሕዝብ፡ነው፤ዅላቸው፡በዋሻ፡ውስጥ፡ተጠምደዋል፡በግዞት፡ቤትም፡ተሸሽ ገዋል፤ብዝበዛ፡ኾነዋል፡የሚያድንም፡የለም፥ምርኮም፡ኾነዋል፥ማንም፦መልሱ፡አይልም።
23፤ከመካከላችኹ፡ይህን፡የሚያደምጥ፥ለሚመጣውም፡ጊዜ፡የሚያደምጥና፡የሚሰማ፡ማን፡ነው፧
24፤ያዕቆብን፡ለማረኩ፡እስራኤልንም፡ለበዘበዙ፡ሰዎች፡የሰጠ፡ማን፡ነው፧እኛ፡የበደልነው፥እነርሱም፡በመንገ ዱ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ያልወደዱት፡ለሕጉም፡ያልታዘዙለት፡እግዚአብሔር፡ርሱ፡አይደለምን፧
25፤ስለዚህ፥የቍጣውን፡መዓትና፡የሰልፉን፡ጽናት፡አፈሰሰበት፤በዙሪያም፡አነደደው፥ርሱ፡ግን፡አላወቀም፥አቃ ጠለውም፡ርሱ፡ግን፡ልብ፡አላደረገም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡43።______________
ምዕራፍ፡43።
1፤አኹንም፡ያዕቆብ፡ሆይ፥የፈጠረኽ፥እስራኤልም፡ሆይ፥የሠራኽ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ተቤዥቼኻለኹና፡ አትፍራ፤በስምኽም፡ጠርቼኻለኹ፥አንተ፡የእኔ፡ነኽ።
2፤በውሃ፡ውስጥ፡ባለፍኽ፡ጊዜ፡ከአንተ፡ጋራ፡እኾናለኹ፥በወንዞችም፡ውስጥ፡ባለፍኽ፡ጊዜ፡አያሰጥሙኽም፤በእሳ ትም፡ውስጥ፡በኼድኽ፡ጊዜ፡አትቃጠልም፥ነበልባሉም፡አይፈጅኽም።
3፤እኔ፡የእስራኤል፡ቅዱስ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡መድኀኒትኽ፡ነኝ፤ግብጽን፡ለአንተ፡ቤዛ፡አድርጌ፥ኢትዮጵ ያንና፡ሳባንም፡ለአንተ፡ፋንታ፡ሰጥቻለኹ።
4፤በዐይኔ፡ፊት፡የከበርኽና፡የተመሰገንኽ፡ነኽና፥እኔም፡ወድጄኻለኹና፡ስለዚህ፡ሰዎችን፡ለአንተ፡አሕዛብንም ፡ለነፍስኽ፡እሰጣለኹ።
5፤እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡አትፍራ፤ዘርኽንም፡ከምሥራቅ፡አመጣዋለኹ፥ከምዕራብም፡እሰበስብኻለኹ።
6፤7፤ሰሜንን፦መልሰኽ፡አምጣ፥ደቡብንም፦አትከልክል፤ወንዶች፡ልጆቼን፡ከሩቅ፡ሴቶች፡ልጆቼንም፡ከምድር፡ዳር ቻ፥በስሜ፡የተጠራውን፡ለክብሬም፡የፈጠርኹትን፥የሠራኹትንና፡ያደረግኹትን፡ዅሉ፡አምጣ፡እለዋለኹ።
8፤ዐይኖች፡ያሏቸውን፡ዕውሮችን፡ሕዝብ፥ዦሮዎችም፡ያሏቸውን፡ደንቈሮዎቹን፡አውጣ።
9፤አሕዛብ፡ዅሉ፡በአንድነት፡ይሰብሰቡ፡ወገኖችም፡ይከማቹ፤ከመካከላቸው፤ይህን፡የሚናገር፥የቀድሞውንስ፡ነገ ር፡የሚያሳየን፡ማን፡ነው፧ይጸድቁ፡ዘንድ፡ምስክሮቻቸውን፡ያምጡ፥ሰምተውም፡እውነት፡ነው፡ይበሉ።
10፤ታውቁና፡ታምኑብኝ፡ዘንድ፡እኔም፡እንደኾንኹ፡ታስተውሉ፡ዘንድ፥እናንተ፡የመረጥኹትም፡ባሪያዬ፡ምስክሮቼ ፡ናችኹ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤ከእኔ፡በፊት፡አምላክ፡አልተሠራም፡ከእኔም፡በዃላ፡አይኾንም።
11፤እኔ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥ከእኔ፡ሌላም፡የሚያድን፡የለም።
12፤ተናግሬያለኹ፡አድኜማለኹ፡አሳይቼማለኹ፥በእናንተም፡ዘንድ፡ባዕድ፡አምላክ፡አልነበረም፤ስለዚህ፥እናንተ ፡ምስክሮቼ፡ናችኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እኔም፡አምላክ፡ነኝ።
13፤ከጥንት፡ዠምሮ፡እኔ፡ነኝ፡ከእጄም፡የሚያመልጥ፡የለም፤እሠራለኹ፥የሚከለክልስ፡ማን፡ነው፧
14፤የእስራኤል፡ቅዱስ፥የሚቤዣችኹ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለ፡እናንተ፡ወደ፡ባቢሎን፡ሰድጃለኹ፥ከለ ዳውያንንም፡ዅሉ፡ስደተኛዎች፡አድርጌ፡በሚመኩባቸው፡መርከቦች፡አዋርዳቸዋለኹ።
15፤ቅዱሳችኹ፥የእስራኤል፡ፈጣሪ፥ንጉሣችኹ፥እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ።
16፤እግዚአብሔር፡በባሕር፡ውስጥ፡መንገድን፡በኀይለኛም፡ውሃ፡ውስጥ፡መተላለፊያን፡ያደርጋል፤
17፤እግዚአብሔር፡ሠረገላውንና፡ፈረሱን፡ሰራዊቱንና፡ዐርበኛውን፡ያወጣል፤እነርሱ፡ግን፡በአንድነት፡ተኝተዋ ል፥አይነሡም፤ቀርተዋል፥እንደ፡ጧፍ፡ኵስታሪም፡ጠፍተዋል፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
18፤የፊተኛውን፡ነገር፡አታስተውሉ፥የጥንቱንም፡ነገር፡አታስቡ።
19፤እንሆ፥ዐዲስ፡ነገርን፡አደርጋለኹ፤ርሱም፡አኹን፡ይበቅላል፥እናንተም፡አታውቁትምን፧በምድረ፡በዳም፡መን ገድን፥በበረሓም፡ወንዞችን፡አደርጋለኹ።
20፤21፤ምስጋናዬን፡እንዲናገሩ፡ለእኔ፡የፈጠርኹት፡ሕዝብ፥የመረጥኹትን፡ሕዝቤን፡አጠጣ፡ዘንድ፥በምድረ፡በዳ ፡ውሃን፡በበረሓም፡ወንዞችን፡ሰጥቻለኹና፥የምድረ፡በዳ፡አራዊት፥ቀበሮዎችና፡ሰጐኖች፥ያከብሩኛል።
22፤ያዕቆብ፡ሆይ፥አንተ፡ግን፡አልጠራኸኝም፥አንተም፡እስራኤል፡ሆይ፥በእኔ፡ዘንድ፡ደክመኻል።
23፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡በጎችኽን፡አላቀረብኽልኝም፡በሌላም፡መሥዋዕትኽ፡አላከበርኸኝም፤በእኽልም፡ቍርባን ፡አላስቸገርኹኽም፡በዕጣንም፡አላደከምኹኽም።
24፤ዕጣንም፡በገንዘብ፡አልገዛኽልኝም፡በመሥዋዕትኽም፡ስብ፡አላጠገብኸኝም፤ነገር፡ግን፥በኀጢአትኽ፡አስቸገ ርኸኝ፥በበደልኽም፡አደከምኸኝ።
25፤መተላለፍኽን፦ስለ፡እኔ፡ስል፡የምደመስስ፡እኔ፡ነኝ፤ኀጢአትኽንም፡አላስብም።
26፤አሳስበኝ፥በአንድነትም፡ኾነን፡እንፋረድ፤እንድትጸድቅ፡ነገርኽን፡ተናገር።
27፤ፊተኛው፡አባትኽ፡ኀጢአት፡ሠርቷል፥መምህሮችኽም፡በድለውኛል።
28፤ስለዚህ፥የመቅደሱን፡አለቃዎች፡አረከስኹ፥ያዕቆብንም፡ርግማን፥እስራኤልንም፡ስድብ፡አደረግኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡44።______________
ምዕራፍ፡44።
1፤አኹንም፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡የመረጥኹኽም፡እስራኤል፡ሆይ፥ስማ።
2፤የፈጠረኽ፡ከማሕፀንም፡የሠራኽ፡የሚረዳኽም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡የመረጥኹኽም፡ ይሹሩን፡ሆይ፥አትፍራ።
3፤በተጠማ፡ላይ፡ውሃን፡በደረቅም፡መሬት፡ላይ፡ፈሳሾችን፡አፈሳ፟ለኹና፤መንፈሴን፡በዘርኽ፡ላይ፡በረከቴንም፡ በልጆችኽ፡ላይ፡አፈሳ፟ለኹ፥
4፤በፈሳሾችም፡አጠገብ፡እንደሚበቅሉ፡እንደ፡አሓያ፡ዛፎች፡በሣር፡መካከል፡ይበቅላሉ።
5፤ይህ፦እኔ፡የእግዚአብሔር፡ነኝ፡ይላል፥ያም፡በያዕቆብ፡ስም፡ይጠራል፤ይህም፦እኔ፡የእግዚአብሔር፡ነኝ፡ብሎ ፡በእጁ፡ይጽፋል፥በእስራኤልም፡የቍልምጫ፡ስም፡ይጠራል።
6፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡እግዚአብሔር፥የሚቤዥም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ፊተኛ፡ነኝ ፥እኔም፡ዃለኛ፡ነኝ፤ከእኔ፡ሌላም፡አምላክ፡የለም።
7፤እንደ፡እኔ፡ያለ፡ማን፡ነው፧ይነሣና፡ይጥራ፡ይናገርም፤ከጥንት፡የፈጠርኹትን፡ሕዝብ፡ያዘጋጅልኝ፥የሚመጣው ም፡ነገር፡ሳይደርስ፡ይንገሩኝ።
8፤አትፍሩ፡አትደንግጡም፤ከጥንቱ፡ዠምሬ፡አልነገርዃችኹምን፧ወይስ፡አላሳየዃችኹምን፧እናንተ፡ምስክሮቼ፡ናች ኹ።ከእኔ፡ሌላ፡አምላክ፡አለን፧ዐምባ፡የለም፤ማንንም፡አላውቅም።
9፤የተቀረጸውን፡ምስል፡የሚሠሩ፡ዅሉ፡ከንቱዎች፡ናቸው፥የወደዱትም፡ነገር፡አይረባቸውም፤ምስክሮቻቸውም፡አያ ዩምና፡አያውቁም፤ስለዚህ፥ያፍራሉ።
10፤አምላክን፡የሠራ፡ወይስ፡ለምንም፡የማይረባ፡ምስልን፡የቀረጸ፡ማን፡ነው፧
11፤እንሆ፥ባልንጀራዎቹ፡ዅሉ፡ያፍራሉ፥ሠራተኛዎቹም፡ከሰዎች፡ወገን፡ናቸው፤ዅላቸው፡ተሰብስበው፡ይቁሙ፤ይፈ ራሉ፡በአንድነትም፡ያፍራሉ።
12፤ብረት፡ሠሪ፡መጥረቢያውን፡ይሠራል፥በፍምም፡ውስጥ፡ያደርገዋል፥በመዶሻም፡መቶ፟፡ቅርጽ፡ይሰጠዋል፥በክን ዱም፡ኀይል፡ይሠራዋል፥ርሱም፡ይራባል፡ይደክምማል፥ውሃም፡አይጠጣም፡ይታክትማል።
13፤ጠራቢውም፡ገመድ፡ይዘረጋል፡በበረቅም፡ያመለክተዋል፡በመቅረጫም፡ይቀርጸዋል፡በመለኪያም፡ይለካዋል፤በቤ ትም፡ውስጥ፡ይቀመጥ፡ዘንድ፡በሰው፡አምሳልና፡በሰው፡ውበት፡ያስመስለዋል።
14፤የዝግባን፡ዛፎች፡ይቈርጣል፤የዞጲንና፡የኮምቦልን፡ዛፍ፡ይመርጣል፥ከዱር፡ዛፎችም፡መካከል፡ይጠነክር፡ዘ ንድ፡ይተወዋል፤የጥድንም፡ዛፍ፡ይተክላል፡ዝናብም፡ያበቅለዋል።
15፤ለሰውም፡ማገዶ፡ይኾናል፤ከርሱም፡ወስዶ፡ይሞቃል፥አንድዶም፡እንጀራ፡ይጋግርበታል፤ከርሱም፡አምላክ፡አበ ጅቶ፡ይሰግድለታል፥የተቀረጸውንም፡ምስል፡ሠርቶ፡በርሱ፡ፊት፡ይንበረከካል።
16፤ግማሹን፡በእሳት፡ያቃጥላል፥በዚያ፡በግማሹ፡ሥጋ፡ይበላል፥ሥጋም፡ይጠብስበትና፡ይጠግባል፤ይሞቃልና፦ዕሠ ይ፡ሞቅኹ፥እሳቱን፡አይቻለኹ፡ይላል።
17፤የቀረውንም፡ዕንጨት፡አምላክ፡አድርጎ፡ምስል፡ይቀርጽበታል፤በፊቱም፡ተጐንብሶ፡ይሰግዳል፡ወደ፡ርሱም፡እ የጸለየ፦አምላኬ፡ነኽና፥አድነኝ፡ይላል።
18፤አያውቁም፥አያስቡም፤እንዳያዩ፡ዐይኖቻቸውን፥እንዳያስተውሉ፡ልቦቻቸውን፡ጨፍነዋል።
19፤በልቡም፡ማንም፡አያስብም፦ግማሿን፡በእሳት፡አቃጥያለኹ፥በፍሟም፡ላይ፡እንጀራን፡ጋግሬያለኹ፥ሥጋም፡ጠብ ሼ፡በልቻለኹ፤የቀረውንም፡አስጸያፊ፡ነገር፡አደርጋለኹን፧ለዛፍስ፡ግንድ፡እሰግዳለኹን፧እንዲልም፡ዕውቀትና ፡ማስተዋል፡የለውም።
20፤ዐመድ፡ይበላል፥የተታለለ፡ልብ፡አስቶታል፥ነፍሱን፡ለማዳን፡አይችልም፥ወይም፦በቀኝ፡እጄ፡ሐሰት፡አለ፡አ ይልም።
21፤ያዕቆብ፡ሆይ፥አንተም፡እስራኤል፥ባሪያዬ፡ነኽና፥ይህን፡ዐስብ፤እኔ፡ሠርቼኻለኹ፡አንተም፡ባሪያዬ፡ነኽ፤ እስራኤል፡ሆይ፥በእኔ፡ዘንድ፡ያልተረሳ፡ትኾናለኽ።
22፤መተላለፍኽን፡እንደ፡ደመና፥ኀጢአትኽንም፡እንደ፡ጭጋግ፡ደምስሻለኹ፤ተቤዥቼኻለኹና፡ወደ፡እኔ፡ተመለስ።
23፤ሰማያት፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡አድርጎታልና፥ዘምሩ፤እግዚአብሔር፡ያዕቆብን፡ተቤዥቷልና፥በእስራኤልም፡ዘን ድ፡ይከበራልና፥አንተ፡የምድር፡ጥልቅ፡ሆይ፥ጩኽ፤እናንተም፡ተራራዎች፡አንተም፡ዱር፡ባንተም፡ያለ፡ዛፍ፡ዅሉ ፥እልል፡በሉ።
24፤ከማሕፀን፡የሠራኽ፥የሚቤዥኽ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዅሉን፡የፈጠርኹ፥ሰማያትን፡ለብቻዬ፡የዘረጋ ኹ፡ምድርንም፡ያጸናኹ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ፤ከእኔ፡ጋራ፡ማን፡ነበረ፧
25፤የሐሰተኛዎችን፡ምልክት፡ከንቱ፡አደርጋለኹ፥ሟርተኛዎችንም፡አሳብዳለኹ፥ጥበበኛዎቹንም፡ወደ፡ዃላ፡እመል ሳለኹ፡ዕውቀታቸውንም፡ስንፍና፡አደርጋለኹ፤
26፤የባሪያዬን፡ቃል፡አጸናለኹ፥የመልእክተኛዎቼንም፡ምክር፡እፈጽማለኹ፤ኢየሩሳሌምን፦የሰው፡መኖሪያ፡ትኾኛ ለሽ፥የይሁዳንም፡ከተማዎች።ትታነጻላችኹ፡ፍራሾቻችኹንም፡አቆማለኹ፡እላለኹ፤
27፤ቀላዩንም፦ደረቅ፡ኹን፥ፈሳሾችኽንም፡አደርቃለኹ፡እላለኹ፤
28፤ቂሮስንም፦ርሱ፡እረኛዬ፡ነው፤ርሱም፡ኢየሩሳሌምን፦ትታነጺ᎗ያለሽ፡ቤተ፡መቅደስም፡ይመሠረታል፡ብሎ፡ፈቃ ዴን፡ዅሉ፡ይፈጽማል፡እላለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡45።______________
ምዕራፍ፡45።
1፤እግዚአብሔር፡ለቀባኹት፥አሕዛብንም፡በፊቱ፡አስገዛ፡ዘንድ፡የነገሥታትንም፡ወገብ፡እፈታ፡ዘንድ፥በሮቹም፡ እንዳይዘጉ፡መዝጊያዎቹን፡በፊቱ፡እከፍት፡ዘንድ፥ቀኝ፡እጁን፡ለያዝኹት፡ለቂሮስ፡እንዲህ፡ይላል፦
2፤በፊትኽ፡እኼዳለኹ፡ተራራዎችንም፡ትክክል፡አደርጋለኹ፥የናሱንም፡ደጆች፡እሰብራለኹ፡የብረቱንም፡መወርወሪ ያዎች፡እቈርጣለኹ፤
3፤በስምኽም፡የምጠራኽ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቅ፡ዘንድ፡በጨለማ፡የነበረ ችውን፡መዝገብ፡በስውርም፡የተደበቀችውን፡ሀብት፡እሰጥኻለኹ።
4፤ስለ፡ባሪያዬ፡ስለ፡ያዕቆብ፥ስለ፡መረጥኹትም፡ስለ፡እስራኤል፡ብዬ፡በስምኽ፡ጠርቼኻለኹ፤በቍልምጫ፡ስምኽ፡ ጠራኹኽ፥አንተ፡ግን፡አላወቅኸኝም።
5፤6፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡ከእኔም፡ሌላ፡ማንም፡የለም፤ከእኔም፡በቀር፡አምላክ፡የለም፤በፀሓይ፡መውጫና፡ በምዕራብ፡ያሉ፡ከእኔ፡በቀር፡ማንም፡ሌላ፡እንደሌለ፡ያውቁ፡ዘንድ፡አስታጠቅኹኽ፥አንተ፡ግን፡አላወቅኸኝም፤ እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥ከእኔም፡ሌላ፡ማንም፡የለም።
7፤ብርሃንን፡ሠራኹ፥ጨለማውንም፡ፈጠርኹ፤ደኅንነትን፡እሠራለኹ፥ክፋትንም፡እፈጥራለኹ፤እነዚህን፡ዅሉ፡ያደረ ግኹ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ።
8፤እናንተ፡ሰማያት፡ከላይ፡አንጠባጥቡ፥ደመናትም፡ጽድቅን፡ያዝንቡ፤ምድርም፡ትከፈት፥መድኀኒትንም፡ታብቅል፥ ጽድቅም፡በአንድነት፡ይብቀል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ፈጥሬዋለኹ።
9፤ከሠሪው፡ጋራ፡ለሚታገል፡ወዮለት! በምድር፡ሸክላዎች፡መካከል፡ያለ፡ሸክላ፡ነው።ጭቃ፡ሠሪውን፦ምን፡ትሠራለኽ፧ወይስ፡ሥራኽ፦እጅ፡የለውም፡ይላ ልን፧
10፤አባትን፦ምን፡ወልደኻል፧ወይም፡ሴትን፦ምን፡አማጥሽ፧ለሚል፡ወዮ!
