ኦሪት፡ዘጸአት።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡1።_______________
ምዕራፍ፡1።
1፤ከያዕቆብ፡ጋራ፡ወደ፡ግብጽ፡የገቡት፡የእስራኤል፡ልጆች፡ስሞች፡እነዚህ፡ናቸው፤ሰው፡ዅሉ፡ከቤተ፡ሰቡ፡ ጋራ፡ገባ።
2፤ሮቤል፥
3፤ስምዖን፥ሌዊ፥ይሁዳ፥ይሳኮር፥ዛብሎን፥
4፤ብንያም፥ዳን፥ንፍታሌም፥ጋድ፥አሴር።
5፤ከያዕቆብ፡ጕልበት፡የወጡት፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሰባ፡ነፍሶች፡ነበሩ፤ዮሴፍም፡አስቀድሞ፡በግብጽ፡ነበረ።
6፤ዮሴፍም፡ሞተ፥ወንድሞቹም፥ያም፡ትውልድ፡ዅሉ።
7፤የእስራኤልም፡ልጆች፡አፈሩ፥እጅግም፡በዙ፥ተባዙም፥እጅግም፡ጸኑ፤ምድሪቱም፡በእነርሱ፡ሞላች።
8፤በግብጽም፡ዮሴፍን፡ያላወቀ፡ዐዲስ፡ንጉሥ፡ተነሣ።
9፤ርሱም፡ሕዝቡን፦እንሆ፥የእስራኤል፡ልጆች፡ሕዝብ፡ከእኛ፡ይልቅ፡በዝተዋል፡በርትተውማል፤
10፤እንዳይበዙ፥ሰልፍም፡በተነሣብን፡ጊዜ፡ጠላቶቻችንን፡አግዘው፡እንዳይወጉን፡ከምድሪቱም፡እንዳይወጡ፥ኑ ፡እንጠበብባቸው፡አለ።
11፤በብርቱ፡ሥራም፡ያስጨንቋቸው፡ዘንድ፡ግብር፡አስገባሪዎችን፡ሾመባቸው፤ለፈርዖንም፡ፊቶምንና፡ራምሴን፡ ጽኑ፡ከተማዎች፡አድርገው፡ሠሩ።
12፤ነገር፡ግን፥እንዳስጨነቋቸው፡መጠን፡እንዲሁ፡በዙ፥እጅግም፡ጸኑ፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡የተነሣ፡ተጸይፈ ዋቸው፡ነበር።
13፤ግብጻውያንም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በመከራ፡ገዟቸው።
14፤በጽኑ፡ሥራ፥በጭቃ፥በጡብም፡በዕርሻም፡ሥራ፡ዅሉ፥በመከራም፡በሚያሠሯቸው፡ሥራ፡ዅሉ፥ሕይወታቸውን፡ያስ መርሯቸው፡ነበር።
15፤የግብጽም፡ንጉሥ፡አንዲቱ፡ሲፓራ፡ኹለተኛዪቱም፡ፉሐ፡የሚባሉትን፡የዕብራውያንን፡አዋላጆች፡እንዲህ፡ብ ሎ፡ተናገረ፦
16፤እናንተ፡የዕብራውያንን፡ሴቶች፡ስታዋልዱ፥ለመውለድ፡እንደ፡ደረሱ፡ባያችኹ፡ጊዜ፥ወንድ፡ቢኾን፡ግደሉት ፤ሴት፡ብትኾን፡ግን፡በሕይወት፡ትኑር።
17፤አዋላጆች፡ግን፡እግዚአብሔርን፡ፈሩ፥የግብጽ፡ንጉሥም፡እንዳዘዛቸው፡አላደረጉም፥ወንዶቹን፡ሕፃናትንም ፡አዳኗቸው።
18፤የግብጽም፡ንጉሥ፡አዋላጆችን፡ጠርቶ፦ለምን፡እንዲህ፡አደረጋችኹ፧ወንዶቹን፡ሕፃናትንስ፡ለምን፡አዳናች ኹ፧አላቸው።
19፤አዋላጆቹም፡ፈርዖንን፦የዕብራውያን፡ሴቶች፡እንደ፡ግብጽ፡ሴቶች፡ስላልኾኑ፤እነርሱ፡ጠንካራዎች፡ናቸው ና፥አዋላጆች፡ሳይገቡ፡ስለሚወልዱ፡ነው፡አሉት።
20፤እግዚአብሔርም፡ለአዋላጆች፡መልካም፡አደረገላቸው፤ሕዝቡም፡በዛ፥እጅግም፡ጸና።
21፤እንዲህም፡ኾነ፤አዋላጆች፡እግዚአብሔርን፡ስለ፡ፈሩ፡ቤቶችን፡አደረገላቸው።
22፤ፈርዖንም፦የሚወለደውን፡ወንድ፡ልጅ፡ዅሉ፡ወደ፡ወንዝ፡ጣሉት፥ሴትን፡ልጅ፡ዅሉ፡ግን፡በሕይወት፡አድኗት ፡ብሎ፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡አዘዘ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ከሌዊ፡ወገንም፡አንድ፡ሰው፡ኼዶ፡የሌዊን፡ልጅ፡አገባ።
2፤ሴቲቱም፡ፀነሰች፥ወንድ፡ልጅም፡ወለደች፤መልካምም፡እንደ፡ኾነ፡ባየች፡ጊዜ፡ሦስት፡ወር፡ሸሸገችው።
3፤ደግሞም፡ልትሸሽገው፡ባልቻለች፡ጊዜ፥የደንገል፡ሣጥን፡ለርሱ፡ወስዳ፡ዝፍትና፡ቅጥራን፡ለቀለቀችው፤ሕፃ ኑንም፡አኖረችበት፥በወንዝም፡ዳር፡ባለ፡በቄጠማ፡ውስጥ፡አስቀመጠችው።
4፤እኅቱም፡የሚደረግበትን፡ታውቅ፡ዘንድ፡በሩቅ፡ቆማ፡ትጐበኘው፡ነበር።
5፤የፈርዖንም፡ልጅ፡ልትታጠብ፡ወደ፡ወንዝ፡ወረደች፤ደንገጥሮቿም፡በወንዝ፡ዳር፡ይኼዱ፡ነበር፤ሣጥኑንም፡ በቄጠማ፡ውስጥ፡አየች፥ደንገጥሯንም፡ልካ፡አስመጣችው።
6፤በከፈተችውም፡ጊዜ፡ሕፃኑን፡አየች፥እንሆም፡ሕፃኑ፡ያለቅስ፡ነበር፤ዐዘነችለትም፦ይህ፡ከዕብራውያን፡ል ጆች፡አንድ፡ነው፡አለች።
7፤እኅቱም፡ለፈርዖን፡ልጅ፦ሕፃኑን፡ታጠባልሽ፡ዘንድ፡ኼጄ፡የምታጠባ፡ሴት፡ከዕብራውያን፡ሴቶች፡ልጥራልሽ ን፧አለቻት።
8፤የፈርዖንም፡ልጅ፦ኺጂ፡አለቻት፤ብላቴናዪቱም፡ኼዳ፡የሕፃኑን፡እናት፡ጠራች።
9፤የፈርዖንም፡ልጅ፦ይህን፡ሕፃን፡ወስደሽ፡አጥቢልኝ፥ዋጋሽንም፡እሰጥሻለኹ፡አለቻት።ሴቲቱም፡ሕፃኑን፡ወ ስዳ፡አጠባችው።
10፤ሕፃኑም፡አደገ፥ወደፈርዖንም፡ልጅ፡ዘንድ፡አመጣችው፥ለርሷም፡ልጅ፡ኾነላት፦እኔ፡ከውሃ፡አውጥቼዋለኹና ፡ስትልም፡ስሙን፡ሙሴ፡ብላ፡ጠራችው።
11፤በዚያም፡ወራት፡እንዲህ፡ኾነ፤ሙሴ፡ጐበዝ፡በኾነ፡ጊዜ፡ወደ፡ወንድሞቹ፡ወጣ፥የሥራቸውንም፡መከራ፡ተመለ ከተ፤የግብጽም፡ሰው፡የወንድሞቹን፡የዕብራውያንን፡ሰው፡ሲመታ፡አየ።
12፤ወዲህና፡ወዲያም፡ተመለከተ፥ማንንም፡አላየም፥ግብጻዊውንም፡ገደለ፥በአሸዋም፡ውስጥ፡ሸሸገው።
13፤በኹለተኛውም፡ቀን፡ወጣ፥ኹለቱም፡የዕብራውያን፡ሰዎች፡ሲጣሉ፡አየ፤በዳዩንም፦ለምን፡ባልንጀራኽን፡ትመ ታዋለኽ፧አለው።
14፤ያም፦በእኛ፡ላይ፡አንተን፡አለቃ፡ወይስ፡ዳኛ፡ማን፡አደረገኽ፧ወይስ፡ግብጻዊውን፡እንደ፡ገደልኸው፡ልት ገድለኝ፡ትሻለኽን፧አለው።ሙሴም፦በእውነት፡ይህ፡ነገር፡ታውቋል፡ብሎ፡ፈራ።
15፤ፈርዖንም፡ይህን፡ነገር፡በሰማ፡ጊዜ፡ሙሴን፡ሊገድለው፡ፈለገ።ሙሴ፡ግን፡ከፈርዖን፡ፊት፡ኰበለለ፥በምድ ያምም፡ምድር፡ተቀመጠ፤በውሃም፡ጕድጓድ፡አጠገብ፡ዐረፈ።
16፤ለምድያምም፡ካህን፡ሰባት፡ሴቶች፡ልጆች፡ነበሩት፤እነርሱም፡መጥተው፡ውሃ፡ቀዱ፥የአባታቸውንም፡በጎች፡ ሊያጠጡ፡የውሃውን፡ገንዳ፡ሞሉ።
17፤እረኛዎችም፡መጥተው፡ገፏቸው፤ሙሴ፡ግን፡ተነሥቶ፡ረዳቸው፥በጎቻቸውንም፡አጠጣላቸው።
18፤ወደ፡አባታቸው፡ወደ፡ራጉኤልም፡በመጡ፡ጊዜ፦ስለ፡ምን፡ዛሬ፡ፈጥናችኹ፡መጣችኹ፧አላቸው።
19፤እነርሱም፦አንድ፡የግብጽ፡ሰው፡ከእረኛዎች፡እጅ፡አዳነን፥ደግሞም፡ቀዳልን፥በጎቻችንንም፡አጠጣ፡አሉ።
20፤ልጆቹንም፦ርሱ፡ወዴት፡ነው፧ለምንስ፡ያንን፡ሰው፡ተዋችኹት፧ጥሩት፡እንጀራም፡ይብላ፡አላቸው።
21፤ሙሴም፡ከዚያ፡ሰው፡ጋራ፡ሊቀመጥ፡ወደደ፤ልጁንም፡ሲፓራን፡ለሙሴ፡ሚስት፡ትኾነው፡ዘንድ፡ሰጠው።
22፤ወንድ፡ልጅም፡ወለደች።በሌላ፡ምድር፡መጻተኛ፡ነኝ፡ሲል፡ስሙን፡ጌርሳም፡ብሎ፡ጠራው።
23፤ከዚያም፡ከብዙ፡ቀን፡በዃላ፡እንዲህ፡ኾነ፤የግብጽ፡ንጉሥ፡ሞተ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከባርነት፡የተነሣ ፡አለቀሱ፥ጮኹም፥ስለ፡ባርነታቸውም፡ጩኸታቸው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወጣ።
24፤እግዚአብሔርም፡የለቅሷቸውን፡ድምፅ፡ሰማ፥እግዚአብሔርም፡ከአብርሃምና፡ከይሥሐቅ፡ከያዕቆብም፡ጋራ፡ያ ደረገውን፡ቃል፡ኪዳን፡ዐሰበ።
25፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አየ፥እግዚአብሔርም፡በእነርሱ፡ያለውን፡ነገር፡ዐወቀ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ሙሴም፡የዮቶርን፡የዐማቱን፡የምድያምን፡ካህን፡በጎች፡ይጠብቅ፡ነበር፤ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ዳርቻም፡በጎቹ ን፡ነዳ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ተራራ፡ወደ፡ኰሬብ፡መጣ።
2፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በእሳት፡ነበልባል፡በሾኽ፡ቍጥቋጦ፡መካከል፡ታየው፤እንሆም፡ቍጥቋጦው፡በእሳ ት፡ሲነድ፟፡ቍጥቋጦውም፡ሳይቃጠል፡አየ።
3፤ሙሴም፦ልኺድና፡ቍጥቋጦው፡ስለ፡ምን፡አልተቃጠለም፡ይህን፡ታላቅ፡ራእይ፡ልይ፡አለ።
4፤እግዚአብሔር፡ርሱ፡ይመለከት፡ዘንድ፡እንደ፡መጣ፡ባየ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከቍጥቋጦው፡ውስጥ፡ርሱን፡ጠ ርቶ፦ሙሴ፥ሙሴ፡ሆይ፡አለ።
5፤ርሱም፦እንሆኝ፡አለ።ወደዚህ፡አትቅረብ፤አንተ፡የቆምኽባት፡ስፍራ፡የተቀደሰች፡መሬት፡ናትና፥ጫማኽን፡ ከእግርኽ፡አውጣ፡አለው።
6፤ደግሞም፦እኔ፡የአባትኽ፡አምላክ፥የአብርሃም፡አምላክ፡የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ፡ነኝ፡ አለው።ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ያይ፡ዘንድ፡ፈርቷልና፥ፊቱን፡ሸፈነ።
7፤እግዚአብሔርም፡አለ፦በግብጽ፡ያለውን፡የሕዝቤን፡መከራ፡በእውነት፡አየኹ፥ከአስገባሪዎቻቸውም፡የተነሣ ፡ጩኸታቸውን፡ሰማኹ፤ሥቃያቸውንም፡ዐውቄያለኹ፤
8፤ከግብጻውያንም፡እጅ፡አድናቸው፡ዘንድ፥ከዚያችም፡አገር፡ወተትና፡ማር፡ወደምታፈሰ፟ው፡አገር፡ወደ፡ሰፊ ዪቱና፡ወደ፡መልካሚቱ፡አገር፡ወደከነዓናውያንም፡ወደኬጢያውያንም፡ወደአሞራውያንም፡ወደፌርዛውያንም፡ወደ ዔዊያውያንም፡ወደኢያቡሳውያንም፡ስፍራ፡አወጣቸው፡ዘንድ፡ወረድኹ።
9፤አኹንም፥እንሆ፥የእስራኤል፡ልጆች፡ጩኸት፡ወደ፡እኔ፡ወጣ፤ግብጻውያንም፡የሚያደርጉባቸውን፡ግፍ፡ደግሞ ፡አየኹ።
10፤አኹንም፡ና፥ሕዝቤን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ታወጣ፡ዘንድ፡ወደ፡ፈርዖን፡እልክኻለኹ።
11፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፦ወደ፡ፈርዖን፡የምኼድ፡የእስራኤልንም፡ልጆች፡ከግብጽ፡የማወጣ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧ አለው።
12፤ርሱም፦በእውነት፡እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡እኾናለኹ፤እኔም፡እንደ፡ላክኹኽ፡ምልክትኽ፡ይህ፡ነው፤ሕዝቡን፡ከ ግብጽ፡ባወጣኽ፡ጊዜ፡በዚህ፡ተራራ፡ላይ፡ለእግዚአብሔር፡ትገዛላችኹ፡አለ።
13፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፦እንሆ፥እኔ፡ወደእስራኤል፡ልጆች፡በመጣኹ፡ጊዜ፦የአባቶቻችኹ፡አምላክ፡ወደ፡እና ንተ፡ላከኝ፡ባልኹም፡ጊዜ፦ስሙስ፡ማን፡ነው፧ባሉኝ፡ጊዜ፥ምን፡እላቸዋለኹ፧አለው።
14፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦‟ያለና፡የሚኖር”፡እኔ፡ነኝ፡አለው፤እንዲህ፡ለእስራኤል፡ልጆች።‟ያለና፡የሚኖ ር”፡ወደ፡እናንተ፡ላከኝ፡ትላለኽ፡አለው።
15፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡ሙሴን፡አለው፦ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ትላለኽ፦የአባቶቻችኹ፡አምላክ፥የአብ ርሃም፡አምላክ፡የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡እናንተ፡ላከኝ፤ይህ፡ለዘለዓ ለሙ፡ስሜ፡ነው፥እስከልጅ፡ልጅ፡ድረስም፡መታሰቢያዬ፡ይህ፡ነው።
16፤ኺድ፡የእስራኤልንም፡ሽማግሌዎች፡ሰብስብ።እግዚአብሔር፡የአባቶቻችኹ፡አምላክ፡የአብርሃም፡የይሥሐቅም ፡የያዕቆብም፡አምላክ።መጐብኘትን፡ጐበኘዃችኹ፥በግብጽም፡የሚደረግባችኹን፡አየኹ፤
17፤ከግብጽም፡መከራ፡ወደከነዓናውያን፡ወደኬጢያውያንም፡ወደአሞራውያንም፡ወደፌርዛውያንም፡ወደዔዊያውያን ም፡ወደያቡሳውያንም፡አገር፡ወተትና፡ማር፡ወደምታፈስ፟፡አገር፡አወጣችዃለኹ፡አልኹ፡ብሎ፡ተገለጠልኝ፡በላ ቸው።
18፤እነርሱም፡ቃልኽን፡ይሰማሉ፤አንተና፡የእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ወደግብጽ፡ንጉሥ፡ትገባላችኹ።የዕብራውያ ን፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ተገለጠልን፤አኹንም፡ለአምላካችን፡ለእግዚአብሔር፡እንሠዋ፡ዘንድ፡የሦስት፡ቀን ፡መንገድ፡በምድረ፡በዳ፡እንኺድ፡ትሉታላችኹ።
19፤ነገር፡ግን፥በጽኑ፡እጅ፡ካልኾነ፡በቀር፡ትኼዱ፡ዘንድ፡የግብጽ፡ንጉሥ፡እንደማይፈቅድላችኹ፡እኔ፡ዐውቃ ለኹ።
20፤እኔም፡እጄን፡እዘረጋለኹ፥በማደርግባቸውም፡ተኣምራቴ፡ዅሉ፡ግብጽን፡እመታለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡ይለቃ፟ ችዃል።
21፤በግብጻውያንም፡ፊት፡ለዚህ፡ሕዝብ፡ሞገስን፡እሰጣለኹ፤እንዲህም፡ይኾናል፤በኼዳችኹ፡ጊዜ፡ባዶ፡እጃችኹ ን፡አትኼዱም፤
22፤ነገር፡ግን፥እያንዳንዲቱ፡ሴት፡ከጎረቤቷ፣በቤቷም፡ካለችው፡ሴት፡የብር፡ዕቃ፣የወርቅ፡ዕቃ፣ልብስም፡ት ለምናለች፤በወንዶችና፡በሴቶች፡ልጆቻችኹ፡ላይ፡ታደርጉታላችኹ፤ግብጻውያንንም፡ትበዘብዛላችኹ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ሙሴም፡መለሰ፦እንሆ፥አያምኑኝም፡ቃሌንም፡አይሰሙም።እግዚአብሔር፡ከቶ፡አልተገለጠልኽም፡ይሉኛል፡አለ ።
2፤እግዚአብሔርም፦ይህች፡በእጅኽ፡ያለችው፡ምንድር፡ናት፧አለው።ርሱም፦በትር፡ናት፡አለ።
3፤ወደ፡መሬት፡ጣላት፡አለው፤ርሱም፡በመሬት፡ጣላት፥እባብም፡ኾነች፤ሙሴም፡ከርሷ፡ሸሸ።
4፤5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦የአባቶቻቸው፡አምላክ፥የአብርሃም፡አምላክ፡የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡ አምላክ፥እግዚአብሔር፡እንደ፡ተገለጠልኽ፡እንዲያምኑ፡እጅኽን፡ዘርግተኽ፡ዥራቷን፡ያዝ፡አለው።እጁንም፡ዘ ርግቶ፡ያዛት፡በእጁም፡ውስጥ፡በትር፡ኾነች።
6፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፦እጅኽን፡ወደ፡ብብትኽ፡አግባ፡አለው።እጁንም፡ወደ፡ብብቱ፡አገባት፤ባወጣትም፡ጊ ዜ፥እንሆ፥እጁ፡እንደ፡በረዶ፡ለምጽ፡ኾነች።
7፤ርሱም፦እጅኽን፡ወደ፡ብብትኽ፡መልስ፡አለው።እጁንም፡ወደ፡ብብቱ፡መለሳት፥ከብብቱም፡ባወጣት፡ጊዜ፥እን ሆ፥ተመልሳ፡ገላውን፡መሰለች።
8፤ደግሞም፡አለው፦እንዲህም፡ይኾናል፤ባያምኑኽ፡የፊተኛዪቱንም፡ምልክት፡ነገር፡ባይሰሙ፥የኹለተኛዪቱን፡ ምልክት፡ነገር፡ያምናሉ።
9፤እንዲህም፡ይኾናል፤እነዚህን፡ኹለት፡ምልክቶች፡ባያምኑ፡ቃልኽንም፡ባይሰሙ፥ከወንዙ፡ውሃን፡ውሰድ፥በደ ረቁም፡መሬት፡ላይ፡አፍሰ፟ው፤ከወንዙም፡የወሰድኸው፡ውሃ፡በደረቁ፡መሬት፡ላይ፡ደም፡ይኾናል።
10፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፦ጌታ፡ሆይ፥እኔ፡አፌ፡ኰልታፋ፡ምላሴም፡ጸያፍ፡የኾነ፡ሰው፡ነኝ፤ትናንት፡ከትናን ት፡ወዲያ፡ባሪያኽንም፡ከተናገርኸኝ፡ዠምሮ፡አፈ፡ትብ፡ሰው፡አይደለኹም።
11፤እግዚአብሔርም፦የሰውን፡አፍ፡የፈጠረ፡ማን፡ነው፧ዲዳስ፡ደንቈሮስ፡የሚያይስ፡ዕውርስ፡ያደረገ፡ማን፡ነ ው፧እኔ፡እግዚአብሔር፡አይደለኹምን፧
12፤እንግዲህ፡አኹን፡ኺድ፥እኔም፡ከአፍኽ፡ጋራ፡እኾናለኹ፥የምትናገረውንም፡አስተምርኻለኹ፡አለው።
13፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥በምትልከው፡ሰው፡እጅ፡ትልክ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለ።
14፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በሙሴ፡ላይ፡ነደደ፡እንዲህም፡አለ፦ሌዋዊው፡ወንድምኽ፡አሮን፡አለ፡አይደለምን፧ ርሱ፡ደኅና፡እንዲናገር፡ዐውቃለኹ፤እንሆም፡ደግሞ፡ሊገናኝኽ፡ይመጣል፤ባየኽም፡ጊዜ፡በልቡ፡ደስ፡ይለዋል።
15፤አንተም፡ትናገረዋለኽ፡ቃሉንም፡በአፉ፡ታደርገዋለኽ፤እኔ፡ከአፍኽና፡ከአፉ፡ጋራ፡እኾናለኹ፥የምታደርጉ ትንም፡አስተምራችዃለኹ።
16፤ርሱ፡ስለ፡አንተ፡ከሕዝቡ፡ጋራ፡ይናገራል፤እንዲህም፡ይኾናል፤ርሱ፡አፍ፡ይኾንልኻል፡አንተም፡በእግዚአ ብሔር፡ፋንታ፡ትኾንለታለኽ።
17፤ይህችንም፡ተኣምራት፡የምታደርግባትን፡በትር፡በእጅኽ፡ይዘኻት፡ኺድ።
18፤ሙሴም፡ኼደ፥ወደ፡ዐማቱ፡ወደ፡ዮቶር፡ተመለሰ፦እስከ፡ዛሬ፡በሕይወት፡እንዳሉ፡አይ፡ዘንድ፡ተመልሼ፡ወደ ፡ግብጽ፡ወደ፡ወንድሞቼ፡ልኺድ፡አለው።ዮቶርም፡ሙሴን፦በሰላም፡ኺድ፡አለው።
19፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡በምድያም፦ነፍስኽን፡የሚሿት፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሞተዋልና፥ተመልሰኽ፡ወደ፡ግብጽ፡ኺድ ፡አለው።
20፤ሙሴም፡ሚስቱንና፡ልጆቹን፡ወሰደ፥በአህያ፡ላይም፡አስቀመጣቸው፥ወደ፡ግብጽም፡አገር፡ተመለሰ፤ሙሴም፡የ እግዚአብሔርን፡በትር፡ይዞ፡ኼደ።
21፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ወደ፡ግብጽ፡ስትመለስ፡በእጅኽ፡ያደረግኹትን፡ተኣምራት፡ዅሉ፡በፈርዖን፡ ፊት፡ታደርገው፡ዘንድ፡ተመልከት፤እኔ፡ግን፡ልቡን፡አጸናዋለኹ፥ሕዝቡንም፡አይለቅ፟ም።
22፤ፈርዖንንም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
23፤እስራኤል፡የበኵር፡ልጄ፡ነው፤ይገዛልኝ፡ዘንድ፡ልጄን፡ልቀቅ፡አልኹኽ፤አንተም፡ትለቀ፟ው፡ዘንድ፡እንቢ ፡አልኽ፤እንሆ፥እኔ፡የበኵር፡ልጅኽን፡እገድላለኹ፡ትለዋለኽ።
24፤እንዲህም፡ኾነ፤በመንገድ፡ላይ፡ባደረበት፡ስፍራ፡እግዚአብሔር፡ተገናኘው፥ሊገድለውም፡ፈለገ።
25፤ሲፓራም፡ሚስቱ፡ባልጩት፡ወሰደች፥የልጇንም፡ሸለፈት፡ገረዘች፥ወደ፡እግሩም፡ጣለችው፦አንተ፡ለእኔ፡የደ ም፡ሙሽራ፡ነኽ፡አለች።
26፤ከርሱም፡ፈቀቅ፡አለ።የዚያን፡ጊዜ፦ስለ፡ግርዛቱ፡አንተ፡የደም፡ሙሽራ፡ነኽ፡አለች።
27፤እግዚአብሔርም፡አሮንን፦ኼደኽ፡በምድረ፡በዳ፡ሙሴን፡ተገናኘው፡አለው፤ኼዶም፡በእግዚአብሔር፡ተራራ፡ተ ገናኘው፥ሳመውም።
28፤ሙሴም፡እግዚአብሔር፡በርሱ፡ዘንድ፡የላከውን፡ቃል፡ዅሉ፡ያዘዘውንም፡ተኣምራት፡ዅሉ፡ለአሮን፡ተናገረው ።
29፤ሙሴና፡አሮንም፡ኼዱ፡የእስራኤልንም፡ልጆች፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ሰበሰቡ።
30፤አሮንም፡እግዚአብሔር፡ለሙሴ፡የነገረውን፡ቃል፡ዅሉ፡ተናገረ፥ተኣምራቱንም፡በሕዝቡ፡ፊት፡አደረገ።
31፤ሕዝቡም፡አመኑ፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡እንደ፡ጐበኘ፡ጭንቀታቸውንም፡እንዳየ፡በሰሙ፡ጊዜ ፥አጐነበሱ፡ሰገዱም።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤ከዚህም፡በዃላ፡ሙሴና፡አሮን፡መጥተው፡ፈርዖንን፡እንዲህ፡አሉት።የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እ ንዲህ፡ይላል፦በምድረ፡በዳ፡በዓል፡ያደርግልኝ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡ልቀቅ።
2፤ፈርዖንም፦ቃሉን፡እሰማ፡ዘንድ፡እስራኤልንስ፡እለቅ፟፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ማን፡ነው፧እግዚአብሔርን፡ አላውቅም፥እስራኤልንም፡ደግሞ፡አልለቅ፟ም፡አለ።
3፤እነርሱም፦የዕብራውያን፡አምላክ፡ተገናኘን፤ቸነፈር፡ወይም፡ሰይፍ፡እንዳይጥልብን፡የሦስት፡ቀን፡መንገ ድ፡በምድረ፡በዳ፡እንድንኼድ፥ለአምላካችን፡ለእግዚአብሔር፡እንድንሠዋ፡እንለምንኻለን፡አሉት።
4፤የግብጽ፡ንጉሥም፦አንተ፡ሙሴ፡አንተም፡አሮን፥ሕዝቡን፡ለምን፡ሥራቸውን፡ታስተዋላችኹ፧ወደ፡ተግባራችኹ ፡ኺዱ፡አላቸው።
5፤ፈርዖንም፦እንሆ፥የምድሩ፡ሕዝብ፡አኹን፡በዝቷል፥እናንተም፡ሥራቸውን፡ታስፈቷቸዋላችኹ፡አለ።
6፤ፈርዖንም፡በዚያን፡ቀን፡የሕዝቡን፡አስገባሪዎች፡ሹማምቶቹንም፡እንዲህ፡ሲል፡አዘዘ።
7፤እንደ፡ወትሮው፡ለጡብ፡ሥራ፡ደግሞ፡ገለባ፡ለሕዝቡ፡አትስጡ፤ነገር፡ግን፥እነርሱ፡ኼደው፡ገለባ፡ይሰብስ ቡ።
8፤ቀድሞ፡ያደርጉት፡የነበረውን፡የጡብ፡ቍጥር፡በእነርሱ፡ላይ፡አድርጉት፤ምንም፡ከርሱ፡አታጕድሉ፤ሥራ፡ሰ ልችተዋልና፥ስለዚህ፦ለአምላካችን፡እንድንሠዋ፡እንኺድ፡እያሉ፡ይጮኻሉ።
9፤ርሱንም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡በሰዎች፡ላይ፡ሥራው፡ይክበድባቸው፤ከንቱ፡ቃልም፡አያስቡ።
10፤የሕዝቡም፡አስገባሪዎች፡ሹማምቶቹም፡ወጡ፥ሕዝቡንም፦ፈርዖን፡እንዲህ፡ይላል፦ገለባ፡አልሰጣችኹም።
11፤እናንተ፡ኺዱ፥ከምታገኙበትም፡ስፍራ፡ገለባ፡ሰብስቡ፤ከሥራችኹ፡ግን፡ምንም፡አይጐድልም፡አሏቸው።
12፤ሕዝቡም፡ስለ፡ገለባ፡እብቅ፡ሊሰበስቡ፡በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ተበተኑ።
13፤አስገባሪዎቹም፦ገለባ፡ትቀበሉበት፡እንደ፡ነበረ፡ጊዜ፡የቀን፡ሥራችኹን፡ጨርሱ፡እያሉ፡አስቸኰሏቸው።
14፤የፈርዖንም፡አስገባሪዎች፦ቀድሞ፡ታደርጉ፡እንደ፡ነበራችኹ፡ትናንትናና፡ዛሬ፡የተቈጠረውን፡ጡብ፡ስለ፡ ምን፡አትጨርሱም፧እያሉ፡በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡የተሾሙትን፡አለቃዎቹን፡ገረፉ።
15፤የእስራኤል፡ልጆች፡አለቃዎችም፡ወደ፡ፈርዖን፡መጡ፦ለምን፡በባሪያዎችኽ፡እንዲህ፡ታደርጋለኽ፧
16፤ገለባ፡አይሰጡንም፥የጡቡንም፡ሥራ፡እንድንሠራ፡ያዙ፟ናል፤እንሆም፡ባሪያዎችኽን፡ይገርፉናል፤ግድፈቱ፡ ግን፡ባንተ፡ሕዝብ፡ላይ፡ነው፡ብለው፡ጮኹ።
17፤ርሱ፡ግን፦ሰልችታችዃል፥ሰልችታችዃል፤ስለዚህም፦እንኺድ፥ለእግዚአብሔርም፡እንሠዋ፡ትላላችኹ።
18፤አኹንም፡ኺዱ፥ሥሩ፤ገለባ፡አይሰጧችኹም፥የጡቡን፡ቍጥር፡ግን፡ታመጣላችኹ፡አላቸው።
19፤የእስራኤልም፡ልጆች፡አለቃዎች፦ዕለት፡ዕለት፡ከምትሠሩት፡ከጡቡ፡ቍጥር፡ምንም፡አታጕድሉ፡ባሏቸው፡ጊዜ ፡ነገሩ፡እንደ፡ከፋባቸው፡አዩ።
20፤ከፈርዖንም፡ዘንድ፡ሲወጡ፡ሙሴንና፡አሮንን፡በፊታቸው፡ቆመው፡ተገናኟቸው።
21፤እነርሱም፦በፈርዖንና፡በባሪያዎቹ፡ፊት፡ሽታችንን፡አግምታችኹታልና፥ይገድሉንም፡ዘንድ፡ሰይፍን፡በእጃ ቸው፡ሰጥታችዃቸዋልና፥እግዚአብሔር፡ይመልከታችኹ፥ይፍረድባችኹም፡አሏቸው።
22፤ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ተመለሰና፦ጌታ፡ሆይ፥ስለ፡ምን፡ይህን፡ሕዝብ፡አስከፋኽ፧ስለ፡ምንስ፡ላክኸኝ ፧
23፤በስምኽ፡እናገር፡ዘንድ፡ወደ፡ፈርዖን፡ከገባኹ፡ወዲህ፥ይህን፡ሕዝብ፡አስከፍቶታልና፤አንተም፡ሕዝብኽን ፡ከቶ፡አላዳንኸውም፡አለ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦በጸናች፡እጅ፡ይለቃ፟ችዃልና፥በጸናችም፡እጅ፡ከምድሩ፡አስወጥቶ፡ይሰዳ፟ ቸዋልና፥አኹን፡በፈርዖን፡የማደርገውን፡ታያለኽ።
2፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡ተናገረው፡አለውም፦እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤
3፤ለአብርሃምም፡ለይሥሐቅም፡ለያዕቆብም፡ዅሉን፡እንደሚችል፡አምላክ፡ተገለጥኹ፤ነገር፡ግን፥ስሜ፡እግዚአ ብሔር፡አልታወቀላቸውም፡ነበር።
4፤የተሰደዱባትንም፡ምድር፥የእንግድነታቸውን፡የከነዓንን፡ምድር፥እሰጣቸው፡ዘንድ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪ ዳኔን፡አቆምኹ።
5፤ደግሞ፡እኔ፡ግብጻውያን፡የገዟቸውን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ልቅሶ፡ሰማኹ፤ቃል፡ኪዳኔንም፡ዐሰብኹ።
6፤ስለዚህም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡በላቸው፦እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥ከግብጻውያንም፡ባርነት፡አወጣ ችዃለኹ፥ከተገዢነታቸውም፡አድናችዃለኹ፤በተዘረጋ፡ክንድ፡በታላቅ፡ፍርድም፡እታደጋችዃለኹ፥
7፤ለኔም፡ሕዝብ፡እንድትኾኑ፡እቀበላችዃለኹ፥አምላክም፡እኾናችዃለኹ፤እኔም፡ከግብጻውያን፡ባርነት፡ያወጣ ዃችኹ፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡እንደኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
8፤ለአብርሃምና፡ለይሥሐቅ፡ለያዕቆብም፡እሰጣት፡ዘንድ፡ወደማልኹባት፡ምድር፡አገባችዃለኹ፤ርሷንም፡ርስት ፡አድርጌ፡እሰጣችዃለኹ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
9፤ሙሴም፡ይህን፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ተናገረ፤እነርሱ፡ግን፡ከሰውነታቸው፡መጨነቅ፡ከከባዱም፡ሥራ፡የተነሣ ፡ቃሉን፡አልሰሙትም።
10፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
11፤ግባ፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡ከአገሩ፡ይለቅ፟፡ዘንድ፡ለግብጽ፡ንጉሥ፡ለፈርዖን፡ንገር።
12፤ሙሴም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፦እንሆ፥የእስራኤል፡ልጆች፡አልሰሙኝም፤እንዴትስ፡ፈርዖን፡ይሰማኛል፧ይልቁ ንም፡እኔ፡ከንፈረ፡ቈላፍ፡ነኝ፡ብሎ፡ተናገረ።
13፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡ተናገራቸው፥የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖንም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ እንዲያወጣቸው፡ይነግሩት፡ዘንድ፡አዘዛቸው።
14፤የአባታቸውም፡ቤት፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው።የእስራኤል፡የበኵር፡ልጅ፡የሮቤል፡ልጆች፤ሄኖኅ፥ፈሉስ፥ አስሮን፥ከርሚ፤እነዚህ፡የሮቤል፡ወገኖች፡ናቸው።
15፤የስምዖንም፡ልጆች፤ይሙኤል፥ያሚን፥ኦሃድ፥ያኪን፥ዶሐር፥የከነዓናዊቱም፡ልጅ፡ሳኡል፤እነዚህ፡የስምዖን ፡ወገኖች፡ናቸው።
16፤እነዚህም፡እንደ፡ወገኖቻቸው፡የሌዊ፡ልጆች፡ስሞች፡ጌድሶን፥ቀአት፥ሜራሪ፡ናቸው።የሌዊም፡የሕይወት፡ዘ መን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ዓመት፡ነው።
17፤የጌድሶንም፡ልጆች፡እንደ፡ወገኖቻቸው፡ሎቤኒ፥ሰሜኢ፡ናቸው።
18፤የቀአትም፡ልጆች፡ዕምበረም፥ይስዓር፥ኬብሮን፥ዑዝኤል፡ናቸው፤የቀአትም፡የሕይወቱ፡ዘመን፡መቶ፡ሠላሳ፡ ሦስት፡ዓመት፡ነው።
19፤የሜራሪ፡ልጆች፡ሞሖሊ፥ሙሲ፡ናቸው።እነዚህ፡እንደ፡ትውልዳቸው፡የሌዊ፡ወገኖች፡ናቸው።
20፤ዕምበረምም፡የአጎቱን፡ልጅ፡ዮካብድን፡አገባ፥አሮንና፡ሙሴንም፡ወለደችለት፤የዕምበረምም፡የሕይወቱ፡ዘ መን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ዓመት፡ነው።
21፤የይስአር፡ልጆች፡ቆሬ፥ናፌግ፥ዝክሪ፡ናቸው።
22፤የዑዝኤል፡ልጆች፡ሚሳኤል፥ኤልዳፋን፥ሥትሪ፡ናቸው።
23፤አሮንም፡የዐሚናዳብን፡የነአሶንን፡እኅት፡ኤልሳቤጥን፡አገባ፥ርሷም፡ናዳብንና፡አብዮድን፡አልዓዛርንና ፡ኢታምርን፡ወለደችለት።
24፤የቆሬ፡ልጆች፡አሴር፥ሕልቃና፥አብያሣፍ፡ናቸው፤እነዚህ፡የቆሬ፡ልጆች፡ወገኖች፡ናቸው።
25፤የአሮንም፡ልጅ፡አልዓዛር፡ከፉትኤል፡ልጆች፡ሚስት፡አገባ፥ርሷም፡ፊንሐስን፡ወለደችለት።እነዚህ፡እንደ ፡ወገኖቻቸው፡የሌዋውያን፡አባቶች፡አለቃዎች፡ናቸው።
26፤እነዚህ፡አሮንና፡ሙሴ፡እግዚአብሔር፦ከግብጽ፡ምድር፡በየሰራዊቶቻቸው፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አውጡ፡ያላ ቸው፡ናቸው።
27፤እነዚህ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ያወጡ፡ዘንድ፡ከግብጽ፡ንጉሥ፡ከፈርዖን፡ጋራ፡የተነጋገሩ፡ናቸው ፤እነዚህ፡ሙሴና፡አሮን፡ናቸው።
28፤እግዚአብሔርም፡በግብጽ፡አገር፡ሙሴን፡በተናገረው፡ቀን፡እንዲህ፡ኾነ፤
29፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፦እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤እኔ፡የምነግርኽን፡ዅሉ፡ለግብጽ፡ንጉሥ፡ለፈርዖን፡ንገር ፡ብሎ፡ተናገረው።
30፤ሙሴም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፦እንሆ፥እኔ፡ከንፈረ፡ቈላፍ፡ነኝ፤እንዴትስ፡ፈርዖን፡ይሰማኛል፧አለ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦እይ፥እኔ፡ለፈርዖን፡አምላክ፡አድርጌኻለኹ፤ወንድምኽም፡አሮን፡ነቢይ፡ይ ኾንልኻል።
2፤ያዘዝኹኽን፡ነገር፡ዅሉ፡አንተ፡ትነግረዋለኽ፤ወንድምኽም፡አሮን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ከአገሩ፡ይለቅ፟ ፡ዘንድ፡ከፈርዖን፡ጋራ፡ይናገራል።
3፤እኔም፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸናለኹ፥በግብጽ፡ምድርም፡ድንቄንና፡ተኣምራቴን፡አበዛለኹ።
4፤ፈርዖንም፡አይሰማችኹም፥እጄንም፡በግብጽ፡ላይ፡አደርጋለኹ፥ሰራዊቴንም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ሕዝቤን፡ በታላቅ፡ፍርድ፡ከግብጽ፡አገር፡አወጣለኹ።
5፤ግብጻውያንም፥እጄን፡በግብጽ፡ላይ፡በዘረጋኹ፡ጊዜ፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡ከመካከላቸው፡ባወጣኹ፡ጊዜ፥ እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
6፤ሙሴና፡አሮንም፡እንዲህ፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡እንዳዘዛቸው፡አደረጉ።
7፤ፈርዖንንም፡በተናገሩት፡ጊዜ፡ሙሴ፡የሰማንያ፡ዓመት፡ሰው፡ነበረ፥አሮንም፡የሰማንያ፡ሦስት፡ዓመት፡ሰው ፡ነበረ።
8፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገራቸው።
9፤ፈርዖን፦ተኣምራትን፡አሳዩኝ፡ሲላችኹ፥አሮንን፦በትርኽን፡ወስደኽ፡እባብ፡እንድትኾን፡በፈርዖን፡ፊት፡ ጣላት፡በለው።
10፤ሙሴና፡አሮንም፡ወደ፡ፈርዖን፡ገቡ፥እግዚአብሔርም፡እንዳዘዛቸው፡እንዲሁ፡አደረጉ፤አሮንም፡በትሩን፡በ ፈርዖንና፡በባሮቹ፡ፊት፡ጣለ፥እባብም፡ኾነች።
11፤ፈርዖንም፡ጠቢባንንና፡መተተኛዎችን፡ጠራ፤የግብጽም፡ጠንቋዮች፡በአስማታቸው፡እንዲሁ፡ደግሞ፡አደረጉ።
12፤እያንዳንዳቸውም፡በትራቸውን፡ጣሉ፥እባቦችም፡ኾኑ፤የአሮን፡በትር፡ግን፡በትራቸውን፡ዋጠች።
13፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገረ፥የፈርዖን፡ልብ፡ጸና፥አልሰማቸውምም።
14፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦የፈርዖን፡ልብ፡ደነደነ፥ሕዝቡንም፡ለመልቀቅ፡እንቢ፡አለ።
15፤ማልደኽ፡ወደ፡ፈርዖን፡ኺድ፤እንሆ፥ወደ፡ውሃ፡ይወጣል፥ትገናኘውም፡ዘንድ፡አንተ፡በወንዝ፡ዳር፡ትቆማለ ኽ፤እባብም፡ኾና፡የተለወጠችውን፡በትር፡በእጅኽ፡ትወስዳለኽ።
16፤እንዲህም፡ትለዋለኽ፦የዕብራውያን፡አምላክ፡እግዚአብሔር፦በምድረ፡በዳ፡እንዲያገለግሉኝ፡ሕዝቤን፡ልቀ ቅ፡ብሎ፡ወዳንተ፡ላከኝ፤እንሆም፡እስከ፡ዛሬ፡አልሰማኽም።
17፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡በዚህ፡ታውቃለኽ፤እንሆ፥እኔ፡የወንዙን ፡ውሃ፡በእጄ፡ባለችው፡በትር፡እመታለኹ፥ውሃውም፡ተለውጦ፡ደም፡ይኾናል።
18፤በወንዙም፡ያሉት፡ዓሣዎች፡ይሞታሉ፥ወንዙም፡ይገማል፤ግብጻውያንም፡የወንዙን፡ውሃ፡ለመጠጣት፡ይጠላሉ።
19፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦አሮንን፦በትርኽን፡ውሰድ፥ደምም፡እንዲኾኑ፡በግብጽ፡ውሃዎች፡በወንዞቻቸ ውም፡በመስኖቻቸውም፡በኩሬዎቻቸውም፡በውሃ፡ማከማቻዎቻቸውም፡ዅሉ፡ላይ፡እጅኽን፡ዘርጋ፡በለው፤በግብጽም፡ አገር፡ዅሉ፡በዕንጨት፡ዕቃና፡በድንጋይ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ደም፡ይኾናል።
20፤ሙሴና፡አሮንም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዛቸው፡እንዲሁ፡አደረጉ፤በትሩንም፡አነሣ፥በፈርዖንና፡በባሪያዎቹ ም፡ፊት፡የወንዙን፡ውሃ፡መታ፤የወንዙም፡ውሃ፡ዅሉ፡ተለውጦ፡ደም፡ኾነ።
21፤በወንዙም፡የነበሩ፡ዓሣዎች፡ሞቱ፤ወንዙም፡ገማ፥ግብጻውያንም፡ከወንዙ፡ውሃ፡ይጠጡ፡ዘንድ፡አልቻሉም፡ደ ሙም፡በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡ነበረ።
22፤የግብጽም፡ጠንቋዮች፡በአስማታቸው፡እንዲሁ፡አደረጉ፤እግዚአብሔርም፡እንደተናገረ፡የፈርዖን፡ልብ፡ጸና ፥አልሰማቸውምም።
23፤ፈርዖንም፡ተመልሶ፡ወደ፡ቤቱ፡ገባ፥ይህንም፡ደግሞ፡በልቡ፡አላኖረውም።
24፤ግብጻውያንም፡ዅሉ፡የወንዙን፡ውሃ፡ይጠጡ፡ዘንድ፡አልቻሉምና፡በወንዙ፡አጠገብ፡ውሃ፡ሊጠጡ፡ቈፈሩ።
25፤እግዚአብሔርም፡ወንዙን፡ከመታ፡በዃላ፡ሰባት፡ቀን፡ተፈጸመ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡ተናገረው፦ወደ፡ፈርዖን፡ግባ፡እንዲህም፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ያ ገለግለኝ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡ልቀቅ።
2፤ለመልቀቅ፡እንቢ፡ብትል፡ግን፥እንሆ፥እኔ፡አገርኽን፡ዅሉ፡በጓጕንቸሮች፡እመታለኹ፤
3፤ወንዙም፡ጓጕንቸሮችን፡ያፈላል፥ወጥተውም፡ወደ፡ቤትኽ፥ወደ፡መኝታ፡ቤትኽ፥ወደ፡ዐልጋኽም፥ወደባሪያዎች ኽም፡ቤት፥በሕዝብኽም፡ላይ፥ወደ፡ምድጆችኽም፥ወደ፡ቡሓቃዎችኽም፡ይገባሉ፤
4፤ጓጕንቸሮችም፡ባንተ፡በሕዝብኽም፡በባሪያዎችም፡ዅሉ፡ላይ፡ይወጣሉ።
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦አሮንን፦በትርኽን፡ይዘኽ፡በወንዞቹና፡በመስኖቹ፡በውሃ፡ማከማቻዎቹም፡ላ ይ፡እጅኽን፡ዘርጋ፥በግብጽም፡አገር፡ላይ፡ጓጕንቸሮችን፡አውጣ፡በለው።
6፤አሮንም፡በግብጽ፡ውሃዎች፡ላይ፡እጁን፡ዘረጋ፤ጓጕንቸሮቹም፡ወጡ፥የግብጽንም፡አገር፡ሸፈኑ።
7፤ጠንቋዮችም፡በአስማታቸው፡እንዲህ፡አደረጉ፥በግብጽም፡አገር፡ላይ፡ጓጕንቸሮችን፡አወጡ።
8፤ፈርዖንም፡ሙሴንና፡አሮንን፡ጠርቶ፦ጓጕንቸሮቹን፡ከእኔ፡ከሕዝቤም፡እንዲያርቅ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸል ዩልኝ፤ለእግዚአብሔርም፡ይሠዋ፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡እለቃ፟ለኹ፡አላቸው።
9፤ሙሴም፡ፈርዖንን፦ጓጕንቸሮቹ፡ከአንተ፡ከቤቶችኽም፡እንዲጠፉ፥በወንዙም፡ብቻ፡እንዲቀሩ፥ለአንተ፡ለባሪ ያዎችኽም፡ለሕዝብኽም፡መቼ፡እንድጸልይ፡አስታውቀኝ፡አለው።ርሱም፦ነገ፥አለ።
10፤ሙሴም፦አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡የሚመስል፡እንደሌለ፡ታውቅ፡ዘንድ፡እንደ፡ቃልኽ፡ይኹን።
11፤ጓጕንቸሮቹም፡ከአንተ፡ከቤቶችኽም፡ከባሪያዎችኽም፡ከሕዝብኽም፡ይኼዳሉ፤በወንዙም፡ብቻ፡ይቀራሉ፡አለ።
12፤ሙሴና፡አሮንም፡ከፈርዖን፡ዘንድ፡ወጡ፤ሙሴም፡በፈርዖን፡ላይ፡ስላመጣቸው፡ጓጕንቸሮች፡ወደ፡እግዚአብሔ ር፡ጮኸ።
13፤እግዚአብሔርም፡ሙሴ፡እንዳለ፡አደረገ፤ጓጕንቸሮቹም፡ከቤት፣ከወጀድም፣ከሜዳም፡ሞቱ።
14፤እንደ፡ክምርም፡አድርገው፡ሰበሰቧቸው፤ምድርም፡ገማች።
15፤ፈርዖንም፡ጸጥታ፡እንደ፡ኾነ፡ባየ፡ጊዜ፡ልቡን፡አደነደነ፤እግዚአብሔርም፡እንደተናገረ፡አልሰማቸውም።
16፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦አሮንን፦በትርኽን፡ዘርጋ፥በግብጽም፡አገር፡ዅሉ፡ቅማል፡እንዲኾን፡የምድ ሩን፡ትቢያ፡ምታ፡በለው።
17፤እንዲሁም፡አደረጉ፤አሮንም፡እጁን፡ዘረጋ፥በበትሩም፡የምድሩን፡ትቢያ፡መታው፥በሰውና፡በእንስሳም፡ላይ ፡ቅማል፡ኾነ፤በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡የምድር፡ትቢያ፡ዅሉ፡ቅማል፡ኾነ።
18፤ጠንቋዮችም፡በአስማታቸው፡ያወጡ፡ዘንድ፡እንዲሁ፡አደረጉ፥ነገር፡ግን፥አልቻሉም፤ቅማሉም፡በሰውና፡በእ ንስሳ፡ላይ፡ነበረ።
19፤ጠንቋዮችም፡ፈርዖንን፦ይህስ፡የእግዚአብሔር፡ጣት፡ነው፡አሉት፤የፈርዖን፡ልብ፡ግን፡ጸና፥እግዚአብሔር ም፡እንደ፡ተናገረ፡አልሰማቸውም።
20፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ማልደኽ፡ተነሣ፥በፈርዖንም፡ፊት፡ቁም፤እንሆ፥ርሱ፡ወደ፡ውሃ፡ይወርዳል፤ እንዲህም፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲያገለግለኝ፡ሕዝቤን፡ልቀቅ።
21፤ሕዝቤንም፡ባትለቅ፟፥እንሆ፥ባንተ፡በባሪያዎችኽም፡በሕዝብኽም፡በቤቶችኽም፡ላይ፡የዝንብ፡መንጋዎች፡እ ሰዳ፟ለኹ፤የግብጻውያን፡ቤቶች፡የሚኖሩባትም፡ምድር፡ዅሉ፡በዝንብ፡መንጋዎች፡ይሞላሉ።
22፤በዚያን፡ቀን፡በምድር፡መካከል፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደኾንኹ፡ታውቅ፡ዘንድ፥በዚያ፡የዝንብ፡መንጋ፡እ ንዳይኾን፡ሕዝቤ፡የሚቀመጥባትን፡የጌሤምን፡ምድር፡እለያለኹ።
23፤በሕዝቤና፡በሕዝብኽ፡መካከል፡እለያለኹ፤ይህም፡ተኣምራት፡ነገ፡ይኾናል።
24፤እግዚአብሔርም፡እንዲሁ፡አደረገ፤በፈርዖንም፡ቤት፡በባሪያዎቹም፡ቤቶች፡ውስጥ፡ብዙ፡የዝንብ፡መንጋ፡መ ጣ፤በግብጽም፡አገር፡ዅሉ፡ላይ፡ከዝንቡ፡መንጋ፡የተነሣ፡ምድር፡ጠፋች።
25፤ፈርዖንም፡ሙሴንና፡አሮንን፡ጠርቶ፦ኺዱ፥በአገሩ፡ውስጥ፡ለአምላካችኹ፡ሠዉ፡አላቸው።
26፤ሙሴም፦ለእግዚአብሔር፡ለአምላካችን፡የግብጻውያንን፡ርኵሰት፡እንሠዋለንና፡እንዲህ፡ይደረግ፡ዘንድ፡አ ይገ፟ባ፟ም፤እንሆ፥እኛ፡የግብጻውያንን፡ርኵሰት፡በፊታቸው፡ብንሠዋ፡አይወግሩንምን፧
27፤እኛስ፡ለእግዚአብሔር፡ለአምላካችን፡እንሠዋ፡ዘንድ፡እንደሚያዘ፟ን፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ፡ወደ፡ምድረ ፡በዳ፡እንኼዳለን፡አለ።
28፤ፈርዖንም፦ለእግዚአብሔር፡ለአምላካችኹ፡በምድረ፡በዳ፡ትሠዉ፡ዘንድ፡እለቃ፟ችዃለኹ፤ነገር፡ግን፥ርቃች ኹ፡አትኺዱ፥ጸልዩልኝ፡አለ።
29፤ሙሴም፦እንሆ፥ከአንተ፡ዘንድ፡እወጣለኹ፥የዝንቡም፡መንጋዎች፡ከፈርዖን፡ከባሪያዎቹም፡ከሕዝቡም፡ነገ፡ እንዲኼዱ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እጸልያለኹ፤ነገር፡ግን፥ለእግዚአብሔር፡ይሠዋ፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡እንዳይለቅ፟ ፡ፈርዖን፡እንደገና፡አያታለ፟ን፥አለ።
30፤ሙሴም፡ከፈርዖን፡ዘንድ፡ወጣ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጸለየ።
31፤እግዚአብሔርም፡ሙሴ፡እንዳለ፡አደረገ፤የዝንቡንም፡መንጋዎች፡ከፈርዖን፡ከባሪያዎቹም፡ከሕዝቡም፡አስነ ሣ፤አንድ፡ስንኳ፡አልቀረም።
32፤ፈርዖንም፡በዚህ፡ጊዜ፡ደግሞ፡ልቡን፡አደነደነ፥ሕዝቡንም፡አልለቀቀም።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ወደ፡ፈርዖን፡ዘንድ፡ገብተኽ፡ንገረው።የዕብራውያን፡አምላክ፡እግዚአብሔ ር፡እንዲህ፡ይላል፦ያገለግሉኝ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡ልቀቅ።
2፤ልትለቃ፟ቸውም፡እንቢ፡ብትል፡ብትይዛቸውም፥
3፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡እጅ፡በሜዳ፡ውስጥ፡ባሉት፡በከብቶችኽ፥በፈረሶችም፡በአህያዎችም፡በግመሎችም፡በ በሬዎችም፡በበጎችም፡ላይ፡ትኾናለች፤ብርቱ፡ቸነፈርም፡ይወርዳል።
4፤እግዚአብሔርም፡በእስራኤልና፡በግብጽ፡ከብቶች፡መካከል፡ይለያል፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ከብት፡አንዳች፡ አይጠፋም።
5፤እግዚአብሔርም፦ነገ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ነገር፡በምድር፡ላይ፡ያደርጋል፡ብሎ፡ጊዜን፡ወሰነ።
6፤እግዚአብሔርም፡ያንን፡ነገር፡በነጋው፡አደረገ፥የግብጽም፡ከብት፡ዅሉ፡ሞተ፤ከእስራኤል፡ልጆች፡ከብት፡ ግን፡አንድ፡ስንኳ፡አልሞተም።
7፤ፈርዖንም፡ላከ፥እንሆም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ከብት፡አንድ፡ስንኳ፡አልሞተም።የፈርዖን፡ልብ፡ግን፡ደነደ ነ፥ሕዝቡንም፡አልለቀቀም።
8፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፦እጃችኹን፡ሞልታችኹ፡ከምድጃ፡ዐመድ፡ውሰዱ፥ሙሴም፡በፈርዖን፡ፊት፡ወ ደ፡ሰማይ፡ይበትነው።
9፤ርሱም፡በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡ትቢያ፡ይኾናል፥በግብጽም፡አገር፡ዅሉ፡በሰውና፡በእንስሳ፡ላይ፡ሻሕኝ፡የሚ ያመጣ፡ቍስል፡ይኾናል፡አላቸው።
10፤ከምድጃውም፡ዐመድ፡ወስደው፡በፈርዖን፡ፊት፡ቆሙ፤ሙሴም፡ወደ፡ሰማይ፡በተነው፥በሰውና፡በእንስሳም፡ላይ ፡ሻሕኝ፡የሚያወጣ፡ቍስል፡ኾነ።
11፤ጠንቋዮችም፡ቍስል፡ስለ፡ነበረባቸው፡በሙሴ፡ፊት፡መቆም፡አልቻሉም፤ቍስል፡በጠንቋዮችና፡በግብጻውያን፡ ዅሉ፡ላይ፡ነበረና።
12፤እግዚአብሔርም፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸና፤እግዚአብሔር፡ለሙሴ፡እንደተናገረው፡አልሰማቸውም።
13፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ማልደኽ፡ተነሣ፥በፈርዖንም፡ፊት፡ቆመኽ፡በለው፦የዕብራውያን፡አምላክ፡እ ግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲያገለግሉኝ፡ሕዝቤን፡ልቀቅ።
14፤በምድር፡ዅሉ፡እንደ፡እኔ፡ያለ፡እንደሌለ፡ታውቅ፡ዘንድ፡በሰውነትኽ፡በባሪያዎችኽም፡በሕዝብኽም፡ላይ፡ መቅሠፍቴን፡ዅሉ፡አኹን፡እልካለኹ።
15፤አኹን፡እጄን፡ዘርግቼ፡አንተን፡ሕዝብኽንም፡በቸነፈር፡በመታኹኽ፡ነበር፥አንተም፡ከምድር፡በጠፋኽ፡ነበ ር፤
16፤ነገር፡ግን፥ኀይሌን፡እገልጥብኽ፡ዘንድ፡ስሜም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ይነገር፡ዘንድ፡ስለዚህ፡አስነሥቼኻ ለኹ።
17፤እንዳትለቃ፟ቸው፡ገና፡በሕዝቤ፡ላይ፡ትታበያለኽን፧
18፤እንሆ፥ነገ፡በዚህ፡ጊዜ፥ከተመሠረተች፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እንደ፡ርሱ፡ያለ፡በግብጽ፡ኾኖ፡የማያ ውቅ፥እጅግ፡ታላቅ፡በረዶ፡አዘንብብኻለኹ።
19፤በሜዳ፡የተገኘ፡ወደ፡ቤት፡ያልገባ፡ሰውና፡እንስሳ፡ዅሉ፡በረዶ፡ወርዶበት፡ይሞታልና፥አኹን፡እንግዲህ፡ ላክ፥ከብቶችኽንም፡በሜዳም፡ያለኽን፡ዅሉ፡አስቸኵል።
20፤ከፈርዖንም፡ባሪያዎች፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡የፈራ፡ባሪያዎቹንና፡ከብቶቹን፡ወደ፡ቤቶቹ፡አሸሸ፤
21፤የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ያላሰበ፡ባሪያዎቹንና፡ከብቶቹን፡በሜዳ፡ተወ።
22፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በግብጽ፡አገር፡በሰው፡በእንስሳም፡በዕርሻም፡ቡቃያ፡ዅሉ፡ላይ፥በግብጽ፡አገር፡ ዅሉ፡በረዶ፡ይኾን፡ዘንድ፡እጅኽን፡ወደ፡ሰማይ፡ዘርጋ፡አለው።
23፤ሙሴም፡በትሩን፡ወደ፡ሰማይ፡ዘረጋ፤እግዚአብሔርም፡ነጐድጓድና፡በረዶ፡ላከ፥እሳትም፡ወደ፡ምድር፡ወረደ ፤እግዚአብሔርም፡በግብጽ፡አገር፡ላይ፡በረዶ፡አዘነበ።
24፤በረዶም፡ነበረ፥በበረዶውም፡መካከል፡እሳት፡ይቃጠል፡ነበር፥በረዶውም፡በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡ሕዝብ፡ከኾ ነ፡ዠምሮ፡እንደ፡ርሱ፡ያልኾነ፡እጅግ፡ታላቅ፡ነበረ።
25፤በረዶውም፡በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡በሜዳ፡ያለውን፡ዅሉ፡ሰውንና፡እንስሳን፡መታ፤በረዶውም፡የዕርሻን፡ቡቃ ያ፡ዅሉ፡መታ፥የአገሩንም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ሰበረ።
26፤የእስራኤል፡ልጆች፡ተቀምጠው፡በነበሩባት፡በጌሤም፡አገር፡ብቻ፡በረዶ፡አልወረደም።
27፤ፈርዖንም፡ልኮ፡ሙሴንና፡አሮንን፡ጠራ፦በዚህ፡ጊዜ፡በደልኹ፤እግዚአብሔር፡ጻድቅ፡ነው፥እኔና፡ሕዝቤም፡ ኀጢአተኛዎች፡ነን።
28፤የአምላክ፡ነጐድጓድ፣በረዶውም፡በዝቷልና፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልዩ፤እለቃ፟ችኹማለኹ፥ከዚያም፡በዃላ፡ በዚህ፡አትቀመጡም፡አላቸው።
29፤ሙሴም፦ከከተማ፡በወጣኹ፡ጊዜ፡እጄን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እዘረጋለኹ፤ምድሪቱ፡ለእግዚአብሔር፡እንደ፡ኾ ነች፡ታውቅ፡ዘንድ፡ነጐድጓዱ፡ይቀራል፥በረዶውም፡ደግሞ፡አይወርድም።
30፤ነገር፡ግን፥አንተና፡ባሪያዎችኽ፡አምላክን፡እግዚአብሔርን፡ገና፡እንደማትፈሩ፡ዐውቃለኹ፡አለው።
31፤ገብሱ፡አሽቶ፣ተልባውም፡አፍርቶ፡ነበርና፥ተልባና፡ገብሱ፡ተመታ።
32፤ስንዴውና፡ዐጃው፡ግን፡ጊዜው፡ገና፡ነበርና፥አልተመታም።
33፤ሙሴም፡ከፈርዖን፡ዘንድ፡ከከተማ፡ወጣ፥እጁንም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ዘረጋ፤ነጐድጓዱም፡በረዶውም፡ተቋረ ጠ፥ዝናቡም፡በምድር፡ላይ፡አልፈሰሰም።
34፤ፈርዖንም፡ዝናቡ፡በረዶውም፡ነጐድጓዱም፡እንደ፡ተቋረጠ፡ባየ፡ጊዜ፡ኀጢአትን፡ጨመረ፥ርሱና፡ባሪያዎቹም ፡ልባቸውን፡አደነደኑ።
35፤የፈርዖንም፡ልብ፡ጸና፤እግዚአብሔርም፡በሙሴ፡አፍ፡እንደተናገር፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አልለቀቀም።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤2፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቁ፡ዘንድ፥በግብጻውያን፡ያደረግኹትን፡ነ ገር፥ያደረግኹባቸውንም፡ተኣምራቴን፥በልጅኽ፡በልጅ፡ልጅኽም፡ዦሮዎች፡ትነግር፡ዘንድ፥ይህችንም፡ተኣምራቴ ን፡በመካከላቸው፡አደርግ፡ዘንድ፥የርሱን፡የባሪያዎቹንም፡ልብ፡አደንድኛለኹና፥ወደ፡ፈርዖን፡ግባ፡አለው።
3፤ሙሴም፡አሮንም፡ወደ፡ፈርዖን፡ገቡ፥አሉትም፦የዕብራውያን፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በፊቴ ፡ለመዋረድ፡እስከ፡መቼ፡እንቢ፡ትላለኽ፧ያገለግሉኝ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡ልቀቅ።
4፤ሕዝቤን፡ለመልቀቅ፡እንቢ፡ብትል፡ግን፥እንሆ፥ነገ፡በአገርኽ፡አንበጣዎችን፡አመጣለኹ፤
5፤የምድሩንም፡ፊት፡ይሸፍኑታልና፥ምድሩን፡ለማየት፡አይቻልም፤ከበረዶውም፡አምልጦ፡የተረፈላችኹን፡ትርፍ ፡ይበሉታል፥ያደገላችኹንም፡የዕርሻውን፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይበሉታል፤
6፤ቤቶችኽም፡የባሪያዎችኽም፡ዅሉ፡ቤቶች፡የግብጻውያንም፡ዅሉ፡ቤቶች፡በእነርሱ፡ይሞላል፤አባቶችኽ፡የአባ ቶችኽም፡አባቶች፡በምድር፡ላይ፡ከተቀመጡበት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከዚህ፡ቀን፡ድረስ፡እንደ፡ርሱ፡ያለ፡ያላዩት ፡ነው።ተመልሶም፡ከፈርዖን፡ዘንድ፡ወጣ።
7፤የፈርዖንም፡ባሪያዎች፦ይህ፡ሰው፡እስከ፡መቼ፡ዕንቅፋት፡ይኾንብናል፧አምላካቸውን፡እግዚአብሔርን፡ያገ ለግሉት፡ዘንድ፡ሰዎችን፡ልቀቅ፡ግብጽስ፡እንደ፡ጠፋች፡ገና፡አታውቅምን፧አሉት።
8፤ፈርዖንም፡ሙሴንና፡አሮንን፡መልሶ፡አስመጣቸው።ኺዱ፥አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡አገልግሉ፤ነገር፡ግ ን፥የሚኼዱት፡እነማን፡ናቸው፧አላቸው።
9፤ሙሴም፦እኛ፡እንኼዳለን፥የእግዚአብሔር፡በዓል፡ኾኖልናልና፥ታናናሾቻችንና፡ሽማግሌዎቻችን፡ወንዶችና፡ ሴቶች፡ልጆቻችንም፡በጎቻችንና፡ከብቶቻችንም፡ከእኛ፡ጋራ፡ይኼዳሉ፡አለ።
10፤ፈርዖንም፦እናንተን፡ከልጆቻችኹ፡ጋራ፡ስለቅ፟፡እግዚአብሔር፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኹን፤ነገር፡ግን፥ክፉ፡ ነገር፡በፊታችኹ፡እንደሚኾን፡ተመልከቱ።
11፤እንዲህም፡አይደለም፤እናንተ፡ወንዶቹ፡ኺዱ፥ይህን፡ፈልጋችዃልና፥እግዚአብሔርን፡አገልግሉ፡አላቸው።ከ ፈርዖንም፡ፊት፡አባረሯቸው።
12፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በግብጽ፡አገር፡ላይ፡እንዲወጡ፥ከበረዶውም፡የተረፈውን፡የምድርን፡ቡቃያ፡ዅሉ፡ እንዲበሉ፥ስለ፡አንበጣዎች፡በግብጽ፡አገር፡ላይ፡እጅኽን፡ዘርጋ፡አለው።
13፤ሙሴም፡በግብጽ፡አገር፡ላይ፡በትሩን፡ዘረጋ፥እግዚአብሔርም፡የምሥራቅን፡ነፋስ፡ያን፡ቀን፡ዅሉ፡ሌሊቱን ፡ዅሉ፡አመጣ፤ማለዳም፡በኾነ፡ጊዜ፡የምሥራቁ፡ነፋስ፡አንበጣዎቹን፡አመጣ።
14፤አንበጣዎችም፡በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡ላይ፡ወጡ፥በግብጽም፡ዳርቻ፡ዅሉ፡ላይ፡ተቀመጡ፤እጅግም፡ብዙ፡ነበሩ ፤ይህንም፡የሚያኽል፡አንበጣ፡በፊት፡አልነበረም፥ወደ፡ፊትም፡ደግሞ፡እንደ፡ርሱ፡አይኾንም።
15፤የምድሩንም፡ፊት፡ፈጽመው፡ሸፈኑት፡አገሪቱም፡ጨለመች፤የአገሪቱን፡ቡቃያ፡ዅሉ፡በረዶውም፡የተወውን፡በ ዛፉ፡የነበረውን፡ፍሬ፡ዅሉ፡በሉ፤ለምለም፡ነገር፡ዛፍም፡የምድር፡ሣርም፡በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡አልቀረም።
16፤ፈርዖንም፡ሙሴንና፡አሮንን፡በፍጥነት፡ጠራ፦አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡እናንተንም፡በደልኹ፤
17፤አኹን፡እንግዲህ፡በዚህ፡ጊዜ፡ብቻ፡ኀጢአቴን፡ይቅር፡በሉኝ፥ይህንም፡ሞት፡ብቻ፡ከእኔ፡ያነሣልኝ፡ዘንድ ፡አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ለምኑ፡አላቸው።
18፤ሙሴም፡ከፈርዖን፡ፊት፡ወጣ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ለመነ።
19፤እግዚአብሔርም፡ከምዕራብ፡ዐውሎ፡ነፋሱን፡አስወገደ፥አንበጣዎችንም፡ወስዶ፡በቀይ፡ባሕር፡ውስጥ፡ጣላቸ ው፤አንድ፡አንበጣም፡በግብጽ፡ዳርቻ፡ዅሉ፡አልቀረም።
20፤እግዚአብሔር፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸና፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡አልለቀቀም።
21፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦እጅኽን፡ወደ፡ሰማይ፡ዘርጋ፥በግብጽም፡አገር፡ላይ፡ሰው፡የሚዳስሰው፡ጽኑ፡ጨለማ ፡ይኹን፡አለው።
22፤ሙሴም፡እጁን፡ወደ፡ሰማይ፡ዘረጋ፥በግብጽም፡አገር፡ዅሉ፡ላይ፡ጽኑ፡ጨለማ፡ሦስት፡ቀን፡ኾነ፤
23፤ማንም፡ወንድሙን፡አላየም፥ሦስት፡ቀንም፡ሙሉ፡ከስፍራው፡ማንም፡አልተነሣም፤ለእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ግ ን፡በተቀመጡበት፡ስፍራ፡ብርሃን፡ነበራቸው።
24፤ፈርዖንም፡ሙሴን፡ጠርቶ፦ኺዱ፥እግዚአብሔርን፡አገልግሉ፤ነገር፡ግን፥በጎቻችኹንና፡ከብቶቻችኹን፡ተዉ፤ ልጆቻችኹ፡ደግሞ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኺዱ፡አለው።
25፤ሙሴም፦አንተ፡ደግሞ፡ለአምላካችን፡ለእግዚአብሔር፡የምንሠዋው፡መሥዋዕትንና፡የሚቃጠል፡መሥዋዕትን፡ት ሰጠናለኽ።
26፤አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡ለማገልገል፡ከነርሱ፡እንወስዳለንና፡ከብቶቻችን፡ከእኛ፡ጋራ፡ይኼዳሉ፥አ ንድ፡ሰኰናም፡አይቀርም፤አምላካችን፡የምናገለግለው፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ከዚያ፡እስክንደርስ፡አናውቅም፡አለ ።
27፤እግዚአብሔር፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸና፥ሊለቃ፟ቸውም፡አልወደደም።
28፤ፈርዖንም፦ከእኔ፡ዘንድ፡ኺድ፤ፊቴን፡ባየኽበት፡ቀን፡ትሞታለኽና፡ፊቴን፡እንዳታይ፡ተጠንቀቅ፡አለው።
29፤ሙሴም፦እንደ፡ተናገርኽ፡ይኹን፤ፊትኽን፡እንደ፡ገና፡አላይም፡አለ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በፈርዖንና፡በግብጽ፡ላይ፡ገና፡አንዲት፡መቅሠፍት፡አመጣለኹ፥ከዚያ፡ወዲያም፡ይ ለቃ፟ችዃል፤ሲለቃ፟ችኹም፡አባሮ፟፡ይሰዳ፟ችዃል።
2፤ወንዱ፡ከወዳጁ፡ሴቲቱም፡ከወዳጇ፡የብርና፡የወርቅ፡ዕቃ፡ይሹ፡ዘንድ፡በሕዝቡ፡ዦሮ፡ተናገር፡አለው።
3፤እግዚአብሔርም፡በግብጻውያን፡ፊት፡ለሕዝቡ፡ሞገስን፡ሰጠው።ሙሴም፡በፈርዖን፡ባሪያዎችና፡በሕዝቡ፡ፊት ፡በግብጽ፡አገር፡እጅግ፡የከበረ፡ሰው፡ነበረ።
4፤ሙሴም፡አለ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእኩል፡ሌሊት፡እኔ፡በግብጽ፡መካከል፡እወጣለኹ፤
5፤በግብጽም፡አገር፡ያለ፡በኵር፡ዅሉ፥በዙፋኑ፡ከሚቀመጠው፡ከፈርዖን፡በኵር፡ዠምሮ፥በወፍጮ፡እግር፡እስካ ለችው፡እስከባሪያዪቱ፡በኵር፡ድረስ፥የከብቱም፡በኵር፡ዅሉ፡ይሞታል።
6፤በግብጽም፡አገር፡ዅሉ፡አስቀድሞ፡እንደ፡ርሱ፡ያልኾነ፡ዃላም፡ደግሞ፡የማይኾን፡ታላቅ፡ጩኸት፡ይኾናል።
7፤እግዚአብሔር፡ግን፡በግብጻውያንና፡በእስራኤል፡መካከል፡እንዲለይ፡እንድታውቁ፡በእስራኤል፡ልጆች፡መካ ከል፡ከሰው፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡ውሻ፡ምላሱን፡አያንቀሳቅስባቸውም።
8፤እነዚህም፡ባሪያዎችኽ፡ዅሉ፦አንተ፡ውጣ፡የሚከተሉኽም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ይውጡ፡እያሉ፡ወደ፡እኔ፡ይወርዳሉ፥ ለኔም፡ይሰግዳሉ፤ከዚያም፡በዃላ፡እወጣለኹ።ሙሴም፡በጽኑ፡ቍጣ፡ከፈርዖን፡ዘንድ፡ወጣ።
9፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ተኣምራቴ፡በግብጽ፡አገር፡ብዙ፡እንዲኾን፡ፈርዖን፡አይሰማችኹም፡አለው።
10፤ሙሴና፡አሮንም፡እነዚህን፡ተኣምራቶች፡ዅሉ፡በፈርዖን፡ፊት፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡የፈርዖንን፡ልብ፡አ ጸና፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡ከአገሩ፡አልለቀቀም።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤እግዚአብሔርም፡በግብጽ፡አገር፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦
2፤ይህ፡ወር፡የወሮች፡መዠመሪያ፡ይኹናችኹ፤የዓመቱም፡መዠመሪያ፡ወር፡ይኹናችኹ።
3፤ለእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ተናገሩ፥በሏቸውም፦በዚህ፡ወር፡በዐሥረኛው፡ቀን፡ሰው፡ዅሉ፡ለአባቱ፡ቤት፡አን ድ፡ጠቦት፥ላንድ፡ቤትም፡አንድ፡ጠቦት፡ይውሰድ።
4፤የቤቱ፡ሰዎች፡ቍጥርም፡ለጠቦቱ፡የማይበቃ፡ቢኾን፡ርሱና፡ለቤቱ፡የቀረበው፡ጎረቤቱ፡እንደ፡ነፍሶቻቸው፡ ቍጥር፡አንድ፡ጠቦት፡ይውሰድ፤እያንዳንዱም፡እንደሚበላው፡መጠን፡ከጠቦቱ፡ይካፈሉ።
