መዝሙረ፡ዳዊት።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________መዝሙር፡1።______________
1፤ምስጉን፡ነው፡በክፉዎች፡ምክር፡ያልኼደ፥በኀጢአተኛዎችም፡መንገድ፡ያልቆመ፥በዋዘኛዎችም፡ወንበር፡ያልተቀ መጠ።
2፤ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ሕግ፡ደስ፡ይለዋል፥ሕጉንም፡በቀንና፡በሌሊት፡ያስባል።
3፤ርሱም፡በውሃ፡ፈሳሾች፡ዳር፡እንደ፡ተተከለች፥ፍሬዋን፡በየጊዜዋ፡እንደምትሰጥ፥ቅጠሏም፡እንደማይረግፍ፡ዛ ፍ፡ይኾናል፤የሚሠራውም፡ዅሉ፡ይከናወንለታል።
4፤ክፉዎች፡እንዲህ፡አይደሉም፥ነገር፡ግን፥ነፋስ፡ጠርጎ፡እንደሚወስደው፡ትቢያ፡ናቸው።
5፤ስለዚህ፥ክፉዎች፡በፍርድ፥ኀጢአተኛዎችም፡በጻድቃን፡ማኅበር፡አይቆሙም።
6፤እግዚአብሔር፡የጻድቃንን፡መንገድ፡ያውቃልና፥የክፉዎች፡መንገድ፡ግን፡ትጠፋለች።
_______________መዝሙር፡2።______________
1፤አሕዛብ፡ለምን፡ያጕረመርማሉ፧ወገኖችስ፡ለምን፡ከንቱን፡ይናገራሉ፧
2፤የምድር፡ነገሥታት፡ተነሡ፥አለቃዎችም፡በእግዚአብሔርና፡በመሲሑ፡ላይ፡እንዲህ፡ሲሉ፡ተማከሩ።
3፤ማሰሪያቸውን፡እንበጥስ፥ገመዳቸውንም፡ከእኛ፡እንጣል።
4፤በሰማይ፡የሚኖር፡ርሱ፡ይሥቃል፥ጌታም፡ይሣለቅባቸዋል።
5፤በዚያን፡ጊዜ፡በቍጣው፡ይናገራቸዋል፥በመዓቱም፡ያውካቸዋል።
6፤እኔ፡ግን፡ንጉሤን፡ሾምኹ፡በተቀደሰው፡ተራራዬ፡በጽዮን፡ላይ።
7፤ትእዛዙን፡እናገራለኹ፤እግዚአብሔር፡አለኝ፦አንተ፡ልጄ፡ነኽ፥እኔ፡ዛሬ፡ወለድኹኽ።
8፤ለምነኝ፥አሕዛብን፡ለርስትኽ፡የምድርንም፡ዳርቻ፡ለግዛትኽ፡እሰጥኻለኹ።
9፤በብረት፡በትር፡ትጠብቃቸዋለኽ፥እንደ፡ሸክላ፡ሠሪ፡ዕቃዎች፡ትቀጠቅጣቸዋለኽ።
10፤አኹንም፡እናንት፡ነገሥታት፥ልብ፡አድርጉ፤እናንት፡የምድር፡ፈራጆችም፥ተገሠጹ።
11፤ለእግዚአብሔር፡በፍርሀት፡ተገዙ፥በረዓድም፡ደስ፡ይበላችኹ።
12፤ተግሣጹን፡ተቀበሉ፡ጌታ፡እንዳይቈጣ፡እናንተም፡በመንገድ፡እንዳትጠፉ፥ቍጣው፡ፈጥና፡ትነዳ፟ለችና።በርሱ ፡የታመኑ፡ዅሉ፡የተመሰገኑ፡ናቸው።
_______________መዝሙር፡3።______________
ከልጁ፡ከአቤሴሎም፡ፊት፡በሸሸ፡ጊዜ፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥የሚያስጨንቁኝ፡ምንኛ፡በዙ! በእኔ፡ላይ፡የሚቆሙት፡ብዙ፡ናቸው።
2፤ብዙ፡ሰዎች፡ነፍሴን፦አምላክሽ፡አያድንሽም፡አሏት።
3፤አንተ፡ግን፡አቤቱ፥መጠጊያዬ፡ነኽ፥ክብሬንና፡ራሴንም፡ከፍ፡ከፍ፡የምታደርገው፡አንተ፡ነኽ።
4፤በቃሌ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እጮኻለኹ፡ከተቀደሰ፡ተራራውም፡ይሰማኛል።
5፤እኔ፡ተኛኹ፡አንቀላፋኹም፤እግዚአብሔርም፡ደግፎኛልና፥ነቃኹ።
6፤ከሚከቡ፟ኝ፡ከአእላፍ፡ሕዝብ፡አልፈራም።
7፤ተነሥ፥አቤቱ፤አምላኬ፡ሆይ፥አድነኝ፤አንተ፡የጠላቶቼን፡መንጋጋ፡መትተኻልና፥የክፉዎችንም፡ጥርስ፡ሰብረኻ ልና።
8፤ማዳን፡የእግዚአብሔር፡ነው፥በረከትኽም፡በሕዝብኽ፡ላይ፡ነው።
_______________መዝሙር፡4።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡በበገናዎች፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤የጽድቄ፡አምላክ፡በጠራኹት፡ጊዜ፡መለሰልኝ፥በጭንቀቴም፡አሰፋኽልኝ፤ማረኝ፥ጸሎቴንም፡ስማ።
2፤እናንት፡የሰው፡ልጆች፥እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ልባችኹን፡ታከብዳላችኹ፧
3፤እግዚአብሔር፡በጻድቁ፡እንደ፡ተገለጠ፡ዕወቁ፤እግዚአብሔር፡ወደ፡ርሱ፡በተጣራኹ፡ጊዜ፡ይሰማኛል።
4፤ተቈጡ፥ነገር፡ግን፥ኀጢአትን፡አታድርጉ፤በመኝታችኹ፡ሳላችኹ፡በልባችኹ፡ዐስቡ፤ዝም፡በሉ።
5፤የጽድቅን፡መሥዋዕት፡ሠዉ፥በእግዚአብሔርም፡ታመኑ።
6፤በጎውን፡ማን፡ያሳየናል፧የሚሉ፡ብዙ፡ናቸው።አቤቱ፥የፊትኽ፡ብርሃን፡በላያችን፡ታወቀ።
7፤በልቤ፡ደስታን፡ጨመርኽ፤ከስንዴ፡ፍሬና፡ከወይን፡ከዘይትም፡ይልቅ፡በዛ።
8፤በሰላም፡እተኛለኹ፡አንቀላፋለኹም፤አቤቱ፥አንተ፡ብቻኽን፡በእምነት፡አሳድረኸኛልና።
_______________መዝሙር፡5።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡በዋሽንት፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ቃሌን፡አድምጥ፥ጩኸቴንም፡አስተውል፤
2፤የልመናዬን፡ቃል፡አድምጥ፥ንጉሤና፡አምላኬ፡ሆይ፥አቤቱ፥ወዳንተ፡እጸልያለኹና።
3፤በማለዳ፡ድምፄን፡ትሰማለኽ፥በማለዳ፡በፊትኽ፡እቆማለኹ፥እጠብቃለኹም።
4፤አንተ፡በደልን፡የማትወድ፟፡አምላክ፡ነኽና፤ክፉ፡ከአንተ፡ጋራ፡አያድርም።
5፤በከንቱ፡የሚመኩ፡በዐይኖችኽ፡ፊት፡አይኖሩም፤ክፉ፡አድራጊዎችን፡ዅሉ፡ጠላኽ።
6፤ሐሰትን፡የሚናገሩትን፡ታጠፋቸዋለኽ፤ደም፡አፍሳሹንና፡ሸንጋዩን፡ሰው፡እግዚአብሔር፡ይጸየፋል።
7፤እኔ፡ግን፡በምሕረትኽ፡ብዛት፡ወደ፡ቤትኽ፡እገባለኹ፤አንተን፡በመፍራት፡ወደ፡ቅድስናኽ፡መቅደስ፡እሰግዳለ ኹ።
8፤አቤቱ፥ስለ፡ጠላቶቼ፡በጽድቅኽ፡ምራኝ፤መንገዴን፡በፊትኽ፡አቅና።
9፤በአፋቸው፡እውነት፡የለምና፥ልባቸውም፡ከንቱ፡ነው፤ጕረሯቸው፡የተከፈተ፡መቃብር፡ነው፤በምላሳቸው፡ይሸነግ ላሉ።
10፤አቤቱ፥ፍረድባቸው፥በምክራቸውም፡ይውደቁ፤ስለ፡ክፋታቸውም፡ብዛት፡አሳዳ፟ቸው፥እነርሱ፡ዐምፀውብኻልና።
11፤ባንተ፡የሚታመኑት፡ዅሉ፡ግን፡ደስ፡ይላቸዋል፤ለዘለዓለሙ፡ደስ፡ይላቸዋል፥እነርሱንም፡ትጠብቃለኽ፤ስምኽ ንም፡የሚወዱ፡ዅሉ፡ባንተ፡ይመካሉ።
12፤አንተ፡ጻድቁን፡ትባርከዋለኽና፤አቤቱ፥እንደ፡ጋሻ፡በሞገስ፡ከለልኸን።
_______________መዝሙር፡6።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡በበገናዎች፡ስለ፡ስምንተኛ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በቍጣኽ፡አትቅሠፈኝ፥በመዓትኽም፡አትገሥጸኝ።
2፤ድውይ፡ነኝና፡አቤቱ፥ማረኝ፤ዐጥንቶቼ፡ታውከዋልና፥ፈውሰኝ።
3፤ነፍሴም፡እጅግ፡ታወከች፤አንተም፡አቤቱ፥እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ነው፧
4፤አቤቱ፥ተመለስ፡ነፍሴንም፡አድናት፥ስለ፡ቸርነትኽም፡አድነኝ።
5፤በሞት፡የሚያስብኽ፡የለምና፥በሲኦልም፡የሚያመሰግንኽ፡ማን፡ነው፧
6፤በጭንቀቴ፡ደክሜያለኹ፤ሌሊቱን፡ዅሉ፡ዐልጋዬን፡ዐጥባለኹ፥በዕንባዬም፡መኝታዬን፡አርሳለኹ።
7፤ዐይኔ፡ከቍጡ፡ዕንባ፡የተነሣ፡ታወከች፤ከጠላቶቼ፡ዅሉ፡የተነሣ፡አረጀኹ።
8፤ዐመፃን፡የምታደርጉ፡ዅሉ፥ከእኔ፡ራቁ፥እግዚአብሔር፡የልቅሶዬን፡ቃል፡ሰምቷልና።
9፤እግዚአብሔር፡ልመናዬን፡ሰማኝ፤እግዚአብሔር፡ጸሎቴን፡ተቀበለ።
10፤ጠላቶቼ፡ዅሉ፡ይፈሩ፡እጅግም፡ይጐስቍሉ፤ወደ፡ዃላቸው፡ይመለሱ፥በፍጥነትም፡ይፈሩ።
_______________መዝሙር፡7።______________
ስለ፡ብንያማዊ፡ሰው፡ስለኩዝ፡ቃል፡ለእግዚአብሔር፡የዘመረው፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፡አምላኬ፥ባንተ፡ታመንኹ፤ከሚያሳድዱኝ፡ዅሉ፡አድነኝና፡አውጣኝ፥
2፤ነፍሴን፡እንደ፡አንበሳ፡ነጥቀው፡እንዳይሰብሯት፥የሚያድንና፡የሚታደግ፡ሳይኖር።
3፤አቤቱ፡አምላኬ፥እንዲህስ፡ካደረግኹ፥ዐመፃም፡በእጄ፡ቢኖር፥
4፤ክፉ፡ላደረጉብኝም፡ክፉን፡መልሼላቸው፡ብኾን፥ጠላቴንም፡በከንቱ፡ገፍቼው፡ብኾን፥
5፤ጠላት፡ነፍሴን፡ያሳዳ፟ት፡ያግኛትም፥ሕይወቴንም፡በምድር፡ላይ፡ይርገጣት፥ክብሬንም፡በትቢያ፡ላይ፡ያዋርዳ ት።
6፤አቤቱ፥በመዓትኽ፡ተነሥ፥በጠላቶቼ፡ላይ፡በቍጣ፡ተነሣባቸው፤አቤቱ፡አምላኬ፥ባዘዝኸው፡ትእዛዝ፡ንቃ።
7፤የአሕዛብም፡ጉባኤ፡ይከብ፟ኻል፥በእነርሱም፡ላይ፡ወደ፡ከፍታ፡ተመለስ።
8፤እግዚአብሔር፡በአሕዛብ፡ይፈርዳል፤አቤቱ፥እንደ፡ጽድቄ፡ፍረድልኝ፥እንደ፡የዋህነቴም፡ይኹንልኝ።
9፤የኃጥኣን፡ክፋት፡ይጥፋ፥ጻድቁን፡ግን፡አቅና፤እግዚአብሔር፡ልቡናንና፡ኵላሊትን፡ይመረምራል።
10፤እግዚአብሔር፡የጽድቅ፡ጋሻዬ፡ነው፡ልበ፡ቅኖችን፡የሚያድናቸው።
11፤እግዚአብሔር፡የእውነት፡ዳኛ፡ነው፥ኀይለኛም፡ታጋሽም፡ነው፥ዅልጊዜም፡አይቈጣም።
12፤ባትመለሱ፡ግን፡ሰይፉን፡ይስላል፥ቀስቱን፡ገተረ፡አዘጋጀም፤
13፤የሞት፡መሣሪያንም፡አዘጋጀበት፥ፍላጻዎቹንም፡የሚቃጠሉ፡አደረገ።
14፤እንሆ፥በዐመፃ፡ተጨነቀ፡ጕዳትን፡ፀነሰ፡ኀጢአትንም፡ወለደ።
15፤ጕድጓድን፡ማሰ፡ቈፈረም።ባደረገውም፡ጕድጓድ፡ይወድቃል።
16፤ጕዳቱ፡በራሱ፡ይመለሳል፥ዐመፃውም፡በዐናቱ፡ላይ፡ትወርዳለች።
17፤እግዚአብሔርን፡እንደ፡ጽድቁ፡መጠን፡አመሰግናለኹ፥ለልዑል፡እግዚአብሔርም፡ስም፡እዘምራለኹ።
_______________መዝሙር፡8።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡በዋሽንት፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፡ጌታችን፥ስምኽ፡በምድር፡ዅሉ፡እጅግ፡ተመሰገነ፥ምስጋናኽ፡በሰማዮች፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና።
2፤ከሕፃናትና፡ከሚጠቡ፡ልጆች፡አፍ፡ምስጋናን፡አዘጋጀኽ፡ስለ፡ጠላትኽ፥ጠላትንና፡ቂመኛን፡ለማጥፋት።
3፤የጣቶችኽን፡ሥራ፡ሰማዮችን፡ባየኹ፡ጊዜ፥ጨረቃንና፡ከዋክብትን፡አንተ፡የሠራኻቸውን፥
4፤ታስበው፡ዘንድ፡ሰው፡ምንድር፡ነው፧ትጐበኘውም፡ዘንድ፡የሰው፡ልጅ፡ምንድር፡ነው፧
5፤ከመላእክት፡እጅግ፡ጥቂት፡አሳነስኸው፤በክብርና፡በምስጋና፡ዘውድ፡ከለልኸው።
6፤በእጆችኽም፡ሥራ፡ዅሉ፡ላይ፡ሾምኸው፤ዅሉን፡ከእግሮቹ፡በታች፡አስገዛኽለት፥
7፤በጎችንም፡ላሞችንም፡ዅሉ፡ደግሞም፡የምድረ፡በዳውን፡እንስሳዎች፥
8፤የሰማይንም፡ወፎች፡የባሕርንም፡ዓሣዎች፥በባሕር፡መንገድ፡የሚኼደውንም፡ዅሉ፦
9፤አቤቱ፡ጌታችን፥ስምኽ፡በምድር፡ዅሉ፡እጅግ፡ተመሰገነ።
_______________መዝሙር፡9።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በሙትላቤን፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በልቤ፡ዅሉ፡አመሰግንኻለኹ፥ተኣምራትኽንም፡ዅሉ፡እነግራለኹ።
2፤ባንተ፡ደስ፡ይለኛል፥ሐሤትንም፡አደርጋለኹ፤ልዑል፡ሆይ፥ለስምኽ፡እዘምራለኹ።
3፤ጠላቶቼ፡ወደ፡ዃላ፡በተመለሱ፡ጊዜ፥ይሰናከላሉ፡ከፊትኽም፡ይጠፋሉ።
4፤ፍርዴንና፡በቀሌን፡አድርገኽልኛልና፤ጽድቅን፡እየፈረድኽ፡በዙፋንኽ፡ላይ፡ተቀመጥኽ።
5፤አሕዛብን፡ገሠጽኽ፥ዝንጉዎችንም፡አጠፋኽ፥ስማቸውንም፡ለዘለዓለም፡ደመሰስኽ።
6፤ጠላቶች፡በጦር፡ለዘለዓለም፡ጠፉ፥ከተማዎቻቸውንም፡አፈረስኽ፥ዝክራቸውም፡በአንድነት፡ጠፋ።
7፤እግዚአብሔር፡ግን፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፥ዙፋኑንም፡ለመፍረድ፡አዘጋጀ፤
8፤ርሱም፡ዓለምን፡በጽድቅ፡ይፈርዳታል፥አሕዛብንም፡በቅንነት፡ይዳኛቸዋል።
9፤እግዚአብሔርም፡ለድኻዎች፡መጠጊያ፡ኾናቸው፥ርሱም፡በመከራቸው፡ጊዜ፡ረዳታቸው፡ነው።
10፤ስምኽን፡የሚያውቁ፡ዅሉ፡ባንተ፡ይታመናሉ፥አቤቱ፥የሚሹኽን፡አትተዋቸውምና።
11፤በጽዮን፡ለሚኖር፡ለእግዚአብሔር፡ዘምሩ፥በአሕዛብም፡መካከል፡አደራረጉን፡ንገሩ፤
12፤ደማቸውን፡የሚመራመር፡ርሱ፡ዐስቧልና፥የድኻዎችንም፡ጩኸት፡አልረሳምና።
13፤አቤቱ፥ዕዘንልኝ፥ጠላቶቼም፡የሚያመጡብኝን፡መከራ፡እይ፥ከሞት፡ደጆች፡ከፍ፡ከፍ፡የምታደርገኝ፤
14፤ምስጋናውን፡ዅሉ፡እናገር፡ዘንድ፤በጽዮን፡ልጅ፡በደጆቿ፡በማዳንኽ፡ደስ፡ይለኛል።
15፤አሕዛብ፡በሠሩት፡ጕድጓድ፡ወደቁ፥በዚያችም፡በሸሸጓት፡ወጥመድ፡እግራቸው፡ተጠመደች።
16፤እግዚአብሔር፡ፍርድን፡በማድረግ፡የታወቀ፡ነው፤ኀጢአተኛው፡በእጆቹ፡ሥራ፡ተጠመደ።
17፤ኀጢአተኛዎች፡ወደ፡ሲኦል፡ይመለሳሉ፥እግዚአብሔርን፡የሚረሱ፡አሕዛብም፡ዅሉ።
18፤ድኻ፡ለዘለዓለም፡አይረሳምና፥የችግረኛዎችም፡ተስፋቸው፡ለዘለዓለም፡አይጠፋም።
19፤አቤቱ፥ተነሥ፤ሰውም፡አይበርታ፥አሕዛብም፡በፊትኽ፡ይፈረድባቸው።
20፤አቤቱ፥ፍርሀትን፡በላያቸው፡ጫንባቸው፤አሕዛብ፡ሰዎች፡እንደ፡ኾኑ፡ይወቁ።
(መዝሙረ፡10፡በዕብራይስጥ)።
1፤አቤቱ፥ለምን፡ርቀኽ፡ቆምኽ፧በመከራም፡ጊዜ፡ለምን፡ትሰወራለኽ፧
2፤በኀጢአተኛ፡ትዕቢት፡ድኻ፡ይናደዳል፤ባሰቡት፡ተንኰላቸው፡ተጠመዱ።
3፤ኀጢአተኛ፡በነፍሱ፡ፈቃድ፡ይወደሳልና፥ዐመፀኛም፡ይባርካል።
4፤ኀጢአተኛ፡እግዚአብሔርን፡አበሳጨው፥እንደ፡ቍጣውም፡ብዛት፡አይመራመረውም፡በርሱ፡ፊት፡እግዚአብሔር፡የለ ም።
5፤መንገዱ፡ዅሉ፡የረከሰ፡ነው፥ፍርድኽም፡በፊቱ፡የፈረሰ፡ነው፥ጠላቶችንም፡ዅሉ፡ይገዛቸዋል።
6፤በልቡ፡ይላል፦ለልጅ፡ልጅ፡አልታወክም፡ክፉም፡አያገኘኝም።
7፤አፉ፡መርገምንና፡ሽንገላን፡ተንኰልን፡የተመላ፡ነው፤ከምላሱ፡በታች፡ጕዳትና፡መከራ፡ነው።
8፤በመንደሮች፡መሸመቂያ፡ይቀመጣል፡ንጹሓንን፡በስውር፡ይገድል፡ዘንድ፤ዐይኖቹም፡ወደ፡ድኻ፡ይመለከታሉ።
9፤እንደ፡አንበሳ፡በችፍግ፡ዱር፡በስውር፡ይሸምቃል፤ድኻውን፡ለመንጠቅ፡ያደባል፤ድኻውን፡ይነጥቀዋል፡በአሽክ ላውም፡ይስበዋል።
10፤ድኻ፡ይዋረዳል፥ይጐብጣል፤በኀያላኑም፡እጅግ፡ይወድቃል።
11፤በልቡም፡ይላል፦እግዚአብሔር፡ረስቶኛል፤ፈጽሞም፡እንዳያይ፡ፊቱን፡ሰወረ።
12፤አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ተነሥ፡እጅኽም፡ከፍ፡ከፍ፡ትበል፤ድኻዎችን፡አትርሳ።
13፤ኀጢአተኛ፡ስለ፡ምን፡እግዚአብሔርን፡አስቈጣው፧በልቡ፦አይመራመረኝም፡ይላልና።
14፤አየኸው፥አንተ፡ክፋትንና፡ቍጣን፡ትመለከታለኽና፡በእጅኽ፡ፍዳውን፡ለመስጠት፤ድኻ፡ራሱን፡ለአንተ፡ይተዋ ል፥ለድኻ፡አደግም፡ረዳቱ፡አንተ፡ነኽ።
15፤የኀጢአተኛንና፡የክፉን፡ክንድ፡ስበር፥የኀጢአቱንም፡ብድራት፡ክፈል፡ሌላ፡እስከማይገኝ፡ድረስ።
16፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ይነግሣል፤አሕዛብ፡ከምድሩ፡ይጠፋሉ።
17፤እግዚአብሔር፡የድኻዎችን፡ምኞት፡ሰማ፥ዦሮውም፡የልባቸውን፡ዐሳብ፡አደመጠች፥
18፤ፍርዱ፡ለድኻ፡አደግና፡ለችግረኛ፡ይደረግ፡ዘንድ፥ሰዎች፡በምድር፡ላይ፡አፋቸውን፡ከፍ፡ከፍ፡ማድረግ፡እን ዳይደግሙ።
_______________መዝሙር፡10፡(11)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤በእግዚአብሔር፡ታመንኹ፤ነፍሴን፦እንደ፡ወፍ፡ወደ፡ተራራዎች፡ተቅበዝበዢ፡እንዴት፡ትሏታላችኹ፧
2፤ኀጢአተኛዎች፥እንሆ፥ቀስታቸውን፡ገትረዋልና፥ፍላጻቸውንም፡በአውታር፡አዘጋጅተዋልና፥ልበ፡ቅኖችን፡በስው ር፡ይነድፉ፡ዘንድ።
3፤አንተ፡የሠራኸውን፥እንሆ፥እነርሱ፡አፍርሰዋልና፤ጻድቅ፡ግን፡ምን፡አደረገ፧
4፤እግዚአብሔር፡በተቀደሰው፡መቅደሱ፡ነው፤እግዚአብሔር፥ዙፋኑ፡በሰማይ፡ነው፤ዐይኖቹ፡ወደ፡ድኻ፡ይመለከታሉ ፥ቅንድቦቹም፡የሰው፡ልጆችን፡ይመረምራሉ።
5፤እግዚአብሔር፡ጻድቅንና፡ኀጥእን፡ይመረምራል፤ዐመፃን፡የወደዳት፡ግን፡ነፍሱን፡ጠልቷል።
6፤ወጥመድ፡በኃጥኣን፡ላይ፡ያዘንባል፤እሳትና፡ዲን፥ዐውሎ፡ነፋስም፡የጽዋቸው፡ዕድል፡ፈንታ፡ነው።
7፤እግዚአብሔር፡ጻድቅ፡ነውና፥ጽድቅንም፡ይወዳ፟ል፤ቅንነት፡ግን፡ፊቱን፡ታየዋለች።
_______________መዝሙር፡11፡(12)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፥ስለ፡ስምንተኛ፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥አድነኝ፤ደግ፡ሰው፡አልቋልና፥ከሰው፡ልጆችም፡መተማመን፡ጐድሏልና።
2፤ርስ፡በርሳቸው፡ከንቱ፡ነገርን፡ይናገራሉ፤በሽንገላ፡ከንፈር፡ኹለት፡ልብ፡ኾነው፡ይናገራሉ።
3፤የሽንገላን፡ከንፈሮች፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ያጠፋቸዋል፥ታላቅ፡ነገርን፡የምትናገረውን፡ምላስ፤
4፤ምላሳችንን፡እናበረታለን፤ከንፈራችን፡የእኛ፡ነው፥ጌታችን፡ማን፡ነው፧የሚሉትን።
5፤ስለድኻዎች፡መከራ፥ስለችግረኛዎች፡ጩኸት፡እግዚአብሔር፦አኹን፡እነሣለኹ፡ይላል፤መድኀኒትን፡አደርጋለኹ፥ በላዩም፡እገልጣለኹ።
6፤በምድር፡ላይ፡እንደ፡ተፈተነ፡ሰባት፡ጊዜ፡እንደ፡ተጣራ፡ብር።የእግዚአብሔር፡ቃላት፡የነጹ፡ቃላት፡ናቸው።
7፤አቤቱ፥አንተ፡ጠብቀን፥ከዚችም፡ትውልድ፡ለዘለዓለም፡ታደገን።
8፤በሰው፡ልጆች፡ዘንድ፡ምናምንቴ፡ከፍ፡ከፍ፡ባለ፡ጊዜ፡ክፉዎች፡በዙሪያው፡ዅሉ፡ይመላለሳሉ።
_______________መዝሙር፡12፡(13)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥እስከ፡መቼ፡ፈጽመኽ፡ትረሳኛለኽ፧እስከ፡መቼስ፡ፊትኽን፡ከእኔ፡ትሰውራለኽ፧
2፤እስከ፡መቼ፡በነፍሴ፡እመካከራለኹ፧ትካዜስ፡እስከ፡መቼ፡ዅልጊዜ፡ይኾናል፧እስከ፡መቼ፡ጠላቴ፡በላዬ፡ይጓደ ዳል፧
3፤አቤቱ፡አምላኬ፥እየኝ፡ስማኝም፤ጠላቴ።አሸነፍኹት፡እንዳይል፥
4፤የሚያስጨንቁኝም፡እኔ፡ብናወጥ፡ደስ፡እንዳይላቸው፥ለሞትም፡እንዳልተኛ፡ዐይኖቼን፡አብራ።
5፤እኔ፡ግን፡በቸርነትኽ፡ታመንኹ፥ልቤም፡በመድኀኒትኽ፡ደስ፡ይለዋል።
6፤የረዳኝን፡እግዚአብሔርን፡አመሰግናለኹ፥ለልዑል፡እግዚአብሔር፡ስምም፡እዘምራለኹ።
_______________መዝሙር፡13፡(14)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ሰነፍ፡በልቡ፦አምላክ፡የለም፡ይላል።በሥራቸው፡ረከሱ፥ጐሰቈሉ፤በጎ፡ነገርን፡የሚሠራ፡የለም።
2፤የሚያስተውል፡እግዚአብሔርንም፡የሚፈልግ፡እንዳለ፡ያይ፡ዘንድ፥እግዚአብሔር፡ከሰማይ፡የሰው፡ልጆችን፡ተመ ለከተ።
3፤ዅሉ፡ዐመፁ፡በአንድነትም፡ረከሱ፡በጎ፡ነገርን፡የሚሠራ፡የለም፤አንድም፡ስንኳ፡የለም።
4፤ጕረሯቸው፡የተከፈተ፡መቃብር፡ነው፥በምላሳቸው፡ሸነገሉ፤
5፤ከከንፈራቸው፡በታች፡የእባብ፡መርዝ፡አለ፤አፋቸው፡መርገምንና፡መራራን፡ተሞልቷል፤
6፤ደምን፡ለማፍሰስ፡እግራቸው፡ፈጣን፡ነው፤ጥፋትና፡ጕስቍልና፡በመንገዳቸው፡አለ፥የሰላምን፡መንገድ፡አላወቋ ትምና፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡በዐይናቸው፡ፊት፡የለም።
7፤ሕዝቤን፡እንደ፡እንጀራ፡የሚበሉ፡ኀጢአት፡የሚሠሩ፡ዅሉ፡በእውኑ፡አያውቁምን፧እግዚአብሔርንም፡አይጠሩትም ።
8፤በዚያ፡በታላቅ፡ፍርሀት፡እጅግ፡ፈሩ፥እግዚአብሔር፡በጻድቃን፡ትውልድ፡ዘንድ፡ነውና።
9፤የድኻዎችን፡ምክር፡አሳፈራችኹ፥እግዚአብሔር፡ግን፡ተስፋቸው፡ነው።
10፤ከጽዮን፡መድኀኒትን፡ለእስራኤል፡ማን፡ይሰጣል፧እግዚአብሔር፡የሕዝቡን፡ምርኮ፡በመለሰ፡ጊዜ፥ያዕቆብ፡ደ ስ፡ይለዋል፥እስራኤልም፡ሐሤት፡ያደርጋል።
_______________መዝሙር፡14፡(15)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በድንኳንኽ፡ውስጥ፡ማን፡ያድራል፧በተቀደሰውም፡ተራራኽ፡ማን፡ይኖራል፧
2፤በቅንነት፡የሚኼድ፥ጽድቅንም፡የሚያደርግ፥በልቡም፡እውነትን፡የሚናገር።
3፤በአንደበቱ፡የማይሸነግል፥በባልንጀራው፡ላይ፡ክፋትን፡የማያደርግ፥ዘመዶቹንም፡የማይሰድብ።
4፤ኀጢአተኛ፡በፊቱ፡የተናቀ፥እግዚአብሔርንም፡የሚፈሩትን፡የሚያከብር፥ለባልንጀራው፡የሚምል፡የማይከዳም።
5፤ገንዘቡን፡በዐራጣ፡የማያበድር፥በንጹሑ፡ላይ፡መማለጃን፡የማይቀበል።እንዲህ፡የሚያደርግ፡ለዘለዓለም፡አይ ታወክም።
_______________መዝሙር፡15፡(16)።______________
የዳዊት፡ቅኔ።
1፤አቤቱ፥ባንተ፡ታምኛለኹና፡ጠብቀኝ።
2፤እግዚአብሔርን፦አንተ፡ጌታዬ፡ነኽ፡አልኹ፤ከአንተ፡በቀር፡በጎነት፡የለኝም።
3፤ፈቃድኽ፡ዅሉ፡በምድር፡ባሉት፡ቅዱሳንና፡ክቡራን፡ላይ፡ነው።
4፤ወደ፡ሌላ፡ለሚፋጠኑት፡መከራቸው፡ይበዛል፤የቍርባናቸውን፡ደም፡እኔ፡አላፈሰ፟ውም፥ስማቸውንም፡በከንፈሬ፡ አልጠራም።
5፤እግዚአብሔር፡የርስቴ፡ዕድል፡ፈንታና፡ጽዋዬ፡ነው፥ዕጣዬንም፡የምታጠና፡አንተ፡ነኽ።
6፤ገመድ፡ባማረ፡ስፍራ፡ወደቀችልኝ፥ርስቴም፡ተዋበችልኝ።
7፤የመከረኝን፡እግዚአብሔርን፡እባርካለኹ፤ደግሞም፡በሌሊት፡ኵላሊቶቼ፡ይገሥጹኛል።
8፤ዅልጊዜ፡እግዚአብሔርን፡በፊቴ፡አየዋለኹ፤በቀኜ፡ነውና፥አልታወክም።
9፤ስለዚህ፥ልቤን፡ደስ፡አለው፡ምላሴም፡ሐሴት፡አደረገች፤ሥጋዬም፡ደግሞ፡በተስፋ፡ታድራለች፤
10፤ነፍሴን፡በሲኦል፡አትተዋትምና፥ቅዱስኽንም፡መበስበስን፡ያይ፡ዘንድ፡አትተወውም።
11፤የሕይወትን፡መንገድ፡አሳየኸኝ፤ከፊትኽ፡ጋራ፡ደስታን፡አጠገብኸኝ፥በቀኝኽም፡የዘለዓለም፡ፍሥሓ፡አለ።
_______________መዝሙር፡16፡(17)።______________
የዳዊት፡ጸሎት።
1፤አቤቱ፥ጽድቄን፡ስማ፡ጩኸቴንም፡አድምጥ፤በተንኰለኛም፡ከንፈር፡ያልኾነውን፡ጸሎቴን፡አድምጥ።
2፤ፍርዴ፡ከፊትኽ፡ይውጣ፥ዐይኖችኽም፡በቅንነት፡ይዩ።
3፤ልቤን፡ፈተንኸው፡በሌሊትም፡ጐበኘኸኝ፤ፈተንኸኝ፥ምንም፡አላገኘኽብኝም።
4፤የሰውን፡ሥራ፡አፌ፡እንዳይናገር፡ፈቃዴ፡ነው፤ስለከንፈሮችኽ፡ቃል፡ጭንቅ፡የኾኑ፡መንገዶችን፡ጠበቅኹ።
5፤እግሮች፡እንዳይናወጡ፡አረማመዴን፡በመንገድኽ፡አጽና።
6፤አቤቱ፥ሰምተኸኛልና፥ወዳንተ፡ጠራኹ፤ዦሮኽን፡ወደ፡እኔ፡አዘንብል፥ቃሌንም፡ስማ።
7፤የሚያምኑኽን፡ከሚቃወሙ፡በቀኝኽ፡የምታድናቸው፥ቸርነትኽን፡ድንቅ፡አድርገኽ፡ግለጠው።
8፤እንደ፡ዐይን፡ብሌን፡ጠብቀኝ፥በክንፎችኽ፡ጥላ፡ሰውረኝ፥
9፤ከሚያስጨንቁኝ፡ከኀጢአተኛዎች፥ነፍሴንም፡ከሚከቧ፟ት፡ከጠላቶቼ።
10፤አንዠታቸውን፡በስብ፡ቋጠሩ፥በአፋቸውም፡ትንቢትን፡ተናገሩ።
11፤አኹንም፡ርምጃችንን፡ከበቡ፤ዐይናቸውን፡ወደ፡ምድር፡ዝቅ፡ዝቅ፡አደረጉ።
12፤ርሱ፡ንጥቂያን፡እንደሚናፍቅ፡አንበሳ፡ተሸጕጦም፡እንደሚኖር፡እንደ፡አንበሳ፡ደቦል፡ነው።
13፤አቤቱ፥ተነሥ፤ቀድመኽ፡ወደ፡ታች፡ጣለው፤ነፍሴን፡ከኀጢአተኛ፡በሰይፍኽ፡አድናት።
14፤አቤቱ፥ከሰዎች፥ዕድል፡ፈንታቸው፡በሕይወታቸው፡ከኾነች፡ከዚህ፡ዓለም፡ሰዎች፡በእጅኽ፡አድነኝ፤ከሰወርኸ ው፡መዝገብኽ፡ሆዳቸውን፡አጠገብኽ፤ልጆቻቸው፡ብዙ፡ናቸው፡የተረፋቸውንም፡ለሕፃናታቸው፡ያተርፋሉ።
15፤እኔ፡ግን፡በጽድቅ፡ፊትኽን፡አያለኹ፤ክብርኽን፡ሳይ፡እጠግባለኹ።
_______________መዝሙር፡17፡(18)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡ከሳኦል፡እጅና፡ከጠላቶቹ፡ዅሉ፡እጅ፡እግዚአብሔር፡ባዳነው፡ቀን፡በዚህ፡መዝሙር፡ቃል፡ለ እግዚአብሔር፡የተናገረው፡የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡የዳዊት፡መዝሙር።እንዲህም፡አለ፦
1፤አቤቱ፡ጕልበቴ፡ሆይ፥እወድ፟ኻለኹ።
2፤እግዚአብሔር፡አለቴ፥ዐምባዬ፥መድኀኒቴ፥አምላኬ፥በርሱም፡የምተማመንበት፡ረዳቴ፥መታመኛዬና፡የደኅንነቴ፡ ቀንድ፡መጠጊያዬም፡ነው።
3፤ምስጋና፡የሚገ፟ባ፟ውን፡እግዚአብሔርን፡እጠራለኹ፥ከጠላቶቼም፡እድናለኹ።
4፤የሞት፡ጣር፡ያዘኝ፥የዐመፅ፡ፈሳሽም፡አስፈራኝ፤
5፤የሲኦል፡ጣር፡ከበበኝ፤የሞት፡ወጥመድም፡ደረሰብኝ።
6፤በጨነቀኝ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡ጠራኹት፥ወደ፡አምላኬም፡ጮኽኹ፤ከመቅደሱም፡ቃሌን፡ሰማኝ፥ጩኸቴም፡በፊቱ፡ ወደ፡ዦሮው፡ገባ።
7፤ምድርም፡ተንቀጠቀጠች፡ተናወጠችም፥የተራራዎችም፡መሠረቶች፡ተነቃነቁ፥እግዚአብሔርም፡ተቈጥቷልና፥ተንቀጠ ቀጡ።
8፤ከቍጣው፡ጢስ፡ወጣ፥ከፊቱም፡የሚበላ፡እሳት፡ነደደ፤ፍምም፡ከርሱ፡በራ።
9፤ሰማዮችን፡ዝቅ፡ዝቅ፡አደረገ፡ወረደም፥ጨለማ፡ከእግሩ፡በታች፡ነበረ።
10፤በኪሩቤልም፡ላይ፡ተቀምጦ፡በረረ፥በነፋስም፡ክንፍ፡በረረ።
11፤መሰወሪያውን፡ጨለማ፡አደረገ፤በዙሪያውም፡ድንኳኑ፤በደመናት፡ውስጥ፡የጨለማ፡ውሃ፡ነበረ።
12፤በፊቱ፡ካለው፡ብርሃን፡የተነሣ፡ደመናትና፡በረዶ፡የእሳት፡ፍምም፡ዐለፉ።
13፤እግዚአብሔርም፡ከሰማያት፡አንጐደጐደ፥ልዑልም፡ቃሉን፡ሰጠ።
14፤ፍላጻውን፡ላከ፡በተናቸውም፤መብረቆችን፡አበዛ፡አወካቸውም።
15፤አቤቱ፥ከዘለፋኽ፡ከመዓትኽም፡መንፈስ፡እስትንፋስ፡የተነሣ፥የውሃዎች፡ምንጮች፡ታዩ፥የዓለም፡መሠረቶችም ፡ተገለጡ።
16፤ከላይ፡ሰደደ፡ወሰደኝም፥ከብዙ፡ውሃዎችም፡አወጣኝ።
17፤ከብርቱዎች፡ጠላቶቼ፡ከሚጠሉኝም፡አዳነኝ፥በርትተውብኝ፡ነበርና።
18፤በመከራዬ፡ቀን፡ደረሱብኝ፤እግዚአብሔር፡ግን፡ደገፋዬ፡ኾነ።
19፤ወደ፡ሰፊ፡ስፍራም፡አወጣኝ፤ወዶ፟ኛልና፥አዳነኝ።
20፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ጽድቄ፡ይከፍለኛል፤እንደ፡እጄ፡ንጽሕና፡ይመልስልኛል።
21፤የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡ጠብቄያለኹና፥በአምላኬም፡አላመፅኹም።
22፤ፍርዱ፡ዅሉ፡በፊቴ፡ነበረና፥ሥርዐቱንም፡ከፊቴ፡አላራቅኹም።
23፤በርሱ፡ዘንድ፡ቅን፡ነበርኹ፥ከኀጢአቴም፡ተጠበቅኹ።
24፤እግዚአብሔርም፡እንደ፡ጽድቄ፡እንደ፡እጄም፡ንጽሕና፡በዐይኖቹ፡ፊት፡መለሰልኝ።
25፤ከቸር፡ሰው፡ጋራ፡ቸር፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ፤ከቅን፡ሰው፡ጋራ፡ቅን፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ፤
26፤ከንጹሕ፡ጋራ፡ንጹሕ፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ፤ከጠማማም፡ጋራ፡ጠማማ፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ።
27፤አንተ፡የተጠቃውን፡ሕዝብ፡ታድናለኽና፥የትዕቢተኛዎችን፡ዐይን፡ግን፡ታዋርዳለኽ።
28፤አንተ፡መብራቴን፡ታበራለኽና፤እግዚአብሔር፡አምላኬ፡ጨለማዬን፡ያበራል።
29፤ባንተ፡ከጥፋት፡እድናለኹና፡በአምላኬም፡ቅጥሩን፡እዘላ፟ለኹ።
30፤የአምላኬ፡መንገድ፡ፍጹም፡ነው፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡የነጠረ፡ነው፥በርሱ፡ለሚታመኑት፡ዅሉ፡ጋሻ፡ነው።
31፤ከእግዚአብሔር፡በቀር፡አምላክ፡ማን፡ነው፧ከአምላካችን፡በቀር፡አምላክ፡ማን፡ነው፧
32፤ኀይልን፡የሚያስታጥቀኝ፡መንገዴንም፡የሚያቃና፥
33፤እግሮቼን፡እንደ፡ብሖር፡እግሮች፡የሚያረታ፡በኰረብታዎችም፡የሚያቆመኝ፡እግዚአብሔር፡ነው።
34፤እጆቼን፡ሰልፍ፡ያስተምራል፥በክንዴም፡የናስ፡ቀስት፡እገትራለኹ።
35፤ለደኅንነቴም፡መታመኛን፡ሰጠኸኝ፥ቀኝኽም፡ትረዳኛለች፥ትምህርትኽም፡ለዘለዓለም፡ታጠናኛለች፥ተግሣጽኽም ፡ታስተምረኛለች።
36፤አረማመዴን፡በበታቼ፡አሰፋኽ፥እግሮቼም፡አልተንሸራተቱም።
37፤ጠላቶቼን፡አሳድዳቸዋለኹ፡እይዛቸዋለኹም፥እስካጠፋቸውም፡ድረስ፡አልመለስም።
38፤አስጨንቃቸዋለኹ፡መቆምም፡አይችሉም፥ከእግሬም፡በታች፡ይወድቃሉ።
39፤ለሰልፍም፡ኀይልን፡ታስታጥቀኛለኽ፤በበላዬ፡የቆሙትን፡ዅሉ፡በበታቼ፡ታስገዛቸዋለኽ።
40፤የጠላቶቼን፡ዠርባ፡ሰጠኸኝ፥የሚጠሉኝንም፡አጠፋኻቸው።
41፤ጮኹ፡የሚረዳቸውም፡አልነበረም፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጮኹ፡አልሰማቸውም።
42፤እንደ፡ትቢያ፡በነፋስ፡ፊት፡እፈጫቸዋለኹ፥እንደ፡አደባባይም፡ጭቃ፡እረግጣቸዋለኹ።
43፤ከሕዝብ፡ክርክር፡ታድነኛለኽ፥የአሕዛብም፡ራስ፡አድርገኽ፡ትሾመኛለኽ፥የማላውቀው፡ሕዝብም፡ይገዛልኛል።
44፤በዦሮ፡ሰምተው፡ተገዙልኝ፤የባዕድ፡ልጆች፡ደለሉኝ።
45፤የባዕድ፡ልጆች፡አረጁ፥በመንገዳቸውም፡ተሰናከሉ።
46፤እግዚአብሔር፡ሕያው፡ነው፥አምላኬም፡ቡሩክ፡ነው፥የመድኀኒቴም፡አምላክ፡ከፍ፡ከፍ፡ይበል።
47፤በቀሌን፡የሚመልስልኝ፡አምላክ፡አሕዛብን፡በበታቼ፡ያስገዛልኛል።
48፤ከጠላቶቼ፡የሚታደገኝ፡ርሱ፡ነው፤በእኔም፡ላይ፡ከቆሙ፡ከፍ፡ከፍ፡ታደርገኛለኽ፥ከግፈኛ፡ሰው፡ታድነኛለኽ ።
49፤አቤቱ፥ስለዚህ፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡አመሰግንኻለኹ፥ለስምኽም፡እዘምራለኹ።
50፤የንጉሡን፡መድኀኒት፡ታላቅ፡ያደርጋል፥ቸርነቱንም፡ለቀባው፡ለዳዊትና፡ለዘሩ፡ለዘለዓለም፡ይሰጣል።
_______________መዝሙር፡18፡(19)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ሰማያት፡የእግዚአብሔርን፡ክብር፡ይናገራሉ፥የሰማይም፡ጠፈር፡የእጁን፡ሥራ፡ያወራል።
2፤ቀን፡ለቀን፡ነገርን፡ታወጣለች፥ሌሊትም፡ለሌሊት፡ዕውቀትን፡ትናገራለች።
3፤ነገር፡የለም፡መናገርም፡የለም፥ድምፃቸውም፡አይሰማም።
4፤ድምፃቸው፡ወደ፡ምድር፡ዅሉ፥ቃላቸውም፡እስከዓለም፡ዳርቻ፡ወጣ።
5፤በእነርሱም፡ውስጥ፡የፀሓይን፡ድንኳን፡አደረገ፥ርሱም፡እንደ፡ሙሽራ፡ከዕልፍኙ፡ይወጣል፤እንደ፡ዐርበኛ፡በ መንገዱ፡ለመሮጥ፡ደስ፡ይለዋል።
6፤አወጣጡ፡ከሰማያት፡ዳርቻ፡ነው፥ዙረቱም፡እስከ፡ዳርቻቸው፡ነው፤ከትኵሳቱም፡የሚሰወር፡የለም።
7፤የእግዚአብሔር፡ሕግ፡ፍጹም፡ነው፤ነፍስን፡ይመልሳል፤የእግዚአብሔር፡ምስክር፡የታመነ፡ነው፤ሕፃናትን፡ጠቢ ባን፡ያደርጋል።
8፤የእግዚአብሔር፡ሥርዐት፡ቅን፡ነው፥ልብንም፡ደስ፡ያሠኛል፤የእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ብሩህ፡ነው፥ዐይንንም፡ ያበራል።
9፤የእግዚአብሔር፡ፍርሀት፡ንጹሕ፡ነው፤ለዘለዓለም፡ይኖራል፤የእግዚአብሔር፡ፍርድ፡እውነትና፡ቅንነት፡በአን ድነት፡ነው።
10፤ከወርቅና፡ከክቡር፡ዕንቍ፡ይልቅ፡ይወደዳል፤ከማርና፡ከማር፡ወለላም፡ይጣፍጣል።
11፤ባሪያኽ፡ደግሞ፡ይጠብቀዋል፤በመጠበቁም፡እጅግ፡ይጠቀማል።
12፤ስሕተትን፡ማን፡ያስተውላታል፧ከተሰወረ፡ኀጢአት፡አንጻኝ።
13፤የድፍረት፡ኀጢአት፡እንዳይገዛኝ፡ባሪያኽን፡ጠብቅ፤የዚያን፡ጊዜ፡ፍጹም፡እኾናለኹ፥ከታላቁም፡ኀጢአት፡እ ነጻለኹ።
14፤አቤቱ፥ረድኤቴ፡መድኀኒቴም፥የአፌ፡ቃልና፡የልቤ፡ዐሳብ፡በፊትኽ፡ያማረ፡ይኹን።
_______________መዝሙር፡19፡(20)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤በመከራ፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ይስማኽ፤የያዕቆብ፡አምላክ፡ስም፡ያቁምኽ።
2፤ከመቅደሱ፡ረድኤትን፡ይላክልኽ፥ከጽዮንም፡ያጥናኽ።
3፤ቍርባንኽን፡ዅሉ፡ያስብልኽ፤የሚቃጠል፡መሥዋዕትኽን፡ያለምልምልኽ።
4፤እንደ፡ልብኽ፡ይስጥኽ፡ፈቃድኽንም፡ዅሉ፡ይፈጽምልኽ።
5፤በማዳንኽ፡ደስ፡ይለናል፤በአምላካችን፡ስም፡ከፍ፡ከፍ፡እንላለን፤ልመናኽን፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ይፈጽምልኽ ።
6፤እግዚአብሔር፡የቀባውን፡እንዳዳነው፡ዛሬ፡ዐወቅኹ፤ከሰማይ፡መቅደሱ፡ይመልስለታል፤በቀኙ፡ብርታት፡ማዳን።
7፤እነዚያ፡በሠረገላ፡እነዚያም፡በፈረስ፡ይታመናሉ፤እኛ፡ግን፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ከፍ፡ከፍ፡ እንላለን።
8፤እነርሱ፡ተሰነካክለው፡ወደቁ፤እኛ፡ግን፡ተነሣን፥ጸንተንም፡ቆምን።
9፤አቤቱ፥ንጉሥን፡አድነው፥በጠራንኽም፡ቀን፡ስማን።
_______________መዝሙር፡20፡(21)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በኀይልኽ፡ንጉሥ፡ደስ፡ይለዋል፤በማዳንኽ፡እጅግ፡ሐሤትን፡ያደርጋል።
2፤የልቡን፡ፈቃድ፡ሰጠኸው፥የከንፈሩንም፡ልመና፡አልከለከልኸውም።
3፤በበጎ፡በረከት፡ደርሰኽለታልና፤ከክቡር፡ዕንቍ፡የኾነ፡ዘውድን፡በራሱ፡ላይ፡አኖርኽ።
4፤ሕይወትን፡ለመነኽ፡ሰጠኸውም፥ለረዥም፡ዘመን፡ለዘለዓለሙ።
5፤በማዳንኽ፡ክብሩ፡ታላቅ፡ነው፤ክብርንና፡ምስጋናን፡ጨመርኽለት።
6፤የዘለዓለም፡በረከትን፡ሰጥተኸዋልና።በፊትኽም፡ደስታ፡ደስ፡ታሠኘዋለኽ።
7፤ንጉሥ፡በእግዚአብሔር፡ተማምኗልና፥በልዑልም፡ምሕረት፡አይናወጥም።
8፤እጅኽ፡ጠላቶችኽን፡ዅሉ፡ታግኛቸው፥ቀኝኽም፡የሚጠሉኽን፡ዅሉ፡ታግኛቸው።
9፤በተቈጣኽም፡ጊዜ፡እንደ፡እሳት፡እቶን፡አድርጋቸው፤እግዚአብሔር፡በቍጣው፡ያጠፋቸዋል፥እሳትም፡ትበላቸዋለ ች።
10፤ፍሬያቸውን፡ከምድር፡ዘራቸውንም፡ከሰው፡ልጆች፡ታጠፋለኽ።
11፤ክፋትን፡ባንተ፡ላይ፡ዘርግተዋልና፥የማይቻላቸውንም፡ምክር፡ዐሰቡ።
12፤ወደ፡ዃላቸው፡ትመልሳቸዋለኽ፤ፍላጻን፡በፊታቸው፡ላይ፡ታዘጋጃለኽ።