11፤የእስራኤል፡ቅዱስ፡ሠሪውም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሚመጣው፡ነገር፡ጠይቁኝ፥ስለ፡ልጆቼና፡ስለ እጄ፡ሥራም፡እዘዙኝ።
12፤እኔ፡ምድርን፡ሠርቻለኹ፡ሰውንም፡በርሷ፡ላይ፡ፈጥሬያለኹ፤እኔ፡በእጄ፡ሰማያትን፡ዘርግቻለኹ፥ሰራዊታቸው ንም፡ዅሉ፡አዝዣለኹ።
13፤እኔ፡በጽድቅ፡አስነሥቼዋለኹ፥መንገዱንም፡ዅሉ፡አቀናለኹ፤ርሱ፡ከተማዬን፡ይሠራል፥በዋጋም፡ወይም፡በደመ ፡ወዝ፡ሳይኾን፡ምርኮኛዎቼን፡ያወጣል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
14፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦የግብጽ፡ድካምና፡የኢትዮጵያ፡ንግድ፡ቁመተ፡ረዥሞችም፡የሳባ፡ሰዎች፡ወዳ ንተ፡ያልፋሉ፤ለአንተም፡ይኾናሉ፡እጆቻቸውም፡ታስረው፡ይከተሉኻል፤በፊትኽም፡ያልፋሉ፥ለአንተም፡እየሰገዱ፦ በእውነት፡እግዚአብሔር፡ባንተ፡አለ፥ከርሱም፡ሌላ፡አምላክ፡የለም፡ብለው፡ይለምኑኻል።
15፤የእስራኤል፡አምላክ፡መድኀኒት፡ሆይ፥በእውነት፡አንተ፡ራስኽን፡የምትሰውር፡አምላክ፡ነኽ።
16፤ዅሉም፡ያፍራሉ፡ይዋረዱማል፥ጣዖታትንም፡የሚሠሩ፡በአንድነት፡ወደ፡ውርደት፡ይኼዳሉ።
17፤እግዚአብሔር፡ግን፡እስራኤልን፡በዘላለማዊ፡መድኀኒት፡ያድነዋል፥እናንተም፡ለዘለዓለም፡አታፍሩምና፡አት ዋረዱም።
18፤ሰማያትን፡የፈጠረ፡እግዚአብሔር፥ርሱም፡ምድርን፡የሠራና፡ያደረገ፡ያጸናትም፥መኖሪያም፡ልትኾን፡እንጂ፡ ለከንቱ፡እንድትኾን፡ያልፈጠራት፡አምላክ፥እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለ ም።
19፤በስውር፡ወይም፡በጨለማ፡ምድር፡ስፍራ፡አልተናገርኹም፤ለያዕቆብ፡ዘር፦በከንቱ፡ፈልጉኝ፡አላልኹም፤እኔ፡ እግዚአብሔር፡ጽድቅን፡እናገራለኹ፡ቅንንም፡አወራለኹ።
20፤እናንተ፡ከአሕዛብ፡ወገን፡ኾናችኹ፡ያመለጣችኹ፥ተሰብስባችኹ፡ኑ፡በአንድነትም፡ቅረቡ፤የተቀረጸውን፡የም ስላቸውን፡ዕንጨት፡የሚሸከሙና፡ያድን፡ዘንድ፡ወደማይችል፡አምላክ፡የሚጸልዩ፡ዕውቀት፡የላቸውም።
21፤ይናገሩ፡ይቅረቡም፡በአንድነትም፡ይማከሩ፤ከጥንቱ፡ይህን፡ያሳየ፡ከቀድሞስ፡የተናገረ፡ማን፡ነው፧ያሳየኹ ም፡የተናገርኹም፡እኔ፡እግዚአብሔር፡አይደለኹምን፧ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡አምላክ፡የለም፤እኔ፡ጻድቅ፡አምላክ ና፡መድኀኒት፡ነኝ፥ከእኔም፡በቀር፡ማንም፡የለም።
22፤እናንተ፡የምድር፡ዳርቻ፡ዅሉ፥እኔ፡አምላክ፡ነኝና፥ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለምና፡ወደ፡እኔ፡ዘወር፡በሉ፡ ትድኑማላችኹ።
23፤ቃሌ፡ከአፌ፡በጽድቅ፡ወጥታለች፥አትመለስም።ጕልበት፡ዅሉ፡ለእኔ፡ይንበረከካል፥ምላስም፡ዅሉ፡በእኔ፡ይም ላል፡ብዬ፡በራሴ፡ምያለኹ።
24፤ስለ፡እኔም፦በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ብቻ፡ጽድቅና፡ኀይል፡አለ፥ወደ፡ርሱም፡ሰዎች፡ይመጣሉ፥በርሱም፡ላይ፡ የተቈጡ፡ዅሉ፡ያፍራሉ።
25፤የእስራኤልም፡ዘር፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ይጸድቃሉ፥ይመካሉም፡ይባላል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡46።______________
ምዕራፍ፡46።
1፤ቤል፡ተዋረደ፥ናባው፡ተሰባበረ፤ጣዖቶቻቸው፡በእንስሳና፡በከብት፡ላይ፡ተጭነዋል፤ሸክሞቻችኹ፡ለደካማ፡እን ስሳ፡ከባድ፡ጭነት፡ኾነዋል።
2፤ተጐነበሱ፡በአንድነትም፡ተዋረዱ፤ሸክሙን፡ለማዳን፡አልቻሉም፥ራሳቸው፡ግን፡ተማረኩ።
3፤እናንተ፡የያዕቆብ፡ቤት፡ሆይ፥የእስራኤልም፡ቤት፡ቅሬታ፡ዅሉ፥ከሆድ፡ያነሣዃችኹ፡ከማሕፀንም፡የተሸከምዃች ኹ፥ስሙኝ።
4፤እስከ፡ሽምግልና፡ድረስ፡እኔ፡ነኝ፥እስከ፡ሽበትም፡ድረስ፡እሸከማችዃለኹ፤እኔ፡ሠርቻለኹ፡እኔም፡አነሣለኹ ፤እኔ፡እሸከማለኹ፡እኔም፡አድናለኹ።
5፤በማን፡ትመስሉኛላችኹ፧ከማንስ፡ጋራ፡ታስተካክሉኛላችኹ፧እንመሳሰል፡ዘንድ፡ከማን፡ጋራ፡ታስተያዩኛላችኹ፧
6፤ወርቁን፡ከኰረጆ፡የሚያፈሱ፟፥ብሩንም፡በሚዛን፡የሚመዝኑ፡እነርሱ፡አንጥረኛውን፡ይቀጥራሉ፥ርሱም፡አምላክ ፡አድርጎ፡ይሠራ፡ዋል፤ለዚያም፡ይጐ፟ነበሱለታል፥ይሰግዱለትማል።
7፤በጫንቃቸው፡ላይ፡አንሥተው፡ይሸከሙታል፡በስፍራውም፡ያደርጉታል፥በዚያም፡ይቆማል፥ከስፍራውም፡ፈቀቅ፡አይ ልም፤ሰውም፡ወደ፡ርሱ፡ቢጮኽ፡አይሰማውም፡ከመከራውም፡አያድነውም።
8፤ይህን፡ዐስቡና፡አልቅሱ፤ተላላፊዎች፡ሆይ፥ንስሓ፡ግቡ፥ልባችኹንም፡መልሱ።
9፤እኔ፡አምላክ፡ነኝና፥ሌላም፡የለምና፡የቀድሞውን፡የጥንቱን፡ነገር፡ዐስቡ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡እንደ፡ እኔም፡ያለ፡ማንም፡የለም።
10፤በመዠመሪያ፡መጨረሻውን፥ከጥንትም፡ያልተደረገውን፡እነግራለኹ፤ምክሬ፡ትጸናለች፡ፈቃዴንም፡ዅሉ፡እፈጽማ ለኹ፡እላለኹ።
11፤ከምሥራቅ፡ነጣቂ፡ወፍን፥ከሩቅም፡አገር፡ምክሬን፡የሚያደርገውን፡ሰው፡እጠራዋለኹ።ተናግሬያለኹ፤እፈጽማ ለኹ፤ዐስቤያለኹ፡አደርግማለኹ።
12፤እናንተ፡ከጽድቅ፡የራቃችኹ፡እልከኛዎች፥ስሙኝ፤
13፤ጽድቄን፡አቀርባለኹ፥አይርቅም፡መድኀኒቴም፡አይዘገይም፤ከጽዮን፡ለክብር፡እንዲኾን፡መድኀኒትን፡ለእስራ ኤል፡ሰጥቻለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡47።______________
ምዕራፍ፡47።
1፤አንቺ፡ድንግል፡የባቢሎን፡ልጅ፡ሆይ፥ውረጂ፡በትቢያም፡ላይ፡ተቀመጪ፤የከለዳውያን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ከዚህ፡ በዃላ፡ቅልጣናምና፡ቅምጥል፡አትባይምና፥ያለዙፋን፡በመሬት፡ላይ፡ተቀመጪ።
2፤ወፍጮ፡ወስደሽ፡ዱቄትን፡ፍጪ፤መሸፈኛሽን፡አውጪ፡ረዥሙንም፡ልብስሽን፡አውልቀሽ፡ጣዪው፤ባትሽን፡ግለጪ፥ወ ንዙን፡ተሻገሪ።
3፤ኀፍረተ፡ሥጋሽ፡ይገለጣል፡ዕፍረትሽም፡ይታያል፤እኔ፡እበቀላለኹ፥ለማንም፡አልራራም።
4፤ታዳጊያችን፥ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡ቅዱስ፡ነው።
5፤የከለዳውያን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ከዚህ፡በዃላ፦የመንግሥታት፡እመቤት፡አትባይምና፥ዝም፡ብለሽ፡ተቀመጪ፥ወደ፡ ጨለማም፡ውስጥ፡ግቢ።
6፤በሕዝቤ፡ላይ፡ተቈጥቼ፡ነበር፡ርስቴንም፡አረከስኹ፡በእጅሽም፡አሳልፌ፡ሰጠዃቸው፤ከነርሱ፡ጋራ፡ምሕረት፡አ ላደረግሽም፥በሽማግሌዎቻቸው፡ላይ፡ቀንበርሽን፡እጅግ፡አክብደሻል።
7፤አንቺም፦እኔ፡ለዘለዓለም፡እመቤት፡እኾናለኹ፡ብለሻል፤ይህንም፡በልብሽ፡አላደረግሽም፡ፍጻሜውንም፡አላሰብ ሽም።
8፤አኹንም፡አንቺ፡ቅምጥል፡ተዘልለሽ፡የምትቀመጪ፥በልብሽም፦እኔ፡ነኝ፡ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለም፤መበለትም ፡ኾኜ፡አልኖርም፡የወላድ፡መካንነትንም፡አላውቅም፡የምትዪ፡ይህን፡ስሚ፤
9፤አኹን፡ግን፡ባንድ፡ቀን፡እነዚህ፡ኹለት፡ነገሮች፥የወላድ፡መካንነትና፡መበለትነት፥በድንገት፡ይመጡብሻል፤ ስለ፡መተቶችሽ፡ብዛትና፡ስለ፡አስማቶችሽ፡ጽናት፡ፈጽመው፡ይመጡብሻል።
10፤በክፋትሽ፡ታምነሻል፤የሚያየኝ፡የለም፡ብለሻል፤ጥበብሽና፡ዕውቀትሽ፡አታለ፟ውሻል፥በልብሽም፦እኔ፡ነኝ፡ ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለም፡ብለሻል።
11፤ስለዚህ፡ምክንያት፡ክፉ፡ነገር፡ይመጣብሻል፥በሟርትሽም፡እንዴት፡እንደምታርቂው፡አታውቂም፤ጕዳት፡ይወድ ቅብሻል፥ታስወግጂውም፡ዘንድ፡አይቻልሽም፤የማታውቂያትም፡ጕስቍልና፡ድንገት፡ትመጣብሻለች።
12፤ምናልባትም፡መጠቀም፡ትችዪ፡ወይም፡ታስደነግጪ፡እንደ፡ኾነ፥ከአስማቶችሽና፡ከሕፃንነትሽ፡ዠምረሽ፡ከደከ ምሽበት፡ከመተቶችሽ፡ብዛት፡ጋራ፡ቁሚ።
13፤በምክርሽ፡ብዛት፡ደክመሻል፤አኹንም፡የሰማይን፡ከዋክብት፡የሚቈጥሩ፥ከዋክብትንም፡የሚመለከቱ፥በየመባቻ ውም፡የሚመጣውን፡ነገር፡የሚናገሩ፡ተነሥተው፡ከሚመጣብሽ፡ነገር፡ያድኑሽ።
14፤እንሆ፥እንደ፡እብቅ፡ይኾናሉ፥እሳትም፡ያቃጥላቸዋል፡ሰውነታቸውንም፡ከነበልባል፡ኀይል፡አያድኑም፤ርሱም ፡ሰው፡እንደሚሞቀው፡ፍም፥ወይም፡በፊቱ፡ሰው፡እንደሚቀመጥበት፡እሳት፡ያለ፡አይደለም።
15፤የደከምሽባቸው፡ነገሮች፡እንዲህ፡ይኾኑብሻል፤ከሕፃንነትሽ፡ዠምረው፡ከአንቺ፡ጋራ፡ይነግዱ፡የነበሩ፡እያ ንዳንዳቸው፡ወደ፡ስፍራቸው፡ይኼዳሉ፥የሚያድንሽም፡የለም።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡48።______________
ምዕራፍ፡48።
1፤እናንተ፡በእስራኤል፡ስም፡የተጠራችኹ፡ከይሁዳም፡ውሃዎች፡የወጣችኹ፥በእግዚአብሔር፡ስም፡የምትምሉ፥በእው ነት፡ሳይኾን፡በጽድቅም፡ሳይኾን፡የእስራኤልን፡አምላክ፡የምትጠሩ፥
2፤በቅድስት፡ከተማ፡ስም፡የተጠራችኹ፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በሚባል፡በእስራኤል፡አምላክ፡የም ትደገፉ፥የያዕቆብ፡ቤት፡ሆይ፥ይህን፡ስሙ።
3፤የቀድሞውን፡ነገር፡ከጥንት፡ተናግሬያለኹ፥ከአፌም፡ወጥቷል፡አሳይቼውማለኹ፤ድንገት፡አድርጌዋለኹ፡ተፈጽሞ ማል።
4፤አንተ፡እልከኛ፥ዐንገትኽም፡የብረት፡ዥማት፥ግንባርኽም፡ናስ፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቄያለኹ፤
5፤ስለዚህ፥አንተ፦ጣዖቴ፡ይህን፡አድርጓል፥የተቀረጸው፡ምስሌና፡ቀልጦ፡የተሠራው፡ምስሌ፡ይህን፡አዘዙኝ፡እን ዳትል፥አስቀድሜ፡ነግሬኽ፡ነበር፡ሳይኾንም፡አሳይቼኽ፡ነበር።
6፤ሰምተኻል፤ይህን፡ዅሉ፡ተመልከት፤እናንተም፡የምትናገሩት፡አይደላችኹምን፧የተሰወሩትን፡ያላወቅኻቸውንም፡ ዐዲሶች፡ነገሮችን፡ከዚህ፡ዠምሬ፡አሳይቼኻለኹ።
7፤እነርሱም፡አኹን፡እንጂ፡ከጥንት፡አልተፈጠሩም፤አንተም፦እንሆ፥ዐውቄያቸዋለኹ፡እንዳትል፡ከዛሬ፡በፊት፡አ ልሰማኻቸውም።
8፤አልሰማኽም፥አላወቅኽም፥ዦሮኽ፡ከጥንት፡አልተከፈተችም፤አንተ፡ፈጽሞ፡ወንጀለኛ፡እንደ፡ኾንኽ፡ከማሕፀንም ፡ዠምረኽ፡ተላላፊ፡ተብለኽ፡አንደ፡ተጠራኽ፡ዐውቄያለኹና።
9፤ስለ፡ስሜ፡ቍጣዬን፡አዘገያለኹ፥እንዳላጠፋኽም፡ስለ፡ምስጋናዬ፡እታገሣለኹ።
10፤እንሆ፥አንጥሬኻለኹ፥ነገር፡ግን፥እንደ፡ብር፡አይደለም፤በመከራም፡እቶን፡ፈትኜኻለኹ።