5፤የእናንተ፡ጠቦት፡ነውር፡የሌለበት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ይኹን፤ከበጎች፡ወይም፡ከፍየሎች፡ውሰድ።
6፤በዚህም፡ወር፡እስከ፡ዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ድረስ፡ጠብቁት፤የእስራኤልም፡ማኅበር፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ሲመሽ፡ ይረዱት።
7፤ከደሙም፡ወስደው፡በሚበሉበት፡ቤት፡ኹለቱን፡መቃንና፡ጕበኑን፡ይቅቡት።
8፤በእሳት፡የተጠበሰውን፡ሥጋውንና፡ቂጣውን፡እንጀራ፡በዚያች፡ሌሊት፡ይብሉ፤ከመራራ፡ቅጠል፡ጋራ፡ይበሉታ ል።
9፤ጥሬውን፡በውሃም፡የበሰለውን፡አትብሉ፥ነገር፡ግን፥ከራሱ፡ከጭኑ፡ከሆድ፡ዕቃው፡ጋራ፡በእሳት፡የተጠበሰ ውን፡ብሉት።
10፤ከርሱም፡እስከ፡ጧት፡አንዳች፡አታስቀሩ፤እስከ፡ጧትም፡የቀረውን፡በእሳት፡አቃጥሉት።
11፤ወገቦቻችኹን፡ታጥቃችኹ፥ጫማችኹን፡በእግራችኹ፥በትራችኹንም፡በእጃችኹ፡አድርጋችኹ፡እንዲህ፡ብሉት፥ፈ ጥናችኹም፡ትበሉታላችኽ፤ርሱ፡የእግዚአብሔር፡ፋሲካ፡ነው።
12፤እኔም፡በዚያች፡ሌሊት፡በግብጽ፡አገር፡ዐልፋለኹ፥በግብጽም፡አገር፡ከሰው፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡በኵር ን፡ዅሉ፡እገድላለኹ፤በግብጽም፡አማልክት፡ዅሉ፡ላይ፡እፈርድባቸዋለኹ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
13፤ደሙም፡ባላችኹበት፡ቤቶች፡ምልክት፡ይኾንላችዃል፤ደሙንም፡ባየኹ፡ጊዜ፡ከእናንተ፡ዐልፋለኹ፤እኔም፡የግ ብጽን፡አገር፡በመታኹ፡ጊዜ፡መቅሠፍቱ፡ለጥፋት፡አይመጣባችኹም።
14፤ይህም፡ቀን፡መታሰቢያ፡ይኹናችኹ፥ለእግዚአብሔርም፡በዓል፡ታደርጉታላችኹ፤ለልጅ፡ልጃችኹ፡ሥርዐት፡ኾኖ ፡ለዘለዓለም፡ታደርጉታላችኹ።
15፤ሰባት፡ቀን፡ቂጣ፡እንጀራ፡ትበላላችኹ፤በመዠመሪያም፡ቀን፡ርሾውን፡ከቤታችኹ፡ታወጣላችኹ፤ከመዠመሪያው ም፡ቀን፡አንሥቶ፡እስከ፡ሰባተኛው፡ቀን፡ርሾ፡ያለበትን፡እንጀራ፡የሚበላ፡ነፍስ፡ከእስራኤል፡ተለይቶ፡ይጥ ፋ።
16፤በመዠመሪያውም፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡እንዲሁም፡በሰባተኛውም፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኾንላችዃል።ከ ሚበላው፡በቀር፡በእነርሱም፡ምንም፡አትሠሩም፥ይህንም፡ብቻ፡ታደርጉታላችኹ።
17፤በዚህም፡ቀን፡ሰራዊታችኹን፡ከግብጽ፡አገር፡አውጥቻለኹና፡የቂጣውንም፡በዓል፡ጠብቁት፤እንግዲህ፡ይህን ፡ቀን፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡ለዘለዓለም፡ሥርዐት፡ትጠብቃላችኹ።
18፤በመዠመሪያውም፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡በመሸ፡ጊዜ፡ከወሩም፡እስከ፡ኻያ፡አንድ፡ቀን፡በመሸ፡ጊዜ ፡የቂጣ፡እንጀራ፡ትበላላችኹ።
19፤ሰባት፡ቀን፡በቤታችኹ፡ርሾ፡አይገኝ፤ርሾ፡ያለበትንም፡እንጀራ፡የሚበላ፡ነፍስ፥ከመጻተኛው፡ዠምሮ፡እስ ከአገር፡ልጁ፡ድረስ፥ከእስራኤል፡ማኅበር፡ተለይቶ፡ይጥፋ።
20፤ርሾ፡ያለበትን፡ምንም፡አትብሉ፥በቤቶቻችኹም፡ዅሉ፡ውስጥ፡ቂጣ፡እንጀራ፡ብሉ።
21፤ሙሴም፡የእስራኤልን፡ሽማግሌዎች፡ጠርቶ፡አላቸው፦በየቤታችኹ፡ጠቦት፡ምረጡ፥ወስዳችኹም፡ለፋሲካ፡ዕረዱ ት።
22፤ከሂሶጵ፡ቅጠልም፡ጭብ፟ጥ፡ውሰዱ፥በዕቃ፡ውስጥ፡ባለ፟ውም፡ደም፡ንከሩት፥በዕቃውም፡ውስጥ፡ካለው፡ደም፡ ኹለቱን፡መቃኖችና፡ጕበኑን፡ርጩ፤ከእናንተም፡አንድ፡ሰው፡ከቤቱ፡ደጅ፡እስኪነጋ፡ድረስ፡አይውጣ።
23፤እግዚአብሔር፡ግብጻውያንን፡ይመታ፡ዘንድ፡ያልፋልና፤ደሙንም፡በጕበኑና፡በኹለቱ፡መቃኖች፡ላይ፡ባየ፡ጊ ዜ፡እግዚአብሔር፡በደጁ፡ላይ፡ያልፋል፥አጥፊውም፡ይመታችኹ፡ዘንድ፡ወደ፡ቤታችኹ፡እንዲገባ፡አይተውም።
24፤ለእናንተ፡ለልጆቻችኹም፡ለዘለዓለም፡ሥርዐት፡አድርጋችኹ፡ይህችን፡ነገር፡ጠብቁ።
25፤እንዲህም፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገረ፡ወደሚሰጣችኹ፡አገር፡በገባችኹ፡ጊዜ፡ይህን፡አምልኮ፡ ጠብቁት።
26፤እንዲህም፡ይኾናል፤ልጆቻችኹ፦ይህ፡አምልኮ፡ለእናንተ፡ምንድር፡ነው፧
27፤ባሏችኹ፡ጊዜ፥እናንተ፦በግብጽ፡አገር፡በእስራኤል፡ልጆች፡ቤቶች፡ላይ፡ዐልፎ፡ግብጻውያንን፡በመታ፡ጊዜ ፥ቤቶቻችንን፡ያዳነ፡የእግዚአብሔር፡የማለፉ፡መሥዋዕት፡ይህች፡ናት፡ትሏቸዋላችኹ።
28፤ሕዝቡም፡ተጐነበሰ፥ሰገደም።የእስራኤልም፡ልጆች፡ኼዱ፥እንዲሁም፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡ሙሴንና፡አሮን ን፡እንዳዘዘ፡እንዲሁ፡አደረጉ።
29፤እንዲህም፡ኾነ፤እኩል፡ሌሊት፡በኾነ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፥በዙፋን፡ከተቀመጠው፡ከፈርዖን፡በኵር፡ዠምሮ፡ በግዞት፡እስካሉት፡እስከ፡ምርኮኛዎቹ፡በኵር፡ድረስ፥የግብጻውያንን፡በግብጽ፡ምድር፡የተገኘውን፡በኵር፡ዅ ሉ፥የእንስሳውንም፡በኵሮች፡ዅሉ፡መታ።
30፤ፈርዖንም፡ባሪያዎቹም፡ዅሉ፡ግብጻውያንም፡ዅሉ፡በሌሊት፡ተነሡ፤የሞተ፡የሌለበት፡ቤት፡አልነበረምና፡በ ግብጽ፡ምድር፡ታላቅ፡ልቅሶ፡ኾነ።
31፤ፈርዖንም፡ሙሴንና፡አሮንን፡በሌሊት፡ጠርቶ፦እናንተ፡የእስራኤልም፡ልጆች፡ተነሡ፥ከሕዝቤ፡መካከል፡ውጡ ፤ኺዱም፥እንዳላችኹም፡እግዚአብሔርን፡አገልግሉ፤
32፤እንዳላችኹም፡መንጋዎቻችኹንና፡ከብቶቻችኹን፡ውሰዱ፥ኺዱም፥እኔንም፡ደግሞ፡ባርኩኝ፡አለ።
33፤ግብጻውያንም፡ፈጥነው፡ከምድሩ፡ይወጡ፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡ያስቸኵሏቸው፡ነበር።ዅላችን፡እንሞታለን፡ብለዋ ልና።
34፤ሕዝቡም፡ሊጡን፡ሳይቦካ፡ተሸከሙ፥ቡሓቃውንም፡በልብሳቸው፡ጠቅልለው፡በትከሻቸው፡ተሸከሙት።
35፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ሙሴ፡እንዳዘዘ፡አደረጉ፥ከግብጻውያንም፡የብርንና፡የወርቅን፡ዕቃ፡ልብስንም፡ለመ ኑ።
36፤እግዚአብሔርም፡ለሕዝቡ፡በግብጻውያን፡ፊት፡የፈለጉትን፡እንዲሰጧቸው፡ሞገስን፡ሰጠ።እነርሱም፡ግብጻው ያንን፡በዘበዙ።
37፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከራምሴ፡ተነሥተው፡ወደ፡ሱኮት፡ኼዱ፤ከሕፃናቱም፡ሌላ፡ስድስት፡መቶ፡ሺሕ፡ሰው፡የ ሚያኽል፡እግረኛ፡ነበረ።
38፤ደግሞም፡ሌላ፡ብዙ፡ድብልቅ፡ሕዝብ፡መንጋዎችና፡ላሞችም፡እጅግ፡ብዙም፡ከብቶች፡ከነርሱ፡ጋራ፡ወጡ።
39፤ከግብጽም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ያወጡትን፡ሊጥ፡ጋገሩ፥አልቦካም፡ነበርና፥ቂጣ፡ዕንጐቻ፡አደረጉት፤ግብጻውያን ፡በመውጣት፡ስላስቸኰሏቸው፡ይቈዩ፡ዘንድ፡አልተቻላቸውም፥ሥንቅም፡አላሰናዱም፡ነበር።40፤የእስራኤልም፡ል ጆች፡በግብጽ፡ምድር፡የተቀመጡት፡ዘመን፡አራት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ነው።
41፤እንዲህም፡ኾነ፤አራት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ከተፈጸመ፡በዃላ፡በዚያ፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ ከግብጽ፡ምድር፡ወጣ።
42፤ይህች፡ሌሊት፡ከግብጽ፡ምድር፡ስላወጣቸው፡ለእግዚአብሔር፡የተጠበቀች፡ናት፤ይህች፡ሌሊት፡በእስራኤል፡ ልጆች፡ዅሉ፡ዘንድ፡እስከልጅ፡ልጃቸው፡ድረስ፡ለእግዚአብሔር፡የተጠበቀች፡ናት።
43፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡አለ፦ይህ፡የፋሲካ፡ሕግ፡ነው፤ከርሱ፡እንግዳ፡ሰው፡አይብላ።
44፤በብር፡የተገዛ፡ባሪያ፡ቢኖር፡ከተገረዘ፡በዃላ፡ከርሱ፡ይብላ።
45፤መጻተኛና፡ሞያተኛ፡ግን፡ከርሱ፡አይብሉ።
46፤ባንድ፡ቤትም፡ይበላ፤ከሥጋውም፡አንዳች፡ከቤት፡ወደ፡ሜዳ፡አታውጡ፤ዐጥንትም፡አትስበሩበት።
47፤የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ያድርጉት።
48፤እንግዳ፡ሰውም፡በመካከላችኹ፡ቢቀመጥ፡ለእግዚአብሔርም፡ፋሲካን፡ሊያደርግ፡ቢወድ፟፥አስቀድሞ፡ወንድ፡ ዅሉ፡ይገረዝ፥ከዚያም፡ወዲያ፡ይቅረብ፡ያድርግም፤እንደ፡አገር፡ልጅም፡ይኾናል፤ያልተገረዘ፡ዅሉ፡ግን፡ከር ሱ፡አይብላ።
49፤ለአገር፡ልጅ፡በእናንተ፡መካከልም፡ለሚቀመጡ፡እንግዳዎች፡አንድ፡ሥርዐት፡ይኾናል።
50፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡እንዲህ፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዳዘዘ፡እንዲሁ፡አደረጉ ።
51፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ከሰራዊታቸው፡ጋራ፡ከግብጽ፡ምድር፡አወጣ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤በእስራኤል፡ልጆች፡ዘንድ፡ከሰውም፡ከእንስሳም፡ማሕፀንን፡የሚከፈት፡በኵር፡ዅሉ፡ለእኔ፡ቀድስልኝ፤የእ ኔ፡ነው።
3፤ሙሴም፡ሕዝቡን፡አለ፦ከባርነት፡ቤት፣ከግብጽ፡የወጣችኹበትን፡ይህን፡ቀን፡ዐስቡ፥እግዚአብሔር፡ከዚህ፡ ቦታ፡በብርቱ፡እጅ፡አውጥቷችዃልና፤ስለዚህ፥የቦካ፡እንጀራ፡አትብሉ።
4፤እናንተ፡ዛሬ፡በአቢብ፡ወር፡ወጥታችዃል።
5፤እግዚአብሔርም፡ለአንተ፡ይሰጣት፡ዘንድ፡ለአባቶችኽ፡ወደማለላቸው፥ወተትና፡ማር፡ወደምታፈስ፟፡ምድር፥ ወደከነዓናውያን፡ወደኬጢያውያንም፡ወደአሞራውያንም፡ወደዔዊያውያንም፡ወደኢያቡሳውያንም፡ምድር፡ባገባኽ፡ ጊዜ፡ይህችን፡አምልኮ፡በዚህ፡ወር፡ታደርጋለኽ።
6፤ሰባት፡ቀን፡ቂጣ፡እንጀራ፡ትበላለኽ፥በሰባተኛውም፡ቀን፡ለእግዚአብሔር፡በዓል፡ይኾናል።
7፤ሰባት፡ቀንም፡ሙሉ፡ቂጣ፡እንጀራ፡ትበላለኽ፥ባንተም፡ዘንድ፡ርሾ፡ያለበት፡እንጀራ፡አይታይ፥በድንበርኽ ም፡ዅሉ፡ርሾ፡አይታይ።
8፤በዚያም፡ቀን፦ከግብጽ፡በወጣኹ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ስላደረገልኝ፡ነው፡ስትል፡ለልጅኽ፡ትነግረዋለኽ።
9፤እግዚአብሔር፡በብርቱ፡እጅ፡ከግብጽ፡አውጥቶኻልና፥የእግዚአብሔር፡ሕግ፡በአፍኽ፡ይኾን፡ዘንድ፡በእጅኽ ፡እንደ፡ምልክት፡በዐይኖችኽም፡መካከል፡እንደ፡መታሰቢያ፡ይኹንልኽ።
10፤በዓመት፡በዓመት፡በወራቱ፡ይህችን፡ሥርዐት፡ጠብቃት።
11፤እግዚአብሔርም፡ለአንተ፡ለአባቶችኽም፡እንደ፡ማለ፡ወደከነዓናውያን፡ምድር፡ባገባኽ፡ጊዜ፥ርሷንም፡በሰ ጠኽ፡ጊዜ፥
12፤ማሕፀንን፡የሚከፍተውን፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ለይ፤ከሚኾንልኽ፡ከብት፡ዅሉ፡ተባት፡ኾኖ፡አስቀድሞ፡የተ ወለደው፡ለእግዚአብሔር፡ይኾናል።
13፤የአህያውን፡በኵር፡በጠቦት፡ትዋጀዋለኽ፥ባትዋጀውም፡ዐንገቱን፡ትሰብረዋለኽ፤የሰውንም፡በኵር፡ዅሉ፡ከ ልጆችኽ፡መካከል፡ትዋጀዋለኽ።
14፤እንዲህም፡ይኾናል፤በሚመጣው፡ጊዜ፡ልጅኽ፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡በጠየቀኽ፡ጊዜ፡እንዲህ፡ትለዋለኽ፦ እግዚአብሔር፡በብርቱ፡እጅ፡ከባርነት፡ቤት፡ከግብጽ፡ምድር፡አወጣን፤
15፤ፈርዖንም፡እንዳይሰደ፟ን፡ልቡን፡ባጸና፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከሰው፡በኵር፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡በኵር ፡ድረስ፡በግብጽ፡ምድር፡ያለውን፡በኵር፡ዅሉ፡ገደለ፤ስለዚህ፥ወንድ፡ኾኖ፡ማሕፀንን፡የከፈተውን፡ዅሉ፡ለእ ግዚአብሔር፡እሠዋለኹ፥ነገር፡ግን፥የልጆቼን፡በኵር፡ዅሉ፡እዋጃለኹ።
16፤እግዚአብሔርም፡በብርቱ፡እጅ፡ከግብጽ፡አውጥቶናልና፥በእጅኽ፡እንደ፡ምልክት፥በዐይኖችኽም፡መካከል፡እ ንደ፡ተንጠለጠለ፡ነገር፡ይኹንልኽ።
17፤እንዲህም፡ኾነ፤ፈርዖን፡ሕዝቡን፡በለቀቀ፡ጊዜ፥ምንም፡ቅርብ፡ቢኾን፡እግዚአብሔር፡በፍልስጥኤማውያን፡ ምድር፡መንገድ፡አልመራቸውም፤እግዚአብሔር፦ሕዝቡ፡ሰልፉን፡ባየ፡ጊዜ፡እንዳይጸጽተው፡ወደ፡ግብጽም፡እንዳ ይመለስ፡ብሏልና።
18፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡በዙሪያ፡መንገድ፡በቀይ፡ባሕር፡ባለችው፡ምድረ፡በዳ፡መራቸው።የእስ ራኤልም፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ተሰልፈው፡ወጡ።
19፤ዮሴፍም፦እግዚአብሔር፡ሳይጐበኛችኹ፡አይቀርም፥ዐጥንቶቼንም፡ከዚህ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ታወጣላችኹ፡ብሎ፡ የእስራኤልን፡ልጆች፡አምሏቸው፡ነበርና፥ሙሴ፡የርሱን፡ዐጥንቶች፡ከርሱ፡ጋራ፡ወሰደ።
20፤ከሱኮትም፡ተጓዙ፥በምድረ፡በዳውም፡ዳር፡በኤታም፡ሰፈሩ።
21፤በቀንና፡በሌሊትም፡ይኼዱ፡ዘንድ፥መንገድ፡ሊያሳያቸው፡ቀን፡በደመና፡ዐምድ፥ሊያበራላቸውም፡ሌሊት፡በእ ሳት፡ዐምድ፡እግዚአብሔር፡በፊታቸው፡ኼደ።
22፤የደመና፡ዐምድ፡በቀን፥የእሳት፡ዐምድ፡በሌሊት፡ከሕዝቡ፡ፊት፡ከቶ፡ፈቀቅ፡አላለም።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ተመልሰው፡በሚግዶልና፡በባሕር፡መካከል፥በበዓልዛፎንም፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በፊሀሒሮት፡ፊት፡እንዲሰፍ ሩ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ተናገር፤ከርሱም፡አጠገብ፡በባሕር፡ዳር፡ትሰፍራላችኹ።
3፤ፈርዖንም፡ስለእስራኤል፡ልጆች፦በምድር፡ይቅበዘበዛሉ፥ምድረ፡በዳም፡ዘጋቻቸው፡ይላል።
4፤እኔም፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸናለኹ፥ርሱም፡ያባርራቸዋል፤በፈርዖንና፡በሰራዊቱም፡ዅሉ፡ላይ፡ክብር፡አገ ኛለኹ፤ግብጻውያንም፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።እነርሱም፡እንዲሁ፡አደረጉ።
5፤ሕዝቡም፡እንደ፡ኰበለሉ፡ለግብጽ፡ንጉሥ፡ነገሩት፤የፈርዖንና፡የባሪያዎቹም፡ልብ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ተለወጠ ና።እንዳይገዛልን፡እስራኤልን፡የለቀቅነው፡ምን፡አድርገናል፧አሉ።
6፤ሠረገላውንም፡አሰናዳ፥ሕዝቡንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ወሰደ፤
7፤ስድስት፡መቶ፡የተመረጡ፡ሠረገላዎችንም፥የግብጽንም፡ፈረሶች፡ዅሉ፥በያንዳንዱም፡ሠረገላ፡ዅሉ፡ላይ፡ሦ ስተኛዎችን፡ወሰደ።
8፤እግዚአብሔርም፡የግብጽን፡ንጉሥ፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸና፥ርሱም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አሳደደ፤የእስራ ኤልም፡ልጆች፡ከፍ፡ባለች፡እጅ፡ወጡ።
9፤ግብጻውያንም፡የፈርዖን፡ፈረሶች፡ሠረገላዎቹም፡ፈረሰኛዎቹም፡ሰራዊቱም፡ዅሉ፥አሳደዷቸው፤በባሕሩ፡ዳር ፡በበዓልዛፎን፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በፊሀሒሮት፡አጠገብ፡ሰፍረው፡አገኟቸው።
10፤ፈርዖንም፡በቀረበ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ዐይናቸውን፡አነሡ፥እንሆም፡ግብጻውያን፡በዃላቸው፡ገሥግሥ ው፡ነበር፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እጅግ፡ፈሩ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጮኹ።
11፤ሙሴንም፦በግብጽ፡መቃብር፡ስላልኖረ፡በምድረ፡በዳ፡እንሞት፡ዘንድ፡አወጣኸንን፧ከግብጽ፡ታወጣን፡ዘንድ ፡ይህ፡ያደረግኽብን፡ምንድር፡ነው፧
12፤በምድረ፡በዳ፡ከምንሞት፡ብንገዛላቸው፡ይሻላልና።ተወን፥ለግብጻውያን፡እንገዛ፡ብለን፡በግብጽ፡ሳለን፡ ያልንኽ፡ቃል፡ይህ፡አይደለምን፧አሉት።
13፤ሙሴም፡ለሕዝቡ፦አትፍሩ፥ዛሬ፡የምታይዋቸውን፡ግብጻውያንን፡ለዘለዓለም፡አታይዋቸውምና፡ቁሙ፥ዛሬ፡ለእ ናንተ፡የሚያደርጋትን፡የእግዚአብሔርን፡ማዳን፡እዩ።
14፤እግዚአብሔር፡ስለ፡እናንተ፡ይዋጋል፥እናንተም፡ዝም፡ትላላችኹ፡አላቸው።
15፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ለምን፡ትጮኽብኛለኽ፧እንዲጓዙ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ንገር።
16፤አንተም፡በትርኽን፡አንሣ፥እጅኽንም፡በባሕሩ፡ላይ፡ዘርጋ፥ክፈለውም፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በባሕሩ፡ውስ ጥ፡በየብስ፡ያልፋሉ።
17፤እንሆም፡እኔ፡የግብጻውያንን፡ልብ፡አጸናለኹ፥በዃላቸውም፡ይገባሉ፤በፈርዖንና፡በሰራዊቱም፡ዅሉ፡በሠረ ገላዎቹም፡በፈረሰኛዎቹም፡ላይ፡ክብር፡አገኛለኹ።
18፤ግብጻውያንም፡በፈርዖንና፡በሠረገላዎቹ፡በፈረሰኛዎቹም፡ላይ፡ክብር፡ባገኘኹ፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
19፤በእስራኤልም፡ሰራዊት፡ፊት፡ይኼድ፡የነበረው፡የእግዚአብሔር፡መልአክ፡ፈቀቅ፡ብሎ፡በዃላቸው፡ኼደ፤የደ መናውም፡ዐምድ፡ከፊታቸው፡ፈቀቅ፡ብሎ፡በዃላቸው፡ቆመ፥
20፤በግብጻውያን፡ሰፈርና፡በእስራኤል፡ሰፈር፡መካከልም፡ገባ፤በዚያም፡ደመናና፡ጨለማ፡ነበረ፥በዚህ፡በኩል ፡ግን፡ሌሊቱን፡አበራ፤ሌሊቱንም፡ዅሉ፡ርስ፡በርሳቸው፡አልተቃረቡም።
21፤ሙሴም፡በባሕሩ፡ላይ፡እጁን፡ዘረጋ፤እግዚአብሔርም፡ሌሊቱን፡ዅሉ፡ጽኑ፡የምሥራቅ፡ነፋስ፡አምጥቶ፡ባሕሩ ን፡አስወገደው፥ባሕሩንም፡አደረቀው፥ውሃውም፡ተከፈለ።
22፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በባሕሩ፡መካከል፡በየብስ፡ገቡ፤ውሃውም፡በቀኛቸውና፡በግራቸው፡እንደ፡ግድግዳ፡ኾ ነላቸው።
23፤ግብጻውያንም፥የፈርዖን፡ፈረሶችና፡ሠረገላዎች፡ፈረሰኛዎቹም፡ዅሉ፥እያሳደዱ፡በዃላቸው፡ወደ፡ባሕር፡መ ካከል፡ገቡ።
24፤ንጋትም፡በኾነ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡በእሳትና፡በደመና፡ዐምድ፡ኾኖ፡የግብጻውያንን፡ሰራዊት፡ተመለከተ፥ የግብጻውያንንም፡ሰራዊት፡አወከ።
25፤የሠረገላዎቹንም፡መንኰራኵር፡አሰረ፥ወደ፡ጭንቅም፡አገባቸው፤ግብጻውያንም፦እግዚአብሔር፡በግብጻውያን ፡ላይ፡ይዋጋላቸዋልና፥ከእስራኤል፡ፊት፡እንሽሽ፡አሉ።
26፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦እጅኽን፡በባሕሩ፡ላይ፡ዘርጋ፥ውሃውም፡በግብጻውያን፡በሠረገላዎቻቸውም፡በፈረሰ ኛዎቻቸውም፡ላይ፡ይመለስ፡አለው።
27፤ሙሴም፡እጁን፡በባሕሩ፡ላይ፡ዘረጋ፥ባሕሩም፡ማለዳ፡ወደ፡መፍሰሱ፡ተመለሰ፤ግብጻውያንም፡ከርሱ፡ሸሹ፥እ ግዚአብሔርም፡ግብጻውያንን፡በባሕሩ፡መካከል፡ጣላቸው።
28፤ውሃውም፡ተመልሶ፡በዃላቸው፡ወደ፡ባሕር፡የገቡትን፡ሠረገላዎችን፡ፈረሰኛዎችንም፡የፈርዖንንም፡ሰራዊት ፡ዅሉ፡ከደነ፤ከነርሱም፡አንድ፡ስንኳ፡አልቀረም።
29፤የእስራኤል፡ልጆች፡ግን፡በባሕሩ፡ውስጥ፡በየብስ፡ኼዱ፤ውሃዎችም፡በቀኛቸውና፡በግራቸው፡እንደ፡ግድግዳ ፡ኾኑላቸው።
30፤እግዚአብሔር፡በዚያን፡ቀን፡እስራኤልን፡እንደዚህ፡ከግብጻውያን፡እጅ፡አዳነ፤እስራኤልም፡የግብጻውያን ን፡ሬሳ፡በባሕር፡ዳር፡አዩ።
31፤እስራኤልም፡እግዚአብሔር፡በግብጻውያን፡ላይ፡ያደረጋትን፡ታላቂቱን፡እጅ፡አዩ፥ሕዝቡም፡እግዚአብሔርን ፡ፈሩ፥በእግዚአብሔርም፡በባሪያውም፡በሙሴ፡አመኑ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤በዚያም፡ጊዜ፡ሙሴና፡የእስራኤል፡ልጆች፡ይህንን፡መዝሙር፡ለእግዚአብሔር፡ዘመሩ፥እንዲህም፡ብለው፡ተና ገሩ።በክብር፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ለእግዚአብሔር፡እዘምራለኹ፤ፈረሱንና፡ፈረሰኛውን፡በባሕር፡ጣለ።
2፤ጕልበቴ፡ዝማሬዬም፡እግዚአብሔር፡ነው፥
መድኀኒቴም፡ኾነልኝ፤
ይህ፡አምላኬ፡ነው፡አመሰግነውማለኹ፥የአባቴ፡አምላክ፡ነው፡ከፍ፡ከፍም፡አደርገዋለኹ።
3፤እግዚአብሔር፡ተዋጊ፡ነው፥ስሙም፡እግዚአብሔር፡ነው፥
4፤የፈርዖንን፡ሠረገላዎች፡ሰራዊቱንም፡በባሕር፡ጣላቸው፤
የተመረጡት፡ሦስተኛዎች፡በቀይ፡ባሕር፡ሰጠሙ።
5፤ቀላያትም፡ከደኗቸው፤
ወደ፡ባሕር፡ጥልቀት፡እንደ፡ድንጋይ፡ሰጠሙ።
6፤አቤቱ፥ቀኝኽ፡በኀይል፡ከበረ፤
አቤቱ፥ቀኝኽ፡ጠላቱን፡አደቀቀ።
7፤በክብርኽም፡ብዛት፡የተነሡብኽን፡አጠፋኽ፤
ቍጣኽን፡ሰደ፟ኽ፥እንደ፡ገለባም፡በላቸው።
8፤በአፍንጫኽ፡እስትንፋስ፡ውሃዎች፡ተከመሩ፥
ፈሳሾቹም፡እንደ፡ክምር፡ቆሙ፤
ሞገዱም፡በባሕር፡ውስጥ፡ረጋ።
9፤ጠላትም፦አሳድጄ፡እይዛቸዋለኹ፥
ምርኮም፡እካፈላለኹ፥ነፍሴም፡ትጠግባቸዋለች፤ሰይፌንም፡እመዛ፟ለኹ፥እጄም፡ታጠፋቸዋለች፡አለ።
10፤ነፋስኽን፡አነፈስኽ፥ባሕርም፡ከደናቸው፤
በኀይለኛዎች፡ውሃዎችም፡እንደ፡ዐረር፡ሰጠሙ።
11፤አቤቱ፥በአማልክት፡መካከል፡እንደ፡አንተ፡ያለ፡ማን፡ነው፧
በምስጋና፡የተፈራኽ፥ድንቅንም፡የምታደርግ፥
በቅድስና፡የከበረ፡እንደ፡አንተ፡ያለ፡ማን፡ነው፧
12፤ቀኝኽን፡ዘረጋኽ፥ምድርም፡ዋጠቻቸው።
13፤በቸርነትኽ፡የተቤዠኻቸውን፡ሕዝብኽን፡መራኽ፤
በኀይልኽ፡ወደ፡ቅዱስ፡ማደሪያኽ፡አገባኻቸው።
14፤አሕዛብ፡ሰሙ፥ተንቀጠቀጡም፤
በፍልስጥኤም፡የሚኖሩትን፡ምጥ፡ያዛቸው።
15፤የዚያን፡ጊዜ፡የኤዶም፡አለቃዎች፡ደነገጡ፤የሞዐብን፡ኀያላን፡መንቀጥቀጥ፡ያዛቸው፤በከነዓን፡የሚኖሩ፡ ዅሉ፡ቀለጡ።
16፤አቤቱ፥ሕዝብኽ፡እስኪያልፍ፡ድረስ፥የተቤዠኸው፡ሕዝብ፡እስኪያልፍ፡ድረስ፥ፍርሀትና፡ድንጋጤ፡ወደቀባቸ ው፤በክንድኽ፡ብርታት፡እንደ፡ድንጋይ፡ዝም፡አሉ።
17፤አቤቱ፥አንተ፡ታስገባቸዋለኽ፥በርስትኽ፡ተራራም፡ትተክላቸዋለኽ፥አቤቱ፥ለማደሪያኽ፡ባደረግኸው፡ስፍራ ፥አቤቱ፥እጆችኽ፡ባዘጋጁት፡መቅደስ።
18፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለሙ፡እስከ፡ፍጻሜ፡ይነግሣል።
19፤የፈርዖን፡ፈረሶች፡ከሠረገላዎቹ፡ከፈረሰኛዎቹም፡ጋራ፡ወደ፡ባሕር፡ገቡ፥እግዚአብሔርም፡የባሕሩን፡ውሃ ዎች፡መለሰባቸው፤የእስራኤል፡ልጆች፡ግን፡በባሕሩ፡መካከል፡በየብስ፡ኼዱ።
20፤የአሮን፡እኅት፡ነቢዪቱ፡ማርያምም፡ከበሮ፡በእጇ፡ወሰደች፤ሴቶችም፡ዅሉ፡በከበሮና፡በዘፈን፡በዃላዋ፡ወ ጡ።
21፤ማርያምም፡እየዘመረች፡መለሰችላቸው፦በክብር፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ለእግዚአብሔር፡ዘምሩ፤ፈረሱንና፡ፈረ ሰኛውን፡በባሕር፡ጣለ።
22፤ሙሴም፡እስራኤልን፡ከቀይ፡ባሕር፡አስጓዘ፥ወደሱርም፡ምድረ፡በዳ፡ወጡ፤በምድረ፡በዳም፡ሦስት፡ቀን፡ኼዱ ፥ውሃም፡አላገኙም።
23፤ወደ፡ማራም፡በመጡ፡ጊዜ፡የማራ፡ውሃ፡መራራ፡ነበረና፡ሊጠጡ፡አልቻሉም፤ስለዚህ፥የዚያ፡ስፍራ፡ስም፡ማራ ፡ተብሎ፡ተጠራ።
24፤ሕዝቡም፦ምን፡እንጠጣለን፧ብለው፡በሙሴ፡ላይ፡አንጐራጐሩ።
25፤ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ፤እግዚአብሔርም፡ዕንጨትን፡አሳየው፥በውሃውም፡ላይ፡ጣለው፥ውሃውም፡ጣፈ ጠ።በዚያም፡ሥርዐትንና፡ፍርድን፡አደረገላቸው፥በዚያም፡ፈተናቸው፤
26፤ርሱም፦አንተ፡የአምላክኽን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አጥብቀኽ፡ብትሰማ፥በፊቱም፡የሚበጀውን፡ብታደርግ፥ ትእዛዙንም፡ብታደምጥ፥ሥርዐቱንም፡ዅሉ፡ብትጠብቅ፥በግብጻውያን፡ላይ፡ያመጣኹትን፡በሽታ፡አላደርስብኽም፤ እኔ፡ፈዋሽኽ፡እግዚአብሔር፡ነኝና፡አለ።
27፤እነርሱም፡ወደ፡ኤሊም፡መጡ፥በዚያም፡ዐሥራ፡ኹለት፡የውሃ፡ምንጮችና፡ሰባ፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ነበሩባት፤ በዚያም፡በውሃው፡አጠገብ፡ሰፈሩ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤ከኤሊምም፡ተጓዙ፥የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ከግብጽ፡አገር፡ከወጡ፡በዃላ፡በኹለተኛው፡ወር፡ከ ወሩም፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡በኤሊምና፡በሲና፡መካከል፡ወዳለችው፡ወደሲን፡ምድረ፡በዳ፡መጡ።
2፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡በምድረ፡በዳ፡በሙሴና፡በአሮን፡ላይ፡አንጐራጐሩ።
3፤የእስራኤልም፡ልጆች፦ይህን፡ጉባኤ፡ዅሉ፡በራብ፡ልትገድሉ፡እኛን፡ወደዚች፡ምድረ፡በዳ፡አውጥታችዃል፤በ ሥጋው፡ምንቸት፡አጠገብ፡ተቀምጠን፡እንጀራ፡ስንበላ፡ስንጠግብ፡ሳለን፡በግብጽ፡ምድር፡በእግዚአብሔር፡እጅ ፡ምነው፡በሞትን! አሏቸው።
4፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በሕጌ፡ይኼዱ፡ወይም፡አይኼዱ፡እንደ፡ኾነ፡እኔ፡እንድፈትናቸው፥እንሆ፥ከሰማይ፡ እንጀራን፡አዘንብላችዃለኹ፤ሕዝቡም፡ወጥተው፡ለዕለት፡ለዕለት፡የሚበቃቸውን፡ይልቀሙ።
5፤እንዲህም፡ይኾናል፤በስድስተኛው፡ቀን፡ያመጡትን፡ያዘጋጁ፥ዕለት፡ዕለትም፡ከሚለቅሙት፡ይልቅ፡ኹለት፡ዕ ጥፍ፡ይኹን፡አለው።
6፤ሙሴና፡አሮንም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፦እግዚአብሔር፡ከግብጽ፡ምድር፡እንዳወጣችኹ፡ማታ፡ታውቃላችኹ፥
7፤የእግዚአብሔርንም፡ክብር፡ጧት፡ታያላችኹ፤በእግዚአብሔር፡ላይ፡ያንጐራጐራችኹትን፡ሰምቷልና፥በእኛም፡ ላይ፡የምታንጐራጕሩ፥እኛ፡ምንድር፡ነን፧አሉ።
8፤ሙሴም፦እግዚአብሔር፡ያንጐራጐራችኹበትን፡ማንጐራጐራችኹን፡ሰምቷልና፥በመሸ፡ጊዜ፡ትበሉ፡ዘንድ፡ሥጋን ፥ማልዶም፡ትጠግቡ፡ዘንድ፡እንጀራን፡እግዚአብሔር፡ይሰጣችዃል፤እኛም፡ምንድር፡ነን፧ማንጐራጐራችኹ፡በእግ ዚአብሔር፡ላይ፡ነው፡እንጂ፡በእኛ፡አይደለም፡አለ።
9፤ሙሴም፡አሮንን፦ለእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፦ማንጐራጐራችኹን፡ሰምቷልና፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ፊት፡ ቅረቡ፡በል፡አለው።
10፤እንዲህም፡ኾነ፤አሮን፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡በተናገረ፡ጊዜ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ፊታቸውን፡አ ቀኑ፤እንሆም፡የእግዚአብሔር፡ክብር፡በደመናው፡ታየ።
11፤12፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ማንጐራጐር፡ሰማኹ።ወደ፡ማታ፡ሥጋን፡ትበላላች ኹ፥ማለዳም፡እንጀራን፡ትጠግባላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ፡በላቸው።
13፤እንዲህም፡ኾነ፤በመሸ፡ጊዜ፡ድርጭቶች፡መጡ፥ሰፈሩንም፡ከደኑት፤ማለዳም፡በሰፈሩ፡ዙሪያ፡ጠል፡ወድቆ፡ነ በር።
14፤የወደቀውም፡ጠል፡ባለፈ፡ጊዜ፥እንሆ፥በመሬት፡ላይ፡እንደ፡ደቃቅ፡ውርጭ፡ኾኖ፡ቅርፊት፡የሚመስል፡ደቃቅ ፡ነገር፡በምድረ፡በዳ፡ታየ።
15፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ባዩት፡ጊዜ፡ያ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አላወቁምና፡ርስ፡በርሳቸው፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧ ተባባሉ።ሙሴም፦ትበሉት፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡የሰጣችኹ፡እንጀራ፡ነው።