13፤አቤቱ፥በኀይልኽ፡ከፍ፡ከፍ፡በል፤ጽናትኽንም፡እናመሰግናለን፡እንዘምርማለን።
_______________መዝሙር፡21፡(22)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡ስለንጋት፡ኀይል፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አምላኬ፥አምላኬ፥ለምን፡ተውኸኝ፧እኔን፡ከማዳንና፡ከጩኸቴ፡ቃል፡ሩቅ፡ነኽ።
2፤አምላኬ፥በቀን፡ወዳንተ፡እጠራለኹ፥አልመለስኽልኝም፤በሌሊትም፡እንኳ፡ዕረፍት፡የለኝም።
3፤በእስራኤል፡የተመሰገንኽ፡አንተ፡ግን፡በቅድስና፡ትኖራለኽ።
4፤አባቶቻችን፡አንተን፡ተማመኑ፥ተማመኑ፡አንተም፡አዳንኻቸው።
5፤ወዳንተ፡ጮኹ፡አመለጡም፥አንተንም፡ተማመኑ፡አላፈሩም።
6፤እኔ፡ግን፡ትል፡ነኝ፡ሰውም፡አይደለኹም፤የሰው፡ማላገጫ፡በሕዝብም፡ዘንድ፡የተናቅኹ፡ነኝ።
7፤የሚያዩኝ፡ዅሉ፡ይላገዱብኛል፤ራሳቸውን፡እየነቀነቁ፡በከንፈሮቻቸው፡እንዲህ፡ይላሉ።
8፤በእግዚአብሔር፡ተማመነ፥ርሱንም፡ያድነው፤ቢወደ፟ውስ፡ያድነው።
9፤አንተ፡ግን፡ከሆድ፡አውጥተኸኛልና፥በእናቴ፡ጡት፡ሳለኹም፡ባንተ፡ታመንኹ።
10፤ከማሕፀን፡ዠምሮ፡ባንተ፡ላይ፡ተጣልኹ፤ከእናቴ፡ሆድ፡ዠምረኽ፡አንተ፡አምላኬ፡ነኽ።
11፤ጭንቀት፡ቀርባለችና፡የሚረዳኝም፡የለምና፡ከእኔ፡አትራቅ።
12፤ብዙ፡በሬዎች፡ከበቡኝ፥የሰቡትም፡ፍሪዳዎች፡ያዙኝ፤
13፤እንደ፡ነጣቂና፡እንደሚጮኽ፡አንበሳ፡በላዬ፡አፋቸውን፡ከፈቱ።
14፤እንደ፡ውሃ፡ፈሰስኹ፤ዐጥንቶቼም፡ዅሉ፡ተለያዩ፤ልቤ፡እንደ፡ሠም፡ኾነ፥በአንዠቴም፡መካከል፡ቀለጠ።
15፤ኀይሌ፡እንደ፡ገል፡ደረቀ፥በጕረሮዬም፡ምላሴ፡ተጣጋ፥ወደሞትም፡አሸዋ፡አወረድኸኝ።
16፤ብዙ፡ውሻዎች፡ከበ፟ውኛልና፤የክፋተኛዎች፡ጉባኤም፡ያዘኝ፤እጆቼንና፡እግሮቼን፡ቸነከሩኝ።
17፤ዐጥንቶቼ፡ዅሉ፡ተቈጠሩ፤እነርሱም፡አዩኝ፡ተመለከቱኝም።
18፤ልብሶቼን፡ለራሳቸው፡ተከፋፈሉ፥በቀሚሴም፡ላይ፡ዕጣ፡ተጣጣሉ።
19፤አንተ፡ግን፥አቤቱ፥ከእኔ፡አትራቅ፤አንተ፡ጕልበቴ፥እኔን፡ለመርዳት፡ፍጠን።
20፤ነፍሴን፡ከሰይፍ፡አድናት፥ብቻነቴንም፡ከውሻዎች፡እጅ።
21፤ከአንበሳ፡አፍ፡አድነኝ፥ብቻነቴንም፡አንድ፡ቀንድ፡ካላቸው።
22፤ስምኽን፡ለወንድሞቼ፡እነግራቸዋለኹ፥በጉባኤም፡መካከል፡አመሰግንኻለኹ።
23፤እግዚአብሔርን፡የምትፈሩ፥አመስግኑት፤የያዕቆብ፡ዘር፡ዅላችኹ፥አክብሩት፥የእስራኤልም፡ዘር፡ዅላችኹ፥ፍ ሩት።
24፤የችግረኛን፡ችግር፡አልናቀምና፥ቸልም፡አላለምና፤ፊቱንም፡ከእኔ፡አልሰወረምና፥ነገር፡ግን፥ወደ፡ርሱ፡በ ጮኽኹ፡ጊዜ፡ሰማኝ።
25፤በታላቅ፡ጉባኤ፡ምስጋናዬ፡ከአንተ፡ዘንድ፡ነው።ርሱን፡በሚፈሩት፡ፊት፡ስእለቴን፡እሰጣለኹ።
26፤ችግረኛዎች፡ይበላሉ፥ይጠግቡማል፤እግዚአብሔርንም፡የሚሹት፡ያመሰግኑታል፤ልባቸውም፡ለዘለዓለም፡ሕያው፡ ይኾናል።
27፤የምድር፡ዳርቻዎች፡ዅሉ፡ያስቡ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ይመለሱ፤የአሕዛብ፡ነገዶች፡ዅሉ፡በፊቱ፡ይሰግዳሉ።
28፤መንግሥት፡ለእግዚአብሔር፡ነውና፥ርሱም፡አሕዛብን፡ይገዛል።
29፤የምድር፡ደንዳናዎች፡ዅሉ፡ይበላሉ፡ይሰግዳሉም፤ወደ፡መሬት፡የሚወርዱት፡ዅሉ፡በፊቱ፡ይንበረከካሉ፤ነፍሴ ም፡ስለ፡ርሱ፡በሕይወት፡ትኖራለች።
30፤ዘሬ፡ይገዛለታል፤የምትመጣው፡ትውልድ፡ለእግዚአብሔር፡ትነግረዋለች፤
31፤ጽድቁንም፡ለሚወለደው፡ሕዝብ፥እግዚአብሔር፡ያደረገውን፡ጽድቁን፥ይነግራሉ።
_______________መዝሙር፡22፡(23)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡እረኛዬ፡ነው፥የሚያሳጣኝም፡የለም።
2፤በለመለመ፡መስክ፡ያሳድረኛል፤በዕረፍት፡ውሃ፡ዘንድ፡ይመራኛል።
3፤ነፍሴን፡መለሳት፥ስለ፡ስሙም፡በጽድቅ፡መንገድ፡መራኝ።
4፤በሞት፡ጥላ፡መካከል፡እንኳ፡ብኼድ፡አንተ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነኽና፥ክፉን፡አልፈራም፤በትርኽና፡ምርኵዝኽ፡እነር ሱ፡ያጸናኑኛል።
5፤በፊቴ፡ገበታን፡አዘጋጀኽልኝ፡በጠላቶቼ፡ፊት፡ለፊት፡ራሴን፡በዘይት፡ቀባኽ፥ጽዋዬም፡የተረፈ፡ነው።
6፤ቸርነትኽና፡ምሕረትኽ፡በሕይወቴ፡ዘመን፡ዅሉ፡ይከተሉኛል፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለዘለዓለም፡እኖራለኹ።
_______________መዝሙር፡23፡(24)።______________
በመዠመሪያ፡ሰንበት፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ምድርና፡ሞላዋ፡ለእግዚአብሔር፡ናት፥ዓለምም፡በርሷም፡የሚኖሩ፡ዅሉ።
2፤ርሱ፡በባሕሮች፡መሥርቷታልና፥በፈሳሾችም፡አጽንቷታልና።
3፤ወደእግዚአብሔር፡ተራራ፡ማን፡ይወጣል፧በቅድስናውስ፡ስፍራ፡ማን፡ይቆማል፧
4፤እጆቹ፡የነጹ፥ልቡም፡ንጹሕ፡የኾነ፥ነፍሱን፡ለከንቱ፡ያላነሣ፥ለባልንጀራውም፡በሽንገላ፡ያልማለ።
5፤ርሱ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በረከትን፡ከመድኀኒቱ፡አምላክም፡ምሕረትን፡ይቀበላል።
6፤ይህች፡ትውልድ፡ርሱን፡የምትፈልግ፡ናት፥የያዕቆብን፡አምላክ፡ፊት፡የምትፈልግ።
7፤እናንት፡መኳንንቶች፥በሮችን፡ክፈቱ፥የዘለዓለም፡ደጆችም፡ይከፈቱ፥የክብርም፡ንጉሥ፡ይግባ።
8፤ይህ፡የክብር፡ንጉሥ፡ማን፡ነው፧እግዚአብሔር፡ነው፥ብርቱና፡ኀያል፥እግዚአብሔር፡ነው፥በሰልፍ፡ኀያል።
9፤እናንተ፡መኳንንቶች፥በሮችን፡ክፈቱ፥የዘለዓለም፡ደጆችም፡ይከፈቱ፥የክብርም፡ንጉሥ፡ይግባ።
10፤ይህ፡የክብር፡ንጉሥ፡ማን፡ነው፧የጭፍራዎች፡አምላክ፡እግዚአብሔር፥ርሱ፡የክብር፡ንጉሥ፡ነው።
_______________መዝሙር፡24፡(25)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ወዳንተ፡ነፍሴን፡አነሣለኹ።
2፤አምላኬ፥አንተን፡ታመንኹ፤አልፈር፥ጠላቶቼ፡በእኔ፡አይሣቁብኝ።
3፤አንተን፡ተስፋ፡የሚያደርጉ፡አያፍሩም፤በከንቱ፡የሚገበዙ፡ያፍራሉ።
4፤አቤቱ፥መንገድኽን፡አመልክተኝ፥ፍለጋኽንም፡አስተምረኝ።
5፤አንተ፡የመድኀኒቴ፡አምላክ፡ነኽና፥በእውነትኽ፡ምራኝ፥አስተምረኝም፤ቀኑን፡ዅሉ፡አንተን፡ተስፋ፡አድርጌያ ለኹ።
6፤አቤቱ፥ምሕረትኽንና፡ቸርነትኽን፡ዐስብ፥ከጥንት፡ዠምሮ፡ናቸውና።
7፤የልጅነቴን፡ኀጢአትና፡መተላለፍ፡አታስብብኝ፤አቤቱ፥ስለቸርነትኽ፡ብዛት፡እንደ፡ምሕረትኽ፡ዐስበኝ።
8፤እግዚአብሔር፡ቸር፡ቅንም፡ነው፤ስለዚህ፥ኀጢአተኛዎችን፡በመንገድ፡ይመራቸዋል።
9፤ገሮችን፡በፍርድ፡ይመራል፥ለገሮችም፡መንገድን፡ያስተምራቸዋል።
10፤የእግዚአብሔር፡መንገድ፡ዅሉ፡ቸርነትና፡እውነት፡ነው።ቃል፡ኪዳኑንና፡ምስክሩን፡ለሚጠብቁ።
11፤አቤቱ፥ኀጢአቴ፡እጅግ፡ነውና፥ስለ፡ስምኽ፡ይቅር፡በለኝ።
12፤እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፡ሰው፡ማን፡ነው፧በሚመርጠው፡መንገድ፡ያስተምረዋል።
13፤ነፍሱ፡በመልካም፡ታድራለች፥ዘሩም፡ምድርን፡ይወርሳል።
14፤እግዚአብሔር፡ለሚፈሩት፡ኀይላቸው፡ነው፥ቃል፡ኪዳኑንም፡ያስታውቃቸዋል።
15፤ርሱ፡እግሮቼን፡ከወጥመድ፡ያወጣቸዋልና፥ዐይኖቼ፡ዅልጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ናቸው።
16፤እኔ፡ብቻዬንና፡ችግረኛ፡ነኝና፡ፊትኽን፡ወደ፡እኔ፡አድርግ፡ማረኝም።
17፤የልቤ፡ችግር፡ብዙ፡ነው፤ከጭንቀቴ፡አውጣኝ።
18፤ድካሜንና፡መከራዬን፡እይ፥ኀጢአቴንም፡ዅሉ፡ይቅር፡በለኝ።
19፤ጠላቶቼ፡እንደ፡በዙ፡እይ፥የግፍም፡ጥል፡ጠልተውኛል።
20፤ነፍሴን፡ጠብቅና፡አድነኝ፤አንተን፡ታምኛለኹና፡አልፈር።
21፤አንተን፡ተስፋ፡አድርጌያለኹና፡የውሀትና፡ቅንነት፡ይጠብቁኝ።
22፤አቤቱ፥እስራኤልን፡ከመከራው፡ዅሉ፡አድነው።
_______________መዝሙር፡25፡(26)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥እኔ፡በየውሀቴ፡ኼጃለኹና፡ፍረድልኝ፤በእግዚአብሔርም፡አምኛለኹና፡አልናወጥም።
2፤አቤቱ፥ፍተነኝ፥መርምረኝም፤ኵላሊቴንና፡ልቤን፡ፍተን።
3፤ምሕረትኽ፡በዐይኔ፡ፊት፡ነውና፥በእውነትኽም፡ተመላለስኹ።
4፤በከንቱ፡ሸንጎ፡አልተቀመጥኹም፥ከዐመፀኛዎችም፡ጋራ፡አልገባኹም።
5፤የክፉዎችን፡ማኅበር፡ጠላኹ፥ከዝንጉዎችም፡ጋራ፡አልቀመጥም።
6፤እጆቼን፡በንጽሕና፡ዐጥባለኹ፤አቤቱ፥መሠዊያኽን፡እዞራለኹ፥
7፤የምስጋናን፡ድምፅ፡እሰማ፡ዘንድ፥ተኣምራትኽንም፡ዅሉ፡እነግር፡ዘንድ።
8፤አቤቱ፥የቤትኽን፡ስፍራ፡የክብርኽንም፡ማደሪያ፡ቦታ፡ወደድኹ።
9፤ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡ነፍሴን፥ከደም፡ሰዎችም፡ጋራ፡ሕይወቴን፡አታጥፋ።
10፤በእጃቸው፡ተንኰል፡አለባቸው፥ቀኛቸውም፡መማለጃ፡ተሞልታለች።
11፤እኔ፡ግን፡በየውሀቴ፡ኼጃለኹ፤አድነኝ፡ማረኝም።
12፤እግሮቼ፡በቅንነት፡ቆመዋልና፤አቤቱ፥በማኅበር፡አመሰግንኻለኹ።
_______________መዝሙር፡26፡(27)።______________
ሳይቀባ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ብርሃኔና፡መድኀኒቴ፡ነው፤የሚያስፈራኝ፡ማን፡ነው፧እግዚአብሔር፡የሕይወቴ፡መታመኛዋ፡ነው፤ የሚያስደነግጠኝ፡ማን፡ነው፧
2፤ክፉዎች፥አስጨናቂዎቼ፡ጠላቶቼም፥ሥጋዬን፡ይበሉ፡ዘንድ፡በቀረቡ፡ጊዜ፥እነርሱ፡ተሰናከሉና፡ወደቁ።
3፤ሰራዊትም፡ቢሰፍርብኝ፡ልቤ፡አይፈራም፤ሰልፍም፡ቢነሣብኝ፡በዚህ፡እተማመናለኹ።
4፤እግዚአብሔርን፡አንዲት፡ነገር፡ለመንኹት፡ርሷንም፡እሻለኹ፤በሕይወቴ፡ዘመን፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡እ ኖር፡ዘንድ፥እግዚአብሔርን፡ደስ፡የሚያሠኘውንም፡አይ፡ዘንድ፥መቅደሱንም፡እመለከት፡ዘንድ።
5፤በመከራዬ፡ቀን፡በድንኳኑ፡ሰውሮኛልና፥በድንኳኑም፡መሸሸጊያ፡ሸሽጎኛልና፥በአለት፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አድርጎ ኛልና።
6፤እንሆ፥አኹን፡በዙሪያ፡ባሉ፡በጠላቶቼ፡ላይ፡ራሴን፡ከፍ፡ከፍ፡አደረገ፤በድንኳኑም፡የእልልታ፡መሥዋዕትን፡ ሠዋኹ፥ለእግዚአብሔር፡እቀኛለኹ፥እዘምርለትማለኹ።
7፤አቤቱ፥ወዳንተ፡የጮኽኹትን፡ቃሌን፡ስማኝ።ማረኝና፡አድምጠኝ።
8፤አንተ፡ፊቴን፡ሹት፡ባልኽ፡ጊዜ፦አቤቱ፥ፊትኽን፡እሻለኹ፡ልቤ፡አንተን፡አለ።
9፤ፊትኽን፡ከእኔ፡አትሰውር፥ተቈጥተኽ፡ከባሪያኽ፡ፈቀቅ፡አትበል፤ረዳት፡ኹነኝ፥አትጣለኝም፥የመድኀኒቴም፡አ ምላክ፡ሆይ፥አትተወኝ።
10፤አባቴና፡እናቴ፡ትተውኛልና፥እግዚአብሔር፡ግን፡ተቀበለኝ።
11፤አቤቱ፥መንገድኽን፡አስተምረኝ፥ስለ፡ጠላቶቼም፡በቀና፡መንገድ፡ምራኝ።
12፤የሐሰት፡ምስክሮችና፡ዐመፀኛዎች፡ተነሥተውብኛልና፥ለጠላቶቼ፡ፈቃድ፡አትስጠኝ።
13፤የእግዚአብሔርን፡ቸርነት፡በሕያዋን፡ምድር፡አይ፡ዘንድ፡አምናለኹ።
14፤እግዚአብሔርን፡ተስፋ፡አድርግ፤በርታ፥ልብኽም፡ይጽና፤እግዚአብሔርን፡ተስፋ፡አድርግ።
_______________መዝሙር፡27፡(28)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ወዳንተ፡እጠራለኹ፤ዝም፡ብትለኝ፡ወደ፡ጕድጓድ፡እንደሚወርዱት፡እንዳልመስል፥አንተ፡አምላኬ፥ዝም፡ አትበለኝ።
2፤ወደ፡መቅደስኽ፡ማደሪያ፡እጄን፡ባነሣኹ፡ጊዜ፥ወዳንተ፡የጮኽኹትን፡የልመናዬን፡ቃል፡ስማ።
3፤ከኃጥኣንና፡ከክፉ፡አድራጊዎች፡ጋራ፡ነፍሴን፡አትውሰዳት፤ክፋትም፡በልባቸው፡እያለ፡ከባልንጀራቸው፡ጋራ፡ ሰላም፡ከሚናገሩት፡ጋራ፡አትጣለኝ።
4፤እንደ፡ሥራቸው፥እንደ፡አካኼዳቸውም፡ክፋት፡ስጣቸው፤እንደ፡እጃቸውም፡ሥራ፡ስጣቸው፤ፍዳቸውን፡ወደ፡ራሳቸ ው፡መልስ።
5፤ወደእግዚአብሔር፡ሥራ፡ወደ፡እጆቹም፡አደራረግ፡አላሰቡምና፡ያፈርሳቸዋል፡እንጂ፡አይሠራቸውም።
6፤የልመናዬን፡ቃል፡ሰምቶኛልና፥እግዚአብሔር፡ይመስገን።
7፤እግዚአብሔር፡ኀይሌና፡ጋሻዬ፡ነው፤ልቤ፡በርሱ፡ታመነ፡እኔም፡ተረዳኹ፤ሥጋዬም፡ደስ፡ይለዋል፥ፈቅጄም፡አመ ሰግነዋለኹ።
8፤እግዚአብሔር፡ለሕዝቡ፡ኀይላቸው፡ነው፥ለቀባውም፡የመድኀኒቱ፡መታመኛ፡ነው።
9፤ሕዝብኽን፡አድን፥ርስትኽንም፡ባርክ፤ጠብቃቸው፥ለዘለዓለሙም፡ከፍ፡ከፍ፡አድርጋቸው።
_______________መዝሙር፡28፡(29)።______________
ከድንኳን፡በመውጣት፡ጊዜ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤የአምላክ፡ልጆች፡ሆይ፥ለእግዚአብሔር፡አምጡ።ክብርንና፡ምስጋናን፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ።
2፤የስሙን፡ክብር፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ፥በቅድስናው፡ስፍራ፡ለእግዚአብሔር፡ስገዱ።
3፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡በውሃዎች፡ላይ፥የክብር፡አምላክ፡አንጐደጐደ፥እግዚአብሔር፡በብዙ፡ውሃዎች፡ላይ።
4፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡በኀይል፡ነው፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡በታላቅ፡ክብር፡ነው።
5፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡ዝግባን፡ይሰብራል፤እግዚአብሔር፡የሊባኖስን፡ዝግባ፡ይቀጠቅጣል።
6፤እንደ፡ጥጃ፡ሊባኖስን፥አንድ፡ቀን፡እንዳለው፡አውሬ፡ልጅ፡ስርዮንን፡ያዘልላቸዋል።
7፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡የእሳቱን፡ነበልባል፡ይቈርጣል።
8፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡ምድረ፡በዳውን፡ያናውጣል፥እግዚአብሔር፡የቃዴስን፡ምድረ፡በዳ፡ያናውጣል።
9፤የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡ዋላዎችን፡ያጠነክራቸዋል፥ጫካዎቹንም፡ይገልጣል፤ዅሉም፡በመቅደሱ፦ምስጋና፡ይላል።
10፤እግዚአብሔር፡የጥፋት፡ውሃን፡ሰብስቧል፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ንጉሥ፡ኾኖ፡ይቀመጣል።
11፤እግዚአብሔር፡ለሕዝቡ፡ኀይልን፡ይሰጣል፤እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡በሰላም፡ይባርካል።
_______________መዝሙር፡29፡(30)።______________
ለቤቱ፡መመረቅ፡ምስጋና፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ተቀብለኸኛልና፥ጠላቶቼንም፡ደስ፡አላሠኘኽብኝምና፡ከፍ፡ከፍ፡አደርግኻለኹ።
2፤አቤቱ፡አምላኬ፥ወዳንተ፡ጮኽኹ፡ምሕረትም፡አደረግኽልኝ።
3፤አቤቱ፥ነፍሴን፡ከሲኦል፡አወጣኻት፥ወደ፡ጕድጓድም፡እንዳልወርድ፡አዳንኸኝ።
4፤ቅዱሳን፡ሆይ፥ለእግዚአብሔር፡ዘምሩ፥ለቅድስናውም፡መታሰቢያ፡አመስግኑ።
5፤ቍጣው፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ነው፥ሞገሱ፡ግን፡ለሕይወት፡ዘመን፤ልቅሶ፡ማታ፡ይመጣል፥ጧት፡ግን፡ደስታ፡ይኾናል።
6፤እኔም፡በደስታዬ።ለዘለዓለም፡አልታወክም፡አልኹ።
7፤አቤቱ፥በፈቃድኽ፡ለሕይወቴ፡ኀይልን፡ሰጠኻት፤ፊትኽን፡መለስኽ፥እኔም፡ደነገጥኹ።
8፤አቤቱ፥ወዳንተ፡ጠራኹ፥ወደ፡አምላኬም፡ለመንኹ።
9፤ወደ፡ጥፋት፡ብወርድ፡በደሜ፡ምን፡ጥቅም፡አለ፧ዐፈር፡ያመሰግንኻልን፧እውነትኽንም፡ይናገራልን፧
10፤እግዚአብሔር፡ሰማ፡ማረኝም፤እግዚአብሔር፡ረዳቴ፡ኾነኝ።
11፤ክብሬ፡ትዘምርልኽ፡ዘንድ፡ዝምም፡እንዳትል፡ልቅሶዬን፡ለደስታ፡ለወጥኽልኝ፥ማቄን፡ቀደ፟ኽ፡ደስታንም፡አ ስታጠቅኸኝ።
12፤አቤቱ፡አምላኬ፥ለዘለዓለም፡አመሰግንኻለኹ።
_______________መዝሙር፡30፡(31)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በማድነቅ፡ጊዜ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፡አንተን፡ታመንኹ፤ለዘለዓለም፡አልፈር፤በጽድቅኽም፡አድነኝ።
2፤ዦሮኽን፡ወደ፡እኔ፡አዘንብል፥ፈጥነኽም፡አድነኝ፤ታድነኝ፡ዘንድ፡መታመኛ፡አምላክና፡የመጠጊያ፡ቤት፡ኹነኝ ።
3፤ዐምባዬና፡መጠጊያዬ፡አንተ፡ነኽና፥ስለ፡ስምኽ፡መንገዴን፡አቅና፡ምራኝም።
4፤አንተ፡መታመኛዬ፡ነኽና፥ከደበቁብኝ፡ወጥመድ፡አውጣኝ።
5፤በእጅኽ፡ነፍሴን፡እሰጣለኹ፤የእውነት፡አምላክ፡አቤቱ፥ተቤዥተኸኛል።
6፤ከንቱ፡ምናምንቴነትን፡የጠበቁትን፡ጠላኽ፤እኔ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ታመንኹ።
7፤መከራዬን፡አይተኻልና፥ነፍሴንም፡ከጭንቀት፡አድነኻታልና፥በምሕረትኽ፡ደስ፡ይለኛል፡ሐሤትም፡አደርጋለኹ።
8፤በጠላቴ፡እጅ፡አልዘጋኸኝም፥በሰፊም፡ስፍራ፡እግሮቼን፡አቆምኽ።
9፤ተቸግሬያለኹና፡አቤቱ፡ምራኝ፤ዐይኔም፡ከሐዘን፡የተነሣ፡ተፈጀች፥ነፍሴም፡ሆዴም።
10፤ሕይወቴ፡በሐዘን፡አልቃለችና፥ዓመታቴም፡በልቅሶ፡ጩኸት፤ኀይሌ፡በችግር፡ደከመ፥ዐጥንቶቼም፡ተነዋወጡ።
11፤በጠላቶቼ፡ዘንድ፡ተነወርኹ፥ይልቁንም፡በጎረቤቶቼ፡ዘንድ፥ለሚያውቁኝም፡ፍርሀት፡ኾንኹ፤በሜዳ፡ያዩኝም፡ ከእኔ፡ሸሹ።
12፤እንደ፡ሞተ፡ሰው፡ከልብ፡ተረሳኹ፥እንደ፡ተበላሸ፡ዕቃም፡ኾንኹ።
13፤የብዙ፡ሰዎችን፡ስድብ፡ሰምቻለኹና፤በዙሪያው፡ፍርሀት፡ነበረ፤በላዬ፡በአንድነት፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፡ነፍሴ ን፡ለመንጠቅ፡ተማከሩ።
14፤አቤቱ፥እኔ፡ግን፡ባንተ፡ታመንኹ፤አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፡አልኹ።
15፤ርስቴ፡በእጅኽ፡ነው፤ከጠላቶቼ፡እጅና፡ከሚያሳድዱኝ፡አድነኝ።
16፤ፊትኽን፡በባሪያኽ፡ላይ፡አብራ፥ስለ፡ምሕረትኽም፡አድነኝ።
17፤አቤቱ፥አንተን፡ጠርቻለኹና፡አልፈር፤ክፉዎች፡ይፈሩ፡በሲኦልም፡ዝም፡ይበሉ።
18፤በድፍረትና፡በትዕቢት፡በመናቅም፡በጻድቅ፡ላይ፡የሚናገሩ፡የሽንገላ፡ከንፈሮች፡ድዳ፡ይኹኑ።
19፤ባንተ፡ለሚያምኑ፡በሰው፡ልጆች፡ፊት፡ያዘጋጀኻት፡ለሚፈሩኽም፡የሰወርኻት፥ቸርነትኽ፡እንደ፡ምን፡በዛች!
20፤በፊትኽ፡መጋረጃ፡ከሰው፡ክርክር፡ትጋርዳቸዋለኽ፥በድንኳንኽም፡ከአንደበት፡ክርክር፡ትሸፍናቸዋለኽ።
21፤በተከበበ፡ከተማ፡የሚያስደንቅ፡ምሕረቱን፡በእኔ፡የገለጠ፡እግዚአብሔር፡ይመስገን።
22፤እኔስ፡ከዐይንኽ፡ፊት፡ተጣልኹ፥በድንጋጤ፡አልኹ፤አንተ፡ግን፡ወዳንተ፡በጮኽኹ፡ጊዜ፡የልመናዬን፡ቃል፡ሰ ማኸኝ።
23፤ዅላችኹ፡ቅዱሳኑ፥እግዚአብሔርን፡ውደዱት፤እግዚአብሔር፡እውነተኛዎችን፡ይፈልጋል፥ትዕቢተኛዎችንም፡ፈጽ ሞ፡ይበቀላቸዋል።
24፤በእግዚአብሔር፡የምታምኑ፡ዅላችኹ፥በርቱ፡ልባችኹም፡ይጥና።
_______________መዝሙር፡31፡(32)።______________
የዳዊት፡ትምህርት።
1፤መተላለፉ፡የቀረችለት፡ኀጢአቱም፡የተከደነችለት፡ምስጉን፡ነው።
2፤እግዚአብሔር፡በደልን፡የማይቈጥርበት፡በመንፈሱም፡ሽንገላ፡የሌለበት፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
3፤ዅልጊዜ፡ከመጮኼ፡የተነሣ፡ዝም፡ባልኹ፡ጊዜ፡ዐጥንቶቼ፡ተበላሹ፤
4፤በቀንና፡በሌሊት፡እጅኽ፡ከብዳብኛለችና፥ርጥበቴም፡ለበጋ፡ትኵሳት፡ተለወጠ።
5፤ኀጢአቴን፡ለአንተ፡አስታወቅኹ፥በደሌንም፡አልሸፈንኹም፤ለእግዚአብሔር፡መተላለፌን፡እነግራለኹ፡አልኹ፤አ ንተም፡የልቤን፡ኀጢአት፡ተውኽልኝ።
6፤ስለዚህ፥ቅዱስ፡ዅሉ፡በምቹ፡ጊዜ፡ወዳንተ፡ይለምናል፤ብዙ፡የጥፋት፡ውሃም፡ወደ፡ርሱ፡አይቀርብም።
7፤አንተ፡ለእኔ፡መሸሸጊያዬ፡ነኽ፥ከጣርም፡ትጠብቀኛለኽ፤ከከበቡኝ፡ታድነኝ፡ዘንድ፡ደስታዬ፡ነኽ።
8፤አስተምርኻለኹ፡በምትኼድበትም፡መንገድ፡እመራኻለኹ፤ዐይኖቼን፡ባንተ፡ላይ፡አጠናለኹ።
9፤ወዳንተ፡እንዳይቀርቡ፡በልባብና፡በልጓም፡ጕንጫቸውን፡እንደሚለጕሟቸው፥ልብ፡እንደሌላቸው፡እንደ፡ፈረስና ፡እንደ፡በቅሎ፡አትኹኑ።
10፤በኀጢአተኛ፡ብዙ፡መቅሠፍት፡አለበት፤በእግዚአብሔር፡የሚታመነውን፡ግን፡ምሕረት፡ይከበ፟ዋል።
11፤ጻድቃን፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይበላችኹ፡ሐሤትም፡አድርጉ፤
ልባችኹም፡የቀና፡ዅላችኹ፥እልል፡በሉ።
_______________መዝሙር፡32፡(33)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ጻድቃን፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይበላችኹ፤ለቅኖች፡ምስጋና፡ይገ፟ባ፟ል።
2፤እግዚአብሔርን፡በመሰንቆ፡አመስግኑት፥ዐሥር፡አውታርም፡ባለው፡በበገና፡ዘምሩለት።
3፤ዐዲስ፡ቅኔም፡ተቀኙለት፥በእልልታም፡መልካም፡ዝማሬ፡ዘምሩ፤
4፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ቅን፡ነውና፥ሥራውም፡ዅሉ፡በእምነት፡ነውና።
5፤ጽድቅንና፡ፍርድን፡ይወዳ፟ል፤የእግዚአብሔር፡ቸርነት፡ምድርን፡ሞላች።
6፤በእግዚአብሔር፡ቃል፡ሰማዮች፡ጸኑ፥ሰራዊታቸውም፡ዅሉ፡በአፉ፡እስትንፋስ፤
7፤የባሕርን፡ውሃ፡እንደ፡ረዋት፡የሚሰበስበው፥ቀላዮችንም፡በመዝገቦች፡የሚያኖራቸው።
8፤ምድር፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ትፍራው፥በዓለም፡የሚኖሩ፡ዅሉም፡ከርሱ፡የተነሣ፡ይደንግጡ።
9፤ርሱ፡ተናግሯልና፥ኾኑም፤ርሱ፡አዘዘ፥ጸኑም።
10፤እግዚአብሔር፡የአሕዛብን፡ምክር፡ያጠፋል፥የአሕዛብንም፡ዐሳብ፡ይመልሳል።
11፤የእግዚአብሔር፡ምክር፡ግን፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።የልቡም፡ዐሳብ፡ለልጅ፡ልጅ፡ነው።
12፤እግዚአብሔር፡አምላኩ፡የሚኾንለት፡ሕዝብ፡ምስጉን፡ነው፥ርሱ፡ለርስቱ፡የመረጠው፡ሕዝብ።
13፤እግዚአብሔር፡ከሰማይ፡ተመለከተ፥የሰውንም፡ልጆች፡ዅሉ፡አየ።
14፤ከማደሪያው፡ቦታ፡ኾኖ፡በምድር፡ወደሚኖሩ፡ዅሉ፡ተመለከተ፥
15፤ርሱ፡ብቻውን፡ልባቸውን፡የሠራ፡ሥራቸውንም፡ዅሉ፡የሚያስተውል።
16፤ንጉሥ፡በሰራዊቱ፡ብዛት፡አይድንም፡ኀያልም፡በኀይሉ፡ብዛት፡አያመልጥም።
17፤ፈረስም፡ከንቱ፡ነው፥አያድንም፤በኀይሉም፡ብዛት፡አያመልጥም።
18፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡ወደሚፈሩት፡ናቸው፥በምሕረቱም፡ወደሚታመኑ፥
19፤ነፍሳቸውን፡ከሞት፡ያድን፡ዘንድ፥በራብም፡ጊዜ፡ይመግባቸው፡ዘንድ።
20፤ነፍሳችን፡እግዚአብሔርን፡ተስፋ፡ታደርገዋለች፥ረዳታችንና፡መጠጊያችን፡ርሱ፡ነውና።
21፤ልባችን፡በርሱ፡ደስ፡ይለዋልና፥በቅዱስ፡ስሙም፡ታምነናልና።
22፤አቤቱ፥ምሕረትኽ፡በላያችን፡ትኹን፥ባንተ፡እንደ፡ታመን፟።
_______________መዝሙር፡33፡(34)።______________
ባሳደደው፡በአቢሜሌክ፡ፊት፡መልኩን፡በለወጠ፡ጊዜ፡በኼደም፡ጊዜ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔርን፡ዅልጊዜ፡እባርከዋለኹ፥ምስጋናውንም፡ዘወትር፡በአፌ፡ነው።
2፤ነፍሴ፡በእግዚአብሔር፡ትከብራለች፥ገሮችም፡ሰምተው፡ደስ፡ይላቸዋል።
3፤እግዚአብሔርን፡ከእኔ፡ጋራ፡ታላቅ፡አድርጉት፥በአንድነትም፡ስሙን፡ከፍ፡ከፍ፡እናድርግ።
4፤እግዚአብሔርን፡ፈለግኹት፡መለሰልኝም፥ከመከራዬም፡ዅሉ፡አዳነኝ።
5፤ወደ፡ርሱ፡ቅረቡ፡ያበራላችኹማል፥ፊታችኹም፡አያፍርም።
6፤ይህ፡ችግረኛ፡ጮኸ፥እግዚአብሔርም፡ሰማው፥ከመከራውም፡ዅሉ፡አዳነው።
7፤የእግዚአብሔር፡መልአክ፡በሚፈሩት፡ሰዎች፡ዙሪያ፡ይሰፍራል፥ያድናቸውማል።
8፤እግዚአብሔር፡ቸር፡እንደ፡ኾነ፡ቅመሱ፡እዩም፤በርሱ፡የሚታመን፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
9፤የሚፈሩት፡አንዳችን፡አያጡምና፡ቅዱሳኑ፡ዅሉ፥እግዚአብሔርን፡ፍሩት።
10፤ባለጠጋዎች፡ደኸዩ፥ተራቡም፥እግዚአብሔርን፡የሚፈልጉትን፡ግን፡ከመልካም፡ነገር፡ዅሉ፡አይጐድሉም።
11፤ልጆቼ፡ኑ፥ስሙኝ፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡አስተምራችዃለኹ።
12፤ሕይወትን፡የሚፈቅድ፡ሰው፡ማን፡ነው፧በጎንም፡ዘመን፡ለማየት፡የሚወድ፟፧
13፤አንደበትኽን፡ከክፉ፡ከልክል፥ከንፈሮችኽም፡ሽንገላን፡እንዳይናገሩ።
14፤ከክፉ፡ሽሽ፡መልካምንም፡አድርግ፤ሰላምን፡ሻ፥ተከተላትም።
15፤የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡ወደ፡ጻድቃን፥ዦሮዎቹም፡ወደ፡ጩኸታቸው፡ናቸውና።
16፤መታሰቢያቸውን፡ከምድር፡ያጠፋ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉን፡በሚያደርጉ፡ላይ፡ነው።
17፤ጻድቃን፡ጮኹ፥እግዚአብሔርም፡ሰማቸው፡ከመከራቸውም፡ዅሉ፡አዳናቸው።
18፤እግዚአብሔር፡ልባቸው፡ለተሰበረ፡ቅርብ፡ነው፥መንፈሳቸው፡የተሰበረውንም፡ያድናቸዋል።
19፤የጻድቃን፡መከራቸው፡ብዙ፡ነው፥እግዚአብሔርም፡ከዅሉ፡ያድናቸዋል።
20፤እግዚአብሔር፡ዐጥንቶቻቸውን፡ዅሉ፡ይጠብቃል፥ከነርሱም፡አንድ፡አይሰበርም።
21፤ኀጢአተኛዎችን፡ክፋት፡ይገድላቸዋል፡ጻድቃንንም፡የሚጠሉ፡ይጸጸታሉ።
22፤የባሪያዎቹን፡ነፍስ፡እግዚአብሔር፡ይቤዣል፥በርሱም፡የሚያምኑ፡ዅሉ፡አይጸጸቱም።
_______________መዝሙር፡34፡(35)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥የሚበድሉኝን፡በድላቸው፥የሚዋጉኝንም፡ተዋጋቸው።
2፤ጥሩርና፡ጋሻ፡ያዝ፥እኔንም፡ለመርዳት፡ተነሥ።
3፤ሰይፍኽን፡ምዘዝ፥የሚያሳድዱኝንም፡መንገዳቸውን፡ዝጋ፤ነፍሴን፦መድኀኒትሽ፡እኔ፡ነኝ፡በላት።
4፤ነፍሴን፡የሚሹ፡ዅሉ፡ይፈሩ፥ይጐስቈሉም፤ክፋትን፡በእኔ፡ላይ፡የሚያስቡ፡ይፈሩ፥ወደ፡ዃላቸውም፡ይበሉ።
5፤በነፋስ፡ፊት፡እንዳለ፡ትቢያ፡ይኹኑ፥የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ያስጨንቃቸው።
6፤መንገዳቸው፡ድጥና፡ጨለማ፡ይኹን፥የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ያሳ፟ዳ፟ቸው።
7፤በከንቱ፡ያጠፉኝ፡ዘንድ፡ወጥመዳቸውን፡ሸሽገውብኛልና፥ነፍሴን፡በከንቱ፡አበሳጭተዋልና።
8፤ያላወቁት፡ወጥመድ፡ይምጣባቸው፥የሸሸጉትም፡ወጥመድ፡ይያዛቸው፤በዚህ፡ወጥመድ፡ውስጥ፡ይውደቁ።
9፤ነፍሴ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይላታል፥በማዳኑም፡ሐሴት፡ታደርጋለች።
10፤ዐጥንቶቼ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ይሉኻል፦አቤቱ፥እንደ፡አንተ፡ማን፡ነው፧ችግረኛን፡ከሚቀማው፡እጅ፥ችግረኛንና፡ ድኻውንም፡ከሚነጥቀው፡እጅ፡ታድነዋለኽ።
11፤የክፋት፡ምስክሮች፡ተነሡብኝ፥የማላውቀውንም፡በእኔ፡ላይ፡ተናገሩ።
12፤ስለ፡በጎ፡ክፋትን፡መለሱልኝ፥ነፍሴንም፡ልጆችን፡አሳጧት።
13፤እኔስ፡እነርሱ፡በታመሙ፡ጊዜ፡ማቅ፡ለበስኹ፥ነፍሴንም፡በጾም፡አደከምዃት፤ጸሎቴም፡ወደ፡ብብቴ፡ተመለሰ።
14፤ለወዳጄና፡ለወንድሜ፡እንደማደርግ፡አደረግኹ፤ለእናቱም፡እንደሚያለቅስ፡ራሴን፡ዝቅ፡ዝቅ፡አደረግኹ።
15፤በእኔ፡ላይ፡ተሰበሰቡ፡ደስም፡አላቸው፤ግፈኛዎች፡በእኔ፡ላይ፡ተሰበሰቡ፡እኔም፡አላውቅኹም፤ቀደዱኝ፡አል ተዉኝምም።
16፤ፈተኑኝ፡በሣቅም፡ዘበቱብኝ፥ጥርሳቸውንም፡በእኔ፡ላይ፡አንቀጫቅጩ።
17፤አቤቱ፥እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ታይልኛለኽ፧ነፍሴን፡ከክፉ፡ሥራቸው፡ብችነቴንም፡ከአንበሳዎች፡አድናት።
18፤አቤቱ፥በታላቁ፡ጉባኤ፡ውስጥ፡እገዛልኻለኹ፥በብዙ፡ሕዝብ፡መካከልም፡አመሰግንኻለኹ።
19፤በግፍ፡የሚጠሉኝ፡በላዬ፡ደስ፡አይበላቸው፥በከንቱ፡የሚጣሉኝም፡በዐይናቸው፡አይጣቀሱብኝ።
20፤ለኔስ፡ሰላምን፡ይናገሩኛልና፥በቍጣም፡ሽንገላን፡ይመክራሉ።
21፤አፋቸውንም፡በእኔ፡ላይ፡አላቀቁ፤ዕሠይ፡ዕሠይ፥ዐይናችን፡አየው፡ይላሉ።
22፤አቤቱ፥አንተ፡አየኸው፤ዝም፡አትበል፤አቤቱ፥ከእኔ፡አትራቅ።
23፤አምላኬ፡ጌታዬም፥ወደ፡ፍርዴ፡ተነሥ፥አቤቱ፥ፍርዴን፡አድምጥ።
24፤አቤቱ፡አምላኬ፥እንደ፡ጽድቅኽ፡ፍረድልኝ፥በላዬም፡ደስ፡አይበላቸው።
25፤በልባቸው፦ዕሠይ፡ዕሠይ፥ነፍሳችንን፡ደስ፡አላት፡አይበሉ፤ደግሞም፦ዋጥነው፡አይበሉ።
26፤በመከራዬ፡ደስ፡የሚላቸው፡ይፈሩ፥በአንድነትም፡ይጐስቍሉ፤በእኔ፡ላይ፡የሚታበዩ፡ዕፍረትንና፡ጕስቍልናን ፡ይልበሱ።
27፤ጽድቄን፡የሚወዷ፟ት፡ደስ፡ይበላቸው፡ሐሴትንም፡ያድርጉ፤የባሪያውን፡ሰላም፡የሚወድ፟፡እግዚአብሔር፡ታላ ቅ፡ይኹን፡ዘወትር፡ይበሉ።
28፤ምላሴ፡ጽድቅኽን፡ዅልጊዜም፡ምስጋናኽን፡ይናገራል።
_______________መዝሙር፡35፡(36)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ኀጢአተኛ፡በራሱ፡የሚያስት፡ነገርን፡ይናገራል፥የእግዚአብሔርም፡ፍርሀት፡በዐይኖቹ፡ፊት፡የለም።
2፤በአንደበቱ፡ሸንግሏልና፤ኀጢአቱ፡ባገኘችው፡ጊዜ፡ይጠላታል።
3፤የአፉ፡ቃል፡ግፍና፡ሽንገላ፡ነው፤ማስተዋልን፡በጎ፡ማድረግንም፡ተወ።
4፤በመኝታው፡ጠማማነትን፡ዐሰበ፤መልካም፡ባልኾነች፡መንገድ፡ቆሟል፤ክፋትን፡አይንቃትም።
5፤አቤቱ፥ምሕረትኽ፡በሰማይ፡ነው፥እውነትኽም፡ወደ፡ደመናት፡ትደርሳለች።
6፤ጽድቅኽም፡እንደእግዚአብሔር፡ተራራዎች፥ፍርድኽም፡እጅግ፡ጥልቅ፡ናት፤አቤቱ፥ሰውንና፡እንስሳን፡ታድናለኽ ።
7፤አቤቱ፥ምሕረትኽን፡እንዴት፡አበዛኽ! የሰው፡ልጆች፡በክንፎችኽ፡ጥላ፡ይታመናሉ።
8፤ከቤትኽ፡ጠል፡ይጠጣሉ፥ከተድላም፡ፈሳሽ፡ታጠጣቸዋለኽ።
9፤የሕይወት፡ምንጭ፡ከአንተ፡ዘንድ፡ነውና፤በብርሃንኽ፡ብርሃንን፡እናያለን።
10፤ምሕረትኽን፡በሚያውቁኽ፡ላይ፥ጽድቅኽንም፡ልባቸው፡በቀና፡ላይ፡ዘርጋ።
11፤የትዕቢት፡እግር፡አይምጣብኝ፥የኀጢአተኛዎችም፡እጅ፡አያውከኝ።
12፤ዐመፃን፡የሚያደርጉ፡ዅሉ፡ከዚያ፡ወደቁ፤ወድቀዋል፥መቆምም፡አይችሉም።
_______________መዝሙር፡36፡(37)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤በክፉዎች፡ላይ፡አትቅና፥ዐመፃንም፡በሚያደርጉ፡ላይ፡አትቅና፤
2፤እንደ፡ሣር፡ፈጥነው፡ይደርቃሉና፥እንደ፡ለመለመ፡ቅጠልም፡ይረግፋሉና።
3፤በእግዚአብሔር፡ታመን፥መልካምንም፡አድርግ፥በምድርም፡ተቀመጥ፥ታምነኽም፡ተሰማራ።
4፤በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይበልኽ፥የልብኽንም፡መሻት፡ይሰጥኻል።
5፤መንገድኽን፡ለእግዚአብሔር፡ዐደራ፡ስጥ፥በርሱም፡ታመን፥ርሱም፡ያደርግልኻል።
6፤ጽድቅኽን፡እንደ፡ብርሃን፡ፍርድኽንም፡እንደ፡ቀትር፡ያመጣል።
7፤ለእግዚአብሔር፡ተገዛ፥ተስፋም፡አድርገው።መንገድም፡በቀናችለትና፡ጥመትን፡በሚያደርግ፡ሰው፡አትቅና።
8፤ከቍጣ፡ራቅ፥መዓትንም፡ተው፤እንዳትበድል፡አትቅና።
9፤ክፉ፡አድራጊዎች፡ይጠፋሉና፤እግዚአብሔርን፡ተስፋ፡የሚያደርጉ፡ግን፡እነርሱ፡ምድርን፡ይወርሳሉ።
10፤ገና፡ጥቂት፥ኀጢአተኛም፡አይኖርም፤ትፈልገዋለኽ፡ቦታውንም፡አታገኝም።
11፤ገሮች፡ግን፡ምድርን፡ይወርሳሉ፥በብዙም፡ሰላም፡ደስ፡ይላቸዋል።
12፤ኀጢአተኛ፡ጻድቁን፡ይመለካከተዋል፥ጥርሱንም፡በርሱ፡ላይ፡ያንገጫግጫል።
13፤እግዚአብሔር፡ይሥቅበታል፥ቀኑ፡እንደሚደርስ፡አይቷልና።
14፤ኀጢአተኛዎች፡ሰይፋቸውን፡መዘዙ፥ቀስታቸውንም፡ገተሩ፡ድኻውንና፡ችግረኛውን፡ይጥሉ፡ዘንድ፡ልበ፡ቅኖችን ም፡ይወጉ፡ዘንድ፤
15፤ሰይፋቸው፡ወደ፡ልባቸው፡ይግባ፥ቀስታቸውም፡ይሰበር።
16፤ለጻድቅ፡ያለው፡ጥቂት፡ከብዙ፡ከኀጢአተኛዎች፡ሀብት፡ይበልጣል።
17፤የኃጥኣን፡ክንድ፡ትሰበራለችና፤እግዚአብሔር፡ግን፡ጻድቃንን፡ይደግፋቸዋል።
18፤የንጹሓንን፡መንገድ፡እግዚአብሔር፡ያውቃል፥ርስታቸውም፡ለዘለዓለም፡ነው፤
19፤በክፉ፡ዘመንም፡አያፍሩም፡በራብ፡ዘመንም፡ይጠግባሉ።
20፤ኃጥኣን፡ግን፡ይጠፋሉ፥የእግዚአብሔር፡ጠላቶች፡በከበሩና፡ከፍ፡ከፍ፡ባሉ፡ጊዜ፡እንደ፡ጢስ፡ይጠፋሉ።
21፤ኀጢአተኛ፡ይበደራል፡አይከፍልምም፤ጻድቅ፡ግን፡ይራራል፡ይሰጣልም።