11፤ስለ፡እኔ፥ስለ፡ራሴ፡አደርገዋለኹ፡ስሜ፡ተነቅፏልና፤ክብሬንም፡ለሌላ፡አልሰጥም።
12፤ያዕቆብ፡ሆይ፥የጠራኹኽም፡እስራኤል፡ሆይ፥ስማኝ፤እኔ፡ነኝ፤እኔ፡ፊተኛው፡ነኝ፡እኔም፡ዃለኛው፡ነኝ።
13፤እጄም፡ምድርን፡መሥርታለች፡ቀኜም፡ሰማያትን፡ዘርግታለች፤በጠራዃቸው፡ጊዜ፡በአንድነት፡ይቆማሉ።
14፤እናንተ፡ዅሉ፥በአንድነት፡ተሰብስባችኹ፡ስሙ፤ከነርሱ፡ይህን፡የተናገረ፡ማን፡ነው፧እግዚአብሔር፡የወደደ ው፡ፈቃዱን፡በባቢሎን፡ላይ፡ያደርጋል፥ክንዱም፡በከለዳውያን፡ላይ፡ይኾናል።
15፤እኔ፡ራሴ፡ተናግሬያለኹ፤እኔ፡ጠርቼዋለኹ፤አምጥቼዋለኹ፥መንገዱም፡ትከናወንለታለች።
16፤ወደ፡እኔ፡ቅረቡ፡ይህንም፡ስሙ፤እኔ፡ከጥንት፡ዠምሬ፡በስውር፡አልተናገርኹም፤ከኾነበት፡ዘመን፡ዠምሮ፡እ ኔ፡በዚያ፡ነበርኹ፥አኹንም፡ጌታ፡እግዚአብሔርና፡መንፈሱ፡ልከውኛል።
17፤ታዳጊኽ፥የእስራኤል፡ቅዱስ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡የሚረባኽን፡ነገር፡የማስተምርኽ፡በምትኼ ድባትም፡መንገድ፡የምመራኽ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
18፤ትእዛዜን፡ብትሰማ፡ኖሮ፥ሰላምኽ፡እንደ፡ወንዝ፡ጽድቅኽም፡እንደ፡ባሕር፡ሞገድ፡በኾነ፡ነበር፤
19፤ዘርኽም፡እንደ፡አሸዋ፡የሆድኽም፡ትውልድ፡እንደምድር፡ትቢያ፡በኾነ፡ነበር፥ስሙም፡ከፊቴ፡ባልጠፋና፡ባል ፈረሰ፡ነበር።
20፤ከባቢሎን፡ውጡ፡ከከለዳውያንም፡ኰብልሉ፤በእልልታ፡ድምፅ፡ተናገሩ፡ይህንም፡ንገሩ፡እስከምድርም፡ዳርቻ፡ ድረስ፡አውሩና፦እግዚአብሔር፡ባሪያውን፡ያዕቆብን፡ታድጎታል፡በሉ።
21፤በምድረ፡በዳ፡በኩል፡በመራቸው፡ጊዜ፡አልተጠሙም፤ውሃንም፡ከአለቱ፡ውስጥ፡አፈለቀላቸው፥አለቱንም፡ሰነጠ ቀ፡ውሃውም፡ፈሰሰ።
22፤ለክፉዎች፡ሰላም፡የላቸውም፡ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡49።______________
ምዕራፍ፡49።
1፤ደሴቶች፡ሆይ፥ስሙኝ፥እናንተም፡በሩቅ፡ያላችኹ፡አሕዛብ፥አድምጡ፤እግዚአብሔር፡ከማሕፀን፡ጠርቶኛል፥ከእና ቴም፡ሆድ፡ዠምሮ፡ስሜን፡አንሥቷል፤
2፤አፌንም፡እንደ፡ተሳለ፡ሰይፍ፡አድርጓል፥በእጁ፡ጥላ፡ሰውሮኛል፤እንደ፡ተሳለ፡ፍላጻም፡አድርጎኛል፥በሰገባ ውም፡ውስጥ፡ሸሽጎኛል።
3፤ርሱም፦እስራኤል፡ሆይ፥አንተ፡ባሪያዬ፡ነኽ፡ባንተም፡እከበራለኹ፡አለኝ።
4፤እኔ፡ግን፦በከንቱ፡ደከምኹ፥ምንም፡ጥቅም፡ለሌለውና፡ለከንቱ፡ጕልበቴን፡ፈጀኹ፤ፍርዴ፡ግን፡በእግዚአብሔር ፡ዘንድ፥ዋጋዬም፡በአምላኬ፡ዘንድ፡ነው፡አልኹ።
5፤አኹንም፡በእግዚአብሔር፡ዐይን፡ከብሬያለኹና፥አምላኬም፡ጕልበት፡ኾኖኛልና፥ያዕቆብን፡ወደ፡ርሱ፡እንድመል ስ፡እስራኤልንም፡ወደ፡ርሱ፡እንድሰበስብ፡ባሪያ፡እኾነው፡ዘንድ፡ከማሕፀን፡ዠምሮ፡የሠራኝ፡እግዚአብሔር፡እ ንዲህ፡ይላል፦
6፤ርሱም፦የያዕቆብን፡ነገዶች፡እንድታስነሣ፡ከእስራኤልም፡የዳኑትን፡እንድትመስል፡ባሪያዬ፡ትኾን፡ዘንድ፡እ ጅግ፡ቀላል፡ነገር፡ነውና፥እስከምድር፡ዳር፡ድረስ፡መድኀኒት፡ትኾን፡ዘንድ፡ለአሕዛብ፡ብርሃን፡አድርጌ፡ሰጥ ቼኻለኹ፡ይላል።
7፤የእስራኤል፡ታዳጊ፡ቅዱሱም፥እግዚአብሔር፥ሰዎች፡ለሚንቁት፡ሕዝብም፡ለሚጠላው፡ለገዢዎች፡ባሪያ፡እንዲህ፡ ይላል፦ስለ፡ታማኙ፡ስለ፡እግዚአብሔር፥ስለ፡መረጠኽም፡ስለእስራኤል፡ቅዱስ፡ነገሥታት፡አይተው፡ይነሣሉ፥መሳ ፍንትም፡አይተው፡ይሰግዳሉ።
8፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በተወደደ፡ጊዜ፡ሰምቼኻለኹ፥በመድኀኒትም፡ቀን፡ረድቼኻለኹ፤እጠብቅኽማለኹ፥ ምድርንም፡ታቀና፡ዘንድ፥ውድማ፡የኾኑትንም፡ርስቶች፡ታወርስ፡ዘንድ፥
9፤የተጋዙትንም፦ውጡ፥በጨለማም፡የተቀመጡትን፦ተገለጡ፡ትል፡ዘንድ፥ቃል፡ኪዳን፡አድርጌ፡ለሕዝቡ፡ሰጥቼኻለኹ ።በመንገድም፡ላይ፡ይሰማራሉ፥ማሰማሪያቸውም፡በወና፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፡ይኾናል።
10፤የሚራራላቸውም፡ይመራቸዋልና፥በውሃም፡ምንጮች፡በኩል፡ይነዳቸዋልና፥አይራቡም፥አይጠሙም፥ትኵሳት፡ወይም ፡ፀሓይ፡አይጐዳቸውም።
11፤ተራራዎቼንም፡ዅሉ፡መንገድ፡አደርጋለኹ፥ጐዳኖቼም፡ከፍ፡ከፍ፡ይላሉ።
12፤እንሆ፥እነዚህ፡ከሩቅ፥እንሆም፥እነዚህ፡ከሰሜንንና፡ከምዕራብ፥እነዚህም፡ከሢኒም፡አገር፡ይመጣሉ።
13፤እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡አጽናንቷልና፥ለችግረኛዎቹም፡ራርቷልና፥ሰማያት፡ሆይ፥ዘምሩ፥ምድር፡ሆይ፥ደስ፡ይ በልሽ፡ተራራዎችም፡ሆይ፥እልል፡በሉ።
14፤ጽዮን፡ግን፦እግዚአብሔር፡ትቶኛል፡ጌታም፡ረስቶኛል፡አለች።
15፤በእውኑ፡ሴት፡ከማሕፀኗ፡ለተወለደው፡ልጅ፡እስከማትራራ፡ድረስ፡ሕፃኗን፡ትረሳ፡ዘንድ፡ትችላለችን፧አዎን ፥ርሷ፡ትረሳ፡ይኾናል፥እኔ፡ግን፡አልረሳሽም።
16፤እንሆ፥እኔ፡በእጄ፡መጻፍ፡ቀርጬሻለኹ፥ቅጥሮችሽም፡ዅልጊዜ፡በፊቴ፡አሉ።
17፤ልጆችሽ፡ይፈጥናሉ፤ያፈረሱሽና፡ያወደሙሽ፡ከአንቺ፡ዘንድ፡ይወጣሉ።
18፤ዐይንሽን፡አንሥተሽ፡በዙሪያሽ፡ተመልከቺ፤እነዚህ፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ወደ፡አንቺ፡ይመጣሉ።እኔ፡ሕያው፡ነ ኝና፡እነዚህን፡ዅሉ፡እንደ፡ጌጥ፡ትለብሻቸዋለሽ፥እንደ፡ሙሽራም፡ትጐናጸፊአቸዋለሽ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
19፤ባድማሽና፡ውድማሽ፡ወናም፡የኾነው፡ምድርሽ፡ከሚኖሩብሽ፡የተነሣ፡ዛሬ፡ጠባብ፡ትኾናለችና፥የዋጡሽም፡ይር ቃሉና።
20፤የወላድ፡መካን፡ከኾንሽ፡በዃላ፡የተወለዱልሽ፡ልጆችሽ፡በዦሮሽ፦ስፍራ፡ጠቦ፟ኛልና፥እቀመጥ፡ዘንድ፡ቦታ፡ አስፊልኝ፡ይላሉ።
21፤አንቺም፡በልብሽ፥የወላድ፡መካን፡ኾኛለኹና፥እኔም፡ብቻዬን፡ተሰድጃለኹና፡ተቅበዝብዣለኹምና፡እነዚህን፡ ማን፡ወለደልኝ፧እነዚህንስ፡ማን፡አሳደጋቸው፧እንሆ፥ብቻዬን፡ቀርቼ፡ነበር፤እነዚህስ፡ወዴት፡ነበሩ፧ትያለሽ ።
22፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እጄን፡ወደ፡አሕዛብ፡አነሣለኹ፥ዓላማዬንም፡ወደ፡ወገኖች፡አቆ ማለኹ፤ወንዶች፡ልጆችሽንም፡በብብታቸው፡ያመጧቸዋል፥ሴቶች፡ልጆችሽንም፡በጫንቃቸው፡ላይ፡ይሸከሟቸዋል።
23፤ነገሥታትም፡አሳዳጊ፡አባቶችሽ፡ይኾናሉ፥እቴጌዎቻቸውም፡ሞግዚቶችሽ፡ይኾናሉ፤ግንባራቸውንም፡ወደ፡ምድር ፡ዝቅ፡አድርገው፡ይሰግዱልሻል፥የእግርሽንም፡ትቢያ፡ይልሳሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቂያለሽ ፥እኔንም፡በመተማመን፡የሚጠባበቁ፡አያፍሩም።
24፤በእውኑ፡ብዝበዛ፡ከኀያል፡እጅ፡ይወሰዳልን፧ወይስ፡የጨካኙ፡ምርኮኛዎች፡ያመልጣሉን፧
25፤እግዚአብሔር፡ግን፡እንዲህ፡ይላል፦በኀያላን፡የተማረኩ፡ይወሰዳሉ፥የጨካኞችም፡ብዝበዛ፡ያመልጣል፤ከአን ቺ፡ጋራ፡የሚጣሉትን፡እጣላቸዋለኹ፥ልጆችሽንም፡አድናለኹ።
26፤አስጨናቂዎችሽንም፡ሥጋቸውን፡አስበላቸዋለኹ፥እንደ፡ጣፋጭም፡ወይን፡ጠጅ፡ደማቸውን፡ጠጥተው፡ይሰክራሉ፤ ሥጋ፡ለባሹም፡ዅሉ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡መድኀኒትሽና፡ታዳጊሽ፥የያዕቆብ፡ኀያል፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡50።______________
ምዕራፍ፡50።
1፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናታችኹን፡የፈታኹበት፡የፍቿ፡ጽሕፈት፡የት፡አለ፧ወይስ፡እናንተን፡የሸጥኹ ፡ከአበዳሪዎች፡ለየትኛው፡ነው፧እንሆ፥ስለ፡ኀጢአታችኹ፡ተሽጣችዃል፥ስለ፡በደላችኹም፡እናታችኹ፡ተፈታ፟ለች ።
2፤በመጣኹስ፡ጊዜ፡ሰው፡ስለ፡ምን፡አልነበረም፧በጠራኹስ፡ጊዜ፡የሚመልስ፡ስለ፡ምን፡አልነበረም፧መታደግ፡እን ዳትችል፡እጄ፡ዐጪር፡ኾናለችን፧ወይስ፡ለማዳን፡ኀይል፡የለኝምን፧እንሆ፥በገሠጽኹ፡ጊዜ፡ባሕርን፡አደርቃለኹ ፥ወንዞችንም፡ምድረ፡በዳ፡አደርጋቸዋለኹ፤ውሃም፡በማጣት፡ዓሣዎቻቸው፡ይገማሉ፡በጥማትም፡ይሞታሉ።
3፤ሰማያትን፡ጥቍረት፡አለብሳቸዋለኹ፥መጋረጃቸውንም፡ማቅ፡አደርጋለኹ።
4፤የደከመውን፡በቃል፡እንዴት፡እንደምደግፍ፡ዐውቅ፡ዘንድ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የተማሩትን፡ምላስ፡ሰጥቶኛል፡ ማለዳ፡ማለዳ፡ያነቃኛል፥እንደ፡ተማሪዎችም፡ትሰማ፡ዘንድ፡ዦሮዬን፡ያነቃቃል።
5፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ዦሮዬን፡ከፍቷል፥እኔም፡ዐመፀኛ፡አልነበርኹም፡ወደ፡ዃላዬም፡አልተመለስኹም።
6፤ዠርባዬን፡ለገራፊዎች፡ጕንጬንም፡ለጠጕር፡ነጪዎች፡ሰጠኹ፥ፊቴንም፡ከውርደትና፡ከትፋት፡አልመለስኹም።
7፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይረዳኛልና፥ስለዚህ፡አልታወክኹም፤ስለዚህም፡ፊቴን፡እንደ፡ባልጩት፡ድንጋይ፡አድርጌዋ ለኹ፥እንዳላፍርም፡ዐውቃለኹ።
8፤የሚያጸድቀኝ፡ቅርብ፡ነው፤ከእኔስ፡ጋራ፡የሚከራከር፡ማን፡ነው፧በአንድነት፡እንቁም፤የሚከራከረኝ፡ማን፡ነ ው፧ወደ፡እኔ፡ይቅረብ።
9፤እንሆ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይረዳኛል፤ማን፡ይፈርድብኛል፧እንሆ፥ዅሉ፡እንደ፡ልብስ፡ያረጃሉ፡ብልም፡ይበላቸ ዋል።
10፤ከእናንተ፡እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፥የባሪያውንም፡ቃል፡የሚሰማ፥በጨለማም፡የሚኼድ፥ብርሃንም፡የሌለው፥ነ ገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ስም፡የሚታመን፥በአምላኩም፡የሚደገፍ፡ማን፡ነው፧
11፤እንሆ፥እሳት፡የምታነዱ፟፡የእሳትንም፡ወላፈን፡የምትታጠቁ፡ዅላችኹ፥በእሳታችኹ፡ነበልባል፡ባነደዳችኹት ም፡ወላፈን፡ኺዱ፤ይህ፡ከእጄ፡ይኾንባችዃል፤በሐዘን፡ትተኛላችኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡51።______________
ምዕራፍ፡51።
1፤እናንተ፡ጽድቅን፡የምትከተሉ፡እግዚአብሔርንም፡የምትሹ፥ስሙኝ፤ከርሱ፡የተቈረጣችኹበትን፡ድንጋይ፡ከርሱም ፡የተቈፈራችኹበትን፡ጕድጓድ፡ተመልከቱ።
2፤ወደ፡አባታችኹ፡ወደ፡አብርሃም፥ወደ፡ወለደቻችኹም፡ወደ፡ሳራ፡ተመልከቱ፤አንድ፡ብቻውን፡በኾነ፡ጊዜ፡ጠራኹ ት፥ባረክኹትም፥አበዛኹትም።