16፤እግዚአብሔር፡ያዘዘው፡ነገር፡ይህ፡ነው፦እያንዳንዱ፡የሚበላውን፡ያኽል፡ይልቀም፤በድንኳኑ፡ባሉት፡ነፍ ሶች፡ቍጥር፡ላንድ፡ሰው፡አንድ፡ጎሞር፡ውሰዱ፡አላቸው።
17፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እንዲሁ፡አደረጉ፤አንዱ፡አብዝቶ፡አንዱም፡አሳንሶ፡ለቀመ።
18፤በጎሞርም፡በሰፈሩት፡ጊዜ፡እጅግ፡ለለቀመ፡አልተረፈውም፡ጥቂትም፡ለለቀመ፡አልጐደለበትም፤ዅሉ፡እያንዳ ንዱ፡የሚበላውን፡ያኽል፡ለቀመ።
19፤ሙሴም፦ማንም፡ከርሱ፡አንዳች፡ለነገ፡አያስቀር፡አላቸው።
20፤ነገር፡ግን፥ሙሴን፡አልሰሙትም፤አንዳንድ፡ሰዎችም፡ከርሱ፡ለነገ፡አስቀሩ፥ርሱም፡ተላ፡ሸተተም፤ሙሴም፡ ተቈጣቸው።
21፤ሰውም፡ዅሉ፡ዕለት፡ዕለት፡የሚበላውን፡ያኽል፡በጧት፡ለቀመ፤ፀሓይም፡በተኰሰ፡ጊዜ፡ቀለጠ።
22፤እንዲህም፡ኾነ፤በስድስተኛው፡ቀን፡ኹለት፡ዕጥፍ፡አድርገው፡እያንዳንዳቸው፡ኹለት፡ጎሞር፡እንጀራ፡ለቀ ሙ፤የማኀበሩም፡አለቃዎች፡ዅሉ፡መጥተው፡ለሙሴ፡ነገሩት።
23፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡የተናገረው፡ይህ፡ነው።ነገ፡ዕረፍት፥ለእግዚአብሔርም፡የተቀደሰ፡ሰንበት፡ነው፤የ ምትጋግሩትን፡ጋግሩ፥የምትቀቅሉትንም፡ቀቅሉ፥የተረፈውን፡ዅሉ፡ለነገ፡እንዲጠበቅ፡አኑሩት፡አላቸው።
24፤ሙሴም፡እንዳዘዘ፡ለነገ፡አኖሩት፤አልሸተተም፥ትልም፡አልኾነበትም።
25፤ሙሴም፦የእግዚአብሔር፡ሰንበት፡ዛሬ፡ነውና፥ብሉት፤ዛሬ፡በሜዳ፡አታገኙትም።
26፤ስድስት፡ቀን፡ልቀሙት፤ሰባተኛው፡ቀን፡ግን፡ሰንበት፡ነው፤በርሱ፡አይገኝም፡አለ።
27፤በሰባተኛውም፡ቀን፡እንዲህ፡ኾነ፤ከሕዝቡ፡አንዳንድ፡ሰዎች፡ሊለቅሙ፡ወጡ፥ምንም፡ምን፡አላገኙም።
28፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ትእዛዞቼንና፡ሕጎቼን፡ለመጠበቅ፡እስከ፡መቼ፡እንቢ፡ትላላችኹ፧
29፤እግዚአብሔር፡ሰንበትን፡እንደ፡ሰጣችኹ፡እዩ፤ስለዚህ፥በስድስተኛው፡ቀን፡የኹለት፡ቀን፡እንጀራ፡ሰጣች ኹ፤ሰው፡ዅሉ፡በስፍራው፡ይቀመጥ፥በሰባተኛው፡ቀን፡ማንም፡ከስፍራው፡አይኺድ፡አለው።
30፤ሕዝቡም፡በሰባተኛው፡ቀን፡ዐረፈ።
31፤የእስራኤልም፡ወገን፡ስሙን፡መና፟፡ብለው፡ጠሩት፤ርሱም፡እንደ፡ድንብላል፡ዘር፡ነጭ፡ነው፤ጣዕሙም፡እን ደ፡ማር፡ቂጣ፡ነው።
32፤ሙሴም፦እግዚአብሔር፡ያዘዘው፡ነገር፡ይህ፡ነው፦ከግብጽ፡ምድር፡ባወጣዃችኹ፡ጊዜ፥በምድረ፡በዳ፡ያበላዃ ችኹን፡እንጀራ፡ያዩ፡ዘንድ፥ከርሱ፡አንድ፡ጎሞር፡ሙሉ፡ለልጅ፡ልጆቻችኹ፡ይጠበቅ፡አለ።
33፤ሙሴም፡አሮንን፦አንድ፡ማድጋ፡ወስደኽ፡ጎሞር፡ሙሉ፡መና፟፡አግባበት፥ለልጅ፡ልጃችኹም፡ይጠበቅ፡ዘንድ፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡አኑረው፡አለው።
34፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡ይጠበቅ፡ዘንድ፡አሮን፡በምስክሩ፡ፊት፡አኖረው።
35፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደሚኖሩባት፡ምድር፡እስኪመጡ፡ድረስ፡አርባ፡ዓመት፡መና፟፡በሉ፤ወደ፡ከነዓን፡ም ድር፡ድንበር፡እስኪመጡ፡ድረስ፡መና፟፡በሉ።
36፤ጎሞርም፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ዐሥረኛ፡ክፍል፡ነው።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘ፡ከሲን፡ምድረ፡በዳ፡ሊጓዙ፡ተነሡ፥በራፊዲም ም፡ሰፈሩ፤ሕዝቡም፡ይጠጡ፡ዘንድ፡ውሃ፡አልነበረም።
2፤ሕዝቡም፡ሙሴን፡ተጣሉት፦የምንጠጣውን፡ውሃ፡ስጠን፡አሉት።ሙሴም፦ለምን፡ትጣሉኛላችኹ፧እግዚአብሔርንስ ፡ለምን፡ትፈታተናላችኹ፧አላቸው።
3፤ሕዝቡም፡በዚያ፡ስፍራ፡ውሃ፡ተጠሙ፦እኛንና፡ልጆቻችንን፡ከብቶቻችንንም፡በጥማት፡ልትገድል፡ለምን፡ከግ ብጽ፡አወጣኸን፧ሲሉ፡በሙሴ፡ላይ፡አንጐራጐሩ።
4፤ሙሴም፦ሊወግሩኝ፡ቀርበዋልና፥በዚህ፡ሕዝብ፡ምን፡ላድርግ፧ብሎ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ።
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በሕዝቡ፡ፊት፡ዕለፍ፥ከእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤ወንዙንም፡ የመታኽባትን፡በትር፡በእጅኽ፡ይዘኻት፡ኺድ።
6፤እንሆ፥እኔ፡በዚያ፡በኰሬብ፡በአለት፡ላይ፡በፊትኽ፡እቆማለኹ፤አለቱንም፡ትመታለኽ፥ሕዝቡም፡ይጠጣ፡ዘን ድ፡ከርሱ፡ውሃ፡ይወጣል፡አለው።ሙሴም፡በእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ፊት፡እንዲሁ፡አደረገ።
7፤ስለእስራኤልም፡ልጆች፡ክርክር፦እግዚአብሔር፡በመካከላችን፡ነውን፡ወይስ፡አይደለም፧ሲሉ፡እግዚአብሔር ን፡ስለ፡ተፈታተኑት፡የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡ማሣህ፥ደግሞም፡መሪባ፡ብሎ፡ጠራው።
8፤ዐማሌቅም፡መጥቶ፡ከእስራኤል፡ጋራ፡በራፊድም፡ተዋጋ።
9፤ሙሴም፡ኢያሱን፦ጕልማሳዎችን፡ምረጥልን፥ወጥተኽም፡ከዐማሌቅ፡ጋራ፡ተዋጋ፤እኔ፡ነገ፡የእግዚአብሔርን፡ በትር፡በእጄ፡ይዤ፡በኰረብታው፡ራስ፡ላይ፡እቆማለኹ፡አለው።
10፤ኢያሱም፡ሙሴ፡እንዳለው፡አደረገ፥ከዐማሌቅም፡ጋራ፡ተዋጋ፤ሙሴና፡አሮንም፡ሖርም፡ወደኰረብታው፡ራስ፡ወ ጡ።
11፤እንዲህም፡ኾነ፤ሙሴ፡እጁን፡ባነሣ፡ጊዜ፡እስራኤል፡ድል፡ያደርግ፡ነበር፤እጁንም፡ባወረደ፡ጊዜ፡ዐማሌቅ ፡ድል፡ያደርግ፡ነበር።
12፤የሙሴ፡እጆች፡ግን፡ከብደው፡ነበር፤ድንጋይም፡ወሰዱ፥በበታቹም፡አኖሩ፥ርሱም፡ተቀመጠበት፤አሮንና፡ሖር ም፡አንዱ፡በዚህ፡አንዱ፡በዚያ፡ኾነው፡እጆቹን፡ይደግፉ፡ነበር፤ፀሓይም፡እስክትገባ፡ድረስ፡እጆቹ፡ጠነከሩ ።
13፤ኢያሱም፡ዐማሌቅንና፡ሕዝቡን፡በሰይፍ፡ስለት፡አሸነፈ።
14፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦የዐማሌቅን፡ዝክር፡ከሰማይ፡በታች፡ጨርሼ፡እደመስሳለኹና፡ይህን፡ለመታሰቢያ፡በ መጽሐፍ፡ጻፈው፥በኢያሱም፡ዦሮ፡ተናገር፡አለው።
15፤ሙሴም፡መሠዊያ፡ሠራ፥ስሙንም፡ያህዌህ፡ንሲ፡ብሎ፡ጠራው፤
16፤ርሱም፦እጁን፡በእግዚአብሔር፡ዙፋን፡ላይ፡ስለ፡ጫነ፡የእግዚአብሔር፡ሰልፍ፡በዐማሌቅ፡ላይ፡ለልጅ፡ልጅ ፡ይኹን፡አለ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤የምድያምም፡ካህን፡የሙሴ፡ዐማት፡ዮቶር፡እግዚአብሔር፡ለሙሴና፡ለሕዝቡ፡ለእስራኤል፡ያደረገውን፡ዅሉ፥ እግዚአብሔርም፡እስራኤልን፡ከግብጽ፡እንዳወጣ፡ሰማ።
2፤በዚያን፡ጊዜ፡የሙሴ፡ዐማት፡ዮቶር፡መልሷት፡የነበረውን፡የሙሴን፡ሚስት፡ሲፓራን፡ኹለቱንም፡ልጆቿን፡ወ ሰደ።
3፤ከነርሱ፡የአንደኛው፡ስም፡ጌርሳም፡ነበረ፤አባቱ፦በሌላ፡አገር፡ስደተኛ፡ነበርኹ፡ብሏልና፤
4፤የኹለተኛውም፡ስም፡አልዓዛር፡ነበረ፦የአባቴ፡አምላክ፡ረዳኝ፥ከፈርዖንም፡ሰይፍ፡አዳነኝ፡ብሏልና።
5፤የሙሴ፡ዐማት፡ዮቶርም፡ከልጆቹና፡ከሚስቱ፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ተራራ፡አጠገብ፡በምድረ፡በዳ፡ወደ፡ሰፈ ረ፡ወደ፡ሙሴ፡መጣ።
6፤ሙሴንም፦እኔ፡ዐማትኽ፡ዮቶር፥ሚስትኽም፥ከርሷም፡ጋራ፡ኹለቱ፡ልጆቿ፡መጥተንልኻል፡አለው።
7፤ሙሴም፡ዐማቱን፡ሊገናኝ፡ወጣ፥ሰገደም፥ሳመውም፤ርስ፡በርሳቸውም፡ደኅንነታቸውን፡ተጠያየቁ፥ወደ፡ድንኳ ኑም፡ገቡ።
8፤ሙሴም፡እግዚአብሔር፡በፈርዖንና፡በግብጻውያን፡ላይ፡ስለ፡እስራኤል፡ያደረገውን፡ዅሉ፥በመንገድም፡ያገ ኛቸውን፡ድካም፡ዅሉ፥እግዚአብሔርም፡እንዳዳናቸው፡ለዐማቱ፡ነገረው።
9፤ዮቶርም፡እግዚአብሔር፡ለእስራኤል፡ስላደረገው፡ቸርነት፡ዅሉ፥ከግብጻውያንም፡እጅ፡ስላዳናቸው፡ደስ፡አ ለው።
10፤ዮቶርም፦ከግብጻውያንና፡ከፈርዖን፡እጅ፡ያዳናችኹ፥ከግብጻውያንም፡እጅ፡ሕዝቡን፡ያዳነ፡እግዚአብሔር፡ ይባረክ።
11፤ትዕቢት፡ባደረጉባቸው፡ነገር፡እግዚአብሔር፡ከአማልክት፡ዅሉ፡እንዲበልጥ፡አኹን፡ዐወቅኹ፡አለ።
12፤የሙሴ፡ዐማት፡ዮቶርም፡የሚቃጠል፡መሥዋዕትንና፡ሌላ፡መሥዋዕትን፡ለእግዚአብሔር፡ወሰደ፤በእግዚአብሔር ም፡ፊት፡ከሙሴ፡ዐማት፡ጋራ፡እንጀራ፡ሊበሉ፡አሮን፡የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡መጡ።
13፤እንዲህም፡ኾነ፤በነጋው፡ሙሴ፡በሕዝቡ፡ሊፈርድ፡ተቀመጠ፤ሕዝቡም፡በሙሴ፡ፊት፡ከጧት፡እስከ፡ማታ፡ድረስ ፡ቆመው፡ነበር።
14፤የሙሴም፡ዐማት፡በሕዝቡ፡ያደረገውን፡ዅሉ፡ባየ፡ጊዜ፦ይህ፡በሕዝቡ፡የምታደርገው፡ምንድር፡ነው፧ሕዝቡ፡ ዅሉ፡ከጧት፡ዠምሮ፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡በዙሪያኽ፡ቆመው፡ሳሉ፡አንተ፡ብቻኽን፡ስለ፡ምን፡ተቀምጠኻል፧አለው ።
15፤ሙሴም፡ዐማቱን፦ሕዝቡ፡እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ወደ፡እኔ፡ይመጣሉ፤
16፤ነገርም፡ቢኖራቸው፡ወደ፡እኔ፡ይመጣሉ፥በዚህና፡በዚያ፡ሰውም፡መካከል፡እፈርዳለኹ፥የእግዚአብሔርንም፡ ሥርዐትና፡ሕግ፡አስታውቃቸዋለኹ፡አለው።
17፤የሙሴም፡ዐማት፡አለው፦አንተ፡የምታደርገው፡ይህ፡ነገር፡መልካም፡አይደለም።
18፤ይህ፡ነገር፡ይከብድብኻልና፥አንተ፣ከአንተም፡ጋራ፡ያለው፡ሕዝብ፡ትደክማላችኹ፤አንተ፡ብቻኽን፡ልታደር ገው፡አትችልም።
19፤አኹንም፡እመክርኻለኹና፡ቃሌን፡ስማ፥እግዚአብሔርም፡ከአንተ፡ጋራ፡ይኾናል፤አንተ፡በእግዚአብሔር፡ፊት ፡ለሕዝቡ፡ኹን፥ነገራቸውንም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡አድርስ፤
20፤ሥርዐቱንም፡ሕጉንም፡አስተምራቸው፥የሚኼዱበትን፡መንገድ፡የሚያደርጉትንም፡ሥራ፡ዅሉ፡አሳያቸው።
21፤አንተም፡ከሕዝቡ፡ዅሉ፡ዐዋቂዎችን፥እግዚአብሔርን፡የሚፈሩትን፥የታመኑ፥የግፍንም፡ረብ፡የሚጠሉትን፡ሰ ዎች፡ምረጥ፤ከነርሱም፡የሺሕ፡አለቃዎችን፥የመቶ፡አለቃዎችን፥የዐምሳ፡አለቃዎችን፥የዐሥርም፡አለቃዎችን፡ ሹምላቸው።
22፤በሕዝቡ፡ላይ፡ዅል፡ጊዜ፡ይፍረዱ፤አውራውን፡ነገር፡ዅሉ፡ወዳንተ፡ያምጡት፥ታናሹንም፡ነገር፡ዅሉ፡እነር ሱ፡ይፍረዱ፤እነርሱም፡ከአንተ፡ጋራ፡ሸክሙን፡ይሸከማሉ፥ለአንተም፡ይቀልልኻል።
23፤ይህንም፡ብታደርግ፥እግዚአብሔር፡እንዲሁ፡ቢያዝ፟ኽ፥መቆም፡ይቻልኻል፥ደግሞም፡ይህ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡በሰላ ም፡ወደ፡ስፍራው፡ይደርሳል።
24፤ሙሴም፡የዐማቱን፡ቃል፡ሰማ፥ያለውንም፡ዅሉ፡አደረገ።
25፤ሙሴም፡ከእስራኤል፡ዅሉ፡ዐዋቂዎችን፡መረጠ፥በሕዝቡም፡ላይ፡የሺሕ፡አለቃዎች፥የመቶም፡አለቃዎች፥የዐም ሳም፡አለቃዎች፥የዐሥርም፡አለቃዎች፡አድርጎ፡ሾማቸው።
26፤በሕዝቡም፡ላይ፡ዅል፡ጊዜ፡ፈረዱ፤የከበደባቸውንም፡ነገር፡ወደ፡ሙሴ፡አመጡ፥ታናሹን፡ነገር፡ዅሉ፡ግን፡ እነርሱ፡ፈረዱ።
27፤ሙሴም፡ዐማቱን፡ሰደደው፤ርሱም፡ወደ፡አገሩ፡ተመለሰ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤በሦስተኛውም፡ወር፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ከወጡ፡በዃላ፡በዚያ፡ቀን፡ወደሲና፡ምድረ፡በዳ፡ መጡ።
2፤ከራፊድም፡ተነሥተው፡ወደሲና፡ምድረ፡በዳ፡መጡ፥በምድረ፡በዳም፡ሰፈሩ፤በዚያም፡እስራኤል፡በተራራው፡ፊ ት፡ሰፈረ።
3፤ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወጣ፤እግዚአብሔርም፡በተራራው፡ጠርቶ፡አለው፦ለያዕቆብ፡ቤት፡እንዲህ ፡በል፥ለእስራኤልም፡ልጆች፡እንዲህ፡ንገር፦
4፤በግብጻውያን፡ያደረግኹትን፥በንስርም፡ክንፍ፡እንደተሸከምዃችኹ፥ወደ፡እኔም፡እንዳመጣዃችኹ፡አይታችዃ ል።
5፤አኹንም፡ቃሌን፡በእውነት፡ብትሰሙ፡ኪዳኔንም፡ብትጠብቁ፥ምድር፡ዅሉ፡የእኔ፡ናትና፥ከአሕዛብ፡ዅሉ፡የተ መረጠ፡ርስት፡ትኾኑልኛላችኹ፤
6፤እናንተም፡የካህናት፡መንግሥት፡የተቀደሰም፡ሕዝብ፡ትኾኑልኛላችኹ።ለእስራኤል፡ልጆች፡የምትነግራቸው፡ ቃል፡ይህ፡ነው።
7፤ሙሴም፡መጣ፥የሕዝቡንም፡ሽማግሌዎች፡ጠርቶ፡እግዚአብሔር፡ያዘዘውን፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡በፊታቸው፡ተናገ ረ።
8፤ሕዝቡ፡ዅሉ፡አንድ፡አፍ፡ኾነው፦እግዚአብሔር፡ያለውን፡ዅሉ፡እናደርጋለን፡ብለው፡መለሱ፤ሙሴም፡የሕዝቡ ን፡ቃል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡አደረሰ።
9፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ከአንተ፡ጋራ፡ስነጋገር፡ሕዝቡ፡እንዲሰሙ፥ደግሞም፡ለዘለዓለም፡እንዲያምኑብኽ፥ እንሆ፥በከባድ፡ደመና፡እመጣልኻለኹ፡አለው።ሙሴም፡የሕዝቡን፡ቃል፡ለእግዚአብሔር፡ነገረ።
10፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ወደ፡ሕዝቡ፡ኺድ፥ዛሬና፡ነገም፡ቀድሳቸው፥ልብሳቸውንም፡ይጠቡ፤
11፤በሦስተኛው፡ቀን፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ሲያዩ፡እግዚአብሔር፡በሲና፡ተራራ፡ላይ፡ይወርዳልና፥ለሦስተኛው፡ቀን፡ይ ዘጋጁ።
12፤ወሰንም፡ለሕዝቡ፡በዙሪያው፡አድርግላቸው፦ወደ፡ተራራው፡እንዳትወጡ፥ጫፉንም፡እንዳትነኩ፡ተጠንቀቁ፤ተ ራራውንም፡የነካ፡ፈጽሞ፡ይሞታል፤
13፤የማንም፡እጅ፡አይንካ፤ነገር፡ግን፥የሚነካው፡ዅሉ፡ይወ፟ገ፟ራል፥ወይም፡በፍላጻ፡ይወ፟ጋ፟ል፤እንስሳ፡ ወይም፡ሰው፡ቢኾን፡አይድንም፡በላቸው።ሳያቋርጥ፡የመለከት፡ድምፅ፡ሲነፋ፡በዚያን፡ጊዜ፡ወደ፡ተራራው፡ይው ጡ።
14፤ሙሴም፡ከተራራው፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወረደ፥ሕዝቡንም፡ቀደሰ፤ልብሳቸውንም፡ዐጠቡ።
15፤ሕዝቡንም፦ለሦስተኛው፡ቀን፡ተዘጋጁ፥ወደ፡ሴቶቻችኹ፡አትቅረቡ፡አለ።
16፤እንዲህም፡ኾነ፤በሦስተኛው፡ቀን፡በማለዳ፡ጊዜ፡ነጐድጓድና፡መብረቅ፡ከባድም፡ደመና፡እጅግም፡የበረታ፡ የቀንደ፡መለከት፡ድምፅ፡በተራራው፡ላይ፡ኾነ፤በሰፈሩም፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ተንቀጠቀጡ።
17፤ሙሴም፡ሕዝቡን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ለማገናኘት፡ከሰፈር፡አወጣቸው፤ከተራራውም፡እግርጌ፡ቆሙ።
18፤እግዚአብሔርም፡በእሳት፡ስለ፡ወረደበት፡የሲና፡ተራራ፡ዅሉ፡ይጤስ፡ነበር፤ከርሱም፡እንደ፡እቶን፡ጢስ፡ ያለ፡ጢስ፡ይወጣ፡ነበር፥ተራራውም፡ዅሉ፡እጅግ፡ይናወጥ፡ነበር።
19፤የቀንደ፡መለከቱም፡ድምፅ፡እጅግ፡በበረታና፡በጸና፡ጊዜ፡ሙሴ፡ተናገረ፡እግዚአብሔርም፡በድምፅ፡መለሰለ ት።
20፤እግዚአብሔርም፡በሲና፡ተራራ፡ላይ፡ወደ፡ተራራው፡ራስ፡ወረደ፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡ወደ፡ተራራው፡ራስ ፡ጠራው፤ሙሴም፡ወጣ።
21፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ውረድ፥እግዚአብሔርን፡ለማየት፡ዳርቻውን፡እንዳያልፉ፡ከነርሱም፡ብዙ፡እንዳይጠ ፉ፡ለሕዝቡ፡አስጠንቅቃቸው፤
22፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡የሚቀርቡት፡ካህናት፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡እንዳያጠፋቸው፡ራሳቸውን፡ይቀድሱ፡አለ ው።
23፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፦አንተ፦በተራራው፡ዙሪያ፡ወሰን፡አድርግ፡ቀድሰውም፡ብለኽ፡አስጠንቅቀኸናልና፥ሕ ዝቡ፡ወደ፡ተራራ፡ይወጡ፡ዘንድ፡አይችሉም፡አለው።
24፤እግዚአብሔርም፦ኺድ፥ውረድ፤አንተ፡አሮንም፡ከአንተ፡ጋራ፡ትወጣላችኹ፤ካህናቱና፡ሕዝቡ፡ግን፡እግዚአብ ሔር፡እንዳያጠፋቸው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይወጡ፡ዘንድ፡አይተላለፉ፡አለው።
25፤ሙሴም፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወረደ፥ይህንንም፡ነገራቸው።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤እግዚአብሔርም፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦
2፤ከግብጽ፡ምድር፡ከባርነት፡ቤት፡ያወጣኹኽ፡እግዚአብሔር፡አምላክኽ፡እኔ፡ነኝ።
3፤ከእኔ፡በቀር፡ሌላዎች፡አማልክት፡አይኹኑልኽ።
4፤በላይ፡በሰማይ፡ካለው፥በታችም፡በምድር፡ካለው፥ከምድርም፡በታች፡በውሃ፡ካለው፡ነገር፡የማናቸውንም፡ም ሳሌ፥የተቀረጸውንም፡ምስል፡ለአንተ፡አታድርግ።
5፤አትስገድላቸው፥አታምልካቸውምም፤በሚጠሉኝ፡እስከ፡ሦስተኛና፡እስከ፡አራተኛ፡ትውልድ፡ድረስ፡የአባቶች ን፡ኀጢአት፡በልጆች፡ላይ፡የማመጣ፤
6፤ለሚወዱኝ፥ትእዛዜንም፡ለሚጠብቁ፡እስከ፡ሺሕ፡ትውልድ፡ድረስ፡ምሕረትን፡የማደርግ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ አምላክኽ፡ቀናተኛ፡አምላክ፡ነኝና።ፕ፡
7፤የእግዚአብሔርን፡የአምላክኽን፡ስም፡በከንቱ፡አትጥራ፤እግዚአብሔር፡ስሙን፡በከንቱ፡የሚጠራውን፡ከበደ ል፡አያነጻውምና።
8፤የሰንበትን፡ቀን፡ትቀድሰው፡ዘንድ፡ዐስብ።
9፤ስድስት፡ቀን፡ሥራ፡ተግባርኽንም፡ዅሉ፡አድርግ፤
10፤ሰባተኛው፡ቀን፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡ለአምላክኽ፡ሰንበት፡ነው፤አንተ፥ወንድ፡ልጅኽም፥ሴት፡ልጅኽም፥ሎ ሌኽም፥ገረድኽም፥ከብትኽም፥በደጆችኽም፡ውስጥ፡ያለ፡እንግዳ፡በርሱ፡ምንም፡ሥራ፡አትሥሩ፤
11፤እግዚአብሔር፡በስድስት፡ቀን፡ሰማይንና፡ምድርን፥ባሕርንም፥ያለባቸውንም፡ዅሉ፡ፈጥሮ፡በሰባተኛው፡ቀን ፡ዐርፏልና፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡የሰንበትን፡ቀን፡ባርኮታል፡ቀድሶታልም።
12፤አባትኽንና፡እናትኽን፡አክብር፤እግዚአብሔር፡አምላክኽ፡በሚሰጥኽ፡ምድር፡ዕድሜኽ፡እንዲረዝም።
13፤አትግደል።
14፤አታመንዝር።
15፤አትስረቅ።
16፤በባልንጀራኽ፡ላይ፡በሐሰት፡አትመስክር።
17፤የባልንጀራኽን፡ቤት፡አትመኝ፤የባልንጀራኽን፡ሚስት፡ሎሌውንም፡ገረዱንም፡በሬውንም፡አህያውንም፡ከባል ንጀራኽ፡ገንዘብ፡ዅሉ፡ማናቸውንም፡አትመኝ።
18፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ነጐድጓዱንና፡መብረቁን፥የቀንደ፡መለከቱን፡ድምፅ፥ተራራውንም፡ሲጤስ፡አዩ፤ሕዝቡም፡ባዩ ፡ጊዜ፡ተርበደበዱ፥ርቀውም፡ቆሙ።
19፤ሙሴንም፦አንተ፡ተናገረን፡እኛም፡እንሰማለን፤እንዳንሞት፡ግን፡እግዚአብሔር፡አይናገረን፡አሉት።
20፤ሙሴም፡ለሕዝቡ፦እግዚአብሔር፡ሊፈትናችኹ፥ኀጢአትንም፡እንዳትሠሩ፡ርሱን፡መፍራት፡በልባችኹ፡ይኾን፡ዘ ንድ፡መጥቷልና፥አትፍሩ፡አለ።
21፤ሕዝቡም፡ርቀው፡ቆሙ፥ሙሴም፡እግዚአብሔር፡ወዳለበት፡ወደ፡ጨለማው፡ቀረበ።
22፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡አለው፦ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡በል፦እኔ፡ከሰማይ፡እንደ፡ተናገርዃችኹ፡እናን ተ፡አይታችዃል።
23፤በአጠገቤ፡ምንም፡አታድርጉ፤የብር፡አማልክት፡የወርቅም፡አማልክት፡ለእናንተ፡አታድርጉ።
24፤የጭቃ፡መሠዊያ፡ሥራልኝ፥የሚቃጠለውንና፡የደኅንነት፡መሥዋዕትኽን፡በጎችኽንም፡በሬዎችኽንም፡ሠዋበት፤ ስሜን፡በማሳስብበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ወዳንተ፡መጥቼ፡እባርክኻለኹ።
25፤የድንጋይም፡መሠዊያ፡ብታደርግልኝ፡ብረት፡በነካው፡ድንጋይ፡አትሥራው፤በመሣሪያ፡ብትነካው፡ታረክሰዋለ ኽና።
26፤ኀፍረተ፡ሥጋኽ፡በርሱ፡እንዳይገለጥ፡ወደ፡መሠዊያዬ፡በደረጃ፡አትውጣ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤በፊታቸው፡የምታደርገው፡ሥርዐት፡ይህ፡ነው።
2፤ዕብራዊ፡ባሪያ፡የገዛኽ፡እንደ፡ኾነ፡ስድስት፡ዓመት፡ያገልግልኽ፥በሰባተኛውም፡በከንቱ፡ሐራነት፡ይውጣ ።
3፤ብቻውን፡መጥቶ፡እንደ፡ኾነ፡ብቻውን፡ይውጣ፤ከሚስቱ፡ጋራ፡መጥቶ፡እንደ፡ኾነ፡ሚስቱ፡ከርሱ፡ጋራ፡ትውጣ ።
4፤ጌታው፡ሚስት፡አጋብቶት፡እንደ፡ኾነ፡ወንዶች፡ወይም፡ሴቶች፡ልጆች፡ብትወልድለት፥ሚስቱና፡ልጆቿ፡ለጌታ ው፡ይኹኑ፥ርሱም፡ብቻውን፡ይውጣ።
5፤ባሪያውም፦ጌታዬን፡ሚስቴን፡ልጆቼንም፡እወዳ፟ለኹ፥ሐራነት፡አልወጣም፡ብሎ፡ቢናገር፥ጌታው፡ወደ፡ፈራጆ ች፡ይውሰደው፥
6፤ወደ፡ደጁም፡ወደ፡መቃኑ፡አቅርቦ፡ዦሮውን፡በወስፌ፡ይብሳው፤ለዘለዓለምም፡ባሪያው፡ይኹን።
7፤ሰውም፡ሴት፡ልጁን፡ለባርነት፡ቢሸጥ፡ባሪያዎች፡እንደሚወጡ፡ርሷ፡አትውጣ።
8፤ጌታዋን፡ደስ፡ባታሠኘው፡በወጆ፡ይስደዳት፤ስለ፡ናቃት፡ለሌላ፡ወገን፡ሰዎች፡ይሸጣት፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ ውም።
9፤ለልጁም፡ብድራት፥ለሴት፡ልጆች፡የሚገ፟ባ፟ውን፡ያድርግላት።
10፤ከርሷ፡ሌላም፡ቢያጋባው፥መኖዋን፡ልብሷንም፡ለምንጣፏም፡ተገቢውን፡አያጕድልባት።
11፤ይህንም፡ሦስት፡ነገር፡ባያደርግላት፡ያለገንዘብ፡በከንቱ፡ትውጣ።
12፤ሰው፡ሰውን፡ቢመታ፡ቢሞትም፥ርሱ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
13፤ባይሸምቅበትም፥ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ድንገት፡በእጁ፡ቢጥለው፥የሚሸሽበት፡ስፍራ፡እኔ፡አደርግልኻ ለኹ።
14፤ሰው፡ግን፡ቢደፍር፥ባልንጀራውን፡በተንኰል፡ቢገድለው፥እንዲሞት፡ከመሠዊያዬ፡አውጥተኽ፡ውሰደው።
15፤አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሚመታ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
16፤ሰውን፡ሰርቆ፡ቢሸጥ፥ወይም፡በእጁ፡ቢገኝ፥ርሱ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
17፤አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሚሰድብ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
18፤ኹለት፡ሰዎችም፡ቢጣሉ፥አንዱም፡ሌላውን፡በድንጋይ፡ወይም፡በጡጫ፡ቢመታ፥ያም፡ባይሞት፥ነገር፡ግን፥ታሞ ፟፡በዐልጋው፡ላይ፡ቢተኛ፥
19፤ተነሥቶም፡በምርኵዝ፡ወደ፡ሜዳ፡ቢወጣ፥የመታው፡ንጹሕ፡ነው፤ነገር፡ግን፥ተግባሩን፡ስላስፈታው፡ገንዘብ ፡ይከፍለው፡ዘንድ፥ያስፈውሰውም፡ዘንድ፡ግዴታ፡አለበት።
20፤ሰውም፡ወንድ፡ባሪያውን፡ወይም፡ሴት፡ባሪያውን፡በበትር፡ቢመታ፥ቢሞትበትም፥ፈጽሞ፡ይቀጣ።
21፤የተመታው፡ግን፡አንድ፡ወይም፡ኹለት፡ቀን፡ቢቈይ፡ገንዘቡ፡ነውና፥አይቀጣ።
22፤ኹለት፡ሰዎች፡ቢጣሉ፥ያረገዘችንም፡ሴት፡ልጁን፡እስክትጨነግፍ፡ቢገፏት፡ባትጐዳ፡ግን፥የሴቲቱ፡ባል፡የ ጫነበትን፡ያኽል፡ካሳ፡ይስጥ፤ፈራጆቹም፡እንደ፡ፈረዱበት፡ይክፈል።
23፤ጕዳት፡ግን፡ቢያገኛት፡ሕይወት፡በሕይወት፥
24፤ዐይን፡በዐይን፥ጥርስ፡በጥርስ፥እጅ፡በእጅ፥
25፤እግር፡በእግር፥መቃጠል፡በመቃጠል፥ቍስል፡በቍስል፥ግርፋት፡በግርፋት፡ይከፈል።
26፤ሰውም፡የባሪያውን፡ወይም፡የባሪያዪቱን፡ዐይን፡ቢመታ፡ቢያጠፋውም፥ስለ፡ዐይኑ፡ሐራነት፡ያውጣው።
27፤የባሪያውን፡ወይም፡የባሪያዪቱን፡ጥርስ፡ቢሰብር፥ስለ፡ጥርሱ፡ሐራነት፡ያውጣው።
28፤በሬም፡ወንድን፡ወይም፡ሴትን፡እስኪሞቱ፡ድረስ፡ቢወጋ፥በሬው፡ይወገር፥ሥጋውም፡አይበላ፤የበሬው፡ባለቤ ት፡ግን፡ንጹሕ፡ነው።
29፤በሬው፡ግን፡አስቀድሞ፡ተዋጊ፡ቢኾን፥ሰዎችም፡ለባለቤቱ፡ቢመሰክሩለት፡ባይጠብቀውም፥ወንድንም፡ወይም፡ ሴትን፡ቢገድል፥በሬው፡ይወገር፥ባለቤቱ፡ደግሞ፡ይገደል።
30፤ከርሱ፡ግን፡ካሳ፡ቢፈልጉ፥የሕይወቱን፡ወጆ፡የጫኑበትን፡ያኽል፡ይስጥ።
31፤ደግሞ፡ወንድን፡ልጅ፡ቢወጋ፥ሴትንም፡ልጅ፡ቢወጋ፥ይህንኑ፡ፍርድ፡ያድርጉበት።
32፤በሬው፡ወንድ፡ባሪያ፡ወይም፡ሴት፡ባሪያ፡ቢወጋ፥የበሬው፡ባለቤት፡ሠላሳ፡የብር፡ሰቅል፡ለጌታቸው፡ይስጥ ፥በሬውም፡ይወገር።
33፤ሰውም፡ጕድጓድ፡ቢከፍት፥ወይም፡ጕድጓድ፡ቢቈፍር፡ባይከድነውም፥በሬም፡ወይም፡አህያ፡ቢወድቅበት፥
34፤የጕድጓዱ፡ባለቤት፡ዋጋቸውን፡ለባለቤታቸው፡ይክፈል፤የሞተውም፡ለርሱ፡ይኹን።
35፤የሰው፡በሬ፡የሌላውን፡በሬ፡እስኪሞት፡ድረስ፡ቢወጋ፥ደኅናውን፡በሬ፡ይሽጡ፥ዋጋውንም፡በትክክል፡ይካፈ ሉ፤የሞተውንም፡ደግሞ፡በትክክል፡ይካፈሉ።
36፤በሬውም፡አስቀድሞ፡ተዋጊ፡መኾኑ፡ቢታወቅ፥ባለቤቱም፡ባይጠብቀው፥በሬውን፡በበሬው፡ፈንታ፡ይስጥ፥የሞተ ውም፡ለርሱ፡ይኹነው።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤ሰው፡በሬ፡ወይም፡በግ፡ቢሰርቅ፥ቢያርደው፡ወይም፡ቢሸጠው፥በበሬው፡ፋንታ፡ዐምስት፡በሬዎች፥በበጉም፡ፋ ንታ፡አራት፡በጎች፡ይክፈል።
2፤ሌባው፡ቤት፡ሲምስ፡ቢገኝ፥ርሱም፡እስኪሞት፡ቢመታ፥በመታው፡ሰው፡ላይ፡የደም፡ዕዳ፡አይኾንበትም።
3፤ፀሓይ፡ግን፡ከወጣችበት፡የደም፡ዕዳ፡አለበት፤ሌባው፡የሰረቀውን፡ይመልስ፤የሚከፍለውም፡ቢያጣ፡ስለሰረ ቀው፡ይሸጥ።
4፤የሰረቀው፡ደኅና፡ኾኖ፡በእጁ፡ቢገኝ፥በሬም፡ወይም፡አህያ፡ወይም፡በግ፡ቢኾን፥የሰረቀውን፡ያኽል፡ኹለት ፡ዕጥፍ፡ይክፈል።
5፤ማንም፡ሰው፡ወደ፡ዕርሻ፡ወይም፡ወደወይን፡ስፍራ፡ከብቱን፡ቢነዳው፥የሌላውንም፡ዕርሻ፡ቢያስበላ፥ከተመ ረጠ፡ዕርሻው፡ከማለፊያውም፡ወይኑ፡ይካስ።
6፤እሳት፡ቢነሣ፥ሾኽንም፡ቢይዝ፥ክምሩንም፡ወይም፡ያልታጨደውን፡እኽል፡ወይም፡ዕርሻውን፡ቢያቃጥል፥እሳቱ ን፡ያነደደው፡ይካስ።
7፤ሰው፡በባልንጀራው፡ዘንድ፡ብር፡ወይም፡ሌላ፡ነገር፡እንዲጠብቅለት፡ዐደራ፡ቢያኖር፡ከቤቱም፡ቢሰረቅ፥ሌ ባው፡ቢገኝ፡ስለ፡አንድ፡ኹለት፡ይክፈል።
8፤ሌባውም፡ባይገኝ፡ባለቤቱ፡ወደ፡ፈራጆች፡ይቅረብ፥እጁንም፡በባልንጀራው፡ከብት፡ላይ፡እንዳልዘረጋ፡ይማ ል።
9፤ሰዎች፡ስለ፡በሬ፡ወይም፡ስለ፡አህያ፡ወይም፡ስለ፡በግ፡ወይም፡ስለ፡ልብስ፡ወይም፡ስለ፡ሌላ፡ስለጠፋ፡ነ ገር፡ቢካሰሱ፥አንዱም፦ይህ፡የእኔ፡ነው፡ቢል፥ክርክራቸው፡ወደ፡ፈራጆች፡ይድረስ፤ፈራጆቹም፡የፈረዱበት፡ር ሱ፡ለባልንጀራው፡ባንድ፡ኹለት፡ይክፈል።
10፤ሰው፡በባልንጀራው፡ዘንድ፡አህያ፡ወይም፡በሬ፡ወይም፡በግ፡ወይም፡ሌላ፡እንስሳ፡እንዲጠብቅለት፡ዐደራ፡ ቢያኖር፥ማንም፡ሳያይ፡ቢሞት፡ወይም፡ቢጐዳ፡ወይም፡ቢማረክ፥
11፤በባልንጀራው፡ከብት፡ላይ፡እጁን፡እንዳልዘረጋ፡የእግዚአብሔር፡መሐላ፡በኹለታቸው፡መካከል፡ይኹን፤የከ ብቱም፡ባለቤት፡መሐላውን፡ይቀበል፥ርሱም፡ምንም፡አይክፈል።
12፤ከርሱም፡ዘንድ፡ቢሰረቅ፡የጠፋውን፡ያኽል፡ለባለቤቱ፡ይመልስ።
13፤ተቧጭሮም፡ቢገኝ፡ለምስክር፡ያምጣው፤በመቧጨሩም፡ምክንያት፡አይክፈል።
14፤ከባልንጀራው፡አንዳች፡ቢዋስ፡ባለቤቱ፡ከርሱ፡ጋራ፡ሳይኖር፡ቢጐዳ፥ወይም፡ቢሞት፥ፈጽሞ፡ይክፈለው።
15፤ባለቤቱ፡ግን፡ከርሱ፡ጋራ፡ቢኖር፡አይክፈል፤ቢከራየው፡በክራዩ፡ይግባ።
16፤ሰው፡ያልታጨችውን፡ድንግል፡ቢያስታት፥ከርሷም፡ጋራ፡ቢተኛ፥ማጫዋን፡ሰጥቶ፡ሚስት፡ያድርጋት።
17፤አባቷም፡ርሷን፡እንዳይሰጠው፡ፈጽሞ፡እንቢ፡ቢል፡እንደ፡ደናግል፡ማጫ፡ያኽል፡ብር፡ይክፈላት።
18፤መተተኛዪቱን፡በሕይወት፡እንድትኖር፡አትፍቀድላት።
19፤ከእንስሳ፡ጋራ፡የሚረክስ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
20፤ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ለአንዳች፡አምላክ፡የሚሠዋ፡ፈጽሞ፡ይጥፋ።