22፤ርሱን፡የሚባርኩት፡ምድርን፡ይወርሳሉና፤የሚረግሙት፡ግን፡ይጠፋሉ።
23፤የሰው፡አካኼድ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ይጸናል፥መንገዱንም፡ይወዳ፟ል።
24፤ቢወድቅም፡ለድንጋፄ፡አይጣልም፥እግዚአብሔር፡እጁን፡ይዞ፡ይደግፈዋልና።
25፤ጐለመስኹ፡አረጀኹም፤ጻድቅ፡ሲጣል፥ዘሩም፡እኽል፡ሲለምን፡አላየኹም።
26፤ዅልጊዜ፡ይራራል፡ያበድርማል፥ዘሩም፡በበረከት፡ይኖራል።
27፤ከክፉ፡ሽሽ፥መልካምንም፡አድርግ፤ለዘለዓለምም፡ትኖራለኽ።
28፤እግዚአብሔር፡ፍርዱን፡ይወዳ፟ልና፥ቅዱሳኑንም፡አይጥላቸውምና፤ለዘለዓለምም፡ይጠብቃቸዋል፡ለንጹሓንም፡ ይበቀልላቸዋል፤የኃጥኣን፡ዘር፡ግን፡ይጠፋል።
29፤ጻድቃን፡ምድርን፡ይወርሳሉ፥በርሷም፡ለዘለዓለም፡ይኖራሉ።
30፤የጻድቅ፡አፍ፡ጥበብን፡ያስተምራል፥አንደበቱም፡ፍርድን፡ይናገራል።
31፤የአምላኩ፡ሕግ፡በልቡ፡ውስጥ፡ነው፥በርምጃውም፡አይሰናከልም።
32፤ኀጢአተኛ፡ጻድቁን፡ይመለከተዋል፥ሊገድለውም፡ይወዳ፟ል።
33፤እግዚአብሔር፡ግን፡በእጁ፡አይተወውም፥በተፋረደውም፡ጊዜ፡አያሸንፈውም።
34፤እግዚአብሔርን፡ደጅ፡ጥና፥መንገዱንም፡ጠብቅ፥ምድርንም፡ትወርስ፡ዘንድ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርግኻል፤ኀጢአተኛ ዎችም፡ሲጠፉ፡ታያለኽ።
35፤ኃጥኣን፡ከፍ፡ከፍ፡ብሎ፡እንደ፡ሊባኖስ፡ዝግባም፡ለምልሞ፡አየኹት።
36፤ብመለስ፡ግን፡ዐጣኹት፤ፈለግኹት፡ቦታውንም፡አላገኘኹም።
37፤ቅንነትን፡ጠብቅ፥ጽድቅንም፡እይ፤ለሰላም፡ሰው፡ቅሬታ፡አለውና።
38፤በደለኛዎች፡በአንድነት፡ይጠፋሉ።የኀጢአተኛዎች፡ቅሬታ፡ይጠፋል።
39፤የጻድቃን፡መድኀኒታቸው፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው፤በመከራቸውም፡ጊዜ፡መጠጊያቸው፡ርሱ፡ነው።
40፤እግዚአብሔር፡ይረዳቸዋል፥ያድናቸዋልም፥ከኀጢአተኛዎችም፡እጅ፡ያወጣቸዋል፥ያድናቸዋል፥በርሱ፡ታምነዋል ና።
_______________መዝሙር፡37፡(38)።______________
ለሰንበት፡መታሰቢያ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በቍጣኽ፡አትቅሠፈኝ፥በመዓትኽም፡አትገሥጸኝ።
2፤ፍላጻዎችኽ፡ወግተውኛልና፥እጅኽንም፡አክብደኽብኛልና።
3፤ከቍጣኽ፡የተነሣ፡ለሥጋዬ፡ጤና፡የለውም፤ከኀጢአቴም፡የተነሣ፡ለዐጥንቶቼ፡ሰላም፡የላቸውም።
4፤ኀጢአቴ፡በራሴ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥እንደ፡ከባድ፡ሸክምም፡በላዬ፡ከብዷልና።
5፤ከስንፍናዬ፡የተነሣ፡ቍስሌ፡ሸተተ፡በሰበሰም፤
6፤እጅግ፡ጐሰቈልኹ፡ተዋረድኹም፥ዅልጊዜም፡በትካዜ፡እመላለሳለኹ።
7፤ነፍሴ፡ስድብን፡ተሞልታለችና፥ለሥጋዬም፡ጤና፡የላትምና።
8፤ታመምኹ፤እጅግም፡ተቸገርኹ፥ከልቤ፡ውዝዋዜም፡የተነሣ፡ጮኽኹ።
9፤አቤቱ፥ፈቃዴ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ነው፥ጭንቀቴም፡ከአንተ፡አይሰወርም።
10፤ልቤ፡ደነገጠብኝ፥ኀይሌም፡ተወችኝ፥የዐይኖቼም፡ብርሃን፡ፈዘዘ።
11፤ወዳጆቼም፡ባልንጀራዎቼም፡ከቍስሌ፡ገለል፡ብለው፡ቆሙ፥ዘመዶቼም፡ርቀው፡ቆሙ።
12፤ነፍሴንም፡የሚሿት፡በረቱብኝ፥መከራዬንም፡የሚፈልጉ፡ከንቱን፡ተናገሩ፥ዅልጊዜም፡በሽንገላ፡ይመክራሉ።
13፤እኔ፡ግን፡እንደማይሰማ፡ደንቈሮ፡አፉንም፡እንደማይከፍት፡ዲዳ፡ኾንኹ።
14፤እንደማይሰማ፡ሰው፡በአፉም፡ተግሣጽ፡እንደሌለው፡ሰው፡ኾንኹ።
15፤አቤቱ፥ባንተ፡ታምኛለኹና፤አቤቱ፡አምላኬ፥አንተ፡ትሰማኛለኽ።
16፤ጠላቶቼ፡በእኔ፡ላይ፡ደስ፡እንዳይላቸው፡ብያለኹና፥እግሮቼም፡ቢሰናከሉ፡ራሳቸውን፡በእኔ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ ፡ያደርጋሉ።
17፤እኔስ፡ወደ፡ማንከስ፡ቀርቤያለኹና፥ቍስሌም፡ዅልጊዜም፡በፊቴ፡ነውና።
18፤በደሌን፡እናገራለኹና፥ስለ፡ኀጢአቴም፡እተክዛለኹ።
19፤ጠላቶቼ፡ሕያዋን፡ናቸው፡ይበረቱብኝማል፥በጠማማነትም፡የሚጠሉኝ፡በዙ።
20፤ጽድቅን፡ስለ፡ተከተልኹ፥በበጎ፡ፋንታ፡ክፉን፡የሚመልሱልኝ፡ይጠሉኛል።
21፤አቤቱ፥አንተ፡አትጣለኝ፤አምላኬ፥ከእኔ፡አትራቅ።
22፤አቤቱ፡መድኀኒቴ፥እኔን፡ለመርዳት፡ፍጠን።
_______________መዝሙር፡38፡(39)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፥ለኤዶታም፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤በአንደበቴ፡እንዳልስት፡መንገዴን፡እጠብቃለኹ፤ኀጢአተኛ፡በፊቴ፡በተቃወመኝ፡ጊዜ፡በአፌ፡ላይ፡ጠባቂ፡አኖ ራለኹ፡አልኹ።
2፤ከዝምታ፡የተነሣ፡እንደ፡ዲዳ፡ኾንኹ፥ለበጎ፡እንኳ፡ዝም፡አልኹ፥ቍስሌም፡ታደሰብኝ።
3፤ልቤም፡በውስጤ፡ሞቀብኝ፤ከማሰቤም፡የተነሣ፡እሳት፡ነደደ፥በአንደበቴም፡ተናገርኹ።
4፤አቤቱ፥ፍጻሜዬን፡አስታውቀኝ፥የዘመኔ፡ቍጥሮች፡ምን፡ያኽል፡እንደ፡ኾኑ፥እኔ፡ምን፡ያኽል፡ወደ፡ዃላ፡እንደ ምቀር፡ዐውቅ፡ዘንድ።
5፤እንሆ፥ዘመኖቼን፡አስረጀኻቸው፤አካሌም፡በፊትኽ፡እንደ፡ኢምንት፡ነው።ሕያው፡የኾነ፡ሰው፡ዅሉ፡በእውነት፡ ከንቱ፡ብቻ፡ነው።
6፤በከንቱ፡ይታወካል፡እንጂ፡በእውነት፡ሰው፡እንደ፡ጣላ፡ይመላለሳል፤ያከማቻል፡የሚሰበስብለትንም፡አያውቅም ።
7፤አኹንስ፡ተስፋዬ፡ማን፡ነው፧እግዚአብሔር፡አይደለምን፧ትዕግሥቴም፡ከአንተ፡ዘንድ፡ነው።
8፤ከኀጢአቴ፡ዅሉ፡አድነኝ፥ለሰነፎችም፡ስድብ፡አታድርገኝ።
9፤አንተ፡ሠርተኸኛልና፥ዝም፡አልኹ፡አፌንም፡አልከፈትኹም።
10፤መቅሠፍትኽን፡ከእኔ፡አርቅ፥ከእጅኽ፡ብርታት፡የተነሣ፡አልቄያለኹና።
11፤በተግሣጽኽ፡ስለ፡ኀጢአቱ፡ሰውን፡ዘለፍኸው፥ነፍሱም፡እንደ፡ሸረሪት፡ድር፡ታልቃለች፤በእውነት፡ሰው፡ዅሉ ፡ከንቱ፡ነው።
12፤አቤቱ፥ጸሎቴን፡ስማ፥ጩኸቴንም፡አድምጥ፥ልቅሶዬንም፡ቸል፡አትበለኝ፤እኔ፡በምድር፡ላይ፡መጻተኛ፡ነኝና፥ እንደ፡አባቶችም፡እንግዳ፡ነኝና።
13፤ወደማልመለስበት፡ሳልኼድ፡ዐርፍ፡ዘንድ፡ተወኝ።
_______________መዝሙር፡39፡(40)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ቈይቼ፡እግዚአብሔር፡ደጅ፡ጠናኹት፥ርሱም፡ዘንበል፡አለልኝ፡ጩኸቴንም፡ሰማኝ።
2፤ከጥፋት፡ጕድጓድ፡ከረግረግም፡ጭቃ፡አወጣኝ፥እግሮቼንም፡በድንጋይ፡ላይ፡አቆማቸው፥አረማመዴንም፡አጸና።
3፤ዐዲስ፡ዝማሬን፡ለአምላካችን፡ምስጋና፡በአፌ፡ጨመረ፤ብዙዎች፡ያያሉ፡ይፈሩማል፥በእግዚአብሔርም፡ይታመናሉ ።
4፤እግዚአብሔርን፡የታመነ፡ወደ፡ትዕቢተኛና፡ወደ፡ሐሰተኛ፡ያልተመለከተ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
5፤አቤቱ፡አምላኬ፥ያደረግኸው፡ተኣምራት፡ብዙ፡ነው፥ዐሳብኽንም፡ምንም፡የሚመስለው፡የለም፤ባወራም፡ብናገርም ፡ከቍጥር፡ዅሉ፡በዛ።
6፤መሥዋዕትንና፡ቍርባንን፡አልወደድኽም፤ሥጋን፡አዘጋጀኽልኝ፤የሚቃጠለውንና፡ስለ፡ኀጢአት፡የሚቀርበውን፡መ ሥዋዕት፡አልሻኽም።
7፤በዚያን፡ጊዜ፡አልኹ፦እንሆ፥መጣኹ፤ስለ፡እኔ፡በመጽሐፍ፡ራስ፡ተጽፏል፤
8፤አምላኬ፡ሆይ፥ፈቃድኽን፡ለማድረግ፡ወደድኹ፥ሕግኽም፡በልቤ፡ውስጥ፡ነው።
9፤በታላቅ፡ጉባኤ፡ጽድቅን፡አወራኹ፤እንሆ፥ከንፈሮቼን፡አልከለክልም፤አቤቱ፥አንተ፡ጽድቄን፡ታውቃለኽ።
10፤እውነትኽንም፡በልቤ፡ውስጥ፡አልሰወርኹም፥ማዳንኽንም፡ተናገርኹ፤ምሕረትኽንና፡እውነትኽን፡ከታላቅ፡ጉባ ኤ፡አልሰወርኹም።
11፤አቤቱ፥አንተ፡ምሕረትኽን፡ከእኔ፡አታርቅ፤ቸርነትኽና፡እውነትኽ፡ዘወትር፡ይጠብቁኝ።
12፤ቍጥር፡የሌላት፡ክፋት፡አግኝታኛለችና፤ኀጢአቶቼ፡ያዙኝ፥ማየትም፡ተስኖኛል፡ከራሴ፡ጠጕር፡ይልቅ፡በዙ፥ል ቤም፡ተወኝ።
13፤አቤቱ፥ታድነኝ፡ዘንድ፡ፍቀድ፤አቤቱ፥እኔን፡ለመርዳት፡ፍጠን።
14፤ነፍሴን፡ለማጥፋት፡የሚወዱ፡ይፈሩ፥በአንድነትም፡ይጐስቍሉ፤በእኔ፡ላይ፡ክፋትን፡ሊያደርጉ፡የሚወዱ፡ወደ ፡ዃላቸው፡ይመለሱ፡ይጐስቍሉም።
15፤ዕሠይ፡ዕሠይ፡የሚሉኝ፡ዕፍረታቸውን፡ወዲያው፡ይከፈሉ።
16፤አቤቱ፥የሚፈልጉኽ፡ዅሉ፡ባንተ፡ደስ፡ይበላቸው፡ሐሤትም፡ያድርጉ፤ዅልጊዜ፡ማዳንኽን፡የሚወዱ፡ዘወትር።እ ግዚአብሔር፡ታላቅ፡ይኹን፡ይበሉ።
17፤እኔ፡ችግረኛና፡ምስኪን፡ነኝ፥ጌታ፡ግን፡ያስብልኛል፤አንተ፡ረዳቴና፡መድኀኒቴ፡ነኽ፤አምላኬ፡ሆይ፥አትዘ ግይ።
_______________መዝሙር፡40፡(41)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ለችግረኛና፡ለምስኪን፡የሚያስብ፡ምስጉን፡ነው፤እግዚአብሔር፡በክፉ፡ቀን፡ያድነዋል።
2፤እግዚአብሔር፡ይጠብቀዋል፥ሕያውም፡ያደርገዋል፥በምድር፡ላይም፡ያስመሰግነዋል፥በጠላቶቹም፡እጅ፡አያሳልፈ ውም።
3፤እግዚአብሔር፡በደዌው፡ዐልጋ፡ሳለ፡ይረዳዋል፤መኝታውን፡ዅሉ፡በበሽታው፡ጊዜ፡ያነጥፍለታል።
4፤እኔስ፦አቤቱ፡ማረኝ፤አንተን፡በድያለኹና፡ነፍሴን፡ፈውሳት፡አልኹ።
5፤ጠላቶቼም፡በላዬ፡ክፋትን፡ይናገራሉ፦መቼም፡ይሞታል፡ስሙስ፡መቼ፡ይሻራል፧ይላሉ።
6፤እኔን፡ለማየት፡ቢገባ፡ከንቱን፡ይናገራል፤ልቡ፡ኀጢአትን፡ሰበሰበለት፤ወደ፡ሜዳ፡ይወጣል፡ይናገራልም።
7፤በላዬ፡በመተባበር፡ጠላቶቼ፡ዅሉ፡ይሾካሾኩብኛል፥በእኔ፡ላይም፡ክፋትን፡ያስባሉ።
8፤ክፉ፡ነገር፡መጣበት፤ተኝቷል፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይነሣም፡ይላሉ።
9፤ደግሞ፡የሰላሜ፡ሰው፡የታመንኹበት፡እንጀራዬን፡የበላ፡በእኔ፡ላይ፡ተረከዙን፡አነሣ።
10፤አንተ፡ግን፡አቤቱ፥ማረኝ፡እመልስላቸውም፡ዘንድ፡አስነሣኝ።
11፤ጠላቴ፡እልል፡አይልብኝምና፡ስለዚህ፡እንደ፡ወደድኸኝ፡ዐወቅኹ።
12፤እኔን፡ግን፡ስለ፡ቅንነቴ፡ተቀበልኸኝ፥በፊትኽም፡ለዘለዓለም፡አጸናኸኝ።
13፤ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረክ።አሜን፡አሜን።
_______________መዝሙር፡41፡(42)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የቆሬ፡ልጆች፡ትምህርት።
1፤ዋላ፡ወደ፡ውሃ፡ምንጭ፡እንደሚናፍቅ፥አቤቱ፥እንዲሁ፡ነፍሴ፡ወዳንተ፡ትናፍቃለች።
2፤ነፍሴ፡ወደ፡ሕያው፡አምላክ፡ተጠማች፤መቼ፡እደርሳለኹ፧የአምላክንስ፡ፊት፡መቼ፡አያለኹ፧
3፤ዘወትር።አምላክኽ፡ወዴት፡ነው፧ሲሉኝ፡እንባዬ፡በቀንና፡በሌሊት፡ምግብ፡ኾነኝ።
4፤ይህን፡ሳስብ፡ነፍሴ፡በእኔ፡ውስጥ፡ፈሰሰች፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደምስጋና፡መኖሪያ፡ስፍራ፡እገባለኹና ፤በዓል፡የሚያደርጉ፡ሰዎች፡የደስታና፡ምስጋና፡ቃል፡አሰሙ።
5፤ነፍሴ፡ሆይ፥ለምን፡ታዝኛለሽ፧ለምንስ፡ታውኪኛለሽ፧የፊቴን፡መድኀኒት፡አምላኬን፡አመሰግነው፡ዘንድ፡በእግ ዚአብሔር፡ታመኚ።
6፤አምላኬ፡ሆይ፥ነፍሴ፡በእኔ፡ውስጥ፡ታወከች፤ስለዚህ፥በዮርዳኖስ፡ምድር፡በአርሞንኤምም፡በታናሹ፡ተራራ፡ዐ ስብኻለኹ።
7፤በፏፏቴኽ፡ድምፅ፡ቀላይ፡ቀላይን፡ትጠራታለች፤ማዕበልኽና፡ሞገድኽ፡ዅሉ፡በላዬ፡ዐለፈ።
8፤እግዚአብሔር፡በቀን፡ቸርነቱን፡ያዛ፟ል፥በሌሊትም፡ዝማሬው፡በእኔ፡ዘንድ፡ይኾናል፤የእኔ፡ስእለት፡ለሕይወ ቴ፡አምላክ፡ነው።
9፤እግዚአብሔርን፦አንተ፡መጠጊያዬ፡ነኽ፤ለምን፡ረሳኸኝ፧ጠላቶቼ፡ሲያስጨንቁኝ፡ለምን፡ዐዝኜ፡እመላለሳለኹ፧ እለዋለኹ።
10፤ጠላቶቼ፡ዅልጊዜ፦አምላክኽ፡ወዴት፡ነው፧ባሉኝ፡ጊዜ፡ዐጥንቶቼን፡እየቀለጣጠሙ፡ሰደቡኝ።
11፤ነፍሴ፡ሆይ፥ለምን፡ታዝኛለሽ፧ለምንስ፡ታውኪኛለሽ፧የፊቴን፡መድኀኒት፡አምላኬን፡አመሰግነው፡ዘንድ፡በእ ግዚአብሔር፡ታመኚ።
_______________መዝሙር፡42፡(43)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ፍረድልኝ፥ከጽድቅ፡ከራቁ፡ሕዝብም፡ክርክሬን፡ተከራከር፤ከሸንጋይና፡ከግፈኛ፡ሰው፡አድነኝ።
2፤አንተ፡አምላኬ፡ኀይሌም፥ለምን፡ትተወኛለኽ፧ጠላቶቼ፡ሲያስጨንቁኝ፡ለምን፡ዐዝኜ፡እመላለሳለኹ፧
3፤ብርሃንኽንና፡እውነትኽን፡ላክ፤እነርሱ፡ይምሩኝ፥ወደቅድስናኽ፡ተራራና፡ወደ፡ማደሪያኽ፡ይውሰዱኝ።
4፤ወደእግዚአብሔር፡መሠዊያ፥ጕልማሳነቴንም፡ደስ፡ወዳሠኛት፡ወደ፡አምላኬ፡እገባለኹ፤አቤቱ፡አምላኬ፥በበገና ፡አመሰግንኻለኹ።
5፤ነፍሴ፡ሆይ፥ለምን፡ታዝኛለሽ፧ለምንስ፡ታውኪኛለሽ፧የፊቴን፡መድኀኒት፡አምላኬን፡አመሰግነው፡ዘንድ፡በእግ ዚአብሔር፡ታመኚ።
_______________መዝሙር፡43፡(44)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የቆሬ፡ልጆች፡ትምህርት።
1፤አቤቱ፥በዦሯችን፡ሰማን፥አባቶቻችንም፡በዘመናቸው፡በቀድሞ፡ዘመን፡የሠራኸውን፡ሥራ፡ነገሩን።
2፤እጅኽ፡አሕዛብን፡አጠፋች፥እነርሱንም፡ተከልኽ፤አሕዛብን፡ሣቀይኻቸው፡አሳደድኻቸውም።
3፤በሰይፋቸው፡ምድርን፡አልወረሱም፡ክንዳቸውም፡አላዳናቸው፤ቀኝኽና፡ክንድኽ፡የፊትኽም፡ብርሃን፡ነው፡እንጂ ፡ወደ፟ኻቸዋልና።
4፤አምላኬና፡ንጉሤ፡አንተ፡ነኽ፤ለያዕቆብ፡መድኀኒትን፡እዘዝ።
5፤ባንተ፡ጠላቶቻችንን፡እንወጋቸዋለን፥በስምኽም፡በላያችን፡የቆሙትን፡እናዋርዳቸዋለን።
6፤በቀስቴ፡የምታመን፡አይደለኹምና፥ሰይፌም፡አያድነኝምና፤
7፤አንተ፡ግን፡ከጠላቶቻችን፡አዳንኸን፥የሚጠሉንንም፡አሳፈርኻቸው።
8፤ዅልጊዜ፡በእግዚአብሔር፡እንከብራለን፥ስምኽንም፡ለዘለዓለም፡እናመሰግናለን።
9፤አኹን፡ግን፡ጠላኸን፡አሳፈርኸንም፥ከሰራዊታችንም፡ጋራ፡አትወጣም።
10፤ከጠላቶቻችንም፡ፊት፡ወደ፡ዃላችን፡መለስኸን፥የሚጠሉንም፡ተነጣጠቁን።
11፤እንደ፡በጎች፡ሊበሉን፡ሰጠኸን፥ወደ፡አሕዛብም፡በተንኸን።
12፤ሕዝብኽን፡ያለዋጋ፡ሰጠኽ፥በመለወጣቸውም፡ትርፍ፡የለም።
13፤ለጎረቤቶቻችን፡ስድብ፥በዙሪያችንም፡ላሉ፡መሣቂያና፡መዘበቻ፡አደረግኸን።
14፤በአሕዛብ፡ዘንድ፡ምሳሌ፥በሕዝብም፡ዘንድ፡የራስ፡መንቀሳቀሻ፡አደረግኸን።
15፤ጕስቍልናዬ፡ዅልጊዜም፡በፊቴ፡ነው፥የፊቴም፡ዕፍረት፡ሸፈነኝ።
16፤ከሚሳደብና፡ከሚላገድ፡ቃል፡የተነሣ፥ከጠላትና፡ከቂመኛ፡ፊት፡የተነሣ፡ነው።
17፤ይህ፡ዅሉ፡በእኛ፡ላይ፡ደረሰ፥አልረሳንኽም፥ኪዳንኽንም፡አልወነጀልንም።
18፤ልባችን፡ወደ፡ዃላው፡አልተመለሰም፥ፍለጋችንም፡ከመንገድኽ፡ፈቀቅ፡አላለም፤
19፤በክፉ፡ስፍራ፡አዋርደኸናልና፥በሞት፡ጥላም፡ሰውረኸናልና።
20፤የአምላካችንን፡ስም፡ረስተንስ፡ቢኾን፥እጃችንንም፡ወደ፡ሌላ፡አምላክ፡አንሥተንስ፡ቢኾን፥
21፤እግዚአብሔር፡ይህንን፡አይመረምርም፡ነበርን፧ርሱ፡ልብ፡የሰወረውን፡ያውቃልና።
22፤ስለ፡አንተ፡ዅልጊዜም፡ተገድለናል፥እንደሚታረዱም፡በጎች፡ኾነናል።
23፤አቤቱ፥ንቃ፤ለምንስ፡ትተኛለኽ፧ተነሥ፥ለዘወትርም፡አትጣለን።
24፤ለምንስ፡ፊትኽን፡ትሰውራለኽ፧መከራችንንና፡ችግራችንንስ፡ለምን፡ትረሳለኽ፧
25፤ነፍሳችን፡በመሬት፡ላይ፡ተጐሳቍላለችና፥ሆዳችንም፡ወደ፡ምድር፡ተጣብቃለችና።
26፤አቤቱ፥ተነሥና፡ርዳን፥ስለ፡ስምኽም፡ተቤዠን።
_______________መዝሙር፡44፡(45)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በመለኮቶች፤የቆሬ፡ልጆች፡ትምህርት፤የፍቅር፡መዝሙር።
1፤ልቤ፡መልካም፡ነገርን፡አፈለቀ፥እኔ፡ሥራዬን፡ለንጉሥ፡እነግራለኹ፤አንደበቴ፡እንደ፡ፈጣን፡ጸሓፊ፡ብርዕ፡ ነው።
2፤ውበትኽ፡ከሰው፡ልጆች፡ይልቅ፡ያምራል፤ሞገስ፡በከንፈሮችኽ፡ፈሰሰ፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ባረ ከኽ።
3፤ኀያል፡ሆይ፥በቍንዥናኽና፡በውበትኽ፡ሰይፍኽን፡በወገብኽ፡ታጠቅ።
4፤ስለ፡ቅንነትና፡ስለ፡የዋህነት፡ስለ፡ጽድቅም፡አቅና፡ተከናወን፡ንገሥም፤ቀኝኽም፡በክብር፡ይመራኻል።
5፤ኀያል፡ሆይ፥ፍላጻዎችኽ፡የተሳሉ፡ናቸው፥እነርሱም፡በንጉሥ፡ጠላቶች፡ልብ፡ውስጥ፡ይገባሉ፥አሕዛብም፡በበታ ችኽ፡ይወድቃሉ።
6፤አምላክ፡ሆይ፥ዙፋንኽ፡ለዘለዓለም፡ነው፤የመንግሥትኽ፡በትር፡የቅንነት፡በትር፡ነው።
7፤ጽድቅን፡ወደድኽ፡ዐመፃንም፡ጠላኽ፤ስለዚህ፥ከባልንጀራዎችኽ፡ይልቅ፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡የደስታ፡ዘይት ን፡ቀባኽ።
8፤በልብሶችኽ፡ዅሉ፡ከርቤና፡ሽቱ፡ዝባድም፡አሉ፤ከዝኆን፡ጥርሶች፡አዳራሽ፡ደስ፡ያሠኙኻል።
9፤የንጉሦች፡ሴት፡ልጆች፡ለክብርኽ፡ናቸው፤በወርቅ፡ልብስ፡ተጐናጽፋና፡ተሸፋፍና፡ንግሥቲቱ፡በቀኝኽ፡ትቆማለ ች።
10፤ልጄ፡ሆይ፥ስሚ፡እዪ፡ዦሮሽንም፡አዘንብዪ፤ወገንሽን፡ያባትሽንም፡ቤት፡ርሺ፤
11፤ንጉሥ፡ውበትሽን፡ወዷ፟ልና፥ርሱ፡ጌታሽ፡ነውና።
12፤የጢሮስ፡ሴቶች፡ልጆች፡እጅ፡መንሻን፡ይዘው፡ይሰግዱለታል።የምድር፡ባለጠጋዎች፡አሕዛብ፡በፊትኽ፡ይማለላ ሉ።
13፤ለሐሴቦን፡ንጉሥ፡ልጅ፡ዅሉ፡ክብሯ፡ነው፤ልብሷ፡የወርቅ፡መጐናጸፊያ፡ነው።
14፤በዃላዋ፡ደናግሉን፡ለንጉሥ፡ይወስዳሉ፥ባልንጀራዎቿንም፡ወዳንተ፡ያቀርባሉ፤
15፤በደስታና፡በሐሴት፡ይወስዷቸዋል፥ወደንጉሥ፡ዕልፍኝም፡ያስገቧቸዋል።
16፤በአባቶችሽ፡ፋንታ፡ልጆች፡ተወለዱልሽ፥በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡ገዢዎች፡አድርገሽ፡ትሾሚያቸዋለሽ።
17፤ለልጅ፡ልጅ፡ዅሉ፡ስምሽን፡ያሳስባሉ፤ስለዚህ፥ለዓለምና፡ለዘለዓለም፡አሕዛብ፡ይገዙልኻል።
_______________መዝሙር፡45፡(46)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ስለ፡ምስጢር፤የቆሬ፡ልጆች፡መዝሙር።
1፤አምላካችን፡መጠጊያችንና፡ኀይላችን፥ባገኘን፡በታላቅ፡መከራም፡ረዳታችን፡ነው።
2፤ስለዚህ፥ምድር፡ብትነዋወጥ፥ተራራዎችም፡ወደባሕር፡ልብ፡ቢወሰዱ፥አንፈራም።
3፤ውሃዎቻቸው፡ጮኹ፡ተናወጡም፥ተራራዎችም፡ከኀይሉ፡የተነሣ፡ተናወጡ።
4፤የወንዝ፡ፈሳሾች፡የእግዚአብሔርን፡ከተማ፡ደስ፡ያሠኛሉ፤ልዑል፡ማደሪያውን፡ቀደሰ።
5፤እግዚአብሔር፡በመካከሏ፡ነው፡አትናወጥም፥እግዚአብሔርም፡ፈጥኖ፡ይረዳታል።
6፤አሕዛብ፡ተናወጡ፡መንግሥታትም፡ተመለሱ፤ርሱ፡ቃሉን፡ሰጠ፥ምድርም፡ተንቀጠቀጠች።
7፤የሰራዊት፡ጌታ፡ከእኛ፡ጋራ፡ነው፤የያዕቆብ፡አምላክ፡መጠጊያችን፡ነው።
8፤የእግዚአብሔርን፡ሥራ፥በምድር፡ያደረገውንም፡ተኣምራት፡እንድታዩ፡ኑ።
9፤እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ጦርነት፡ይሽራል።ቀስትን፡ይሰብራል፥ጦርንም፡ይቈርጣል፡በእሳትም፡ጋሻን፡ያቃጥ ላል።
10፤ዕረፉ፥እኔም፡አምላክ፡እንደ፡ኾንኹ፡ዕወቁ፤በአሕዛብ፡ዘንድ፡ከፍ፡ከፍ፡እላለኹ፥በምድርም፡ላይ፡ከፍ፡ከ ፍ፡እላለኹ።
11፤የሰራዊት፡ጌታ፡ከእኛ፡ጋራ፡ነው፤የያዕቆብ፡አምላክ፡መጠጊያችን፡ነው።
_______________መዝሙር፡46፡(47)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የቆሬ፡ልጆች፡መዝሙር።
1፤አሕዛብ፡ዅላችኹ፥እጆቻችኹን፡አጨብጭቡ፥በደስታ፡ቃልም፡ለእግዚአብሔር፡እልል፡በሉ።
2፤እግዚአብሔር፡ልዑል፡ግሩምም፡ነውና፥በምድር፡ዅሉ፡ላይም፡ታላቅ፡ንጉሥ፡ነውና።
3፤አሕዛብን፡ከእኛ፡በታች፥ወገኖችንም፡ከእግራችን፡በታች፡አስገዛልን።
4፤ለርስቱ፡እኛን፡መረጠን፥የወደደውን፡የያዕቆብን፡ውበት።
5፤አምላክ፡በእልልታ፥እግዚአብሔር፡በመለከት፡ድምፅ፡ዐረገ።
6፤ዘምሩ፥ለአምላካችን፡ዘምሩ፤ዘምሩ፥ለንጉሣችን፡ዘምሩ።
7፤እግዚአብሔር፡ለምድር፡ዅሉ፡ንጉሥ፡ነውና፤በማስተዋል፡ዘምሩ።
8፤እግዚአብሔር፡በአሕዛብ፡ላይ፡ነገሠ፤እግዚአብሔር፡በቅድስናው፡ዙፋን፡ይቀመጣል።
9፤የምድር፡ኀይለኛዎች፡ለእግዚአብሔር፡ናቸውና፥የአሕዛብ፡አለቃዎች፡ወደአብርሃም፡አምላክ፡ተሰበሰቡ፤ርሱን ም፡ከፍ፡ከፍ፡አደረጉት።
_______________መዝሙር፡47፡(48)።______________
በኹለተኛ፡ሰንበት፡የቆሬ፡ልጆች፤የምስጋና፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ትልቅ፡ነው፤በአምላካችን፡ከተማ፡በተቀደሰ፡ተራራ፡ምስጋናው፡ብዙ፡ነው።
2፤በሰሜን፡ወገን፡በመልካም፡ስፍራ፡የቆመ፡የምድር፡ዅሉ፡ደስታ፡የጽዮን፡ተራራ፡ነው፤ርሱም፡የትልቁ፡ንጉሥ፡ ከተማ፡ነው።
3፤እግዚአብሔር፡በአዳራሾቿ፡መጠጊያ፡ኾኖ፡ይታወቃል።
4፤እንሆ፥ነገሥታት፡ተከማችተው፡በአንድነት፡መጥተዋል።
5፤እነርሱስ፡አይተው፡ተደነቁ፥ደነገጡ፥ታወኩ።
6፤መንቀጥቀጥ፡እንደ፡ወላድ፡ምጥ፡በዚያ፡ያዛቸው።
7፤በኀይለኛ፡ነፋስ፡የተርሴስን፡መርከቦች፡ትሰብራለኽ።
8፤እንደ፡ሰማን፡እንዲሁ፡አየን፡በሰራዊት፡ጌታ፡ከተማ፥በአምላካችን፡ከተማ፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ያጸና ታል።
9፤አምላክ፡ሆይ፥በሕዝብኽ፡መካከል፡ምሕረትኽን፡ተቀበልን።
10፤አምላክ፡ሆይ፥እንደ፡ስምኽ፡እንዲሁም፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ምስጋናኽ፡ነው፤ቀኝኽ፡ጽድቅን፡የተሞላ ች፡ናት።
11፤አቤቱ፥ስለ፡ፍርድኽ፡የጽዮን፡ተራራ፡ደስ፡ይበለው፥የአይሁድም፡ሴት፡ልጆች፡ሐሤት፡ያድርጉ።
12፤ጽዮንን፡ክበቧት፥በዙሪያዋም፡ተመላለሱ፥ግንቦቿንም፡ቍጠሩ፤
13፤በብርታቷ፡ልባችኹን፡አኑሩ፤አዳራሿን፡ዐስቡ፤ለሚመጣው፡ትውልድ፡ትነግሩ፡ዘንድ።
14፤ለዓለምና፡ለዘለዓለም፡ይህ፡አምላካችን፡ነው፥ርሱም፡ለዘለዓለም፡ይመራናል።
_______________መዝሙር፡48፡(49)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የቆሬ፡ልጆች፡መዝሙር።
1፤አሕዛብ፡ዅላችኹ፥ይህን፡ስሙ፤በዓለም፡የምትኖሩትም፡ዅላችኹ፥አድምጡ፤
2፤ዝቅተኛዎችና፡ከፍተኛዎች፥ባለጠጋዎችና፡ድኻዎች፡በአንድነት።
3፤አፌ፡ጥበብን፡ይናገራል፥የልቤም፡ዐሳብ፡ማስተዋልን።
4፤ዦሮዬን፡ወደ፡ምሳሌ፡አዘነብላለኹ፥በበገናም፡ምስጢሬን፡እገልጣለኹ።
5፤ኀጢአት፡ተረከዜን፡በከበበኝ፡ጊዜ፡በክፉ፡ቀን፡ለምን፡እፈራለኹ፧
6፤በኀይላቸው፡የሚታመኑ፥በባለጠግነታቸውም፡ብዛት፡የሚመኩ፤
7፤ወንድም፡ወንድሙን፡አያድንም፥ሰውም፡አያድንም፤ቤዛውን፡ለእግዚአብሔር፡አይሰጥም፥
8-9፤ለዘለዓለም፡እንዲኖር፥ጥፋትንም፡እንዳያይ፤የነፍሳቸው፡ለውጥ፡ከብሯልና፥ለዘለዓለምም፡ቀርቷልና።
10፤ብልኀተኛዎች፡እንዲሞቱ፥ሰነፎችና፡ደንቈሮዎች፡በአንድነት፡እንዲጠፉ፥ገንዘባቸውንም፡ለሌላዎች፡እንዲተ ዉ፡አይቷል።
11፤በልባቸውም፡ቤታቸው፡ለዘለዓለም፡የሚኖር፥ማደሪያቸውም፡ለልጆች፡ልጅ፡የሚኾን፡ይመስላቸዋል፤በያገራቸው ም፡ስማቸው፡ይጠራል።
12፤ሰው፡ግን፡ክቡር፡ኾኖ፡ሳለ፡አያውቅም፤እንደሚጠፉ፡እንስሳዎች፡መሰለ።
13፤ይህች፡መንገዳቸው፡መሰናክላቸው፡ናት፥ከነርሱም፡በዃላ፡የሚመጡ፡በአፋቸው፡ዕሺ፡ይላሉ።
14፤እንደ፡በጎች፡ወደ፡ሲኦል፡የሚኼዱ፡ናቸው፥እረኛቸውም፡ሞት፡ነው፤ቅኖችንም፡በማለዳ፡ይገዟቸዋል፥ውበታቸ ውም፡ከመኖሪያቸው፡ተለይታ፡በሲኦል፡ታረጃለች።
15፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ይቀበለኛልና፥ነፍሴን፡ከሲኦል፡እጅ፡ይቤዣታል።
16፤የሰው፡ባለጠግነት፡የቤቱም፡ክብር፡በበዛ፡ጊዜ፡አትፍራ፥
17፤በሞተ፡ጊዜ፡ከርሱ፡ጋራ፡ምንም፡አይወስድምና፥ክብሩም፡ከርሱ፡በዃላ፡አይወርድምና።
18፤በሕይወቱ፡ሳለ፡ነፍሱን፡ባርኳልና፥ለሰውነቱ፡መልካም፡ብታደርግለት፡ያመሰግንኻል።
19፤ኾኖም፡ወዳባቶቹ፡ትውልድ፡ይወርዳል፤ለዘለዓለም፡ብርሃንን፡አያይም።
20፤አእምሮ፡የሌለው፡ክቡር፡ሰው፡እንደሚጠፋ፡እንስሳዎች፡መሰለ።
_______________መዝሙር፡49፡(50)።______________
የአሣፍ፡መዝሙር።
1፤የአማልክት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ተናገረ፥ከፀሓይም፡መውጫ፡ዠምሮ፡እስከ፡መግቢያዋ፡ድረስ፡ምድርን፡ጠራ ት።
2፤ከክብሩ፡ውበት፡ከጽዮን፡እግዚአብሔር፡ግልጥ፡ኾኖ፡ይመጣል።
3፤አምላካችን፡ይመጣል፡ዝምም፡አይልም፤እሳት፡በፊት፡ይቃጠላል፥በዙሪያውም፡ብዙ፡ዐውሎ፡አለ።
4፤በላይ፡ያለውን፡ሰማይን፡ምድርንም፡በሕዝቡ፡ለመፍረድ፡ይጠራል፤
5፤ከርሱ፡ጋራ፡ለመሥዋዕት፡ኪዳን፡የቆሙትን፡ቅዱሳኑን፡ሰብስቡለት።
6፤ሰማያት፡ጽድቁን፡ይናገራሉ፥እግዚአብሔር፡ፈራጅ፡ነውና።
7፤ሕዝቤ፥ስማኝ፥ልንገርኽ፤እስራኤልም፥ስማኝ፥ልመስክርብኽ፤አምላክስ፡እኔ፡አምላክኽ፡ነኝ።
8፤ስለ፡ቍርባንኽ፡የምዘልፍኽ፡አይደለኹም፤የሚቃጠል፡መሥዋዕትኽ፡ዅልጊዜ፡በፊቴ፡ነው።
9፤ከቤትኽ፡ፍሪዳን፡ከመንጋኽም፡አውራ፡ፍየልን፡አልወስድም፤
10፤የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ዅሉ፡በሺሕ፡ተራራዎች፡ያሉ፡እንስሳዎችም፡የእኔ፡ናቸውና።
11፤የሰማይን፡አዕዋፍ፡ዅሉ፡ዐውቃለኹ፥የምድረ፡በዳ፡አራዊትም፡በእኔ፡ዘንድ፡ናቸው።
12፤ብራብም፡ለአንተ፡አልነግርኽም፥ዓለምና፡ሞላው፡የእኔ፡ነውና።
13፤የፍሪዳውን፡ሥጋ፡እበላለኹን፧የፍየሉንስ፡ደም፡እጠጣለኹን፧
14፤ለእግዚአብሔር፡የምስጋናን፡መሥዋዕት፡ሠዋ፥ለልዑልም፡ስእለትኽን፡ስጥ፤
15፤በመከራ፡ቀን፡ጥራኝ፥አድንኽማለኹ፡አንተም፡ታከብረኛለኽ።
16፤ኀጢአተኛውን፡ግን፡እግዚአብሔር፡አለው፦ለምን፡አንተ፡ሕጌን፡ትናገራለኽ፧ኪዳኔንም፡በአፍኽ፡ለምን፡ትወ ስዳለኽ፧
17፤አንተስ፡ተግሣጼን፡ጠላኽ፥ቃሎቼንም፡ወደ፡ዃላኽ፡ጣልኽ።
18፤ሌባውን፡ባየኽ፡ጊዜ፡ከርሱ፡ጋራ፡ትሮጥ፡ነበር፡ዕድል፡ፈንታኽንም፡ከአመንዝራዎች፡ጋራ፡አደረግኽ።
19፤አፍኽ፡ክፋትን፡አበዛ፥አንደበትኽም፡ሽንገላን፡ተበተበ።
20፤ተቀምጠኽ፡ወንድምኽን፡ዐማኸው፥ለእናትኽም፡ልጅ፡ዕንቅፋት፡አኖርኽ።
21፤ይህን፡አድርገኽ፡ዝም፡አልኹኽ፤እኔ፡እንደ፡አንተ፡እኾን፡ዘንድ፡ጠረጠርኽ፤እዘልፍኻለኹ፡በፊትኽም፡እቆ ማለኹ።
22፤እግዚአብሔርን፡የምትረሱ፡እናንተ፥ይህን፡አስተውሉ፤አለዚያ፡ግን፡ይነጥቃል፡የሚያድንም፡የለም።
23፤ምስጋና፡የሚሠዋ፡ያከብረኛል፤የእግዚአብሔርን፡ማዳን፡ለርሱ፡የማሳይበት፡መንገድ፡ከዚያ፡አለ።
_______________መዝሙር፡50፡(51)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ወደ፡ቤርሳቤሕ፡ከገባ፡በዃላ፡ነቢዩ፡ናታን፡ወደ፡ርሱ፡በመጣ፡ጊዜ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥እንደ፡ቸርነትኽ፡መጠን፡ማረኝ፤እንደ፡ምሕረትኽም፡ብዛት፡መተላለፌን፡ደምስስ።
2፤ከበደሌ፡ፈጽሞ፡ዕጠበኝ፥ከኀጢአቴም፡አንጻኝ፤
3፤እኔ፡መተላለፌን፡ዐውቃለኹና፥ኀጢአቴም፡ዅልጊዜ፡በፊቴ፡ነውና።
4፤አንተን፡ብቻ፡በደልኹ፥በፊትኽም፡ክፋትን፡አደረግኹ፥በነገርኽም፡ትጸድቅ፡ዘንድ፡በፍርድኽም፡ንጹሕ፡ትኾን ፡ዘንድ።
5፤እንሆ፥በዐመፃ፡ተፀነስኹ፥እናቴም፡በኀጢአት፡ወለደችኝ።
6፤እንሆ፥እውነትን፡ወደድኽ፤የማይታይ፡ስውር፡ጥበብን፡አስታወቅኸኝ።
7፤በሂሶጵ፡ርጨኝ፥እነጻማለኹ፤ዕጠበኝ፥ከበረዶም፡ይልቅ፡ነጭ፡እኾናለኹ።
8፤ሐሤትንና፡ደስታን፡አሰማኝ፥የሰበርኻቸውም፡ዐጥንቶቼ፡ደስ፡ይላቸዋል።
9፤ከኀጢአቴ፡ፊትኽን፡መልስ፥በደሌንም፡ዅሉ፡ደምስስልኝ።
10፤አቤቱ፥ንጹሕ፡ልብን፡ፍጠርልኝ፥የቀናውንም፡መንፈስ፡በውስጤ፡ዐድስ።
11፤ከፊትኽ፡አትጣለኝ፥ቅዱስ፡መንፈስኽንም፡ከእኔ፡ላይ፡አትውሰድብኝ።
12፤የማዳንኽን፡ደስታ፡ስጠኝ፥በእሽታ፡መንፈስም፡ደግፈኝ።
13፤ለሕግ፡ተላላፊዎች፡መንገድኽን፡አስተምራለኹ፥ኀጢአተኛዎችም፡ወዳንተ፡ይመለሳሉ።
14፤የመድኀኒቴ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ከደም፡አድነኝ፥አንደበቴም፡ባንተ፡ጽድቅ፡ትደሰታለች።
15፤አቤቱ፥ከንፈሮቼን፡ክፈት፥አፌም፡ምስጋናኽን፡ያወራል።
16፤መሥዋዕትን፡ብትወድ፟ስ፡በሰጠኹኽ፡ነበር፤የሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡ደስ፡አያሠኝኽም።
17፤የእግዚአብሔር፡መሥዋዕት፡የተሰበረ፡መንፈስ፡ነው፥የተሰበረውንና፡የተዋረደውን፡ልብ፡እግዚአብሔር፡አይ ንቅም።
18፤አቤቱ፥በውዴታኽ፡ጽዮንን፡አሰማምራት፤የኢየሩሳሌምንም፡ቅጽሮች፡ሥራ።
19፤የጽድቁን፡መሥዋዕት፡መባውንም፡የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡በወደድኽ፡ጊዜ፥ያን፡ጊዜ፡በመሠዊያኽ፡ላይ፡ፍ ሪዳዎችን፡ይሠዋሉ።
_______________መዝሙር፡51፡(52)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ኤዶማዊው፡ዶይቅ፡መጥቶ፡ለሳኦል፦ዳዊት፡ወደአቢሜሌክ፡ቤት፡መጥቷል፡ብሎ፡በነገረው፡ጊዜ ፤የዳዊት፡ትምህርት።
1፤ኀያል፡ሆይ፥በክፋት፡ለምን፡ትጓደዳለኽ፧ዅልጊዜስ፡በመተላለፍ፧
2፤አንደበትኽ፡ኀጢአትን፡ያስባል፤እንደ፡ተሳለ፡ምላጭ፡ሽንገላን፡አደረግኽ።
3፤ከመልካም፡ይልቅ፡ክፋትን፥ጽድቅንም፡ከመናገር፡ይልቅ፡ዐመፃን፡ወደድኽ።
4፤የሚያጠፉ፡ቃልን፡ዅሉ፥የሽንገላ፡ምላስን፡ወደድኽ።
5፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ያፈርስኻል፤ከቤትኽም፡ይነቅልኻል፥ያፈልስኻልም፥ሥርኽንም፡ከሕያዋን፡ ምድር።
6፤ጻድቃን፡አይተው፡ይፈራሉ፤በርሱም፡ይሥቃሉ፥እንዲህም፡ይላሉ፦
7፤እግዚአብሔርን፡ረዳቱ፡ያላደረገ፥በባለጠግነቱም፡ብዛት፡የታመነ፥በከንቱ፡ነገርም፡የበረታ፡ያ፡ሰው፡እንሆ ።
8፤እኔስ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ለመለመ፥እንደ፡ወይራ፡ዛፍ፡ነኝ፤ለዓለምና፡ለዘለዓለም፡በእግዚአብሔር ፡ምሕረት፡ታመንኹ።
9፤አድርገኽልኛልና፥ለዘለዓለም፡አመሰግንኻለኹ፥በቅዱሳንኽም፡ዘንድ፡መልካም፡ነውና፥ስምኽን፡ተስፋ፡አደርጋ ለኹ።
_______________መዝሙር፡52፡(53)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡በማኸላት፤የዳዊት፡ትምህርት።
1፤ሰነፍ፡በልቡ፦አምላክ፡የለም፡ይላል።ረከሱ፥በበደላቸውም፡ጐሰቈሉ፤በጎ፡ነገርን፡የሚያደርጋት፡የለም።
2፤የሚያስተውል፡እግዚአብሔርንም፡የሚፈልግ፡እንዳለ፡ያይ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ከሰማይ፡የሰው፡ልጆችን፡ተመ ለከተ።
3፤ዅሉ፡በደሉ፥ዐብረውም፡ረከሱ፤አንድ፡ስንኳ፡በጎን፡ነገር፡የሚያደርጋት፡የለም።
4፤ሕዝቤን፡እንጀራ፡እንደሚበላ፡የሚበሉ፡ግፍ፡አድራጊዎች፡ዅሉ፡አያውቁምን፧እግዚአብሔርንም፡አይጠሩትም።
5፤እግዚአብሔር፡የግብዞችን፡ዐጥንቶች፡በትኗልና።በዚያ፡የሚያስፈራ፡ሳይኖር፡እጅግ፡ፈሩ፤እግዚአብሔር፡ንቋ ቸዋልና፥አሳፈርኻቸው።
6፤መድኀኒትን፡ከጽዮን፡ለእስራኤል፡ማን፡በሰጠ! እግዚአብሔር፡የሕዝቡን፡ምርኮ፡በመለሰ፡ጊዜ፥ያዕቆብ፡ደስ፡ይለዋል፡እስራኤልም፡ሐሤት፡ያደርጋል።
_______________መዝሙር፡53፡(54)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በበገናዎች፤ዜፋውያን፡መጥተው፡ለሳኦል፦እንሆ፥ዳዊት፡በእኛ፡ዘንድ፡ተሸሽጓል፡ብለው፡በ ነገሩት፡ጊዜ፤የዳዊት፡ትምህርት።
1፤አቤቱ፥በስምኽ፡አድነኝ፥በኀይልኽም፡ፍረድልኝ።
2፤አቤቱ፥ጸሎቴን፡ስማኝ፥የአፌንም፡ቃል፡አድምጥ፤
3፤እንግዳዎች፡ቁመውብኛልና፥ኀያላንም፡ነፍሴን፡ሽተዋታልና።እግዚአብሔርን፡በፊታቸው፡አላደረጉትም።
4፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡ይረዳኛል፥ጌታዬም፡ለነፍሴ፡ደጋፊዋ፡ነው።
5፤ክፋትን፡ወደ፡ጠላቶቼ፡ይመልሳታል፤በእውነትኽም፡አጥፋቸው።
6፤ከፈቃዴ፡እሠዋልኻለኹ፤አቤቱ፥መልካም፡ነውና፥ስምኽን፡አመሰግናለኹ፤
7፤ከመከራ፡ዅሉ፡አድኖኛልና፥ዐይኔም፡በጠላቶቼ፡ላይ፡አይታለችና።
_______________መዝሙር፡54፡(55)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በበገናዎች፤የዳዊት፡ትምህርት።
1፤አቤቱ፥ጸሎቴን፡አድምጥ፥ልመናዬንም፡ቸል፡አትበል።
2፤ተመልከተኝ፡ስማኝም።በሐዘኔ፡ተቅበዘበዝኹ፡ተናወጥኹም፤
3፤ከጠላት፡ድምፅ፡ከዐመፀኛም፡ግፍ፡የተነሣ፤ዐመፃን፡በላዬ፡ጥለውብኛልና፥በቍጣም፡ጠልተውኛልና።
4፤ልቤ፡በላዬ፡ተናወጠብኝ፥የሞት፡ድንጋጤም፡ወደቀብኝ።
5፤ፍርሀትና፡እንቅጥቅጥ፡መጡብኝ፥ጨለማም፡ሸፈነኝ።
6፤በርሬ፡ዐርፍ፡ዘንድ፡እንደ፡ርግብ፡ክንፍን፡ማን፡በሰጠኝ!