3፤እግዚአብሔርም፡ጽዮንን፡ያጽናናል፤በርሷም፡ባድማ፡የኾነውን፡ዅሉ፡ያጽናናል፥ምድረ፡በዳዋንም፡እንደ፡ዔዴ ን፡በረሓዋንም፡እንደእግዚአብሔር፡ገነት፡ያደርጋል፤ደስታና፡ተድላ፡ምስጋናና፡የዝማሬ፡ድምፅ፡ይገኝበታል።
4፤ወገኔ፡ሆይ፥አድምጠኝ፤ሕዝቤ፡ሆይ፥ስማኝ፤ሕግ፡ከእኔ፡ይወጣልና፥ፍርዴም፡ለአሕዛብ፡ብርሃን፡ይኾናልና።
5፤ጽድቄ፡ፈጥኖ፡ቀርቧል፥ማዳኔም፡ወጥቷል፥ክንዴም፡በአሕዛብ፡ላይ፡ይፈርዳል፤ደሴቶች፡እኔን፡በመተማመን፡ይ ጠባበቃሉ፥በክንዴም፡ይታመናሉ።
6፤ዐይናችኹን፡ወደ፡ሰማይ፡አንሡ፥ወደ፡ታችም፡ወደ፡ምድር፡ተመልከቱ፤ሰማያት፡እንደ፡ጢስ፡በነ፟ው፡ይጠፋሉ፥ ምድርም፡እንደ፡ልብስ፡ታረጃለች፥የሚኖሩባትም፡እንዲሁ፡ይሞታሉ፤ማዳኔ፡ግን፡ለዘለዓለም፡ይኾናል፥ጽድቄም፡ አይፈርስም።
7፤ጽድቅን፡የምታውቁ፡ሕጌም፡በልባችኹ፡ያለ፡ሕዝብ፡ሆይ፥ስሙኝ፤የሰውን፡ተግዳሮት፡አትፍሩ፥በስድባቸውም፡አ ትደንግጡ።
8፤እንደ፡ልብስም፡ብል፡ይበላቸዋል፥እንደ፡በግ፡ጠጕርም፡ትል፡ይበላቸዋል፤ጽድቄ፡ግን፡ለዘለዓለም፡ማዳኔም፡ ለትውልድ፡ዅሉ፡ይኾናል።
9፤የእግዚአብሔር፡ክንድ፡ሆይ፥ተነሥ፥ተነሥ፥ኀይልንም፡ልበስ፤በቀድሞው፡ወራትና፡በጥንቱ፡ዘመን፡በነበረው፡ ትውልድ፡እንደኾነው፡ተነሥ።ረዓብን፡የቈራረጥኽ፡ዘንዶውንም፡የወጋኽ፡አንተ፡አይደለኽምን፧
10፤ባሕሩንና፡የታላቁን፡ጥልቅ፡ውሃ፡ያደረቅኸው፥የዳኑትም፡ይሻገሩ፡ዘንድ፡ጠሊቁን፡ባሕር፡መንገድ፡ያደረግ ኽ፡አንተ፡አይደለኽምን፧
11፤እግዚአብሔርም፡የተቤዣቸው፡ይመለሳሉ፡ወደ፡ጽዮንም፡ይመጣሉ፤የዘለዓለምም፡ደስታ፡በራሳቸው፡ላይ፡ይኾና ል፤ደስታንና፡ተድላን፡ያገኛሉ፥ሐዘንና፡ልቅሶም፡ይሸሻል።
12፤የማጽናናችኹ፡እኔ፡ነኝ፥እኔ፡ነኝ፤የሚሞተውን፡ሰው፡እንደ፡ሣርም፡የሚጠወልገውን፡የሰው፡ልጅ፡ትፈራ፡ዘ ንድ፡አንተ፡ማን፡ነኽ፧
13፤ሰማያትንም፡የዘረጋው፡ምድርንም፡የመሠረተውን፡ፈጣሪኽን፡እግዚአብሔርን፡ረስተኻል፤ያጠፋ፡ዘንድ፡ባዘጋ ጀ፡ጊዜ፡ካስጨናቂው፡ቍጣ፡የተነሣ፡ዅልጊዜ፡ቀኑን፡ዅሉ፡ፈርተኻል፤የአስጨናቂው፡ቍጣ፡የት፡አለ፧
14፤ምርኮኛ፡ፈጥኖ፡ይፈታል፤አይሞትም፡ወደ፡ጕድጓድም፡አይወርድም፥እንጀራም፡አይጐድልበትም።
15፤ሞገዱም፡እንዲተም፟፡ባሕርን፡የማናውጥ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ፥ስሜም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚ አብሔር፡ነው።
16፤ሰማያትን፡እዘረጋ፡ዘንድ፡ምድርንም፡እመሠርት፡ዘንድ፥ጽዮንንም፦አንቺ፡ሕዝቤ፡ነሽ፡እል፡ዘንድ፡ቃሌን፡ በአፍኽ፡አድርጌያለኹ፥በእጄም፡ጥላ፡ጋርጄኻለኹ።
17፤ከእግዚአብሔር፡እጅ፡የቍጣውን፡ጽዋ፡የጠጣሽ፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ንቂ፥ንቂ፥ቁሚ፤የሚያንገደግድን፡ዋንጫ፡ ጠጥተሻል፡ጨልጠሽውማል።
18፤ከወለደቻቸው፡ልጆች፡ዅሉ፡የሚመራት፡የለም፥ካሳደገቻቸውም፡ልጆች፡ዅሉ፡እጇን፡የሚይዝ፡የለም።
19፤እነዚህ፡ኹለት፡ነገሮች፡ኾነውብሻል፥ማንስ፡ያስተዛዝንሻል፧መፈታትና፡ጥፋት፡ራብና፡ሰይፍ፡ናቸው፤እንዴ ትስ፡አድርጌ፡አጽናናሻለኹ፧
20፤ልጆችሽ፡ዝለዋል፤በወጥመድ፡እንደተያዘ፡ሚዳቋ፡በአደባባይ፡ዅሉ፡ራስ፡ላይ፡ተኝተዋል፤በእግዚአብሔር፡ቍ ጣና፡በአምላክሽ፡ተግሣጽ፡ተሞልተዋል።
21፤ስለዚህም፡ያለወይን፡ጠጅ፡የሰከርሽ፡አንቺ፡ችግረኛ፥ይህን፡ስሚ፤
22፤ስለ፡ወገኑ፡የሚሟገት፡አምላክሽ፡ጌታሽ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የሚያንገደግድን፡ጽዋ፡የቍ ጣዬንም፡ዋንጫ፡ከእጅሽ፡ወስጃለኹ፤ደግመሽም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አትጠጪውም።
23፤ነፍስሽንም፦እንሻገር፡ዘንድ፡ዝቅ፡በዪ፡በሚሏት፡በአስጨናቂዎችሽ፡እጅ፡አኖረዋለኹ፤ዠርባሽንም፡ለሚሻገ ሩት፡እንደ፡መሬትና፡እንደ፡መንገድ፡አደረግሽላቸው።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡52።______________
ምዕራፍ፡52።
1፤ጽዮን፡ሆይ፥ተነሺ፥ተነሺ፥ኀይልሽን፡ልበሺ፤ቅድስቲቱ፡ከተማ፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ያልተገረዘና፡ርኩስ፡ከእን ግዲህ፡ወዲህ፡አይገባብሽምና፡ጌጠኛ፡ልብስሽን፡ልበሺ።
2፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ትቢያን፡አራግፊ፤ተነሺ፥ተቀመጪ፤ምርኮኛዪቱ፡የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥የዐንገትሽን፡እስራት፡ ፍቺ።
3፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በከንቱ፡ተሽጣችኹ፡ነበር፥ያለገንዘብም፡ትቤዣላችኹ።
4፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወገኔ፡በዚያ፡እንግዳ፡ኾኖ፡ይቀመጥ፡ዘንድ፡አስቀድሞ፡ወደ፡ግብጽ፡ወረ ደ፥አሶርም፡ያለምክንያት፡በደለው።
5፤ወገኔ፡በከንቱ፡ተወስዷልና፥አኹን፡ከዚህ፡ምን፡አለኝ፧ይላል፡እግዚአብሔር፤የሚገዟቸው፡ይጮኻሉ፥ይላል፡እ ግዚአብሔር፥ስሜም፡ዅልጊዜ፡ቀኑን፡ዅሉ፡ይሰደባል።
6፤ስለዚህ፥ወገኔ፡ስሜን፡ያውቃል፥ስለዚህም፡የምናገር፡እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡በዚያ፡ቀን፡ያውቃሉ፤እንሆ፥እኔ፡ ነኝ።
7፤የምሥራች፡የሚናገር፥ሰላምንም፡የሚያወራ፥የመልካምንም፡ወሬ፡የምሥራች፡የሚናገር፥መድኀኒትንም፡የሚያወራ ፥ጽዮንንም፦አምላክሽ፡ነግሧል፡የሚል፡ሰው፡እግሩ፡በተራራዎች፡ላይ፡እጅግ፡ያማረ፡ነው።
8፤እንሆ፥ጕበኛዎችሽ፡ጮኸዋል፤እግዚአብሔር፡ወደ፡ጽዮን፡በተመለሰ፡ጊዜ፡ዐይን፡በዐይን፡ይተያያሉና፡ድምፃቸ ውን፡ያነሣሉ፥በአንድነትም፡ይዘምራሉ።
9፤እናንተ፡የኢየሩሳሌም፡ፍርስራሾች፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡አጽናንቷልና፥ኢየሩሳሌምንም፡ታድጓልና፥ደ ስ፡ይበላችኹ፥በአንድነትም፡ዘምሩ።
10፤እግዚአብሔር፡የተቀደሰውን፡ክንዱን፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ፊት፡ገልጧል፥በምድር፡ዳርቻ፡የሚኖሩትም፡ዅሉ፡የአ ምላካችንን፡መድኀኒት፡ያያሉ።
11፤እናንተ፡የእግዚአብሔር፡ዕቃ፡የምትሸከሙ፡ሆይ፥እልፍ፡በሉ፥እልፍ፡በሉ፥ከዚያ፡ውጡ፥ርኩስን፡ነገር፡አት ንኩ፥ከመካከሏ፡ውጡ፥ንጹሓን፡ኹኑ።
12፤እግዚአብሔር፡ይቀድማችዃልና፥የእስራኤልም፡አምላክ፡ይከተላችዃልና፥በችኰላ፡አትወጡም፡በመኰብለልም፡አ ትኼዱም።
13፤እንሆ፥ባሪያዬ፡በማስተዋል፡ያደርጋል፤ይከብራል፡ከፍ፡ከፍም፡ይላል፥እጅግ፡ታላቅም፡ይኾናል።
14፤ፊቱ፡ከሰዎች፡ዅሉ፡ይልቅ፥መልኩም፡ከሰዎች፡ልጆች፡ይልቅ፡ተጐሳቍሏልና፥ብዙ፡ሰዎች፡ስለ፡አንተ፡እንደ፡ ተደነቁ፥እንዲሁ፡ብዙ፡አሕዛብን፡ያስደንቃል፤
15፤ያልተነገረላቸውንም፡ያያሉና፥ያልሰሙትንም፡ያስተውላሉና፡ነገሥታት፡ስለ፡ርሱ፡አፋቸውን፡ይዘጋሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡53።______________
ምዕራፍ፡53።
1፤የሰማነውን፡ነገር፡ማን፡አምኗል፧የእግዚአብሔርስ፡ክንድ፡ለማን፡ተገልጧል፧
2፤በፊቱ፡እንደ፡ቡቃያ፡ከደረቅም፡መሬት፡እንደ፡ሥር፡አድጓል።መልክና፡ውበት፡የለውም፥ባየነውም፡ጊዜ፡እንወ ደ፟ው፡ዘንድ፡ደም፡ግባት፡የለውም።
3፤የተናቀ፡ከሰውም፡የተጠላ፥የሕማም፡ሰው፡ደዌንም፡የሚያውቅ፡ነው፤ሰውም፡ፊቱን፡እንደሚሰውርበት፡የተናቀ፡ ነው፥እኛም፡አላከበርነውም።
4፤በእውነት፡ደዌያችንን፡ተቀበለ፡ሕመማችንንም፡ተሸክሟል፤እኛ፡ግን፡እንደ፡ተመታ፡በእግዚአብሔርም፡እንደ፡ ተቀሠፈ፡እንደ፡ተቸገረም፡ቈጠርነው።
5፤ርሱ፡ግን፡ስለ፡መተላለፋችን፡ቈሰለ፥ስለ፡በደላችንም፡ደቀቀ፤የደኅንነታችንም፡ተግሣጽ፡በርሱ፡ላይ፡ነበረ ፥በርሱም፡ቍስል፡እኛ፡ተፈወስን።
6፤እኛ፡ዅላችን፡እንደ፡በጎች፡ተቅበዝብዘን፡ጠፋን፤ከእኛ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ገዛ፡መንገዱ፡አዘነበለ፤እግዚአ ብሔርም፡የዅላችንን፡በደል፡በርሱ፡ላይ፡አኖረ።
7፤ተጨነቀ፡ተሣቀየም፡አፉንም፡አልከፈተም፤ለመታረድ፡እንደሚነዳ፡ጠቦት፥በሸላቾቹም፡ፊት፡ዝም፡እንደሚል፡በ ግ፥እንዲሁ፡አፉን፡አልከፈተም።
8፤በማስጨነቅና፡በፍርድ፡ተወሰደ፤ስለሕዝቤ፡ኀጢአት፡ተመቶ፟፡ከሕያዋን፡ምድር፡እንደ፡ተወገደ፡ከትውልዱ፡ማ ን፡አስተዋለ፧
9፤ከክፉዎችም፡ጋራ፡መቃብሩን፡አደረጉ፥ከባለጠጋዎችም፡ጋራ፡በሞቱ፡ኾኖም፡ግፍን፡አላደረገም፡ነበር፥በአፉም ፡ተንኰል፡አልተገንበትም፡ነበር።
10፤እግዚአብሔርም፡በደዌ፡ያደቀ፟ው፡ዘንድ፡ፈቀደ፤ነፍሱን፡ስለ፡ኀጢአት፡መሥዋዕት፡ካደረገ፡በዃላ፡ዘሩን፡ ያያል፥ዕድሜውም፡ይረዝማል፥የእግዚአብሔርም፡ፈቃድ፡በእጁ፡ይከናወናል።
11፤ከነፍሱ፡ድካም፡ብርሃን፡ያያል፡ደስም፡ይለዋል፤ጻድቅ፡ባሪያዬም፡በዕውቀቱ፡ብዙ፡ሰዎችን፡ያጸድቃል፥ኀጢ አታቸውን፡ይሰከማል።
12፤ስለዚህም፡ርሱ፡ብዙዎችን፡ይወርሳል፥ከኀያላንም፡ጋራ፡ምርኮን፡ይከፋፈላል፤ነፍሱን፡ለሞት፡አሳልፎ፡ሰጥ ቷልና፥ከዐመፀኛዎችም፡ጋራ፡ተቈጥሯልና፤ርሱ፡ግን፡የብዙ፡ሰዎችን፡ኀጢአት፡ተሸከመ፥ስለ፡ዐመፀኛዎችም፡ማለ ደ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡54።______________
ምዕራፍ፡54።
1፤አንቺ፡ያልወለድሽ፡መካን፡ሆይ፥ዘምሪ፤አንቺ፡ያላማጥሽ፡ሆይ፥እልል፡በዪ፥ጩኺም፤ባል፡ካላት፡ይልቅ፡ፈት፡ የኾነቺቱ፡ልጆች፡በዝተዋልና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
2፤የድንኳንሽን፡ስፍራ፡አስፊ፥መጋረጃዎችሽንም፡ይዘርጉ፤አትቈጥቢ፤አውታሮችሽን፡አስረዝሚ፡ካስማዎችሽንም፡ አጽኚ።
3፤በቀኝና፡በግራ፡ትሰፋፊያለሽና፥ዘርሽም፡አሕዛብን፡ይወርሳልና፥የፈረሱትንም፡ከተማዎች፡መኖሪያ፡ያደርጋል ና።
4፤አታፍሪምና፡አትፍሪ፤አትዋረጂምና፡አትደንግጪ፤የሕፃንነትሽንም፡ዕፍረት፡ትረሺዋለሽ፥የመበለትነትሽንም፡ ስድብ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታስቢም።
5፤ፈጣሪሽ፡ባልሽ፡ነው፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው፤የእስራኤልም፡ቅዱስ፡ታዳጊሽ፡ነው፥ርሱም፡ የምድር፡ዅሉ፡አምላክ፡ይባላል።
6፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ተተወችና፡እንደ፡ተበሳጨች፡በልጅነቷም፡እንደ፡ተጣለች፡ሚስት፡ጠርቶሻል፥ይላል፡አም ላክሽ።
7፤ጥቂት፡ጊዜ፡ተውኹሽ፥በታላቅም፡ምሕረት፡እሰበስብሻለኹ።
8፤በጥቂት፡ቍጣ፡ለቅጽበት፡ዐይን፡ፊቴን፡ከአንቺ፡ሰወርኹ፥በዘለዓለምም፡ቸርነት፡እምርሻለኹ፥ይላል፡ታዳጊሽ ፡እግዚአብሔር።
9፤ይህ፡ለእኔ፡እንደ፡ኖኅ፡ውሃ፡ነው፤የኖኅ፡ውሃ፡ደግሞ፡በምድር፡ላይ፡እንዳያልፍ፡እንደ፡ማልኹ፥እንዲሁ፡አ ንቺን፡እንዳልቈጣ፡እንዳልዘልፍሽም፡ምያለኹ።
10፤ተራራዎች፡ይፈልሳሉ፥ኰረብታዎችም፡ይወገዳሉ፤ቸርነቴ፡ግን፡ከአንቺ፡ዘንድ፡አይፈልስም፡የሰላሜም፡ቃል፡ ኪዳን፡አይወገድም፥ይላል፡መሓሪሽ፡እግዚአብሔር።
11፤አንቺ፡የተቸገርሽ፡በዐውል፡ነፋስም፡የተናወጥሽ፡ያልተጽናናሽም፥እንሆ፥ድንጋዮችሽን፡ሸላልሜ፡እገነባለ ኹ፥በሰንፔርም፡እመሠርትሻለኹ።
12፤የግንብሽንም፡ጕልላት፡በቀይ፡ዕንቍ፥በሮችሽንም፡በሚያብረቀርቅ፡ዕንቍ፥ዳርቻሽንም፡ዅሉ፡በከበሩ፡ድንጋ ዮች፡እሠራለኹ።
13፤ልጆችሽም፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡የተማሩ፡ይኾናሉ፥የልጆችሽም፡ሰላም፡ብዙ፡ይኾናል።
14፤በጽድቅ፡ትታነጺ᎗ያለሽ፤ከግፍ፡ራቂ፥አትፈሪምም፥ድንጋጤም፡ወደ፡አንቺ፡አትቀርብም።
15፤እንሆ፥ይሰበሰባሉ፥ነገር፡ግን፥ከእኔ፡ዘንድ፡አይኾንም፤ባንቺም፡ላይ፡የሚሰበሰቡ፡ዅሉ፡ከአንቺ፡የተነሣ ፡ይወድቃሉ።
16፤እንሆ፥ፍሙን፡በወናፍ፡የሚያናፋ፡ለሥራውም፡መሣሪያ፡የሚያወጣ፡ብረት፡ሠሪን፡እኔ፡ፈጥሬያለኹ፤የሚያፈር ሰውንም፡እንዲያጠፋ፡ፈጥሬያለኹ።
17፤ባንቺ፡ላይ፡የተሠራ፡መሣሪያ፡ዅሉ፡አይከናወንም፤በፍርድም፡በሚነሣብሽ፡ምላስ፡ዅሉ፡ትፈርጂበታለሽ።የእ ግዚአብሔር፡ባሪያዎች፡ርስት፡ይህ፡ነው፥ጽድቃቸውም፡ከእኔ፡ዘንድ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡55።______________
ምዕራፍ፡55።
1፤እናንተ፡የተጠማችኹ፡ዅሉ፥ወደ፡ውሃ፡ኑ፥ገንዘብም፡የሌላችኹ፡ኑና፡ግዙ፡ብሉም፤ኑ፡ያለገንዘብም፡ያለዋጋም ፡የወይን፡ጠጅና፡ወተት፡ግዙ።
2፤ገንዘብን፡እንጀራ፡ላይደለ፥የድካማችኹንም፡ዋጋ፡ለማያጠግብ፡ነገር፡ለምን፡ትመዝናላችኹ፧አድምጡኝ፥በረከ ትንም፡ብሉ፥ሰውነታችኹም፡በጮማ፡ደስ፡ይበለው።
3፤ዦሯችኹን፡አዘንብሉ፡ወደ፡እኔም፡ቅረቡ፤ስሙ፡ሰውነታችኹም፡በሕይወት፡ትኖራለች፤የታመነችዪቱን፡የዳዊትን ፡ምሕረት፥የዘለዓለምን፡ቃል፡ኪዳን፡ከእናንተ፡ጋራ፡አደርጋለኹ።
4፤እንሆ፥ለአሕዛብ፡ምስክር፥ለወገኖችም፡አለቃና፡አዛዥ፡እንዲኾን፡ሰጥቼዋለኹ።
5፤እንሆ፥የማታውቀውን፡ሕዝብ፡ትጠራለኽ፥የእስራኤልም፡ቅዱስ፡አክብሮኻልና፥ስለ፡አምላክኽ፡ስለ፡እግዚአብሔ ር፡የማያውቁኽ፡ሕዝብ፡ወዳንተ፡ይሮጣሉ።
6፤እግዚአብሔር፡በሚገኝበት፡ጊዜ፡ፈልጉት፥ቀርቦም፡ሳለ፡ጥሩት፤
7፤ክፉ፡ሰው፡መንገዱን፡በደለኛም፡ዐሳቡን፡ይተው፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ይመለስ፡ርሱም፡ይምረዋል፥ይቅርታውም ፡ብዙ፡ነውና፥ወደ፡አምላካችን፡ይመለስ።
8፤ዐሳቤ፡እንደ፡ዐሳባችኹ፡መንገዳችኹም፡እንደ፡መንገዴ፡አይደለምና፡ይላል፡እግዚአብሔር።
9፤ሰማይ፡ከምድር፡ከፍ፡እንደሚል፥እንዲሁ፡መንገዴ፡ከመንገዳችኹ፡ዐሳቤም፡ከዐሳባችኹ፡ከፍ፡ያለ፡ነው።
10፤ዝናብና፡በረዶ፡ከሰማይ፡እንደሚወርድ፥ምድርን፡እንደሚያረካት፥ታበቅልና፡ታፈራም፡ዘንድ፡እንደሚያደርጋ ት፥ዘርንም፡ለሚዘራ፡እንጀራንም፡ለሚበላ፡እንደሚሰጥ፡እንጂ፡ወደ፡ሰማይ፡እንደማይመለስ፥
11፤ከአፌ፡የሚወጣ፡ቃሌ፡እንዲሁ፡ይኾናል፤የምሻውን፡ያደርጋል፡የላክኹትንም፡ይፈጽማል፡እንጂ፡ወደ፡እኔ፡በ ከንቱ፡አይመለስም።
12፤እናንተም፡በደስታ፡ትወጣላችኹ፡በሰላምም፡ትሸኛላችኹ፤ተራራዎችና፡ኰረብታዎች፡በፊታችኹ፡እልልታ፡ያደር ጋሉ፥የሜዳም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ያጨበጭባሉ።
13፤በሾኽም፡ፋንታ፡ጥድ፡በኵርንችትም፡ፋንታ፡ባርሰነት፡ይበቅላል፤ለእግዚአብሔርም፡መታሰቢያን፡ለዘለዓለም ም፡የማይጠፋ፥ምልክት፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡56።______________
ምዕራፍ፡56።
1፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ማዳኔ፡ሊመጣ፡ጽድቄም፡ሊገለጥ፡ቀርቧልና፥ፍርድን፡ጠብቁ፡ጽድቅንም፡አድርጉ ።
2፤ይህን፡የሚያደርግ፡ሰው፡ይህንንም፡የሚይዝ፡የሰው፡ልጅ፥እንዳያረክሰው፡ሰንበትንም፡የሚጠብቅ፡እጁንም፡ክ ፋት፡ከማድረግ፡የሚጠብቅ፡ብፁዕ፡ነው።
3፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡የተጠጋ፡መጻተኛ፦በእውነት፡እግዚአብሔር፡ከሕዝቡ፡ይለየኛል፡አይበል፤ጃን፡ደረባም፦ እንሆ፥እኔ፡ደረቅ፡ዛፍ፡ነኝ፡አይበል።
4፤እግዚአብሔር፡ሰንበቴን፡ስለሚጠብቁ፡ደስ፡የሚያሠኘኝንም፡ነገር፡ስለሚመርጡ፡ቃል፡ኪዳኔንም፡ስለሚይዙ፡ጃ ን፡ደረባዎች፡እንዲህ፡ይላልና፦
5፤በቤቴና፡በቅጥሬ፡ውስጥ፡ከወንዶችና፡ከሴቶች፡ልጆች፡ይልቅ፡የሚበልጥ፡መታሰቢያና፡ስም፡እሰጣቸዋለኹ፤የማ ይጠፋም፡የዘለዓለም፡ስም፡እሰጣቸዋለኹ።
6፤ያገለግሉት፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርንም፡ስም፡ይወዱ፡ዘንድ፡ባሪያዎቹም፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡የ ሚጠጉትንም፡መጻተኛዎች፥እንዳያረክሱት፡ሰንበትን፡የሚጠብቁትን፡ቃል፡ኪዳኔንም፡የሚይዙትን፡ዅሉ፥
7፤ወደተቀደሰ፡ተራራዬ፡አመጣቸዋለኹ፥በጸሎቴም፡ቤት፡ደስ፡አሠኛቸዋለኹ፤ቤቴ፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡የሚኾን፡የጸሎ ት፡ቤት፡ይባላልና፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታቸውንና፡ሌላ፡መሥዋዕታቸውን፡በመሠዊያዬ፡ላይ፡እቀበላለኹ።
8፤ከእስራኤል፡የተበተኑትን፡የሚሰበስብ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦ወደተሰበሰቡት፡ዘንድ፡ሌላዎችን፡እሰበስብለታለ ኹ፡ይላል።
9፤እናንተ፡የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ዅሉ፥እናንተም፡የዱር፡አራዊት፡ዅሉ፥ትበሉ፡ዘንድ፡ቅረቡ።
10፤ጕበኛዎቹ፡ዕውሮች፡ናቸው፥ዅሉ፡ያለዕውቀት፡ናቸው፤ዅሉም፡ዲዳ፡የኾኑ፡ውሻዎች፡ናቸው፡ይጮኹም፡ዘንድ፡አ ይችሉም፤ሕልምን፡ያልማሉ፤ይተኛሉ፤ማንቀላፋትንም፡ይወዳ፟ሉ።
11፤መብል፡ወዳጆች፡ከቶ፡የማይጠግቡ፡ውሻዎች፡ናቸው፥እነርሱም፡ያስተውሉ፡ዘንድ፡የማይችሉ፡እረኛዎች፡ናቸው ፤ዅሉ፡ወደ፡መንገዳቸው፥ከፊተኛው፡እስከ፡ዃለኛው፡ድረስ፡ዅሉ፥እያንዳንዳቸው፡ወደ፡ጥቅማቸው፡ዘወር፡ብለዋ ል።
12፤ኑ፡የወይን፡ጠጅ፡እንውሰድ፥በሚያሰክርም፡መጠጥ፡እንርካ፤ዛሬም፡እንደ፡ኾነ፡እንዲሁ፡ነገ፡ይኾናል፥ከዛ ሬም፡ይልቅ፡እጅግ፡ይበልጣል፡ይላሉ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡57።______________
ምዕራፍ፡57።
1፤ጻድቅ፡ይሞታል፥በልቡም፡ነገሩን፡የሚያኖር፡የለም፤ምሕረተኛዎችም፡ይወገዳሉ፥ጽድቅም፡ከክፋት፡ፊት፡እንደ ፡ተወገደ፡ማንም፡አያስተውልም።
2፤ወደ፡ሰላም፡ይገባል፤በቅንነት፡የኼደ፡በዐልጋው፡ላይ፡ያርፋል።
3፤እናንተ፡የአስማተኛዪቱ፡ልጆች፥የአመንዝራውና፡የጋለሞታዪቱ፡ዘር፥ወደዚህ፡ቅረቡ።
4፤በማን፡ታላግጣላችኹ፧በማንስ፡ላይ፡አፋችኹን፡ታላቅቃላችኹ፧ምላሳችኹንስ፡በማን፡ላይ፡ታስረዝማላችኹ፧
5፤እናንተ፡በአድባር፡ዛፎች፡መካከል፡በለመለመም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡በፍትወት፡የምትቃጠሉ፥እናንተም፡በሸለቆ ዎች፡ውስጥ፡በአለትም፡ስንጣቂዎች፡በታች፡ሕፃናትን፡የምታርዱ፥የዐመፅ፡ልጆችና፡የሐሰት፡ዘር፡አይደላችኹም ን፧
6፤በሸለቆው፡ውስጥ፡ያሉ፡የለዘቡ፡ድንጋዮች፡ዕድል፡ፈንታሽ፡ናቸው፥እነርሱም፡ዕጣሽ፡ናቸው፤ለእነርሱም፡የመ ጠጥ፡ቍርባን፡አፍሰ፟ሻል፥የእኽልንም፡ቍርባን፡አቅርበሻል።እንግዲህ፡በዚህ፡ነገር፡አልቈጣምን፧
7፤ከፍ፡ባለውም፡በረዘመውም፡ተራራ፡ላይ፡መኝታሽን፡አደረግሽ፥መሥዋዕትንም፡ትሠዊ፡ዘንድ፡ወደዚያ፡ወጣሽ።
8፤ከመዝጊያውና፡ከመቃኑ፡በዃላ፡መታሰቢያሽን፡አደረግሽ፤እኔን፡ትተሽ፡ለሌላ፡ተገልጠሻል፥ወጥተሽ፡መኝታሽን ፡አስፍተሻል፤ቃል፡ኪዳንም፡ተጋባሻቸው፥ባየሽበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡መኝታቸውን፡ወደድሽ።
9፤ዘይትም፡ይዘሽ፡ወደ፡ንጉሡ፡ኼድሽ፥ሽቱሽንም፡አበዛሽ፥መልእክተኛዎችሽንም፡ወደ፡ሩቅ፡ላክሽ፥እስከ፡ሲኦል ም፡ድረስ፡ተዋረድሽ።
10፤በመንገድሽም፡ብዛት፡ደከምሽ፥ነገር፡ግን፦ተስፋ፡የለም፡አላልሽም፤የጕልበትን፡መታደስ፡አገኘሽ፥ስለዚህ ም፡አልዛልሽም።
11፤ሐሰትን፡የተናገርሺው፡እኔንም፡ያላሰብሺው፡በልብሽም፡ነገሩን፡ያላኖርሺው፡ማንን፡ሠግተሽ፡ነው፧ማንንስ ፡ፈርተሽ፡ነው፧እኔ፡ብዙ፡ጊዜ፡ዝም፡አልኹ፥አንቺም፡አልፈራሽም።
12፤እኔ፡ጽድቅሽን፡እናገራለኹ፥ሥራሽም፡አይረባሽም።
13፤ወደ፡አንቺ፡የሰበሰብሻቸው፡በጮኽሽ፡ጊዜ፡ይታደጉሽ፤ነፋስ፡ግን፡ይወስዳቸዋል፡ሽውሽውታም፡ዅሉን፡ያስወ ግዳቸዋል።በእኔ፡የታመነ፡ግን፡ምድሪቱን፡ይገዛል፥የተቀደሰውንም፡ተራራዬን፡ይወርሳል።
14፤ርሱም፦ጥረጉ፥መንገድን፡አዘጋጁ፥ከሕዝቤም፡መንገድ፡ዕንቅፋትን፡አውጡ፡ይላል።
15፤ለዘለዓለም፡የሚኖር፡ስሙም፡ቅዱስ፡የኾነ፥ከፍ፡ያለው፡ልዑል፡እንዲህ፡ይላል፦የተዋረዱትን፡ሰዎች፡መንፈ ስ፡ሕያው፡ኣደርግ፡ዘንድ፥የተቀጠቀጠውንም፡ልብ፡ሕያው፡ኣደርግ፡ዘንድ፥የተቀጠቀጠና፡የተዋረደ፡መንፈስ፡ካ ለው፡ጋራ፡በከፍታና፡በተቀደሰ፡ስፍራ፡እቀመጣለኹ።
16፤መንፈስም፡የፈጠርኹትም፡ነፍስ፡ከፊቴ፡እንዳይዝል፡ለዘለዓለም፡አልጣላም፥ዅልጊዜም፡አልቈጣም።
17፤ስለ፡ኀጢአቱ፡ጥቂት፡ጊዜ፡ተቈጥቼ፡ቀሠፍኹት፥ፊቴን፡ሰውሬ፡ተቈጣኹ፤ርሱም፡በልቡ፡መንገድ፡እያፈገፈገ፡ ኼደ።
18፤መንገዱን፡አይቻለኹ፡እፈውሰውማለኹ፥እመራውማለኹ፥ለርሱና፡ስለ፡ርሱም፡ለሚያለቅሱ፡መጽናናትን፡እመልሳ ለኹ።