21፤እናንተ፡በግብጽ፡ምድር፡ስደተኛዎች፡ነበራችኹና፡ስደተኛውን፡አትበድለው፥ግፍም፡አታድርግበት።
22፤መበለቲቱንና፡ድኻ፡አደጎቹን፡አታስጨንቋቸው።
23፤ብታስጨንቋቸውና፡ወደ፡እኔ፡ቢጮኹ፡እኔ፡ጩኸታቸውን፡ፈጽሞ፡እሰማለኹ፤
24፤ቍጣዬም፡ይጸናባችዃል፥በሰይፍም፡አስገድላችዃለኹ፤ሚስቶቻችኹም፡መበለት፥ልጆቻችኹም፡ድኻ፡አደጎች፡ይ ኾናሉ።
25፤ከአንተ፡ጋራ፡ለተቀመጠው፡ለወገኔ፡ለድኻው፡ገንዘብ፡ብታበድረው፥እንደ፡ባለዐራጣ፡አትኹን፥ዐራጣም፡አ ትጫንበት።
26፤የባልንጀራኽን፡ልብስ፡ለመያዣ፡ብትወስድ፡ፀሓይ፡ሳትገባ፡መልስለት፤
27፤ሥጋውን፡የሚከድንበት፡ርሱ፡ብቻ፡ነውና፤የሚተኛበትም፡ሌላ፡የለውምና፤ወደ፡እኔም፡ቢጮኽ፡መሓሪ፡ነኝና ፡እሰማዋለኹ።
28፤ፈራጆችን፡አትስደብ፥የሕዝብኽንም፡አለቃ፡አትርገመው።
29፤ነዶኽንም፡የወይንኽንም፡ጭማቂ፡ለማቅረብ፡አትዘግይ፤የልጆችኽንም፡በኵር፡ትሰጠኛለኽ።
30፤እንዲህም፡በበሬዎችኽና፡በበጎችኽ፡ታደርገዋለኽ፤ሰባት፡ቀን፡ከእናቱ፡ጋራ፡ይቀመጥ፥በስምንተኛውም፡ቀ ን፡ለእኔ፡ትሰጠዋለኽ።
31፤ቅዱስ፡ወገን፡ትኾኑልኛላችኹ፤ስለዚህ፥በምድረ፡በዳ፡አውሬ፡የቧጨረውን፡ሥጋ፡ለውሻ፡ጣሉት፡እንጂ፡አት ብሉት።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤ሐሰተኛ፡ወሬ፡አትቀበል፤ሐሰተኛ፡ምስክርም፡ትኾን፡ዘንድ፡ከኀጢአተኛ፡ጋራ፡እጅኽን፡አታንሣ።
2፤ክፉውን፡ለማድረግ፡ብዙ፡ሰዎችን፡አትከተል፤ፍርድንም፡ለማጥመም፡ከብዙ፡ሰዎች፡ጋራ፡ተስማምተኽ፡አትመ ስክር።
3፤በፍርድ፡ነገርም፡ለድኻው፡አታድላ።
4፤የጠላትኽን፡በሬ፡ወይም፡አህያውን፡ጠፍቶ፡ብታገኘው፡በፍጹም፡መልስለት።
5፤የሚጠላኽን፡ሰው፡አህያ፡ከሸክሙ፡በታች፡ወድቆ፡ብታየው፡አትተወው፥ነገር፡ግን፥ከርሱ፡ጋራ፡አንሣው።
6፤በሚሟገትበት፡ጊዜ፡የድኻኽን፡ፍርድ፡አታጥምም።
7፤ከሐሰት፡ነገር፡ራቅ፤እኔ፡ኀጢአተኛውን፡አላጸድቅምና፡ንጹሕንና፡ጻድቅን፡አትግደል።
8፤ማማለጃን፡አትቀበል፤ማማለጃ፡የዐይናማዎችን፡ሰዎች፡ዐይን፡ያሳውራልና፥የጻድቃንንም፡ቃል፡ያጣምማልና ።
9፤በስደተኛው፡ግፍ፡አታድርጉ፤እናንተ፡በግብጽ፡ምድር፡ስደተኛዎች፡ስለ፡ነበራችኹ፡የስደተኛ፡ነፍስ፡እን ዴት፡እንደ፡ኾነች፡ዐውቃችዃልና።
10፤ስድስት፡ዓመት፡ምድርኽን፡ዝራ፥ፍሬዋንም፡አግባ፤
11፤በሰባተኛው፡ዓመት፡ግን፡ተዋት፡አሳርፋትም፤የሕዝብኽም፡ድኻዎች፡ይበሉታል፤ያስቀሩትንም፡የሜዳ፡እንስ ሳ፡ይብላው።እንዲሁም፡በወይንኽና፡በወይራኽ፡አድርግ።
12፤ስድስት፡ቀን፡ሥራኽን፡ሥራ፤በሬኽና፡አህያኽ፡ያርፉ፡ዘንድ፡ለባሪያኽም፡ልጅ፡ለመጻተኛውም፡ዕረፍት፡ይ ኾን፡ዘንድ፡በሰባተኛው፡ቀን፡ዕረፍ።
13፤ያልዃችኹንም፡ነገር፡ዅሉ፡ጠብቁ፤የሌላዎችንም፡አማልክት፡ስም፡አትጥሩ፥ከአፋችኹም፡አይሰማ።
14፤በዓመት፡ሦስት፡ጊዜ፡በዓል፡ታደርግልኛለኽ።
15፤የቂጣውን፡በዓል፡ጠብቅ፤በአቢብ፡ወር፡ከግብጽ፡ምድር፡ወጥታችዃልና፥በዚህ፡ወር፡እንዳዘዝኹኽ፡ሰባት፡ ቀን፡ቂጣ፡እንጀራ፡ትበላለኽ፤በፊቴም፡ባዶ፡እጃችኹን፡አትታዩ።
16፤በዕርሻም፡የምትዘራትን፡የፍሬኽን፡በኵራት፡የመከር፡በዓል፥ዓመቱም፡ሳያልቅ፡ፍሬኽን፡ከዕርሻ፡ባከማቸ ኽ፡ጊዜ፡የመክተቻውን፡በዓል፡ጠብቅ።
17፤በዓመት፡ሦስት፡ጊዜ፡ባንተ፡ዘንድ፡ያለው፡ወንድ፡ዅሉ፡በጌታ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይታይ።
18፤የመሥዋዕቴን፡ደም፡ከቦካ፡እንጀራ፡ጋራ፡አትሠዋ፤የበዓሌም፡ስብ፡እስኪነጋ፡አይደር።
19፤የተመረጠውን፡የምድርኽን፡ፍሬ፡በኵራት፡ወደአምላክኽ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አምጣ።ጠቦትን፡በእናቱ፡ ወተት፡አትቀቅል።
20፤በመንገድ፡ይጠብቅኽ፡ዘንድ፡ወዳዘጋጀኹትም፡ስፍራ፡ያገባኽ፡ዘንድ፥እንሆ፥እኔ፡መልአክን፡በፊትኽ፡እሰ ዳ፟ለኹ።
21፤በፊቱ፡ተጠንቀቁ፥ቃሉንም፡አድምጡ፤ስሜም፡በርሱ፡ስለ፡ኾነ፡ኀጢአት፡ብትሠሩ፡ይቅር፡አይልምና፡አታስመ ርሩት።
22፤አንተ፡ግን፡ቃሉን፡ብትሰማ፥ያልኹኽንም፡ዅሉ፡ብታደርግ፥ጠላቶችኽን፡እጣላቸዋለኹ፥የሚያስጨንቁኽንም፡ አስጨንቃቸዋለኹ።
23፤መልአኬ፡በፊትኽ፡ይኼዳልና፥ወደ፡አሞራውያንም፡ወደ፡ኬጢያውያንም፡ወደ፡ፌርዛውያንም፡ወደ፡ከነዓናውያ ንም፡ወደ፡ዔዊያውያንም፡ወደ፡ኢያቡሳውያንም፡ያገባኻል፤እኔም፡አጠፋቸዋለኹ።
24፤ለአማልክታቸው፡አትስገድ፥አታምልካቸውም፤እንደ፡ሥራቸውም፡አትሥራ፤ነገር፡ግን፥ፈጽመኽ፡አፍርሳቸው፥ ሐውልቶቻቸውንም፡ሰባብራቸው።
25፤አምላካችኹንም፡እግዚአብሔርን፡ታመልኩታላችኹ፥ርሱም፡እኽልኽንና፡ውሃኽን፡ይባርካል፤በሽታንም፡ከመካ ከልኽ፡አርቃለኹ።
26፤በምድርኽም፡መካን፡ወይም፡የምትጨነግፍ፡አትኾንም፤የዘመንኽን፡ቍጥር፡እሞላለኹ።
27፤መፈራቴንም፡በፊትኽ፡እሰዳ፟ለኹ፥የምትኼድበትንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡አስደነግጣቸዋለኹ፥ጠላቶችኽንም፡ዅሉ፡ በፊትኽ፡ዠርባቸውን፡እንዲያዞሩ፡አደርጋለኹ።
28፤በፊትኽም፡ተርብ፡እሰዳ፟ለኹ፥ዔዊያዊውንም፡ከነዓናዊውንም፡ኬጢያዊውንም፡ከፊትኽ፡አባርራለኹ።
29፤ምድር፡ባድማ፡እንዳትኾን፥የምድር፡አራዊትም፡እንዳይበዙብኽ፥ባንድ፡ዓመት፡ከፊታችኹ፡አላባርራቸውም።
30፤ነገር፡ግን፥እስክትበዛ፡ምድርንም፡እስክትወርስ፡ድረስ፡በጥቂት፡በጥቂት፡አባርራቸዋለኹ።
31፤ድንበርኽንም፡ከቀይ፡ባሕር፡እስከፍልስጥኤም፡ባሕር፥ከምድረ፡በዳም፡እስከ፡ወንዙ፡ድረስ፡አደርጋለኹ፤ በምድር፡የሚኖሩትን፡በእጅኽ፡እጥላለኹና፤ከፊትኽም፡ታባርራቸዋለኽ።
32፤ከነርሱና፡ከአማልክታቸው፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አታድርግ።
33፤አማልክታቸውንም፡ብታመልክ፡ወጥመድ፡ይኾኑብኻልና፥እኔን፡እንድትበድል፡እንዳያደርጉኽ፡በአገርኽ፡አይ ቀመጡ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤ሙሴንም፦አንተ፡አሮንም፡ናዳብም፡አብዩድም፡ከእስራኤልም፡ሰባ፡ሽማግሌዎች፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ውጡ፥በ ሩቁም፡ስገዱ፤
2፤ሙሴም፡ብቻውን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይቅረብ፥እነርሱ፡ግን፡አይቅረቡ፤ሕዝቡም፡ከርሱ፡ጋራ፡አይውጡ፡አለ ው።
3፤ሙሴም፡መጣ፡ለሕዝቡም፡የእግዚአብሔርን፡ቃሎች፡ዅሉ፡ሥርዐቱንም፡ዅሉ፡ነገረ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ባንድ፡ድም ፅ፦እግዚአብሔር፡የተናገራቸውን፡ቃሎች፡ዅሉ፡እናደርጋለን፡ብለው፡መለሱ።
4፤ሙሴም፡የእግዚአብሔርን፡ቃሎች፡ጻፈ፤ማለዳም፡ተነሣ፥ከተራራውም፡በታች፡መሠዊያን፥ዐሥራ፡ኹለትም፡ሐው ልቶች፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፡የእስራኤል፡ነገድ፡ሠራ።
5፤የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡እንዲያቀርቡ፥ለእግዚአብሔርም፡ስለ፡ደኅንነት፡መሥዋዕት፡በሬዎችን፡እንዲሠዉ፡የ እስራኤልን፡ልጆች፡ጐበዛዝት፡ሰደደ።
6፤ሙሴም፡የደሙን፡እኩሌታ፡ወስዶ፡በቈሬ፡ውስጥ፡አደረገው፤የደሙንም፡እኩሌታ፡በመሠዊያው፡ረጨው።
7፤የቃል፡ኪዳኑንም፡መጽሐፍ፡ወስዶ፡ለሕዝቡ፡አነበበላቸው፤እነርሱም፦እግዚአብሔር፡ያለውን፡ዅሉ፡እናደር ጋለን፡እንታዘዛለንም፡አሉ።
8፤ሙሴም፡ደሙን፡ወስዶ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ረጨው፦በዚህ፡ቃል፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ከእናንተ፡ጋራ፡ያደረገው፡የ ቃል፡ኪዳኑ፡ደም፥እንሆ፥አለ።
9፤ሙሴም፡አሮንም፡ናዳብም፡አብዩድም፡ከእስራኤልም፡ሰባ፡ሽማግሌዎች፡ወጡ፤
10፤የእስራኤልንም፡አምላክ፡አዩ፤ከእግሩም፡በታች፡እንደሰማይ፡መልክ፡የሚያበራ፡እንደ፡ብሩህ፡ሰንፔር፡ድ ንጋይ፡የሚመስል፡ወለል፡ነበረ።
11፤እጁንም፡በእስራኤል፡ዐዛውንቶች፡ላይ፡አልዘረጋም፤እነርሱም፡እግዚአብሔርን፡አዩ፥በሉም፡ጠጡም።
12፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ወደ፡እኔ፡ወደ፡ተራራው፡ውጣ፥በዚያም፡ኹን፤እነርሱን፡ታስተምር፡ዘንድ፡እኔ፡የ ጻፍኹትን፡ሕግና፡ትእዛዝ፡የድንጋይም፡ጽላት፡እሰጥኻለኹ፡አለው።
13፤ሙሴና፡ሎሌው፡ኢያሱ፡ተነሡ፤ሙሴም፡ወደእግዚአብሔር፡ተራራ፡ወጣ።
14፤ሽማግሌዎችንም፦ወደ፡እናንተ፡እስክንመለስ፡ድረስ፡በዚህ፡ቈዩን፤አሮንና፡ሖርም፥እንሆ፥ከእናንተ፡ጋራ ፡ናቸው፥ነገረተኛም፡ቢኖር፡ወደ፡እነርሱ፡ይምጣ፡አላቸው።
15፤ሙሴም፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ፥ደመናውም፡ተራራውን፡ሸፈነው።
16፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡በሲና፡ተራራ፡ላይ፡ተቀመጠ፥ደመናውም፡ስድስት፡ቀን፡ሸፈነው፤በሰባተኛውም፡ቀ ን፡ከደመናው፡ውስጥ፡ሙሴን፡ጠራው።
17፤በተራራው፡ራስ፡ላይ፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡የእግዚአብሔር፡ክብር፡መታየት፡እንደሚያቃጥል፡እሳት፡ነ በረ።
18፤ሙሴም፡ወደ፡ደመናው፡ውስጥ፡ገባ፡ወደ፡ተራራውም፡ወጣ፤ሙሴም፡በተራራው፡ላይ፡አርባ፡ቀን፡አርባ፡ሌሊት ም፡ቈየ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረው፦
2፤ስጦታ፡ያመጡልኝ፡ዘንድ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ተናገር፤በገዛ፡እጁ፡ሊሰጠኝ፡በልቡ፡ከሚያምረው፡ሰው፡ዅሉ ፡መባ፡ተቀበሉ።
3፤ከነርሱም፡የምትቀበሉት፡መባ፡ይህ፡ነው፤
4፤ወርቅ፥ብር፥ናስም፥ሰማያዊና፡ሐምራዊ፡ቀይም፡ግምጃ፥ጥሩ፡በፍታም፥
5፤የፍየልም፡ጠጕር፥ቀይ፡የአውራ፡በግ፡ቍርበት፥የአቍስጣ፡ቍርበት፥የግራርም፡ዕንጨት፥
6፤የመብራትም፡ዘይት፥ለቅብዐት፡ዘይትና፡ለጣፋጭ፡ዕጣን፡ቅመም፥
7፤መረግድም፥ለኤፉድና፡ለደረት፡ኪስ፡የሚደረግ፡ፈርጥ።
8፤በመካከላቸውም፡ዐድር፡ዘንድ፡መቅደስ፡ይሥሩልኝ።
9፤እኔ፡እንደማሳይኽ፡ዅሉ፥እንደ፡ማደሪያው፡ምሳሌ፡እንደ፡ዕቃውም፡ዅሉ፡ምሳሌ፥እንዲሁ፡ሥሩት።
10፤ከግራር፡ዕንጨትም፡ታቦትን፡ይሥሩ፤ርዝመቱ፡ኹለት፡ክንድ፡ተኩል፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፥ቁመቱም ፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡ይኹን።
11፤በውስጥና፡በውጭም፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለብጠው፤በርሱም፡ላይ፡በዙሪያው፡የወርቅ፡አክሊል፡አድርግለት።
12፤አራት፡የወርቅ፡ቀለበቶችም፡አድርግለት፥እነርሱንም፡በአራቱ፡እግሮቹ፡ላይ፡አኑር፤ባንድ፡ወገን፡ኹለት ፡ቀለበቶች፥በሌላው፡ወገን፡ኹለት፡ቀለበቶች፡ይኹኑ።
13፤መሎጊያዎችንም፡ከግራር፡ዕንጨት፡ሥራ፥በወርቅም፡ለብጣቸው።
14፤ለታቦቱ፡መሸከሚያ፡በታቦቱ፡ጐን፡ባሉት፡ቀለበቶች፡መሎጊያዎቹን፡አግባ።
15፤መሎጊያዎቹም፡በታቦቱ፡ቀለበቶች፡ውስጥ፡ይኑሩ፥ከቶም፡አይውጡ።
16፤በታቦቱም፡ውስጥ፡እኔ፡የምሰጥኽን፡ምስክር፡ታስቀምጣለኽ።
17፤ከጥሩ፡ወርቅም፡ርዝመቱ፡ኹለት፡ክንድ፡ተኩል፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡የኾነ፡የስርየት፡መክደኛ፡ ሥራ።
18፤ኹለት፡ኪሩቤል፡ከተቀጠቀጠ፡ወርቅ፡ሥራ፥በስርየት፡መክደኛውም፡ላይ፡በኹለት፡ወገን፡ታደርጋቸዋለኽ።
19፤ከስርየት፡መክደኛውም፡ጋራ፡አንዱን፡ኪሩብ፡ባንድ፡ወገን፥ኹለተኛውንም፡ኪሩብ፡በሌላው፡ወገን፡አድርገ ኽ፡ባንድ፡ላይ፡ትሠራዋለኽ።
20፤ኪሩቤልም፡ክንፎቻቸውን፡ወደ፡ላይ፡ይዘረጋሉ፥የስርየት፡መክደኛውንም፡በክንፎቻቸው፡ይሸፍናሉ፥ፊታቸው ም፡ርስ፡በርሱ፡ይተያያል፤የኪሩቤልም፡ፊቶቻቸው፡ወደ፡ስርየት፡መክደኛው፡ይመለከታሉ።
21፤የስርየት፡መክደኛውንም፡በታቦቱ፡ላይ፡ታደርገዋለኽ፤እኔም፡የምሰጥኽን፡ምስክር፡በታቦቱ፡ውስጥ፡ታኖረ ዋለኽ።
22፤በዚያም፡ከአንተ፡ጋራ፡እገናኛለኹ፤የእስራኤልንም፡ልጆች፡ታዝ፟፡ዘንድ፡የምሰጥኽን፡ነገር፡ዅሉ፥በምስ ክሩ፡ታቦት፡ላይ፡ባለው፡በኹለት፡ኪሩቤል፡መካከል፥በስርየት፡መክደኛውም፡ላይ፡ኾኜ፡እነጋገርኻለኹ።
23፤ርዝመቱም፡ኹለት፡ክንድ፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፥ቁመቱ፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡የኾነ፡ገበታ፡ከግራር፡ዕን ጨት፡ሥራ።
24፤በጥሩም፡ወርቅ፡ትለብጠዋለኽ፤በዙሪያውም፡የወርቅ፡አክሊል፡አድርግለት፤
25፤በዙሪያውም፡አንድ፡ጋት፡የሚያኽል፡ክፈፍ፡አድርግለት፤የወርቅም፡አክሊል፡በክፈፉ፡ዙሪያ፡አድርግለት።
26፤አራትም፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡አድርግለት፤ቀለበቶቹንም፡አራቱ፡እግሮቹ፡ባሉበት፡በአራቱ፡ማእዘኖች፡አድ ርግ።
27፤ገበታውንም፡ለመሸከም፡መሎጊያዎቹ፡እንዲሰኩባቸው፡ቀለበቶቹ፡በክፈፉ፡አቅራቢያ፡ይኹኑ።
28፤ገበታውን፡ይሸከሙባቸው፡ዘንድ፡መሎጊያዎቹን፡ከግራር፡ዕንጨት፡ሠርተኽ፡በወርቅ፡ለብጣቸው።
29፤ለማፍሰሻም፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ወጭቶቿን፡ጭልፋዎቿንም፡መቅጃዎቿንም፡ጽዋዎቿንም፡አድርግ፤እነርሱንም፡ከጥ ሩ፡ወርቅ፡አድርጋቸው።
30፤በገበታም፡ላይ፡የገጽ፡ኅብስት፡ዅል፡ጊዜ፡በፊቴ፡ታደርጋለኽ።
31፤መቅረዝንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡አድርግ፤መቅረዙ፡ከእግሩና፡ከአገዳው፡ጋራ፡በተቀጠቀጠ፡ሥራ፡ይደረግ፤ጽዋዎ ቹም፡ጕብጕቦቹም፡አበባዎቹም፡አንድነት፡በርሱ፡ይደረጉበት።
32፤በስተጐኑ፡ስድስት፡ቅርንጫፎች፡ይውጡለት፤ሦስት፡የመቅረዙ፡ቅርንጫፎች፡ባንድ፡ወገን፥ሦስትም፡የመቅረ ዙ፡ቅርንጫፎች፡በሌላ፡ወገን፡ይውጡ።
33፤በአንደኛውም፡ቅርንጫፍ፡ጕብጕብና፡አበባ፡ሦስትም፡የለውዝ፡አበባ፡የሚመስሉትን፡ጽዋዎች፥በኹለተኛውም ፡ቅርንጫፍ፡ጕብጕብና፡አበባ፡ሦስትም፡የለውዝ፡አበባ፡የሚመስሉትን፡ጽዋዎች፤እንዲሁም፡ከመቅረዙ፡ለሚወጡ ፡ለስድስቱ፡ቅርንጫፎች፡አድርግ።
34፤በመቅረዙም፡ጕብጕቦቹንና፡አበባዎቹን፡አራትም፡የለውዝ፡አበባ፡የሚመስሉትን፡ጽዋዎች፡አድርግ።
35፤ከመቅረዙ፡ለሚወጡ፡ለስድስቱ፡ቅርንጫፎች፡ከኹለት፡ቅርንጫፎች፡በታች፡አንድ፡ኾኖ፡የተሠራ፡አንድ፡ጕብ ጕብ፥ከኹለትም፡ቅርንጫፎች፡በታች፡አንድ፡ኾኖ፡የተሠራ፡አንድ፡ጕብጕብ፥ደግሞ፡ከኹለት፡ቅርንጫፎች፡በታች ፡አንድ፡ኾኖ፡የተሠራ፡አንድ፡ጕብጕብ፡ይኹን።
36፤ጕብጕቦቹና፡ቅርንጫፎቹ፡ዅሉ፡ከርሱ፡ጋራ፡አንድ፡ይኹኑ፤ዅሉም፡አንድ፡ኾኖ፡ከተቀረጸ፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ይ ደረግ።
37፤ሰባቱንም፡መብራቶች፡ሥራ፤በፊቱ፡ያበሩ፡ዘንድ፡መብራቶቹን፡ያቀጣጥሏቸዋል።
38፤መኰስተሪያዎቿን፡የኵስታሪ፡ማድረጊያዎቿንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡አድርግ።
39፤መቅረዙም፡ዕቃውም፡ዅሉ፡ካንድ፡መክሊት፡ጥሩ፡ወርቅ፡ይሠሩ።
40፤በተራራ፡ላይ፡እንዳሳየኹኽ፡ምሳሌ፡እንድትሠራ፡ተጠንቀቅ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤ደግሞም፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታ፥ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡የተሠሩ፡ዐሥር፡መጋረጃዎች፡ያ ሉበትን፡ማደሪያ፡ሥራ፤ብልኅ፡ሠራተኛ፡እንደሚሠራ፡ኪሩቤል፡በእነርሱ፡ላይ፡ይኹኑ።
2፤የያንዳንዱ፡መጋረጃ፡ርዝመት፡ኻያ፡ስምንት፡ክንድ፥ወርዱም፡አራት፡ክንድ፡ይኹን፤የመጋረጃዎቹ፡ዅሉ፡መ ጠን፡ትክክል፡ይኹን።
3፤ዐምስቱ፡መጋረጃዎች፡ርስ፡በርሳቸው፡የተጋጠሙ፡ይኹኑ፤ዐምስቱም፡መጋረጃዎች፡እንዲሁ፡ርስ፡በርሳቸው፡ የተጋጠሙ፡ይኹኑ።
4፤ከሚጋጠሙት፡መጋረጃዎች፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡የሰማያዊውን፡ግምጃ፡ቀለበቶች፡አድርግ፤ደግ ሞ፡ከተጋጠሙት፡ከሌላዎች፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡እንዲሁ፡አድርግ።
5፤ዐምሳ፡ቀለበቶችን፡ባንድ፡መጋረጃ፡አድርግ፥ዐምሳውንም፡ቀለበቶች፡በኹለተኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡አድርግ ፤ቀለበቶቹ፡ዅሉ፡ርስ፡በርሳቸው፡ፊት፡ለፊት፡ይኾናሉ።
6፤ዐምሳ፡የወርቅ፡መያዣዎች፡ሥራ፤ማደሪያውንም፡አንድ፡እንዲኾን፡መጋረጃዎችን፡ርስ፡በርሳቸው፡በመያዣዎ ች፡አጋጥማቸው።
7፤ከማደሪያውም፡በላይ፡ለድንኳን፡የሚኾኑ፡መጋረጃዎች፡ከፍየል፡ጠጕር፡አድርግ፤ዐሥራ፡አንድ፡መጋረጃዎች ፡ታደርጋለኽ።
8፤እያንዳንዱም፡መጋረጃ፡ርዝመቱ፡ሠላሳ፡ክንድ፥እያንዳንዱም፡መጋረጃ፡ወርዱ፡አራት፡ክንድ፡ይኹን፤የዐሥ ራ፡አንዱም፡መጋረጃዎች፡መጠናቸው፡ትክክል፡ይኹን።
9፤ዐምስቱ፡መጋረጃዎች፡አንድ፡ኾነው፡ይጋጠሙ፥ስድስቱም፡መጋረጃዎች፡ርስ፡በርሳቸው፡አንድ፡ኾነው፡ይጋጠ ሙ፤ስድስተኛውም፡መጋረጃ፡በድንኳኑ፡ፊት፡ይደረብ።
10፤ከተጋጠሙት፡መጋረጃዎች፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡ዐምሳ፡ቀለበቶች፡አድርግ፤ደግሞ፡ከተጋጠሙት ፡ከሌላዎቹ፡በአንድኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡እንዲሁ፡ዐምሳ፡ቀለበቶች፡አድርግ።
11፤ዐምሳም፡የናስ፡መያዣዎችን፡ሥራ፥መያዣዎችንም፡ወደ፡ቀለበቶች፡አግባቸው፥ድንኳኑም፡አንድ፡እንዲኾን፡ አጋጥመው።
12፤ከድንኳኑ፡መጋረጃዎች፡የቀረ፡ትርፍ፡ግማሽ፡መጋረጃ፡በማደሪያው፡ዠርባ፡ይንጠልጠል።
13፤ማደሪያውን፡እንዲሸፍን፡ከርዝመቱ፡ባንድ፡ወገን፡አንድ፡ክንድ፥ባንድ፡ወገንም፡አንድ፡ክንድ፡ከድንኳኑ ፡መጋረጃዎች፡የቀረው፡ትርፍ፡በማደሪያው፡ውጭ፡በወዲህና፡በወዲያ፡ይንጠልጠል።
14፤ለድንኳኑም፡መደረቢያ፡ከቀይ፡አውራ፡በግ፡ቍርበት፥ከዚያም፡በላይ፡ሌላ፡መደረቢያ፡ከአቍስጣ፡ቍርበት፡ አድርግ።
15፤ለማደሪያውም፡የሚቆሙትን፡ሳንቃዎች፡ከግራር፡ዕንጨት፡አድርግ።
16፤የሳንቃው፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡ዐሥር፡ክንድ፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡ይኹን።
17፤ለያንዳንዱም፡ሳንቃ፡አንዱን፡በአንዱ፡ላይ፡የሚያያይዙ፡ኹለት፡ማጋጠሚያዎች፡ይኹኑለት፤ለማደሪያው፡ሳ ንቃዎች፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አድርግ።
18፤ለማደሪያውም፡በደቡብ፡ወገን፡ኻያ፡ሳንቃዎችን፡አድርግ።
19፤ከኻያውም፡ሳንቃዎች፡በታች፡አርባ፡የብር፡እግሮችን፡አድርግ፤ከያንዳንዱ፡ሳንቃ፡በታች፡ለኹለት፡ማጋጠ ሚያዎች፡ኹለት፡እግሮች፡ይኹኑ።
20፤ለማደሪያው፡ለኹለተኛው፡ወገን፡በሰሜን፡በኩል፡ኻያ፡ሳንቃዎች፥
21፤ለእነርሱም፡አርባ፡የብር፡እግሮች፡ይኹኑ፤ከያንዳንዱም፡ሳንቃ፡በታች፡ኹለት፡እግሮች፡ይኹኑ።
22፤ለማደሪያውም፡በምዕራቡ፡ወገን፡በስተዃላ፡ስድስት፡ሳንቃዎችን፡አድርግ።
23፤ለማደሪያውም፡ለኹለቱ፡ማእዘን፡በስተዃላ፡ኹለት፡ሳንቃዎችን፡አድርግ።
24፤ከታችም፡እስከ፡ላይ፡እስከ፡አንደኛው፡ቀለበት፡ድረስ፡አንዱ፡ሳንቃ፡ድርብ፡ይኹን፤እንዲሁም፡ለኹለቱ፡ ይኹን፤እነርሱም፡ለኹለቱ፡ማእዘን፡ይኾናሉ።
25፤ስምንት፡ሳንቃዎችና፡ዐሥራ፡ስድስት፡የብር፡እግሮቻቸው፡ይኹኑ፤ከያንዳንዱም፡ሳንቃ፡በታች፡ኹለት፡እግ ሮች፡ይኾናሉ።
26፤ከግራርም፡ዕንጨት፡በማደሪያው፡ባንድ፡ወገን፡ላሉት፡ሳንቃዎች፡ዐምስት፡መወርወሪያዎች፥
27፤በማደሪያውም፡በኹለተኛው፡ወገን፡ላሉት፡ሳንቃዎች፡ዐምስት፡መወርወሪያዎች፥በማደሪያውም፡በስተዃላ፡በ ምዕራብ፡ወገን፡ላሉት፡ሳንቃዎች፡ዐምስት፡መወርወሪያዎች፡አድርግ።
28፤መካከለኛውም፡መወርወሪያ፡በሳንቃዎች፡መካከል፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ይለፍ።
29፤ሳንቃዎቹንም፡በወርቅ፡ለብጣቸው፤ቀለበቶቻቸውንም፡የመወርወሪያ፡ቤት፡እንዲኾኑላቸው፡ከወርቅ፡ሥራቸው ፤መወርወሪያዎችንም፡በወርቅ፡ለብጣቸው።
30፤ማደሪያውንም፡በተራራ፡እንዳሳየኹኽ፡ምሳሌ፡አቁም።
31፤መጋረጃውንም፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታም፡አድርግ፤ብልኅ፡ሠራተኛ ፡እንደሚሠራ፡ኪሩቤል፡በርሱ፡ላይ፡ይኹኑ።
32፤በወርቅ፡በተለበጡት፡ከግራር፡ዕንጨትም፡በተሠሩት፡በአራቱ፡ምሰሶዎች፡ላይ፡ስቀለው፤ኵላቦቻቸውም፡ከወ ርቅ፥አራቱም፡እግሮቻቸው፡ከብር፡የተሠሩ፡ይኹኑ።
33፤መጋረጃውንም፡ከመያዣዎቹ፡በታች፡ታንጠለጥለዋለኽ፥በመጋረጃውም፡ውስጥ፡የምስክርን፡ታቦት፡አግባው፤መ ጋረጃውም፡በቅድስቱና፡በቅድስተ፡ቅዱሳኑ፡መካከል፡መለያ፡ይኹናችኹ።
34፤በቅድስተ፡ቅዱሳኑም፡ውስጥ፡የስርየት፡መክደኛውን፡በምስክሩ፡ታቦት፡ላይ፡አድርግ።
35፤ገበታውንም፡በመጋረጃው፡ውጭ፥መቅረዙንም፡በገበታው፡ፊት፡ለፊት፡በማደሪያው፡በደቡብ፡ወገን፡አድርግ፤ ገበታውንም፡በሰሜን፡ወገን፡አድርገው።
36፤ለድንኳኑም፡ደጃፍ፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታም፡በጥልፍ፡አሠራር፡ የተሠራ፡መጋረጃ፡አድርግለት።
37፤ለመጋረጃውም፡ዐምስት፡ምሰሶዎች፡ከግራር፡ዕንጨት፡አድርግ፥በወርቅም፡ለብጣቸው፤ኵላቦቻቸውም፡ከወርቅ ፡የተሠሩ፡ይኹኑ፤ዐምስትም፡እግሮች፡አድርግላቸው።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤ርዝመቱ፡ዐምስት፡ክንድ፥ወርዱም፡ዐምስት፡ክንድ፡መሠዊያ፡ከግራር፡ዕንጨት፡አድርግ፤አራት፡ማእዘንም፡ ይኹን፤ከፍታውም፡ሦስት፡ክንድ፡ይኹን።
2፤በአራቱም፡ማእዘን፡ቀንዶችን፡ታደርጋለኽ፥ቀንዶቹም፡ከርሱ፡ጋራ፡ባንድ፡የተሠሩ፡ይኹኑ፤በናስም፡ለብጠ ው።
3፤ዐመድ፡የሚኾንባቸውን፡ምንቸቶች፥መጫሪያዎቹንም፥ድስቶቹንም፥ሜንጦቹንም፥ማንደጃዎቹንም፡አድርግ፤ዕቃ ውንም፡ዅሉ፡ከናስ፡አድርግ።
4፤እንደ፡መረብ፡ኾኖ፡የተሠራ፡የናስ፡መከታ፡አድርግለት፤ለመከታውም፡አራት፡የናስ፡ቀለበት፡በአራት፡ማእ ዘኑ፡አድርግለት።
5፤መከታውም፡እስከመሠዊያው፡እኩሌታ፡ይደርስ፡ዘንድ፡በመሠዊያው፡በሚዞረው፡በዕርከኑ፡ታች፡አድርገው።
6፤ለመሠዊያውም፡ከግራር፡ዕንጨት፡መሎጊያዎችን፡ሠርተኽ፡በናስ፡ለብጣቸው።
7፤መሎጊያዎቹም፡በቀለበቶች፡ውስጥ፡ይግቡ፤መሠዊያውንም፡ስትሸከሙ፡መሎጊያዎቹ፡በኹለቱ፡ወገኖች፡ይኹኑ።
8፤ከሳንቃዎች፡ሠርተኽ፡ባዶ፡አድርገው፤በተራራው፡እንዳሳየኹኽ፡ምሳሌ፡እንዲሁ፡ያድርጉት።
9፤የማደሪያውንም፡አደባባይ፡ሥራ፤በደቡብ፡ወገን፡የጥሩ፡በፍታ፡መጋረጃዎች፡ይኹኑለት፥የአንዱም፡ወገን፡ ርዝመት፡መቶ፡ክንድ፡ይኹን፤
10፤ከናስ፡የተሠሩ፡ኻያ፡ምሰሶዎችና፡ኻያ፡እግሮች፡ይኹኑለት፤የምሰሶዎቹም፡ኵላቦችና፡ዘንጎች፡የብር፡ይኹ ኑ።
11፤እንዲሁም፡በሰሜን፡ወገን፡መቶ፡ክንድ፡ርዝመት፡ያላቸው፡መጋረጃዎች፥ከናስ፡የተሠሩ፡ኻያ፡ምሶሶች፡ኻያ ም፡እግሮች፡ይኹኑ፤ለምሰሶዎችም፡የብር፡ኵላቦችና፡ዘንጎች፡ይኹኑ።
12፤በምዕራብም፡ወገን፡ለአደባባዩ፡ስፋት፡ዐምሳ፡ክንድ፡ርዝመት፡ያላቸው፡መጋረጃዎች፥ዐሥርም፡ምሰሶዎች፥ ዐሥርም፡እግሮች፡ይኹኑለት።
13፤በምሥራቅም፡ወገን፡የአደባባዩ፡ስፋት፡ዐምሳ፡ክንድ፡ይኹን።
14፤ባንድ፡ወገን፡የመጋረጃዎቹ፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ክንድ፡ይኹን፤ምሰሶዎቹም፡ሦስት፥እግሮቹም፡ሦስት ፡ይኹኑ።
15፤በሌላውም፡ወገን፡የመጋረጃዎች፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ክንድ፡ይኾናል፤ምሰሶዎቹም፡ሦስት፥እግሮቹም፡ ሦስት፡ይኹኑ።
16፤ለአደባባዩም፡ደጅ፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ከጥሩ፡በፍታም፡በጥልፍ፡አሠራር፡የተሠራ፡ኻ ያ፡ክንድ፡መጋረጃ፡ይኾናል፤ምሰሶዎቹም፡አራት፥እግሮቹም፡አራት፡ይኹኑ።
17፤በአደባባዩም፡ዙሪያ፡ላሉት፡ምሰሶዎች፡ዅሉ፡የብር፡ዘንጎች፥የብርም፡ኵላቦች፥የናስም፡እግሮች፡ይኹኑላ ቸው።
18፤የአደባባዩ፡ርዝመት፡መቶ፡ክንድ፡ስፋቱም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ይኹን፥የመጋረጃውም፡ከፍታ፡ዐምስት፡ክንድ፡ይ ኹን፤መጋረጃውም፡ከጥሩ፡በፍታ፥እግሮቹም፡ከናስ፡የተሠሩ፡ይኹኑ።
19፤ለማገልገል፡ዅሉ፡የማደሪያው፡ዕቃ፡ዅሉ፥ካስማዎቹም፡ዅሉ፡የአደባባዩም፡ካስማዎች፡ዅሉ፥የናስ፡ይኹኑ።
20፤አንተም፡መብራቱን፡ዅል፡ጊዜ፡ያበሩት፡ዘንድ፡ለመብራት፡ተወቅጦ፡የተጠለለ፡ጥሩ፡የወይራ፡ዘይት፡እንዲ ያመጡልኽ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡እዘዛቸው።
21፤በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡በምስክሩ፡ታቦት፡ፊት፡ባለው፡መጋረጃ፡ውጭ፡አሮንና፡ልጆቹ፡ከማታ፡እስከ፡ ማለዳ፡ድረስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንዲበራ፡ያሰናዱት፤በእስራኤል፡ልጆች፡ዘንድ፡ለልጅ፡ልጃቸው፡የዘለዓ ለም፡ሥርዐት፡ይኹን።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤አንተም፡ወንድምኽን፡አሮንን፡ከርሱም፡ጋራ፡ልጆቹን፡ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ለይተኽ፡ካህናት፡ይኾ ኑልኝ፡ዘንድ፡ወዳንተ፡አቅርብ፤አሮንን፡የአሮንንም፡ልጆች፥ናዳብን፡አብዮድንም፡አልዓዛርንም፡ኢታምርንም ፥አቅርብ።
2፤የተቀደሰውንም፡ልብስ፡ለክብርና፡ለጌጥ፡እንዲኾን፡ለወንድምኽ፡ለአሮን፡ሥራለት።
3፤አንተም፡ካህን፡ኾኖ፡እንዲያገለግለኝ፡አሮን፡ቅዱስ፡ይኾን፡ዘንድ፡ልብስ፡እንዲሠሩለት፡የጥበብ፡መንፈ ስ፡ለሞላኹባቸው፡በልባቸው፡ጥበበኛዎች፡ለኾኑት፡ዅሉ፡ተናገር።
4፤የሚሠሯቸውም፡ልብሶች፡እነዚህ፡ናቸው፤የደረት፡ኪስ፡ኤፉድም፡ቀሚስም፡ዝንጕርጕር፡የደረት፡ልብስም፡መ ጠምጠሚያም፡መታጠቂያም፤እነዚህም፡ካህናት፡ይኾኑልኝ፡ዘንድ፡ለወንድምኽ፡ለአሮን፡ለልጆቹም፡የተቀደሰ፡ል ብስ፡ያድርጉ።
5፤ወርቅንም፥ሰማያዊና፡ሐምራዊ፡ቀይም፡ግምጃ፥ጥሩ፡በፍታም፡ይውሰዱ።
6፤ኤፉዱንም፡በብልኀት፡የተሠራ፡በወርቅና፡በሰማያዊ፡በሐምራዊም፡በቀይም፡ግምጃ፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታ ም፡ብልኅ፡ሠራተኛ፡እንደሚሠራ፡ያድርጉ።
7፤ኹለቱ፡ወገን፡አንድ፡እንዲኾን፡በኹለቱ፡ጫንቃ፡ላይ፡የሚጋጠም፡ጨርቅ፡ይኹን።
8፤በላዩም፡መታጠቂያ፡ኾኖ፡በብልኀት፡የተጠለፈው፡የኤፉድ፡ቋድ፡እንደ፡ርሱ፡ከርሱም፡ጋራ፡አንድ፡ይኹን፤ ከወርቅና፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊ፡ከቀይ፡ግምጃም፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታም፡የተሠራ፡ይኹን።
9፤ኹለትም፡የመረግድ፡ድንጋይ፡ወስደኽ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ስም፡ስማቸውን፡ቅረጽባቸው፤
10፤እንደ፡አወላለዳቸው፡ስድስት፡ስም፡ባንድ፡ድንጋይ፥የቀረውንም፡ስድስቱን፡ስም፡በሌላው፡ቅረጽ።