7፤እንሆ፥ኰብልዬ፡በራቅኹ፡በምድረ፡በዳም፡በተቀመጥኹ፤
8፤ከዐውሎና፡ከብርቱ፡ነፋስ፡ሸሽቼ፡በፈጠንኹ፡አልኹ።
9፤አቤቱ፥ግፍንና፡ጠብን፡በከተማ፡ውስጥ፡አይቻለኹና፥አስጥማቸው፥አንደበታቸውንም፡ቍረጥ።
10፤በቀንና፡በሌሊት፡በቅጥሯ፡ይከቧ፟ታል፤ዐመፃና፡ድካም፡ኀጢአትም፡በመካከሏ፡ነው፤
11፤ተንኰልና፡ሽንገላ፡ከአደባባይዋ፡አይርቁም።
12፤ጠላትስ፡ቢሰድበኝ፥በታገሥኹ፡ነበር፤የሚጠላኝም፡ራሱን፡በላዬ፡ከፍ፡ከፍ፡ቢያደርግ፥ከርሱ፡በተሸሸግኹ፡ ነበር።
13፤አንተ፡ግን፥እኩያዬ፡ሰው፥ባልንጀራዬና፡የልቤ፡ወዳጅ፤
14፤መብልን፡ከእኔ፡ጋራ፡በአንድነት፡ያጣፈጥኽ፤ባንድ፡ልብ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ተራመድን።
15፤ሞት፡ይምጣባቸው፤በሕይወት፡ሳሉ፡ወደ፡ሲኦል፡ይውረዱ፤ክፋት፡በማደሪያቸውና፡በመካከላቸው፡ነውና።
16፤እኔ፡ግን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኽኹ፥እግዚአብሔርም፡ሰማኝ።
17፤በማታና፡በጧት፡በቀትርም፡እናገራለኹ፡እጮኽማለኹ፥ቃሌንም፡ይሰማኛል።
18፤በእኔ፡ላይ፡ብዙ፡ነበሩና፥ከሚቃረቡኝ፡ነፍሴን፡በሰላም፡አድናት።
19፤ቤዛ፡የላቸውምና፥እግዚአብሔርንም፡አልፈሩትምና፡ከጥንት፡ዠምሮ፡የነበረ፡እግዚአብሔር፡ሰምቶ፡ያጐሰቍላ ቸዋል።
20፤ከርሱ፡ጋራ፡ሰላም፡በነበሩት፡ላይ፡እጁን፡ዘረጋ፤ኪዳኑንም፡አረከሱ።
21፤አፉ፡ከቅቤ፡ይልቅ፡ለዘበ፥በልቡ፡ግን፡ሰልፍ፡ነበረ፤ቃሎቹም፡ከዘይት፡ይልቅ፡ለሰለሱ፥እነርሱ፡ግን፡እን ደ፡ተመዘዘ፡ሰይፍ፡ናቸው።
22፤ትካዜኽን፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ጣል፥ርሱም፡ይደግፍኻል፤ለጻድቁም፡ለዘለዓለም፡ሁከትን፡አይሰጠውም።
23፤አንተ፡ግን፥አቤቱ፥ወደሞት፡ጕድጓድ፡ታወርዳቸዋለኽ፤የደም፡ሰዎችና፡ሸንጋዮች፡ዘመናቸው፡ግማሽ፡አይሞላ ም፤እኔ፡ግን፥አቤቱ፥እታመንኻለኹ።
_______________መዝሙር፡55፡(56)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ከቅዱሳን፡ስለራቁ፡ሕዝብ፤ፍልስጥኤማውያን፡በጌት፡በያዙት፡ጊዜ፤የዳዊት፡ቅኔ።
1፤አቤቱ፥ሰው፡ረግጦኛልና፥ማረኝ፤ዅልጊዜም፡በሰልፍ፡አስጨንቆኛል።
2፤የሚዋጉኝ፡በዝተዋልና፥ዅልጊዜ፡ቀኑን፡ዅሉ፡ጠላቶቼ፡ረገጡኝ።
3፤እኔ፡ግን፡ፈራኹ፡ባንተም፡ታመንኹ።
4፤በእግዚአብሔር፡ቃሉን፡አመሰግናለኹ፤በእግዚአብሔር፡ታመንኹ፥አልፈራም፤ሰው፡ምን፡ያደርገኛል፧
5፤ዅልጊዜ፡ቃሎቼን፡ያጸይፉብኛል፤በእኔ፡ላይም፡የሚመክሩት፡ዅሉ፡ለክፉ፡ነው።
6፤ይሸምቁብኛል፡ይሸሽጉኝማል፥እነርሱም፡ተረከዜን፡ይመለካከታሉ፥ዅልጊዜም፡ነፍሴን፡ይሸምቁባታል።
7፤በምንም፡ምን፡አታድናቸውም፤አሕዛብን፡በቍጣ፡ትጥላቸዋለኽ።
8፤አምላክ፡ሆይ፥ሕይወቴን፡ነገርኹኽ፤እንባዬን፡እንደ፡ትእዛዝኽ፡በፊትኽ፡አኖርኽ።
9፤በጠራኹኽ፡ጊዜ፡ጠላቶቼ፡ወደ፡ዃላቸው፡ይመለሳሉ፤አንተ፡አምላኬ፡እንደ፡ኾንኽ፥እንሆ፥ዐወቅኹ።
10፤በእግዚአብሔር፡ቃሉን፡አመሰግናለኹ፤በእግዚአብሔር፡ቃሉን፡አከብራለኹ።
11፤በእግዚአብሔር፡ታመንኹ፥አልፈራም፡ሰው፡ምን፡ያደርገኛል፧
12፤አቤቱ፥የምስጋና፡ስእለት፡የምሰጥኽ፡ከእኔ፡ዘንድ፡ነው፤
13፤ነፍሴን፡ከሞት፥እግሮቼን፡ከመውደቅ፡አድነኻልና፥በሕያዋን፡ብርሃን፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡አሠኘው፡ዘንድ ።
_______________መዝሙር፡56፡(57)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤አታጥፋ።ከሳኦል፡ፊት፡ሸሽቶ፡በዋሻ፡በነበረበት፡ጊዜ፤የዳዊት፡ቅኔ።
1፤ማረኝ፥አቤቱ፥ማረኝ፥ነፍሴ፡አንተን፡ታምናለችና፤ጕዳት፡እስክታልፍ፡ድረስ፡በክንፎችኽ፡ጥላ፡እታመናለኹ።
2፤ወደሚረዳኝ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ልዑል፡እግዚአብሔር፡እጮኻለኹ።
3፤ከሰማይ፡ልኮ፡አዳነኝ፥ለረገጡኝም፡ውርደትን፡ሰጣቸው፤እግዚአብሔር፡ቸርነቱንና፡እውነቱን፡ላከ።
4፤ነፍሴን፡ከአንበሳዎች፡መካከል፡አዳናት።ደንግጬ፡ተኛኹ፤የሰው፡ልጆች፡ጥርሳቸው፡ጦርና፡ፍላጻ፥አንደበታቸ ው፡የተሳለ፡ሾተል፡ነው።
5፤አምላክ፡ሆይ፥በሰማያት፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡በል፤ክብርኽም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ትኹን።
6፤ለእግሮቼ፡ወጥመድን፡አዘጋጁ፥ነፍሴንም፡አጐበጧት፤ጕድጓድ፡በፊቴ፡ቈፈሩ፥በርሱም፡ወደቁ።
7፤ልቤ፡ጨካኝ፡ነው፥አቤቱ፥ልቤ፡ጨካኝ፡ነው፤እቀኛለኹ፥እዘምራለኹ።
8፤ክብሬ፡ይነሣ፥በገናና፡መሰንቆም፡ይነሡ፤እኔም፡ማልጄ፡እነሣለኹ።
9፤አቤቱ፥በአሕዛብ፡ዘንድ፡አመሰግንኻለኹ፥በወገኖችም፡ዘንድ፡እዘምርልኻለኹ፤
10፤ምሕረትኽ፡እስከ፡ሰማይ፡ድረስ፡ከፍ፡ብላለችና፥እውነትኽም፡እስከ፡ደመናት፡ድረስ።
11፤አምላክ፡ሆይ፥በሰማያት፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡በል፤ክብርኽም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ትኹን።
_______________መዝሙር፡57፡(58)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤አታጥፋ።የዳዊት፡ቅኔ።
1፤በእውነት፡ጽድቅን፡ብትናገሩስ፥የሰው፡ልጆች፡ሆይ፥በቅን፡ትፈርዳላችኹ፤
2፤በልባችኹ፡በምድር፡ላይ፡ኀጢአትን፡ትሠራላችኹና፥እጆቻችኹም፡ግፍን፡ይታታሉና።
3፤ኃጥኣን፡ከማሕፀን፡ዠምረው፡ተለዩ፤ከሆድም፡ዠምረው፡ሳቱ፥ሐሰትንም፡ተናገሩ።
4፤ቍጣቸው፡እንደ፡እባብ፡መርዝ፡ነው፥እንደምድር፡አውሬም፡ዦሮዋ፡የተደፈነ፡ነው፥
5፤ዐዋቂ፡ሲደግምባት፡የአስማተኛውን፡ቃል፡እንደማትሰማ።
6፤እግዚአብሔር፡ጥርሳቸውን፡በአፋቸው፡ውስጥ፡ይሰብራል፤እግዚአብሔር፡የአንበሳዎቹን፡መንጋጋቸውን፡ያደቃ፟ ል።
7፤እንደሚፈስ፟፡ውሃ፡ይቀልጣሉ፤እስኪያደክማቸው፡ድረስ፡ፍላጻዎቹን፡ይገትራል።
8፤እንደሚቀልጥ፡ሠም፡ያልቃሉ፤እሳት፡ወደቀች፥ፀሓይንም፡አላይዋትም።
9፤እሾኻችኹ፡ሳይታወቅ፡በትር፡ኾነ፤ሕያዋን፡ሳላችኹ፡በመዓቱ፡ይነጥቃችዃል።
10፤ጻድቅ፡በቀልን፡ባየ፡ጊዜ፡ደስ፡ይለዋል፤በኀጢአተኛው፡ደምም፡እጁን፡ይታጠባል።
11፤ሰውም፦በእውነት፡ለጻድቅ፡ፍሬ፡አለው፤በእውነት፡በምድር፡ላይ፡የሚፈርድ፡አምላክ፡አለ፡ይላል።
_______________መዝሙር፡58፡(59)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤አታጥፋ።ሳኦል፡ይገድሉት፡ዘንድ፡ቤቱን፡እንዲጠብቁ፡በላከ፡ጊዜ፤የዳዊት፡ቅኔ።
1፤አምላኬ፡ሆይ፥ከጠላቶቼ፡አድነኝ፤በላዬም፡ከቆሙት፡አስጥለኝ።
2፤ከግፍ፡አድራጊዎች፡ታደገኝ፥ከደም፡ሰዎችም፡አድነኝ።
3፤እንሆ፥ነፍሴን፡ሸምቀውባታልና፥ብርቱዎችም፡በላዬ፡ተሰበሰቡ።አቤቱ፥በበደሌም፡አይደለም፥በኀጢአቴም፡አይ ደለም።
4፤ያለበደል፡ሮጥኹ፥ተዘጋጀኹም፤ተነሥ፥ተቀበለኝ፥እይም።
5፤አንተም፡አቤቱ፥የኀያላን፡አምላክ፥የእስራኤል፡አምላክ፥አሕዛብን፡ዅሉ፡ትጐበኛቸው፡ዘንድ፡ተነሥ፤ዐመፅ፡ የሚያደርጉትን፡ዅሉ፡አትማራቸው።
6፤ማታ፡ይመለሱ፡እንደ፡ውሻዎችም፡ይራቡ፥በከተማም፡ይዙሩ።
7፤እንሆ፥በአፋቸው፡አሰምተው፡ይናገራሉ፤ሰይፍም፡በከንፈሮቻቸው፡አለ፤ማን፡ይሰማል፧ይላሉ።
8፤አንተ፡ግን፡አቤቱ፥ትሥቅባቸዋለኽ፥አሕዛብንም፡ዅሉ፡ትንቃቸዋለኽ።
9፤እግዚአብሔር፡መጠጊያዬ፡ነውና፥ኀይሌን፡ወዳንተ፡አስጠጋለኹ።
10፤የአምላኬ፡ቸርነቱ፡ይገናኘኛል፡አምላኬ፡በጠላቶቼ፡ላይ፡ያሳየኛል።
11፤ሕግኽን፡እንዳይረሱ፡አትግደላቸው፤አቤቱ፡ጋሻዬ፥በኀይልኽ፡በትናቸው፡አውርዳቸውም።
12፤ስለአፋቸው፡ኀጢአት፡ስለከንፈራቸውም፡ቃል፥መርገምንና፡ሐሰትን፡ስለሚናገሩ፥በትዕቢታቸው፡ይጠመዱ።
13፤በቍጣ፡አጥፋቸው፥እንዳይኖሩም፡አጥፋቸው፤የያዕቆብም፡አምላክ፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡እንዲገዛ፡ይወ ቁ።
14፤ማታ፡ይመለሱ፡እንደ፡ውሻዎችም፡ይራቡ፥በከተማም፡ይዙሩ።
15፤እነርሱም፡መብል፡ለመፈለግ፡ይበተኑ፤ያልጠገቡ፡እንደ፡ኾነም፡ያንጐረጕራሉ።
16፤እኔ፡ግን፡ለኀይልኽ፡እቀኛለኹ፤በምሕረትኽም፡ማልዶ፡ደስ፡ይለኛል፤በመከራዬ፡ቀን፡መጠጊያዬና፡ዐምባዬ፡ ኾነኸኛልና።
17፤ረዳቴ፡ሆይ፥ለአንተ፡ለአምላኬ፡እዘምራለኹ፤አንተ፥አምላኬ፥መጠጊያዬ፡ምሕረቴም፡ነኽና።
_______________መዝሙር፡59፡(60)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የሶርያን፡ኹለቱን፡ወንዞችና፡የሶርያን፡ሶባልን፡ባቃጠለ፡ጊዜ፡ኢዮአብም፡ተመልሶ፡ከኤዶ ማውያን፡ሰዎች፡በጨው፡ሸለቆ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ሺሕ፡በገደለ፡ጊዜ፡ለትምህርት፡የዳዊት፡ቅኔ።
1፤አቤቱ፥ጣልኸን፡አፈረስኸንም፤ተቈጣኸን፡ይቅርም፡አልኸን።
2፤ምድርን፡አናወጥኻት፡አወክኻትም፤ተናውጣለችና፡ቍስሏን፡ፈውስ።
3፤ለሕዝብኽ፡ጭንቅን፡አሳየኻቸው፥አስደንጋጩንም፡ወይን፡አጠጣኸን።
4፤ከቀስት፡ፊት፡ያመልጡ፡ዘንድ፥ለሚፈሩኽ፡ምልክትን፡ሰጠኻቸው።
5፤ወዳጆችኽ፡እንዲድኑ፡በቀኝኽ፡አድን፥አድምጠኝም።
6፤እግዚአብሔር፡በቅድስናው፡ተናገረ፤ደስ፡ይለኛል፥ሴኬምንም፡እካፈላለኹ፥የሱኮትንም፡ሸለቆ፡እሰፍራለኹ።
7፤ገለዓድ፡የእኔ፡ነው፥ምናሴም፡የእኔ፡ነው፤ኤፍሬም፡የራሴ፡መጠጊያ፡ነው።ይሁዳ፡ንጉሤ፡ነው፤
8፤ሞዐብ፡መታጠቢያዬ፡ነው፥በኤዶምያስ፡ላይ፡ጫማዬን፡እዘረጋለኹ፤ፍልስጥኤም፡ይገዙልኛል።
9፤ወደ፡ጽኑ፡ከተማ፡ማን፡ይወስደኛል፧ማንስ፡እስከ፡ኤዶምያስ፡ይመራኛል፧
10፤አቤቱ፥የጣልኸን፡አንተ፡አይደለኽምን፧አምላክ፡ሆይ፥ከሰራዊታችን፡ጋራ፡አትወጣም።
11፤በመከራችን፡ረድኤትን፡ስጠን፡የሰውም፡ማዳን፡ከንቱ፡ነው።
12፤በእግዚአብሔር፡ኀይልን፡እናደርጋለን፥ርሱ፡የሚያስጨንቁንን፡ያዋርዳቸዋልና።
_______________መዝሙር፡60፡(61)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በበገናዎች፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አምላክ፡ሆይ፥ልመናዬን፡ስማ፥ጸሎቴንም፡አድምጥ።
2፤ልቤ፡ተስፋ፡በቈረጠ፡ጊዜ፡ከምድር፡ዳርቻ፡ወዳንተ፡እጮኻለኹ፤በድንጋይ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረግኸኝ።
3፤ጽኑ፡ግንብ፡በጠላት፡ፊት፡ተስፋዬም፡ኾነኸኛልና፥መራኸኝ።
4፤በድንኳንኽ፡ለዘለዓለም፡እኖራለኹ፤በክንፎችኽም፡ጥላ፡እጋረዳለኹ፤
5፤አቤቱ፥አንተ፡ስእለቴን፡ሰምተኻልና፤ስምኽንም፡ለሚፈሩ፡ርስትኽን፡ሰጠኻቸው።
6፤ለንጉሥ፡ከቀን፡በላይ፡ቀን፡ትጨምራለኽ፥ዓመታቱም፡ከትውልድ፡ወደ፡ትውልድ፡ይኾናሉ።
7፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፤ይጠብቁት፡ዘንድ፡ምሕረትንና፡እውነትን፡አዘጋጅለት።
8፤እንዲሁ፡ለስምኽ፡ለዘለዓለም፡እዘምራለኹ፡ስእለቴን፡ዅልጊዜ፡እፈጽም፡ዘንድ።
_______________መዝሙር፡61፡(62)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ስለ፡ኤዶታም፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ነፍሴ፡ለእግዚአብሔር፡የምትገዛ፡አይደለችምን፧መድኀኒቴ፡ከርሱ፡ዘንድ፡ናትና።
2፤ርሱ፡አምላኬ፡መድኀኒቴም፡ነውና፤ርሱ፡መጠጊያዬ፡ነው፥እጅግም፡አልታወክም።
3፤እስከ፡መቼ፡በሰው፡ላይ፡ትቆማላችኹ፧እናንተ፡ዅላችኹ፡እንዳዘነበለ፡ግድግዳ፡እንደ፡ፈረሰም፡ቅጥር፡ትገድ ላላችኹ።
4፤ነገር፡ግን፥ክብሬን፡ይሽሩ፡ዘንድ፡መከሩ፥ሐሰትንም፡ይወዳ፟ሉ፤በአፋቸው፡ይባርካሉ፥በልባቸውም፡ይረግማሉ ።
5፤ነገር፡ግን፥ነፍሴ፡ሆይ፥አንቺ፡ለእግዚአብሔር፡ተገዢ፥ተስፋዬ፡ከርሱ፡ዘንድ፡ናትና።
6፤ርሱ፡አምላኬ፡መድኀኒቴም፡ነውና፤ርሱ፡መጠጊያዬ፡ነው፤አልታወክም።
7፤መድኀኒቴና፡ክብሬ፡በእግዚአብሔር፡ነው፤የረድኤቴ፡አምላክ፡ተስፋዬም፡እግዚአብሔር፡ነው።
8፤የሕዝብ፡ማኅበር፡ዅላችኹ፥በርሱ፡ታመኑ፥ልባችኹንም፡በፊቱ፡አፍሱ፟፤እግዚአብሔር፡ረዳታችን፡ነው።
9፤ነገር፡ግን፥የሰው፡ልጆች፡ከንቱ፡ናቸው፥የሰው፡ልጆችም፡ሐሰተኛዎች፡ናቸው፤በሚዛንም፡ይበድላሉ፥እነርሱስ ፡በፍጹም፡ከንቱ፡ናቸው።
10፤ዐመፃን፡ተስፋ፡አታድርጉ፥ቅሚያንም፡አትተማመኑት፤ባለጠግነት፡ቢበዛ፡ልባችኹ፡አይኵራ።
11፤እግዚአብሔር፡አንድ፡ጊዜ፡ተናገረ፥እኔም፡ይህን፡ብቻ፡ሰማኹ፤ኀይል፡የእግዚአብሔር፡ነው፥
12፤አቤቱ፥ምሕረትም፡ያንተ፡ነው፤አንተ፡ለያንዳንዱ፡እንደ፡ሥራው፡ፍዳውን፡ትሰጣለኽና።
_______________መዝሙር፡62፡(63)።______________
በኤዶምያስ፡ምድረ፡በዳ፡በነበረ፡ጊዜ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አምላኬ፥አምላኬ፥ወዳንተ፡እገሠግሣለኹ፤ነፍሴ፡አንተን፡ተጠማች፥ሥጋዬ፡አንተን፡እንዴት፡ናፈቀች፡ዕንጨት ና፡ውሃ፡በሌለበት፡በምድረ፡በዳ።
2፤ኀይልኽንና፡ክብርኽን፡አይ፡ዘንድ፡እንዲሁ፡በመቅደስ፡ውስጥ፡ተመለከትኹኽ።
3፤ምሕረትኽ፡ከሕይወት፡ይሻላልና፥ከንፈሮቼ፡ያመሰግኑኻል።
4፤እንዲህ፡በሕይወቴ፡ዘመን፡አመሰግንኻለኹ፥ባንተም፡ስም፡እጆቼን፡አነሣለኹ።
5፤ነፍሴ፡በቅቤና፡በስብ፡እንደሚጠግቡ፡ትጠግባለች፥ከንፈሮቼም፡ስምኽን፡በደስታ፡ያመሰግናሉ።
6፤በመኝታዬም፡ዐስብኻለኹ፥በማለዳም፡እናገርልኻለኹ፤
7፤ረዳቴ፡ኾነኸኛልና፥በክንፎችኽም፡ጥላ፡ደስ፡ይለኛልና።
8፤ነፍሴ፡በዃላኽ፡ተከታተለች፥እኔንም፡ቀኝኽ፡ተቀበለችኝ።
9፤እነርሱ፡ግን፡ነፍሴን፡ለከንቱ፡ፈለጓት፤ወደ፡ምድር፡ጥልቅ፡ይገባሉ።
10፤ለሰይፍ፡እጅ፡ዐልፈው፡ይሰጣሉ፥የቀበሮም፡ዕድል፡ፈንታ፡ይኾናሉ።
11፤ንጉሥ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይለዋል፤በርሱ፡የሚምል፡ዅሉ፡ይከብራል፥ሐሰትን፡የሚናገር፡አፍ፡ይዘጋ ልና።
_______________መዝሙር፡63፡(64)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ወዳንተ፡በለመንኹ፡ጊዜ፡ጸሎቴን፡ስማኝ፥ከጠላትም፡ፍርሀት፡ነፍሴን፡አድን።
2፤ከክፉዎች፡ሸንጎ፡ከዐመፀኛዎችም፡ብዛት፡ሰውረኝ።
3፤እንደ፡ሰይፍ፡ምላሳቸውን፡አሰሉ፤መራራ፡ነገርን፡ለማድረግ፥
4፤ንጹሕንም፡በስውር፡ለመንደፍ፡ቀስትን፡ገተሩ፤ድንገት፡ይነድፉታል፡አይፈሩምም።
5፤ለእነርሱ፡ለራሳቸው፡ክፉ፡ነገርን፡አጸኑ፤ወጥመድን፡ይሰውሩ፡ዘንድ፡ተማከሩ፤ማንስ፡ያየናል፧ይላሉ።
6፤ዐመፃን፡ፈልጓት፥ሲፈትኑም፡አለቁ፤የሰው፡የውስጥ፡ዐሳቡና፡ልቡ፡የጠለቀ፡ነው፥
7፤እግዚአብሔርም፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።የድንገትም፡ፍላጻ፡ያቈስላቸዋል፤
8፤አንደበታቸው፡ያሰናክላቸዋል፥የሚያይዋቸውም፡ዅሉ፡ይደነግጣሉ።
9፤ሰዎች፡ዅሉ፡ፈሩ፥የእግዚአብሔርንም፡ሥራ፡ተናገሩ፥ሥራውንም፡አስተዋሉ።
10፤ጻድቅ፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይለዋል፥በርሱም፡ይታመናል፤ልባቸውም፡የቀና፡ዅሉ፡እልል፡ይላሉ።
_______________መዝሙር፡64፡(65)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በጽዮን፡ለአንተ፡ምስጋና፡ይገ፟ባ፟ል፥ለአንተም፡ጸሎት፡ይቀርባል።
2፤ሥጋ፡ዅሉ፡ጸሎትን፡ወደምትሰማ፡ወዳንተ፡ይመጣል።
3፤የዐመፃ፡ነገር፡በረታብን፤ኀጢአታችንንስ፡አንተ፡ይቅር፡ትላለኽ።
4፤አንተ፡የመረጥኸው፡በአደባባዮችኽም፡ለማደር፡የተቀበልኸው፡ምስጉን፡ነው፤ከቤትኽ፡በረከት፡እንጠግባለን።
5፤ቤተ፡መቅደስኽ፡ቅዱስ፡ነው፡በጽድቅም፡ድንቅ፡ነው።በምድር፡ዳርቻ፡ዅሉና፡በሩቅ፡ባሕር፡ውስጥ፡ላሉ፡ተስፋ ቸው፡የኾንኽ፥አምላካችንና፡መድኀኒታችን፡ሆይ፥ስማን።
6፤በጕልበትኽ፡ተራራዎችን፡አጸናኻቸው፥በኀይልም፡ታጥቀኻል።
7፤የባሕሩን፡ጥልቀት፡የሞገድንም፡ጩኸት፡ታናውጣለኽ።
8፤ከተኣምራትኽ፡የተነሣ፡አሕዛብ፡ይደነግጣሉ፥በምድር፡ዳርቻም፡የሚኖሩ፡ይፈራሉ፤የጧትንና፡የማታን፡መውጫ፡ ደስ፡ታሠኛቸዋለኽ።
9፤ምድርን፡ጐበኘኻት፡አጠጣኻትም፥ብልጥግናዋንም፡እጅግ፡አበዛኽ፤የእግዚአብሔርን፡ወንዝ፡ውሃን፡የተመላ፡ነ ው፤ምግባቸውን፡አዘጋጀኽ፡እንዲሁ፡ታሰናዳለኽና።
10፤ትልሟን፡ታረካለኽ፥ቦይዋንም፡ታስተካክላለኽ፤በነጠብጣብ፡ታለሰልሳታለኽ፥ቡቃያዋንም፡ትባርካለኽ።
11፤በቸርነትኽ፡ዓመትን፡ታቀዳጃለኽ፥ምድረ፡በዳውም፡ስብን፡ይጠግባል።
12፤የምድረ፡በዳ፡ተራራዎች፡ይረካሉ፥ኰረብታዎችም፡በደስታ፡ይታጠቃሉ።
13፤ማሰማሪያዎች፡መንጋዎችን፡ለበሱ፥ሸለቆዎችም፡በእኽል፡ተሸፈኑ፤በደስታ፡ይጮኻሉ፡ይዘምራሉም።
_______________መዝሙር፡65፡(66)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የመነሣት፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤በምድር፡ያላችኹ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡እልል፡በሉ፥
2፤ለስሙም፡ዘምሩ፥ለምስጋናውም፡ክብርን፡ስጡ።
3፤እግዚአብሔርን፡እንዲህ፡በሉት፦ሥራኽ፡ግሩም፡ነው፤ኀይልኽ፡ብዙ፡ሲኾን፡ጠላቶች፡ዋሹብኽ።
4፤በምድር፡ያሉ፡ዅሉ፡ለአንተ፡ይሰግዳሉ፥ለአንተም፡ይዘምራሉ፥ለስምኽም፡ይዘምራሉ።
5፤ኑ፡የእግዚአብሔርንም፡ሥራ፡እዩ፤ከሰው፡ልጆች፡ይልቅ፡በምክር፡ግሩም፡ነው።
6፤ባሕርን፡የብስ፡አደረጋት፥ወንዙንም፡በእግር፡ተሻገሩ፤በዚያ፡በርሱ፡ደስ፡ይለናል።
7፤በኀይሉ፡ለዘለዓለም፡ይገዛል፤ዐይኖቹ፡ወደ፡አሕዛብ፡ይመለከታሉ፤ዐመፀኛዎች፡ራሳቸውን፡ከፍ፡ከፍ፡አያድር ጉ።
8፤አሕዛብ፡ሆይ፥አምላካችንን፡ባርኩ፥የምስጋናውንም፡ድምፅ፡አሰሙ።
9፤ነፍሴን፡በሕይወት፡ያኖራታል፥እግሮቼንም፡ለመናወጥ፡አልሰጠም።
10፤አቤቱ፥ፈትነኸናልና፥ብርንም፡እንደሚያነጥሩት፡አንጥረኸናልና።
11፤ወደ፡ወጥመድ፡አገባኸን፥በዠርባችንም፡መከራን፡አኖርኽ።
12፤በራሳችን፡ላይ፡ሰውን፡አስረገጥኸን፤በእሳትና፡በውሃ፡መካከል፡ዐለፍን፥ወደ፡ዕረፍትም፡አወጣኸን።
13-14፤ከሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ጋራ፡ወደ፡ቤትኽ፡እገባለኹ፤በመከራዬ፡ጊዜ፡በአፌ፡የተናገርኹትን፡ከንፈሮቼም፡ያ ሉትን፡ስእለቴን፡ለአንተ፡እፈጽማለኹ።
15፤ከዕጣንና፡ከወጠጤዎች፡ጋራ፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ፍሪዳን፡አቀርባለኹ፤ላሞችንና፡ፍየሎችን፡እሠዋልኻለኹ ።
16፤እግዚአብሔርን፡የምትፈሩት፡ዅሉ፥ኑ፥ስሙኝ፤ለነፍሴ፡ያደረገላትን፡ልንገራችኹ።
17፤በአፌ፡ወደ፡ርሱ፡ጮኽኹ፥በአንደበቴም፡አመሰገንኹት።
18፤በልቤስ፡በደልን፡አይቼ፡ብኾን፡ጌታ፡አይሰማኝም፡ነበር።
19፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ሰማኝ፤የልመናዬን፡ድምፅ፡አደመጠ።
20፤ጸሎቴን፡ያልከለከለኝ፡ምሕረቱንም፡ከእኔ፡ያላራቀ፡እግዚአብሔር፡ይመስገን።
_______________መዝሙር፡66፡(67)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በበገናዎች፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ይማረን፡ይባርከንም፥ፊቱንም፡በላያችን፡ያብራ፤
2፤በአሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡ማዳንኽን፥መንገድኽንም፡በምድር፡እናውቅ፡ዘንድ።
3፤አቤቱ፥አሕዛብ፡ያመስግኑኽ፥አሕዛብ፡ዅሉ፡ያመስግኑኽ።
4፤ለአሕዛብ፡በቅን፡ትፈርድላቸዋለኽና፥አሕዛብንም፡በምድር፡ላይ፡ትመራለኽና፡አሕዛብ፡ደስ፡ይበላቸው፡ሐሤት ም፡ያድርጉ።
5፤አቤቱ፥አሕዛብ፡ያመስግኑኽ፥አሕዛብ፡ዅሉ፡ያመስግኑኽ።
6፤ምድር፡ፍሬዋን፡ሰጠች፤እግዚአብሔር፡አምላካችንም፡ይባርከናል።
7፤እግዚአብሔር፡ይባርከናል፥የምድርም፡ዳርቻ፡ዅሉ፡ይፈሩታል።
_______________መዝሙር፡67፡(68)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ይነሣ፥ጠላቶቹም፡ይበተኑ፥የሚጠሉትም፡ከፊቱ፡ይሽሹ።
2፤ጢስ፡እንደሚበን፟፡እንዲሁ፡ይብነኑ፤ሠም፡በእሳት፡ፊት፡እንደሚቀልጥ፥እንዲሁ፡ኃጥኣን፡ከእግዚአብሔር፡ፊ ት፡ይጥፉ።
3፤ጻድቃንም፡ደስ፡ይበላቸው፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ሐሤት፡ያድርጉ፥በደስታም፡ደስ፡ይበላቸው።
4፤ለእግዚአብሔር፡ተቀኙ፡ለስሙም፡ዘምሩ፤ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ለወጣም፡መንገድ፡አድርጉ፤ስሙ፡እግዚአብሔር፡ነው ፥በፊቱም፡ደስ፡ይበላችኹ፤በፊቱም፡ይደነግጣሉ።
5፤እግዚአብሔር፡በቅዱስ፡ቦታው፡ለድኻ፡አደጎች፡አባት፥ለባልቴቶችም፡ዳኛ፡ነው።
6፤እግዚአብሔር፡ብቸኛዎችን፡በቤት፡ያሳድራቸዋል፥እስረኛዎችንም፡በኀይሉ፡ያወጣቸዋል፤ዐመፀኛዎች፡ግን፡በም ድረ፡በዳ፡ይኖራሉ።
7፤አቤቱ፥በሕዝብም፡ፊት፡በወጣኽ፡ጊዜ፥በምድረ፡በዳም፡ባለፍኽ፡ጊዜ፥ምድር፡ተናወጠች፥
8፤ከሲና፡አምላክ፡ፊት፥ከእስራኤል፡አምላክ፡ፊት፡ሰማያትም፡አንጠበጠቡ።
9፤አቤቱ፥የሞገስን፡ዝናብ፡ለርስትኽ፡አዘነብኽ፥በደከመም፡ጊዜ፡አንተ፡አጸናኸው።
10፤እንስሳዎችኽ፡በውስጡ፡ዐደሩ፤አቤቱ፥በቸርነትኽ፡ለድኻዎች፡አዘጋጀኽ።
11፤እግዚአብሔር፡ቃሉን፡ሰጠ፤የሚያወሩት፡ብዙ፡ሰራዊት፡ናቸው።
12፤የሰራዊት፡ነገሥታት፡ፈጥነው፡ይሸሻሉ፤በቤትም፡የምትኖር፡ምርኮን፡ተካፈለች።
13፤በርስቶች፡መካከል፡ብታድሩ፥ከብር፡እንደ፡ተሠሩ፡እንደ፡ርግብ፡ክንፎች፥በቅጠልያ፡ወርቅም፡እንደ፡ተለበ ጡ፡ላባዎቿ፡ትኾናላችኹ።
14፤ሰማያዊ፡ንጉሥ፡በላይዋ፡ባዘዘ፡ጊዜ፥በሰልሞን፡ላይ፡በረዶ፡ዘነበ።
15፤የእግዚአብሔር፡ተራራ፡የለመለመ፡ተራራ፡ነው፤የጸና፡ተራራና፡የለመለመ፡ተራራ፡ነው።
16፤የጸኑ፡ተራራዎች፡ለምን፡ይነሣሉ፧እግዚአብሔር፡ይህን፡ተራራ፡ያድርበት፡ዘንድ፡ወደደው፤በእውነት፡እግዚ አብሔር፡ለዘለዓለም፡ያድርበታል።
17፤የእግዚአብሔር፡ሠረገላዎች፡የብዙ፡ብዙ፡ሺሕ፡ናቸው፤ጌታ፡በመቅደሱ፡በሲና፡በመካከላቸው፡ነው።
18፤ወደ፡ላይ፡ዐረግኽ፥ምርኮን፡ማረክኽ፥ስጦታንም፡ለሰዎች፡ሰጠኽ፥ደግሞም፡ለዐመፀኛዎች፡በዚያ፡ያድሩ፡ዘን ድ።
19፤እግዚአብሔር፡አምላክ፡ቡሩክ፡ነው፤እግዚአብሔር፡በየዕለቱ፡ቡሩክ፡ነው፤የመድኀኒታችን፡አምላክ፡ይረዳና ል።
20፤አምላካችንስ፡የደኅንነት፡አምላክ፡ነው፤ከሞት፡መውጣትም፡ከእግዚአብሔር፡ነው።
21፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡የጠላቶቹን፡ራስ፥በኀጢአት፡የሚኼድንም፡የጠጕሩን፡ዐናት፡ይቀጠቅጣል።
22፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አለ፦ከባሳን፡አመጣቸዋለኹ፥ከባሕርም፡ጥልቅ፡እመልሳቸዋለኹ፥
23፤እግሮችኽ፡በደም፡ይረገጡ፡ዘንድ፥የውሻዎችኽ፡ምላስ፡በጠላቶች፡ላይ፡ይኾን፡ዘንድ።
24፤የአምላኬ፡የንጉሥ፡መንገድ፡በመቅደሱ፥አቤቱ፥መንገድኽ፡ተገለጠ።
25፤አለቃዎች፡ቀደሙ፥መዘምራንም፡ተከተሉ፤ከበሮን፡በሚመቱ፡በቈነዣዥት፡መካከል።
26፤እግዚአብሔርን፡በጉባኤ፥ጌታችንንም፡በእስራኤል፡ምንጭ፡አመስግኑት።
27፤ወጣቱ፡ብንያም፡በጕልበቱ፡በዚያ፡አለ፥ገዢዎቻቸው፡የይሁዳ፡አለቃዎች፡የዛብሎን፡አለቃዎችና፡የንፍታሌም ም፡አለቃዎች።
28፤አቤቱ፥ኀይልኽን፡እዘዝ፤አቤቱ፥ይህንም፡ለእኛ፡የሠራኸውን፡አጽናው።
29፤በኢየሩሳሌም፡ስላለው፡መቅደስኽ፡ነገሥታት፡እጅ፡መንሻን፡ለአንተ፡ያመጣሉ።
30፤በሸምበቆ፡ውስጥ፡ያሉትን፡አራዊት፥በአሕዛብ፡ውስጥ፡ያሉትን፡የበሬዎችንና፡የወይፈኖችን፡ጉባኤ፡ገሥጽ፥ እንደ፡ብር፡የተፈተኑት፡አሕዛብ፡እንዳይዘጉ፤ሰልፍን፡የሚወዱትን፡አሕዛብን፡በትናቸው።
31፤መኳንንት፡ከግብጽ፡ይመጣሉ፤ኢትዮጵያ፡እጆቿን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ትዘረጋለች።
32፤የምድር፡ነገሥታት፥ለእግዚአብሔር፡ተቀኙ፥ለጌታም፡ዘምሩ።
33፤በምሥራቅ፡በኩል፡ወደ፡ሰማየ፡ሰማያት፡ለወጣ፡ለእግዚአብሔር፡ዘምሩ፤የኀይል፡ቃል፡የኾነ፡ቃሉን፥እንሆ፥ ይሰጣል።
34፤ለእግዚአብሔር፡ክብርን፡ስጡ፤ግርማው፡በእስራኤል፡ላይ፥ኀይሉም፡በደመናት፡ላይ፡ነው።
35፤እግዚአብሔር፡በቅዱሳኑ፡ላይ፡ድንቅ፡ነው፤የእስራኤል፡አምላክ፡ርሱ፡ኀይልን፡ብርታትንም፡ለሕዝቡ፡ይሰጣ ል፤እግዚአብሔርም፡ይመስገን።
_______________መዝሙር፡68፡(69)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በመለከቶች፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ውሃ፡እስከ፡ነፍሴ፡ደርሶብኛልና፥አድነኝ።
2፤በጥልቅ፡ረግረግ፡ጠለቅኹ፡መቋሚያም፡የለኝም።ወደ፡ጥልቅ፡ባሕር፡ገባኹ፡ማዕበልም፡አሰጠመኝ።
3፤በጩኸት፡ደከምኹ፡ጕረሮዬም፡ሰለለ፤አምላኬን፡ስጠብቅ፡ዐይኖቼ፡ፈዘዙ።
4፤በከንቱ፡የሚጠሉኝ፡ከራሴ፡ጠጕር፡በዙ፤በዐመፅ፡ያሚያሳድዱኝ፡ጠላቶቼ፡በረቱ፤በዚያን፡ጊዜ፡ያልቀማኹትን፡ መለስኹ።
5፤አቤቱ፥አንተ፡ስንፍናዬን፡ታውቃለኽ፥ኀጢአቴም፡ከአንተ፡አልተሰወረም።
6፤አቤቱ፡የሰራዊት፡አምላክ፥ተስፋ፡የሚያደርጉኽ፡በእኔ፡አይፈሩ፤የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥የሚሹኽ፡በእኔ፡ አይነወሩ።
7፤ስለ፡አንተ፡ስድብን፡ታግሻለኹና፥ዕፍረትም፡ፊቴን፡ሸፍናለችና።
8፤ለወንድሞቼ፡እንደ፡ሌላ፥ለእናቴ፡ልጆችም፡እንደ፡እንግዳ፡ኾንኹባቸው፥
9፤የቤትኽ፡ቅንአት፡በልታኛለችና፥የሚሰድቡኽም፡ስድብ፡በላዬ፡ወድቋልና።
10፤ነፍሴን፡በጾም፡አስመረርዃት፥ለስድብም፡ኾነብኝ።
11፤ማቅ፡ለበስኹ፡ምሳሌም፡ኾንኹላቸው።
12፤በደጅ፡የሚቀመጡ፡በእኔ፡ይጫወታሉ፤ወይን፡የሚጠጡ፡እኔን፡ይዘፍናሉ።
13፤አቤቱ፥በመልካሙ፡ጊዜ፡ጸሎቴ፡ወዳንተ፡ነው፤አቤቱ፥በምሕረትኽ፡ብዛት፡በማዳንኽም፡እውነት፡አድምጠኝ።
14፤እንዳይውጠኝ፡ከረግረግ፡አውጣኝ፤ከሚጠሉኝና፡ከጥልቅ፡ውሃ፡አስጥለኝ።
15፤የውሃው፡ማዕበል፡አያስጥመኝ፥ጥልቁም፡አይዋጠኝ፥ጕድጓድም፡አፉን፡በእኔ፡ላይ፡አይዝጋ።
16፤አቤቱ፥ምሕረትኽ፡መልካም፡ናትና፥ስማኝ።እንደ፡ርኅራኄኽም፡ብዛት፡ወደ፡እኔ፡ተመልከት፤
17፤ከባሪያኽም፡ፊትኽን፡አትሰውር፤ተጨንቄያለኹና፡ፈጥነኽ፡አድምጠኝ።
18፤ነፍሴን፡ተመልክተኽ፡ተቤዣት፤ስለ፡ጠላቶቼም፡አድነኝ።
19፤አንተ፡ስድቤን፡ዕፍረቴንም፡ነውሬንም፡ታውቃለኽ፤የሚያስጨንቁኝ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ናቸው።
20፤ነፍሴ፡ስድብንና፡ኃሣርን፡ታገሠች፤አስተዛዛኝም፡ተመኘኹ፡አላገኘኹም።የሚያጽናናኝም፡ዐጣኹ።
21፤ለመብሌ፡ሐሞት፡ሰጡኝ፥ለጥማቴም፡ሖምጣጤ፡አጠጡኝ።
22፤ማእዳቸው፡በፊታቸው፡ለወጥመድ፡ለፍዳ፡ለዕንቅፋት፡ትኹንባቸው፤
23፤ዐይኖቻቸው፡እንዳያዩ፡ይጨልሙ፥ዠርባቸውም፡ዘወትር፡ይጕበጥ።
24፤መዓትኽን፡በላያቸው፡አፍስ፟፥የቍጣኽ፡መቅሠፍትም፡ያግኛቸው።
25፤ማደሪያቸው፡በረሓ፡ትኹን፥በድንኳኖቻቸውም፡የሚቀመጥ፡አይገኝ፤
26፤አንተ፡የቀሠፍኸውን፡እነርሱ፡አሳድደዋልና፥በቍስሌም፡ላይ፡ጥዝጣዜ፡ጨመሩብኝ።
27፤በኀጢአታቸው፡ላይ፡ኀጢአትን፡ጨምርባቸው፥በጽድቅኽም፡አይግቡ።
28፤ከሕያዋን፡መጽሐፍ፡ይደምሰሱ፥ከጻድቃንም፡ጋራ፡አይጻፉ።
29፤እኔ፡ችግረኛና፡ቍስለኛ፡ነኝ፤አቤቱ፥የፊትኽ፡መድኀኒት፡ይቀበለኝ።
30፤የእግዚአብሔርን፡ስም፡በዝማሬ፡አመሰግናለኹ፥በምስጋናም፡ከፍ፡ከፍ፡አደርገዋለኹ።
31፤ቀንድና፡ጥፍር፡ካበቀለ፡ከእንቦሳ፡ይልቅ፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ያሠኘዋል።
32፤ችግረኛዎች፡ያያሉ፡ደስ፡ይላቸዋል፤እግዚአብሔርን፡ፈልጉ፡ሕያዋንም፡ኹኑ።
33፤እግዚአብሔር፡ችግረኛዎችን፡ሰምቷልና፥እስረኛዎቹንም፡አልናቀምና።
34፤ሰማይና፡ምድር፡ባሕርም፡በርሷም፡የሚንቀሳቀስ፡ዅሉ፡ያመሰግኑታል።
35፤እግዚአብሔር፡ጽዮንን፡ያድናታልና፥የይሁዳንም፡ከተማዎች፡ይሠራልና፤በዚያም፡ይቀመጣሉ፥ይወርሷትማል።
36፤የባሪያዎቹ፡ዘር፡ይኖሩባታል።ስሙንም፡የሚወዱ፡በዚያ፡ይቀመጣሉ።
_______________መዝሙር፡69፡(70)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ለመታሰቢያ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥እኔን፡ለማዳን፡ተመልከት፤አቤቱ፥እኔን፡ለመርዳት፡ፍጠን።
2፤ነፍሴን፡የሚሿት፡ይፈሩ፡ይጐስቍሉም፥ክፉንም፡የሚመክሩብኝ፡ወደ፡ዃላቸው፡ይመለሱ፡ይፈሩም።
3፤እንኳ! እንኳ! የሚሉኝ፡ዐፍረው፡ወዲያው፡ወደ፡ዃላቸው፡ይመለሱ።
4፤የሚሹኽ፡ዅሉ፡ባንተ፡ሐሤት፡ያድርጉ፡ደስ፡ይበላቸው፤ማዳንኽን፡የሚወዱ፡ዅልጊዜ፦እግዚአብሔር፡ታላቅ፡ነው ፡ይበሉ።
5፤እኔ፡ችግረኛና፡ምስኪን፡ነኝ፤አቤቱ፥ርዳኝ፤ረዳቴ፡ታዳጊዬም፡አንተ፡ነኽ፤አቤቱ፥አትዘግይ።
_______________መዝሙር፡70፡(71)።______________
አስቀድመው፡ስለ፡ማረኩ፡ስለዐሚናዳብ፡ልጆች፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥አንተን፡ታመንኹ፤ለዘለዓለም፡አልፈር።
2፤በጽድቅኽ፡አስጥለኝ፡ታደገኝም፤ዦሮኽን፡ወደ፡እኔ፡አዘንብል፡አድነኝም።
3፤በጠንካራ፡ቦታ፡ታድነኝ፡ዘንድ፡አምላክና፡መሸሸጊያ፡ኹነኝ፤ኀይሌ፡መጠጊያዬ፡አንተ፡ነኽና።
4፤አምላኬ፥ከኀጢአተኛ፡እጅ፥ከዐመፀኛና፡ከግፈኛም፡እጅ፡አድነኝ።
5፤አቤቱ፥አንተ፡ተስፋዬ፡ነኽና፥እግዚአብሔር፡ሆይ፥ከታናሽነቴ፡ዠምረኽ፡መታመኛዬ፡ነኽና።
6፤ከማሕፀን፡ዠምሮ፡ባንተ፡ተደገፍኹ፥ከእናቴም፡ሆድ፡ዠምሮ፡አንተ፡መሸሸጊያዬ፡ነኽ፤ዅልጊዜም፡ዝማሬዬ፡ለአ ንተ፡ነው።