19፤የከንፈሮችን፡ፍሬ፡እፈጥራለኹ፤በሩቅም፡በቅርብም፡ላለው፡ሰላም፡ሰላም፡ይኹን፥እፈውሰውማለኹ፥ይላል፡እ ግዚአብሔር።
20፤ክፉዎች፡ግን፡እንደሚንቀሳቀስ፡ባሕር፡ናቸው፤ጸጥ፡ይል፡ዘንድ፡አይችልምና፥ውሃዎቹም፡ጭቃና፡ጕድፍ፡ያወ ጣሉና።
21፤ለክፉዎች፡ሰላም፡የላቸውም፡ይላል፡አምላኬ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡58።______________
ምዕራፍ፡58።
1፤በኀይልኽ፡ጩኽ፥አትቈጥብ፥ድምፅኽን፡እንደ፡መለከት፡አንሣ፥ለሕዝቤ፡መተላለፋቸውን፡ለያዕቆብ፡ቤትም፡ኀጢ አታቸውን፡ንገር።
2፤ነገር፡ግን፥ዕለት፡ዕለት፡ይሹኛል፡መንገዴንም፡ያውቁ፡ዘንድ፡ይወዳ፟ሉ፤ጽድቅን፡እንዳደረጉ፡የአምላካቸው ንም፡ፍርድ፡እንዳልተዉ፡ሕዝብ፡እውነተኛውን፡ፍርድ፡ይለምኑኛል፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ለመቅረብ፡ይወዳ፟ሉ።
3፤ስለ፡ምን፡ጾምን፥አንተም፡አልተመለከትኸንም፧ሰውነታችንንስ፡ስለ፡ምን፡አዋረድን፥አንተም፡አላወቅኽም፧ይ ላሉ።እንሆ፥በጾማችኹ፡ቀን፡ፈቃዳችኹን፡ታደርጋላችኹ፥ሠራተኛዎቻችኹንም፡ዅሉ፡ታስጨንቃላችኹ።
4፤እንሆ፥ለጥልና፡ለክርክር፡ትጾማላችኹ፡በግፍ፡ጡጫም፡ትማታላችኹ፤ድምፃችኹንም፡ወደ፡ላይ፡ታሰሙ፡ዘንድ፡ዛ ሬ፡እንደምትጾሙት፡አትጾሙም።
5፤እኔ፡የመረጥኹት፡ጾም፡ይህ፡ነውን፧ሰውስ፡ነፍሱን፡የሚያዋርደው፡እንደዚህ፡ባለ፡ቀን፡ነውን፧በእውኑ፡ራሱ ን፡እንደ፡እንግጫ፡ዝቅ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ማቅንና፡ዐመድንም፡በበታቹ፡ያነጥፍ፡ዘንድ፡ነውን፧በእውኑ፡ይህን፡ ጾም፥በእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡የተወደደ፡ቀን፡ትለዋለኽን፧
6፤እኔስ፡የመረጥኹት፡ጾም፡ይህ፡አይደለምን፧የበደልን፡እስራት፡ትፈቱ፡ዘንድ፥የቀንበርንስ፡ጠፍር፡ትለቅቁ፡ ዘንድ፥የተገፉትንስ፡ሐራነት፡ትሰዱ፟፡ዘንድ፥ቀንበሩንስ፡ዅሉ፡ትሰብሩ፡ዘንድ፡አይደለምን፧
7፤እንጀራኽንስ፡ለተራበ፡ትቈርስ፡ዘንድ፥ስደተኛዎቹን፡ድኻዎች፡ወደ፡ቤትኽ፡ታገባ፡ዘንድ፥የተራቈተውንስ፡ብ ታይ፡ታለብሰው፡ዘንድ፥ከሥጋ፡ዘመድኽ፡እንዳትሸሽግ፡አይደለምን፧
8፤የዚያን፡ጊዜ፡ብርሃንኽ፡እንደ፡ንጋት፡ይበራል፥ፈውስኽም፡ፈጥኖ፡ይበቅላል፥ጽድቅኽም፡በፊትኽ፡ይኼዳል፥የ እግዚአብሔርም፡ክብር፡በዃላኽ፡ኾኖ፡ይጠብቅኻል።
9፤የዚያን፡ጊዜ፡ትጠራለኽ፡እግዚአብሔርም፡ይሰማኻል፤ትጮኻለኽ፡ርሱም፦እንሆኝ፡ይላል።ከመካከልኽ፡ቀንበርን ፡ብታርቅ፥ጣትኽንም፡መጥቀስ፡ብትተው፥
10፤ባታንጐራጕርም፥ነፍስኽንም፡ለተራበ፡ብታፈስ፟፥የተጨነቀውንም፡ነፍስ፡ብታጠግብ፥ብርሃንኽ፡በጨለማ፡ይወ ጣል፡ጨለማኽም፡እንደ፡ቀትር፡ይኾናል።
11፤እግዚአብሔርም፡ዅልጊዜ፡ይመራኻል፤ነፍስኽንም፡በመልካም፡ነገር፡ያጠግባል፡ዐጥንትኽንም፡ያጠናል፤አንተ ም፡እንደሚጠጣ፡ገነት፥ውሃውም፡እንደማያቋርጥ፡ምንጭ፡ትኾናለኽ።
12፤ከዱሮ፡ዘመን፡የፈረሱት፡ስፍራዎች፡ይሠራሉ፥የብዙ፡ትውልድም፡መሠረት፡ይታነጻል፤አንተም፦ሰባራውን፡ጠጋ ኝ፥የመኖሪያ፡መንገድን፡ዐዳሽ፡ትባላለኽ።
13፤ፈቃድኽን፡በተቀደሰው፡ቀኔ፡ከማድረግ፡እግርኽን፡ከሰንበት፡ብትመልስ፥ሰንበትንም፡ደስታ፥እግዚአብሔርም ፡የቀደሰውን፡ክቡር፡ብትለው፥የገዛ፡መንገድኽንም፡ከማድረግ፡ፈቃድኽንም፡ከማግኘት፡ከንቱ፡ነገርንም፡ከመና ገር፡ተከልክለኽ፡ብታከብረው፥
14፤በዚያን፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይልኻል፥በምድርም፡ከፍታዎች፡ላይ፡አወጣኻለኹ፥የአባትኽንም፡የያዕቆ ብን፡ርስት፡አበላኻለኹ፤የእግዚአብሔር፡አፍ፡ተናግሯልና።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡59።______________
ምዕራፍ፡59።
1፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡እጅ፡ከማዳን፡አላጠረችም፥ዦሮውም፡ከመስማት፡አልደነቈረችም፤
2፤ነገር፡ግን፥በደላችኹ፡በእናንተና፡በአምላካችኹ፡መካከል፡ለይታለች፥እንዳይሰማም፡ኀጢአታችኹ፡ፊቱን፡ከእ ናንተ፡ሰውሮታል።
3፤እጃችኹ፡በደም፡ጣታችኹም፡በበደል፡ረክሳለች፥ከንፈራችኹም፡ሐሰትን፡ተናግሯል፥ምላሳችኹም፡ኀጢአትን፡አሰ ምቷል።
4፤በጽድቅ፡የሚጠራ፡በእውነትም፡የሚፈርድ፡የለም፤በምናምንቴ፡ነገር፡ታምነዋል፡ሐሰትንም፡ተናግረዋል፤ጕዳት ን፡ፀንሰዋል፡በደልንም፡ወልደዋል፤
5፤የእባብን፡ዕንቍላል፡ቀፈቀፉ፥የሸረሪትንም፡ድር፡አደሩ፟፤ዕንቍላላቸውንም፡የሚበላ፡ሰው፡ይሞታል፥ዕንቍላ ሉም፡ሲሰበር፡እፍኝት፡ይወጣል።
6፤ድሮቻቸውም፡ልብስ፡አይኾኑላቸውም፥በሥራቸውም፡አይሸፈኑም፤ሥራቸውም፡የበደል፡ሥራ፡ነው፥የግፍም፡ሥራ፡በ እጃቸው፡ነው።
7፤እግሮቻቸው፡ወደ፡ክፋት፡ይሮጣሉ፥ንጹሑን፡ደም፡ለማፍሰስ፡ይፈጥናሉ፤ዐሳባቸው፡የኀጢአት፡ዐሳብ፡ነው፥ጕስ ቍልናና፡ቅጥቃጤ፡በመንገዳቸው፡አለ።
8፤የሰላምን፡መንገድ፡አያውቁም፥በአካኼዳቸውም፡ፍርድ፡የለም፤መንገዳቸውን፡አጣ፟መ፟ዋል፥የሚኼድባትም፡ዅሉ ፡ሰላምን፡አያውቅም።
9፤ስለዚህ፥ፍርድ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ርቋል፥ጽድቅም፡አላገኘንም፤ብርሃንን፡በተስፋ፡እንጠባበቅ፡ነበር፥እንሆም፥ ጨለማ፡ኾነ፤ጸዳልን፡በተስፋ፡እንጠባበቅ፡ነበር፥ነገር፡ግን፥በጨለማ፡ኼድን።
10፤እንደ፡ዕውሮች፡ወደ፡ቅጥሩ፡ተርመሰመስን፥ዐይን፡እንደሌላቸው፡ተርመሰመስን፤በቀትር፡ጊዜ፡በድግዝግዝታ ፡እንዳለ፡ሰው፡ተሰናከልን፥እንደ፡ሙታን፡በጨለማ፡ስፍራ፡ነን።
11፤ዅላችን፡እንደ፡ድቦች፡እንጮኻለን፥እንደ፡ርግብ፡እንለቃቀሳለን፤ፍርድን፡በተስፋ፡እንጠባበቅ፡ነበር፥ር ሱም፡የለም፤መዳንም፡ከእኛ፡ዘንድ፡ርቋል።
12፤ዐመፃችን፡ባንተ፡ፊት፡በዝቷልና፥ኀጢአታችን፡መስክሮብናልና፥ዐመፃችን፡ከእኛ፡ጋራ፡ነውና፥በደላችንን፡ እናውቃለንና።
13፤ዐምፀናል፥ሐሰትን፡ተናግረናል፥አምላካችንንም፡ከመከተል፡ተመልሰናል፤ግፍንና፡ዐመፅንም፡ተናግረናል፥የ ኀጢአት፡ቃልንም፡ፀንሰን፡ከልብ፡አውጥተናል።
14፤ፍርድም፡ወደ፡ዃላ፡ተመልሷል፥ጽድቅም፡በሩቅ፡ቆሟል፤እውነትም፡በአደባባይ፡ላይ፡ወድቋልና፥ቅንነትም፡ሊ ገባ፡አልቻለምና።
15፤እውነትም፡ታጥቷል፥ከክፋትም፡የራቀ፡ሰው፡ለብዝበዛ፡ኾኗል።
እግዚአብሔርም፡አየ፥ፍርድም፡ስለሌለ፡ተከፋ።
16፤ሰውም፡እንደሌለ፡አየ፥ወደ፡ርሱ፡የሚማልድ፡እንደሌለ፡ተረዳ፥ተደነቀም፤ስለዚህ፥የገዛ፡ክንዱ፡መድኀኒት ፡አመጣ፟ለት፥ጽድቁም፡አገዘው።
17፤ጽድቅንም፡እንደ፡ጥሩር፡ለበሰ፥በራሱም፡ላይ፡የማዳንን፡ራስ፡ቍር፡አደረገ፤የበቀልንም፡ልብስ፡ለበሰ፥በ ቅንአትም፡መጐናጸፊያ፡ተጐናጸፈ።
18፤እንደ፡ሥራቸው፡መጠን፡እንዲሁ፡ቍጣን፡ለባላጋራዎቹ፥ፍዳንም፡ለጠላቶቹ፡ይከፍላል፤ለደሴቶችም፡ፍዳቸውን ፡ይከፍላል።
19፤ርሱ፡የእግዚአብሔር፡ነፋስ፡እንደሚነዳው፡እንደ፡ጐርፍ፡ፈሳሽ፡ይመጣልና፥በምዕራብ፡ያሉት፡የእግዚአብሔ ርን፡ስም፥በፀሓይ፡መውጫም፡ያሉት፡ክብሩን፡ይፈራሉ።
20፤ለጽዮን፡ታዳጊ፡ይመጣል፥በያዕቆብም፡ዘንድ፡ከኀጢአት፡ለሚርቁ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
21፤ከርሱ፡ጋራ፡ያለው፡ቃል፡ኪዳኔ፡ይህ፡ነው፡ይላል፡እግዚአብሔር፥ባንተ፡ላይ፡ያለው፡መንፈሴ፡በአፍኽም፡ው ስጥ፡ያደረግኹት፡ቃሌ፡ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡ከአፍኽ፡ከዘርኽም፡አፍ፡ከዘር፡ዘርኽም፡አፍ፡ አያልፍም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡60።______________
ምዕራፍ፡60።
1፤ብርሃንሽ፡መጥቷልና፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ወጥቶልሻልና፥ተነሺ፥አብሪ።
2፤እንሆ፥ጨለማ፡ምድርን፡ድቅድቅ፡ጨለማም፡አሕዛብን፡ይሸፍናል፤ነገር፡ግን፥ባንቺ፡ላይ፡እግዚአብሔር፡ይወጣ ል፡ክብሩም፡ባንቺ፡ላይ፡ይታያል፤
3፤አሕዛብም፡ወደ፡ብርሃንሽ፡ነገሥታትም፡ወደ፡መውጫሽ፡ጸዳል፡ይመጣሉ።
4፤ዐይኖችሽን፡አንሥተሽ፡በዙሪያሽ፡ተመልከቺ፤እነዚህ፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ወደ፡አንቺ፡ይመጣሉ፤ወንዶች፡ልጆች ሽ፡ከሩቅ፡ይመጣሉ፥ሴቶች፡ልጆችሽንም፡በጫንቃ፡ላይ፡ይሸከሟቸዋል።
5፤በዚያን፡ጊዜ፡የባሕሩ፡በረከት፡ወደ፡አንቺ፡ስለሚመለስ፥የአሕዛብም፡ብልጥግና፡ወደ፡አንቺ፡ስለሚመጣ፥አይ ተሽ፡ደስ፡ይልሻል፥ልብሽም፡ይደነቃል፡ይሰፋማል።
6፤የግመሎች፡ብዛት፥የምድያምና፡የጌፌር፡ግመሎች፥ይሸፍኑሻል፤ዅሉ፡ከሳባ፡ይመጣሉ፥ወርቅንና፡ዕጣንን፡ያመጣ ሉ፡የእግዚአብሔርንም፡ምስጋና፡ያወራሉ።
7፤የቄዳር፡መንጋዎች፡ዅሉ፡ወደ፡አንቺ፡ይሰበሰባሉ፡የነባዮትም፡አውራ፡በጎች፡ያገለግሉሻል፤እኔን፡ደስ፡ሊያ ሠኙ፡በመሠዊያዬ፡ላይ፡ይወጣሉ፥የክብሬንም፡ቤት፡አከብራለኹ።
8፤ርግቦች፡ወደ፡ቤታቸው፡እንደሚበሩ፟፥እነዚህ፡እንደ፡ደመና፡የሚበሩ፟፡እነማን፡ናቸው፧
9፤ርሱ፡አክብሮሻልና፥ለአምላክሽ፡ለእግዚአብሔር፡ስምና፡ለእስራኤል፡ቅዱስ፡ልጆችሽን፡ከሩቅ፡ከነርሱ፡ጋራም ፡ብራቸውንና፡ወርቃቸውን፡ያመጡ፡ዘንድ፡ደሴቶች፡የተርሴስ፡መርከቦችም፡አስቀድመው፡ይጠባበቁኛል።
10፤በቍጣዬ፡ቀሥፌ፡በፍቅሬ፡ምሬሻለኹና፡መጻተኛዎች፡ቅጥርሽን፡ይሠራሉ፥ነገሥታታቸውም፡ያገለግሉሻል።
11፤በሮችሽም፡ዅልጊዜ፡ይከፈታሉ፤ሰዎች፡የአሕዛብን፡ብልጥግና፡የተማረኩትንም፡ነገሥታታቸውን፡ወደ፡አንቺ፡ ያመጡ፡ዘንድ፡ሌሊትና፡ቀን፡አይዘጉም።
12፤ለአንቺም፡የማይገዛ፡ሕዝብና፡መንግሥት፡ይጠፋል፥እነዚያ፡አሕዛብም፡ፈጽመው፡ይጠፋሉ።
13፤የመቅደሴንም፡ስፍራ፡ያስጌጡ፡ዘንድ፡የሊባኖስ፡ክብር፥ጥዱና፡አስታው፡ባርሰነቱም፥ወደ፡አንቺ፡ይመጣሉ፥ የእግሬንም፡ስፍራ፡አከብራለኹ።
14፤የአስጨናቂዎችሽም፡ልጆች፡ዐንገታቸውን፡ደፍተው፡ወደ፡አንቺ፡ይመጣሉ፥የናቁሽም፡ዅሉ፡ወደእግርሽ፡ጫማ፡ ይሰግዳሉ፤የእግዚአብሔርም፡ከተማ፥የእስራኤል፡ቅዱስ፡የኾንሽ፡ጽዮን፡ይሉሻል።
15፤ከሰውም፡ማንም፡እስከማያልፍብሽ፡ድረስ፡የተተውሽና፡የተጠላሽ፡ነበርሽ፤ነገር፡ግን፥የዘለዓለም፡ትምክሕ ትና፡የልጅ፡ልጅ፡ደስታ፡አደርግሻለኹ።