11፤በቅርጽ፡ሠራተኛ፡ሥራ፡እንደ፡ማኅተም፡ቅርጽ፡አድርገኽ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ስም፡በኹለት፡ድንጋዮች፡ ቅረጽ፡በወርቅም፡ፈርጥ፡አድርግ።
12፤የእስራኤል፡ልጆችም፡የመታሰቢያ፡ድንጋዮች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ኹለቱን፡ዕንቍዎች፡በኤፉዱ፡ጫንቃዎች፡ላይ፡ ታደርጋለኽ፤አሮንም፡በኹለቱ፡ጫንቃዎች፡ላይ፡ለመታሰቢያ፡ስማቸውን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይሸከማል።
13፤14፤የወርቅም፡ፈርጦች፡ኹለትም፡ድሪዎች፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሥራ፤እንደ፡ተጐነጐነም፡ገመድ፡አድርግ፤የተጐ ነጐኑትንም፡ድሪዎች፡በፈርጦቹ፡ላይ፡አንጠልጥል።
15፤ብልኅ፡ሠራተኛም፡እንደሚሠራ፡የፍርዱን፡የደረት፡ኪስ፡ሥራው፡እንደ፡ኤፉዱም፡አሠራር፡ሥራው፤ከወርቅና ፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ከጥሩ፡በፍታም፡ሥራው።
16፤ርዝመቱ፡ስንዝር፡ስፋቱም፡ስንዝር፡ኾኖ፡ትክክልና፡ድርብ፡ይኾናል።
17፤በአራት፡ተራ፡የኾነ፡የዕንቍ፡ፈርጥ፡አድርግበት፤በፊተኛው፡ተራ፡ሰርድዮን፥ቶጳዝዮን፥የሚያብረቀርቅ፡ ዕንቍ፤
18፤በኹለተኛውም፡ተራ፡በሉር፥ሰንፔር፥አልማዝ፤
19፤በሦስተኛውም፡ተራ፡ያክንት፥ኬልቄዶን፥አሜቴስጢኖስ፤
20፤በአራተኛውም፡ተራ፡ቢረሌ፥መረግድ፥ኢያስጲድ፡በወርቅ፡ፈርጥ፡ይደረጋሉ።
21፤የዕንቍዎቹም፡ድንጋዮች፡እንደ፡እስራኤል፡ልጆች፡ስሞች፡ዐሥራ፡ኹለት፡ይኾናሉ፤በየስማቸውም፡ማተሚያ፡ እንደሚቀረጽ፡ይቀረጹ፤ስለ፡ዐሥራ፡ኹለቱ፡ነገዶችም፡ይኹኑ።
22፤ለደረቱ፡ኪስም፡የተጐነጐኑትን፡ድሪዎች፡እንደ፡ገመድ፡አድርገኽ፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሥራቸው።
23፤ለደረቱ፡ኪስም፡ኹለት፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሥራ፥ኹለቱንም፡ቀለበቶች፡በደረቱ፡ኪስ፡በኹለቱ፡ወገን፡አድ ርጋቸው።
24፤የተጐነጐኑትንም፡ኹለቱን፡የወርቅ፡ድሪዎች፡በደረቱ፡ኪስ፡ወገኖች፡ወዳሉት፡ወደ፡ኹለቱ፡ቀለበቶች፡ታገ ባቸዋለኽ።
25፤የኹለቱንም፡ድሪዎች፡ጫፎች፡በኹለቱ፡ፈርጦች፡ውስጥ፡አግብተኽ፡በኤፉዱ፡ጫንቃዎች፡ላይ፡በፊታቸው፡ታደ ርጋቸዋለኽ።
26፤ኹለት፡የወርቅ፡ቀለበቶችም፡ሥራ፥እነርሱንም፡በኤፉዱ፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በደረቱ፡ኪስ፡በኹለቱ፡ጫፎች ፡ላይ፡ታደርጋቸዋለኽ።
27፤ደግሞም፡ኹለት፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሥራ፥በኤፉዱም፡ፊት፡ከጫንቃዎች፡በታች፡በብልኀት፡ከተጠለፈ፡ከኤፉ ዱ፡ቋድ፡በላይ፡በመያዣው፡አጠገብ፡ታደርጋቸዋለኽ።
28፤የደረቱም፡ኪስ፡በብልኀት፡ከተጠለፈ፡ከኤፉዱ፡ቋድ፡በላይ፡እንዲኾን፡ከኤፉዱም፡እንዳይለይ፥የደረቱን፡ ኪስ፡ከቀለበቶቹ፡ወደኤፉዱ፡ቀለበቶች፡በሰማያዊ፡ፈትል፡ያስሩታል።
29፤አሮንም፡ወደ፡መቅደስ፡በገባ፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለዘለዓለም፡መታሰቢያ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ስ ሞች፡በፍርዱ፡በደረት፡ኪስ፡ውስጥ፡በልቡ፡ላይ፡ይሸከም።
30፤በፍርዱ፡በደረት፡ኪስም፡ውስጥ፡ኡሪምንና፡ቱሚምን፡ታደርጋለኽ፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡በገባ፡ጊዜ፡በአ ሮን፡ልብ፡ላይ፡ይኾናሉ፤አሮንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዅል፡ጊዜ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ፍርድ፡በልቡ፡ላይ፡ ይሸከማል።
31፤የኤፉዱንም፡ቀሚስ፡ዅሉ፡ሰማያዊ፡አድርገው።
32፤ከላይም፡በመካከል፡ዐንገትጌ፡ይኹንበት፤እንዳይቀደድም፡እንደ፡ጥሩር፡የተሠራ፡ጥልፍ፡በዐንገትጌው፡ዙ ሪያ፡ይኹንበት።
33፤በታችኛውም፡ዘርፍ፡ዙሪያ፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ሮማኖች፡አድርግ፤በዚያም፡መካከል፡በ ዙሪያው፡የወርቅ፡ሻኵራዎች፡አድርግ፤
34፤የወርቅ፡ሻኵራ፡ሮማንም፥ሌላም፡የወርቅ፡ሻኵራ፡ሮማንም፡በቀሚሱ፡ዘርፍ፡ዙሪያውን፡ይኾናሉ።
35፤በማገልገል፡ጊዜም፡በአሮን፡ላይ፡ይኾናል፤ርሱም፡እንዳይሞት፡ወደ፡መቅደሱ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሲገባ ና፡ሲወጣ፡ድምፁ፡ይሰማል።
36፤ከጥሩ፡ወርቅም፡ቅጠል፡የሚመስል፡ምልክት፡ሥራ፥በርሱም፡እንደ፡ማኅተም፡ቅርጽ፡አድርገኽ፦ቅድስና፡ለእ ግዚአብሔር፡የሚል፡ትቀርጽበታለኽ።
37፤በሰማያዊም፡ፈትል፡በመጠምጠሚያው፡ፊት፡ላይ፡ታንጠለጥለዋለኽ።
38፤በአሮንም፡ግንባር፡ላይ፡ይኾናል፥አሮንም፡የእስራኤል፡ልጆች፡በሚያቀርቡትና፡በሚቀድሱት፡በቅዱስ፡ስጦ ታቸው፡ዅሉ፡ላይ፡ያለውን፡ኀጢአት፡ይሸከም፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ሞገስ፡እንዲኾንላቸው፡ቅጠል፡የሚመስለ ው፡ምልክቱ፡ዅል፡ጊዜ፡በግንባሩ፡ላይ፡ይኹን።
39፤ሸሚዙንም፡ከጥሩ፡በፍታ፡ዝንጕርጕር፡አድርገኽ፥መጠምጠሚያውን፡ከበፍታ፡ትሠራለኽ፤በጥልፍ፡አሠራር፡መ ታጠቂያም፡ትሠራለኽ።
40፤ለአሮንም፡ልጆች፡የደረት፡ልብሶችን፡መታጠቂያዎችንም፡ቆቦችንም፡ለክብርና፡ለጌጥ፡ታደርግላቸዋለኽ።
41፤ይህንም፡ዅሉ፡ወንድምኽን፡አሮንን፡ከርሱም፡ጋራ፡ልጆቹን፡ታለብሳቸዋለኽ፤በክህነት፡እንዲያገለግሉኝ፡ ትቀባቸዋለኽ፥ትክናቸዋለኽ፥ትቀድሳቸውማለኽ።
42፤ኀፍረተ፡ሥጋቸውንም፡ይከድኑበት፡ዘንድ፡የበፍታ፡ሱሪ፡ታደርግላቸዋለኽ፤ከወገባቸውም፡እስከ፡ጭናቸው፡ ይደርሳል፤
43፤ኀጢአትም፡እንዳይኾንባቸው፡እንዳይሞቱም፥ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ሲገቡ፡በመቅደሱም፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡ ወደ፡መሠዊያው፡ሲቀርቡ፡በአሮንና፡በልጆቹ፡ላይ፡ይኾናል፤ለርሱ፡ከርሱም፡በዃላ፡ለዘሩ፡ለዘለዓለም፡ሥርዐ ት፡ይኾናል።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤እኔንም፡በክህነት፡እንዲያገለግሉኝ፡ትቀድሳቸው፡ዘንድ፡የምታደርግባቸው፡ነገር፡ይህ፡ነው፤ነውር፡የሌ ለባቸውን፡አንድ፡ወይፈንና፡ኹለት፡አውራ፡በጎች፡ትወስዳለኽ።
2፤ቂጣ፡እንጀራ፥በዘይትም፡የተለወሰ፡የቂጣ፡ዕንጐቻ፥በዘይትም፡የተቀባ፡ሥሥ፡ቂጣ፡ከመልካም፡ስንዴ፡ታደ ርጋለኽ።
3፤ባንድ፡ሌማትም፡ታደርጋቸዋለኽ፤ከወይፈኑና፡ከኹለቱ፡አውራ፡በጎች፡ጋራ፡በሌማቱ፡ታቀርባቸዋለኽ።
4፤አሮንና፡ልጆቹንም፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ታቀርባቸዋለኽ፥በውሃም፡ታጥባቸዋለኽ።
5፤ልብሶችን፡ወስደኽ፡ለአሮን፡የደረት፡ልብስና፡የኤፉድ፡ቀሚስ፡ኤፉድም፡የደረት፡ኪስም፡ታለብሰዋለኽ፥በ ብልኀትም፡በተጠለፈ፡ቋድ፡ታስታጥቀዋለኽ፤
6፤መጠምጠሚያውንም፡በራሱ፡ላይ፡ታደርጋለኽ፥የተቀደሰውንም፡አክሊል፡በመጠምጠሚያው፡ላይ፡ታኖራለኽ።
7፤የቅብዐትንም፡ዘይት፡ወስደኽ፡በራሱ፡ላይ፡ታፈሰ፟ዋለኽ፥ትቀባውማለኽ።
8፤ልጆቹንም፡ታቀርባቸዋለኽ፥የደረት፡ልብሶቹንም፡ታለብሳቸዋለኽ።
9፤አሮንንና፡ልጆቹንም፡በመታጠቂያ፡ታስታጥቃቸዋለኽ፥ቆብንም፡ታለብሳቸዋለኽ፤ለዘለዓለም፡ሥርዐትም፡ክህ ነት፡ይኾንላቸዋል፤እንዲሁም፡አሮንንና፡ልጆቹን፡ትክናቸዋለኽ።
10፤ወይፈኑንም፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡በር፡ፊት፡ታቀርበዋለኽ፤አሮንና፡ልጆቹም፡እጆቻቸውን፡በወይፈኑ፡ራ ስ፡ላይ፡ይጭናሉ።
11፤ወይፈኑንም፡በመገናኛው፡ድንኳን፡በር፡አጠገብ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ታርደዋለኽ።
12፤ከወይፈኑም፡ደም፡ወስደኽ፡በመሠዊያው፡ቀንዶች፡ላይ፡በጣትኽ፡ትረጨዋለኽ፤ደሙንም፡ዅሉ፡ከመሠዊያው፡በ ታች፡ታፈሰ፟ዋለኽ።
13፤የሆድ፡ዕቃውንም፡የሚሸፍነውን፡ስብ፡ዅሉ፡በጕልበቱም፡ላይ፡ያለውን፡መረብ፡ኹለቱንም፡ኵላሊቶች፡በላያ ቸውም፡ያለውን፡ስብ፡ወስደኽ፡በመሠዊያው፡ላይ፡ታቃጥላለኽ።
14፤የወይፈኑን፡ሥጋ፡ግን፥ቍርበቱንም፥ፈርሱንም፡ከሰፈር፡ውጭ፡በእሳት፡ታቃጥለዋለኽ፤የኀጢአት፡መሥዋዕት ፡ነው።
15፤አንደኛውንም፡አውራ፡በግ፡ትወስደዋለኽ፤አሮንና፡ልጆቹም፡በአውራው፡በግ፡ራስ፡ላይ፡እጆቻቸውን፡ይጭና ሉ።
16፤አውራውንም፡በግ፡ታርደዋለኽ፥ደሙንም፡ወስደኽ፡በመሠዊያው፡ላይ፡በዙሪያው፡ትረጨዋለኽ።
17፤አውራውንም፡በግ፡በየብልቱ፡ትቈርጠዋለኽ፥የሆድ፡ዕቃውንና፡እግሮቹንም፡ታጥባለኽ፥ከብልቱና፡ከራሱም፡ ጋራ፡ታኖረዋለኽ።
18፤አውራውንም፡በግ፡በሞላው፡በመሠዊያው፡ላይ፡ታቃጥላለኽ፤ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነው፤ጣፋ ጭ፡ሽቱ፡ነው።ለእግዚአብሔር፡የቀረበ፡የእሳት፡ቍርባን፡ነው።
19፤ኹለተኛውንም፡አውራ፡በግ፡ትወስደዋለኽ፤አሮንና፡ልጆቹም፡እጆቻቸውን፡በአውራው፡በግ፡ራስ፡ላይ፡ይጭና ሉ።
20፤አውራውንም፡በግ፡ታርደዋለኽ፥ደሙንም፡ትወስዳለኽ፥የአሮንንም፡የቀኝ፡ዦሮ፡ጫፍ፥የልጆቹንም፡የቀኝ፡ዦ ሯቸውን፡ጫፍ፥የቀኝ፡እጃቸውንና፡የቀኝ፡እግራቸውን፡አውራ፡ጣት፡ታስነካለኽ፤ደሙንም፡በመሠዊያው፡ላይ፡በ ዙሪያው፡ትረጨዋለኽ።
21፤በመሠዊያውም፡ላይ፡ካለው፡ደም፣ከቅብዐት፡ዘይትም፡ወስደኽ፡በአሮንና፡በልብሱ፡ላይ፥ከርሱም፡ጋራ፡ባሉ ት፡በልጆቹና፡በልብሶቻቸው፡ላይ፡ትረጨዋለኽ፤ርሱም፡ልብሶቹም፥ከርሱም፡ጋራ፡ልጆቹ፡ልብሶቻቸውም፡ይቀደሳ ሉ።
22፤ደግሞም፡የሚካኑበት፡አውራ፡በግ፡ነውና፥የበጉን፡ስብ፥ላቱንም፥የሆድ፡ዕቃውንም፡የሚሸፍነውን፡ስብ፥በ ጕበቱም፡ላይ፡ያለውን፡መረብ፥ኹለቱንም፡ኵላሊቶች፡በላያቸውም፡ያለውን፡ስብ፥የቀኙንም፡ወርች፡ትወስዳለኽ ።
23፤አንድ፡እንጀራ፥አንድም፡የዘይት፡እንጀራ፥አንድም፡ሥሥ፡ቂጣ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በሌማት፡ካለው፡ቂጣ ፡እንጀራ፡ትወስዳለኽ፤
24፤ዅሉንም፡በአሮን፡እጆችና፡በልጆቹ፡እጆች፡ታኖረዋለኽ፤ለሚወዘወዝ፡ቍርባን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ትወዘ ውዘዋለኽ።
25፤ከእጃቸውም፡ትቀበለዋለኽ፥በመሠዊያውም፡ላይ፡ከሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጣፋጭ፡ሽ ቱ፡እንዲኾን፡ታቃጥለዋለኽ፤ርሱ፡ለእግዚአብሔር፡የእሳት፡ቍርባን፡ነው።
26፤ለአሮንም፡ክህነት፡የታረደውን፡በግ፡ፍርምባ፡ወስደኽ፡ለሚወዘወዝ፡ቍርባን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ትወዘ ውዘዋለኽ፤ርሱም፡የአንተ፡ወግ፡ይኾናል።
27፤ከሚካኑበትም፡አውራ፡በግ፡የተወሰደ፡ለአሮንና፡ለልጆቹ፡ወግ፡የሚኾን፡ለመሥዋዕት፡የተወዘወዘውን፡ፍር ምባና፡የተነሣውን፡ወርች፡ትቀድሳለኽ።
28፤ያውም፡የማንሣት፡ቍርባን፡ነውና፥ከእስራኤል፡ልጆች፡ዘንድ፡ለዘለዓለም፡የአሮንና፡የልጆቹ፡ወግ፡ይኹን ፤የእስራኤል፡ልጆች፡የሚያቀርቡት፡የደኅንነት፡መሥዋዕታቸው፡የማንሣት፡ቍርባን፡ይኾናል፤ለእግዚአብሔር፡ የማንሣት፡ቍርባን፡ይኾናል።
29፤የተቀደሰውም፡የአሮን፡ልብስ፡ይቀቡበትና፡ይካኑበት፡ዘንድ፡ከርሱ፡በዃላ፡ለልጆቹ፡ይኹን።
30፤ከልጆቹም፡በርሱ፡ፋንታ፡ካህን፡የሚኾነው፡በመቅደስ፡ለማገልገል፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ሲገባ፡ሰባት፡ ቀን፡ይልበሰው።
31፤የሚካንበትንም፡አውራ፡በግ፡ወስደኽ፡ሥጋውን፡በተቀደሰ፡ስፍራ፡ትቀቅለዋለኽ።
32፤አሮንና፡ልጆቹም፡የአውራውን፡በግ፡ሥጋ፡በሌማትም፡ያለውን፡እንጀራ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡በር፡ይበሉታ ል።
33፤የተካኑና፡የተቀደሱ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ማስተስረያ፡የኾነውን፡ነገር፡ይብሉት፤ሌላ፡ሰው፡ግን፡አይብላው፤የ ተቀደሰ፡ነውና።
34፤የተካኑበትም፡ሥጋ፡ወይም፡እንጀራ፡ተርፎ፡ቢያድር፥የቀረውን፡በእሳት፡ታቃጥለዋለኽ፤የተቀደሰ፡ነውና፥ አይበላም።
35፤እንዳዘዝኹኽም፡ዅሉ፡በአሮንና፡በልጆቹ፡እንዲህ፡አድርግ፤ሰባት፡ቀን፡ትክናቸዋለኽ።
36፤ዕለት፡ዕለትም፡ስለ፡ማስተስረይ፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡ወይፈኑን፡ታቀርባለኽ፤ማስተስረያም፡ባደረግኽ፡ ጊዜ፡መሠዊያውን፡ታነጻዋለኽ፤ቅዱስም፡ይኾን፡ዘንድ፡ትቀባዋለኽ።
37፤ሰባት፡ቀን፡ለመሠዊያው፡ማስተስረያ፡ታደርጋለኽ፥ትቀድሰውማለኽ፤መሠዊያውም፡ቅድስተ፡ቅዱሳን፡ይኾናል ፤መሠዊያውንም፡የሚነካ፡ዅሉ፡ቅዱስ፡ይኾናል።
38፤በመሠዊያውም፡ላይ፡የምታቀርበው፡ይህ፡ነው፤በቀን፡በቀን፡ዘወትር፡ኹለት፡የዓመት፡ጠቦቶች፡ታቀርባለኽ ።
39፤አንዱን፡ጠቦት፡በማለዳ፡ቍርባን፡አድርገኽ፡ታቀርበዋለኽ፤ኹለተኛውንም፡ጠቦት፡በማታ፡ቍርባን፡አድርገ ኽ፡ታቀርበዋለኽ።
40፤ከአንዱ፡ጠቦትም፡ጋራ፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡በኾነ፡ተወቅጦ፡በተጠለለ፡ዘይት፡የተለወሰ፡የኢ ፍ፡መስፈሪያ፡ዐሥረኛ፡እጅ፡መልካም፡ዱቄት፥ደግሞ፡ለመጠጥ፡ቍርባን፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡የወይ ን፡ጠጅ፡ታቀርባለኽ።
41፤ኹለተኛውንም፡ጠቦት፡በማታ፡ታቀርበዋለኽ፥እንደ፡ማለዳውም፡የእኽልና፡የመጠጥ፡ቍርባን፡ታደርግበታለኽ ፤ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽቱ፡እንዲኾን፡የእሳት፡ቍርባን፡ይኾናል።
42፤ለአንተ፡እናገር፡ዘንድ፡ከእናንተ፡ጋራ፡በምገናኝበት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፥በእግዚአብሔር፡ፊት ፡ይህ፡ዘወትር፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ይኾናል።
43፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ጋራ፡በዚያ፡እገናኛለኹ፤ድንኳኑም፡በክብሬ፡ይቀደሳል።
44፤የመገናኛውንም፡ድንኳን፡መሠዊያውንም፡እቀድሳለኹ፤በክህነትም፡ያገለግሉኝ፡ዘንድ፡አሮንንና፡ልጆቹን፡ እቀድሳለኹ።
45፤በእስራኤልም፡ልጆች፡መካከል፡እኖራለኹ፥አምላክም፡እኾናቸዋለኹ።
46፤በመካከላቸውም፡እኖር፡ዘንድ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣዃቸው፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡እኔ፡እንደ፡ኾንኹ ፡ያውቃሉ፤እኔ፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤የዕጣን፡መሠዊያውን፡ሥራ፤ከግራር፡ዕንጨት፡አድርገው።
2፤ርዝመቱ፡አንድ፡ክንድ፥ስፋቱም፡አንድ፡ክንድ፥አራት፡ማእዘን፡ይኹን፤ከፍታውም፡ኹለት፡ክንድ፡ይኾናል፤ ቀንዶቹም፡ከርሱ፡ጋራ፡በአንድነት፡የተሠሩ፡ይኹኑ።
3፤ላይኛውንና፡የግድግዳውንም፡ዙሪያ፡ቀንዶቹንም፡በጥሩ፡ወርቅ፡ትለብጠዋለኽ፤በዙሪያውም፡የወርቅ፡ክፈፍ ፡ታደርግለታለኽ።
4፤ከክፈፉም፡በታች፡ኹለት፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡አድርግለት።በዚህና፡በዚያ፡በኹለቱ፡ጐን፡ታደርጋቸዋለኽ፤ ለመሸከምም፡የመሎጊያዎች፡ስፍራ፡ይኹኑ።
5፤መሎጊያዎቹንም፡ከግራር፡ዕንጨት፡አድርግ፥በወርቅም፡ለብጣቸው።
6፤በምስክሩ፡ታቦት፡አጠገብም፡ካለው፡መጋረጃ፡በፊት፡ታኖረዋለኽ፡ይህንም፡አንተን፡በምገናኝበት፡ከምስክ ሩ፡በላይ፡ባለው፡በስርየት፡መክደኛ፡ፊት፡ታኖረዋለኽ።
7፤አሮንም፡የጣፋጭ፡ሽቱ፡ዕጣን፡ይጠንበት፤በማለዳ፡በማለዳ፡መብራቶቹን፡ሲያዘጋጅ፡ይጠነው።
8፤ይህን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡የዘወትር፡ዕጣን፡ይኾን፡ዘንድ፡አሮን፡በማታ፡ጊዜ፡መብራቶ ቹን፡ሲያበራ፡ያጥነዋል።
9፤ሌላም፡ዕጣን፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፥የእኽሉንም፡ቍርባን፡አታቀርብበትም፤የመጠጥም፡ቍርባን፡አታፈ ስ፟በትም።
10፤አሮንም፡በዓመት፡አንድ፡ጊዜ፡በቀንዶቹ፡ላይ፡ማስተስረያ፡ያደርጋል፤በዓመት፡አንድ፡ጊዜ፡ለልጅ፡ልጃች ኹ፡ማስተስረያ፡በሚኾን፡በኀጢአት፡መሥዋዕት፡ደም፡ማስተስረያ፡ያደርግበታል።ለእግዚአብሔር፡ቅድስተ፡ቅዱ ሳን፡ናት።
11፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
12፤አንተ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ቍጥር፡ተቀብለኽ፥በቈጠርኻቸው፡ጊዜ፡መቅሠፍት፡እንዳይኾንባቸው፥በቈጠርኻ ቸው፡ጊዜ፡ከነርሱ፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡ቍጥራቸው፡መጠን፡የነፍሱን፡ቤዛ፡ለእግዚአብሔር፡ይስጥ።
13፤ዐልፎ፡የሚቈጠር፡ዅሉ፡ግማሽ፡ሰቅል፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፡ይሰጣል፤የሰቅል፡ግማሽ፡ለእግዚአብ ሔር፡ያነሣል።
14፤ሰቅሉ፡ኻያ፡ኦቦሊ፡ነው።ዐልፎ፡የተቈጠረ፡ዅሉ፥ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡ከፍ፡ያለ፥የእግዚአብሔር ን፡ስጦታ፡ይሰጣል።
15፤ለነፍሳችኹ፡ማስተስረያ፡የእግዚአብሔርን፡ስጦታ፡ስትሰጡ፡ባለጠጋው፡ከሰቅል፡ግማሽ፡አይጨምር፥ድኻውም ፡አያጕድል።
16፤የማስተስረያውንም፡ገንዘብ፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ወስደኽ፡ለመገናኛው፡ድንኳን፡ማገልገያ፡ታደርገዋለኽ፤ በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ለነፍሳችኹ፡ቤዛ፡እንዲኾን፡ለእስራኤል፡ልጆች፡መታሰቢያ፡ይኹን።
17፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
18፤የመታጠቢያ፡ሰንና፡መቀመጫውን፡ከናስ፡ሥራ፤በመገናኛው፡ድንኳንና፡በመሠዊያው፡መካከል፡ርሱን፡አድርገ ኽ፡ውሃን፡ትጨምርበታለኽ።
19፤አሮንና፡ልጆቹም፡እጆቻቸውንና፡እግሮቻቸውን፡ይታጠቡበታል።
20፤ወደመገናኛው፡ድንኳን፡በገቡ፡ጊዜ፥ለእግዚአብሔርም፡የእሳት፡መሥዋዕት፡ያቃጥሉ፡ዘንድ፡ወደ፡መሠዊያው ፡ሊያገለግሉ፡በቀረቡ፡ጊዜ፥እንዳይሞቱ፡ይታጠቡበታል።
21፤እንዳይሞቱም፡እጆቻቸውንና፡እግሮቻቸውን፡ይታጠቡ፤ይህም፡ለርሱ፡ከርሱም፡በዃላ፡ለዘሩ፡የዘለዓለም፡ሥ ርዐት፡ይኾንላቸዋል።
22፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
23፤አንተም፡ክቡሩን፡ሽቱ፡ውሰድ፤የተመረጠ፡ከርቤ፡ዐምስት፡መቶ፡ሰቅል፥ግማሽም፡ጣፋጭ፡ቀረፋ፡ኹለት፡መቶ ፡ዐምሳ፡ሰቅል፥የጠጅ፡ሣርም፡እንዲሁ፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰቅል፥
24፤ብርጕድም፡ዐምስት፡መቶ፡ሰቅል፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፥የወይራ፡ዘይትም፡አንድ፡የኢን፡መስፈሪያ ፡ትወስዳለኽ።
25፤በቀማሚም፡ብልኀት፡እንደ፡ተሠራ፡ቅመም፥የተቀደሰ፡የቅብዐት፡ዘይት፡ታደርገዋለኽ፤የተቀደሰ፡የቅብዐት ፡ዘይት፡ይኾናል።
26፤የመገናኛውንም፡ድንኳን፥የምስክሩንም፡ታቦት፥
27፤ገበታውንም፡ዕቃውንም፡ዅሉ፥መቅረዙንም፡ዕቃውንም፥የዕጣን፡መሠዊያውንም፥
28፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡መሠዊያና፡ዕቃውንም፡ዅሉ፥የመታጠቢያውን፡ሰንና፡መቀመጫውንም፡ትቀባ በታለኽ።
29፤ዅሉንም፡ትቀድሳቸዋለኽ፥ቅድስተ፡ቅዱሳንም፡ይኾናሉ፤የሚነካቸውም፡ዅሉ፡ቅዱስ፡ይኾናል።
30፤በክህነትም፡ያገለግሉኝ፡ዘንድ፡አሮንንና፡ልጆቹን፡ቅባቸው፥ቀድሳቸውም።
31፤አንተም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ተናገር፦ይህ፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡የተቀደሰ፡የቅብዐት፡ዘይት፡ ይኹንልኝ።
32፤በሰው፡ሥጋ፡ላይ፡አይፍሰስ፤እንደ፡ርሱም፡የተሠራ፡ሌላ፡ቅብዐት፡አታድርጉ፤ቅዱስ፡ነው፥ለእናንተም፡ቅ ዱስ፡ይኹን።
33፤እንደ፡ርሱ፡ያለውን፡የሚያደርግ፡ሰው፥በሌላም፡ሰው፡ላይ፡የሚያፈሰ፟ው፡ከሕዝቡ፡ተለይቶ፡ይጥፋ።
34፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ጣፋጭ፡ሽቱ፡ውሰድ፤የሚንጠባጠብ፡ሙጫ፥በዛጐል፡ውስጥ፡የሚገኝ፡ሽቱ፥የሚ ሸት፟ም፡ሙጫ፥ጥሩም፡ዕጣን፡ውሰድ፤የዅሉም፡መጠን፡ትክክል፡ይኹን።
35፤በቀማሚ፡ብልኀት፡እንደ፡ተሠራ፥በጨው፡የተቀመመ፡ንጹሕና፡ቅዱስ፡ዕጣን፡አድርገው።
36፤ከርሱም፡ጥቂት፡ትወቅጣለኽ፥ታልመውማለኽ፤ከዚያም፡ወስደኽ፡አንተን፡በምገናኝበት፡በመገናኛው፡ድንኳን ፡ውስጥ፡በምስክሩ፡ፊት፡ታኖረዋለኽ።ርሱም፡የቅዱሳን፡ቅዱስ፡ይኹንላችኹ።
37፤እንደ፡ርሱ፡የተሠራ፡ዕጣን፡ለእናንተ፡አታድርጉ፤በእናንተ፡ዘንድም፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ይኹን።
38፤ሊያሸተ፟ውም፡እንደ፡ርሱ፡የሚያደርግ፡ሰው፡ከሕዝቡ፡ተለይቶ፡ይጥፋ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤እይ፡ከይሁዳ፡ነገድ፡የሚኾን፡የሆር፡የልጅ፡ልጅ፥የኡሪ፡ልጅ፡ባስልኤልን፡በስሙ፡ጠርቼዋለኹ።
3፤በሥራ፡ዅሉ፡ብልኀት፡በጥበብም፡በማስተዋልም፡በዕውቀትም፡የእግዚአብሔርን፡መንፈስ፡ሞላኹበት፤
4፤የጥበብን፡ሥራ፡ያስተውል፡ዘንድ፥በወርቅና፡በብር፡በናስም፡ይሰራ፡ዘንድ፥
5፤ለፈርጥ፡የሚኾነውን፡የዕንቍ፡ድንጋይ፡ይቀርጽ፡ዘንድ፥ዕንጨቱንም፡ይጠርብ፡ዘንድ፥ሥራውንም፡ዅሉ፡ይሠ ራ፡ዘንድ።
6፤እኔም፥እንሆ፥ከርሱ፡ጋራ፡ከዳን፡ነገድ፡የሚኾን፡የአሂሳሚክን፡ልጅ፡ኤልያብን፡ሰጠኹ፤ያዘዝኹኽን፡ዅሉ ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡በልባቸው፡ጥበበኛዎች፡በኾኑት፡ዅሉ፡ጥበብን፡አኖርኹ።
7፤የመገናኛውን፡ድንኳን፥የምስክሩንም፡ታቦት፥በርሱም፡ላይ፡ያለውን፡የስርየት፡መክደኛውን፥የድንኳኑንም ፡ዕቃ፡ዅሉ፥
8፤ገበታውንም፡ዕቃውንም፥ከዕቃው፡ዅሉ፡ጋራ፡የነጻውን፡መቅረዝ፥የዕጣን፡መሠዊያውን፥
9፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነውንም፡መሠዊያ፡ዕቃውንም፡ዅሉ፥የመታጠቢያውን፡ሰንም፡መቀመጫውንም፥በብል ኀት፡የተሠራውንም፡ልብስ፥
10፤በክህነት፡እኔን፡የሚያገለግሉበትን፡የካህኑን፡የአሮንን፡ልብሰ፡ተክህኖና፡የልጆቹን፡ልብስ፥
11፤የቅብዓቱንም፡ዘይት፥ለመቅደሱ፡የሚኾን፡የጣፋጭ፡ሽቱውንም፡ዕጣን፡እንዳዘዝኹኽ፡ዅሉ፡ያድርጉ።
12፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረው፦
13፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦እኔ፡የምቀድሳችኹ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቁ፡ዘ ንድ፡በእኔና፡በእናንተ፡ዘንድ፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡ምልክት፡ነውና፥ሰንበቶቼን፡ፈጽሞ፡ጠብቁ።
14፤ስለዚህ፥ለእናንተ፡ቅዱስ፡ነውና፥ሰንበትን፡ጠብቁ፤የሚያረክሰውም፡ሰው፡ዅሉ፡ፈጽሞ፡ይገደል፥ሥራንም፡ በርሱ፡የሠራ፡ሰው፡ዅሉ፡ከሕዝቡ፡መካከል፡ተለይቶ፡ይጥፋ።
15፤ስድስት፡ቀን፡ሥራን፡ሥራ፤ሰባተኛው፡ቀን፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡የዕረፍት፡ሰንበት፡ነው፤በሰ ንበት፡ቀን፡የሚሠራ፡ዅሉ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
16፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ለልጅ፡ልጃቸው፡ለዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡በሰንበት፡ያርፉ፡ዘንድ፡ሰንበትን፡ይጠብ ቁ።
17፤እግዚአብሔር፡ሰማይንና፡ምድርን፡በስድስት፡ቀን፡ስለ፡ፈጠረ፥በሰባተኛውም፡ቀን፡ከሥራው፡ስላረፈና፡ስ ለ፡ተነፈሰ፥በእኔና፡በእስራኤል፡ልጆች፡ዘንድ፡የዘለዓለም፡ምልክት፡ነው።
18፤እግዚአብሔርም፡ከሙሴ፡ጋራ፡በሲና፡ተራራ፡የተናገረውን፡በፈጸመ፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ጣት፡የተጻፈባቸ ውን፡ከድንጋይ፡የኾኑ፡ኹለቱን፡የምስክር፡ጽላቶች፡ሰጠው።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32።
1፤ሕዝቡም፡ሙሴ፡ከተራራው፡ሳይወርድ፡እንደ፡ዘገየ፡ባዩ፡ጊዜ፥ወደ፡አሮን፡ተሰብስበው፦ይህ፡ከግብጽ፡ምድ ር፡ያወጣን፡ሰው፡ሙሴ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አናውቅምና፡ተነሥተኽ፡በፊታችን፡የሚኼዱ፡አማልክት፡ሥራልን፡አሉ ት።
2፤አሮንም፦በሚስቶቻችኹ፡በወንዶችና፡በሴቶች፡ልጆቻችኹም፡ዦሮ፡ያሉትን፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሰብራችኹ፡አ ምጡልኝ፡አላቸው።
3፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡በዦሮዎቻቸው፡ያሉትን፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሰብረው፡ወደ፡አሮን፡አመጡለት።
4፤ከእጃቸውም፡ተቀብሎ፡በመቅረጫ፡ቀረጸው፥ቀልጦ፡የተሠራ፡ጥጃም፡አደረገው፤ርሱም፦እስራኤል፡ሆይ፥እነዚ ህ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጡኽ፡አማልክትኽ፡ናቸው፡አላቸው።
5፤አሮንም፡ባየው፡ጊዜ፡መሠዊያን፡በፊቱ፡ሠራ፤አሮንም፦ነገ፡የእግዚአብሔር፡በዓል፡ነው፡ሲል፡ዐወጀ።
6፤በነጋውም፡ማልደው፡ተነሥተው፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ሠዉ፥የደኅንነትም፡መሥዋዕት፡አቀረቡ፤ሕዝቡም፡ሊበ ሉና፡ሊጠጡ፡ተቀመጡ፥ሊዘፍኑም፡ተነሡ።
7፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣኸው፡ሕዝብኽ፡ኀጢአት፡ሠርተዋልና፥ኺድ፥ውረድ።
8፤ካዘዝዃቸው፡መንገድ፡ፈጥነው፡ፈቀቅ፡አሉ፤ቀልጦ፡የተሠራ፡የጥጃ፡ምስል፡ለራሳቸው፡አደረጉ፥ሰገዱለትም ፥ሠዉለትም፦እስራኤል፡ሆይ፥እነዚህ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጡኽ፡አማልክትኽ፡ናቸው፡አሉ፡ሲል፡ተናገረው።
9፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦እኔ፡ይህን፡ሕዝብ፡አየኹት፥እንሆም፡ዐንገተ፡ደንዳና፡ሕዝብ፡ነው።
10፤አኹንም፡ቍጣዬ፡እንዲቃጠልባቸው፡እንዳጠፋቸውም፡ተወኝ፤አንተንም፡ለታላቅ፡ሕዝብ፡አደርግኻለኹ፡አለው ።
11፤ሙሴም፡በእግዚአብሔር፡በአምላኩ፡ፊት፡ጸለየ፥አለም፦አቤቱ፥ቍጣኽ፡በታላቅ፡ኀይልና፡በጽኑ፡እጅ፡ከግብ ጽ፡ምድር፡ባወጣኸው፡በሕዝብኽ፡ላይ፡ስለ፡ምን፡ተቃጠለ፧