7፤ለብዙዎች፡መደነቂያ፡ኾንኹ፤አንተ፡ግን፡ብርቱ፡መጠጊያዬ፡ነኽ።
8፤አፌን፡ምስጋና፡ምላ፡ዅልጊዜ፡ክብርኽንና፡ግርማኽን፡እዘምር፡ዘንድ።
9፤በእርጅናዬ፡ዘመን፡አትጣለኝ፥ጕልበቴም፡ባለቀ፡ጊዜ፡አትተወኝ።
10፤ጠላቶቹ፡በላዬ፡ተናግረዋልና፤ነፍሴንም፡የሚሿት፡በአንድነት፡ተማክረዋልና፥እንዲህም፡አሉ።
11፤እግዚአብሔር፡ትቶታል፤የሚያድነው፡የለምና፡ተከትላችኹ፡ያዙት።
12፤አምላክ፡ሆይ፥ከእኔ፡አትራቅ፤አምላኬ፡ሆይ፥እኔን፡ለመርዳት፡ፍጠን።
13፤ነፍሴን፡የሚቃወሟት፡ይፈሩ፡ይጥፉም፥ጕዳቴንም፡የሚፈልጉ፡ዕፍረትንና፡ኃሣርን፡ይልበሱ።
14፤እኔ፡ግን፡ዅልጊዜ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ፥በምስጋናኽም፡ዅሉ፡ላይ፡እጨምራለኹ።
15፤ሥራን፡አላውቅምና፡አፌ፡ጽድቅኽን፡ዅልጊዜም፡ማዳንኽን፡ይናገራል።
16፤በእግዚአብሔር፡ኀይል፡እገባለኹ፤አቤቱ፥ጽድቅኽን፡ብቻ፡ዐስባለኹ።
17፤አምላኬ፥ከታናሽነቴ፡ዠምረኽ፡አስተማርኸኝ፤እስከ፡ዛሬም፡ተኣምራትኽን፡እነግራለኹ።
18፤እስካረጅም፡እስክሸመግልም፡ድረስ፥ለሚመጣ፡ትውልድም፡ዅሉ፡ክንድኽን፡ኀይልኽንም፡ጽድቅኽንም፡እስክነግ ር፡ድረስ፥አቤቱ፥አትተወኝ።
19፤አቤቱ፥እስከ፡አርያም፡ታላላቅ፡ነገሮችን፡አደረግኽ፤አምላክ፡ሆይ፥እንደ፡አንተ፡ያለ፡ማን፡ነው፧
20፤ብዙ፡ጭንቀትንና፡መከራን፡አሳይተኸኛልና፥ተመለስኽ፡ሕያውም፡አደረግኸኝ፤ከምድር፡ጥልቅም፡እንደ፡ገና፡ አወጣኸኝ።
21፤ጽድቅኽንም፡አብዛው፥ተመልሰኽም፡ደስ፡አሠኘኝ፥ከጥልቅም፡እንደ፡ገና፡አወጣኸኝ።
22፤እኔም፡በበገና፡ስለ፡እውነትኽ፡አመሰግንኻለኹ፤የእስራኤል፡ቅዱስ፡አምላክ፡ሆይ፥በመሰንቆ፡እዘምርልኻለ ኹ።
23፤ዝማሬን፡ባቀርብኹልኽ፡ጊዜ፡ከንፈሮቼ፡ደስ፡ይላቸዋል፥አንተ፡ያዳንኻትም፡ነፍሴ።
24፤ጕዳቴን፡የሚሹ፡ባፈሩና፡በተነወሩ፡ጊዜ፡አንደበቴ፡ደግሞ፡ዅልጊዜ፡ጽድቅኽን፡ይናገራል።
_______________መዝሙር፡71፡(72)።______________
ስለ፡ሰሎሞን።
1፤አቤቱ፥ፍርድኽን፡ለንጉሥ፡ስጥ፥ጽድቅኽንም፡ለንጉሥ፡ልጅ፥
2፤ሕዝብኽን፡በጽድቅ፥ችግረኛዎችኽንም፡በፍርድ፡ይዳኝ፡ዘንድ።
3፤ተራራዎችና፡ኰረብታዎች፡ለሕዝብኽ፡ሰላምን፡ይቀበሉ።
4፤ለችግረኛዎች፡ሕዝብ፡በጽድቅ፡ትፈርዳለኽ፡የድኻዎችንም፡ልጆች፡ታድናለኽ፤ክፉውንም፡ታዋርደዋለኽ።
5፤ፀሓይ፡በሚኖርበት፡ዘመን፡ዅሉ፥በጨረቃም፡ፊት፡ለፊት፡ለልጅ፡ልጅ፡ይኖራል።
6፤እንደ፡ዝናብ፡በታጨደ፡መስክ፡ላይ፥በምድርም፡ላይ፡እንደሚንጠባጠብ፡ጠብታ፡ይወርዳል።
7፤በዘመኑም፡ጽድቅ፡ያብባል፥ጨረቃም፡እስኪያልፍ፡ድረስ፡ሰላም፡ብዙ፡ነው።
8፤ከባሕር፡እስከ፡ባሕር፡ድረስ፥ከወንዝም፡እስከ፡ምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ይገዛል።
9፤በፊቱም፡ኢትዮጵያ፡ይሰግዳሉ፥ጠላቶቹም፡ዐፈር፡ይልሳሉ።
10፤የተርሴስና፡የደሴቶች፡ነገሥታት፡ስጦታን፡ያመጣሉ፤የዐረብና፡የሳባ፡ነገሥታት፡እጅ፡መንሻን፡ያቀርባሉ።
11፤ነገሥታት፡ዅሉ፡ይሰግዱለታል።አሕዛብም፡ዅሉ፡ይገዙለታል።
12፤ችግረኛውን፡ከቀማኛው፡እጅ፥ረዳት፡የሌለውንም፡ምስኪን፡ያድነዋልና።
13፤ለችግረኛና፡ለምስኪን፡ይራራል፥የችግረኛዎችንም፡ነፍስ፡ያድናል።
14፤ከግፍና፡ከጭንቀት፡ነፍሳቸውን፡ያድናል፤ስማቸው፡በፊቱ፡ክቡር፡ነው።
15፤ርሱ፡ይኖራል፡ከዐረብም፡ወርቅ፡ይሰጡታል፤ዅልጊዜም፡ወደ፡ርሱ፡ይጸልያሉ፥ዘወትርም፡ይባርኩታል።
16፤በምድር፡ውስጥ፡በተራራዎች፡ላይ፡መጠጊያ፡ይኾናል፤ፍሬውም፡ከሊባኖስ፡ይልቅ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፤እንደምድ ር፡ሣር፡በከተማ፡ይበቅላል።
17፤ስሙ፡ለዘለዓለም፡ቡሩክ፡ይኾናል፥ከፀሓይም፡አስቀድሞ፡ስሙ፡ይኖራል፤የምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡በርሱ፡ይባረ ካሉም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ያመሰግኑታል።
18፤ብቻውን፡ተኣምራትን፡የሚያደርግ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረክ።
19፤የምስጋናው፡ስም፡ለዓለምና፡ለዘለዓለም፡ይባረክ፤ምስጋናውም፡ምድርን፡ዅሉ፡ይምላ።ይኹን፤ይኹን።
20፤የእሴይ፡ልጅ፡የዳዊት፡መዝሙር፡ተፈጸመ።
_______________መዝሙር፡72፡(73)።______________
የአሣፍ፡መዝሙር።
1፤ልባቸው፡ለቀና፡ለእስራኤል፡እግዚአብሔር፡እንዴት፡ቸር፡ነው።
2፤እኔ፡ግን፡እግሮቼ፡ሊሰናከሉ፥አረማመዴም፡ሊወድቅ፡ትንሽ፡ቀረ።
3፤የኀጢአተኛዎችን፡ሰላም፡አይቼ፡በዐመፀኛዎች፡ቀንቼ፡ነበርና።
4፤ለሞታቸው፡መጣጣር፡የለውምና፤ኀይላቸውም፡ጠንካራ፡ነውና።
5፤እንደ፡ሰው፡በድካም፡አልኾኑም፥ከሰው፡ጋራም፡አልተገረፉም።
6፤ስለዚህ፥ትዕቢት፡ያዛቸው፤ኀጢአትንና፡በደልን፡ተጐናጸፏት።
7፤ዐይናቸው፡ስብ፡ስለ፡ኾነ፡ወጣ፤ልባቸውም፡ከምኞታቸው፡ይልቅ፡አገኘ።
8፤ዐስበው፡ክፉ፡ነገርን፡ተናገሩ።ከፍ፡ከፍ፡ብለውም፡በዐመፃ፡ተናገሩ።
9፤አፋቸውን፡በሰማይ፡አኖሩ፥አንደበታቸውም፡በምድር፡ውስጥ፡ተመላለሰ።
10፤ስለዚህ፥ሕዝቤ፡ወደዚህ፡ይመለሳሉ፤ፍጹም፡ጊዜም፡በላያቸው፡ይገኛል፤
11፤እግዚአብሔር፡እንዴት፡ያውቃል፧በልዑልስ፡ዘንድ፡በእውኑ፡ዕውቀት፡አለ፧ይላሉ።
12፤እንሆ፥እነዚህ፡ኀጢአተኛዎች፡ይደሰታሉ፥ዅልጊዜም፡ባለጠግነታቸውን፡ያበዛሉ።
13፤እንዲህም፡አልኹ፦በእውኑ፡ልቤን፡በከንቱ፡አጸደቅኹ፥እጆቼንም፡በንጽሕና፡በከንቱ፡አጠብኹ።
14፤ዅልጊዜም፡የተገረፍኹ፡ኾንኹ፥መሰደቤም፡በማለዳ፡ነው።
15፤እንደዚህ፡ብዬ፡ብናገር፡ኖሮ፥እንሆ፥የልጆችኽን፡ትውልድ፡በበደልኹ፡ነበር።
16፤ዐውቅም፡ዘንድ፡ዐሰብኹ፥ይህ፡ግን፡በፊቴ፡ችግር፡ነበረ።
17፤ወደእግዚአብሔር፡መቅደስ፡እስክገባ፡ድረስ፥ፍጻሜያቸውንም፡እስካስተውል፡ድረስ።
18፤በድጥ፡ስፍራ፡አስቀመጥኻቸው፥ወደ፡ጥፋትም፡ጣልኻቸው።
19፤እንዴት፡ለጥፋት፡ኾኑ! በድንገት፡አለቁ፡ስለ፡ኀጢአታቸውም፡ጠፉ።
20፤ከሕልም፡እንደሚነቃ፥አቤቱ፥ስትነቃ፡ምልክታቸውን፡ታስነውራለኽ።
21፤ልቤ፡ነዷ፟ልና፥ኵላሊቴም፡ቀልጧልና፤
22፤እኔ፡የተናቅኹ፡ነኝ፡አላውቅኹምም፥ባንተ፡ዘንድም፡እንደ፡እንስሳ፡ኾንኹ።
23፤እኔ፡ግን፡ዘወትር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝ፥ቀኝ፡እጄንም፡ያዝኸኝ።
24፤ባንተ፡ምክር፡መራኸኝ፤ከክብር፡ጋራ፡ተቀበልኸኝ።
25፤በሰማይ፡ያለኝ፡ምንድር፡ነው፧በምድርስ፡ውስጥ፡ከአንተ፡ዘንድ፡ምን፡እሻለኹ፧
26፤የልቤ፡አምላክ፡ሆይ፥ልቤና፡ሥጋዬ፡አለቀ፤እግዚአብሔር፡ግን፡ለዘለዓለም፡ዕድል፡ፈንታዬ፡ነው።
27፤እንሆ፥ከአንተ፡የሚርቁ፡ይጠፋሉና፡ከአንተ፡ርቀው፡የሚያመነዝሩትንም፡ዅሉ፡አጠፋኻቸው።
28፤ለእኔ፡ግን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡መቅረብ፡ይሻለኛል፤መታመኛዬም፡እግዚአብሔር፡ነው፡በጽዮን፡ልጅ፡በሮች፡ ምስጋናኽን፡ዅሉ፡እናገር፡ዘንድ።
_______________መዝሙር፡73፡(74)።______________
የአሣፍ፡ትምህርት።
1፤አቤቱ፥ስለ፡ምን፡ለዘወትር፡ጣልኸኝ፧በማሰማሪያኽ፡በጎች፡ላይስ፡ቍጣኽን፡ስለ፡ምን፡ተቈጣኽ፧
2፤አስቀድመኽ፡የፈጠርኻትን፡ማኅበርኽን፥የተቤዠኻትንም፡የርስትኽን፡በትር፥በርሷ፡ያደርኽባትን፡የጽዮንን፡ ተራራ፡ዐስብ።
3፤ጠላት፡በቅዱሳንኽ፡ላይ፡እንደ፡ከፋ፟፡መጠን፥ዅልጊዜም፡በትዕቢታቸው፡ላይ፡እጅኽን፡አንሣ።
4፤ጠላቶችኽ፡በበዓል፡መካከል፡ተመኩ፤የማያውቁትንም፡ምልክት፡ምልክታቸው፡አደረጉ።
5፤እንደ፡ላይኛው፡መግቢያ፡ውስጥ፡በዱር፡እንዳሉም፡ዕንጨቶች፥በመጥረቢያ፡በሮቿን፡ሰበሩ።
6፤እንዲሁ፡በመጥረቢያና፡በመዶሻ፡ሰበሯት።
7፤መቅደስኽን፡በእሳት፡አቃጠሉ፤የስምኽንም፡ማደሪያ፡በምድር፡ውስጥ፡አረከሱ።
8፤አንድ፡ኾነው፡በልባቸው፡በየሕዝባቸው።ኑ፥የእግዚአብሔርን፡በዓሎች፡ከምድር፡እንሻር፡አሉ።
9፤ምልክታችንን፡አናይም፡ከእንግዲህ፡ወዲህም፡ነቢይ፡የለም፤እስከ፡መቼ፡እንዲኖር፡የሚያውቅ፡በኛ፡ዘንድ፡የ ለም።
10፤አቤቱ፥ጠላት፡እስከ፡መቼ፡ይሳደባል፧ስምኽን፡ጠላት፡ዅልጊዜ፡ያቃልላልን፧
11፤ቀኝኽንም፡በብብትኽ፡መካከል፥እጅኽንም፡ፈጽመኽ፡ለምን፡ትመልሳለኽ፧
12፤እግዚአብሔር፡ግን፡ከዓለም፡አስቀድሞ፡ንጉሥ፡ነው፥በምድርም፡መካከል፡መድኀኒትን፡አደረገ።
13፤አንተ፡ባሕርን፡በኀይልኽ፡አጸናኻት፤አንተ፡የእባቦችን፡ራስ፡በውሃ፡ውስጥ፡ሰበርኽ።
14፤አንተም፡የዘንዶውን፡ራሶች፡ቀጠቀጥኽ፤ለኢትዮጵያ፡ሰዎችም፡ምግባቸውን፡ሰጠኻቸው።
15፤አንተ፡ምንጮቹንና፡ፈሳሾቹን፡ሰነጠቅኽ፤አንተ፡ዅልጊዜ፡የሚፈሱ፟ትን፡ወንዞች፡አደረቅኽ።
16፤ቀኑ፡የአንተ፡ነው፡ሌሊቱም፡የአንተ፡ነው፤አንተ፡ፀሓዩንና፡ጨረቃውን፡አዘጋጀኽ።
17፤አንተ፡የምድርን፡ዳርቻ፡ዅሉ፡ሠራኽ፤በጋንም፡ክረምትንም፡አንተ፡አደረግኽ።
18፤ይህን፡ፍጥረትኽን፡ዐስብ።ጠላት፡እግዚአብሔርን፡ተላገደ፥ሰነፍ፡ሕዝብም፡ስሙን፡አስቈጣ።
19፤የምትገዛልኽን፡ነፍስ፡ለአራዊት፡አትስጣት፤የችግረኛዎችኽን፡ነፍስ፡ለዘወትር፡አትርሳ።
20፤ወደ፡ኪዳንኽ፡ተመልከት፥የምድር፡የጨለማ፡ስፍራዎች፡በኃጥኣን፡ቤቶች፡ተሞልተዋልና።
21፤ችግረኛ፡ዐፍሮ፡አይመለስ፤ችግረኛና፡ምስኪን፡ስምኽን፡ያመሰግናሉ።
22፤አቤቱ፥ተነሥ፡በቀልኽንም፡ተበቀል፤ሰነፎች፡ዅልጊዜም፡የተላገዱኽን፡ዐስብ።
23፤የባሪያዎችኽን፡ቃል፡አትርሳ፤የጠላቶችኽ፡ኵራት፡ዅልጊዜ፡ወዳንተ፡ይወጣል።
_______________መዝሙር፡74፡(75)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤አታጥፋ።የአሣፍ፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥እናመሰግንኻለን፡እናመሰግንኻለን፡ስምኽንም፡እንጠራለን፤ተኣምራትኽን፡ዅሉ፡እናገራለኹ።
2፤ጊዜውን፡ስቀበል፡እኔ፡በቅን፡እፈርዳለኹ።
3፤ምድርና፡በርሷ፡ውስጥ፡የሚኖሩት፡ዅሉ፡ቀለጡ፥እኔም፡ምሰሶዎቿን፡አጠናኹ።
4፤ዐመፀኛዎችን፦አትበድሉ፡አልዃቸው፥ኀጢአተኛዎችንም፦ቀንዳችኹን፡አታንሡ፤
5፤ቀንዳችኹን፡እስከ፡ላይ፡አታንሡ፥በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ዐመፅን፡አትናገሩ።
6፤ክብር፡ከምሥራቅ፡ወይም፡ከምዕራብ፡ወይም፡ከምድረ፡በዳ፡የለምና፤
7፤እግዚአብሔር፡ፈራጅ፡ነውና፥ይህን፡ያዋርዳል፡ይህንም፡ያከብራል።
8፤ጽዋ፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ነውና፤ያልተቀላቀለ፡የወይን፡ጠጅ፡ሞላበት፤ከዚህ፡ወደዚያ፡አገላበጠው፥ነገር፡ ግን፥አተላው፡አልፈሰሰም፤የምድር፡ኀጢአተኛዎች፡ዅሉ፡ይጠጡታል።
9፤እኔ፡ግን፡ለዘለዓለም፡ደስ፡ይለኛል፥ለያዕቆብም፡አምላክ፡ዝማሬን፡አቀርባለኹ።
10፤የኃጥኣንን፡ቀንዶች፡ዅሉ፡እሰብራለኹ፤የጻድቃን፡ቀንዶች፡ግን፡ከፍ፡ከፍ፡ይላሉ።
_______________መዝሙር፡75፡(76)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በበገናዎች፤ስለ፡አሶራውያን፤የአሣፍ፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡በይሁዳ፡ታወቀ፥ስሙም፡በእስራኤል፡ታላቅ፡ነው።
2፤ስፍራው፡በሳሌም፥ማደሪያውም፡በጽዮን፡ነው።
3፤በዚያም፡የቀስትን፡ኀይል፥ጋሻን፡ሰይፍን፡ሰልፍንም፡ሰበረ፤በዚያም፡ቀንዶችን፡ሰበረ።
4፤አንተ፡በዘለዓለም፡ተራራዎች፡ኾነኽ፡በድንቅ፡ታበራለኽ።
5፤ልበ፡ሰነፎች፡ዅሉ፡ደነገጡ፥እንቅልፋቸውንም፡አንቀላፉ፤ባለጠጋዎች፡ዅሉ፡በእነርሱ፡እጅ፡ምንም፡አላገኙም ።
6፤የያዕቆብ፡አምላክ፡ሆይ፥ከተግሣጽኽ፡የተነሣ፡ፈረሰኛዎች፡ዅሉ፡አንቀላፉ።
7፤አንተ፡ግን፥አንተ፡ግሩም፡ነኽ፤ቍጣኽን፡ማን፡ይቃወማል፧
8፤ፍርድን፡ከሰማይ፡አሰማኽ፤ምድር፡ፈራች፡ዝምም፡አለች፥
9፤ልበ፡የዋሃንን፡ያድን፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ለፍርድ፡በተነሣ፡ጊዜ።
10፤ሰው፡በፈቃዱ፡ያመሰግንኻልና፥ከኅሊናቸው፡ትርፍም፡በዓልኽን፡ያደርጋሉ።
11፤ለአምላካችን፡ለእግዚአብሔር፡ስእለትን፡ክፈሉ፤በዙሪያው፡ያሉ፡ዅሉ፡እጅ፡መንሻን፡ለሚያስፈራው፡ያገባሉ ።
12፤የመኳንንትን፡ነፍስ፡ያወጣል፤በምድርም፡ነገሥታት፡ዘንድ፡ያስፈራል።
_______________መዝሙር፡76፡(77)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤ስለ፡ኤዶታም፤የአሣፍ፡መዝሙር።
1፤በቃሌ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኽኹ፥ቃሌም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ነው፥ርሱም፡አደመጠኝ።
2፤በመከራዬ፡ቀን፡እግዚአብሔርን፡ፈለግኹት፤እጆቼ፡በሌሊት፡በፊቱ፡ናቸው፥አላረፍኹምም፥ነፍሴም፡መጽናናትን ፡አልቻለችም።
3፤እግዚአብሔርን፡ዐሰብኹት፡ደስ፡አለኝም፤ተናገርኹ፥ነፍሴም፡ፈዘዘች።
4፤ዐይኖቼ፡እንዲተጉ፡ያዝኻቸው፤ደነገጥኹ፡አልተናገርኹም።
5፤የዱሮውን፡ዘመን፡ዐሰብኹ፤የዘለዓለሙን፡ዓመታት፡ዐሰብኹ፤አጠናጠንኹም፡
6፤በሌሊት፡ከልቤ፡ጋራ፡ተጫወትኹ፥ነፍሴንም፡አነቃቃዃት።
7፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ይጥላልን፧እንግዲህስ፡ቸርነቱን፡አይጨምርምን፧
8፤ለዘለዓለምስ፡ምሕረቱ፡ለልጅ፡ልጅ፡ተቈረጠችን፧የተናገረውስ፡ቃል፡አልቋልን፧
9፤እግዚአብሔርስ፡ሞገሱን፡ረሳን፧በቍጣውስ፡ምሕረቱን፡ዘጋውን፧
10፤ይህ፡ድካሜ፡ነው፡አልኹ፥የልዑል፡ቀኝ፡እንደ፡ተለወጠ።
11፤የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡አስታወስኹ፤የቀደመውን፡ተኣምራትኽን፡አስታውሳለኹና፤
12፤በምግባርኽም፡ዅሉ፡እናገራለኹ፥በሥራኽም፡እጫወታለኹ።
13፤አቤቱ፥መንገድኽ፡በመቅደስ፡ውስጥ፡ነው፤እንደ፡አምላካችን፡ያለ፡ታላቅ፡አምላክ፡ማን፡ነው፧
14፤ተኣምራትን፡የምታደርግ፡አምላክ፡አንተ፡ነኽ።ለሕዝብኽ፡ኀይልን፡አስታወቅኻቸው።
15፤የያዕቆብንና፡የዮሴፍን፡ልጆች፥ሕዝብኽን፡በክንድኽ፡አዳንኻቸው።
16፤አቤቱ፥ውሃዎች፡አዩኽ፥ውሃዎችም፡አይተውኽ፡ፈሩ፤ጥልቆች፡ተነዋወጡ፥ውሃዎችም፡ጮኹ።
17፤ደመኖች፡ድምፅን፡ሰጡ፥ፍላጻዎችኽም፡ወጡ።
18፤የነጐድጓድኽ፡ድምፅ፡በዐውሎ፡ነበረ፤መብረቆች፡ለዓለም፡አበሩ፤ምድር፡ተናወጠች፡ተንቀጠቀጠችም።
19፤መንገድኽ፡በባሕር፡ውስጥ፡ነው፥ፍለጋኽም፡በብዙ፡ውሃዎች፡ነው፥አረማመድኽም፡አልታወቀም።
20፤በሙሴና፡በአሮን፡እጅ፡ሕዝብኽን፡እንደ፡በጎች፡መራኻቸው።
_______________መዝሙር፡77፡(78)።______________
የአሣፍ፡ትምህርት።
1፤ሕዝቤ፡ሆይ፥ሕጌን፡አድምጡ፤ዦሯችኹንም፡ወደአፌ፡ቃል፡አዘንብሉ።
2፤አፌን፡በምሳሌ፡እከፍታለኹ፤ከቀድሞ፡ዠምሮ፥ያለውንም፡ተምሳሊት፡እናገራለኹ።
3፤የሰማነውንና፡ያወቅነውን፥አባቶቻችንም፡የነገሩንን፥ለሚመጣ፡ትውልድ፡ከልጆቻቸው፡አልሰወሩም።
4፤የእግዚአብሔርን፡ምስጋናና፡ኀይሉን፡ያደረገውንም፡ተኣምራት፡ተናገሩ።
5፤ለልጆቻቸው፡ያስታውቅ፡ዘንድ፡ለአባቶቻችን፡ያዘዘውን፡ምስክር፡በያዕቆብ፡አቆመ፥በእስራኤልም፡ሕግን፡ሠራ ፤
6፤የሚመጣ፥ትውልድ፡የሚወለዱም፡ልጆች፡ያውቁ፡ዘንድ፥ተነሥተው፡ለልጆቻቸው፡ይነግራሉ፤
7፤ተስፋቸውን፡በእግዚአብሔር፡እንዲያደርጉ፥የእግዚአብሔርንም፡ሥራ፡እንዳይረሱ፥ትእዛዙንም፡እንዲጠብቁ፤
8፤እንደ፡አባቶቻቸው፡እንዳይኾኑ፡ጠማማና፡የምታስመርር፡ትውልድ፥ልቧን፡ያላቀናች፡ትውልድ፥ነፍሷ፡በእግዚአ ብሔር፡ዘንድ፡ያልታመነች።
9፤የኤፍሬም፡ልጆች፡ለሰልፍ፡ታጥቀው፡ቀስትንም፡ገትረው፡በሰልፍ፡ቀን፡ወደ፡ዃላ፡ተመለሱ።
10፤የእግዚአብሔርን፡ኪዳን፡አልጠበቁም፥በሕጉም፡ለመመላለስ፡እንቢ፡አሉ፤
11፤መልካም፡ሥራውንና፡ያሳያቸውን፡ተኣምራቱን፡ረሱ፥
12፤በግብጽ፡አገርና፡በጣኔዎስ፡በረሓ፡በአባቶቻቸው፡ፊት፡የሠራውን፡ተኣምራት።
13፤ባሕርን፡ከፍሎ፡አሳለፋቸው፤ውሃዎችን፡እንደ፡ክምር፡አቆመ።
14፤ቀን፡በደመና፡መራቸው፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡በእሳት፡ብርሃን።
15፤አለቱን፡በምድረ፡በዳ፡ሰነጠቀ፤ከጥልቅ፡እንደሚገኝ፡ያኽል፡በብዙ፡አጠጣቸው።
16፤ውሃን፡ከጭንጫ፡አወጣ፥ውሃንም፡እንደ፡ወንዞች፡አፈሰሰ።
17፤ነገር፡ግን፥ይበድሉት፡ዘንድ፡እንደ፡ገና፡ደገሙ፥ልዑልንም፡በምድረ፡በዳ፡አስቈጡት።
18፤ለነፍሳቸው፡መብልን፡ይፈልጉ፡ዘንድ፥እግዚአብሔርን፡በልባቸው፡ፈተኑት።
19፤እግዚአብሔርን፡እንዲህ፡ብለው፡ዐሙት፦እግዚአብሔር፡በምድረ፡በዳ፡ማእዱን፡ያሰናዳ፡ዘንድ፡ይችላልን፧
20፤አለቱን፡መታ፤ውሃዎችም፡ወጡ፥ወንዞችም፡ጐረፉ፤እንጀራን፡መስጠትስ፡ይችላልን፧ለሕዝቡስ፡ማእዱን፡ያዘጋ ጃልን፧
21፤እግዚአብሔርም፡ይህን፡ሰምቶ፡ተቈጣ፤በያዕቆብም፡ላይ፡እሳት፡ነደደ፥መዓትም፡በእስራኤል፡ላይ፡መጣ፤
22፤በእግዚአብሔር፡አላመኑምና፥በመድኀኒቱም፡አልተማመኑምና።
23፤ደመናውንም፡ከላይ፡አዘዘ፥የሰማይንም፡ደጆች፡ከፈተ፤
24፤ይበሉም፡ዘንድ፡መናን፡አዘነበላቸው፥የሰማይንም፡እንጀራ፡ሰጣቸው።
25፤የመላክትንም፡እንጀራ፡ሰው፡በላ፡ሥንቅንም፡እስኪተርፋቸው፡ላከላቸው።
26፤ከሰማይ፡የምሥራቅን፡ነፋስ፡አስነሣ፥በኀይሉም፡የደቡብን፡ነፋስ፡አመጣ፤
27፤ሥጋን፡እንደ፡ዐፈር፥የሚበሩ፟ትንም፡ወፎች፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡አዘነበላቸው፤
28፤በሰፈራቸው፡መካከል፥በድንኳናቸውም፡ዙሪያ፡ወደቀ።
29፤በሉ፡እጅግም፡ጠገቡ፤ምኞታቸውንም፡ሰጣቸው።
30፤ከወደዱትም፡አላሳጣቸውም፤መብላቸውም፡ገና፡በአፋቸው፡ሳለ፥
31፤የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በላያቸው፡መጣ፥ከነርሱም፡ከፍ፡ያሉትን፡ገደለ፥የእስራኤልንም፡ምርጦች፡አሰናከለ።
32፤ከዚህም፡ዅሉ፡ጋራ፡እንደ፡ገና፡በደሉ፥ተኣምራቱንም፡አላመኑም፤
33፤ቀኖቻቸውም፡በከንቱ፡አለቁ፥ዓመቶቻቸውም፡በችኰላ።
34፤በገደላቸውም፡ጊዜ፡ወዲያው፡ፈለጉት፤ተመለሱ፡ወደ፡እግዚአብሔርም፡ገሠገሡ፤
35፤ረዳታቸውም፡እግዚአብሔር፥መድኀኒታቸውም፡ልዑል፡አምላክ፡እንደ፡ኾነ፡ዐሰቡ።
36፤በአፋቸው፡ብቻ፡ወደዱት፤በአንደበታቸውም፡ዋሹበት፤
37፤ልባቸውም፡ከርሱ፡ጋራ፡አልቀናም፥በቃል፡ኪዳኑም፡አልተማመኑትም።
38፤ርሱ፡ግን፡መሓሪ፡ነው፥ኀጢአታቸውንም፡ይቅር፡አላቸው፥አላጠፋቸውምም፤ቍጣውንም፡መመለስ፡አበዛ፥መዓቱን ም፡ዅሉ፡አላቃጠለም።
39፤ወጥቶ፡የማይመለስ፡መንፈስ፥ሥጋም፡እንደ፡ኾኑ፡ዐሰበ።
40፤በምድረ፡በዳ፡ምን፡ያኽል፡አስቈጡት፥በበረሓም፡አሳዘኑት።
41፤ተመለሱ፥እግዚአብሔርንም፡ፈተኑት፥የእስራኤልንም፡ቅዱስ፡አሳዘኑት።
42፤እነርሱም፡እጁን፡አላሰቡም፥ከጠላቶቻቸው፡እጅ፡ያዳነበትን፡ቀን፥
43፤በግብጽ፡ያደረገውን፡ተኣምራቱን፥በጣኔዎስም፡በረሓ፡ያደረገውን፡ድንቁን።
44፤ወንዞቻቸውንም፡ወደ፡ደም፡ለወጠ፥ምንጮቻቸውን፡ደግሞ፡እንዳይጠጡ።
45፤ዝንቦችንም፡በላያቸው፡ሰደደባቸው፥በሏቸውም፤በጓጕንቸርም፡አጠፋቸው።
46፤ፍሬያቸውን፡ለኵብኵባ፥ሥራቸውንም፡ለአንበጣ፡ሰጠ።
47፤ወይናቸውን፡በበረዶ፥በለሳቸውንም፡በዐመዳይ፡አጠፋ።
48፤እንስሳዎቻቸውን፡ለበረዶ፥ሀብታቸውንም፡ለእሳት፡ሰጠ።
49፤የመዓቱን፡መቅሠፍት፡በላያቸው፡ሰደደ፤መቅሠፍትን፡መዓትንም፡መከራንም፡በክፉዎች፡መላእክት፡ሰደደ።
50፤ለቍጣው፡መንገድን፡ጠረገ፤ነፍሳቸውንም፡ከሞት፡አላዳናትም፥እንስሳዎቻቸውንም፡በሞት፡ውስጥ፡ዘጋ፤
51፤በኵሮቻቸውን፡ዅሉ፡በግብጽ፥የድካማቸውንም፡መዠመሪያ፡በካም፡ድንኳኖች፡ገደለ።
52፤ሕዝቡን፡ግን፡እንደ፡በጎች፡አሰማራቸው፥እንደ፡መንጋም፡በምድረ፡በዳ፡መራቸው።
53፤በተስፋም፡መራቸው፡አልፈሩምም፥ጠላቶቻቸውንም፡ባሕር፡ደፈናቸው።
54፤ወደመቅደሱም፡ተራራ፡አገባቸው፥ቀኙ፡ወደ፡ፈጠረችው፡ወደዚች፡ተራራ፤
55፤ከፊታቸውም፡አሕዛብን፡አባረረ፥ርስቱንም፡በገመድ፡አካፈላቸው፥የእስራኤልንም፡ወገኖች፡በቤታቸው፡አኖረ ።
56፤ነገር፡ግን፥ልዑል፡እግዚአብሔርን፡ፈተኑት፡አስቈጡትም፥ምስክሩንም፡አልጠበቁም፤
57፤ተመለሱም፡እንደ፡አባቶቻቸውም፡ከዱ፤እንደ፡ጠማማ፡ቀስትም፡ተገለበጡ፤
58፤በኰረብታ፡መስገጃዎቻቸውም፡አስቈጡት፥በተቀረጹ፡ምስሎቻቸውም፡አስቀኑት።
59፤እግዚአብሔርም፡ይህን፡ሰምቶ፡ተቈጣ፥እስራኤልንም፡እጅግ፡ናቀ፤
60፤የሴሎምን፡ማደሪያ፡ተዋት፡በሰዎች፡መካከል፡ያደረገባትን፡ድንኳኑን፤
61፤ኀይላቸውን፡ለምርኮ፥ሽልማቱንም፡በጠላት፡እጅ፡ሰጠ።
62፤ሕዝቡንም፡በጦር፡ውስጥ፡ዘጋቸው፥ርስቱንም፡ቸል፡አላቸው።
63፤ጕልማሳዎቻቸውን፡እሳት፡በላቸው፥ቈነዣዥቶቻቸውም፡አላዘኑም፤
64፤ካህናታቸውም፡በሰይፍ፡ወደቁ፥ባልቴቶቻቸውም፡አላለቀሱላቸውም።
65፤እግዚአብሔርም፡ከእንቅልፍ፡እንደሚነቃ፡ተነሣ፥የወይን፡ስካር፡እንደ፡ተወው፡እንደ፡ኀያልም፡ሰው፤
66፤ጠላቶቹንም፡በዃላቸው፡መታ፤የዘለዓለምን፡ኀሣር፡ሰጣቸው።
67፤የዮሴፍንም፡ድንኳን፡ተዋት፥የኤፍሬምንም፡ወገን፡አልመረጠውም፤
68፤የይሁዳን፡ወገን፡ግን፡መረጠ፥የወደደውን፡የጽዮንን፡ተራራ።
69፤መቅደሱን፡እንደ፡አርያም፡ሠራ፥ለዘለዓለምም፡በምድር፡ውስጥ፡መሠረታት።
70፤ዳዊትንም፡ባሪያውን፡መረጠው፥ከበጎቹም፡መንጋ፡ውስጥ፡ወሰደው፤
71፤ከሚያጠቡ፡በጎችም፡በዃላ፥ባሪያውን፡ያዕቆብን፡ርስቱንም፡እስራኤልን፡ይጠብቅ፡ዘንድ፡ወሰደው።
72፤በልቡ፡ቅንነት፡ጠበቃቸው፥በእጁም፡ብልኀት፡መራቸው።
_______________መዝሙር፡78፡(79)።______________
የአሣፍ፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥አሕዛብ፡ወደ፡ርስትኽ፡ገቡ፤የቅድስናኽንም፡መቅደስ፡አረከሱ፥ኢየሩሳሌምንም፡እንደ፡መደብ፡አደረጓ ት።
2፤የባሪያዎችኽንም፡በድኖች፡ለሰማይ፡ወፎች፡መብል፡አደረጉ፥የጻድቃንኽንም፡ሥራ፡ለምድር፡አራዊት፤
3፤ደማቸውንም፡በኢየሩሳሌም፡ዙሪያ፡እንደ፡ውሃ፡አፈሰሱ፥የሚቀብራቸውም፡ዐጡ።
4፤ለጎረቤቶቻችንም፡ስድብ፡ኾን፟፥በዙሪያችንም፡ላሉ፡ሣቅና፡ዘበት።
5፤አቤቱ፥እስከ፡መቼ፡ለዘለዓለም፡ትቈጣለኽ፧ቅንአትኽም፡እንደ፡እሳት፡ይነዳ፟ል፧
6፤ስምኽን፡በማይጠሩ፡መንግሥታት፡ላይ፡በማያውቁኽም፡አሕዛብ፡ላይ፡መዓትኽን፡አፍስ፟፤
7፤ያዕቆብን፡በልተውታልና፥ስፍራውንም፡ባድማ፡አድርገዋልና።
8፤የቀደመውን፡በደላችንን፡አታስብብን፥ምሕረትኽ፡በቶሎ፡ታግኘን፥እጅግ፡ተቸግረናልና።
9፤አምላካችንና፡መድኀኒታችን፡ሆይ፥ርዳን፤ስለስምኽ፡ክብር፥አቤቱ፥ታደገን፥ስለ፡ስምኽም፡ኀጢአታችንን፡አስ ተሰርይልን።
10፤አሕዛብ፥አምላካቸው፡ወዴት፡ነው፧እንዳይሉ፥የፈሰሰውን፡የባሪያዎችኽን፡ደም፡በቀል፡በዐይኖቻችን፡ፊት፡ አሕዛብ፡ያወቁ፤
11፤የእስረኛዎች፡ጩኸት፡ወደ፡ፊትኽ፡ይግባ፤እንደ፡ክንድኽም፡ታላቅነት፡ሊገደሉ፡የተፈረደባቸውን፡አድን።
12፤አቤቱ፥የተዘባበቱብኽን፡መዘባበታቸውን፡ለጎረቤቶቻችን፡ሰባት፡ዕጥፍ፡በብብታቸው፡ክፈላቸው።
13፤እኛ፡ሕዝብኽ፡ግን፥የማሰማሪያኽም፡በጎች፥ለዘለዓለም፡እናመሰግንኻለን፤ለልጅ፡ልጅም፡ምስጋናኽን፡እንና ገራለን።
_______________መዝሙር፡79፡(80)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በመለከቶች፤ስለ፡አሶራውያን፤የአሣፍ፡የምስክር፡መዝሙር።
1፤ዮሴፍን፡እንደ፡መንጋ፡የምትመራ፥የእስራኤል፡ጠባቂ፡ሆይ፥አድምጥ፤በኪሩቤል፡ላይ፡የምትቀመጥ፥ተገለጥ።
2፤በኤፍሬምና፡በብንያም፡በምናሴም፤ኀይልኽን፡አንሣ፡እኛንም፡ለማዳን፡ና።
3፤አቤቱ፥መልሰን፥ፊትኽንም፡አብራ፥እኛም፡እንድናለን።
4፤የሰራዊት፡አምላክ፡አቤቱ፥በባሪያኽ፡ጸሎት፡ላይ፡እስከ፡መቼ፡ትቈጣለኽ፧
5፤የእንባ፡እንጀራን፡ትመግበናለኽ፥እንባም፡በስፍር፡ታጠጣናለኽ።
6፤ለጎረቤቶቻችን፡ክርክር፡አደረግኸን፥ጠላቶቻችንም፡በላያችን፡ተሣለቁብን።
7፤የሰራዊት፡አምላክ፡አቤቱ፥መልሰን፥ፊትኽንም፡አብራ፥እኛም፡እንድናለን።
8፤ከግብጽ፡የወይን፡ግንድ፡አመጣኽ፤አሕዛብን፡አባረርኽ፡ርሷንም፡ተከልኽ።
9፤በፊቷም፡ስፍራን፡አዘጋጀኽ፥ሥሮቿንም፡ተከልኽ፡ምድርንም፡ሞላች።
10፤ጥላዋ፡ተራራዎችን፡ከደነ፥ጫፎቿም፡እንደእግዚአብሔር፡ዝግባ፡ኾኑ።
11፤ቅርንጫፎቿንም፡እስከ፡ባሕር፥ቡቃያዋንም፡እስከ፡ወንዙ፡ዘረጋች።
12፤ዐጥሯን፡ለምን፡አፈረስኽ፧መንገድ፡ዐላፊም፡ዅሉ፡ይቀጥፋታል።
13፤የዱር፡ዕሪያ፡አረከሳት፥የአገር፡አውሬም፡ተሰማራባት።
14፤የሰራዊት፡አምላክ፡ሆይ፥እንግዲህ፡ተመለስ፤ከሰማይ፡ተመልከት፥እይም፥ይህችንም፡የወይን፡ግንድ፡ጐብኝ።
15፤በሰው፡ልጅ፡ለአንተ፡ያጸናኸውን፡ቀኝኽ፡የተከላትን፡አንሣ።
16፤በእሳት፡ተቃጥላለች፡ተነቅላማለች፤ከፊትኽ፡ተግሣጽም፡የተነሣ፡ይጠፋሉ።
17፤ለአንተ፡ባጸናኸው፡በሰው፡ልጅ፡ላይ፥በቀኝኽ፡ሰው፡ላይ፡እጅኽ፡ትኹን።
18፤ከአንተም፡አንራቅ፤አድነን፡ስምኽንም፡እንጠራለን።
19፤የሰራዊት፡አምላክ፡አቤቱ፥መልሰን፥ፊትኽንም፡አብራ፥እኛም፡እንድናለን።
_______________መዝሙር፡80፡(81)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በዋሽንት፤የአሣፍ፡መዝሙር።
1፤በረድኤታችን፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይበላችኹ፥ለያዕቆብም፡አምላክ፡እልል፡በሉ።
2፤ዝማሬውን፡አንሡ፡ከበሮንም፡ስጡ፥ደስ፡የሚያሠኘውን፡በገና፡ከመሰንቆ፡ጋራ፤
3፤በመባቻ፡ቀን፡በከፍተኛው፡በዓላችን፡ቀን፡መለከትን፡ንፉ፤
4፤ለእስራኤል፡ሥርዐቱ፡ነውና፥የያዕቆብም፡አምላክ፡ፍርድ።
5፤ከግብጽ፡በወጣ፡ጊዜ፡ለዮሴፍ፡ምስክር፡አቆመው።ያላወቅኹትን፡ቋንቋ፡ሰማኹ።
6፤ጫንቃውን፡ከሸክም፥እጆቹንም፡በቅርጫት፡ከመገዛት፡አራቅኹ።
7፤በመከራኽ፡ጊዜ፡ጠራኸኝ፡አዳንኹኽም፥በተሰወረ፡ዐውሎም፡መለስኹልኽ፥በክርክር፡ውሃ፡ዘንድም፡ፈተንኹኽ።
8፤ሕዝቤ፡ሆይ፥ስማኝ፡እነግርኻለኹም፤እስራኤል፡ሆይ፥እመሰክርልኻለኹ።
9፤አንተስ፡ብትሰማኝ፡ሌላ፡አምላክ፡አይኾንልኽም፥ለሌላ፡አምላክም፡አትሰግድም።
10፤ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣኹኽ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላክኽ፡ነኝና፤አፍኽን፡አስፋ፡እሞላዋለኹም።
11፤ሕዝቤ፡ግን፡ቃሌን፡አልሰሙኝም፥እስራኤልም፡አላዳመጠኝም።
12፤እንደ፡ልባቸው፡ሥራ፡ተውዃቸው፥በልባቸውም፡ዐሳብ፡ኼዱ።
13፤ሕዝቤስ፡ሰምቶኝ፡ቢኾን፥እስራኤልም፡በመንገዴ፡ኼደው፡ቢኾን፤
14፤ጠላቶቻቸውን፡ፈጥኜ፡ባዋረድዃቸው፡ነበር፥በሚያስጨንቋቸውም፡ላይ፡እጄን፡በጣልኹ፡ነበር፤
15፤የእግዚአብሔር፡ጠላቶችም፡በተገዙለት፡ነበር፥ዘመናቸውም፡ለዘለዓለም፡በኾነ፡ነበር፤
16፤ከስንዴም፡ስብ፡ባበላቸው፡ነበር፥ከአለቱም፡ማር፡ባጠገባቸው፡ነበር።
_______________መዝሙር፡81፡(82)።______________
የአሣፍ፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡በአማልክት፡ማኅበር፡ቆመ፥በአማልክትም፡መካከል፡ይፈርዳል።
2፤እስከ፡መቼ፡ሐሰትን፡ትፈርዳላችኹ፧እስከ፡መቼ፡ለኀጢአተኛዎች፡ፊት፡ታደላላችኹ፧
3፤ለድኻዎችና፡ለድኻ፡አደጎች፡ፍረዱ፤ለችግረኛውና፡ለምስኪኑ፡ጽድቅ፡አድርጉ፤
4፤ብቸኛውንና፡ችግረኛውን፡አድኑ፤ከኀጢአተኛዎችም፡እጅ፡አስጥሏቸው።
5፤አያውቁም፥አያስተውሉም፤በጨለማ፡ውስጥ፡ይመላለሳሉ፤የምድር፡መሠረቶች፡ዅሉ፡ተናወጡ።
6፤እኔ፡ግን፦አማልክት፡ናችኹ፥ዅላችኹም፡የልዑል፡ልጆች፡ናችኹ፤
7፤ነገር፡ግን፥እንደ፡ሰው፡ትሞታላችኹ፥ከአለቃዎችም፡እንደ፡አንዱ፡ትወድቃላችኹ፡አልኹ።
8፤አቤቱ፥ተነሥ፥በምድር፡ላይ፡ፍርድ፥አንተ፡አሕዛብን፡ዅሉ፡ትወርሳለኽና።
_______________መዝሙር፡82፡(83)።______________
የአሣፍ፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥እንደ፡አንተ፡ማን፡ነው፧አቤቱ፥ዝም፡አትበል፥ቸልም፡አትበል።
2፤እንሆ፥ጠላቶችኽ፡ጮኽዋልና፥የሚጠሉኽም፡ራሳቸውን፡አንሥተዋልና።
3፤ሕዝብኽን፡በምክር፡ሸነገሏቸው፥በቅዱሳንኽም፡ላይ፡ተማከሩ።
4፤ኑ፡ከሕዝብ፡እናጥፋቸው፥ደግሞም፡የእስራኤል፡ስም፡አይታሰብ፡አሉ።
5፤አንድ፡ኾነው፡ባንተ፡ላይ፡ተማከሩ፤ባንተ፡ላይ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረጉ፤
6፤የኤዶማውያን፡ድንኳኖች፡እስማኤላውያንም፥ሞዐብም፡አጋራውያንም፥
7፤ጌባል፡ዐሞንም፡ዐማሌቅም፥ፍልስጥኤማውያንም፡ከጢሮስ፡ሰዎች፡ጋራ፤
8፤አሶርም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ተባበረ፥ለሎጥ፡ልጆችም፡ረዳት፡ኾኗቸው።
9፤እንደ፡ምድያምና፡እንደ፡ሢሣራ፥በቂሶንም፡ወንዝ፡እንደ፡ኢያቢስ፡አድርግባቸው።
10፤በዐይንዶር፡ጠፉ፥እንደምድርም፡ጕድፍ፡ኾኑ።
11፤አለቃዎቻቸውን፡እንደ፡ሔሬብና፡እንደ፡ዜብ፥ታላላቆቻቸውንም፡እንደ፡ዛብሄልና፡እንደ፡ስልማና፡አድርጋቸ ው።
12፤የእግዚአብሔርን፡መሠዊያ፡እንወርሳለን፡የሚሉትን።
13፤አምላኬ፡ሆይ፥እንደ፡ትቢያ፡በነፋስ፡ፊትም፡እንደ፡ገለባ፡አድርጋቸው።
14፤እሳት፡ዱርን፡እንደሚያቃጥል፥ነበልባልም፡ተራራዎች፡እንደሚያነድ፟፥
15፤እንዲሁ፡በቍጣኽ፡አሳዳ፟ቸው፥በመቅሠፍትኽም፡አስደንግጣቸው።
16፤ፊታቸውን፡ዕፍረት፡ሙላው፥አቤቱ፥ስምኽንም፡ይፈልጋሉ።
17፤ይፈሩ፡ለዘለዓለሙም፡ይታወኩ፤ይጐስቍሉ፡ይጥፉም።
18፤ስምኽም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾነ፥በምድር፡ዅሉ፡ላይም፡አንተ፡ብቻ፡ልዑል፡እንደ፡ኾንኽ፡ይወቁ።
_______________መዝሙር፡83፡(84)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤በዋሽንት፤የቆሬ፡ልጆች፡መዝሙር።
1፤የሰራዊት፡አምላክ፡ሆይ፥ማደሪያዎችኽ፡እንደምን፡የተወደዱ፡ናቸው!