16፤የአሕዛብንም፡ወተት፡ትጠጫለሽ፡የነገሥታትንም፡ጡት፡ትጠቢያለሽ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡የያዕቆብ፡ኀይል፥ መድኀኒትሽና፡ታዳጊሽ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቂያለሽ።
17፤በናስ፡ፋንታ፡ወርቅን፥በብረትም፡ፋንታ፡ብርን፥በዕንጨትም፡ፋንታ፡ናስን፥በድንጋይም፡ፋንታ፡ብረትን፡አ መጣለኹ።አለቃዎችሽንም፡ሰላም፥የበላይ፡ገዢዎችሽንም፡ጽድቅ፡አደርጋለኹ፤
18፤ከዚያ፡በዃላ፡በምድርሽ፡ውስጥ፡ግፍ፥በዳርቻሽም፡ውስጥ፡ጕስቍልናና፡ቅጥቃጤ፡አይሰማም፤ቅጥርሽን፡መዳን ፡በሮችሽንም፡ምስጋና፡ብለሽ፡ትጠሪያለሽ፡
19፤ከዚያ፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡የዘለዓለም፡ብርሃንሽ፥አምላክሽም፡ክብርሽ፡ይኾናልና፥ፀሓይ፡በቀን፡ብርሃን ፡አይኾንልሽም፥የጨረቃም፡ብርሃን፡በሌሊት፡አይበራልሽም።
20፤እግዚአብሔር፡የዘለዓለም፡ብርሃንሽ፡ይኾናልና፥የልቅሶሽም፡ወራት፡ታልቃለችና፡ፀሓይሽ፡ከዚያ፡በዃላ፡አ ትጠልቅም፡ጨረቃሽም፡አይቋረጥም።
21፤ሕዝብሽም፡ዅሉ፡ጻድቃን፡ይኾናሉ፤እኔም፡እከብር፡ዘንድ፡የአታክልቴን፡ቡቃያ፥የእጄ፡ሥራ፡የምትኾን፡ምድ ሪቱንም፡ለዘለዓለም፡ይወርሳሉ።
22፤ታናሹ፡ለሺሕ፡የዅሉም፡ታናሹ፡ለብርቱ፡ሕዝብ፡ይኾናል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡በዘመኑ፡ይህን፡አፋጥነዋለኹ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡61።______________
ምዕራፍ፡61።
1፤የጌታ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በእኔ፡ላይ፡ነው፥ለድኻዎች፡የምሥራችን፡እሰብክ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ቀብ ቶኛልና፤ልባቸው፡የተሰበረውን፡እጠግን፡ዘንድ፥ለተማረኩትም፡ነጻነትን፡ለታሰሩትም፡መፈታትን፡እናገር፡ዘን ድ፡ልኮኛል።
2፤የተወደደችውን፡የእግዚአብሔርን፡ዓመት፡አምላካችንም፡የሚበቀልበትን፡ቀን፡እናገር፡ዘንድ፥የሚያለቅሱትን ም፡ዅሉ፡አጽናና፡ዘንድ፤
3፤እግዚአብሔር፡ለክብሩ፡የተከላቸው፡የጽድቅ፡ዛፎች፡እንዲባሉ፡ለጽዮን፡አልቃሾች፡ኣደርግላቸው፡ዘንድ፥በዐ መድ፡ፋንታ፡አክሊልን፥በልቅሶም፡ፋንታ፡የደስታን፡ዘይት፥በሐዘንም፡መንፈስ፡ፋንታ፡የምስጋናን፡መጐናጸፊያ ፡እሰጣቸው፡ዘንድ፡ልኮኛል።
4፤ከጥንትም፡ዠምሮ፡ባድማ፡የነበሩትን፡ይሠራሉ፡ከቀድሞ፡የፈረሱትንም፡ያቆማሉ፤ባድማ፡የነበሩትንና፡ከብዙ፡ ትውልድ፡በፊት፡የፈረሱትን፡ከተማዎች፡እንደ፡ገና፡ይሠራሉ።
5፤መጻተኛዎችም፡ቆመው፡በጎቻችኹን፡ያሰማራሉ፥ሌላዎች፡ወገኖችም፡ዐራሾችና፡ወይም፡ጠባቂዎች፡ይኾኑላችዃል።
6፤እናንተ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ካህናት፡ትባላላችኹ፥ሰዎቹም፡የአምላካችን፡አገልጋዮች፡ብለው፡ይጠሯችዃል፤ የአሕዛብን፡ሀብት፡ትበላላችኹ፥በክብራቸውም፡ትመካላችኹ።
7፤በዕፍረታችኹ፡ፋንታ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡ይኾንላችዃል፥በውርደታችኹም፡ፋንታ፡ዕድል፡ፈንታችኹ፡ደስ፡ይላቸዋል፤ ስለዚህ፥በምድራቸው፡ዅሉ፡ዕጥፍ፡ይገዛሉ፥የዘለዓለምም፡ደስታ፡ይኾንላቸዋል።
8፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ፍርድን፡የምወድ፟፡ስርቆትንና፡በደልን፡የምጠላ፡ነኝ፤ፍዳቸውንም፡በእውነት፡እሰጣቸዋ ለኹ፥ከነርሱም፡ጋራ፡የዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡አደርጋለኹ።
9፤ዘራቸውም፡በአሕዛብ፡መካከል፥ልጆቻቸውም፡በወገኖች፡መካከል፡የታወቁ፡ይኾናሉ፤ያያቸው፡ዅሉ፡እግዚአብሔር ፡የባረካቸው፡ዘር፡እንደ፡ኾኑ፡ይገነዘባል።
10፤አክሊልን፡እንደ፡ለበሰ፡ሙሽራ፥በጌጥ፡ሽልማቷም፡እንዳጌጠች፡ሙሽራ፥የማዳንን፡ልብስ፡አልብሶኛልና፥የጽ ድቅንም፡መጐናጸፊያ፡ደርቦልኛልና፥በእግዚአብሔር፡እጅግ፡ደስ፡ይለኛል፥ነፍሴም፡በአምላኬ፡ሐሤት፡ታደርጋለ ች።
11፤ምድርም፡ቡቃያዋን፡እንደምታወጣ፥ገነትም፡ዘሩን፡እንደሚያበቅል፥እንዲሁ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ጽድቅንና፡ ምስጋናን፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ፊት፡ያበቅላል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡62።______________
ምዕራፍ፡62።
1፤ስለ፡ጽዮን፡ዝም፡አልልም፥ስለ፡ኢየሩሳሌምም፡ጸጥ፡አልልም፥ጽድቋ፡እንደ፡ጸዳል፡መዳኗም፡እንደሚበራ፡ፋና ፡እስኪወጣ፡ድረስ።
2፤አሕዛብም፡ጽድቅሽን፡ነገሥታትም፡ዅሉ፡ክብርሽን፡ያያሉ፤የእግዚአብሔርም፡አፍ፡በሚጠራበት፡በዐዲሱ፡ስም፡ ትጠሪያለሽ።
3፤በእግዚአብሔር፡እጅ፡የክብር፡አክሊል፥በአምላክሽም፡እጅ፡የመንግሥት፡ዘውድ፡ትኾኛለሽ።
4፤ከእንግዲህ፡ወዲህ።የተተወች፡አትባዪም፤ምድርሽም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ።ውድማ፡አትባልም፤ነገር፡ግን፥እግዚ አብሔር፡ባንቺ፡ደስ፡ብሎታልና፥ምድርሽም፡ባል፡ታገባለችና፡አንቺ።ደስታዬ፡የሚኖርባት፡ትባያለሽ፡ምድርሽም ፦ባል፡ያገባች፡ትባላለች።
5፤ጕልማሳም፡ድንግሊቱን፡እንደሚያገባ፥እንዲሁ፡ልጆችሽ፡ያገቡሻል፤ሙሽራም፡በሙሽራዪቱ፡ደስ፡እንደሚለው፥እ ንዲሁ፡አምላክሽ፡ባንቺ፡ደስ፡ይለዋል።
6፤7፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ጕበኛዎችን፡በቅጥርሽ፡ላይ፡አቁሜያለኹ፤ቀንና፡ሌሊት፡ከቶ፡ዝም፡አይሉም፤እናንተ፡እ ግዚአብሔርን፡የምታሳስቡ፥ኢየሩሳሌምን፡እስኪያጸና፡በምድርም፡ላይ፡ምስጋና፡እስኪያደርጋት፡ድረስ፡አትረፉ ፡ለርሱም፡ዕረፍት፡አትስጡ።
8፤እግዚአብሔር፦ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በርግጥ፡ለጠላቶችሽ፡መብል፡ይኾን፡ዘንድ፡እኽልሽን፡አልሰጥም፥መጻተኛዎ ችም፡የደከምሽበትን፡ወይንሽን፡አይጠጡም፤
9፤ነገር፡ግን፥የሰበሰቡት፡ይበሉታል፡እግዚአብሔርንም፡ያመሰግናሉ፥ያከማቹትም፡በመቅደሴ፡አደባባይ፡ላይ፡ይ ጠጡታል፡ብሎ፡በቀኙና፡በኀይሉ፡ክንድ፡ምሏል።
10፤ዕለፉ፥በበሮች፡በኩል፡ዕለፉ፤የሕዝቡንም፡መንገድ፡ጥረጉ፤አዘጋጁ፥ጐዳናውን፡አዘጋጁ፥ድንጋዮቹንም፡አስ ወግዱ፤ለአሕዛብም፡ዓላማ፡አንሡ።
11፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡ለምድር፡ዳርቻ፡ዐዋጅ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነግሯል፦ለጽዮን፡ልጅ፦እንሆ፥መድኀኒትሽ፡ይመ ጣል፤እንሆ፥ዋጋው፡ከርሱ፡ጋራ፡ሥራውም፡በፊቱ፡አለ፡በሏት።
12፤እግዚአብሔር፦የተቤዣቸው፥የተቀደሰ፡ሕዝብ፡ብለው፡ይጠሯቸዋል፤አንቺም፦የተፈለገች፡ያልተተወችም፡ከተማ ፡ትባያለሽ።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡63።______________
ምዕራፍ፡63።
1፤ይህ፡ከኤዶምያስ፥ልብሱም፡የቀላ፡ከባሶራ፡የሚመጣ፥አለባበሱ፡ያማረ፥በጕልበቱ፡ጽናት፡የሚራመድ፡ማን፡ነው ፧በጽድቅ፡የምናገር፡ለማዳንም፡የምበረታ፡እኔ፡ነኝ።
2፤ቀሚስኽ፡ስለ፡ምን፡ቀላ፧ልብስኽስ፡በወይን፡መጥመቂያ፡እንደሚረግጥ፡ሰው፡ልብስ፡ስለ፡ምን፡መሰለ፧
3፤መጥመቂያውን፡ብቻዬን፡ረግጫለኹ፥ከአሕዛብም፡አንድ፡ሰው፡ከእኔ፡ጋራ፡አልነበረም፤በቍጣዬ፡ረገጥዃቸው፡በ መዓቴም፡ቀጠቀጥዃቸው፤ደማቸውም፡በልብሴ፡ላይ፡ተረጭቷል፥ልብሴንም፡ዅሉ፡አሳድፌያለኹ።
4፤የምበቀልበት፡ቀን፡በልቤ፡ነውና፥የምቤዥበትም፡ዓመት፡ደርሷልና።
5፤ተመለከትኹ፥የሚረዳም፡አልተገኘም፤የሚያግዝም፡አልነበረምና፡ተደነቅኹ፤ስለዚህ፥የገዛ፡ክንዴ፡መድኀኒት፡ አመጣልኝ፥ቍጣዬም፡ርሱ፡አገዘኝ።
6፤በቍጣዬም፡አሕዛብን፡ረገጥኹ፡በመዓቴም፡ቀጠቀጥዃቸው፥ደማቸውንም፡ወደ፡ምድር፡አፈሰስኹት።
7፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ሰጠን፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቸርነትና፡የእግዚአብሔርን፡ምስጋና፥እንደ፡ምሕረቱና፡ እንደ፡ቸርነቱም፡ብዛት፡ለእስራኤል፡ቤት፡የሰጠውን፡ትልቅ፡በጎነት፡አሳስባለኹ።
8፤ርሱም፦በእውነት፡ሕዝቤ፥ሐሰትን፡የማያደርጉ፡ልጆች፥ናቸው፡አለ፤መድኀኒትም፡ኾነላቸው።
9፤በጭንቃቸው፡ዅሉ፡ርሱ፡ተጨነቀ፥የፊቱም፡መልአክ፡አዳናቸው፤በፍቅሩና፡በርኅራኄውም፡ተቤዣቸው፥በቀደመውም ፡ዘመን፡ዅሉ፡አንሥቶ፡ተሸከማቸው።
10፤እነርሱ፡ግን፡ዐመፁ፡ቅዱስ፡መንፈሱንም፡አስመረሩ፤ስለዚህ፥ተመልሶ፡ጠላት፡ኾናቸው፥ርሱም፡ተዋጋቸው።
11፤ርሱም፡እንዲህ፡ብሎ፡የቀደመውን፡ዘመን፡ዐሰበ።የበጎቹን፡እረኛ፡ከባሕሩ፡ያወጣው፡ወዴት፡ነው፡ያለ፧ቅዱ ስ፡መንፈሱንም፡በመካከላቸው፡ያኖረ፡ወዴት፡ነው፡ያለ፧
12፤የከበረውንም፡ክንድ፡በሙሴ፡ቀኝ፡ያስኼደ፥ለራሱም፡የዘለዓለምን፡ስም፡ያደርግ፡ዘንድ፡ውሃውን፡በፊታቸው ፡የከፈለ፥
13፤በምድረ፡በዳም፡እንደሚያልፍ፡ፈረስ፥በቀላይ፡ውስጥ፡ያለዕንቅፋት፡ያሳለፋቸው፡ወዴት፡ነው፡ያለ፧
14፤ወደ፡ሸለቆ፡እንደሚወርዱ፡ከብቶች፥እንዲሁ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ወደ፡ዕረፍት፡አመጣቸው፤እንዲሁም፡ ለራስኽ፡የከበረ፡ስም፡ታደርግ፡ዘንድ፡ሕዝብን፡መራኽ።
15፤ከሰማይ፡ተመልከት፥ከቅዱስነትኽና፡ከክብርኽም፡ማደሪያ፡ጐብኝ፤ቅንአትኽና፡ኀይልኽስ፡ወዴት፡ነው፧ለኔም ፡የኾነው፡የልብኽ፡ናፍቆትና፡ርኅራኄኽ፡ተከለከለ።
16፤አብርሃም፡ባያውቀን፡እስራኤልም፡ባይገነዘበን፡አንተ፡አባታችን፡ነኽ፤አቤቱ፥አንተ፡አባታችን፡ነኽ፥ስም ኽም፡ከዘለዓለም፡ታዳጊያችን፡ነው።
17፤አቤቱ፥ከመንገድኽ፡ለምን፡አሳትኸን፧እንዳንፈራኽም፡ልባችንን፡ለምን፡አጸናኽብን፧ስለ፡ባሪያዎችኽ፡ስለ ፡ርስትኽ፡ነገዶች፡ተመለስ።
18፤የተቀደሰው፡ሕዝብኽ፡መቅደስኽን፡ጥቂት፡ጊዜ፡ወረሱት፤ጠላቶቻችንም፡ረግጠውታል።
19፤ከዘለዓለም፡እንዳልገዛኸን፡በስምኽም፡እንዳልተጠራን፡ኾነናል።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡64።______________
ምዕራፍ፡64።
1፤ሰማዮችን፡ቀደ፟ኽ፡ምነው፡ብትወርድ! ተራራዎችም፡ምነው፡ቢናወጡ!