12፤ግብጻውያንስ፦በተራራ፡መካከል፡ሊገድላቸው፥ከምድርም፡ፊት፡ሊያጠፋቸው፡ለክፋት፡አወጣቸው፡ብለው፡ስለ ፡ምን፡ይናገራሉ፧ከመዓትኽ፡ተመለስ፥ለሕዝብኽም፡በክፋታቸው፡ላይ፡ራራ።
13፤ዘራችኹን፡እንደሰማይ፡ከዋክብት፡አበዛለኹ፥ይህችንም፡የተናገርዃትን፡ምድር፡ዅሉ፡ለዘራችኹ፡እሰጣታለ ኹ፥ለዘለዓለምም፡ይወርሷታል፡ብለኽ፡በራስኽ፡የማልኽላቸውን፡ባሪያዎችኽን፡አብርሃምንና፡ይሥሐቅን፡እስራ ኤልንም፡ዐስብ።
14፤እግዚአብሔርም፡በሕዝቡ፡ላይ፡ሊያደርግ፡ስላሰበው፡ክፋት፡ራራ።
15፤ሙሴም፡ተመለሰ፥ኹለቱንም፡የምስክር፡ጽላቶች፡በእጁ፡ይዞ፡ከተራራው፡ወረደ፤ጽላቶቹም፡በዚህና፡በዚያ፡ በኹለት፡ወገን፡ተጽፎባቸው፡ነበር።
16፤ጽላቶቹም፡የእግዚአብሔር፡ሥራ፡ነበሩ፤ጽሕፈቱም፡በጽላቶች፡ላይ፡የተቀረጸባቸው፡የእግዚአብሔር፡ጽሕፈ ት፡ነበረ።
17፤ኢያሱም፡እልል፡ሲሉ፡የሕዝቡን፡ድምፅ፡ሰምቶ፡ሙሴን፦የሰልፍ፡ድምፅ፡በሰፈሩ፡ውስጥ፡አለ፡አለው።
18፤ርሱም፦ይህ፡የድል፡ነሺዎች፡ወይም፡የድል፡ተነሺዎች፡ድምፅ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥የዘፈን፡ድምፅ፡እሰ ማለኹ፡አለው።
19፤እንዲህም፡ኾነ፤ወደ፡ሰፈሩ፡ሲቀርብ፡ጥጃውንም፡ዘፈኑንም፡አየ፤የሙሴም፡ቍጣ፡ተቃጠለ፥ጽላቶቹንም፡ከእ ጁ፡ጥሎ፡ከተራራው፡በታች፡ሰበራቸው።
20፤የሠሩትንም፡ጥጃ፡ወስዶ፡በእሳት፡አቀለጠው፥እንደ፡ትቢያም፡እስኪኾን፡ድረስ፡ፈጨው፥በውሃውም፡ላይ፡በ ተነው፥ለእስራኤልም፡ልጆች፡አጠጣው።
21፤ሙሴም፡አሮንን፦ይህን፡ታላቅ፡ኀጢአት፡ታመጣበት፡ዘንድ፡ይህ፡ሕዝብ፡ምን፡አደረገኽ፧አለው።
22፤አሮንም፡እንዲህ፡አለ፦ጌታዬ፡ሆይ፥ቍጣኽ፡አይቃጠል፤ይህ፡ሕዝብ፡ክፋትን፡እንዲወድ፟፡አንተ፡ታውቃለኽ ።
23፤እነርሱም፦ይህ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣን፡ሰው፡ሙሴ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አናውቅምና፡በፊታችን፡የሚኼዱ፡አ ማልክት፡ሥራልን፡አሉኝ።
24፤እኔም፦ከእናንተ፡ወርቅ፡ያለው፡ሰው፡ከርሱ፡ሰብሮ፡ያምጣልኝ፡አልዃቸው፤ሰጡኝም፤በእሳትም፡ላይ፡ጣልኹ ት፥ይህም፡ጥጃ፡ወጣ።
25፤ሙሴም፡በጠላቶቻቸው፡ፊት፡እንዲነወሩ፡አሮን፡ስድ፡ለቋ፟ቸዋልና፥ሕዝቡ፡ስድ፡እንደ፡ተለቀቁ፡ባየ፡ጊዜ ፥
26፤በሰፈሩ፡ደጅ፡ቆሞ፦የእግዚአብሔር፡ወገን፡የኾነ፡ወደ፡እኔ፡ይምጣ!  አለ፤የሌዊም፡ልጆች፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ።
27፤ርሱም፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእናንተ፡ሰው፡ዅሉ፡ሰይፉን፡በወገቡ፡ላይ፡ ይታጠቅ፥በሰፈሩም፡ውስጥ፡በዚህና፡በዚያ፡ከበር፡እስከ፡በር፡ተመላለሱ፥የእናንተም፡ሰው፡ዅሉ፡ወንድሙን፡ ወዳጁንም፡ጎረቤቱንም፡ይግደል፡አላቸው።
28፤የሌዊም፡ልጆች፡ሙሴ፡እንዳለ፡አደረጉ፤በዚያም፡ቀን፡ከሕዝቡ፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ሞቱ።
29፤ሙሴም፦ዛሬ፡በረከትን፡እንዲያወርድላችኹ፡እያንዳንዳችኹ፡በልጃችኹና፡በወንድማችኹ፡ላይ፡ዛሬ፡እጃችኹ ን፡ለእግዚአብሔር፡ቅዱስ፡አድርጉ፡አለ።
30፤በነጋውም፡ሙሴ፡ለሕዝቡ፦እናንተ፡ታላቅ፡ኀጢአት፡ሠርታችዃል፤አኹንም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እወጣለኹ፤ም ናልባት፡ኀጢአታችኹን፡አስተሰርይላችዃለኹ፡አላቸው።
31፤ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ተመልሶ፦ወዮ! እኒህ፡ሕዝብ፡ታላቅ፡ኀጢአት፡ሠርተዋል፥ለራሳቸውም፡የወርቅ፡አማልክት፡አድርገዋል፤
32፤አኹን፡ይህን፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡በላቸው፤ያለዚያ፡ግን፡ከጻፍኸው፡መጽሐፍኽ፡እባክኽ፡ደምሰ፟ኝ፡አለ ።
33፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦የበደለኝን፡ርሱን፡ከመጽሐፌ፡እደመስሰዋለኹ።
34፤አኹንም፡ኺድ፥ይህንም፡ሕዝብ፡ወደነገርኹኽ፡ምራ፤እንሆ፥መልአኬ፡በፊትኽ፡ይኼዳል፤ነገር፡ግን፥በምጐበ ኝበት፡ቀን፡ኀጢአታቸውን፡አመጣባቸዋለኹ፡አለው።
35፤አሮን፡የሠራውን፡ጥጃ፡ስለ፡ሠሩ፡እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡ቀሠፈ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33።
1፤2፤3፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦ኺድ፥ለአብርሃምና፡ለይሥሐቅ፡ለያዕቆብም፦ለዘርኽ ፡እሰጣታለኹ፡ብዬ፡ወደማልኹባት፡ምድር፥ወተትና፡ማርም፡ወደምታፈሰ፟ው፡ምድር፡አንተ፡ከግብጽ፡ምድር፡ካወ ጣኸው፡ሕዝብ፡ጋራ፡ከዚህም፡ውጣ።ዐንገተ፡ደንዳና፡ሕዝብ፡ስለ፡ኾንኽ፡በመንገድ፡ላይ፡እንዳላጠፋኽ፡እኔ፡ ባንተ፡መካከል፡አልወጣምና፡በፊትኽ፡መልአክ፡እሰዳ፟ለኹ፤ከነዓናዊውን፡አሞራዊውንም፡ኬጢያዊውንም፡ፌርዛ ዊውንም፡ዔዊያዊውንም፡ኢያቡሳዊውንም፡አወጣልኻለኹ።
4፤ሕዝቡም፡ይህን፡ክፉ፡ወሬ፡ሰምተው፡ዐዘኑ፤ከነርሱም፡ማንም፡ጌጡን፡አልለበሰም።
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ለእስራኤል፡ልጆች፦እናንተ፡ዐንገተ፡ደንዳና፡ሕዝብ፡ናችኹ፥አንድ፡ጊዜ፡በእናን ተ፡መካከል፡ብወጣ፡አጠፋችዃለኹ፤አኹንም፡የማደርግባችኹን፡ዐውቅ፡ዘንድ፡ጌጣችኹን፡ከእናንተ፡አውጡ፡በላ ቸው፡አለው።
6፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከኰሬብ፡ተራራ፡ዠምረው፡ጌጣቸውን፡አወጡ።
7፤ሙሴም፡ድንኳኑን፡እየወሰደ፡ከሰፈር፡ውጭ፡ይተክለው፡ነበር፤ከሰፈሩም፡ራቅ፡ያደርገው፡ነበር፤የመገናኛ ውም፡ድንኳን፡ብሎ፡ጠራው።እግዚአብሔርንም፡የፈለገ፡ዅሉ፡ከሰፈር፡ውጭ፡ወዳለው፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ይ ወጣ፡ነበር።
8፤ሙሴም፡ወደ፡ድንኳኑ፡በኼደ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ይነሡ፡ነበር፥እያንዳንዱም፡በድንኳኑ፡ደጃፍ፡ይቆም፡ነበ ር፥ሙሴም፡ወደ፡ድንኳኑ፡እስኪገባ፡ድረስ፡ይመለከቱት፡ነበር።
9፤ሙሴም፡ወደ፡ድንኳኑ፡በገባ፡ጊዜ፡የደመና፡ዐምድ፡ይወርድ፡ነበር፥በድንኳኑም፡ደጃፍ፡ይቆም፡ነበር፤እግ ዚአብሔርም፡ሙሴን፡ይናገረው፡ነበር።
10፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡የደመናው፡ዐምድ፡በድንኳኑ፡ደጃፍ፡ሲቆም፡ያየው፡ነበር፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ተነሥቶ፡እያንዳን ዱ፡በድንኳኑ፡ደጃፍ፡ይሰግድ፡ነበር።
11፤እግዚአብሔርም፡ሰው፡ከባልንጀራው፡ጋራ፡እንደሚነጋገር፡ፊት፡ለፊት፡ከሙሴ፡ጋራ፡ይነጋገር፡ነበር።ሙሴ ም፡ወደ፡ሰፈሩ፡ይመለስ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥ሎሌው፡ብላቴና፡የነዌ፡ልጅ፡ኢያሱ፡ከድንኳኑ፡አይለይም፡ነበር ።
12፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፦እንሆ፥አንተ፦ይህን፡ሕዝብ፡አውጣ፡ትለኛለኽ፤ከእኔም፡ጋራ፡የምትልከውን፡አላስ ታወቅኸኝም።አንተም፦በስምኽ፡ዐወቅኹኽ፥ደግሞም፡በእኔ፡ፊት፡ሞገስን፡አገኘኽ፡አልኸኝ።
13፤አኹንም፡በፊትኽ፡ሞገስን፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፥ዐውቅኽ፡ዘንድ፡በፊትኽም፡ሞገስን፡አገኝ፡ዘንድ፡መንገ ድኽን፡እባክኽ፡አሳየኝ፤ይህም፡ሕዝብ፡ሕዝብኽ፡እንደ፡ኾነ፡ተመልከት፡አለው።
14፤እግዚአብሔርም፦እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡እኼዳለኹ፥አሳርፍኽማለኹ፡አለው።
15፤ርሱም፦አንተ፡ከእኛ፡ጋራ፡ካልወጣኽስ፥ከዚህ፡አታውጣን።
16፤በምድርም፡ፊት፡ካለው፡ሕዝብ፡ዅሉ፡እኔና፡ሕዝብኽ፡የተለየን፡እንኾን፡ዘንድ፡አንተ፡ከእኛ፡ጋራ፡ካልወ ጣኽ፥እኔና፡ሕዝብኽ፡ባንተ፡ዘንድ፡ሞገስ፡ማግኘታችን፡በምን፡ይታወቃል፧አለው።
17፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በፊቴ፡ሞገስ፡ስላገኘኽ፡በስምኽም፡ስላወቅኹኽ፡ይህን፡ያልኸውን፡ነገር፡አደርጋ ለኹ፡አለው።
18፤ርሱም፦እባክኽ፡ክብርኽን፡አሳየኝ፡አለ።
19፤እግዚአብሔርም፦እኔ፡መልካምነቴን፡ዅሉ፡በፊትኽ፡አሳልፋለኹ፤የእግዚአብሔርንም፡ስም፡በፊትኽ፡ዐውጃለ ኹ፤ይቅርም፡የምለውን፡ይቅር፡እላለኹ፥የምምረውንም፡እምራለኹ፡አለ።
20፤ደግሞም፦ሰው፡አይቶኝ፡አይድንምና፡ፊቴን፡ማየት፡አይቻልኽም፡አለ።
21፤እግዚአብሔርም፡አለ፦እንሆ፥ስፍራ፡በእኔ፡ዘንድ፡አለ፥በአለቱም፡ላይ፡ትቆማለኽ፤
22፤ክብሬም፡ባለፈ፡ጊዜ፡በሰንጣቃው፡አለት፡አኖርኻለኹ፥እስካልፍ፡ድረስ፡እጄን፡በላይኽ፡እጋርዳለኹ፤
23፤እጄንም፡ፈቀቅ፡አደርጋለኹ፥ዠርባዬንም፡ታያለኽ፤ፊቴ፡ግን፡አይታይም።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ኹለት፡የድንጋይ፡ጽላቶች፡እንደ፡ፊተኛዎች፡አድርገኽ፡ጥረብ፤በሰበርኻቸ ው፡በፊተኛዎቹ፡ጽላቶች፡የነበሩትን፡ቃሎች፡እጽፍባቸዋለኹ።
2፤ነገም፡የተዘጋጀኽ፡ኹን፥በማለዳም፡ወደሲና፡ተራራ፡ወጥተኽ፡በዚያ፡በተራራው፡ራስ፡ላይ፡በፊቴ፡ቁም።
3፤ከአንተም፡ጋራ፡ማንም፡ሰው፡አይውጣ፥በተራራውም፡ዅሉ፡ማንም፡አይታይ፤መንጋዎችና፡ከብቶችም፡በዚያ፡ተ ራራ፡ፊት፡አይሰማሩ።
4፤ሙሴም፡እንደ፡ፊተኛዎቹ፡አድርጎ፡ኹለት፡የድንጋይ፡ጽላቶች፡ጠረበ፤በነጋውም፡ማልዶ፡እግዚአብሔር፡እን ዳዘዘው፡ወደሲና፡ተራራ፡ወጣ፥ኹለቱንም፡የድንጋይ፡ጽላቶች፡በእጁ፡ወሰደ፥
5፤እግዚአብሔርም፡በደመናው፡ውስጥ፡ወረደ፥በዚያም፡ከርሱ፡ጋራ፡ቆመ፥የእግዚአብሔርንም፡ስም፡ዐወጀ።
6፤እግዚአብሔርም፡በፊቱ፡ዐልፎ፦እግዚአብሔር፥እግዚአብሔር፡መሓሪ፥ሞገስ፡ያለው፥ታጋሽም፥ባለብዙ፡ቸርነ ትና፡እውነት፥
7፤እስከ፡ሺሕ፡ትውልድም፡ቸርነትን፡የሚጠብቅ፥አበሳንና፡መተላለፍን፡ኀጢአትንም፡ይቅር፡የሚል፥በደለኛው ንም፡ከቶ፡የማያነጻ፥የአባቶችንም፡ኀጢአት፡በልጆች፡እስከ፡ሦስትና፡እስከ፡አራት፡ትውልድም፡በልጅ፡ልጆች ፡የሚያመጣ፡አምላክ፡ነው፡ሲል፡ዐወጀ።
8፤ሙሴም፡ፈጥኖ፡ወደ፡መሬት፡ተጐነበሰና፡ሰገደ።
9፤አቤቱ፡በፊትኽስ፡ሞገስን፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፥ይህ፡ዐንገተ፡ደንዳና፡ሕዝብ፡ነውና፥ጌታዬ፡በመካከላች ን፡ይኺድ፤ጠማማነታችንንና፡ኀጢአታችንንም፡ይቅር፡በለን፥ለርስትኽም፡ተቀበለን፡አለ።
10፤ርሱም፡አለው፦እንሆ፥እኔ፡ቃል፡ኪዳን፡አደርጋለኹ፤በምድር፡ዅሉ፥በአሕዛብም፡ዅሉ፡ዘንድ፡እንደ፡ርሱ፡ ያለ፡ከቶ፡ያልተደረገውን፡ተኣምራት፡በሕዝብኽ፡ዅሉ፡ፊት፡አደርጋለኹ፤እኔም፡ባንተ፡ዘንድ፡የምሠራው፡ነገ ር፡የሚያስፈራ፡ነውና፥አንተ፡ያለኽበት፡ይህ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡ያያል።
11፤በዚህ፡ቀን፡የማዝ፟ኽን፡ነገር፡ጠብቅ፤እንሆ፥እኔ፡አሞራዊውን፡ከነዓናዊውንም፡ኬጢያዊውንም፡ፌርዛዊው ንም፡ዔዊያዊውንም፡ኢያቡሳዊውንም፡በፊትኽ፡አወጣለኹ።
12፤በመካከልኽ፡ወጥመድ፡እንዳይኾኑብኽ፡አንተ፡በምትኼድባት፡ምድር፡ከሚኖሩ፡ሰዎች፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡እን ዳታደርግ፡ተጠንቀቅ፤
13፤ነገር፡ግን፥መሠዊያዎቻቸውን፡ታፈርሳላችኹ፥ሐውልቶቻቸውንም፡ትሰብራላችኹ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቻቸውንም ፡ትቈርጣላችኹ፤
14፤ስሙ፡ቀናተኛ፡የኾነ፡እግዚአብሔር፡ቅንአት፡ያለው፡አምላክ፡ነውና፥ለሌላ፡አምላክ፡አትስገድ።
15፤በዚያች፡ምድር፡ከሚኖሩ፡ሰዎች፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡እንዳታደርግ፥እነርሱ፡አምላኮቻቸውን፡ተከትለው፡ባመ ነዘሩና፡በሠዉላቸው፡ጊዜ፡እንዳይጠሩኽ፥ከመሥዋዕታቸውም፡እንዳትበላ፥
16፤ሴት፡ልጆቻቸውንም፡ከወንድ፡ልጆችኽ፡ጋራ፡እንዳታጋባ፥ልጆቻቸውም፡አምላኮቻቸውን፡ተከትለው፡ሲያመነዝ ሩ፡ከአምላኮቻቸው፡በዃላ፡ኼደው፡አመንዝረውም፡ልጆችኽን፡እንዳያስቱ፡ተጠንቀቅ።
17፤ቀልጠው፡የተሠሩትን፡የአማልክት፡ምስሎች፡ለአንተ፡አታድርግ።
18፤የቂጣውን፡በዓል፡ትጠብቀዋለኽ።በአቢብ፡ወር፡ከግብጽ፡ወጥተኻልና፥በታዘዘው፡ዘመን፡በአቢብ፡ወር፡እን ዳዘዝኹኽ፡ሰባት፡ቀን፡ቂጣ፡እንጀራ፡ብላ።
19፤ማሕፀንንም፡የሚከፍት፡ዅሉ፡የእኔ፡ነው፤የከብትኽም፡ተባት፡በኵር፡ዅሉ፥በሬም፡ቢኾን፡በግም፡ቢኾን፥የ እኔ፡ነው።
20፤የአህያውንም፡በኵር፡በጠቦት፡ትዋጀዋለኽ፤ባትዋጀውም፡ዐንገቱን፡ትሰብረዋለኽ።የልጆችኽንም፡በኵር፡ዅ ሉ፡ትዋጃለኽ።በፊቴም፡አንድ፡ሰው፡ባዶ፡እጁን፡አይታይ።
21፤ስድስት፡ቀን፡ትሠራለኽ፥በሰባተኛውም፡ቀን፡ታርፋለኽ፤በምታርስበትና፡በምታጭድበት፡ዘመን፡ታርፋለኽ።
22፤የሰባቱንም፡ሱባዔ፡በዓል፡ታደርጋለኽ፥ርሱም፡የስንዴ፡መከር፡በኵራት፡ነው፤በዓመቱም፡ፍጻሜ፡የመክተቻ ፡በዓል፡ታደርጋለኽ።
23፤ባንተ፡ዘንድ፡ያለው፡ወንድ፡ዅሉ፡በእስራኤል፡አምላክ፡በጌታ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በዓመት፡ሦስት፡ጊዜ ፡ይታይ።
24፤አሕዛብን፡ከፊትኽ፡አወጣለኹ፥አገርኽንም፡አሰፋለኹ፤በአምላክኽም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለመታየት፡በዓ መት፡ሦስት፡ጊዜ፡ስትወጣ፡ማንም፡ምድርኽን፡አይመኝም።
25፤የመሥዋዕቴን፡ደም፡ከቦካ፡እንጀራ፡ጋራ፡አትሠዋ፤የፋሲካውም፡በዓል፡መሥዋዕት፡እስከ፡ነገ፡አይደር።
26፤የተመረጠውን፡የምድርኽን፡ፍሬ፡በኵራት፡ወደአምላክኽ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ታገባለኽ።ጠቦቱን፡በእና ቱ፡ወተት፡አትቀቅልም።
27፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በእነዚህ፡ቃሎች፡መጠን፡ከአንተና፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አድርጌያለኹና ፡እነዚህን፡ቃሎች፡ጻፍ፡አለው።
28፤በዚያም፡አርባ፡ቀንና፡አርባ፡ሌሊት፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ነበረ፤እንጀራም፡አልበላም፥ውሃም፡አልጠጣም ።በጽላቶቹም፡ዐሥሩን፡የቃል፡ኪዳን፡ቃሎች፡ጻፈ።
29፤እንዲህም፡ኾነ፤ሙሴ፡ከሲና፡ተራራ፡በወረደ፡ጊዜ፡ኹለቱ፡የምስክር፡ጽላቶች፡በሙሴ፡እጅ፡ነበሩ፤ሙሴም፡ ከተራራው፡በወረደ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ስለ፡ተነጋገረ፡የፊቱ፡ቍርበት፡እንዳንጸባረቀ፡አላወቀ ም፡ነበር።
30፤አሮንና፡የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡ሙሴን፡ባዩ፡ጊዜ፥እንሆ፥የፊቱ፡ቍርበት፡አንጸባረቀ፤ወደ፡ርሱም፡ይ ቀርቡ፡ዘንድ፡ፈሩ።
31፤ሙሴም፡ጠራቸው፤አሮንም፡የማኅበሩን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ተመለሱ፤ሙሴም፡ተናገራቸው።
32፤ከዚያም፡በዃላ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ቀረቡ፤እግዚአብሔርም፡በሲና፡ተራራ፡የተናገረውን፡ነገር፡ዅሉ ፡አዘዛቸው።
33፤ሙሴም፡ለእነርሱ፡ተናግሮ፡ከጨረሰ፡በዃላ፡በፊቱ፡መሸፈኛ፡አደረገ።
34፤ሙሴም፡ከርሱ፡ጋራ፡ሲነጋገር፡ወደ፡እግዚአብሔር፡በገባ፡ጊዜ፡እስኪ፡ወጣ፡ድረስ፡መሸፈኛውን፡ከፊቱ፡አ ነሣ፤በወጣም፡ጊዜ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡የታዘዘውን፡ነገር፡ነገረ።
35፤የእስራኤልም፡ልጆች፡የሙሴን፡ፊት፡ቍርበት፡እንዳንጸባረቀ፡ያዩ፡ነበር፤ርሱም፡ከርሱ፡ጋራ፡ሊነጋገር፡ እስኪገባ፡ድረስ፡እንደ፡ገና፡በፊቱ፡መሸፈኛ፡ያደርግ፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35።
1፤ሙሴም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ሰብስቦ፡እንዲህ፡አላቸው፦ታደርጉ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ያዘ ዘው፡ቃል፡ይህ፡ነው፤
2፤ስድስት፡ቀን፡ሥራ፡ይደረጋል፥ሰባተኛው፡ቀን፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡የዕረፍት፡ሰንበት፡የተቀደሰ፡ቀን፡ ይኾንላችዃል፤የሚሠራበትም፡ዅሉ፡ይገደል።
3፤በማደሪያዎቻችኹ፡ውስጥ፡በሰንበት፡ቀን፡እሳትን፡አታንድዱ።
4፤ሙሴም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡አላቸው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ያዘዘው፡ነገር፡ይህ፡ነው ፤
5፤ከእናንተ፡ዘንድ፡ለእግዚአብሔር፡ቍርባንን፡አቅርቡ፤የልብ፡ፈቃድ፡ያለው፡የእግዚአብሔርን፡ቍርባን፡ያ ምጣ፤ወርቅና፡ብርም፡ናስም፤
6፤ሰማያዊም፡ሐምራዊም፡ቀይ፡ግምጃም፥ጥሩ፡በፍታም፥የፍየል፡ጠጕርም፤
7፤ቀይም፡የአውራ፡በግ፡ቍርበት፥የአቍስጣም፡ቍርበት፥የግራርም፡ዕንጨት፤
8፤ለመብራትም፡ዘይት፥ለቅብዐት፡ዘይትና፡ለጣፋጭ፡ዕጣን፡ቅመም፤
9፤መረግድ፡ለኤፉዱና፡ለደረት፡ኪስ፡የሚደረግ፡ፈርጥ፡ያምጣ።
10፤በእናንተም፡ዘንድ፡ያሉ፡በልባቸው፡ጥበበኛዎች፡ዅሉ፡መጥተው፡እግዚአብሔር፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡ያድርጉ።
11፤ማደሪያውን፥ድንኳኑንም፡መደረቢያውንም፥መያዣዎቹንም፥ሳንቃዎቹንም፥መወርወሪያዎቹንም፥ምሰሶዎቹንም፥ እግሮቹንም፤
12፤ታቦቱን፡መሎጊያዎቹንም፥የስርየት፡መክደኛውንም፡በርሱም፡ፊት፡የሚሸፍነውን፡መጋረጃ፤
13፤ገበታውን፡መሎጊያዎቹንም፡ዕቃውንም፡ዅሉ፥የገጹንም፡ኅብስት፤
14፤መብራት፡የሚያበሩበትን፡መቅረዙን፡ዕቃውንም፥ቀንዲሉንም፥የመብራቱንም፡ዘይት፤
15፤የዕጣኑን፡መሠዊያም፡መሎጊያዎቹንም፥የቅብዓቱንም፡ዘይት፥ጣፋጩንም፡ዕጣን፥ለማደሪያውም፡ደጃፍ፡የሚኾ ን፡የደጃፉን፡መጋረጃ፤
16፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡መሠዊያውን፥የናሱንም፡መከታ፥መሎጊያዎቹንም፥ዕቃውንም፡ዅሉ፤የመታጠ ቢያውን፡ሰንም፡መቀመጫውንም፤
17፤የአደባባዩን፡መጋረጃዎች፡ምሰሶዎቹንም፡እግሮቻቸውንም፥የአደባባዩንም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፤
18፤የማደሪያውን፡ካስማዎች፥የአደባባዩንም፡ካስማዎች፡አውታሮቻቸውንም፤
19፤በመቅደስ፡ውስጥ፡ለማገልገል፡በብልኀት፡የተሠሩትን፡ልብሶች፥በክህነት፡ያገለግሉበት፡ዘንድ፡የተቀደሱ ትን፡የካህኑን፡የአሮን፡ልብሶች፥የልጆቹንም፡ልብሶች።
20፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ከሙሴ፡ፊት፡ወጡ።
21፤ከነርሱም፡ሰው፡ዅሉ፡ልቡ፡እንዳነሣሣው፡መንፈሱም፡ዕሺ፡እንዳሠኘው፡ለመገናኛው፡ድንኳን፡ሥራ፡ለማገል ገያውም፡ዅሉ፡ለተቀደሰውም፡ልብስ፡ለእግዚአብሔር፡ስጦታ፡አመጡ።
22፤ወንዶችና፡ሴቶችም፡ልባቸው፡እንደ፡ፈቀደ፡ማርዳዎችን፥ሎቲዎችንም፥ቀለበቶችንም፥ድሪዎችንም፥የወርቅ፡ ጌጦችንም፡ዅሉ፡አመጡ፤ሰዎችም፡ዅሉ፡የወርቅ፡ስጦታ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡አቀረቡ።
23፤ሰማያዊም፡ሐምራዊም፡ቀይ፡ግምጃም፥ጥሩ፡በፍታም፥የፍየል፡ጠጕርም፥ቀይ፡የአውራ፡በግ፡ቍርበትም፥የአቍ ስጣ፡ቍርበትም፡ያላቸው፡ሰዎች፡ዅሉ፡አመጡ።
24፤ስእለት፡የተሳለ፡ዅሉ፡የብርንም፡የናስንም፡ስጦታ፡ለእግዚአብሔር፡ቍርባን፡አቀረበ፤የግራርም፡ዕንጨት ፡ያለው፡ዅሉ፡ለማገልገያ፡ሥራ፡አመጣ።
25፤በልባቸው፡ጥበበኛዎች፡የኾኑ፡ሴቶችም፡በእጃቸው፡ፈተሉ፥የፈተሉትንም፡ሰማያዊውን፡ሐምራዊውንም፡ቀዩን ም፡ግምጃ፥ጥሩውንም፡በፍታ፡አመጡ።
26፤ልባቸውም፡በጥበብ፡ያስነሣቸው፡ሴቶች፡ዅሉ፡የፍየልን፡ጠጕር፡ፈተሉ።
27፤አለቃዎችም፡መረግድን፥ለኤፉድና፡ለደረት፡ኪስ፡የሚገቡትንም፡ፈርጦችን፥
28፤ለመብራትም፡ለቅብዐት፡ዘይትም፡ለጣፋጭ፡ዕጣንም፡ሽቱንና፡ዘይትን፡አመጡ።
29፤ከእስራኤል፡ልጆችም፡ያመጡ፡ዘንድ፡ልባቸው፡ያስነሣቸው፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ዅሉ፡ሙሴ፡ይሠራ፡ዘንድ፡እግ ዚአብሔር፡ላዘዘው፡ሥራ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ስጦታ፡በፈቃዳቸው፡አመጡ።
30፤ሙሴም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አላቸው፦እዩ፥እግዚአብሔር፡ከይሁዳ፡ነገድ፡የኾነውን፡የሆር፡የልጅ፡ልጅ፥ የኡሪ፡ልጅ፡ባስልኤልን፡በስሙ፡ጠራው።
31፤በሥራ፡ዅሉ፡ብልኀት፡በጥበብም፡በማስተዋልም፡በዕውቀትም፡የእግዚአብሔርን፡መንፈስ፡ሞላበት፤
32፤የጥበብን፡ሥራ፡ያስተውል፡ዘንድ፥በወርቅና፡በብር፡በናስም፡ይሠራ፡ዘንድ፥
33፤በፈርጥ፡የሚኾነውን፡የዕንቍ፡ድንጋይ፡ይቀርጽ፡ዘንድ፥ዕንጨቱንም፡ይጠርብ፡ዘንድ፥የብልኀት፡ሥራውንም ፡ዅሉ፡ይሠራ፡ዘንድ።
34፤ርሱና፡የዳን፡ነገድ፡የኾነው፡የአሂሳሚክ፡ልጅ፡ኤልያብ፡ያስተምሩ፡ዘንድ፡በልባቸው፡አሳደረባቸው።
35፤በአንጥረኛ፥በብልኅ፡ሠራተኛም፥በሰማያዊና፡በሐምራዊ፡በቀይም፡ግምጃ፡በጥሩ፡በፍታም፡በሚሠራ፡ጠላፊ፥ በሸማኔም፡ሥራ፡የሚሠራውን፥ማናቸውንም፡ሥራና፡በብልኀት፡የሚሠራውን፡ዅሉ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡በእነርሱ፡ልብ ፡ጥበብን፡ሞላ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36።
1፤ለመቅደስም፡ማገልገያ፡ሥራ፡ዅሉ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡እንዲያውቁ፡እግዚአብሔር፡ጥበብንና፡ማስተዋልን፡የሰ ጣቸው፡ባስልኤልና፡ኤልያብ፡በልባቸው፡ጥበበኛዎችም፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡ነገር፡ዅሉ፡አደረጉ።
2፤ሙሴም፡ባስልኤልንና፡ኤልያብን፥እግዚአብሔርም፡በልቡ፡ጥበብን፡ያደረገለትን፡በልብ፡ጥበበኛ፡ሰው፡ዅሉ ፥ሥራውንም፡ለመሥራት፡ይቀርብ፡ዘንድ፡ልቡ፡ያስነሣውን፡ዅሉ፡ጠራቸው።
3፤እነርሱም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ለመቅደስ፡ማገልገያ፡ሥራ፡ያመጡትን፡ስጦታ፡ዅሉ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ከሙሴ፡ተ ቀበሉ።እነዚያም፡እንደ፡ፈቃዳቸው፡ማለዳ፡ማለዳ፡ስጦታውን፡ገና፡ወደ፡ርሱ፡ያመጡ፡ነበር።
4፤የመቅደሱንም፡ሥራ፡የሚሠሩ፡ጠቢባን፡ዅሉ፡የሚያደርጉትን፡ሥራ፡ትተው፡መጡ፥
5፤እነርሱም፡ሙሴን፦እግዚአብሔር፡ለማገልገያ፡ሥራ፡ይደረግ፡ዘንድ፡ላዘዘው፡ከሚበቃ፡ይልቅ፡እጅግ፡የሚበ ልጥ፡ሕዝቡ፡አመጡ፡ብለው፡ተናገሩት።
6፤7፤ያመጡትም፡ነገር፡ሥራን፡ዅሉ፡ለመፈጸም፡በቅቶ፡ገና፡ይተርፍ፡ስለ፡ነበረ፡ሙሴ፡አዘዘና።ወንድ፡ወይም ፡ሴት፡ለመቅደስ፡ስጦታ፡ከዚህ፡የበለጠ፡የሚያመጣ፡አይኑር፡ብሎ፡በሰፈሩ፡ውስጥ፡አሳወጀ።ሕዝቡም፡እንዳያ መጡ፡ተከለከሉ።ፕ
8፤በእነርሱም፡ዘንድ፡ያሉት፡ሥራ፡ሲሠሩ፡የነበሩት፡በልባቸው፡ጥበበኛዎች፡ዅሉ፡ማደሪያውን፡ከዐሥር፡መጋ ረጃዎች፡ሠሩ፤እነርሱንም፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታ፥ከሰማያዊም፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ሠሩ፤በእነርሱ ም፡ላይ፡ብልኅ፡ሠራተኛ፡እንደሚሠራ፡ኪሩቤልን፡አደረጉባቸው።
9፤የያንዳንዱ፡መጋረጃ፡ርዝመት፡ኻያ፡ስምንት፡ክንድ፥ወርዱም፡አራት፡ክንድ፡ነበረ፤የመጋረጃዎቹ፡ዅሉ፡ል ክ፡ትክክል፡ነበረ።
10፤ዐምስቱንም፡መጋረጃዎች፡ርስ፡በርሳቸው፡አጋጠሙ፤ዐምስቱንም፡መጋረጃዎች፡እንዲሁ፡ርስ፡በርሳቸው፡አጋ ጠሙ።
11፤ከሚጋጠሙትም፡መጋረጃዎች፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡የሰማያዊውን፡ግምጃ፡ቀለበቶች፡አደረጉ፤ደ ግሞ፡ከተጋጠሙት፡ከሌላዎቹ፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡እንዲሁ፡አደረጉ።
12፤ዐምሳ፡ቀለበቶችን፡ባንድ፡መጋረጃ፡አደረጉ፤ዐምሳውንም፡ቀለበቶች፡በኹለተኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡አደረጉ ፤ቀለበቶቹ፡ርስ፡በርሳቸው፡ፊት፡ለፊት፡የሚተያዩ፡ነበሩ።
13፤ዐምሳም፡የወርቅ፡መያዣዎች፡ሠሩ፤መጋረጃዎችንም፡ርስ፡በርሳቸው፡በመያዣዎች፡አጋጠሟቸው፤አንድ፡ማደሪ ያም፡ኾነ።
14፤ከማደሪያውም፡በላይ፡ለድንኳን፡የሚኾኑ፡መጋረጃዎችን፡ከፍየል፡ጠጕር፡አደረጉ፤ዐሥራ፡አንድ፡መጋረጃዎ ች፡አደረጉ።
15፤እያንዳንዱም፡መጋረጃ፡ርዝመቱ፡ሠላሳ፡ክንድ፥እያንዳንዱም፡መጋረጃ፡ወርዱ፡አራት፡ክንድ፡ነበረ፤የዐሥ ራ፡አንዱም፡መጋረጃዎች፡መጠናቸው፡ትክክል፡ነበረ።
16፤ዐምስቱንም፡መጋረጃዎች፡ርስ፡በርሳቸው፡አንድ፡አድርገው፥ስድስቱንም፡መጋረጃዎች፡አንድ፡አድርገው፡አ ጋጠሟቸው።
17፤ከተጋጠሙትም፡መጋረጃዎች፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡ዐምሳ፡ቀለበቶች፡አደረጉ፤ደግሞ፡ከተጋጠሙ ት፡ከሌላዎቹ፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡ዐምሳ፡ቀለበቶች፡አደረጉ።
18፤ድንኳኑም፡አንድ፡እንዲኾን፡ያጋጥሙት፡ዘንድ፡ዐምሳ፡የናስ፡መያዣዎችን፡ሠሩ።
19፤ለድንኳኑም፡መደረቢያ፡ከቀይ፡ከአውራ፡በግ፡ቍርበት፥ከዚያም፡በላይ፡ሌላ፡መደረቢያ፡ከአቍስጣ፡ቍርበት ፡አደረጉ።
20፤ለማደሪያውም፡ከግራር፡ዕንጨት፡የሚቆሙትን፡ሳንቃዎች፡አደረጉ።
21፤የሳንቃው፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡ዐሥር፡ክንድ፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡ነበረ።
22፤ለያንዳንዱም፡ሳንቃ፡አንዱን፡በአንዱ፡ላይ፡የሚያያይዙ፡ኹለት፡ማጋጠሚያዎች፡ነበሩ፤ለማደሪያው፡ሳንቃ ዎች፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረጉ።
23፤ለማደሪያውም፡በደቡብ፡ወገን፡ኻያ፡ሳንቃዎችን፡አደረጉ፤
24፤ከኻያውም፡ሳንቃዎች፡በታች፡አርባ፡የብር፡እግሮች፡አደረጉ፤ከያንዳንዱም፡ሳንቃ፡በታች፡ለኹለቱ፡ማጋጠ ሚያዎች፡ኹለት፡እግሮች፡ነበሩ።
25፤ለማደሪያው፡ለኹለተኛው፡ወገን፡በሰሜን፡በኩል፡ኻያ፡ሳንቃዎች፡አደረጉ፤
26፤ለእነርሱም፡አርባ፡የብር፡እግሮች፥ከያንዳንዱም፡ሳንቃ፡በታች፡ኹለት፡እግሮች፡አደረጉ።
27፤ለማደሪያውም፡በምዕራቡ፡ወገን፥በስተዃላ፡ስድስት፡ሳንቃዎች፡አደረጉ።
28፤ለማደሪያውም፡ለኹለቱ፡ማእዘን፡በስተዃላ፡ኹለት፡ሳንቃዎች፡አደረጉ።
29፤ከታችም፡እስከ፡ላይ፡እስከ፡አንደኛው፡ቀለበት፡ድረስ፡አንድ፡ሳንቃ፡ድርብ፡ነበረ፤ለኹለቱም፡ማእዘን፡ እንዲሁ፡ኹለት፡ነበሩ።
30፤ስምንት፡ሳንቃዎችና፡ዐሥራ፡ስድስቱ፡የብር፡እግሮቻቸው፥ከያንዳንዱም፡ሳንቃ፡በታች፡ኹለት፡ኹለት፡እግ ሮች፡ነበሩ።