2፤ነፍሴ፡የእግዚአብሔርን፡አደባባዮች፡ትወዳ፟ለች፡ትናፍቅማለች፤ልቤም፡ሥጋዬም፡በሕያው፡አምላክ፡ደስ፡ተሠ ኘ።
3፤ወፍ፡ለርሷ፡ቤትን፡አገኘች፥ዋኖስም፡ጫጩቶቿን፡የምታኖርበት፡ቤት፡አገኘች፤የሰራዊት፡አምላክ፡ንጉሤም፡አ ምላኬም፡ሆይ፥ርሱ፡መሠዊያኽ፡ነው።
4፤በቤትኽ፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡የተመሰገኑ፡ናቸው፤ለዓለምና፡ለዘለዓለምም፡ያመሰግኑኻል።
5፤አቤቱ፥ርዳታው፡ከአንተ፡ዘንድ፡የኾነለት፥በልቡም፡የላይኛውን፡መንገድ፡የሚያስብ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
6፤በልቅሶ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡በወሰነው፡ስፍራ፡የሕግ፡መምህር፡በረከትን፡ይሰጣልና።
7፤ከኀይል፡ወደ፡ኀይል፡ይኼዳሉ፤የአማልክት፡አምላክ፡በጽዮን፡ይታያል።
8፤የሰራዊት፡አምላክ፡አቤቱ፥ጸሎቴን፡ስማ፤የያዕቆብ፡አምላክ፡ሆይ፥አድምጥ።
9፤አቤቱ፥መታመናችንን፡እይልን፥ወደ፡ቀባኸውም፡ፊት፡ተመልከት።
10፤ከአእላፍ፡ይልቅ፡በአደባባዮችኽ፡አንዲት፡ቀን፡ትሻላለች፤በኃጥኣን፡ድንኳኖች፡ከመቀመጥ፡ይልቅ፥በእግዚ አብሔር፡ቤት፡እጣል፡ዘንድ፡መረጥኹ።
11፤እግዚአብሔር፡አምላክ፡ምሕረትንና፡እውነትን፡ስለ፡ወደደ፥ሞገስንና፡ክብርን፡ይሰጣል፤እግዚአብሔር፡በቅ ንነት፡የሚኼዱትን፡ከመልካም፡ነገር፡አያሳጣቸውም።
12፤የሰራዊት፡አምላክ፡ሆይ፥ባንተ፡የታመነ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
_______________መዝሙር፡84፡(85)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የቆሬ፡ልጆች፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ለምድርኽ፡ሞገስን፡አደረግኽ፥የያዕቆብንም፡ምርኮ፡መለስኽ።
2፤የሕዝብኽን፡ኀጢአት፡አስቀረኽ፥አበሳቸውንም፡ዅሉ፡ከደንኽ።
3፤መዓትኽንም፡ዅሉ፡አስወገድኽ፤ከቍጣኽ፡፡መቅሠፍት፡ተመለስኽ።
4፤የመድኀኒታችን፡አምላክ፡ሆይ፥መልሰን፥ቍጣኽንም፡ከእኛ፡መልስ።
5፤በእውኑ፡ለዘለዓለም፡ትቈጣናለኽን፧ቍጣኽንስ፡ለልጅ፡ልጅ፡ታስረዝማለኽን፧
6፤አቤቱ፥ትመለሳለኽ፡ታድነንማለኽ፤ሕዝቡም፡ባንተ፡ደስ፡ይላቸዋል።
7፤አቤቱ፥ምሕረትኽን፡አሳየን፥አቤቱ፥መድኀኒትኽንም፡ስጠን።
8፤እግዚአብሔር፡አምላክ፡የሚናገረውን፡እሰማለኹ፤ሰላምን፡ለሕዝቡና፡ለቅዱሳኑ፡ልባቸውንም፡ወደ፡ርሱ፡ለሚመ ልሱ፡ይናገራልና።
9፤ነገር፡ግን፥ክብር፡በምድራችን፡ያድር፡ዘንድ፡ማዳኑ፡ለሚፈሩት፡ቅርብ፡ነው፤
10፤ምሕረትና፡እውነት፡ተገናኙ፤ጽድቅና፡ሰላም፡ተስማሙ።
11፤እውነት፡ከምድር፡በቀለች፥ጽድቅም፡ከሰማይ፡ተመለከተች።
12፤እግዚአብሔርም፡በጎ፡ነገርን፡ይሰጣል፥ምድራችንም፡ፍሬዋን፡ትሰጣለች።
13፤ጽድቅ፡በፊቱ፡ይኼዳል፥ፍለጋውንም፡በመንገድ፡ውስጥ፡ያኖራል።
_______________መዝሙር፡85፡(86)።______________
የዳዊት፡ጸሎት።
1፤አቤቱ፥ዦሮኽን፡ወደ፡እኔ፡አዘንብል፡አድምጠኝም፥ችግረኛና፡ምስኪን፡ነኝና።
2፤ቅዱስ፡ነኝና፡ነፍሴን፡ጠብቅ፤አምላኬ፡ሆይ፥አንተን፡የታመነውን፡ባሪያኽን፡አድነው።
3፤አቤቱ፥ቀኑን፡ዅሉ፡ወዳንተ፡እጮኻለኹና፡ማረኝ።
4፤የባሪያኽን፡ነፍስ፡ደስ፡አሠኛት፥አቤቱ፥ነፍሴን፡ወዳንተ፡አነሣለኹና።
5፤አቤቱ፥አንተ፡መሓሪና፡ይቅር፡ባይ፡ነኽና፥ምሕረትኽም፡ለሚጠሩኽ፡ዅሉ፡ብዙ፡ነውና።
6፤አቤቱ፥ጸሎቴን፡አድምጥ፥የልመናዬንም፡ድምፅ፡ስማ።
7፤ትመልስልኛለኽና፡በመከራዬ፡ቀን፡ወዳንተ፡እጠራለኹ።
8፤አቤቱ፥ከአማልክት፡የሚመስልኽ፡የለም፥እንደ፡ሥራኽም፡ያለ፡የለም።
9፤ያደረግኻቸው፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ይመጣሉ፥አቤቱ፥በፊትኽም፡ይሰግዳሉ፥ስምኽንም፡ያከብራሉ፤
10፤አቤቱ፥ድንቅ፡የምታደርግ፡አንተ፡ታላቅ፡ነኽና፥አንተም፡ብቻኽን፡ታላቅ፡አምላክ፡ነኽና።
11፤አቤቱ፥መንገድኽን፡ምራኝ፥በእውነትኽም፡እኼዳለኹ፤ስምኽን፡ለመፍራት፡ልቤ፡ደስ፡ይለዋል።
12፤አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥በልቤ፡ዅሉ፡አመሰግንኻለኹ፥ለዘለዓለምም፡ስምኽን፡አከብራለኹ፤
13፤ምሕረትኽ፡በእኔ፡ላይ፡ታላቅ፡ናትና፥ነፍሴንም፡ከታችኛዪቱ፡ሲኦል፡አድነኻታልና።
14፤አቤቱ፥ዐመፀኛዎች፡በእኔ፡ላይ፡ተነሥተዋል፥የክፉዎችንም፡ማኅበር፡ነፍሴን፡ፈለጓት፤በፊታቸውም፡አላደረ ጉኽም።
15፤አቤቱ፥አንተ፡ግን፡መሓሪና፡ርኅሩኅ፡አምላክ፡ነኽ፤መዓትኽ፡የራቀ፡ምሕረትኽም፡እውነትኽም፡የበዛ፤
16፤ወደ፡እኔ፡ተመልከት፡ማረኝም፤ለባሪያኽ፡ኀይልኽን፡ስጥ፥የሴት፡ባሪያኽንም፡ልጅ፡አድን።
17፤ምልክትንም፡ለመልካም፡ከእኔ፡ጋራ፡አድርግ፤የሚጠሉኝ፡ይዩ፡ይፈሩም፥አቤቱ፥አንተ፡ረድተኸኛልና፥አጽንተ ኸኛልምና።
_______________መዝሙር፡86፡(87)።______________
የቆሬ፡ልጆች፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤መሠረቶቹ፡በተቀደሱ፡ተራራዎች፡ናቸው፤
2፤ከያዕቆብ፡ድንኳኖች፡ይልቅ፥እግዚአብሔር፡የጽዮንን፡ደጆች፡ይወዳ፟ቸዋል።
3፤የእግዚአብሔር፡ከተማ፡ሆይ፥ባንቺ፡የተከበረ፡ነገር፡ይባላል።
4፤የሚያውቁኝን፡ረዓብንና፡ባቢሎንን፡ዐስባቸዋለኹ፤እንሆ፥ፍልስጥኤማውያን፡ጢሮስም፡የኢትዮጵያም፡ሕዝብ፥እ ነዚህ፡በዚያ፡ተወለዱ።
5፤ሰው፡እናታችን፡ጽዮን፡ይላል፥በውስጧም፡ሰው፡ተወለደ፤ርሱ፡ራሱም፡ልዑል፡መሠረታት።
6፤እግዚአብሔር፡ለሕዝቡ፥በውስጧም፡ለተወለዱት፡አለቃዎቿ፡በመጽሐፍ፡ይነግራቸዋል።
7፤ባንቺ፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ደስ፡እንደሚላቸው፡ይነግራቸዋል።
_______________መዝሙር፡87፡(88)።______________
የቆሬ፡ልጆች፡የምስጋና፡መዝሙር።ለመዘምራን፡አለቃ፡በማኸላት፡ለመዘመር፤የይዝራኤላዊው፡የኤማን፡ትምህርት ።
1፤አቤቱ፥የመድኀኒቴ፡አምላክ፥በቀንና፡በሌሊት፡በፊትኽ፡ጮኽኹ፤
2፤ጸሎቴ፡ወደ፡ፊትኽ፡ትግባ፥ዦሮኽንም፡ወደ፡ጩኸቴ፡አዘንብል፤
3፤ነፍሴ፡መከራን፡ጠግባለችና፥ሕይወቴም፡ወደ፡ሲኦል፡ቀርባለችና።
4፤ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ተቈጠርኹ፥ረዳትም፡እንደሌለው፡ሰው፡ኾንኹ።
5፤ለዘለዓለም፡እንደማታስባቸው፥እንደ፡ተገደሉና፡በመቃብር፡ውስጥ፡እንደ፡ተጣሉ፥በሙታን፡ውስጥ፡እንዳሉ፡የ ተጣልኹ፡ኾንኹ፤እነርሱም፡ከእጅኽ፡ተለዩ።
6፤በጨለማና፡በሞት፡ጥላ፡ውስጥ፥በታችኛው፡ጕድጓድ፡አስቀመጥኸኝ።
7፤በእኔ፡ላይ፡ቍጣኽ፡ጸና፥መቅሠፍትኽን፡ዅሉ፡በእኔ፡ላይ፡አመጣኽ።
8፤የሚያውቁኝን፡ከእኔ፡አራቅኽ፤በእነርሱ፡ዘንድ፡ርኩስ፡አደረግኸኝ፤ያዙኝ፥መውጫም፡የለኝም።
9፤ዐይኖቼም፡በመከራ፡ፈዘዙ፤አቤቱ፥ዅልጊዜ፡ወዳንተ፡ጮኽኹ፥እጆቼንም፡ወዳንተ፡ዘረጋኹ፥
10፤በእውኑ፡ለሙታን፡ተኣምራት፡ታደርጋለኽን፧የሞቱትስ፡ተነሥተው፡ያመሰግኑኻልን፧
11፤በመቃብርስ፡ውስጥ፡ቸርነትኽን፥እውነትኽንስ፡በጥፋት፡ስፍራ፡ይናገራሉን፧
12፤ተኣምራትኽ፡በጨለማ፥ጽድቅኽንም፡በመርሳት፡ምድር፡ትታወቃለችን፧
13፤አቤቱ፥እኔ፡ግን፡ወዳንተ፡ጮኽኹ፤በጧት፡ጸሎቴ፡ወደ፡ፊትኽ፡ትደርሳለች።
14፤አቤቱ፥ነፍሴን፡ለምን፡ትጥላለኽ፧ፊትኽንስ፡ከእኔ፡ለምን፡ትሰውራለኽ፧
15፤እኔ፡ከታናሽነቴ፡ችግረኛ፡ለሞትም፡የቀረብኹ፡ነኝ፤ከፍ፡ከፍ፡ካልኹ፡በዃላ፡ግን፡ተዋረድኹ፡ተናቅኹም።
16፤መቅሠፍትኽ፡በላዬ፡ዐለፈ፥ግርማኽም፡አስደነገጠኝ።
17፤ዅልጊዜ፡እንደ፡ውሃ፡ከበቡኝ፥በአንድነትም፡ያዙኝ።
18፤ወዳጄንና፡ባልንጀራዬን፡ዘመዶቼንም፡ከመከራ፡የተነሣ፡ከእኔ፡አራቅኽ።
_______________መዝሙር፡88፡(89)።______________
የይዝራኤላዊው፡የኤታን፡ትምህርት።
1፤አቤቱ፥ምሕረትኽን፡ለዘለዓለም፡እዘምራለኹ፥እውነትኽንም፡በአፌ፡ለልጅ፡ልጅ፡እናገራለኹ።
2፤እንዲህ፡ብለኻልና።ምሕረት፡ለዘለዓለም፡ይመሠረታል፥እውነትኽም፡በሰማይ፡ይጸናል።
3፤ከመረጥኹት፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳኔን፡አደረግኹ፥ለባሪያዬም፡ለዳዊት፡ማልኹ።
4፤ዘርኽን፡ለዘለዓለም፡አዘጋጃለኹ፥ዙፋንኽንም፡ለልጅ፡ልጅ፡እመሠርታለኹ።
5፤አቤቱ፥ሰማያት፡ተኣምራትኽን፡እውነትኽንም፡ደግሞ፡በቅዱሳን፡ማኅበር፡ያመሰግናሉ።
6፤እግዚአብሔርን፡በሰማይ፡የሚተካከለው፡ማን፡ነው፧ከአማልክትስ፡ልጆች፡እግዚአብሔርን፡ማን፡ይመስለዋል፧
7፤በቅዱሳን፡ምክር፡እግዚአብሔር፡ክቡር፡ነው፤በዙሪያው፡ባሉት፡ዅሉ፡ላይ፡ታላቅና፡ግሩም፡ነው።
8፤አቤቱ፡የሰራዊት፡አምላክ፥እንደ፡አንተ፡ያለ፡ማን፡ነው፧አቤቱ፥አንተ፡ብርቱ፡ነኽ፥እውነትኽም፡ይከብ፟ኻል ።
9፤የባሕርን፡ኀይል፡አንተ፡ትገዛለኽ፥የሞገዱንም፡መናወጥ፡አንተ፡ዝም፡ታሠኘዋለኽ።
10፤አንተ፡ረዓብን፡እንደ፡ተገደለ፡አዋረድኸው፥በኀይልኽም፡ክንድ፡ጠላቶችኽን፡በተንኻቸው።
11፤ሰማያት፡የአንተ፡ናቸው፥ምድርም፡የአንተ፡ናት፤ዓለምንና፡ሞላውም፡አንተ፡መሠረትኽ።
12፤ሰሜንና፡ደቡብን፡አንተ፡ፈጠርኽ፤ታቦርና፡አርሞንዔም፡በስምኽ፡ደስ፡ይላቸዋል።
13፤ክንድኽ፡ከኀይልኽ፡ጋራ፡ነው፤እጅኽ፡በረታች፡ቀኝኽም፡ከፍ፡ከፍ፡አለች።
14፤የዙፋንኽ፡መሠረት፡ጽድቅና፡ፍርድ፡ነው፤ምሕረትና፡እውነት፡በፊትኽ፡ይኼዳሉ።
15፤እልልታ፡የሚያውቅ፡ሕዝብ፡ምስጉን፡ነው፤አቤቱ፥በፊትኽ፡ብርሃን፡ይኼዳሉ።
16፤በስምኽ፡ቀኑን፡ዅሉ፡ደስ፡ይላቸዋል፥በጽድቅኽም፡ከፍ፡ከፍ፡ይላሉ፤
17፤የኀይላቸው፡ትምክሕት፡አንተ፡ነኽና፥በሞገስኽም፡ቀንዳችን፡ከፍ፡ከፍ፡ይላልና።
18፤ረድኤታችን፡ከእግዚአብሔር፡ከንጉሣችንም፡ከእስራኤል፡ቅዱስ፡ነውና።
19፤በዚያ፡ጊዜ፡ለልጆችኽ፡በራእይ፡ተናገርኽ፡እንዲህም፡አልኽ፦ረድኤቴን፡በኀይል፡ላይ፡አኖርኹ፤ከሕዝቤ፡የ ተመረጠውን፡ከፍ፡ከፍ፡አደረግኹ።
20፤ባሪያዬን፡ዳዊትን፡አገኘኹት፥ቅዱስ፡ዘይትም፡ቀባኹት።
21፤እጄም፡ትረዳዋለች፥ክንዴም፡ታጸናዋለች።
22፤ጠላት፡በርሱ፡ላይ፡አይጠቀምም፥የዐመፃ፡ልጅም፡መከራ፡አይጨምርበትም።
23፤ጠላቶቹን፡ከፊቱ፡አጠፋለኹ፥የሚጠሉትንም፡አዋርዳቸዋለኹ።
24፤እውነቴና፡ምሕረቴም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነው፥በስሜም፡ቀንዱ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።
25፤እጁን፡በባሕር፡ላይ፡ቀኙንም፡በወንዞች፡ላይ፡አኖራለኹ።
26፤ርሱ፦አባቴ፡አንተ፡ነኽ፥አምላኬ፡የመድኀኒቴም፡መጠጊያ፡ይላል።
27፤እኔም፡ደግሞ፡በኵሬ፡አደርገዋለኹ፥ከምድር፡ነገሥታትም፡ከፍ፡ይላል።
28፤ለዘለዓለምም፡ምሕረቴን፡ለርሱ፡እጠብቃለኹ፥ኪዳኔም፡በርሱ፡ዘንድ፡የታመነ፡ነው።
29፤ዘሩንም፡ለዓለምና፡ለዘለዓለም፥ዙፋኑንም፡እንደሰማይ፡ዘመን፡አደርጋለኹ።
30፤ልጆቹ፡ግን፡ሕጌን፡ቢተዉ፥በፍርዴም፡ባይኼዱ፤
31፤ሥርዐቴንም፡ቢያረክሱ፥ትእዛዜንም፡ባይጠብቁ፤
32፤ኀጢአታቸውን፡በበትር፥በደላቸውንም፡በመቅሠፍት፡እጐበኛታለኹ።
33፤ምሕረቴን፡ግን፡ከርሱ፡አላርቅም፥በእውነቴም፡አልበድልም፤
34፤ኪዳኔንም፡አላረክስም፥ከከንፈሬም፡የወጣውን፡አልለውጥም።
35፤ዳዊትን፡እንዳልዋሸው፡አንድ፡ጊዜ፡በቅዱስነቴ፡ማልኹ።
36፤ዘሩ፡ለዘለዓለም፥ዙፋኑም፡በፊቴ፡እንደ፡ፀሓይ፡ይኖራል።
37፤ለዘለዓለም፡እንደ፡ጨረቃ፡ይጸናል፤ምስክርነቱ፡በሰማይ፡የታመነ፡ነው።
38፤አንተ፡ግን፡ናቅኸው፡ጣልኸውም፥የቀባኸውንም፡ጣልኸው።
39፤የባሪያኽንም፡ኪዳን፡አፈረስኽ፥መቅደሱንም፡በምድር፡አረከስኽ።
40፤ቅጥሩን፡ዅሉ፡ጣልኽ፥ዐምባዎቹንም፡አጠፋኽ።
41፤መንገድ፡ዐላፊም፡ዅሉ፡ተናጠቀው፥ለጎረቤቶቹም፡ስድብ፡ኾነ።
42፤የጠላቶቹንም፡ቀኝ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረግኽ፥ጠላቶቹንም፡ዅሉ፡ደስ፡አሠኘኽ።
43፤የሰይፉንም፡ረድኤት፡መለስኽ፥በሰልፍም፡ውስጥ፡አልደገፍኸውም።
44፤ከንጽሕናውም፡ሻርኸው፥ዙፋኑንም፡በምድር፡ጣልኽ።
45፤የዙፋኑንም፡ዘመን፡አሳነስኽ፥በዕፍረትም፡ሸፈንኸው።
46፤አቤቱ፥እስከ፡መቼ፡ለዘለዓለም፡ፊትኽን፡ትመልሳለኽ፧እስከ፡መቼስ፡ቍጣኽ፡እንደ፡እሳት፡ይነዳ፟ል፧
47፤ችሎታዬ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ዐስብ፤በእውኑ፡የሰውን፡ልጅ፡ዅሉ፡ለከንቱ፡ፈጠርኸውን፧
48፤ሕያው፡ኾኖ፡የሚኖር፥ሞትንስ፡የማያይ፡ማን፡ነው፧ነፍሱንስ፡ከሲኦል፡እጅ፡የሚያድን፡ማን፡ነው፧
49፤ለዳዊት፡በእውነት፡የማልኽ፥አቤቱ፥የቀድሞ፡ምሕረትኽ፡ወዴት፡ነው፧
50፤አቤቱ፥የባሪያዎችኽን፡ስድብ፥በብብቴ፡ብዙ፡አሕዛብን፡የተቀበልኹትን፥
51፤አቤቱ፥ጠላቶችኽን፡የሰደቡትን፡የቀባኸውን፡ዘመን፡የሰደቡትን፡ዐስብ።
52፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ይባረክ።ይኹን፤ይኹን።
_______________መዝሙር፡89፡(90)።______________
የእግዚአብሔር፡ሰው፡የሙሴ፡ጸሎት።
1፤አቤቱ፥አንተ፡ለትውልድ፡ዅሉ፡መጠጊያ፡ኾንኽልን።
2፤ተራራዎች፡ሳይወለዱ፥ምድርም፡ዓለምም፡ሳይሠሩ፥ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡አንተ፡ነኽ።
3፤ሰውን፡ወደ፡ኀሳር፡አትመልስም፤የሰው፡ልጆች፡ሆይ፥ተመለሱ፡ትላለኽ፤
4፤ሺሕ፡ዓመት፡በፊትኽ፡እንዳለፈች፡እንደ፡ትናንት፡ቀን፥እንደ፡ሌሊትም፡ትጋት፡ነውና።
5፤ዘመኖች፡የተናቁ፡ይኾናሉ፥በማለዳም፡እንደ፡ሣር፡ያልፋል።
6፤ማልዶ፡ያብባል፡ያልፋልም፥በሠርክም፡ጠውልጎና፡ደርቆ፡ይወድቃል።
7፤እኛ፡በቍጣኽ፡አልቀናልና፥በመዓትኽም፡ደንግጠናልና።
8፤የተሰወረውን፡ኀጢአታችንን፡በፊትኽ፡ብርሃን፥በደላችንንም፡በፊትኽ፡አስቀመጥኽ።
9፤ዘመናችን፡ዅሉ፡ዐልፏልና፥እኛም፡በመዓትኽ፡አልቀናልና፤ዘመኖቻችንም፡እንደ፡ሸረሪት፡ድር፡ይኾናሉ።
10፤የዘመኖቻችንም፡ዕድሜ፡ሰባ፡ዓመት፥ቢበረታም፡ሰማንያ፡ዓመት፡ነው፤ቢበዛ፡ግን፡ድካምና፡መከራ፡ነው፤ከእ ኛ፡ቶሎ፡ያልፋልና፥እኛም፡እንገሠጻለንና።
11፤የቍጣኽን፡ጽናት፡ማን፡ያውቃል፧ከቍጣኽ፡ግርማ፡የተነሣ፡አለቁ።
12፤በልብ፡ጥበብን፡እንድንማር፥ቀኝኽን፡እንዲህ፡አስታውቀን።
13፤አቤቱ፥ተመለስ፥እስከ፡መቼስ፡ነው፧ስለ፡ባሪያዎችኽም፡ተሟገት።
14፤በማለዳ፡ምሕረትኽን፡እንጠግባለን፤በዘመናችን፡ዅሉ፡ደስ፡ይለናል፡ሐሤትም፡እናደርጋለን።
15፤መከራ፡ባሳየኸን፡ዘመን፡ፈንታ፥ክፉም፡ባየንባቸው፡ዘመኖች፡ፋንታ፡ደስ፡ይለናል።
16፤ባሪያዎችኽንና፡ሥራኽን፡እይ፥ልጆቻቸውንም፡ምራ።
17፤የአምላካችን፡የእግዚአብሔር፡ብርሃን፡በላያችን፡ይኹን፦የእጆቻችንንም፡ሥራ፡በላያችን፡አቅና።
_______________መዝሙር፡90፡(91)።______________
የዳዊት፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤በልዑል፡መጠጊያ፡የሚኖር፡ዅሉን፡በሚችል፡አምላክ፡ጥላ፡ውስጥ፡ያድራል።
2፤እግዚአብሔርን፦አንተ፡መታመኛዬ፡ነኽ፡እለዋለኹ፤አምላኬና፡መሸሸጊያዬ፡ነው፥በርሱም፡እታመናለኹ።
3፤ርሱ፡ከአዳኝ፡ወጥመድ፡ከሚያስደነግጥም፡ነገር፡ያድንኻልና።
4፤በላባዎቹ፡ይጋርድኻል፥በክንፎቹም፡በታች፡ትተማመናለኽ፤እውነት፡እንደ፡ጋሻ፡ይከብ፟ኻል።
5፤ከሌሊት፡ግርማ፥በቀን፡ከሚበር፟፡ፍላጻ፥
6፤በጨለማ፡ከሚኼድ፡ክፉ፡ነገር፥ከአደጋና፡ከቀትር፡ጋኔን፡አትፈራም።
7፤በአጠገብኽ፡ሺሕ፡በቀኝኽም፡ዐሥር፡ሺሕ፡ይወድቃሉ፤ወዳንተ፡ግን፡አይቀርብም።
8፤በዐይኖችኽ፡ብቻ፡ትመለከታለኽ፥የኃጥኣንንም፡ብድራት፡ታያለኽ።
9፤አቤቱ፥አንተ፡ተስፋዬ፡ነኽና፤ልዑልን፡መጠጊያኽ፡አደረግኽ።
10፤ክፉ፡ነገር፡ወዳንተ፡አይቀርብም፥መቅሠፍትም፡ወደ፡ቤትኽ፡አይገባም።
11፤በመንገድኽ፡ዅሉ፡ይጠብቁኽ፡ዘንድ፡መላእክቱን፡ስለ፡አንተ፡ያዛ፟ቸዋልና፤
12፤እግርኽም፡በድንጋይ፡እንዳትሰናከል፡በእጆቻቸው፡ያነሡኻል።
13፤በተኵላና፡በእባብ፡ላይ፡ትጫማለኽ፤አንበሳውንና፡ዘንዶውን፡ትረግጣለኽ።
14፤በእኔ፡ተማምኗልና፥አስጥለዋለኹ፤ስሜንም፡ዐውቋልና፥እጋርደዋለኹ።
15፤ይጠራኛል፥እመልስለትማለኹ፤በመከራውም፡ጊዜ፡ከርሱ፡ጋራ፡እኾናለኹ፤አድነዋለኹ፥አከብረውማለኹ።
16፤ረዥምን፡ዕድሜ፡አጠግበዋለኹ፥ማዳኔንም፡አሳየዋለኹ።
_______________መዝሙር፡91፡(92)።______________
በሰንበት፡ቀን፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔርን፡ማመስገን፡መልካም፡ነው፥ልዑል፡ሆይ፥ለስምኽም፡ዝማሬ፡ማቅረብ፤
2፤በማለዳ፡ምሕረትን፥በሌሊትም፡እውነትኽን፡ማውራት፡
3፤ዐሥር፡አውታር፡ባለው፡በበገና፥ከምስጋና፡ጋራም፡በመሰንቆ።
4፤አቤቱ፥በሥራኽ፡ደስ፡አሠኝተኸኛልና፤በእጅኽም፡ሥራ፡ደስ፡ይለኛልና።
5፤አቤቱ፥ሥራኽ፡እጅግ፡ትልቅ፡ነው፥ዐሳብኽም፡እጅግ፡ጥልቅ፡ነው።
6፤ሰነፍ፡ሰው፡አያውቅም።ልብ፡የሌለውም፡ይህን፡አያስተውለውም።
7፤ኀጢአተኛዎች፡እንደ፡ሣር፡ሲበቅሉ፡ዐመፃ፡የሚያደርጉ፡ዅሉ፡ሲለመልሙ፥ለዘለዓለም፡ዓለም፡እንዲጠፋ፡ነው።
8፤አቤቱ፥አንተ፡ግን፡ለዘለዓለም፡ልዑል፡ነኽ፤
9፤አቤቱ፥እንሆ፥ጠላቶችኽ፡ይጠፋሉና፥ዐመፃንም፡የሚሠሩ፡ዅሉ፡ይበተናሉና።
10፤ቀንዴ፡አንድ፡ቀንድ፡እንዳለው፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፤ሽምግልናዬም፡በዘይት፡ይለመልማል።
11፤ዐይኔም፡በጠላቶቼ፡ላይ፡አየች፥ዦሮዬም፡በእኔ፡ላይ፡በቆሙ፡በክፉዎች፡ላይ፡ሰማች።
12፤ጻድቅ፡እንደ፡ዘንባባ፡ያፈራል፥እንደ፡ሊባኖስ፡ዝግባም፡ያድጋል።
13፤በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ተተክለዋል፥በአምላካችንም፡አደባባይ፡ውስጥ፡ይበቅላሉ።
14፤ያን፡ጊዜ፡በለመለመ፡ሽምግልና፡ያፈራሉ፡ደስተኛዎችም፡ኾነው፡ይኖራሉ።
15፤አምላኬ፡እግዚአብሔር፡እውነተኛ፡እንደ፡ኾነ፡ይነግራሉ፥በርሱም፡ዘንድ፡ዐመፃ፡የለም።
_______________መዝሙር፡92፡(93)።______________
በሰንበት፡ቀን፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ነገሠ፥ክብርንም፡ለበሰ፤እግዚአብሔር፡ኀይልን፡ለበሰ፥ታጠቀም፤ዓለምን፡እንዳትናወጥ፡አጸና ት።
2፤ዙፋንኽ፡ከጥንት፡ዠምሮ፡የተዘጋጀ፡ነው፥አንተም፡ከዘለዓለም፡ነኽ።
3፤አቤቱ፥ወንዞች፡ከፍ፡ከፍ፡አደረጉ፥ወንዞች፡ቃሎቻቸውን፡ከፍ፡ከፍ፡አደረጉ።
4፤ከብዙ፡ውሃዎች፡ድምፅ፡ከባሕርም፡ታላቅ፡ሞገድ፡ይልቅ፡እግዚአብሔር፡በከፍታው፡ድንቅ፡ነው።
5፤ምስክርኽ፡እጅግ፡የታመነ፡ነው፤አቤቱ፥እስከ፡ረዥም፡ዘመን፡ድረስ፡ለቤትኽ፡ቅድስና፡ይገ፟ባ፟ል።
_______________መዝሙር፡93፡(94)።______________
በአራተኛ፡ሰንበት፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡የበቀል፡አምላክ፡ነው።የበቀል፡አምላክ፡ተገለጠ።
2፤የምድር፡ፈራጅ፡ሆይ፥ከፍ፡ከፍ፡በል፤ለትዕቢተኛዎች፡ፍዳቸውን፡ክፈላቸው።
3፤አቤቱ፥ኀጢአተኛዎች፡እስከ፡መቼ፧ኀጢአተኛዎች፡እስከ፡መቼ፡ይጓደዳሉ፧
4፤ይከራከራሉ፥ዐመፃንም፡ይናገራሉ፤ዐመፃንም፡የሚያደርጉ፡ዅሉ፡ይናገራሉ።
5፤አቤቱ፥ሕዝብን፡አዋረዱ፥ርስትኽንም፡አስቸገሩ።
6፤ባልቴቲቱንና፡ድኻ፡አደጉን፡ገደሉ፥ስደተኛውንም፡ገደሉ።
7፤እግዚአብሔር፡አያይም፥የያዕቆብ፡አምላክ፡አያስተውልም፡አሉ።
8፤የሕዝብ፡ደንቈሮዎች፡ሆይ፥አስተውሉ፤ሰነፎችማ፡መቼ፡ይጠበባሉ፧
9፤ዦሮን፡የተከለው፡አይሰማምን፧ዐይንን፡የሠራው፡አያይምን፧
10፤አሕዛብንስ፡የሚገሥጸው፥ለሰውም፡ዕውቀት፡የሚያስተምረው፡ርሱ፡አይዘልፍምን፧
11፤የሰዎች፡ዐሳብ፡ከንቱ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡ያውቃል።
12-13፤ለኀጢአተኛ፡ጕድጓድ፡እስኪቈፈር፡ድረስ፡ከክፉዎች፡ዘመናት፡ይወገድ፡ዘንድ፥አቤቱ፥አንተ፡የገሠጽኸው፡ ሕግኽንም፡ያስተማርኸው፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
14፤እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡አይጥልምና፥ርስቱንም፡አይተውምና፡
15፤ፍርድ፡ወደ፡ጽድቅ፡እስኪመልስ፡ድረስ፡ልበ፡ቅኖችም፡ዅሉ፡ይከተሏታል።
16፤በክፉዎች፡ላይ፡ለእኔ፡የሚቆም፡ማን፡ነው፧ዐመፃንስ፡በሚያደርጉ፡ላይ፡ለእኔ፡የሚከራከር፡ማን፡ነው፧
17፤እግዚአብሔር፡የረዳኝ፡ባይኾን፡ነፍሴ፡ለጥቂት፡ጊዜ፡በሲኦል፡ባደረች፡ነበር።
18፤እግሮቼ፡ተሰናከሉ፡ባልኹ፡ጊዜ፥አቤቱ፥ምሕረትኽ፡ረዳኝ።
19፤አቤቱ፥ለልቤ፡እንደ፡መከራዋ፡ብዛት፡ማጽናናትኽ፡ነፍሴን፡ደስ፡አሠኛት።
20፤በሕግ፡ላይ፡ዐመፅን፡የሚሠራ፡የዐመፅ፡ዙፋን፡ከአንተ፡ጋራ፡አንድ፡ይኾናልን፧
21፤የጻድቅን፡ነፍስ፡ያደቡባታል፥በንጹሕ፡ደምም፡ይፈርዳሉ።
22፤እግዚአብሔር፡መጠጊያ፡ኾነኝ፥አምላኬ፡የተስፋዬም፡ረዳት፡ነው።
23፤እንደ፡በደላቸውም፡እንደ፡ክፋታቸውም፡ፍዳቸውን፡ይከፍላቸዋል፥አምላካችን፡እግዚአብሔርም፡ያጠፋቸዋል።
_______________መዝሙር፡94፡(95)።______________
የዳዊት፡ምስጋና፡መዝሙር።
1፤ኑ፥በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይበለን፤ለአምላክ፡ለመድኀኒታችን፡እልል፡እንበል።
2፤በምስጋና፡ወደ፡ፊቱ፡እንድረስ፥በዝማሬም፡ለርሱ፡እልል፡እንበል፤
3፤እግዚአብሔር፡ታላቅ፡አምላክ፡ነውና፥በአማልክትም፡ዅሉ፡ላይ፡ታላቅ፡ንጉሥ፡ነውና።
4፤እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡አይጥላቸውም፤የምድር፡ዳርቻዎችም፡በእጁ፡ውስጥ፡ናቸው፥የተራራዎች፡ከፍታዎች፡የር ሱ፡ናቸው።
5፤ባሕር፡የርሱ፡ናት፥ርሱም፡አደረጋት፤የብስንም፡እጆቹ፡ሠሯት።
6፤ኑ፥እንስገድ፥ለርሱም፡እንገዛ፤በርሱ፡ባደረገን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንንበርከክ፤
7፤ርሱ፡አምላካችን፡ነውና፥እኛ፡የማሰማሪያው፡ሕዝብ፡የእጁም፡በጎች፡ነንና።
8፤በምድረ፡በዳ፡እንደ፡ተፈታተኑት፡እንዳስቈጡት፡ጊዜ፥ዛሬ፡ድምፁን፡ብትሰሙ፡ልባችኹን፡አታጽኑ።
9፤የተፈታተኑኝ፡አባቶቻችኹ፡ፈተኑኝ፡ሥራዬንም፡አዩ።
10፤ያችን፡ትውልድ፡አርባ፡ዓመት፡ተቈጥቻት፡ነበር።ዅልጊዜ፡ልባቸው፡ይስታል፥እነርሱም፡መንገዴን፡አላወቁም ፡አልኹ።
11፤ወደ፡ዕረፍቴም፡እንዳይገቡ፡በቍጣዬ፡ማልኹ።
_______________መዝሙር፡95፡(96)።______________
ከምርኮ፡በዃላ፡ቤት፡በተሠራ፡ጊዜ።
1፤ለእግዚአብሔር፡ዐዲስ፡ምስጋናን፡አመስግኑ፤ምድር፡ዅሉ፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ።
2፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፡ስሙንም፡ባርኩ፥ዕለት፡ዕለትም፡ማዳኑን፡አውሩ።
3፤ክብሩን፡ለአሕዛብ፡ተኣምራቱንም፡ለወገኖች፡ዅሉ፡ንገሩ፤
4፤እግዚአብሔር፡ታላቅ፡ምስጋናውም፡ብዙ፡ነውና፥በአማልክትም፡ዅሉ፡ላይ፡የተፈራ፡ነውና።
5፤የአሕዛብ፡አማልክት፡ዅሉ፡አጋንንት፡ናቸውና፤እግዚአብሔር፡ግን፡ሰማያትን፡ሠራ።
6፤ምስጋናና፡ውበት፡በፊቱ፥ቅዱስነትና፡ግርማ፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡ናቸው።
7፤የአሕዛብ፡ወገኖች፥ለእግዚአብሔር፡አምጡ፥ክብርና፡ምስጋናን፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ፤
8፤ለስሙ፡የሚገ፟ባ፟፡ክብርን፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ፤ቍርባን፡ያዙ፡ወደ፡አደባባዮችም፡ግቡ።
9፤በቅድስናው፡ስፍራ፡ለእግዚአብሔር፡ስገዱ፤ምድር፡ዅሉ፡በፊቱ፡ትነዋወጥ።
10፤በአሕዛብ፡መካከል።እግዚአብሔር፡ነገሠ፡በሉ።እንዳይናወጥም፡ዓለሙን፡ርሱ፡አጸናው፥አሕዛብንም፡በቅንነ ት፡ይፈርዳል።
11፤ሰማያት፡ደስ፡ይበላቸው፥ምድርም፡ሐሤትን፡ታድርግ፤ባሕርና፡ሞላዋ፡ይናወጡ፤
12፤በረሓ፡በርሷም፡ያሉ፡ዅሉ፡ሐሤትን፡ያድርጉ፤የዱር፡ዛፎች፡ዅሉ፡በዚያን፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ደስ፡ ይላቸዋል፤
13፤ይመጣልና፤በምድር፡ላይ፡ሊፈርድ፡ይመጣልና፤ርሱም፡ዓለምን፡በጽድቅ፡አሕዛብንም፡በቅንነት፡ይፈርዳል።
_______________መዝሙር፡96፡(97)።______________
1፤እግዚአብሔር፡ነገሠ፤ምድር፡ሐሤትን፡ታድርግ፥ብዙ፡ደሴቶችም፡ደስ፡ይበላቸው።
2፤ደመና፡ጭጋግም፡በዙሪያው፡ናቸው፤ጽድቅና፡ፍርድ፡የዙፋኑ፡መሠረት፡ናቸው።
3፤እሳት፡በፊቱ፡ይኼዳል፥ጠላቶቹንም፡በዙሪያው፡ያቃጥላል።
4፤መብረቆቹ፡ለዓለም፡አበሩ፤ምድር፡አየችና፡ተናወጠች።
5፤ተራራዎችም፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፥ከምድር፡ዅሉ፡ጌታ፡ፊት፡እንደ፡ሠም፡ቀለጡ።
6፤ሰማያት፡የርሱን፡ጽድቅ፡አወሩ፥አሕዛብም፡ዅሉ፡ክብሩን፡አዩ።
7፤ለተቀረጸ፡ምስል፡የሚሰግዱ፡ዅሉ፥በጣዖቶቻቸውም፡የሚመኩ፡ይፈሩ፤መላእክቱ፡ዅሉ፥ስገዱለት።
8፤አቤቱ፥ስለ፡ፍርድኽ፡ጽዮን፡ሰምታ፡ደስ፡አላት፥የይሁዳም፡ሴት፡ልጆች፡ደስ፡አላቸው፤
9፤አንተ፥እግዚአብሔር፥በምድር፡ላይ፡ዅሉ፡ልዑል፡ነኽና፥በአማልክትም፡ዅሉ፡ላይ፡እጅግ፡ከፍ፡ከፍ፡ብለኻልና ።
10፤እግዚአብሔርን፡የምትወዱ፥ክፋትን፡ጥሉ፤እግዚአብሔር፡የቅዱሳኑን፡ነፍሶች፡ይጠብቃል፥ከኃጥኣንም፡እጅ፡ ያድናቸዋል።
11፤ብርሃን፡ለጻድቃን፥ደስታም፡ለልበ፡ቅኖች፡ወጣ።
12፤ጻድቃን፥በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይበላችኹ፥ለቅድስናውም፡መታሰቢያ፡አመስግኑ።
_______________መዝሙር፡97፡(98)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ለእግዚአብሔር፡ዐዲስ፡ምስጋናን፡አመስግኑ፥እግዚአብሔር፡ተኣምራትን፡አድርጓልና፤ቀኙ፡የተቀደሰም፡ክንዱ ፡ለርሱ፡ማዳን፡አደረገ።
2፤እግዚአብሔር፡ማዳኑን፡አስታወቀ፥በአሕዛብም፡ፊት፡ጽድቁን፡ገለጠ።
3፤ለያዕቆብ፡ምሕረቱን፡ለእስራኤልም፡ቤት፡እውነቱን፡ዐሰበ፤የምድር፡ዳርቻዎች፡ዅሉ፡የአምላካችንን፡ማዳን፡ አዩ።
4፤ምድር፡ዅሉ፡ሆይ፥ለእግዚአብሔር፡እልል፡በሉ፤አመስግኑ፥ደስ፡ይበላችኹ፥ዘምሩም።
5፤ለእግዚአብሔር፡በመሰንቆ፥በመሰንቆና፡በዝማሬ፡ድምፅ፡ዘምሩ።
6፤በዋሽንትና፡በመለከት፡ድምፅ፡በንጉሥ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እልል፡በሉ።
7፤ባሕርና፡ሞላዋ፥ዓለምም፡በርሷም፡የሚኖሩ፡ይናወጡ።
8፤ወንዞችም፡በአንድነት፡በእጅ፡ያጨብጭቡ፤ተራራዎች፡ደስ፡ይበላቸው፥በምድር፡ሊፈርድ፡ይመጣልና።
9፤ለዓለምም፡በጽድቅ፡ለአሕዛብም፡በቅንነት፡ይፈርዳል።
_______________መዝሙር፡98፡(99)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ነገሠ፥አሕዛብ፡ይደንግጡ፤በኪሩቤል፡ላይ፡ተቀመጠ፥ምድር፡ትናወጥ።
2፤እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ታላቅ፡ነው፤ርሱም፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አለ።
3፤ግሩምና፡ቅዱስ፡ነውና፥ዅሉ፡ታላቅ፡ስምኽን፡ያመስግኑ።
4፤የንጉሥ፡ክብር፡ፍርድን፡ይወዳ፟ል፤አንተ፡ቅንነትን፡አጸናኽ፥ለያዕቆብ፡ፍርድንና፡ጽድቅን፡አንተ፡አደረግ ኽ።
5፤አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡ከፍ፡ከፍ፡አድርጉት፥ቅዱስ፡ነውና፥ወደእግሩ፡መረገጫ፡ስገዱ።
6፤ሙሴና፡አሮን፡በካህናቱ፡ዘንድ፥ሳሙኤልም፡ስሙን፡በሚጠሩት፡ዘንድ፡ናቸው።እግዚአብሔርን፡ጠሩት፥ርሱም፡መ ለሰላቸው።
7፤በደመና፡ዐምድም፡ተናገራቸው፤ምስክሩንና፡የሰጣቸውን፡ትእዛዝ፡ጠበቁ።
8፤አቤቱ፡አምላክችን፡ሆይ፥አንተ፡ሰማኻቸው፤አቤቱ፥አንተ፡ማርኻቸው፥ሥራቸውን፡ዅሉ፡ግን፡ተበቀልኻቸው።
9፤አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡ከፍ፡ከፍ፡አድርጉት፥በቅዱስ፡ተራራውም፡ስገዱ፤አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ቅ ዱስ፡ነውና።
_______________መዝሙር፡99፡(100)።______________
የምስጋና፡መዝሙር።
1፤ምድር፡ዅሉ፥ለእግዚአብሔር፡እልል፡በሉ፥
2፤በደስታም፡ለእግዚአብሔር፡ተገዙ፥በሐሤትም፡ወደ፡ፊቱ፡ግቡ።
3፤እግዚአብሔር፡ርሱ፡አምላክ፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቁ፤ርሱ፡ሠራን፡እኛም፡አይደለንም፤እኛስ፡ሕዝቡ፡የማሰማሪያው ም፡በጎች፡ነን።
4፤ወደ፡ደጆቹ፡በመገዛት፥ወደ፡አደባባዮቹም፡በምስጋና፡ግቡ፤አመስግኑት፥ስሙንም፡ባርኩ፤
5፤እግዚአብሔር፡ቸር፥ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፥እውነቱም፡ለልጅ፡ልጅ፡ነውና።
_______________መዝሙር፡100፡(101)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ምሕረትንና፡ፍርድን፡እቀኝልኻለኹ።
2፤እዘምራለኹ፥ንጹሕ፡መንገዱንም፡አስተውላለኹ፤ወደ፡እኔ፡መቼ፡ትመጣለኽ፧በቤቴ፡መካከል፡በልቤ፡ቅንነት፡እ ኼዳለኹ።
3፤በዐይኔ፡ፊት፡ክፉን፡ነገር፡አላኖርኹም፤ሕግ፡ተላላፊዎችን፡ጠላኹ።
4፤ጠማማ፡ልብም፡አልተጠጋኝም፤ክፉ፡ከእኔ፡በራቀ፡ጊዜ፡አላወቅኹም።
5፤ባልንጀራውን፡በቀስታ፡የሚያማን፡ርሱን፡አሳደድኹ፤በዐይኑ፡ትዕቢተኛ፡የኾነውና፡ልቡ፡የሚሣሣው፡ከእኔ፡ጋ ራ፡አይተባበርም።
6፤ከእኔ፡ጋራ፡ይኖሩ፡ዘንድ፤ዐይኖቼ፡በምድር፡ምእመናን፡ላይ፡ናቸው፤በቀና፡መንገድ፡የሚኼድ፡ርሱ፡ያገለግለ ኛል።
7፤ትዕቢትን፡የሚያደርግ፡በቤቴ፡መካከል፡አይኖርም፤ዐመፅን፡የሚናገር፡በዐይኔ፡ፊት፡አይቀናም።
8፤ዐመፃ፡የሚያደርጉትን፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡ከተማ፡አጠፋቸው፡ዘንድ፥የምድርን፡ኀጢአተኛዎች፡ዅሉ፡በማለዳ ፡እገድላቸዋለኹ።
_______________መዝሙር፡101፡(102)።______________
ባዘነና፡ልመናውን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ባፈሰሰ፡ጊዜ፡የችግረኛ፡ጸሎት።
1፤አቤቱ፥ጸሎቴን፡ስማኝ፥ጩኸቴም፡ወዳንተ፡ይድረስ።
2፤በመከራዬ፡ቀን፡ፊትኽን፡ከእኔ፡አትመልስ፤ዦሮኽን፡ወደ፡እኔ፡አዘንብል፤በጠራኹኽ፡ቀን፡ፈጥነኽ፡ስማኝ።
3፤ዘመኔ፡እንደ፡ጢስ፡አልቃለችና፥ዐጥንቶቼም፡እንደ፡መቃጠያ፡ተቃጥለዋልና።
4፤እኽል፡መብላት፡ተረስቶኛልና፥ተቀሠፍኹ፤ልቤም፡እንደ፡ሣር፡ደረቀ።
5፤ከጩኸቴ፡ድምፅ፡የተነሣ፡ዐጥንቶቼ፡ከሥጋዬ፡ጋራ፡ተጣበቁ።
6፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡እርኩም፡መሰልኹ፤በፈረሰ፡ቤት፡እንዳለ፡እንደ፡ጕጕት፡ኾንኹ።
7፤ተጋኹ፥በሰገነትም፡እንደሚኖር፡ብቸኛ፡ድንቢጥ፡ኾንኹ።
8፤ጠላቶቼ፡ዅልጊዜ፡ይሰድቡኛል፥የሚያሳድዱኝም፡ተማማሉብኝ።
9፤ዐመድን፡እንደ፡እኽል፡ቅሜያለኹና፥መጠጤንም፡ከእንባዬ፡ጋራ፡ቀላቅያለኹና፥
10፤ከቍጣኽና፡ከመዓትኽም፡የተነሣ፤አንሥተኸኛልና፥ጥለኸኝማልና።
11፤ዘመኖቼ፡እንደ፡ጥላ፡አዘንብለዋል፤እኔም፡እንደ፡ሣር፡ደርቄያለኹ።
12፤አንተ፡ግን፥አቤቱ፥ለዘለዓለም፡ትኖራለኽ፥መታሰቢያኽም፡ለልጅ፡ልጅ፡ነው።
13፤አንተ፡ተነሥ፡ጽዮንንም፡ይቅር፡በላት፥የምሕረቷ፡ጊዜ፡ነውና፥ዘመኗም፡ደርሷልና፤
14፤ባሪያዎችኽም፡ድንጋዮቿን፡ወደ፟ዋልና፥ለመሬቷም፡አዝነዋልና።
15፤አቤቱ፥አሕዛብ፡ስምኽን፥ነገሥታትም፡ዅሉ፡ክብርኽን፡ይፈራሉ፤
16፤እግዚአብሔር፡ጽዮንን፡ይሠራታልና፥በክብሩም፡ይገለጣልና።
17፤ወደችግረኛዎች፡ጸሎት፡ተመለከተ፥ልመናቸውንም፡አልናቀም።
18፤ይህ፡ለሚመጣ፡ትውልድ፡ይጻፍ፥የሚፈጠርም፡ሕዝብ፡ለእግዚአብሔር፡እልል፡ይላል፤
19፤እግዚአብሔር፡ከመቅደሱ፡ከፍታ፡ኾኖ፡ተመልክቷልና፥ከሰማይ፡ኾኖ፡ምድርን፡አይቷልና፤
20፤የእስረኛዎችን፡ጩኸት፡ይሰማ፡ዘንድ፥ሊገድሉ፡የተፈረደባቸውን፡ያድን፡ዘንድ፤
21፤የእግዚአብሔርን፡ስም፡በጽዮን፡ምስጋናውንም፡በኢየሩሳሌም፡ይናገሩ፡ዘንድ፤
22፤አሕዛብ፡በአንድነት፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፡መንግሥታትም፡ለእግዚአብሔር፡ይገዙ፡ዘንድ።
23፤በኀይሉ፡ጐዳና፡መለሰለት፦የዘመኔን፡አነስተኛነት፡ንገረኝ።
24፤በዘመኔ፡እኩሌታ፡አትውሰደኝ፤ዓመቶችኽ፡ለልጅ፡ልጅ፡ናቸው።
25፤አቤቱ፥አንተ፡ከጥንት፡ምድርን፡መሠረትኽ፥ሰማያትም፡የእጅኽ፡ሥራ፡ናቸው።
26፤እነርሱ፡ይጠፋሉ፥አንተ፡ግን፡ትኖራለኽ፤ዅላቸው፡እንደ፡ልብስ፡ያረጃሉ፥እንደ፡መጐናጸፊያም፡ትለውጣቸዋ ለኽ፥ይለወጡማል፤
27፤አንተ፡ግን፡ያው፡አንተ፡ነኽ፥ዓመቶችኽም፡ከቶ፡አያልቁም።
28፤የባሪያዎችኽም፡ልጆች፡ይኖራሉ፥ዘራቸውም፡ለዘለዓለም፡ትጸናለች።
_______________መዝሙር፡102፡(103)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ፥ዐጥንቶቼም፡ዅሉ፥የተቀደሰ፡ስሙን።
2፤ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ፥ምስጋናውንም፡ዅሉ፡አትርሺ፤
3፤ኀጢአትሽን፡ዅሉ፡ይቅር፡የሚል፥ደዌሽንም፡ዅሉ፡የሚፈውስ፥
4፤ሕይወትሽን፡ከጥፋት፡የሚያድናት፥በምሕረቱና፡በቸርነቱ፡የሚከልልሽ፥
5፤ምኞትሽን፡ከበረከቱ፡የሚያጠግባት፥ጕልማሳነትሽን፡እንደ፡ንስር፡ያድሳል።
6፤እግዚአብሔር፡ይቅርታ፡አድራጊ፡ነው፤ለተበደሉ፡ዅሉ፡ይፈርዳል።
7፤ለሙሴ፡መንገዱን፡አስታወቀ፥ለእስራኤል፡ልጆችም፡አደራረጉን።
8፤እግዚአብሔር፡መሓሪና፡ይቅር፡ባይ፡ነው፥ከቍጣ፡የራቀ፡ምሕረቱም፡የበዛ።
9፤ዅልጊዜም፡አይቀሥፍም፥ለዘለዓለምም፡አይቈጣም።
10፤እንደ፡ኀጢአታችን፡አላደረገብንም፥እንደ፡በደላችንም፡አልከፈለንም።
11፤ሰማይ፡ከምድር፡ከፍ፡እንደሚል፥እንዲሁ፡እግዚአብሔር፡ምሕረቱን፡በሚፈሩት፡ላይ፡አጠነከረ።
12፤ምሥራቅ፡ከምዕራብ፡እንደሚርቅ፥እንዲሁ፡ኀጢአታችንን፡ከእኛ፡አራቀ።
13፤አባት፡ለልጆቹ፡እንደሚራራ፡እንዲሁ፡እግዚአብሔር፡ለሚፈሩት፡ይራራል፤
14፤ፍጥረታችንን፡ርሱ፡ያውቃልና፤አቤቱ፥እኛ፡ዐፈር፡እንደ፡ኾን፟፡ዐስብ።
15፤ሰውስ፡ዘመኑ፡እንደ፡ሣር፡ነው፤እንደ፡ዱር፡አበባ፡እንዲሁ፡ያብባል፤
16፤ነፋስ፡በነፈሰበት፡ጊዜ፡ያልፋልና፥ስፍራውንም፡ደግሞ፡አያውቀውምና።
17፤የእግዚአብሔር፡ምሕረት፡ግን፡ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡በሚፈሩት፡ላይ፥ጽድቁም፡በልጅ፡ልጆች፡ላይ፡ ነው፤
18፤ቃል፡ኪዳኑን፡በሚጠብቁ፥ትእዛዙንም፡ያደርጓት፡ዘንድ፡በሚያስቡ፡ላይ፡ነው።
19፤እግዚአብሔር፡ዙፋኑን፡በሰማይ፡አዘጋጀ፥መንግሥቱም፡ዅሉን፡ትገዛለች።
20፤ቃሉን፡የምትፈጽሙ፥ብርቱዎችና፡ኀያላን፥የቃሉንም፡ድምፅ፡የምትሰሙ፡መላእክቱ፡ዅሉ፥እግዚአብሔርን፡ባር ኩ።