2፤እሳት፡ጭራሮውን፡እንደሚያቃጥል፥እሳትም፡ውሃውን፡እንደሚያፈላ፥ስምኽ፡ለጠላቶችኽ፡ይገለጥ፡ዘንድ፥አሕዛ ብም፡በፊትኽ፡ይንቀጠቀጡ፡ዘንድ።
3፤ያልተጠባበቅነውን፡የክብርኽን፡ሥራ፡ባደረግኽ፡ጊዜ፥ወረድኽ፡ተራራዎችም፡በፊትኽ፡ተንቀጠቀጡ።
4፤ሰዎች፡ከጥንት፡ዠምሮ፡ለሚጠብቁኽ፥ከምትሠራላቸው፡ከአንተ፡በቀር፡ሌላ፡አምላክን፡አልሰሙም፥በዦሯቸውም፡ አልተቀበሉም፥ዐይንም፡አላየችም።
5፤ጽድቅን፡የሚያደርገውን፥በመንገዶችኽም፡የሚያስቡኽን፡ትገናኛቸዋለኽ።እንሆ፥አንተ፡ተቈጣኽ፥እኛም፡ኀጢአ ት፡ሠራን፤ስለዚህም፡ተሳሳትን።
6፤ዅላችን፡እንደ፡ርኩስ፡ሰው፡ኾነናል፥ጽድቃችንም፡ዅሉ፡እንደ፡መርገም፡ጨርቅ፡ነው፤ዅላችንም፡እንደ፡ቅጠል ፡ረግፈናል፥በደላችንም፡እንደ፡ነፋስ፡ወስዶናል።
7፤ስምኽንም፡የሚጠራ፥አንተንም፡ሊይዝ፡የሚያስብ፡የለም፤ፊትኽንም፡ከእኛ፡ሰውረኻል፥በኀጢአታችንም፡አጥፍተ ኸናል።
8፤አኹን፡ግን፥አቤቱ፥አንተ፡አባታችን፡ነኽ፤እኛ፡ጭቃ፡ነን፡አንተም፡ሠሪያችን፡ነኽ፥እኛም፡ዅላችን፡የእጅኽ ፡ሥራ፡ነን።
9፤አቤቱ፥እጅግ፡አትቈጣ፥ለዘለዓለምም፡ኀጢአትን፡አታስብ፤እንሆ፥እባክኽ፥ተመልከት፥እኛ፡ዅላችን፡ሕዝብኽ፡ ነን።
10፤የተቀደሱ፡ከተማዎችኽ፡ምድረ፡በዳ፡ኾነዋል፤ጽዮን፡ምድረ፡በዳ፡ኢየሩሳሌምም፡ውድማ፡ኾናለች።
11፤አባቶቻችን፡አንተን፡ያመሰገኑበት፡የተቀደሰና፡የተዋበ፡ቤታችን፡በእሳት፡ተቃጥሏል፥ያማረውም፡ስፍራችን ፡ዅሉ፡ፈርሷል።
12፤አቤቱ፥በእውኑ፡በዚህ፡ነገር፡ትታገሣለኽን፧ዝምስ፡ትላለኽን፧አጥብቀኽስ፡ታስጨንቀናለኽን፧
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡65።______________
ምዕራፍ፡65።
1፤ላልጠየቁኝ፡ተገለጥኹ፥ላልፈለጉኝም፡ተገኘኹ፤በስሜም፡ያልተጠራውን፡ሕዝብ፦እንሆኝ፥እንሆኝ፡አልኹት።
2፤መልካም፡ባልኾነው፡መንገድ፥ዐሳባቸውን፡እየተከተሉ፥ወደሚኼዱ፡ወደ፡ዐመፀኛ፡ሕዝብ፡ቀኑን፡ዅሉ፡እጆቼን፡ ዘረጋኹ።
3፤ይህ፡ሕዝብ፡ዘወትር፡የሚያስቈጡኝ፡ናቸው፤እነርሱ፡በአትክልት፡ውስጥ፡የሚሠዉ፡በጡብም፡ላይ፡የሚያጥኑ፥
4፤በመቃብርም፡መካከል፡የሚቀመጡ፥በስውርም፡ስፍራ፡የሚያድሩ፥የዕሪያ፡ሥጋም፡የሚበሉ፡ናቸው።የረከሰው፡መረ ቅ፡በዕቃቸው፡ውስጥ፡አለ።
5፤እነርሱም፦ለራስኽ፡ቁም፥እኔ፡ከአንተ፡ይልቅ፡ቅዱስ፡ነኝና፡ወደ፡እኔ፡አትቅረብ፡ይላሉ፤እነዚህ፡በአፍንጫ ዬ፡ዘንድ፡ጢስ፡ቀኑንም፡ዅሉ፡የምትነድ፟፡እሳት፡ናቸው።
6፤እንሆ፥በፊቴ፡ተጽፏል፦ኀጢአታችኹና፡የአባቶቻችኹን፡ኀጢአት፡ባንድ፡ላይ፡ወደ፡ብብታቸው፡ፍዳ፡አድርጌ፡እ መልሳለኹ፡እንጂ፡ዝም፡አልልም፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
7፤በተራራዎችም፡ላይ፡ስላጠኑ፥በኰረብታዎችም፡ላይ፡ስለ፡ሰደቡኝ፥ስለዚህ፡አስቀድመው፡የሠሩትን፡ሥራቸውን፡ በብብታቸው፡እሰፍራለኹ።
8፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወይን፡በዘለላው፡በተገኘች፡ጊዜ፦በረከት፡በርሷ፡ላይ፡አለና፡አታጥፉት፡እን ደሚባለው፥ዅሉን፡እንዳላጠፉ፡ስለ፡ባሪያዎቼ፡እንዲሁ፡አደርጋለኹ።
9፤ከያዕቆብ፡ዘርን፡ከይሁዳም፡ተራራዎቼን፡የሚወርሰውን፡አወጣለኹ፤እኔም፡የመረጥዃቸው፡ይወርሷታል፥ባሪያዎ ቼም፡በዚያ፡ይኖራሉ።
10፤ሳሮንም፡የበጎች፡ማሰማሪያ፥የዐኮርም፡ሸለቆ፡የላሞች፡መመሰጊያ፡ለፈልጉኝ፡ሕዝቤ፡ይኾናል።
11፤እናንተን፡ግን፡እግዚአብሔርን፡የተዋችኹትን፥ቅዱሱንም፡ተራራዬን፡የረሳችኹትን፥ጕድ፡ለተባለ፡ጣዖትም፡ ማእድ፡ያዘጋጃችኹትን፥ዕድል፡ለተባለ፡ጣዖትም፡የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጥ፡ቍርባን፡የቀዳችኹትን፥
12፤ዕድላችኹን፡ለሰይፍ፡አደርገዋለኹ፥ዅላችኹም፡ለመታረድ፡ትጐነበሳላችኹ፤በፊቴም፡ክፉ፡ነገርን፡አደረጋች ኹ፥ያልወደድኹትንም፡መረጣችኹ፡እንጂ፡በጠራኹ፡ጊዜ፡አልመለሳችኹልኝምና፥በተናገርኹም፡ጊዜ፡አልሰማችኹኝም ና።
13፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ባሪያዎቼ፡ይበላሉ፥እናንተ፡ግን፡ትራባላችኹ፤እንሆ፥ ባሪያዎቼ፡ይጠጣሉ፡እናንተ፡ግን፡ትጠማላችኹ፤እንሆ፥ባሪያዎቼ፡ደስ፡ይላቸዋል፡እናንተ፡ግን፡ታፍራላችኹ፤
14፤እንሆ፥ባሪያዎቼ፡ከልባቸው፡ደስታ፡የተነሣ፡ይዘምራሉ፥እናንተ፡ግን፡ከልባችኹ፡ሐዘን፡የተነሣ፡ትጮኻላች ኹ፥መንፈሳችኹም፡ስለ፡ተሰበረ፡ወዮ፡ትላላችኹ።
15፤ስማችኹንም፡ለተመረጡት፡ሕዝቤ፡ርግማን፡አድርጋችኹ፡ትተዋላችኹ፥ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ይገድላችዃል፥ባሪ ያዎቹንም፡በሌላ፡ስም፡ይጠራቸዋል።
16፤እንዲሁም፡በምድር፡ላይ፡የተባረከ፡በእውነት፡አምላክ፡ይባረካል፥በምድርም፡ላይ፡የማለ፡በእውነት፡አምላ ክ፡ይምላል፤የቀድሞው፡ጭንቀት፡ተረስቷልና፥ከዐይኔም፡ተሰውሯልና።
17፤እንሆ፥ዐዲስ፡ሰማይና፡ዐዲስ፡ምድር፡እፈጥራለኹና፤የቀደሙትም፡አይታሰቡም፥ወደ፡ልብም፡አይገቡም።
18፤ነገር፡ግን፥በፈጠርኹት፡ደስ፡ይበላችኹ፡ለዘለዓለምም፡ሐሤት፡አድርጉ፤እንሆ፥ኢየሩሳሌምን፡ለሐሤት፥ሕዝ ቧንም፡ለደስታ፡እፈጥራለኹና።
19፤እኔም፡በኢየሩሳሌም፡ሐሤት፡አደርጋለኹ፡በሕዝቤም፡ደስ፡ይለኛል፤ከዚያም፡ወዲያ፡የልቅሶ፡ድምፅና፡የዋይ ታ፡ድምፅ፡አይሰማባትም።
20፤ከዚያም፡ወዲያ፡ጥቂት፡ዘመን፡ብቻ፡የሚኖር፡ሕፃን፥ወይም፡ዕድሜውን፡ያልፈጸመ፡ሽማግሌ፡አይገኝም፤ጕልማ ሳው፡የመቶ፡ዓመት፡ኾኖት፡ይሞታልና፥ኀጢአተኛውም፡የመቶ፡ዓመት፡ኾኖት፡የተረገመ፡ይኾናልና።
21፤ቤቶችንም፡ይሠራሉ፡ይቀመጡባቸውማል፤ወይኑንም፡ይተክላሉ፡ፍሬውንም፡ይበላሉ።
22፤ሌላ፡እንዲቀመጥበት፡አይሠሩም፥ሌላም፡እንዲበላው፡አይተከሉም፤የሕዝቤ፡ዕድሜ፡እንደ፡ዛፍ፡ዕድሜ፡ይኾና ልና፥እኔም፡የመረጥዃቸው፡በእጃቸው፡ሥራ፡ረዥም፡ዘመን፡ደስ፡ይላቸዋልና።
23፤እነርሱ፡ከነልጆቻቸው፡የእግዚአብሔር፡ቡሩካን፡ዘር፡ናቸውና፥በከንቱ፡አይደክሙም፡ለጥፋትም፡አይወልዱም ።
24፤እንዲህም፡ይኾናል፤ሳይጠሩ፡እመልስላቸዋለኹ፥ገናም፡ሲናገሩ፡እሰማለኹ።
25፤ተኵላና፡ጠቦት፡በአንድነት፡ይሰማራሉ፥አንበሳም፡እንደ፡በሬ፡ገለባ፡ይበላል፥የእባብም፡መብል፡ትቢያ፡ይ ኾናል።በተቀደሰው፡ተራራዬ፡ዅሉ፡አይጐዱም፥አያጠፉምም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ኢሳይያስ፥ምዕራፍ፡66።______________
ምዕራፍ፡66።
1፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰማይ፡ዙፋኔ፡ነው፥ምድርም፡የእግሬ፡መረገጫ፡ናት፤የምትሠሩልኝ፡ቤት፡ምን፡ ዐይነት፡ነው፧የማርፍበትስ፡ስፍራ፡ምንድር፡ነው፧
2፤እነዚህን፡ዅሉ፡እጄ፡ሠርታለችና፡እነዚህ፡ዅሉ፡የእኔ፡ናቸው፡ይላል፡እግዚአብሔር፤ነገር፡ግን፥ወደዚህ፡ወ ደ፡ትሑት፥መንፈሱም፡ወደተሰበረ፥በቃሌም፡ወደሚንቀጠቀጥ፡ሰው፡እመለከታለኹ።
3፤በሬን፡የሚያርድልኝ፡ሰውን፡እንደሚገድል፡ነው፤ጠቦትንም፡የሚሠዋ፡የውሻውን፡ዐንገት፡እንደሚሰብር፡ነው፤ የእኽልን፡ቍርባን፡የሚያቀርብ፡የዕሪያን፡ደም፡እንደሚያቀርብ፡ነው፤ዕጣንን፡የሚያጥን፡ጣዖትን፡እንደሚባር ክ፡ነው።እነዚህ፡የገዛ፡መንገዳቸውን፡መረጡ፤ነፍሳቸውም፡በርኵሰታቸው፡ደስ፡ይላታል፤
4፤እኔ፡ደግሞ፡የተሳለቀባቸውን፡እመርጣለኹ፥የፈሩትንም፡ነገር፡አመጣባቸዋለኹ፤በፊቴ፡ክፉ፡ነገርን፡አደረጉ ፥ያልወደድኹትንም፡መረጡ፡እንጂ፡በጠራኹ፡ጊዜ፡አልመለሱልኝምና፥በተናገርኹም፡ጊዜ፡አልሰሙኝምና።
5፤በቃሉ፡የምትንቀጠቀጡ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፦የጠሏችኹ፡ስለ፡ስሜም፡ያባረሯችኹ፡ወንድሞቻችኹ፦ ደስታችኹን፡እናይ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ይክበር፡ብለዋል፤ነገር፡ግን፥ያፍራሉ።
6፤የጩኸት፡ድምፅ፡ከከተማ፥ድምፅም፡ከመቅደስ፥በጠላቶቹ፡ላይ፡ፍዳን፡የሚያመጣ፡የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡ተሰም ቷል።
7፤ሳታምጥ፡ወለደች፤ምጥም፡ሳያገኛት፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደች።
8፤ከቶ፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ማን፡ሰምቷል፧እንዲህስ፡ያለ፡ነገር፡ማን፡አይቷል፧በእውኑ፡አገር፡ባንድ፡ቀን፡ ታምጣለችን፧ወይስ፡ባንድ፡ጊዜ፡ሕዝብ፡ይወለዳልን፧ጽዮን፡እንዳማጠች፡ወዲያው፡ልጆቿን፡ወልዳለችና።
9፤በእውኑ፡ወደ፡መውለድ፡የማደርስ፡እኔ፡አላስወልድምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤የማስወልድስ፡ማሕፀንን፡እኔ፡ እዘጋለኹን፧ይላል፡አምላክሽ።
10፤እናንተ፡የምትወዷ፟ት፡ዅሉ፥ከኢየሩሳሌም፡ጋራ፡ሐሤትን፡አድርጉ፥ስለ፡ርሷም፡ደስ፡ይበላችኹ፤እናንተም፡ የምታለቅሱላት፡ዅሉ፥ከርሷ፡ጋራ፡በደስታ፡ሐሤትን፡አድርጉ፥
11፤ትጠቡ፡ዘንድ፡ከማጽናናቷም፡ጡት፡ትጠግቡ፡ዘንድ፤እጅግ፡ጠጥታችኹ፡በክብሯ፡ሙላት፡ደስ፡ይላችኹ፡ዘንድ።
12፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ሰላምን፡እንደ፡ወንዝ፥የአሕዛብንም፡ክብር፡እንደሚጐርፍ፡ፈሳሽ፡ እመልስላታለኹ፤ከዚያም፡ትጠባላችኹ፥በጫንቃ፡ላይ፡ይሸከሟችዃል፡በጕልበትም፡ላይ፡እያስቀመጡ፡ያቀማጥሏችዃ ል።
13፤እናት፡ልጇን፡እንደምታጽናና፡እንዲሁ፡አጽናናችዃለኹ፥በኢየሩሳሌምም፡ውስጥ፡ትጽናናላችኹ።
14፤ታያላችኹ፥ልባችኹም፡ሐሤት፡ታደርጋለች፥ዐጥንታችኹም፡እንደ፡ለምለም፡ሣር፡ትበቅላለች፤የእግዚአብሔርም ፡እጅ፡ለሚፈሩት፡ትታወቃለች፥በጠላቶቹም፡ላይ፡ይቈጣል።
15፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡መዓቱን፡በቍጣ፥ዘለፋውንም፡በእሳት፡ነበልባል፡ይመልስ፡ዘንድ፡ከእሳት፡ጋራ፡ይመጣ ል፥ሠረገላዎቹም፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይኾናሉ።
16፤እግዚአብሔርም፡በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፡በእሳትና፡በሰይፉ፡ይፈርዳል፤በእግዚአብሔርም፡ተወግተው፡የሞቱ ት፡ይበዛሉ።
17፤በመካከላቸው፡ያለውን፡አንዱን፡ተከትለው፡ወደ፡ገነቱ፡ይገቡ፡ዘንድ፡ሰውነታቸውን፡የሚቀድሱና፡የሚያነጹ ፥የዕሪያንም፡ሥጋ፡አስጸያፊ፡ነገርንም፡ዐይጥንም፡የሚበሉ፡በአንድነት፡ይጠፋሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
18፤ሥራቸውንና፡ዐሳባቸውን፡ዐውቄያለኹና፤አሕዛብንና፡ልሳናትን፡ዅሉ፡የምሰበስብበት፡ጊዜ፡ይደርሳል፥እነር ሱም፡ይመጣሉ፡ክብሬንም፡ያያሉ።
19፤በመካከላቸውም፡ምልክት፡አደርጋለኹ፥ከነርሱም፡የዳኑትን፡ዝናዬን፡ወዳልሰሙ፥ክብሬንም፡ወዳላዩ፡ወደ፡አ ሕዛብ፡ወደ፡ተርሴስ፡ወደ፡ፉጥ፡ወደ፡ሉድ፡ወደ፡ሞሳሕ፡ወደ፡ቶቤል፡ወደ፡ያዋን፡በሩቅ፡ወዳሉ፡ደሴቶች፡እልካ ቸዋለኹ፥በአሕዛብም፡መካከል፡ክብሬንም፡ይናገራሉ።
20፤የእስራኤል፡ልጆች፡ቍርባናቸውን፡በጥሩ፡ዕቃ፡አድርገው፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደሚያመጡ፥እንዲሁ፡ለ እግዚአብሔር፡ቍርባን፡ይኾን፡ዘንድ፡ወንድሞቻችኹን፡ዅሉ፥በፈረሶችና፡በሠረገላዎች፥በዐልጋዎችና፡በበቅሎዎ ች፡በጠያር፡ግመሎችም፡ላይ፡አድርገው፥ከአሕዛብ፡ዅሉ፡ወደተቀደሰው፡ተራራዬ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ያመጧቸዋል፥ ይላል፡እግዚአብሔር።
21፤ካህናትና፡ሌዋውያን፡እንዲኾኑ፡ከነርሱ፡እወስዳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
22፤እኔ፡የምሠራቸው፡ዐዲስ፡ሰማይና፡ዐዲስ፡ምድር፡ከፊቴ፡ጸንተው፡እንደሚኖሩ፥እንዲሁ፡ዘራችኹና፡ስማችኹ፡ ጸንተው፡ይኖራሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
23፤እንዲህ፡ይኾናል፤በየመባቻውና፡በየሰንበቱ፡ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡በፊቴ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡ዘወትር፡ይመጣል፥ይ ላል፡እግዚአብሔር።
24፤ወጥተውም፡በእኔ፡ያመፁብኝን፡ሰዎች፡ሬሳቸውን፡ያያሉ፤ትላቸው፡አይሞትምና፥እሳታቸውም፡አይጠፋምና፤ለሥ ጋ፡ለባሽም፡ዅሉ፡አስጸያፊ፡ነገር፡ይኾናሉ፨

http://www.gzamargna.net