31፤ከግራርም፡ዕንጨት፡በማደሪያው፡በአንደኛው፡ወገን፡ላሉት፡ሳንቃዎች፡ዐምስት፡መወርወሪያዎች፥
32፤በማደሪያውም፡በኹለተኛው፡ወገን፡ላሉት፡ሳንቃዎች፡ዐምስት፡መወርወሪያዎች፥ከማደሪያውም፡በስተዃላ፡በ ምዕራቡ፡ወገን፡ላሉት፡ሳንቃዎች፡ዐምስት፡መወርወሪያዎች፡አደረጉ።
33፤መካከለኛውንም፡መወርወሪያ፡በሳንቃዎቹ፡መካከል፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡አሳለፉ።
34፤ሳንቃዎቹንም፡በወርቅ፡ለበጧቸው፤ቀለበቶቻቸውንም፡የመወርወሪያ፡ቤት፡እንዲኾኑላቸው፡ከወርቅ፡አደረጉ ፤መወርወሪያዎቹንም፡በወርቅ፡ለበጧቸው።
35፤መጋረጃውንም፡ከሰማያዊና፡ከሐምራዊ፡ከቀይም፡ግምጃ፥ከተፈተለም፡ከጥሩ፡በፍታ፡አደረጉ፤ብልኅ፡ሠራተኛ ፡እንደሚሠራ፡ኪሩቤልን፡በርሱ፡ላይ፡አደረጉ።
36፤ከግራርም፡ዕንጨት፡አራት፡ምሰሶዎች፡አደረጉለት፥በወርቅም፡ለበጧቸው፤ኵላቦቻቸው፡የወርቅ፡ነበሩ፤ለእ ነርሱም፡አራት፡የብር፡እግሮች፡አደረጉ።
37፤ለድንኳኑም፡ደጃፍ፡ከሰማያዊና፡ከሐምራዊ፡ከቀይም፡ግምጃ፥ከተፈተለም፡ከጥሩ፡በፍታ፡በጥልፍ፡አሠራር፡ የተሠራ፡መጋረጃ፡አደረጉ፤
38፤ዐምስቱንም፡ምሰሶዎች፥ኵላቦቻቸውንም፡አደረጉ፤ጕልላቶቻቸውንና፡ዘንጎቻቸውንም፡በወርቅ፡ለበጧቸው፤ዐ ምስቱም፡እግሮቻቸው፡የናስ፡ነበሩ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡37።______________
ምዕራፍ፡37።
1፤ባስልኤልም፡ከግራር፡ዕንጨት፡ታቦቱን፡ሠራ፤ርዝመቱም፡ኹለት፡ክንድ፡ተኩል፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩ ል፥ቁመቱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡ነበረ።
2፤በውስጥም፡በውጭም፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለበጠው፤በዙሪያውም፡የወርቅ፡አክሊል፡አደረገለት።
3፤አራት፡የወርቅ፡ቀለበቶችም፡አደረገለት፤እነርሱንም፡በአራቱ፡እግሮቹ፡ላይ፡አኖረ።ባንድ፡ወገን፡ኹለት ፡ቀለበቶች፥በሌላውም፡ወገን፡ኹለት፡ቀለበቶች፡ኾኑ።
4፤መሎጊያዎቹንም፡ከግራር፡ዕንጨት፡ሠራ፥በወርቅም፡ለበጣቸው።
5፤ታቦቱንም፡ለመሸከም፡በታቦቱ፡አጠገብ፡ባሉት፡ቀለበቶች፡መሎጊያዎቹን፡አገባ።
6፤ከጥሩ፡ወርቅም፡ርዝመቱ፡ኹለት፡ክንድ፡ተኩል፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡የኾነ፡የስርየት፡መክደኛ፡ ሠራ።
7፤ኹለት፡ኪሩቤልንም፡ከተቀጠቀጠ፡ወርቅ፡ሠራ፤በስርየት፡መክደኛውም፡ላይ፡በኹለት፡ወገን፡አደረጋቸው።
8፤ከስርየት፡መክደኛውም፡ጋራ፡አንዱን፡ኪሩብ፡ባንድ፡ወገን፥ኹለተኛውንም፡ኪሩብ፡በሌላው፡ወገን፡አድርጎ ፡ባንድ፡ላይ፡ሠራቸው።
9፤ኪሩቤልም፡ክንፎቻቸውን፡ወደ፡ላይ፡የዘረጉ፡ኾኑ፥የስርየት፡መክደኛውንም፡በክንፎቻቸው፡ሸፈኑ፥ርስ፡በ ርሳቸውም፡ተያዩ፤የኪሩቤልም፡ፊቶቻቸው፡ወደ፡መክደኛው፡ተመለከቱ።
10፤ርዝመቱ፡ኹለት፡ክንድ፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፥ቁመቱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡የኾነውን፡ገበታ፡ከግራር፡ ዕንጨት፡ሠራ።
11፤በጥሩም፡ወርቅ፡ለበጠው፥በዙሪያውም፡የወርቅ፡አክሊል፡አደረገለት።
12፤በዙሪያውም፡አንድ፡ጋት፡የሚያኽል፡ክፈፍ፡አደረገለት፤የወርቅም፡አክሊል፡በክፈፉ፡ዙሪያ፡አደረገለት።
13፤አራትም፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡አደረገለት፤ቀለበቶቹንም፡አራቱ፡እግሮቹ፡ባሉበት፡በአራቱ፡ማእዘኖች፡አደ ረገ።
14፤ገበታውንም፡ለመሸከም፡መሎጊያዎቹ፡እንዲሰኩባቸው፡ቀለበቶች፡በክፈፉ፡አቅራቢያ፡ነበሩ።
15፤ገበታውንም፡ይሸከሙባቸው፡ዘንድ፡መሎጊያዎቹን፡ከግራር፡ዕንጨት፡ሠርቶ፡በወርቅ፡ለበጣቸው።
16፤ለማፍሰሻም፡ይኾኑ፡ዘንድ፡በገበታው፡ላይ፡የሚኖሩትን፡ዕቃዎች፥ወጭቶቹንና፡ጭልፋዎቹን፡ጽዋዎቹንም፡መ ቅጃዎቹንም፥ከጥሩ፡ወርቅ፡አደረጋቸው።
17፤መቅረዙንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡አደረገ፤መቅረዙንም፡ከእግሩና፡ከአገዳው፡ጋራ፡በተቀረጸ፡ሥራ፡አደረገ፤ጽዋ ዎቹን፥ጕብጕቦቹን፥አበባዎቹን፡ከዚያው፡በአንድነት፡አደረገ።
18፤በስተጐኑም፡ስድስት፡ቅርንጫፎች፡ወጡለት፤ሦስቱ፡የመቅረዙ፡ቅርንጫፎች፡ባንድ፡ወገን፥ሦስቱም፡የመቅረ ዙ፡ቅርንጫፎች፡በሌላ፡ወገን፡ወጡ።
19፤በአንደኛው፡ቅርንጫፍ፡ጕብጕቡንና፡አበባውን፡ሦስትም፡የለውዝ፡አበባ፡የሚመስሉትን፡ጽዋዎች፥በኹለተኛ ውም፡ቅርንጫፍ፡ጕብጕቡንና፡አበባውን፡ሦስትም፡የለውዝ፡አበባ፡የሚመስሉትን፡ጽዋዎች፥እንዲሁም፡ከመቅረዙ ፡ለወጡ፡ለስድስቱ፡ቅርንጫፎች፡አደረገ።
20፤በመቅረዙም፡ጕብጕቦቹንና፡አበባዎቹን፡አራትም፡የለውዝ፡አበባ፡የሚመስሉትን፡ጽዋዎች፡አደረገ።
21፤ከመቅረዙ፡ለወጡ፡ለስድስት፡ቅርንጫፎች፡ከኹለት፡ቅርንጫፎች፡በታች፡አንድ፡ኾኖ፡የተሠራ፡አንድ፡ጕብጕ ብ፥ከኹለትም፡ቅርንጫፎች፡በታች፡አንድ፡ኾኖ፡የተሠራ፡አንድ፡ጕብጕብ፥ደግሞ፡ከኹለት፡ቅርንጫፎች፡በታች፡ አንድ፡ኾኖ፡የተሠራ፡አንድ፡ጕብጕብ፡ነበረ።
22፤ጕብጕቦቹና፡ቅርንጫፎቹ፡ከርሱ፡ጋራ፡አንድ፡ነበሩ፤ዅሉም፡አንድ፡ኾኖ፡ከተቀረጸ፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ተሠርቶ ፡ነበር።
23፤ሰባቱንም፡መብራቶች፡መኰስተሪያዎቹንም፥የኵስታሪ፡ማድረጊያዎቹንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሠራ።
24፤መቅረዙንም፡ዕቃውንም፡ዅሉ፡ካንድ፡መክሊት፡ጥሩ፡ወርቅ፡አደረገ።
25፤የዕጣን፡መሠዊያ፡ከግራር፡ዕንጨት፡ሠራ፤ርዝመቱ፡አንድ፡ክንድ፥ስፋቱ፡አንድ፡ክንድ፥አራት፡ማእዘን፡ነ በረ፤ከፍታውም፡ኹለት፡ክንድ፡ነበረ፤ቀንዶቹም፡ከርሱ፡ጋራ፡በአንድነት፡የተሠሩ፡ነበሩ።
26፤ላይኛውንና፡የግድግዳውንም፡ዙሪያ፡ቀንዶቹንም፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለበጠው፤በዙሪያውም፡የወርቅ፡ክፈፍ፡አደ ረገበት።
27፤ከክፈፉም፡በታች፡ኹለት፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡አደረገበት፥በዚህና፡በዚያ፡በኹለቱም፡ጐን፡አደረጋቸው፤ለ መሸከምም፡የመሎጊያዎች፡ስፍራ፡ነበሩ።
28፤መሎጊያዎቹንም፡ከግራር፡ዕንጨት፡አደረገ፥በወርቅም፡ለበጣቸው።
29፤የተቀደሰውንም፡የቅብዓቱን፡ዘይት፥ጥሩውንም፡የጣፋጭ፡ሽቱ፡ዕጣን፡በቀማሚ፡ብልኀት፡እንደ፡ተሠራ፡አደ ረገ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡38።______________
ምዕራፍ፡38።
1፤ርዝመቱ፡ዐምስት፡ክንድ፥ወርዱም፡ዐምስት፡ክንድ፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾን፡መሠዊያን፡ከግራር፡ዕን ጨት፡አደረገ፤አራት፡ማእዘንም፡ነበረ፤ከፍታው፡ሦስት፡ክንድ፡ነበረ።
2፤ቀንዶቹንም፡በአራቱ፡ማእዘን፡አደረገበት፤ቀንዶቹም፡ከርሱ፡ጋራ፡ባንድ፡የተሠሩ፡ነበሩ፤በናስም፡ለበጠ ው።
3፤የመሠዊያውንም፡ዕቃ፡ዅሉ፥ምንቸቶቹንም፥መጫሪያዎቹንም፥ድስቶቹንም፥ሜንጦቹንም፥ማንደጃዎቹንም፡አደረ ገ፤ዕቃውንም፡ዅሉ፡ከናስ፡አደረገ።
4፤እንደ፡መረብ፡ኾኖም፡የተሠራ፡የናስ፡መከታ፡ለመሠዊያ፡አደረገ፤መከታውም፡እስከመሠዊያው፡እኩሌታ፡ይደ ርስ፡ዘንድ፡በመሠዊያው፡በሚዞረው፡በደረጃው፡ታች፡አደረገው።
5፤ለናሱም፡መከታ፡ለአራቱ፡ማእዘን፡የመሎጊያዎች፡ስፍራ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡አራት፡ቀለበቶች፡አደረገ።
6፤መሎጊያዎቹንም፡ከግራር፡ዕንጨት፡ሠራ፥በናስም፡ለበጣቸው።
7፤ይሸከሙትም፡ዘንድ፡በመሠዊያ፡ጐን፡ባሉት፡ቀለበቶች፡ውስጥ፡መሎጊያዎቹን፡አገባ፤ከሳንቃዎቹም፡ሠርቶ፡ ባዶ፡አደረገው።
8፤የመታጠቢያውን፡ሰንና፡መቀመጫውንም፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ከሚያገለግሉ፡ከሴቶች፡መስተዋት፡ከና ስ፡አደረገ።
9፤አደባባዩንም፡አደረገ፤በደቡብ፡ወገን፡ርዝመቱ፡መቶ፡ክንድ፡የኾነ፥የተፈተለ፡የጥሩ፡በፍታ፡መጋረጃዎች ፡ነበሩ።
10፤ከናስ፡የተሠሩ፡ኻያውን፡ምሰሶዎችና፡ኻያውን፡እግሮች፡አደረገ፤የምሰሶዎቹንም፡ኵላቦችና፡ዘንጎች፡ከብ ር፡አደረገ።
11፤በሰሜኑም፡ወገን፡መቶ፡ክንድ፡ርዝመት፡ያላቸውን፡መጋረጃዎች፥ከናስም፡የተሠራ፡ኻያ፡ምሰሶዎችንና፡ኻያ ፡እግሮችን፥ለምሰሶዎቹም፡የብር፡ኵላቦችንና፡ዘንጎችን፡አደረገ።
12፤በምዕራብም፡ወገን፡ዐምሳ፡ክንድ፡ርዝመት፡ያላቸውን፡መጋረጃዎች፥ዐሥሩንም፡ምሰሶዎች፥ዐሥሩንም፡የናስ ፡እግሮች፥ለምሰሶዎቹም፡የብር፡ኵላቦችንና፡ዘንጎችን፡አደረገ።
13፤በምሥራቅም፡ወገን፡ዐምሳ፡ክንድ፡ርዝመት፡ያላቸውን፡መጋረጃዎች፡አደረገ።
14፤ባንድ፡ወገንም፡የመጋረጃዎቹ፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ክንድ፥ምሰሶዎቹም፡ሦስት፥እግሮቹም፡ሦስት፡ነበ ሩ።
15፤እንዲሁም፡በኹለተኛው፡ወገን፡በአደባባዩ፡ደጅ፡በዚህና፡በዚያ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ክንድ፡ርዝመት፡ያላቸው ፡መጋረጃዎች፥ሦስትም፡ምሰሶዎች፥ሦስትም፡እግሮች፡ነበሩ።
16፤በአደባባዩ፡ዙሪያ፡ያሉ፡መጋረጃዎች፡ዅሉ፡ከተፈተለ፡ከጥሩ፡በፍታ፡ተሠርተው፡ነበር።
17፤የምሰሶዎቹም፡እግሮች፡የናስ፥የምሰሶዎቹም፡ኵላቦችና፡ዘንጎች፡የብር፡ነበሩ፤የምሰሶዎችም፡ጕልላቶች፡ በብር፡ተለብጠው፡ነበር፤በአደባባዩ፡ላሉ፡ምሰሶዎች፡ዅሉ፡የብር፡ዘንጎች፡ነበሯቸው።
18፤የአደባባዩም፡ደጅ፡መጋረጃ፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፥ከጥሩም፡በፍታ፡በጥልፍ፡አሠራር፡የ ተሠራ፡ነበረ፤ርዝመቱ፡ኻያ፡ክንድ፡ነበረ፥ቁመቱም፡እንደ፡አደባባዩ፡መጋረጃዎች፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፤
19፤ከናስ፡የተሠሩ፡ምሰሶዎቹም፡አራት፥እግሮቹም፡አራት፡ነበሩ፤ኵላቦቹ፡የብር፡ነበሩ፤ጕልላቶቹና፡ዘንጎቹ ም፡በብር፡ተለብጠው፡ነበር።
20፤የማደሪያውም፡ካስማዎች፡በዙሪያውም፡ያለ፡የአደባባዩ፡ካስማዎች፡የናስ፡ነበሩ።
21፤በሙሴ፡ትእዛዝ፡ለሌዋውያን፡ማገልገል፡ሊኾን፡በካህኑ፡በአሮን፡ልጅ፡በኢታማር፡እጅ፡እንደ፡ተቈጠረው፡ የማደሪያው፥የምስክሩ፡ማደሪያ፥ዕቃ፡ድምር፡ይህ፡ነው።
22፤ከይሁዳ፡ነገድም፡የኾነ፡የሆር፡የልጅ፡ልጅ፥የኡሪ፡ልጅ፡ባስልኤል፡እግዚአብሔር፡ለሙሴ፡ያዘዘውን፡ዅሉ ፡አደረገ።
23፤ከርሱም፡ጋራ፡ከዳን፡ነገድ፡የኾነ፡የአሂሳሚክ፡ልጅ፡ኤልያብ፡ነበረ፤ርሱም፡የቅርጽ፡ሠራተኛና፡ብልኅ፡ ሠራተኛ፥በሰማያዊ፡በሐምራዊም፡በቀይም፡ግምጃ፥በጥሩም፡በፍታ፡የሚሠራ፡ጠላፊ፡ነበረ።
24፤የተሰጠው፡ወርቅ፡ዅሉ፥በመቅደሱ፡ሥራ፡ዅሉ፡የተደረገው፡ወርቅ፥እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፡ኻያ፡ዘጠ ኝ፡መክሊት፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡ነበረ።
25፤በማኅበሩም፡ከሚቈጠሩት፡የተገኘ፡ብር፥እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፥መቶ፡መክሊትና፡አንድ፡ሺሕ፡ሰባት ፡መቶ፡ከሰባ፡ዐምስት፡ሰቅል፡ነበረ።
26፤እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፥የሰቅል፡ግማሽ፡ከተቈጠረው፡ከያንዳንዱ፡ሰው፡የተሰጠ፡ነው፤ከኻያ፡ዓመት ፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡የተቈጠሩት፡ዅሉ፡ስድስት፡መቶ፡ሦስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰዎች፡ነበሩ።
27፤መቶውም፡የብር፡መክሊት፡የመቅደሱንና፡የመጋረጃውን፡እግሮች፡ለመሥራት፡ነበረ፤ከመቶውም፡መክሊት፡መቶ ፡እግሮች፡አደረገ፤ላንድ፡እግርም፡አንድ፡መክሊት፡ነበረ።
28፤ከሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ሰባ፡ዐምስት፡ሰቅል፡የምሰሶዎቹን፡ኵላቦችና፡ዘንጎች፡አደረገ፥የምሰሶዎቹንም፡ጕል ላቶች፡ለበጠ።
29፤የተሰጠውም፡ናስ፡ሰባ፡መክሊትና፡ኹለት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ሰቅል፡ነበረ።
30፤ከርሱም፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡ደጃፍ፡እግሮች፥የናሱንም፡መሠዊያ፥ለርሱም፡የኾነውን፡የናሱን፡መከታ፥ የመሠዊያውንም፡ዕቃ፡ዅሉ፥
31፤በአደባባዩ፡ዙሪያ፡ያሉትን፡እግሮች፥የአደባባዩንም፡ደጃፍ፡እግሮች፥የማደሪያውንም፡ካስማዎች፡ዅሉ፡በ አደባባዩ፡ዙሪያም፡ያሉትን፡ካስማዎች፡ዅሉ፡አደረገ።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡39።______________
ምዕራፍ፡39።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥በመቅደሱ፡ለማገልገል፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይ፡ግምጃም፡በብል ኀት፡የተሠራ፡ልብስ፥ለአሮንም፡የተቀደሰውን፡ልብስ፡አደረጉ።
2፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥ኤፉዱን፡ከወርቅ፡ከሰማያዊም፡ከሐምራዊም፡ከቀይ፡ግምጃም፡ከተፈተለ ም፡ከጥሩ፡በፍታ፡አደረገ።
3፤ወርቁንም፡ቀጥቅጠው፡እንደ፡ቅጠል፡ሥሥ፡አድርገው፡እንደ፡ፈትል፡ቈረጡ።ብልኅ፡ሠራተኛም፡እንደሚሠራ፡ ሰማያዊ፡ሐምራዊም፡ቀይም፡ግምጃ፡የተፈተለም፡ጥሩ፡በፍታ፡ከርሱ፡ጠለፉ።
4፤ኹለቱ፡ወገን፡እንዲጋጠም፡በኹለቱ፡ጫንቃዎች፡ላይ፡የሚጋጠም፡ልብስ፡አደረጉት።
5፤በላዩም፡መታጠቂያ፡ኾኖ፡በብልኀት፡የተጠለፈው፡የኤፉዱ፡ቋድ፡እንደ፡ርሱ፡ከርሱም፡ጋራ፡አንድ፡ነበረ፤ ከወርቅና፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊ፡ከቀይ፡ግምጃም፡ከተፈተለም፡ከጥሩ፡በፍታ፡የተሠራ፡ነበረ።
6፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥በወርቅ፡ፈርጥ፡የተያዙ፡የመረግድ፡ድንጋዮች፡ሠርተው፡እንደ፡ማኅተ ም፡ቅርጽ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ስም፡ቀረጹባቸው።
7፤ለእስራኤል፡ልጆች፡የመታሰቢያ፡ድንጋዮች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡በኤፉዱ፡ጫንቃዎች፡ላይ፡አደረጋቸው።
8፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥የደረቱን፡ኪስ፡ብልኅ፡ሠራተኛ፡እንደሚሠራ፡እንደ፡ኤፉዱ፡አሠራር፡ ከወርቅና፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡ከተፈተለም፡ከጥሩ፡በፍታ፡አደረገው።
9፤አራት፡ማእዘንም፡ነበረ፤የደረቱን፡ኪስም፡ድርብ፡አደረጉ፤ርዝመቱ፡ስንዝር፥ወርዱም፡ስንዝር፥ድርብም፡ ነበረ።
10፤ዕንቍዎቹንም፡በአራት፡ተራ፡አደረጉበት፤በፊተኛውም፡ተራ፡ሰርድዮን፥ቶጳዝዮን፥የሚያብረቀርቅ፡ዕንቍ፤
11፤በኹለተኛውም፡ተራ፡በሉር፥ሰንፔር፥አልማዝ፤
12፤በሦስተኛውም፡ተራ፡ያክንት፥ኬልቄዶን፥አሜቴስጢኖስ፤
13፤በአራተኛውም፡ተራ፡ቢረሌ፥መረግድ፥ኢያስጲድ፡በወርቅ፡ፈርጥ፡ተደረጉ።
14፤የዕንቍዎችም፡ድንጋዮች፡እንደ፡ዐሥራ፡ኹለቱ፡እንደ፡እስራኤል፡ልጆች፡ስሞች፡ነበሩ፤በየስማቸውም፡ማተ ሚያ፡እንደሚቀረጽ፡ተቀረጹ፥ስለ፡ዐሥራ፡ኹለቱም፡ነገዶች፡ነበሩ።
15፤ለደረቱ፡ኪስም፡የተጐነጐኑትን፡ድሪዎች፡እንደ፡ገመድ፡አድርገው፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሠሩ።
16፤ኹለትም፡የወርቅ፡ፈርጦች፥ኹለትም፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሠሩ፤ኹለቱንም፡ቀለበቶች፡በደረቱ፡ኪስ፡በኹለቱ ፡ወገን፡አደረጉ።
17፤ኹለቱንም፡የተጐነጐኑትን፡የወርቅ፡ድሪዎች፡በደረቱ፡ኪስ፡ወገኖች፡ወዳሉት፡ወደ፡ኹለቱ፡ቀለበቶች፡አገ ቡ።
18፤የኹለቱንም፡ድሪዎች፡ጫፎች፡በኹለቱ፡ፈርጦች፡ውስጥ፡አግብተው፡በኤፉዱ፡ጫንቃዎች፡ላይ፡በፊታቸው፡አደ ረጉ።
19፤ኹለቱንም፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሠሩ፥እነርሱንም፡በኤፉዱ፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በደረቱ፡ኪስ፡በኹለት፡ጫፎ ቹ፡ላይ፡አደረጓቸው።
20፤ደግሞም፡ኹለት፡የወርቅ፡ቀለበቶች፡ሠሩ፥በኤፉዱም፡ፊት፥ከጫንቃዎች፡በታች፥በብልኀት፡ከተጠለፈ፡ከኤፉ ዱ፡ቋድ፡በላይ፥በመያዣው፡አጠገብ፡አደረጓቸው።
21፤የደረቱ፡ኪስ፡በብልኀት፡ከተጠለፈው፡ከኤፉዱ፡ቋድ፡በላይ፡እንዲኾን፥ከኤፉዱም፡እንዳይለይ፡የደረቱን፡ ኪስ፡ከቀለበቶቹ፡ጋራ፡ወደኤፉዱ፡ቀለበቶች፡በሰማያዊ፡ፈትል፡አሰሩት።
22፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥የኤፉዱን፡ቀሚስ፡ሞላውን፡በሸማኔ፡ሥራ፡ሰማያዊ፡አደረገው።
23፤በቀሚሱም፡መካከል፡ዐንገትጌ፡ነበረ፤እንዳይቀደድም፡እንደ፡ጥሩር፡የተሠራ፡ጥልፍ፡በዐንገትጌው፡ዙሪያ ፡ነበረ።
24፤በቀሚሱም፡ታችኛ፡ዘርፍ፡ከሰማያዊ፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፥ከተፈተለ፡በፍታም፡ሮማኖች፡አደረጉ።
25፤ከጥሩ፡ወርቅም፡ሻኵራዎችን፡ሠሩ፥ሻኵራዎቹንም፡ከሮማኖች፡መካከል፡በቀሚሱ፡ዘርፍ፡ዙሪያ፡አደረጉ።
26፤በቀሚሱ፡ዘርፍ፡ዙሪያ፡ሻኵራንና፡ሮማንን፥ሻኵራንና፡ሮማንን፡ለማገልገል፡አደረጉ።
27፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥እንደ፡ሸማኔ፡ሥራ፡ከጥሩ፡በፍታ፡ለአሮንና፡ለልጆቹ፡የደረት፡ልብሶ ችን፥
28፤ከጥሩ፡በፍታም፡መጠምጠሚያውን፥ከጥሩ፡በፍታም፡መልካሞቹን፡ቆቦች፥ከተፈተለም፡ከጥሩ፡በፍታ፡የእግር፡ ሱሪዎችን፥
29፤ከተፈተለም፡ከጥሩ፡በፍታ፥ከሰማያዊም፡ከሐምራዊም፡ከቀይም፡ግምጃ፡በጥልፍ፡አሠራር፡የተሠራ፡መታጠቂያ ውን፡አደረጉ።
30፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥ከጥሩ፡ወርቅ፡የተቀደሰውን፡የአክሊል፡ምልክት፡ሠሩ፤በርሱም፡እንደ ፡ማኅተም፡ቅርጽ፡አድርገው።ቅድስና፡ለእግዚአብሔር፡የሚል፡ጻፉበት።
31፤በመጠምጠሚያውም፡ላይ፡ያንጠለጥሉት፡ዘንድ፡ሰማያዊውን፡ፈትል፡አሰሩበት።
32፤እንዲሁም፡የመገናኛው፡ድንኳን፡የማደሪያው፡ሥራ፡ዅሉ፡ተጨረሰ።እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡ዅሉ ፡የእስራኤል፡ልጆች፡አደረጉ፤እንዲሁ፡አደረጉ።
33፤ማደሪያውንም፥ድንኳኑንም፥ዕቃውንም፡ዅሉ፡ወደ፡ሙሴ፡አመጡ፤መያዣዎቹን፥ሳንቃዎቹን፥መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹንም፥እግሮቹንም፤
34፤ከቀይ፡ከአውራ፡በግ፡ቍርበትም፡የተሠራ፡መደረቢያ፥ከአቍስጣ፡ቍርበትም፡የተሠራ፡መደረቢያ፥የሚሸፍነው ንም፡መጋረጃ፤
35፤የምስክሩንም፡ታቦት፥መሎጊያዎቹንም፥የስርየት፡መክደኛውንም፤
36፤ገበታውንም፥ዕቃውንም፡ዅሉ፥የገጹንም፡ኅብስት፤
37፤ጥሩውንም፡መቅረዝ፥መብራቶቹንም፥በተራ፡የሚኾኑትንም፡ቀንዲሎች፥ዕቃውንም፡ዅሉ፥የመብራቱንም፡ዘይት፤
38፤የወርቁንም፡መሠዊያ፥የቅብዓቱንም፡ዘይት፥ጣፋጩንም፡ዕጣን፥የድንኳኑንም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፤
39፤የናሱንም፡መሠዊያ፥የናሱንም፡መከታ፥መሎጊያዎቹንም፥ዕቃውንም፡ዅሉ፥የመታጠቢያውን፡ሰንም፡መቀመጫውን ም፤
40፤የአደባባዩንም፡መጋረጃዎች፥ምሰሶዎቹንም፥እግሮቹንም፥የአደባባዩንም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፥አውታሮቹንም፥ካ ስማዎቹንም፥ለመገናኛው፡ድንኳን፡ለማደሪያው፡ማገልገያ፡የሚኾኑን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፤
41፤በመቅደስ፡ውስጥ፡ለማገልገል፡በብልኀት፡የተሠሩትን፡ልብሶች፥በክህነትም፡ያገለግሉበት፡ዘንድ፡የተቀደ ሱትን፡የካህኑን፡የአሮንን፡ልብሶች፥የልጆቹንም፡ልብሶች፡አመጡ።
42፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ሥራውን፡ዅሉ፡ሠሩ።
43፤ሙሴም፡ሥራውን፡ዅሉ፡አየ፥እንሆም፡አድርገውት፡ነበር፤እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡አድርገውት፡ ነበር፤ሙሴም፡ባረካቸው።
_______________ኦሪት፡ዘጸአት፥ምዕራፍ፡40።______________
ምዕራፍ፡40።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረው፦
2፤ከመዠመሪያው፡ወር፡በፊተኛው፡ቀን፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡ማደሪያ፡ትተክላለኽ።
3፤በርሱም፡ውስጥ፡የምስክሩን፡ታቦት፡ታኖራለኽ፥ታቦቱንም፡በመጋረጃ፡ትጋርዳለኽ።
4፤ገበታውንም፡አግብተኽ፡በርሱ፡ላይ፡የሚኖረውን፡ዕቃ፡ታሰናዳለኽ፤መቅረዙንም፡አግብተኽ፡ቀንዲሎቹን፡ት ለኵሳለኽ።
5፤ለዕጣንም፡የሚኾነውን፡የወርቅ፡መሠዊያ፡በምስክሩ፡ታቦት፡ፊት፡ታኖራለኽ፥በማደሪያውም፡ደጃፍ፡ፊት፡መ ጋረጃውን፡ትጋርዳለኽ።
6፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነውንም፡መሠዊያ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡በማደሪያው፡ደጅ፡ፊት፡ታኖረዋለኽ።
7፤የመታጠቢያውን፡ሰንም፡በመገናኛው፡ድንኳንና፡በመሠዊያው፡መካከል፡አኑረኽ፡ውሃ፡ትጨምርበታለኽ።
8፤በዙሪያውም፡አደባባዩን፡ትተክላለኽ፥የአደባባዩንም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፡ትዘረጋለኽ።
9፤የቅብዓቱንም፡ዘይት፡ወስደኽ፡ማደሪያውን፡በርሱም፡ያለውን፡ዅሉ፡ትቀባለኽ፥ርሱንም፡ዕቃውንም፡ዅሉ፡ት ቀድሳለኽ፤ቅዱስም፡ይኾናል።
10፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነውንም፡መሠዊያ፡ዕቃውንም፡ዅሉ፡ትቀባዋለኽ፥መሠዊያውንም፡ትቀድሳለኽ፤መሠ ዊያውም፡ቅድስተ፡ቅዱሳን፡ይኾናል።
11፤የመታጠቢያውን፡ሰንና፡መቀመጫውን፡ቀብተኽ፡ትቀድሳለኽ።
12፤አሮንንና፡ልጆቹንም፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡አቅርበኽ፡በውሃ፡ታጥባቸዋለኽ።
13፤የተቀደሰውንም፡ልብስ፡አሮንን፡ታለብሰዋለኽ፤በክህነትም፡ያገለግለኝ፡ዘንድ፡ቀብተኽ፡ትቀድሰዋለኽ።
14፤ልጆቹንም፡አቅርበኽ፡የደረት፡ልብሶችን፡ታለብሳቸዋለኽ፤
15፤በክህነትም፡ያገለግሉኝ፡ዘንድ፡አባታቸውን፡እንደ፡ቀባኽ፡ትቀባቸዋለኽ፤መቀባታቸውም፡ለልጅ፡ልጃቸው፡ ለዘለዓለም፡ክህነት፡ይኾንላቸዋል።
16፤ሙሴም፡እንዲሁ፡አደረገ፤እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገ።
17፤እንዲህም፡ኾነ፤በኹለተኛው፡ዓመት፡በፊተኛው፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ማደሪያው፡ተተከለ።
18፤እግዚአብሔርም፡እንዳዘዘው፡ሙሴ፡ማደሪያውን፡ተከለ፥እግሮቹንም፡አኖረ፥ሳንቃዎቹንም፡አቆመ፥መወርወሪ ያዎቹንም፡አደረገባቸው፥ምሰሶዎቹንም፡አቆመ።
19፤ድንኳኑንም፡በማደሪያው፡ላይ፡ዘረጋ፥የድንኳኑን፡መደረቢያ፡በላዩ፡አደረገበት።
20፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡ጽላቱን፡ወስዶ፡በታቦቱ፡ውስጥ፡አኖረው፥መሎጊያዎቹን፡በታቦቱ፡ዘን ድ፡አደረገ፥የስርየት፡መክደኛውንም፡በታቦቱ፡ላይ፡አኖረው፤
21፤ታቦቱን፡ወደ፡ማደሪያው፡አገባ፥የሚሸፍነውንም፡መጋረጃ፡አድርጎ፡የምስክሩን፡ታቦት፡ሸፈነ።
22፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡ገበታውን፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፥ከመጋረጃው፡ውጭ፥በማደሪያው ፡በሰሜን፡በኩል፡አኖረው፤
23፤እንጀራውን፡በላዩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አሰናዳ።
24፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡መቅረዙን፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፥በገበታው፡ፊት፡ለፊት፥በማደ ሪያው፡በደቡብ፡በኩል፡አኖረ፤
25፤ቀንዲሎቹን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለኰሰ።
26፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡የወርቁን፡መሠዊያ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡በመጋረጃው፡ፊት፡አ ኖረ፤
27፤የጣፋጩን፡ሽቱ፡ዕጣን፡ዐጠነበት።
28፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡በማደሪያው፡ደጃፍ፡ፊት፡መጋረጃውን፡ዘረጋ።
29፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡መሠዊያ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡በማደሪያው፡ደጅ፡ፊት፡አኖረ፥የሚቃጠለ ውንና፡የእኽልን፡መሥዋዕት፡ሠዋበት።
30፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡የመታጠቢያውን፡ሰን፡በመገናኛው፡ድንኳንና፡በመሠዊያው፡መካከል፡አ ኖረ፥ለመታጠቢያም፡ውሃን፡ጨመረበት።
31፤በርሱም፡ሙሴና፡አሮን፡ልጆቹም፡እጆቻቸውንና፡እግሮቻቸውን፡ታጠቡ፤
32፤ወደመገናኛው፡ድንኳን፡በገቡ፡ጊዜ፥ወደ፡መሠዊያውም፡በቀረቡ፡ጊዜ፡ይታጠቡ፡ነበር።
33፤በማደሪያውና፡በመሠዊያውም፡ዙሪያ፡አደባባዩን፡ተከለ፤የአደባባዩንም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፡ዘረጋ።እንዲሁም ፡ሙሴ፡ሥራውን፡ፈጸመ።
34፤ደመናውም፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡ከደነ፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ማደሪያውን፡ሞላ።
35፤ደመናውም፡በላዩ፡ስለ፡ነበረ፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ማደሪያውን፡ስለ፡ሞላ፥ሙሴ፡ወደመገናኛው፡ድንኳ ን፡ይገባ፡ዘንድ፡አልቻለም።
36፤ደመናውም፡ከማደሪያው፡በተነሣ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡በመንገዳቸው፡ዅሉ፡ይጓዙ፡ነበር።
37፤ደመናው፡ባይነሣ፡እስከሚነሣበት፡ቀን፡ድረስ፡አይጓዙም፡ነበር።
38፤በመንገዳቸውም፡ዅሉ፡በእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ፊት፡የእግዚአብሔር፡ደመና፡በማደሪያው፡ላይ፡በቀን፡ነበረ ና፥እሳትም፡በሌሊት፡በዚያ፡ላይ፡ነበረና፨

http://www.gzamargna.net