21፤ሰራዊቱ፡ዅሉ፥ፈቃዱን፡የምታደርጉ፡አገልጋዮቹ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩ።
22፤ፍጥረቶቹ፡ዅሉ፡በግዛቱ፡ስፍራ፡ዅሉ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩ።ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ።
_______________መዝሙር፡103፡(104)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ፤አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥አንተ፡እጅግ፡ታላቅ፡ነኽ፤ክብርንና፡ግርማን፡ለበ ስኽ።
2፤ብርሃንን፡እንደ፡ልብስ፡ለበስኽ፤ሰማይንም፡እንደ፡መጋረጃ፡ዘረጋኽ፤
3፤ዕልፍኙን፡በውሃ፡የሚሠራ፥ሠረገላውን፡ደመና፡የሚያደርግ፥በነፋስ፡ክንፍም፡የሚኼድ፥
4፤መላእክቱን፡መንፈስ፡የሚያደርግ፥አገልጋዮቹንም፡የእሳት፡ነበልባል።
5፤ለዘላለም፡እንዳትናወጥ፡ምድርን፡በመሠረቷ፡ላይ፡መሠረታት።
6፤በጥልቅ፡እንደ፡ልብስ፡ከደንኻት፥በተራራዎችም፡ላይ፡ውሃዎች፡ይቆማሉ።
7፤ከዘለፋኽም፡ይሸሻሉ፥ከነጐድጓድኽም፡ድምፅ፡ይደነግጣሉ፤
8፤ወደ፡ተራራዎች፡ይወጣሉ፥ወደ፡ቈላዎች፡ወዳዘጋጀኽላቸው፡ስፍራ፡ይወርዳሉ፤
9፤እንዳያልፉትም፡ድንበር፡አደረግኽላቸው፥ምድርን፡ይከድኑ፡ዘንድ፡እንዳይመለሱ።
10፤ምንጮችን፡ወደ፡ቈላዎች፡ይልካል፤በተራራዎች፡መካከል፡ውሃዎች፡ያልፋሉ፤
11፤የዱር፡አራዊትን፡ዅሉ፡ያጠጣሉ፥የበረሓ፡አህያዎችም፡ጥማታቸውን፡ይረካሉ።
12፤የሰማይም፡ወፎች፡በእነርሱ፡ዘንድ፡ያድራሉ፥በድንጋዩ፡ስንጥቅ፡መካከልም፡ይጮኻሉ።
13፤ተራራዎችን፡ከላይ፡የሚያጠጣቸው፤ከሥራኽ፡ፍሬ፡ምድር፡ትጠግባለች።
14፤እንጀራን፡ከምድር፡ያወጣ፡ዘንድ፡ለምለሙን፡ለሰው፡ልጆች፡ጥቅም፥ሣርንም፡ለእንስሳ፡ያበቅላል።
15፤ወይን፡የሰውን፡ልብ፡ደስ፡ያሰኛል፥ዘይትም፡ፊትን፡ያበራል፥እኽልም፡የሰውን፡ጕልበት፡ያጠነክራል።
16፤የእግዚአብሔር፡ዛፎች፡ርሱም፡የተከላቸው፡የሊባኖስ፡ዝግባዎች፡ይጠግባሉ።
17፤በዚያም፡ወፎች፡ይዋለዳሉ፥የሽመላ፡ቤትም፡የእነርሱ፡ጎረቤት፡ነው።
18፤ረዣዥም፡ተራራዎች፡ለዋላዎች፥ድንጋዮችም፡ለሽኮኮዎች፡መሸሻ፡ናቸው።
19፤ጨረቃን፡ለጊዜዎች፡አደረገ፤ፀሓይም፡መግቢያውን፡ያውቃል።
20፤ጨለማ፡ታደርጋለኽ፥ሌሊትም፡ይሆናል፤በርሱም፡የዱር፡አራዊት፡ዅሉ፡ይወጡበታል።
21፤የአንበሳ፡ግልገሎች፡ለመንጠቅ፡ይጮኻሉ፥ከእግዚአብሔርም፡ምግባቸውን፡ይሻሉ።
22፤ፀሓይ፡ስትወጣ፡ይሰበሰባሉ፥በየዋሻቸውም፡ይተኛሉ።
23፤ሰው፡ወደ፡ተግባሩ፥እስኪመሽም፡ድረስ፡ወደ፡ሥራው፡ይወጣል።
24፤አቤቱ፥ሥራኽ፡እጅግ፡ብዙ፡ነው፤ዅሉን፡በጥበብ፡አደረግኽ፥ምድርም፡ከፍጥረትኽ፡ተሞላች።
25፤ይህች፡ባሕር፡ታላቅና፡ሰፊ፡ናት፤በዚያ፡ስፍራ፡ቍጥር፡የሌለው፡ተንቀሳቃሽ፥ታላላቆችና፡ታናናሾች፡እንስ ሳዎች፡አሉ።
26፤በዚያ፡ጊዜ፡መርከቦች፡ይኼዳሉ፥በዚያም፡ላይ፡የፈጠርኸው፡ዘንዶ፡ይጫወትበታል።
27፤ምግባቸውን፡በየጊዜው፡ትሰጣቸው፡ዘንድ፡እነዚህ፡ዅሉ፡አንተን፡ተስፋ፡ያደርጋሉ።
28፤በሰጠኻቸውም፡ጊዜ፡ይሰበስባሉ፤እጅኽን፡ትከፍታለኽ፥ከመልካም፡ነገርም፡ይጠግባሉ።
29፤ፊትኽን፡ስትሰውር፡ይደነግጣሉ፤ነፍሳቸውን፡ታወጣለኽ፡ይሞታሉም፥ወደ፡ዐፈራቸውም፡ይመለሳሉ።
30፤መንፈስኽን፡ትልካለኽ፡ይፈጠራሉም፥የምድርንም፡ፊት፡ታድሳለኽ።
31፤የእግዚአብሔር፡ክብር፡ለዘላለም፡ይኹን፤እግዚአብሔር፡በሥራው፡ደስ፡ይለዋል።
32፤ምድርን፡ያያል፡እንድትንቀጠቀጥም፡ያደርጋል፤ተራራዎችን፡ይዳስሳል፡ይጤሳሉም።
33፤በሕይወቴ፡ሳለኹ፡ለእግዚአብሔር፡እቀኛለኹ፥ለአምላኬም፡በምኖርበት፡ዘመን፡ዅሉ፡እዘምራለኹ።
34፤ቃሌ፡ለርሱ፡ይጣፍጠው፥እኔም፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይለኛል።
35፤ኃጥኣን፡ከምድር፡ይጥፉ፤ዐመፀኛዎች፡እንግዲህ፡አይገኙ።ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡104፡(105)።______________
ሃሌ፡ሉያ።
1፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥ስሙንም፡ጥሩ፥ለአሕዛብም፡ሥራውን፡አውሩ።
2፤ተቀኙለት፥ዘምሩለት፥ተኣምራቱንም፡ዅሉ፡ተናገሩ።
3፤በቅዱስ፡ስሙ፡ተጓደዱ፤እግዚአብሔርን፡የሚፈልግ፡ልብ፡ደስ፡ይበለው።
4፤እግዚአብሔርን፡ፈልጉት፡ትጸናላችኹም፤ዅልጊዜ፡ፊቱን፡ፈልጉ።
5-6፤ባሪያዎቹ፡የአብርሃም፡ዘር፥ለርሱም፡የተመረጣችኹ፡የያዕቆብ፡ልጆች፡ሆይ፥የሠራትን፡ድንቅ፡ዐስቡ፥ተኣም ራቱን፡የአፉንም፡ፍርድ።
7፤ርሱ፡እግዚአብሔር፡አምላካችን፡ነው፤ፍርዱ፡በምድር፡ዅሉ፡ነው።
8፤ቃል፡ኪዳኑን፡ለዘለዓለም፥እስከ፡ሺሕ፡ትውልድ፡ያዘዘውን፡ቃሉን፡ዐሰበ፥
9፤ለአብርሃም፡ያደረገውን፥ለይሥሐቅም፡የማለውን፤
10፤ለያዕቆብ፡ሥርዐት፡እንዲኾን፡ለእስራኤልም፡የዘለዓለም፡ኪዳን፡እንዲኾን፡አጸና።
11፤እንዲህም፡አለ፦ለአንተ፡የከነዓንን፡ምድር፡የርስታችኹን፡ገመድ፡እሰጣለኹ፤
12፤ይህም፡የኾነው፡እነርሱ፡በቍጥር፡ጥቂቶች፡ሰዎች፥እጅግ፡ጥቂቶችና፡ስደተኛዎች፡ሲኾኑ፡ነው።
13፤ከሕዝብ፡ወደ፡ሕዝብ፥ከመንግሥታትም፡ወደ፡ሌላ፡ሕዝብ፡ዐለፉ።
14-15፤የቀባዃቸውን፡አትዳስሱ፥በነቢያቴም፡ክፉ፡አታድርጉ፡ብሎ፥ሰው፡ግፍ፡ያደርግባቸው፡ዘንድ፡አልፈቀደም፥ ስለ፡እነርሱም፡ነገሥታትን፡ገሠጸ።
16፤በምድር፡ላይ፡ራብን፡ጠራ፥የእኽልን፡ኀይል፡ዅሉ፡ሰበረ።
17፤በፊታቸው፡ሰውን፡ላከ፤ዮሴፍ፡ለባርነት፡ተሸጠ።
18፤እግሮቹም፡በእግር፡ብረት፡ደከሙ፥ርሱም፡በብረት፡ውስጥ፡ገባ።
19፤ቃሉ፡እስኪመጣለት፡ድረስ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ፈተነው።
20፤ንጉሥ፡ላከ፡ፈታውም፥የአሕዛብም፡አለቃ፡አስፈታው።
21፤የቤቱ፡ጌታ፥የጥሪቱ፡ዅሉ፡ገዢ፡አደረገው፥
22፤አለቃዎቹን፡እንደ፡ፈቃዱ፡ይገሥጽ፡ዘንድ፥ሽማግሌዎቹንም፡ጥበበኛዎች፡ያደርጋቸው፡ዘንድ።
23፤እስራኤልም፡ወደ፡ግብጽ፡ገባ፥ያዕቆብም፡በካም፡አገር፡ተቀመጠ።
24፤ሕዝቡንም፡እጅግ፡አበዛ፥ከጠላቶቻቸውም፡ይልቅ፡አበረታቸው።
25፤ሕዝቡን፡ይጠሉ፡ዘንድ፡በባሪያዎቹም፡ላይ፡ይተ፟ነኰሉ፡ዘንድ፡ልባቸውን፡ለወጠ።
26፤ባሪያውን፡ሙሴን፡የመረጠውንም፡አሮንን፡ላከ።
27፤የተኣምራቱን፡ነገር፡በላያቸው፡ድንቁንም፡በካም፡አገር፡አደረገ።
28፤ጨለማን፡ላከ፡ጨለመባቸውም፤በቃሉም፡ዐመፁ።
29፤ውሃቸውን፡ወደ፡ደም፡ለወጠ፥ዓሣዎቻቸውንም፡ገደለ።
30፤ምድራቸው፡የንጉሦቻቸውም፡ቤቶች፡በጓጕንቸር፡ሞሉ።
31፤ተናገረ፥የውሻ፡ዝንብ፡ትንኝም፡በዳርቻቸው፡መጡ።
32፤ዝናባቸውን፡በረዶ፡አደረገው፥እሳትም፡በምድራቸው፡ተቃጠለች።
33፤ወይናቸውንና፡በለሳቸውን፡መታ፥የአገራቸውንም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ሰበረ።
34፤ተናገረ፥አንበጣም፡ስፍር፡ቍጥር፡የሌለውም፡ኵብኵባ፡መጣ፥
35፤የአገራቸውንም፡ለምለም፡ዅሉ፡በላ፥የምድራቸውንም፡ፍሬ፡በላ።
36፤የአገራቸውንም፡በኵር፡ዅሉ፥የጕልበታቸውን፡መዠመሪያ፡ዅሉ፡መታ።
37፤ከወርቅና፡ከብርም፡ጋራ፡አወጣቸው፥በወገናቸውም፡ውስጥ፡ደዌ፡አልነበረም።
38፤ፈርተዋቸው፡ነበርና፥ግብጽ፡በመውጣታቸው፡ደስ፡አላት።
39፤ደመናን፡ለመሸፈኛ፡ዘረጋባቸው፥እሳትንም፡በሌሊት፡ያበራላቸው፡ዘንድ፡ዘረጋ።
40፤ለመኑ፥ድርጭትንም፡አመጣላቸው፥የሰማይንም፡እንጀራ፡አጠገባቸው።
41፤አለቱን፡ሰነጠቀ፥ውሃውም፡ፈሰሰ፤ወንዞች፡በበረሓ፡ኼዱ፤
42፤ለባሪያው፡ለአብርሃም፡የነገረውን፡ቅዱስ፡ቃሉን፡ዐስቧልና።
43፤ሕዝቡንም፡በደስታ፡የተመረጡትንም፡በእልልታ፡አወጣ።
44፤የአሕዛብንም፡አገሮች፡ሰጣቸው፥የወገኖችንም፡ድካም፡ወረሱ፥
45፤ሕጉን፡ይጠብቁ፡ዘንድ፥ሥርዐቱንም፡ይፈልጉ፡ዘንድ።ሃሌ፡ሉያ፡
_______________መዝሙር፡105፡(106)።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ፤ቸር፡ነውና፥ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ።
2፤የእግዚአብሔርን፡ኀይል፡ሥራ፡ማን፡ይናገራል፧ምስጋናውንስ፡ዅሉ፡ማን፡ያሰማል፧
3፤ፍርድን፡የሚጠብቁ፥ጽድቅንም፡ዅልጊዜ፡የሚያደርጉ፡ምስጉኖች፡ናቸው።
4፤አቤቱ፥በሕዝብኽ፡ሞገስ፡ዐስበን፥በመድኀኒትኽም፡ጐብኘን፤
5፤የመረጥኻቸውን፡በጎነት፡እናይ፡ዘንድ፥በሕዝብኽም፡ደስታ፡ደስ፡ይለን፡ዘንድ፥ከርስትኽም፡ጋራ፡እንጓደድ፡ ዘንድ።
6፤ከአባቶቻችን፡ጋራ፡ኀጢአትን፡ሠራን፥ዐመፅንም፥በደልንም።
7፤አባቶቻችን፡በግብጽ፡ሳሉ፡ተኣምራትኽን፡አላስተዋሉም፥የምሕረትኽንም፡ብዛት፡አላሰቡም፤በቀይ፡ባሕር፡ባለ ፉ፡ጊዜ፡ዐመፁብኽ።
8፤ኀይሉን፡ግን፡ለማስታወቅ፥ስለ፡ስሙ፡አዳናቸው።
9፤ቀይ፡ባሕርንም፡ገሠጸ፥ርሱም፡ደረቀ፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡በጥልቅ፡መራቸው።
10፤ከሚጠሏቸውም፡እጅ፡አዳናቸው፥ከጠላትም፡እጅ፡ተቤዣቸው።
11፤ያሳደዷቸውንም፡ውሃ፡ደፈናቸው፥ከነርሱም፡አንድ፡አልቀረም።
12፤በዚያን፡ጊዜ፡በቃሉ፡አመኑ፥ምስጋናውንም፡ዘመሩ።
13፤ፈጥነውም፡ሥራውን፡ረሱ፥በምክሩም፡አልታገሡም።
14፤በምድረ፡በዳም፡ምኞትን፡ተመኙ፥በበረሓም፡እግዚአብሔርን፡ተፈታተኑት።
15፤የለመኑትንም፡ሰጣቸው፤ለነፍሳቸው፡ግን፡ክሳትን፡ላከ።
16፤ሙሴንም፡እግዚአብሔር፡የቀደሰውንም፡አሮንን፡በሰፈር፡ተመቀኟቸው።
17፤ምድርም፡ተከፈተች፡ዳታንንም፡ዋጠችው፥የአቤሮንንም፡ወገን፡ደፈነች፤
18፤በማኅበራቸውም፡እሳት፡ነደደች፥ነበልባልም፡ኃጥኣንን፡አቃጠላቸው።
19፤በኰሬብም፡ጥጃን፡ሠሩ፥ቀልጦ፡ለተሠራ፡ምስልም፡ሰገዱ።
20፤ሣርም፡በሚበላ፡በበሬ፡ምሳሌ፡ክብራቸውን፡ለወጡ።
21-22፤ታላቅ፡ነገርንም፡በግብጽ፥ድንቅንም፡በካራን፡ምድር፥ግሩም፡ነገርንም፡በቀይ፡ባሕር፡ያደረገውን፡ያዳና ቸውንም፡እግዚአብሔርን፡ረሱ።
23፤እንዳያጠፋቸው፡ቍጣውን፡ይመልስ፡ዘንድ፡የተመረጠው፡ሙሴ፡በመቅሠፍት፡ጊዜ፡በፊቱ፡ባይቆም፡ኖሮ፥ያጠፋቸ ው፡ዘንድ፡ተናገረ።
24፤የተወደደችውን፡ምድር፡ናቁ፥በቃሉም፡አልታመኑም፥
25፤በድንኳኖቻቸውም፡ውስጥ፡አንጐራጐሩ፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰሙም።
26-27፤በምድረ፡በዳም፡ይጥላቸው፡ዘንድ፥ዘራቸውንም፡በአሕዛብ፡መካከል፡ይጥል፡ዘንድ፥በያገሩም፡ይበትናቸው፡ ዘንድ፥እጁን፡አነሣባቸው።
28፤በብዔል፡ፌጎርም፡ተባበሩበት፥የሙታንንም፡መሥዋዕት፡በሉ።
29፤በሥራቸውም፡አስመረሩት፥ቸነፈርም፡በላያቸው፡በዛ።
30፤ፊንሐስም፡ተነሥቶ፡ፈረደባቸው፥ቸነፈሩም፡ተወ፤
31፤ያም፡እስከ፡ዘለዓለም፡ለልጅ፡ልጅ፡ጽድቅ፡ኾኖ፡ተቈጠረለት።
32-33፤በክርክር፡ውሃ፡ዘንድም፡አስቈጡት፥መንፈሱን፡አስመርረዋታልና፤ስለ፡እነርሱም፡ሙሴ፡ተበሳጨ፤በከንፈሮ ቹም፡በስንፍና፡ተናገረ።
34፤እግዚአብሔርም፡እንዳላቸው፡አሕዛብን፡አላጠፉም፤
35፤ከአሕዛብም፡ጋራ፡ተደባለቁ፥ሥራቸውንም፡ተማሩ።
36፤ለጣዖቶቻቸውም፡ተገዙ፥ወጥመድም፡ኾኑባቸው።
37፤ወንዶች፡ልጆቻቸውንና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡ለአጋንንት፡ሠዉ፤
38፤የወንዶች፡ልጆቻቸውንና፡የሴቶች፡ልጆቻችን፡ደም፥ለከነዓን፡ጣዖቶች፡የሠዉአቸውን፡ንጹሕ፡ደም፡አፈሰሱ፥ ምድርም፡በደም፡ረከሰች።
39፤በሥራቸው፡ረከሱ፥በማድረጋቸውም፡አመነዘሩ።
40፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ነደደ፥ርስቱንም፡ተጸየፈ።
41፤ወደ፡አሕዛብም፡እጅ፡አሳለፋቸው፥የሚጠሏቸውም፡ገዟቸው።
42፤ጠላቶቻቸውም፡ግፍ፡አደረጉባቸው፥ከእጃቸውም፡በታች፡ተዋረዱ።
43፤ብዙ፡ጊዜ፡አዳናቸው፤ነገር፡ግን፥በምክራቸው፡አስመረሩት፥በኀጢአታቸውም፡ተዋረዱ።
44፤ርሱ፡ግን፡ጩኸታቸውን፡በሰማ፡ጊዜ፡ጭንቃቸውን፡ተመለከተ፤
45፤ለእነርሱም፡ኪዳኑን፡ዐሰበ፥እንደ፡ምሕረቱም፡ብዛት፡ተጸጸተ።
46፤በማረኳቸውም፡ዅሉ፡ፊት፡ሞገስን፡ሰጣቸው።
47፤አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥አድነን፤ቅዱስ፡ስምኽን፡እናመሰግን፡ዘንድ፥በምስጋናኽም፡እንመካ፡ዘንድ ፥ከአሕዛብ፡መካከል፡ሰብስበን።
48፤ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረክ፡ሕዝብም፡ዅሉ፡አሜን፡ይበል።ሃ ሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡106፡(107)።______________
ሃሌ፡ሉያ።
1፤ቸር፡ነውና፥ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፤
2፤እግዚአብሔር፡ያዳናቸው፥ከጠላቶች፡እጅ፡ያዳናቸው፡ይናገሩ።
3፤ከምሥራቅና፡ከምዕራብ፥ከሰሜንና፡ከባሕር፥ከየአገሩ፡ሰበሰባቸው።
4፤ውሃ፡በሌለበት፡ምድረ፡በዳ፡ተቅበዘበዙ፤የሚኖሩበትንም፡ከተማ፡መንገድ፡አላገኙም።
5፤ተራቡ፡ተጠሙም፥ነፍሳቸውም፡በውስጣቸው፡አለቀች።
6፤በተጨነቁ፡ጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፥ከመከራቸውም፡አዳናቸው፤
7፤ወደሚኖሩበት፡ከተማ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡የቀና፡መንገድን፡መራቸው።
8፤ለሰው፡ልጆች፡ስላደረገው፡ተኣምራት፡ስለ፡ምሕረቱም፡እግዚአብሔርን፡ያመስግኑ፤
9፤የተራበችን፡ነፍስ፡አጥግቧልና፥የተራቈተችንም፡ነፍስ፡በበረከት፡ሞልቷልና።
10፤በጨለማ፡በሞትም፡ጥላ፡የተቀመጡ፥በችግር፡በብረትም፡የታሰሩ፤
11፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስለ፡ዐመፁ፥የልዑልንም፡ምክር፡ስለ፡ናቁ፥
12፤ልባቸው፡በድካም፡ተዋረደ፤ታመሙ፡የሚረዳቸውም፡ዐጡ።
13፤በተጨነቁ፡ጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፥በመከራቸውም፡አዳናቸው።
14፤ከጨለማና፡ከሞት፡ጥላ፡አወጣቸው፥እስራታቸውንም፡ሰበረ።
15፤ለሰው፡ልጆች፡ስላደረገው፡ተኣምራት፡ስለ፡ምሕረቱም፡እግዚአብሔርን፡ያመስግኑ፤
16፤የናሱን፡ደጆች፡ሰብሯልና፥የብረቱንም፡መወርወሪያ፡ቈርጧልና።
17፤ስለ፡ዐመፃቸው፡ሰነፉ፥ስለ፡ኀጢአታቸውም፡ተቸገሩ።
18፤ሰውነታቸው፡መብልን፡ዅሉ፡ተጸየፈች፥ወደሞትም፡ደጆች፡ቀረቡ።
19፤በተጨነቁ፡ጊዜም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፥ከመከራቸውም፡አዳናቸው።
20፤ቃሉን፡ላከ፡ፈወሳቸውም፥ከጥፋታቸውም፡አዳናቸው።
21፤ለሰው፡ልጆች፡ስላደረገው፡ተኣምራት፡ስለ፡ምሕረቱም፡እግዚአብሔርን፡ያመሰግኑ፤
22፤የምስጋና፡መሥዋዕትንም፡ይሠዉለት፥በእልልታም፡ሥራውን፡ይንገሩ።
23፤በመርከቦች፡ወደ፡ባሕር፡የሚወርዱ፥በታላቅ፡ውሃ፡ሥራቸውን፡የሚሠሩ፥
24፤እነርሱ፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፥በጥልቅም፡ያለችውን፡ድንቁን፡አዩ።
25፤ተናገረ፥ዐውሎ፡ነፋስም፡ተነሣ፥ሞገድም፡ከፍ፡ከፍ፡አለ።
26፤ወደ፡ሰማይ፡ይወጣሉ፡ወደ፡ጥልቅም፡ይወርዳሉ፤ነፍሳቸውም፡በመከራ፡ቀለጠች።
27፤ደነገጡ፡እንደ፡ስካርም፡ተንገደገዱ፥ጥበባቸውም፡ዅሉ፡ተዋጠች።
28፤በተጨነቁ፡ጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፥ከመከራቸውም፡አዳናቸው።
29፤ዐውሎንም፡ጸጥ፡አደረገ፥ሞገዱም፡ዝም፡አለ።
30፤ዝም፡ብሏልና፥ደስ፡አላቸው፤ወደ፡ፈለጉትም፡ወደብ፡መራቸው።
31፤ለሰው፡ልጆች፡ስላደረገው፡ተኣምራት፡ስለ፡ምሕረቱም፡እግዚአብሔርን፡ያመስግኑ።
32፤በአሕዛብ፡ጉባኤ፡ከፍ፡ከፍ፡ያድርጉት፥በሽማግሌዎችም፡ሸንጎ፡ያመስግኑት።
33፤ወንዞችን፡ምድረ፡በዳ፥የውሃውንም፡ምንጮች፡ደረቅ፡አደረጋቸው፤
34፤ከተቀመጡባት፡ክፋት፡የተነሣ፡ፍሬያማዋን፡ምድር፡ጨው፡አደረጋት።
35፤ምድረ፡በዳን፡ለውሃ፡መቆሚያ፥ደረቁንም፡ምድር፡የውሃ፡ምንጮች፡አደረገ።
36፤በዚያም፡ራብተኛዎችን፡አስቀመጠ፥የሚኖርባትንም፡ከተማ፡ሠሩ።
37፤ዕርሻዎችንም፡ዘሩ፡ወይኖችንም፡ተከሉ፥የእኽልንም፡ሰብል፡አደረጉ።
38፤ባረካቸውም፡እጅግም፡በዙ፤እንስሳዎቻቸውንም፡አላሳነሰባቸውም።
39፤እነርሱ፡በችግር፡በክፋት፡በጭንቀት፡ተዋረዱ፡እያነሱም፡ኼዱ፤
40፤በአለቶችም፡ላይ፡ኀሳርን፡አፈሰሰ፥መንገድም፡በሌለበት፡በምድረ፡በዳ፡አሳታቸው።
41፤ችግረኛንም፡ከችግሩ፡ረዳው፤እንደ፡በጎች፡መንጋ፡ወገን፡አደረገው።
42፤ቅኖች፡ያያሉ፥ደስም፡ይላቸዋል፤ኀጢአትም፡ዅሉ፡አፏን፡ትዘጋለች።
43፤ጥበበኛ፡የኾነና፡ይህን፡የሚጠብቅ፡ማን፡ነው፧ርሱ፡የእግዚአብሔርን፡ምሕረት፡ያስተውላል።
_______________መዝሙር፡107፡(108)።______________
የዳዊት፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤ልቤ፡ጽኑ፡ነው፥አቤቱ፥ልቤ፡ጽኑ፡ነው፤እቀኛለኹ፡በክብሬም፡እዘምራለኹ።
2፤በገና፡ሆይ፥ተነሥ፥መሰንቆም፤እኔም፡ማልጄ፡እነሣለኹ።
3፤አቤቱ፥በአሕዛብ፡መካከል፡አመሰግንኻለኹ፥በወገኖችም፡መካከል፡እዘምርልኻለኹ፤
4፤ምሕረትኽ፡በሰማይ፡ላይ፡ታላቅ፡ናትና፥እውነትኽም፡እስከ፡ደመናት፡ድረስ፡ነውና።
5፤አቤቱ፥በሰማያት፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡በል፥ክብርኽም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ትኹን።
6፤ወዳጆችኽ፡ይድኑ፡ዘንድ፤በቀኝኽ፡አድን፡አድምጠኝም።
7፤እግዚአብሔር፡በቅድስናው፡ተናገረ፦ደስ፡ይለኛል፥ሴኬምንም፡እካፈላለኹ፥የሱኮትንም፡ሸለቆ፡እሰፍራለኹ።
8፤ገለዓድ፡የእኔ፡ነው፡ምናሴም፡የእኔ፡ነው፤ኤፍሬም፡የራሴ፡መጠጊያ፡ነው።ይሁዳ፡ንጉሤ፡ነው።
9፤ሞዐብ፡መታጠቢያዬ፡ነው፥በኤዶምያስ፡ላይም፡ጫማዬን፡እዘረጋለኹ፤ፍልስጥኤም፡ይገዙልኛል።
10፤ወደ፡ጽኑ፡ከተማ፡ማን፡ይወስደኛል፧ማንስ፡እስከ፡ኤዶምያስ፡ይመራኛል፧
11፤አቤቱ፥የጣልኸኝ፡አንተ፡አይደለኽምን፧አምላክ፡ሆይ፥ከሰራዊታችን፡ጋራ፡አትወጣም።
12፤በመከራችን፡ረድኤትን፡ስጠን፤የሰውም፡ማዳን፡ከንቱ፡ነው።
13፤በእግዚአብሔር፡ኀይልን፡እናደርጋለን፤ርሱም፡የሚያስጨንቁንን፡ያዋርዳቸዋል።
_______________መዝሙር፡108፡(109)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አምላክ፡ሆይ፥ምስጋናዬን፡ዝም፡አትበል፥
2፤የኀጢአተኛ፡አፍና፡የተንኰለኛ፡አፍ፡በላዬ፡ተላቀ፟ውብኛልና፤በሽንገላ፡አንደበትም፡በላዬ፡ተናገሩ፤
3፤በጥል፡ቃል፡ከበቡኝ፥በከንቱም፡ተሰለፉብኝ።
4፤በወደድዃቸው፡ፋንታ፡አጣሉኝ፥እኔ፡ግን፡እጸልያለኹ።
5፤በመልካም፡ፋንታ፡ክፉን፡በወደድዃቸውም፡ፋንታ፡ጠላትነትን፡መለሱልኝ።
6፤በላዩ፡ኀጢአተኛን፡ሹም፤ሰይጣንም፡በቀኙ፡ይቁም።
7፤በተሟገተም፡ጊዜ፡ተረቶ፟፡ይውጣ፤ጸሎቱም፡ኀጢአት፡ትኹንበት።
8፤ዘመኖቹም፡ጥቂት፡ይኹኑ፤ሹመቱንም፡ሌላ፡ይውሰድ።
9፤ልጆቹም፡ድኻ፡አደግ፡ይኹኑ፥ሚስቱም፡መበለት፡ትኹን።
10፤ልጆቹም፡ተናውጠው፡ይቅበዝበዙ፡ይለምኑም፥ከስፍራቸውም፡ይባረሩ።
11፤ባለዕዳም፡ያለውን፡ዅሉ፡ይበርብረው፥እንግዳዎችም፡ድካሙን፡ዅሉ፡ይበዝብዙት።
12፤የሚያግዘውንም፡አያግኝ።ለድኻ፡አደግ፡ልጆቹም፡የሚራራ፡አይኑር።
13፤ልጆቹ፡ይጥፉ፤ባንድ፡ትውልድ፡ስሙ፡ይደምሰስ።
14፤የአባቶቹ፡ኀጢአት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ትታሰብ፤የእናቱም፡ኀጢአት፡አትደምሰስ።
15፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዅልጊዜ፡ይኑሩ፤መታሰቢያቸው፡ከምድር፡ይጥፋ።
16፤ምሕረትን፡ያደርግ፡ዘንድ፡አላሰበምና፡ችግረኛንና፡ምስኪንን፡ልቡ፡የተሰበረውንም፡ሰው፡ይገድል፡ዘንድ፡ አሳደደ።
17፤መርገምን፡ወደደ፡ወደ፡ርሱም፡መጣች፤በረከትንም፡አልመረጠም፡ከርሱም፡ራቀች።
18፤መርገምን፡እንደ፡ልብስ፡ለበሳት፥እንደ፡ውሃም፡ወደ፡አንዠቱ፥እንደ፡ቅባትም፡ወደ፡ዐጥንቱ፡ገባች።
19፤እንደሚለብሰው፡ልብስ።ዅልጊዜም፡እንደሚታጠቀው፡ትጥቅ፡ይኹነው።
20፤ይህ፡ሥራ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በሚያጣሉኝ፡በነፍሴም፡ላይ፡ክፉን፡በሚናገሩ፡ነው።
21፤አንተ፡ግን፡አቤቱ፡ጌታዬ፥ስለ፡ስምኽ፡ምሕረትኽን፡በእኔ፡ላይ፡አድርግ፤ምሕረትኽ፡መልካም፡ናትና፥አድነ ኝ።
22፤እኔ፡ችግረኛ፡ምስኪንም፡ነኝና፥ልቤም፡በውስጤ፡ደነገጠብኝ።
23፤እንዳለፈ፡ጥላ፡አለቅኹ፥እንደ፡አንበጣም፡ረገፍኹ።
24፤ጕልበቶቼ፡በጾም፡ደከሙ፤ሥጋዬም፡ቅቤ፡በማጣት፡ከሳ።
25፤እኔም፡በእነርሱ፡ዘንድ፡ለነውር፡ኾንኹ፤ባዩኝ፡ጊዜ፡ራሳቸውን፡ነቀነቁ።
26፤አቤቱ፡አምላኬ፥ርዳኝ፥እንደ፡ምሕረትኽም፡አድነኝ።
27፤አቤቱ፥እጅኽ፡ይህች፡እንደ፡ኾነች፥አንተም፡ይህችን፡እንዳደረግኽ፡ይወቁ።
28፤እነርሱ፡ይራገማሉ፡አንተ፡ግን፡ባርክ፤በእኔ፡ላይ፡የሚነሡ፡ይፈሩ፥ባሪያኽ፡ግን፡ደስ፡ይበለው።
29፤የሚያጣሉኝ፡ዕፍረትን፡ይልበሱ፤ዕፍረታቸውን፡እንደ፡መጐናጸፊያ፡ይልበሷት።
30፤እግዚአብሔርን፡በአፌ፡እጅግ፡አመሰግነዋለኹ።በብዙዎችም፡መካከል፡አከብረዋለኹ፤
31፤ነፍሱን፡ከሚያሳድዷት፡ያድን፡ዘንድ፡በድኻ፡ቀኝ፡ቆሟልና።
_______________መዝሙር፡109፡(110)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ጌታዬን፦ጠላቶችኽን፡ለእግርኽ፡መቀመጫ፡እስካደርግልኽ፡ድረስ፡በቀኜ፡ተቀመጥ፡አለው።
2፤እግዚአብሔር፡የኀይልን፡በትር፡ከጽዮን፡ይልክልኻል፤በጠላቶችኽም፡መካከል፡ግዛ።
3፤ከአንተ፡ጋራ፡ቀድሞ፡በኀይልኽ፡ቀን፥በቅዱሳን፡ብርሃን፥ከአጥቢያ፡ኮከብ፡አስቀድሞ፡ከሆድ፡ወለድኹኽ።
4፤እንደ፡መልከ፡ጼዴቅ፡ሥርዐት፡አንተ፡ለዘለዓለም፡ካህን፡ነኽ፡ብሎ፥እግዚአብሔር፡ማለ፡አይጸጸትም።
5፤እግዚአብሔር፡በቀኝኽ፡ነገሥታትን፡በቍጣው፡ቀን፡ይቀጠቅጣቸዋል።
6፤በአሕዛብ፡መካከል፡ይፈርዳል፥ሬሳዎችንም፡ያበዛል፤በሰፊ፡ምድር፡ላይ፡ራሶችን፡ይቀጠቅጣል።
7፤በመንገድ፡ከፈሳሽ፡ውሃ፡ይጠጣል፤ስለዚህ፥ራስ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።
_______________መዝሙር፡110፡(111)።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ።አቤቱ፥በቅኖች፡ሸንጎ፡በጉባኤም፡በፍጹም፡ልቤ፡አመሰግንኻለኹ።
2፤የእግዚአብሔር፡ሥራ፡ታላቅ፡ናት፥ደስ፡በሚሠኙባት፡ዅሉ፡ዘንድ፡የተፈለገች፡ናት።
3፤ሥራው፡ምስጋናና፡ግርማ፡ነው፤ጽድቁም፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።
4፤ለተኣምራቱ፡መታሰቢያን፡አደረገ፤እግዚአብሔር፡መሓሪና፡ይቅር፡ባይ፡ነው።
5፤ለሚፈሩት፡ምግብን፡ሰጣቸው፤ኪዳኑንም፡ለዘለዓለም፡ያስባል።
6፤የአሕዛብን፡ርስት፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፡ለሕዝቡ፡የሥራውን፡ብርታት፡አሳየ።
7፤የእጆቹ፡ሥራ፡እውነትና፡ፍርድ፡ነው፤ትእዛዙም፡ዅሉ፡የታመነ፡ነው፥
8፤ለዘለዓለምም፡የጸና፡ነው፥በእውነትና፡በቅንም፡የተሠራ፡ነው።
9፤መድኀኒትንም፡ለሕዝቡ፡ሰደደ፥ኪዳኑንም፡ለዘለዓለም፡አዘዘ፤ስሙ፡የተቀደሰና፡የተፈራ፡ነው።
10፤የጥበብ፡መዠመሪያ፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ነው፥ለሚያደርጓትም፡ዅሉ፡ደኅና፡ማስተዋል፡አላቸው፤ምስጋና ውም፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።
_______________መዝሙር፡111፡(112)።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ።እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፥ትእዛዙንም፡እጅግ፡የሚወድ፟፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።
2፤ዘሩ፡በምድር፡ላይ፡ኀያል፡ይኾናል፤የቅኖች፡ትውልድ፡ትባረካለች።
3፤ክብርና፡ባለጠግነት፡በቤቱ፡ነው፥ጽድቁም፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።
4፤ለቅኖች፡ብርሃን፡በጨለማ፡ወጣ፤መሓሪና፡ይቅር፡ባይ፡ጻድቅም፡ነው።
5፤ቸር፡ሰው፡ይራራል፡ያበድራልም፥በፍርድም፡ነገሩን፡ይፈጽማል።
6፤ለዘለዓለም፡አይናወጥም፤የጻድቅ፡መታሰቢያ፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።
7፤ከክፉ፡ነገር፡አይፈራም፤በእግዚአብሔር፡ለመታመን፡ልቡ፡የጸና፡ነው።
8፤በጠላቶቹ፡ላይ፡እስኪያይ፡ድረስ፡ልቡ፡ጽኑ፡ነው፥አይፈራም።
9፤በተነ፡ለችግረኛዎችም፡ሰጠ፤ጽድቁ፡ለዘለዓለም፡ዓለም፡ይኖራል፤ቀንዱ፡በክብር፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።
10፤ኀጢአተኛም፡አይቶ፡ይቈጣል፥ጥርሱንም፡ያፋጫል፥ይቀልጣልም፤የኀጢአተኛዎችም፡ምኞት፡ትጠፋለች።
_______________መዝሙር፡112፡(113)።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ።የእግዚአብሔር፡ባሪያዎች፡ሆይ፥አመስግኑት፥የእግዚአብሔርንም፡ስም፡አመስግኑ።
2፤ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡የእግዚአብሔር፡ስም፡ቡሩክ፡ይኹን።
3፤ከፀሓይ፡መውጫ፡ዠምሮ፡እስከ፡መግቢያው፡ድረስ፡የእግዚአብሔር፡ስም፡ይመስገን።
4፤እግዚአብሔር፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡ከፍተኛ፡ነው፥ክብሩም፡ከሰማያት፡በላይ፡ነው።
5፤እንደ፡አምላካችን፡እንደ፡እግዚአብሔር፡ማን፡ነው፧በላይ፡የሚኖር፤
6፤በሰማይና፡በምድር፡የተዋረዱትን፡የሚያይ፤
7-8፤ከአለቃዎች፡ጋራ፡ከሕዝቡም፡አለቃዎች፡ጋራ፡ያኖረው፡ዘንድ፡ችግረኛን፡ከመሬት፡የሚያነሣ፥ምስኪኑንም፡ከ ፋንድያ፡ከፍ፡ከፍ፡የሚያደርግ፤
9፤መካኒቱን፡በቤት፡የሚያኖራት፥ደስ፡የተሠኘችም፡የልጆች፡እናት፡የሚያደርጋት።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡113፡(114)።______________
ሃሌ፡ሉያ።
1፤እስራኤል፡ከግብጽ፥የያዕቆብም፡ቤት፡ከእንግዳ፡ሕዝብ፡በወጣ፡ጊዜ፥
2፤ይሁዳ፡መቅደሱ፥እስራኤልም፡ግዛቱ፡ኾነ።
3፤ባሕር፡አየች፡ሸሸችም፥ዮርዳኖስም፡ወደ፡ዃላው፡ተመለሰ።
4፤ተራራዎች፡እንደ፡ኰርማዎች፥ኰረብታዎችም፡እንደ፡ጠቦቶች፡ዘለሉ።
5፤አንቺ፡ባሕር፡የሸሸሽ፥አንቺም፡ዮርዳኖስ፡ወደ፡ዃላሽ፡የተመለሽ፟፥ምን፡ኾናችዃል፧
6፤እናንተም፡ተራራዎች፥እንደ፡ኰርማዎች፥ኰረብታዎችስ፥እንደ፡ጠቦቶች፡ለምን፡ዘለላችኹ፧
7፤ከያዕቆብ፡አምላክ፡ፊት፥ከጌታ፡ፊት፡ምድር፡ተናወጠች፤
8፤ድንጋዩን፡ወደውሃ፡መቆሚያ፥ጭንጫውንም፡ወደውሃ፡ምንጭ፡ከለወጠ።
_______________መዝሙር፡114፡(115)።______________
1፤ለእኛ፡አይደለም፥አቤቱ፥ለእኛ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ለስምኽ፡ስለ፡ምሕረትኽ፡ስለ፡እውነትኽም፡ምስጋናን ፡ስጥ።
2፤አሕዛብ፦አምላካቸው፡ወዴት፡ነው፧አይበሉ።
3፤አምላካችንስ፡በላይ፡በሰማይ፡ነው፤በሰማይም፡በምድርም፡የፈቀደውን፡ዅሉ፡አደረገ።
4፤የአሕዛብ፡ጣዖታቶች፡የወርቅና፡የብር፥የሰው፡እጅ፡ሥራ፡ናቸው።
5፤አፍ፡አላቸው፡አይናገሩምም፤ዐይን፡አላቸው፡አያዩምም፤
6፤ዦሮ፡አላቸው፡አይሰሙምም፤አፍንጫ፡አላቸው፡አያሸቱ፟ምም፤
7፤እጅ፡አላቸው፡አይዳሰሱምም፤እግር፡አላቸው፡አይኼዱምም፤በጕረሯቸውም፡አይናገሩም።
8፤የሚሠሯቸውም፡የሚያምኑባቸውም፡ዅሉ፡እንደ፡እነርሱ፡ይኹኑ።
9፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ታመኑ፤ረድኤታቸውና፡መታመኛቸው፡ርሱ፡ነው።
10፤የአሮን፡ቤት፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ታመኑ፡ረድኤታቸውና፡መታመኛቸው፡ርሱ፡ነው።
11፤እግዚአብሔርን፡የምትፈሩ፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ታመኑ፤ረድኤታቸውና፡መታመኛቸው፡ርሱ፡ነው።
12፤እግዚአብሔር፡ዐሰበን፡ይባርከንማል፤የእስራኤልን፡ቤት፡ይባረካል፥የአሮንንም፡ቤት፡ይባረካል።
13፤እግዚአብሔርን፡የሚፈሩትን፥ትንንሾችንና፡ትልልቆችን፡ይባርካል።
14፤እግዚአብሔር፡በላያችኹ፥በላያችኹና፡በልጆቻችኹ፡ላይ፡ይጨምር።
15፤እናንተ፡ሰማይንና፡ምድርን፡ለሠራ፡ለእግዚአብሔር፡የተባረካችኹ፡ናችኹ።
16፤የሰማያት፡ሰማይ፡ለእግዚአብሔር፡ነው፤ምድርን፡ግን፡ለሰው፡ልጆች፡ሰጣት።
17፤አቤቱ፥ሙታን፡የሚያመሰግኑኽ፡አይደሉም፡ወደ፡ሲኦልም፡የሚወርዱ፡ዅሉ፤
18፤እኛ፡ሕያዋን፡ግን፡ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡እግዚአብሔርን፡እንባርካለን።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡115፡(116)።______________
ሃሌ፡ሉያ።
1፤እግዚአብሔር፡የልመናዬን፡ድምፅ፡ሰምቷልና፥ወደድኹት።
2፤ዦሮውን፡ወደ፡እኔ፡አዘንብሏልና፥በዘመኔ፡ዅሉ፡እጠራዋለኹ።
3፤የሞት፡ጣር፡ያዘኝ፥የሲኦልም፡ሕማም፡አገኘኝ፤ጭንቀትንና፡መከራን፡አገኘኹ።
4፤የእግዚአብሔርንም፡ስም፡ጠራኹ፦አቤቱ፥ነፍሴን፡አድናት።
5፤እግዚአብሔር፡መሓሪና፡ጻድቅ፡ነው፥አምላካችንም፡ይቅር፡ባይ፡ነው።
6፤እግዚአብሔር፡ሕፃናትን፡ይጠብቃል፤ተቸገርኹ፡ርሱም፡አዳነኝ።
7፤ነፍሴ፡ሆይ፥ወደ፡ዕረፍትሽ፡ተመለሺ፥እግዚአብሔር፡መልካም፡አድርጎልሻልና፤
8፤ነፍሴን፡ከሞት፥ዐይኔንም፡ከእንባ፥እግሬንም፡ከመሰናከል፡አድኗልና።
9፤በሕያዋን፡አገር፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እኼዳለኹ።
10፤አመንኹ፡ስለዚህም፡ተናገርኹ፤እኔም፡እጅግ፡ተቸገርኹ።
11፤እኔም፡ከድንጋጤዬ፡የተነሣ፦ሰው፡ዅሉ፡ሐሰተኛ፡ነው፡አልኹ።
12፤ስላደረገልኝ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ምንን፡እመልሳለኹ፧
13፤የመድኀኒትን፡ጽዋ፡እቀበላለኹ፥የእግዚአብሔርንም፡ስም፡እጠራለኹ።
14፤በሕዝቡ፡ዅሉ፡ፊት፡ስእለቴን፡ለእግዚአብሔር፡እፈጽማለኹ።
15፤የቅዱሳኑ፡ሞት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡የከበረ፡ነው።
16፤አቤቱ፥እኔ፡ባሪያኽ፡ነኝ፥ባሪያኽ፡ነኝ፥የሴት፡ባሪያኽም፡ልጅ፡ነኝ፤ሰንሰለቴን፡ሰበርኽ።
17፤ለአንተ፡የምስጋና፡መሥዋዕትን፡እሠዋለኹ፥የእግዚአብሔርንም፡ስም፡እጠራለኹ።
18፤በሕዝቡ፡ዅሉ፡ፊት፡ስእለቴን፡ለእግዚአብሔር፡እፈጽማለኹ፥
19፤በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፥ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥በመካከልሽም።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡116፡(117)።______________
ሃሌ፡ሉያ።
1፤አሕዛብ፡ዅላችኹ፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑት፥ወገኖችም፡ዅሉ፡ያመስግኑት፤
2፤ምሕረቱ፡በእኛ፡ላይ፡ጸንታለችና፤የእግዚአብሔርም፡እውነት፡ለዘለዓለም፡ትኖራለች።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡117፡(118)።______________
ሃሌ፡ሉያ።
1፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥ቸር፡ነውና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ናትና።
2፤ቸር፡እንደ፡ኾነ፥ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡እንደ፡ኾነች፡የእስራኤል፡ቤት፡አኹን፡ይንገሩ።
3፤ቸር፡እንደ፡ኾነ፥ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡እንደ፡ኾነች፡የአሮን፡ቤት፡አኹን፡ይንገሩ።
4፤ቸር፡እንደ፡ኾነ፥ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡እንደ፡ኾነች፡እግዚአብሔርን፡የሚፈሩ፡ዅሉ፡አኹን፡ይንገሩ።
5፤በተጨነቅኹ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡ጠራኹት፤ሰማኝ፡አሰፋልኝም።
6፤እግዚአብሔር፡ረዳቴ፡ነው፥አልፈራም፡ሰው፡ምን፡ያደርገኛል፧
7፤እግዚአብሔር፡ረዳቴ፡ነው፥እኔም፡በጠላቶቼ፡ላይ፡አያለኹ።
8፤በሰው፡ከመታመን፡ይልቅ፡በእግዚአብሔር፡መታመን፡ይሻላል።
9፤በገዢዎች፡ተስፋ፡ከማድረግ፡ይልቅ፡በእግዚአብሔር፡ተስፋ፡ማድረግ፡ይሻላል።
10፤አሕዛብ፡ዅሉ፡ከበቡኝ፥በእግዚአብሔርም፡ስም፡አሸነፍዃቸው፤
11፤መክበቡንስ፡ከበቡኝ፥በእግዚአብሔርም፡ስም፡አሸነፍዃቸው፤
12፤ንብ፡ማርን፡እንዲከብ፟፡ከበቡኝ፥እሳትም፡በሾኽ፡ውስጥ፡እንዲነድ፟፡ነደዱ፥በእግዚአብሔርም፡ስም፡አሸነ ፍዃቸው።
13፤ገፋኸኝ፥ለመውደቅም፡ተንገዳገድኹ፤እግዚአብሔር፡ግን፡አገዘኝ።
14፤ኀይሌም፡ዝማሬዬም፡እግዚአብሔር፡ነው፥ርሱም፡መድኀኒት፡ኾነልኝ።
15፤የእልልታና፡የመድኀኒት፡ድምፅ፡በጻድቃን፡ድንኳን፡ነው፤የእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ኀይልን፡አደረገች።
16፤የእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረገችኝ፤የእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ኀይልን፡አደረገች።
17፤አልሞትም፡በሕይወት፡እኖራለኹ፡እንጂ፥የእግዚአብሔርንም፡ሥራ፡እናገራለኹ።
18፤መገሠጽስ፡እግዚአብሔር፡ገሠጸኝ፤ለሞት፡ግን፡አልሰጠኝም።
19፤የጽድቅን፡ደጆች፡ክፈቱልኝ፤ወደ፡እነርሱ፡ገብቼ፡እግዚአብሔርን፡አመሰግናለኹ።
20፤ይህች፡የእግዚአብሔር፡ደጅ፡ናት፤ወደ፡ርሷ፡ጻድቃን፡ይገባሉ።
21፤ሰምተኸኛልና፥መድኀኒትም፡ኾነኸኛልና፥አመሰግንኻለኹ።
22፤ግንበኛዎች፡የናቁት፡ድንጋይ፥ርሱ፡የማእዘን፡ራስ፡ኾነ፥
23፤ይህች፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ኾነች፥ለዐይናችንም፡ድንቅ፡ናት።
24፤እግዚአብሔር፡የሠራት፡ቀን፡ይህች፡ናት፤ሐሤትን፡እናድርግ፥በርሷም፡ደስ፡ይበለን።
25፤አቤቱ፥እባክኽ፥አኹን፡አድን፤አቤቱ፥እባክኽ፥አኹን፡አቅና።
26፤በእግዚአብሔር፡ስም፡የሚመጣ፡ቡሩክ፡ነው፤ከእግዚአብሔር፡ቤት፡መረቅናችኹ።
27፤እግዚአብሔር፡አምላክ፡ነው፥ለእኛም፡በራልን፤እስከመሠዊያው፡ቀንዶች፡ድረስ፡የበዓሉን፡መሥዋዕት፡በገመ ድ፡እሰሩት።
28፤አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፡አመሰግንኽማለኹ።አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፥ከፍ፡ከፍ፡አደርግኻለኹ፤ሰምተኸኛልና፥መድኀ ኒትም፡ኾነኸኛልና፥አመሰግንኻለኹ።
29፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥ቸር፡ነውና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ናትና።
_______________መዝሙር፡118፡(119)።______________
አሌፍ
1፤በመንገዳቸው፡ንጹሓን፡የኾኑ፥በእግዚአብሔርም፡ሕግ፡የሚኼዱ፡ምስጉኖች፡ናቸው።
2፤ምስክሩን፡የሚፈልጉ፥በፍጹም፡ልብ፡የሚሹት፡ምስጉኖች፡ናቸው፤
3፤ዐመፅንም፡አያደርጉም፥በመንገዶቹም፡ይኼዳሉ።
4፤ትእዛዛትኽን፡እጅግ፡እንጠብቅ፡ዘንድ፡አንተ፡አዘዝኽ።
5፤ሥርዐትኽን፡ለመጠበቅ፤መንገዶቼ፡ይቀኑ፡ዘንድ፡እወድ፟፡ነበር።
6፤ትእዛዝኽን፡ዅሉ፡ስመለከት፡በዚያን፡ጊዜ፡አላፍርም።
7፤አቤቱ፥የጽድቅኽን፡ፍርድ፡ስማር፡በቅን፡ልብ፡አመሰግንኻለኹ።
8፤ሥርዐትኽን፡እጠብቃለኹ፤በፍጹም፡አትጣለኝ።
ቤት
9፤ጕልማሳ፡መንገዱን፡በምን፡ያነጻል፧ቃልኽን፡በመጠበቅ፡ነው።
10፤በፍጹም፡ልቤ፡ፈለግኹኽ፥ከትእዛዝኽ፡አታርቀኝ።
11፤አንተ፡እንዳልበድል፥ቃልኽን፡በልቤ፡ሰወርኹ።
12፤አቤቱ፥አንተ፡ቡሩክ፡ነኽ፤ሥርዐትኽን፡አስተምረኝ።
13፤የአፍኽን፡ፍርድ፡ዅሉ፡በከንፈሬ፡ነገርኹ።
14፤እንደ፡ብልጥግና፡ዅሉ፡በምስክርኽ፡መንገድ፡ደስ፡አለኝ።
15፤ትእዛዝኽን፡አሰላስላለኹ፥መንገድኽንም፡እፈልጋለኹ።
16፤በትእዛዝኽ፡ደስ፡ይለኛል፤ቃልኽንም፡አልረሳም።
ጋሜል
17፤ለባሪያኽ፡መልካም፡አድርግ፡ሕያው፡እንድኾን፥ቃልኽንም፡እንድጠብቅ።
18፤ዐይኖቼን፡ክፈት፥ከሕግኽም፡ተኣምራትኽን፡አያለኹ።
19፤እኔ፡በምድር፡እንግዳ፡ነኝ፤ትእዛዛትኽን፡ከእኔ፡አትሰውር።
20፤ነፍሴ፡ዅልጊዜ፡ፍርድኽን፡እጅግ፡ናፈቀች።
21፤ከትእዛዛትኽ፡የሳቱትን፡ትዕቢተኛዎችንና፡ርጉማንን፡ዘለፍኽ።
22፤ምስክርኽን፡ፈልጌያለኹና፥ስድብንና፡ነውርን፡ከእኔ፡አርቅ።
23፤አለቃዎች፡ደግሞ፡ተቀምጠው፡እኔን፡ዐሙኝ፤ባሪያኽ፡ግን፡ሕግኽን፡ያሰላስል፡ነበር።
24፤ምስክርኽም፡ተድላዬ፡ነው፥ሥርዐትኽም፡መካሪዬ፡ነው።
ዳሌጥ
25፤ነፍሴ፡ወደ፡ምድር፡ተጠጋች፤እንደ፡ቃልኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
26፤መንገድኽን፡ነገርኹ፡ሰማኸኝም፤ሥርዐትኽን፡አስተምረኝ።
27፤የሥርዐትኽን፡መንገድ፡እንዳስተውል፡አድርገኝ፥ተኣምራትኽንም፡አሰላስላለኹ።
28፤ከሐዘን፡የተነሣ፡ነፍሴ፡አንቀላፋች፤በቃልኽ፡አጠንክረኝ።
29፤የዐመፅን፡መንገድ፡ከእኔ፡አርቅ፥በሕግኽም፡ማረኝ፤
30፤የእውነትኽን፡መንገድ፡መረጥኹ፥ፍርድኽንም፡አልረሳኹም።
31፤አቤቱ፥ምስክርኽን፡ተጠጋኹ፤አታሳፍረኝ።
32፤ልቤን፡ባሰፋኸው፡ጊዜ፥በትእዛዝኽ፡መንገድ፡ሮጥኹ።

33፤አቤቱ፥የሥርዐትኽን፡መንገድ፡አስተምረኝ፥ዅልጊዜም፡እፈልገዋለኹ።
34፤እንዳስተውል፡አድርገኝ፥ሕግኽንም፡እፈልጋለኹ፤በፍጹም፡ልቤም፡እጠብቀዋለኹ።
35፤ርሷን፡ወድጃለኹና፡የትእዛዝኽን፡መንገድ፡ምራኝ።
36፤ልቤን፡ወደ፡ምስክርኽ፡አዘንብል፥ወደ፡ሥሥትም፡አይኹን።
37፤ከንቱ፡ነገርን፡እንዳያዩ፡ዐይኖቼን፡መልስ፤በመንገድኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
38፤እንዲፈራኽ፡ባሪያኽን፡በቃልኽ፡አጽና።
39፤ፍርድኽ፡መልካም፡ናትና፥የተጠራጠርኹትን፡ስድብ፡ከእኔ፡አርቅ።
40፤እንሆ፥ትእዛዝኽን፡ናፈቅኹ፤በጽድቅኽ፡ሕያው፡አድርገኝ
ዋው
41፤አቤቱ፥እንደ፡ቃልኽ፥ምሕረትኽና፡መድኀኒትኽ፡ይምጡልኝ።
42፤በቃልኽ፡ታምኛለኹና፡ለሚሰድቡኝ፡በነገር፡እመልስላቸዋለኹ።
43፤በፍርድኽም፡ታምኛለኹና፡የእውነትን፡ቃል፡ከአፌ፡ፈጽመኽ፡አታርቅ።
44፤ለዘለዓለም፡ዓለም፡ዅልጊዜ፡ሕግኽን፡እጠብቃለኹ።
45፤ትእዛዛትኽንም፡ፈልጌያለኹና፡አስፍቼ፡እኼዳለኹ።
46፤በነገሥታት፡ፊት፡ምስክርኽን፡እናገራለኹ፥አላፍርምም፤
47፤እጅግም፡በወደድዃቸው፡በትእዛዛትኽ፡ደስ፡ይለኛል።
48፤እጆቼንም፡ወደ፡ወደድዃቸው፡ወደ፡ትእዛዛትኽ፡አነሣለኹ፤ሥርዐትኽንም፡አሰላስላለኹ።
ዛይ
49፤ለባሪያኽ፡ተስፋ፡ያስደረግኸውን፡ቃልኽን፡ዐስብ።
50፤ቃልኽ፡ሕያው፡አድርጎኛልና፥ይህች፡በመከራዬ፡ደስ፡አሠኘችኝ።
51፤ትዕቢተኛዎች፡እጅግ፡ዐመፁ፤እኔ፡ግን፡ከሕግኽ፡አልራቅኹም።
52፤ከጥንት፡የነበረውን፡ፍርድኽን፡ዐሰብኹ፥አቤቱ፥ተጽናናኹም።
53፤ሕግኽን፡ከተዉ፡ከኀጢአተኛዎች፡የተነሣ፡ሐዘን፡ያዘኝ።
54፤በእንግድነቴ፡አገር፡ሥርዐትኽ፡መዝሙር፡ኾነችኝ።
55፤አቤቱ፥በሌሊት፡ስምኽን፡ዐሰብኹ፥ሕግኽንም፡ጠበቅኹ።
56፤ትእዛዛትኽንም፡ፈልጌያለኹና፤ይህች፡ኾነችልኝ።
ሔት
57፤እግዚአብሔር፡ክፍሌ፡ነው፤ሕግኽን፡እጠብቃለኹ፡አልኹ።
58፤በፍጹም፡ልቤ፡ወደ፡ፊትኽ፡ተማለልኹ፤እንደ፡ቃልኽ፡ማረኝ።
59፤ስለ፡መንገዶችኽ፡ዐሰብኹ፥እግሬንም፡ወደ፡ምስክሮችኽ፡መለስኹ።
60፤ትእዛዝኽን፡ለመጠበቅ፡ጨከንኹ፡አልዘገየኹምም።
61፤የኃጥኣን፡ገመዶች፡ተተበተቡብኝ፤ሕግኽን፡ግን፡አልረሳኹም።
62፤ስለጽድቅኽ፡ፍርድ፥በእኩለ፡ሌሊት፡አመሰግንኽ፡ዘንድ፡እነሣለኹ።
63፤እኔ፡ለሚፈሩኽ፡ዅሉ፥ትእዛዝኽንም፡ለሚጠብቁ፡ባልንጀራ፡ነኝ።
64፤አቤቱ፥ምሕረትኽ፡በምድር፡ዅሉ፡ሞላች፤ሥርዐትኽን፡አስተምረኝ።
ጤት
65፤አቤቱ፥እንደ፡ቃልኽ፡ለባሪያኽ፡መልካም፡አደረግኽ።
66፤በትእዛዛትኽ፡ታምኛለኹና፡መልካም፡ምክርና፡ዕውቀትን፡አስተምረኝ።
67፤እኔ፡ሳልጨነቅ፡ሳትኹ፤አኹን፡ግን፡ቃልኽን፡ጠበቅኹ።
68፤አቤቱ፥አንተ፡ቸር፡ነኽ፥በቸርነትኽም፡ሥርዐትኽን፡አስተምረኝ።
69፤የትዕቢተኛዎች፡ዐመፅ፡በላዬ፡በዛ፤እኔ፡ግን፡በፍጹም፡ልቤ፡ትእዛዛትኽን፡እፈልጋለኹ።
70፤ልባቸው፡እንደ፡ወተት፡ረጋ፤እኔ፡ግን፡በሕግኽ፡ደስ፡ይለኛል።
71፤ሥርዐትኽን፡እማር፡ዘንድ፡ያስጨነቅኸኝ፡መልካም፡ኾነልኝ።
72፤ከአእላፋት፡ወርቅና፡ብር፡ይልቅ፡የአፍኽ፡ሕግ፡ይሻለኛል።
ዮድ
73፤እጆችኽ፡ሠሩኝ፡አበጃጁኝም፤እንዳስተውል፡አድርገኝ፥ትእዛዛትኽንም፡እማራለኹ።
74፤በቃልኽ፡ታምኛለኹና፡የሚፈሩኽ፡እኔን፡አይተው፡ደስ፡ይላቸዋል።
75፤አቤቱ፥ፍርድኽ፡ጽድቅ፡እንደ፡ኾነች፥በእውነትኽም፡እንዳስቸገርኸኝ፡ዐወቅኹ።
76፤ምሕረትኽ፡ለመጽናናቴ፡ትኹነኝ፥እንደ፡ቃልኽም፡ለባሪያኽ፡ይኹነው።
77፤ሕግኽ፡ተድላዬ፡ናትና፥ቸርነትኽ፡ትምጣልኝ፥በሕይወትም፡ልኑር።
78፤ትዕቢተኛዎች፡በዐመፅ፡ጠመ፟ውብኛልና፥ይፈሩ፤እኔ፡ግን፡በትእዛዝኽ፡እጫወታለኹ።
79፤የሚፈሩኽና፡ምስክሮችኽን፡የሚያውቁ፡ወደ፡እኔ፡ይመለሱ።
80፤እንዳላፍር፡ልቤ፡በሥርዐትኽ፡የቀና፡ይኹን።
ካፍ
81፤ነፍሴ፡መድኀኒትኽን፡ናፈቀች፤በቃልኽም፡ታመንኹ።
82፤መቼ፡ታጽናናኛለኽ፡እያልኹ፡ዐይኖቼ፡ስለ፡ቃልኽ፡ፈዘዙ።
83፤በጢስ፡እንዳለ፡አቍማዳ፡ኾኛለኹና፤ሥርዐትኽን፡ግን፡አልረሳኹም።
84፤የባሪያኽ፡ዘመኖች፡ስንት፡ናቸው፧በሚያሳድዱኝስ፡ላይ፡መቼ፡ትፈርድልኛለኽ፧
85፤ኀጢአተኛዎች፡ጨዋታን፡ነገሩኝ፥አቤቱ፥እንደ፡ሕግኽ፡ግን፡አይደለም።
86፤ትእዛዛትኽ፡ዅሉ፡እውነት፡ናቸው፤በዐመፅ፡አሳ፟ደ፟ውኛል፤ርዳኝ።
87፤ከምድር፡ሊያጠፉኝ፡ጥቂት፡ቀርቷቸው፡ነበር፤እኔ፡ግን፡ትእዛዛትኽን፡አልተውኹም።
88፤እንደ፡ምሕረትኽ፡ሕያው፡አድርገኝ፤የአፍኽንም፡ምስክር፡እጠብቃለኹ።
ላሜድ
89፤አቤቱ፥ቃልኽ፡በሰማይ፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።
90፤እውነትኽ፡ለልጅ፡ልጅ፡ናት፤ምድርን፡መሠረትኻት፡ርሷም፡ትኖራለች።
91፤ዅሉም፡ባሪያዎችኽ፡ናቸውና፥ቀኑ፡በትእዛዝኽ፡ይኖራል።
92፤ሕግኽ፡ተድላዬ፡ባይኾን፥ቀድሞ፡በጕስቍልናዬ፡በጠፋኹ፡ነበር።
93፤በርሱ፡ሕያው፡አድርገኸኛልና፥ፍርድኽን፡ለዘለዓለም፡አልረሳም።
94፤እኔ፡የአንተ፡ነኝ፤ፍርድኽን፡ፈልጌያልኹና፡አድነኝ።
95፤ኀጢአተኛዎች፡ያጠፉኝ፡ዘንድ፡ጠበቁኝ፤ምስክርኽን፡ግን፡መረመርኹ።
96፤የሥራኽን፡ዅሉ፡ፍጻሜ፡አየኹ፤ትእዛዝኽ፡ግን፡እጅግ፡ሰፊ፡ነው።
ሜም
97፤አቤቱ፥ሕግኽን፡እንደ፡ምን፡እጅግ፡ወደድኹ! ቀኑን፡ዅሉ፡ርሱ፡ትዝታዬ፡ነው።
98፤ለዘለዓለም፡ለእኔ፡ነውና፥ትእዛዝኽ፡ከጠላቶቼ፡ይልቅ፡አስተዋይ፡አደረገኝ።
99፤ምስክርኽ፡ትዝታዬ፡ነውና፥ካስተማሩኝ፡ዅሉ፡ይልቅ፡አስተዋልኹ።
100፤ትእዛዝኽን፡ፈልጌያለኹና፡ከሽማግሌዎች፡ይልቅ፡አስተዋልኹ።
101፤ቃልኽን፡እጠብቅ፡ዘንድ፡ከክፉ፡መንገድ፡ዅሉ፡እግሬን፡ከለከልኹ።
102፤አስተምረኸኛልና፥ከፍርድኽ፡አልራቅኹም።
103፤ቃልኽ፡ለጕረሮዬ፡ጣፋጭ፡ነው፤ከማርና፡ከወለላ፡ይልቅ፡ለአፌ፡ጣፈጠኝ።
104፤ከትእዛዝኽ፡የተነሣ፡አስተዋልኹ፤ስለዚህ፥የሐሰትን፡መንገድ፡ጠላኹ።
ኖን
105፤ሕግኽ፡ለእግሬ፡መብራት፥ለመንገዴ፡ብርሃን፡ነው።
106፤የጽድቅኽን፡ፍርድ፡እጠብቅ፡ዘንድ፡ማልኹ፥አጸናኹም።
107፤እጅግ፡ተቸገርኹ፤አቤቱ፥እንደ፡ቃልኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
108፤አቤቱ፥ከአፌ፡የሚወጣውን፡ቃል፡ውደድ፥ፍርድኽንም፡አስተምረኝ።
109፤ነፍሴ፡ዅልጊዜ፡በእጅኽ፡ውስጥ፡ናት፤ሕግኽን፡ግን፡አልረሳኹም።
110፤ኀጢአተኛዎች፡ወጥመድን፡ዘረጉብኝ፤ከትእዛዝኽ፡ግን፡አልሳትኹም።
111፤የልቤ፡ደስታ፡ነውና፥ምስክርኽን፡ለዘለዓለም፡ወረስኹ።
112፤ለዘለዓለም፡ለፍጻሜውም፡ትእዛዝኽን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ልቤን፡አዘነበልኹ።
ሳምኬት
113፤ዐመፀኛዎችን፡ጠላኹ፥ሕግኽን፡ግን፡ወደድኹ።
114፤አንተ፡ረዳቴና፡መጠጊያዬ፡ነኽ፥በቃልኽም፡ተማመንኹ።
115፤እናንተ፡ኀጢአተኛዎች፥ከእኔ፡ራቁ፥የአምላኬንም፡ትእዛዝ፡ልፈልግ።
116፤እንደ፡ቃልኽ፡ደግፈኝ፥ሕያውም፡እኾናለኹ።ከተስፋዬም፡አልፈር።
117፤ርዳኝ፡እድናለኹም፥ዅልጊዜም፡ሥርዐትኽን፡እመረምራለኹ።
118፤ምኞታቸው፡ዐመፃ፡ነውና፥ከሥርዐትኽ፡የሚርቁትን፡ዅሉ፡አጐሳቈልኻቸው።
119፤የምድርን፡ኀጢአተኛዎች፡ዅሉ፡እንደ፡ርኵሰት፡አጠፋኻቸው፤ስለዚህ፥ምስክርኽን፡ወደድኹ።
120፤ሥጋዬ፡አንተን፡ከመፍራት፡የተነሣ፡ደነገጠ፤ከፍርድኽ፡የተነሣ፡ፈርቻለኹ።

121፤ፍርድንና፡ጽድቅን፡ሠራኹ፤ለሚያስጨንቁኝ፡አሳልፈኽ፡አትስጠኝ።
122፤ባሪያኽን፡በመልካም፡ጠብቀው፤ትዕቢተኛዎችም፡አይጋፉኝ።
123፤ዐይኖቼ፡ለማዳንኽ፥ለጽድቅኽም፡ቃል፡ፈዘዙ።
124፤ለባሪያኽ፡እንደ፡ምሕረትኽ፡አድርግ፥ሥርዐትኽንም፡አስተምረኝ።
125፤እኔ፡ባሪያኽ፡ነኝ፤እንዳስተውል፡አድርገኝ፥ምስክርኽንም፡ዐውቃለኹ።
126፤ለእግዚአብሔር፡የሥራ፡ጊዜ፡ነው፥ሕግኽንም፡ሻሩት።
127፤ስለዚህ፥ከወርቅና፡ከዕንቍ፡ይልቅ፡ትእዛዝኽን፡ወደድኹ።
128፤ስለዚህ፥ወደ፡ትእዛዝኽ፡ዅሉ፡አቀናኹ፥የዐመፅንም፡መንገድ፡ዅሉ፡ጠላኹ።

129፤ምስክሮችኽ፡ድንቆች፡ናቸው፤ስለዚህ፥ነፍሴ፡ፈለገቻቸው።
130፤የቃልኽ፡ፍቺ፡ያበራል፥ሕፃናትንም፡አስተዋዮች፡ያደርጋል።
131፤አፌን፡ከፈትኹ፥አለከለክኹም፤ወደ፡ትእዛዝኽ፡ናፍቄያለኹና።
132፤ስምኽን፡ለሚወዱ፡እንደምታደርገው፡ፍርድ፥ወደ፡እኔ፡ተመልከት፥ማረኝም።
133፤አካኼድን፡እንደ፡ቃልኽ፡አቅና፤ኀጢአትም፡ዅሉ፡አይግዛኝ።
134፤ከሰው፡ግፍ፡አድነኝ፤ትእዛዝኽንም፡እጠብቃለኹ።
135፤በባሪያኽ፡ላይ፡ፊትኽን፡አብራ፥ሥርዐትኽንም፡አሰተምረኝ።
136፤ሕግኽን፡አልጠበቅኹምና፡የውሃ፡ፈሳሽ፡ከዐይኖቼ፡ፈሰሰ።
ጻዴ
137፤አቤቱ፥አንተ፡ጻድቅ፡ነኽ፥ፍርድኽም፡ቅን፡ነው።
138፤ምስክርኽን፡በጽድቅ፡አዘዝኽ፥እጅግም፡ቅን፡ነው።
139፤ጠላቶቼ፡ቃልኽን፡ረስተዋልና፥የቤትኽ፡ቅንአት፡አቀለጠኝ።
140፤ቃልኽ፡እጅግ፡የነጠረ፡ነው፥ባሪያኽም፡ወደደው።
141፤እኔ፡ታናሽና፡የተናቅኹ፡ነኝ፤ትእዛዛትኽን፡ግን፡አልረሳኹም።
142፤ጽድቅኽ፡የዘለዓለም፡ጽድቅ፡ነው፥ቃልኽም፡እውነት፡ነው።
143፤መከራና፡ችግር፡አገኙኝ፤ትእዛዛትኽ፡ግን፡ተድላዬ፡ናቸው።
144፤ምስክርኽ፡ለዘለዓለም፡ጽድቅ፡ነው፤እንዳስተውል፡አድርገኝ፥በሕይወትም፡አኑረኝ።
ቆፍ
145፤በፍጹም፡ልቤ፡ጮኽኹ፥አቤቱ፥ስማኝ፤ሥርዐትኽን፡እፈልጋለኹ።
146፤ወዳንተ፡ጮኽኹ፤አድነኝ፥ምስክርኽንም፡እጠብቃለኹ።
147፤ማለዳ፡ጮኽኹ፤ቃልኽንም፡ተስፋ፡አድርጌያለኹ።
148፤ቃልኽን፡ዐስብ፡ዘንድ፡ዐይኖቼ፡ለመማለድ፡ቀደሙ።
149፤አቤቱ፥እንደ፡ቸርነትኽ፡ድምፄን፡ስማ፤እንደ፡ፍርድኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
150፤በዐመፃ፡የሚያሳድዱኝ፡ቀረቡ፥ከሕግኽም፡ራቁ።
151፤አቤቱ፥አንተ፡ቅርብ፡ነኽ፥መንገዶችኽም፡ዅሉ፡ቅኖች፡ናቸው።
152፤ከዘለዓለም፡እንደ፡መሠረትኸው፡ከቀድሞ፡ዠምሮ፡ከምስክርኽ፡የተነሣ፡ዐወቅኹ።
ሬስ
153፤ሕግኽን፡አልረሳኹምና፡ችግሬን፡ተመልከት፡አድነኝም።
154፤ፍርዴን፡ፍረድ፡አድነኝም፤ስለ፡ቃልኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
155፤መድኀኒት፡ከኃጥኣን፡ሩቅ፡ነው፥ሥርዐትኽን፡አልፈለጉምና።
156፤አቤቱ፥ቸርነትኽ፡እጅግ፡ብዙ፡ነው፤እንደ፡ፍርድኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
157፤ያሳደዱኝና፡ያስጨነቁኝ፡ብዙዎች፡ናቸው፤ከምስክር፡ግን፡ፈቀቅ፡አላልኹም።
158፤ቃልኽን፡አልጠበቁምና፥ሰነፎችን፡አይቼ፡ዐዘንኹ።
159፤ትእዛዝኽን፡እንደ፡ወደድኹ፡ተመልከት፤አቤቱ፥በምሕረትኽ፡ሕያው፡አድርገኝ።
160፤የቃልኽ፡መዠመሪያ፡እውነት፡ነው፥የጽድቅኽንም፡ፍርድ፡ዅሉ፡ለዘለዓለም፡ነው።
ሳን
161፤ገዢዎች፡በከንቱ፡አሳደዱኝ፤ከቃልኽ፡የተነሣ፡ግን፡ልቤ፡ደነገጠብኝ።
162፤ብዙ፡ምርኮ፡እንዳገኘ፡በቃልኽ፡ደስ፡አለኝ።
163፤ዐመፃን፡ጠላኹ፡ተጸየፍኹም፤ሕግን፡ግን፡ወደድኹ።
164፤ስለ፡ጽድቅኽ፡ፍርድ፡ሰባት፡ጊዜ፡በቀን፡አመሰግንኻለኹ።
165፤ሕግኽን፡ለሚወዱ፡ብዙ፡ሰላም፡ነው፥ዕንቅፋትም፡የለባቸውም።
166፤አቤቱ፥ማዳንኽን፡ተስፋ፡አደርግኹ፥ትእዛዛትኽንም፡ጠበቅኹ።
167፤ነፍሴ፡ምስክርኽን፡ጠበቀች፡እጅግም፡ወደደችው።
168፤መንገዶቼ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ናቸውና፥ትእዛዝኽንና፡ምስክርኽን፡ጠበቅኹ።
ታው
169፤አቤቱ፥ጸሎቴ፡ወደ፡ፊትኽ፡ትቅረብ፤እንደ፡ቃልኽም፡አስተዋይ፡አድርገኝ።
170፤ልመናዬ፡ወደ፡ፊትኽ፡ትድረስ፤እንደ፡ቃልኽ፡አድነኝ።
171፤ሥርዐትኽን፡አስተምረኸኛልና፥ከንፈሮቼ፡ምስጋናን፡አወጡ።
172፤ትእዛዛትኽ፡ዅሉ፡ጽድቅ፡ናቸውና፥አንደበቴ፡ቃልኽን፡ተናገረ።
173፤ትእዛዛትኽን፡መርጫለኹና፡እጅኽ፡የሚያድነኝ፡ይኹን።
174፤አቤቱ፥ማዳንኽን፡ናፈቅኹ፤ሕግኽም፡ተድላዬ፡ነው።
175፤ነፍሴ፡ትኑርልኝ፡ታመሰግንኽማለች፥ፍርድኽም፡ይርዳኝ።
176፤እንደ፡ጠፉ፡በግ፡ተቅበዘበዝኹ፤ትእዛዛትኽን፡አልረሳኹምና፡ባሪያኽን፡ፈልገው።
_______________መዝሙር፡119፡(120)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤በተጨነቅኹ፡ጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኽኹ፥ሰማኝም።
2፤ከዐመፀኛ፡ከንፈር፡ከሸንጋይም፡አንደበት፥አቤቱ፥ነፍሴን፡አድናት።
3፤ስለሽንገላ፡አንደበት፡ምንም፡ይሰጡኻል፧ምንስ፡ይጨምሩልኻል፧
4፤እንደ፡በረሓ፡ዕንጨት፡ፍም፡የኀያላን፡ፍላጻዎች፡የተሳሉ፡ናቸው።
5፤መኖሪያዬ፡የራቀ፡እኔ፡ወዮልኝ፤በቄዳር፡ድንኳኖች፡ዐደርኹ።
6፤ሰላምን፡ከሚጠሉ፡ጋራ፡ነፍሴ፡ብዙ፡ጊዜ፡ኖረች።
7፤እኔ፡ሰላማዊ፡ነኝ፤በተናገርዃቸው፡ጊዜ፡ግን፡በከንቱ፡ተሰለፉብኝ።
_______________መዝሙር፡120፡(121)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤ዐይኖቼ፡ወደ፡ተራራዎች፡አነሣኹ፤ረዳቴ፡ከወዴት፡ይምጣ፧
2፤ረዳቴ፡ሰማይና፡ምድርን፡ከሠራ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው።
3፤እግርኽን፡ለመናወጥ፡አይሰጠውም፤የሚጠብቅኽም፡አይተኛም።
4፤እንሆ፥እስራኤልን፡የሚጠብቅ፡አይተኛም፡አያንቀላፋምም።
5፤እግዚአብሔር፡ይጠብቅኻል፥እግዚአብሔርም፡በቀኝ፡እጅኽ፡በኩል፡ይጋርድኻል።
6፤ፀሓይ፡በቀን፡አያቃጥልኽም፡ጨረቃም፡በሌሊት።
7፤እግዚአብሔር፡ከክፉ፡ዅሉ፡ይጠብቅኻል፥ነፍስኽንም፡ይጠብቃታል።
8፤ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡እግዚአብሔር፡መውጣትኽና፡መግባትኽን፡ይጠብቃል።
_______________መዝሙር፡121፡(122)።______________
የዳዊት፡የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንኺድ፡ባሉኝ፡ጊዜ፡ደስ፡አለኝ።
2፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥እግሮቻችን፡በአደባባይሽ፡ቆሙ።
3፤ኢየሩሳሌምስ፡ርስ፡በርሷ፡እንደ፡ተገጠገጠች፡ከተማ፡ተሠርታለች።
4፤የእግዚአብሔርን፡ስም፡ያመስግኑ፡ዘንድ፥ለእስራኤል፡ምስክር፡ሊኾኑ፡የእግዚአብሔር፡ነገዶች፡ወደዚያ፡ይወ ጣሉ።
5፤ዙፋኖች፡በዚያ፡ለፍርድ፡ተቀምጠዋልና፥የዳዊት፡ቤት፡ዙፋኖች።
6፤ለኢየሩሳሌም፡ሰላምን፡ለምኑ፤አንተንም፡ለሚወዱ፡ልማት፡ይኹን።
7፤በኀይልኽ፡ሰላም፥በጌጠኛ፡ቤትኽም፡ልማት፡ይኹን።
8፤ስለ፡ወንድሞቼ፡ስለ፡ባልንጀራዎቼም፥በውስጥሽ፡ሰላም፡ይኹን፡አልኹ።
9፤ስለአምላካችን፡ስለእግዚአብሔር፡ቤት፡ላንቺ፡መልካምነትሽን፡ፈለግኹ።
_______________መዝሙር፡122፡(123)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤በሰማይ፡የምትኖር፡ሆይ፥ዐይኖቼን፡ወዳንተ፡አነሣኹ።
2፤እንሆ፥የባሪያዎች፡ዐይኖች፡ወደጌታቸው፡እጅ፡እንደ፡ኾኑ፥የባሪያዪቱም፡ዐይን፡ወደእመቤቷ፡እጅ፡እንደ፡ኾ ነ፥እንዲሁ፡እስኪምረን፡ድረስ፡ዐይናችን፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ነው።
3፤ማረን፥አቤቱ፥ማረን፤ንቀትን፡እጅግ፡ጠግበናልና፤
4፤የባለጠጋዎች፡ስድብና፡የትዕቢተኛዎችን፡ንቀት፡ነፍሳችን፡እጅግ፡ጠገበች።
_______________መዝሙር፡123፡(124)።______________
የዳዊት፡የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ባይኾን፡እስራኤል፡እንዲህ፡ይበል፦
2፤እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ባይኾን፡ሰዎች፡በእኛ፡ላይ፡በተነሡ፡ጊዜ፥
3፤ቍጣቸው፡በላያችን፡በነደደ፡ጊዜ፥በዚያን፡ጊዜ፡ሕያዋን፡ሳለን፡በዋጡን፡ነበር፤
4፤በዚያን፡ጊዜ፡ውሃ፡ባሰጠመን፡ነበር፥በነፍሳችንም፡ላይ፡ፈሳሽ፡ባለፈ፡ነበር፤
5፤በዚያን፡ጊዜ፡የጐርፍ፡ውሃ፡በነፍሳችን፡ላይ፡ባለፈ፡ነበር።
6፤ለጥርሳቸው፡ንክሻ፡ያላደረገን፡እግዚአብሔር፡ይባረክ።
7፤ነፍሳችን፡እንደ፡ወፍ፡ከአዳኞች፡ወጥመድ፡አመለጠች፦ወጥመድ፡ተሰበረ፡እኛም፡አመለጥን።
8፤ረድኤታችን፡ሰማይንና፡ምድርን፡በሠራ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ነው።
_______________መዝሙር፡124፡(125)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤በእግዚአብሔር፡የታመኑ፡እንደማይታወክ፡ለዘለዓለም፡እንደሚኖር፡እንደ፡ጽዮን፡ተራራ፡ናቸው።
2፤ተራራዎች፡በኢየሩሳሌም፡ዙሪያ፡እንደ፡ኾኑ፥ከዛሬ፡ዠምሮ፡ለዘለዓለም፤እግዚአብሔር፡በሕዝቡ፡ዙሪያ፡ነው።
3፤ጻድቃን፡እጃቸውን፡ወደ፡ክፋት፡እንዳይዘረጉ፥የኃጥኣን፡በትር፡በጻድቃን፡ዕጣ፡ላይ፡አይኖርም።
4፤አቤቱ፥ለቸሮች፡ልባቸውም፡ለቀና፡መልካምን፡አድርግ።
5፤ወደ፡ጠማማነት፡የሚመለሱትን፡ግን፡ዐመፃን፡ከሚሠሩት፡ጋራ፡እግዚአብሔር፡ይወስዳቸዋል።ሰላም፡በእስራኤል ፡ላይ፡ይኹን።
_______________መዝሙር፡125፡(126)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡የጽዮንን፡ምርኮ፡በመለሰ፡ጊዜ፥እጅግ፡ደስተኛዎች፡ኾን፟።
2፤በዚያን፡ጊዜ፡አፋችን፡ደስታን፥አንደበታችንም፡ሐሴትን፡ሞላ፤በዚያን፡ጊዜ፡በአሕዛብ፡ዘንድ።እግዚአብሔር ፡ታላቅ፡ነገርን፡አደረገላቸው፡ተባለ።
3፤እግዚአብሔር፡ታላቅ፡ነገርን፡አደረገልን፥ደስም፡አለን።
4፤አቤቱ፥በደቡብ፡እንዳሉ፡ፈሳሾች፡ምርኳችንን፡መልስ።
5፤በልቅሶ፡የሚዘሩ፡በደስታ፡ይለቅማሉ።
6፤በኼዱ፡ጊዜ፥ዘራቸውን፡ተሸክመው፡እያለቀሱ፡ተሰማሩ፤በተመለሱ፡ጊዜ፡ግን፡ነዷቸውን፡ተሸክመው፡ደስ፡እያላ ቸው፡ይመጣሉ።
_______________መዝሙር፡126፡(127)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡ቤትን፡ካልሠራ፥ሠራተኛዎች፡በከንቱ፡ይደክማሉ፤እግዚአብሔር፡ከተማን፡ካልጠበቀ፥ጠባቂ፡በከ ንቱ፡ይተጋል።
2፤በማለዳ፡መገሥገሣችኹም፡ከንቱ፡ነው።ለወዳጆቹ፡እንቅልፍን፡በሰጠ፡ጊዜ፥እናንተ፡የመከራን፡እንጀራ፡የምት በሉ፥ከተቀመጣችኹበት፡ተነሡ።
3፤እንሆ፥ልጆች፡የእግዚአብሔር፡ስጦታ፡ናቸው፥የሆድም፡ፍሬ፡የርሱ፡ዋጋ፡ነው።
4፤በኀያል፡እጅ፡እንዳሉ፡ፍላጻዎች፥የጐልማስነት፡ልጆች፡እንዲሁ፡ናቸው።
5፤ከነርሱ፡ዘንድ፡ምኞቱን፡የሚፈጽም፡ብፁዕ፡ሰው፡ነው፤ጠላቶቻቸውን፡በአደባባይ፡በተናገሩ፡ጊዜ፡ርሱ፡አያፍ ርም።
_______________መዝሙር፡127፡(128)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔርን፡የሚፈሩት፡ዅሉ፥በመንገዶቹም፡የሚኼዱ፡ምስጉኖች፡ናቸው።
2፤የድካምኽንም፡ፍሬ፡ትመገባለኽ፤ምስጉን፡ነኽ፡መልካምም፡ይኾንልኻል።
3፤ሚስትኽ፡በቤትኽ፡ዕልፍኝ፡ውስጥ፡እንደሚያፈራ፡ወይን፡ናት፤ልጆችኽ፡በማእዱኽ፡ዙሪያ፡እንደ፡ወይራ፡ቡቃያ ፡ናቸው።
4፤እንሆ፥እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፡ሰው፡እንዲህ፡ይባረካል።
5፤እግዚአብሔር፡ከጽዮን፡ይባርክኽ፤በሕይወትኽ፡ዘመን፡ዅሉ፥የኢየሩሳሌምን፡መልካምነቷን፡ታያለኽ።
6፤የልጆችኽንም፡ልጆች፡ታያለኽ።በእስራኤል፡ላይ፡ሰላም፡ይኹን።
_______________መዝሙር፡128፡(129)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤እስራኤል።ከትንሽነቴ፡ዠምሮ፡ብዙ፡ጊዜ፡ተሰለፉብኝ፡ይበል፤
2፤ከትንሽነቴ፡ዠምሮ፡ብዙ፡ጊዜ፡ተሰለፉብኝ፤ነገር፡ግን፥አላሸነፉኝም።
3፤ኀጢአተኛዎች፡በዠርባዬ፡ላይ፡መቱኝ፥ኀጢአታቸውንም፡አስረዘሟት።
4፤እግዚአብሔር፡ጻድቅ፡ነው፤የኀጢአተኛዎችን፡ዐንገታቸውን፡ቈረጠ።
5፤ጽዮንን፡የሚጠሉ፡ዅሉ፡ይፈሩ፥ወደ፡ዃላቸውም፡ይመለሱ።
6፤በሰገነት፡ላይ፡እንደ፡በቀለ፡ሣር፥ሳይነቀል፡እንደሚደርቅ፥
7፤ለሚያጭደው፡እጁን፥ነዶዎቹን፡ለሚሰበስብ፡ዕቅፉን፡እንደማይሞላ፡ይኹኑ።
8፤በመንገዱም፡የሚያልፉ፦የእግዚአብሔር፡በረከት፡በእናንተ፡ላይ፡ይኹን፤በእግዚአብሔር፡ስም፡እንመርቃችዃለ ን፡አይሉም።
_______________መዝሙር፡129፡(130)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥አንተን፡ከጥልቅ፡ጠራኹኽ።
2፤አቤቱ፥ድምፄን፡ስማ፤ዦሮኽ፡የልመናዬን፡ቃል፡የሚያደምጥ፡ይኹን።
3፤አቤቱ፥ኀጢአትንስ፡ብትጠባበቅ፥አቤቱ፥ማን፡ይቆማል፧
4፤ይቅርታ፡ከአንተ፡ዘንድ፡ነውና።
5፤አቤቱ፥ስለ፡ስምኽ፡ተስፋ፡አደረግኹኽ፤ነፍሴ፡በሕግኽ፡ታገሠች።
6፤ከማለዳው፡ሰዓት፡ዠምሮ፡እስከ፡ሌሊት፡ነፍሴ፡በእግዚአብሔር፡ታመነች።
7፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምሕረት፥በርሱም፡ዘንድ፡ብዙ፡ማዳን፡ነውና፥እስራኤል፡በእግዚአብሔር፡ይታመን።
8፤ርሱም፡እስራኤልን፡ከኀጢአቱ፡ዅሉ፡ያድነዋል።
_______________መዝሙር፡130፡(131)።______________
የዳዊት፡መዓርግ፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ልቤ፡አይታበይብኝ፥ዐይኖቼም፡ከፍ፡ከፍ፡አይበሉብኝ፤ከትልልቆች፡ጋራ፥ከእኔም፡ይበልጥ፡ከሚከበሩ፡ ጋራ፡አልኼድኹም።
2፤ነፍሴን፡አሳረፍዃት፥የእናቱንም፡ጡት፡እንዳስተዉት፡ዝም፡አሠኘዃት፤ነፍሴ፡የእናቱን፡ጡት፡እንዳስተዉት፡ በእኔ፡ውስጥ፡ናት።
3፤ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡እስራኤል፡በእግዚአብሔር፡ይታመን።
_______________መዝሙር፡131፡(132)።______________
የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ዳዊትን፡ገርነቱንም፡ዅሉ፡ዐስብ፤
2፤ለእግዚአብሔር፡እንደ፡ማለ፥ለያዕቆብም፡አምላክ፡እንደ፡ተሳለ።
3፤በእውነት፡ወደቤቴ፡ድንኳን፡አልገባም፥ወደምንጣፌም፡ዐልጋ፡አልወጣም፥
4፤ለዐይኖቼም፡መኝታ፡ለሽፋሽፍቶቼም፡እንቅልፍ፥ለጕንጮቼም፡ዕረፍትን፡አልሰጥም፥
5፤ለእግዚአብሔር፡ስፍራ፥ለያዕቆብ፡አምላክ፡ማደሪያ፡እስካገኝ፡ድረስ፡ብሎ።
6፤እንሆ፥በኤፍራታ፡ሰማነው፥በዱር፡ውስጥም፡አገኘነው።
7፤ወደ፡ማደሪያዎቹ፡እንገባለን፤እግሮቹ፡በሚቆሙበት፡ስፍራ፡እንሰግዳለን።
8፤አቤቱ፥ወደ፡ዕረፍትኽ፡ተነሥ፥አንተና፡የመቅደስኽ፡ታቦት።
9፤ካህናትኽ፡ጽድቅን፡ይልበሱ፥ቅዱሳንኽም፡ደስ፡ይበላቸው።
10፤ስለ፡ዳዊት፡ስለ፡ባሪያኽ፡የቀባኸውን፡ሰው፡ፊት፡አትመልስ።
11፤እግዚአብሔር፡ለዳዊት፡በእውነት፡ማለ፥አይጸጸትምም፥እንዲህ፡ብሎ፦ከሆድኽ፡ፍሬ፡በዙፋንኽ፡ላይ፡አስቀም ጣለኹ።
12፤ልጆችኽ፡ኪዳኔን፥ይህንም፡የማስተምራቸውን፡ምስክሬን፡ቢጠብቁ፥ልጆቻቸው፡ደግሞ፡በዙፋንኽ፡ላይ፡ለዘለዓ ለም፡ይቀመጣሉ።
13፤እግዚአብሔር፡ጽዮንን፡መርጧታልና፥ማደሪያውም፡ትኾነው፡ዘንድ፡ወዷ፟ታልና፥እንዲህ፡ብሎ፦
14፤ይህች፡ለዘለዓለም፡ማረፊያዬ፡ናት፤መርጫታለኹና፡በዚች፡ዐድራለኹ።
15፤አሮጊቶቿን፡እጅግ፡እባርካለኹ፥ድኻዎቿንም፡እንጀራ፡አጠግባለኹ።
16፤ካህናቷንም፡ደኅንነትን፡አለብሳቸዋለኹ፥ቅዱሳኖቿም፡እጅግ፡ደስ፡ይላቸዋል።
17፤በዚያ፡ለዳዊት፡ቀንድን፡አበቅላለኹ፥ለቀባኹትም፡ሰው፡መብራትን፡አዘጋጃለኹ።
18፤ጠላቶችንም፡ዕፍረትን፡አለብሳቸዋለኹ፤በርሱ፡ግን፡ቅድስናዬ፡ያብባል።
_______________መዝሙር፡132፡(133)።______________
የዳዊት፡የመዓርግ፡መዝሙር።
1፤ወንድሞች፡በኅብረት፡ቢቀመጡ፥እንሆ፥መልካም፡ነው፥እንሆም፥ያማረ፡ነው።
2፤ከራስ፡እስከ፡ጢም፡እንደሚፈስ፟፥እስከአሮን፡ጢም፥በልብሱ፡መደረቢያ፡እንደሚወርድ፡ሽቱ፡ነው።
3፤በጽዮን፡ተራራዎች፡እንደሚወርድ፡እንደ፡አርሞንዔም፡ጠል፡ነው፤በዚያ፡እግዚአብሔር፡በረከቱን፡ሕይወትንም ፡እስከ፡ዘለዓለም፡አዟ፟ልና።
_______________መዝሙር፡133፡(134)።______________
የማዕርግ፡መዝሙር።
1፤እንሆ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩ፥በአምላካችን፡ቤት፡አደባባዮች፡የምትቆሙ፡እናንተ፥የእግዚአብሔር፡ባሪያዎች ፡ዅላችኹ።
2፤በሌሊት፡በቤተ፡መቅደስ፡ውስጥ፡እጆቻችኹን፡አንሡ፥እግዚአብሔርንም፡ባርኩ።
3፤ሰማይንና፡ምድርን፡የሠራ፡እግዚአብሔር፡ከጽዮን፡ይባርክኽ።
_______________መዝሙር፡134፡(135)።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ።የእግዚአብሔርን፡ስም፡አመስግኑ፤እናንተ፡የእግዚአብሔር፡ባሪያዎች፡ሆይ፥አመስግኑት፥
2፤በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፥በአምላካችን፡ቤት፡አደባባይ፡የምትቆሙ።
3፤እግዚአብሔር፡ቸር፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፤ለስሙ፡ዘምሩ፥መልካም፡ነውና፤
4፤እግዚአብሔር፡ያዕቆብን፡ለራሱ፥እስራኤልንም፡ለመዝገቡ፡መርጦታልና፤
5፤እግዚአብሔር፡ታላቅ፡እንደ፡ኾነ፥ጌታችንም፡ከአማልክት፡ዅሉ፡እንዲበልጥ፡ዐውቄያለኹና።
6፤በሰማይና፡በምድር፡በባሕርና፡በጥልቆች፡ዅሉ፥እግዚአብሔር፡የወደደውን፡ዅሉ፡አደረገ።
7፤ከምድር፡ዳር፡ደመናትን፡ያወጣል፤በዝናብ፡ጊዜ፡መብረቅን፡አደረገ፤ነፋሳትንም፡ከመዛግብቱ፡ያወጣል።
8፤የግብጽን፡በኵር፡ልጆች፡ከሰው፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡መታ።
9፤ግብጽ፡ሆይ፥በመካከልሽ፡በፈርዖንና፡በባሪያዎቹ፡ዅሉ፡ላይ፡ተኣምራትንና፡ድንቅን፡ሰደደ።
10፤ብዙ፡አሕዛብን፡መታ፥ብርቱዎችንም፡ነገሥታት፡ገደለ።
11፤የአሞራውያንን፡ንጉሥ፡ሴዎንን፥የባሳንንም፡ንጉሥ፡ዐግን፥የከነዓንን፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ገደለ፤
12፤ምድራቸውንም፡ርስት፡አድርጎ፡ለእስራኤል፡ለሕዝቡ፡ርስት፡ሰጠ።
13፤አቤቱ፥ስምኽ፡ለዘለዓለም፡ነው፥ዝክርኽም፡ለልጅ፡ልጅ፡ነው፤
14፤እግዚአብሔር፡ለሕዝቡ፡ይፈርዳልና፥ባሪያዎቹንም፡ይረዳልና።
15፤የአሕዛብ፡ጣዖታት፡የብርና፡የወርቅ፥የሰው፡እጅ፡ሥራ፡ናቸው።
16፤አፍ፡አላቸው፥አይናገሩምም፤ዐይን፡አላቸው፥አያዩምም፤
17፤ዦሮ፡አላቸው፥አይሰሙምም፤እስትንፋስም፡በአፋቸው፡የለም።
18፤የሚሠሯቸው፡ዅሉ፡የሚታመኑባቸውም፡ዅሉ፡እንደ፡እነርሱ፡ይኹን።
19፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩት።የአሮን፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩት፤
20፤የሌዊ፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩት፡እግዚአብሔርን፡የምትፈሩት፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኩት።
21፤በኢየሩሳሌም፡የሚያድር፡እግዚአብሔር፡ከጽዮን፡የተባረከ፡ነው።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡135፡(136)።______________
1፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፤ቸር፡ነውና፥ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
2፤የአማልክትን፡አምላክ፡አመስግኑ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
3፤የጌታዎችን፡ጌታ፡አመስግኑ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
4፤ርሱ፡ብቻውን፡ታላቅ፡ተኣምራትን፡ያደረገ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
5፤ሰማያትን፡በብልኀት፡የሠራ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
6፤ምድርን፡በውሃ፡ላይ፡ያጸና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
7፤ብቻውን፡ታላላቅ፡ብርሃናትን፡የሠራ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
8፤ለፀሓይ፡ቀንን፡ያስገዛው፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
9፤ለጨረቃና፡ለከዋክብትም፡ሌሊትን፡ያስገዛቸው፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
10፤ከበኵራቸው፡ጋራ፡ግብጽን፡የመታ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
11፤እስራኤልንም፡ከመካከላቸው፡ያወጣ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
12፤በጸናች፡እጅ፡በተዘረጋችም፡ክንድ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
13፤ቀይ፡ባሕርን፡በየክፍሉ፡የከፈለ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
14፤እስራኤልን፡በመካከሉ፡ያሳለፈ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
15፤ፈርዖንንና፡ሰራዊቱን፡በቀይ፡ባሕር፡የጣለ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
16፤ሕዝቡን፡በምድረ፡በዳ፡የመራ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
17፤ታላላቅ፡ነገሥታትን፡የመታ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
18፤ብርቱዎችንም፡ነገሥታት፡የገደለ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
19፤የአሞራውያንን፡ንጉሥ፡ሴዎንን፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
20፤የባሳንን፡ንጉሥ፡ዐግን፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
21፤ምድራቸውን፡ርስት፡አድርጎ፡የሰጠ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
22፤ለባሪያው፡ለእስራኤል፡ርስት፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
23፤እኛን፡በመዋረዳችን፡ዐስቦናልና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
24፤ከጠላቶቻችንም፡እጅ፡አድኖናልና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
25፤ለሥጋ፡ዅሉ፡ምግብን፡የሚሰጥ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
26፤የሰማይን፡አምላክ፡አመስግኑ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
_______________መዝሙር፡136፡(137)።______________
1፤በባቢሎን፡ወንዞች፡አጠገብ፡በዚያ፡ተቀመጥን፤ጽዮንንም፡ባሰብናት፡ጊዜ፡አለቀስን።
2፤በአሓያ፡ዛፎቿ፡ላይ፡መሰንቆቻችንን፡ሰቀልን።
3፤የማረኩን፡በዚያ፡የዝማሬን፡ቃል፡ፈለጉብን፥የወሰዱንም፦የጽዮንን፡ዝማሬ፡ዘምሩልን፡አሉን።
4፤የእግዚአብሔርን፡ዝማሬ፡በባዕድ፡ምድር፡እንዴት፡እንዘምራለን፧
5፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ብረሳሽ፥ቀኜ፡ትርሳኝ።
6፤ባላስብሽ፥ምላሴ፡በጕረሮዬ፡ይጣበቅ፤ከደስታዬ፡ዅሉ፡በላይ፡ኢየሩሳሌምን፡ባልወድ፟።
7፤አቤቱ፥በኢየሩሳሌም፡ቀን፡የኤዶምን፡ልጆች፡ዐስብ።እስከ፡መሠረቷ፡ድረስ፡አፍርሱ፡አፍርሱ፡ያሏትን።
8፤አንቺ፡ወራዳ፡የባቢሎን፡ልጅ፡ሆይ፥ስለ፡ተበቀልሽን፡የሚበቀልሽ፡የተመሰገነ፡ነው።
9፤ሕፃናትሽን፡ይዞ፡በአለት፡ላይ፡የሚፈጠፍጣቸው፡የተመሰገነ፡ነው።
_______________መዝሙር፡137፡(138)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥በፍጹም፡ልቤ፡አመሰግንኻለኹ፥የአፌን፡ነገር፡ሰምተኸኛልና፤በመላእክት፡ፊት፡እዘምርልኻለኹ።
2፤ወደ፡ቅዱስ፡መቅደስኽ፡እሰግዳለኹ፤ስለ፡ምሕረትኽና፡ስለ፡እውነትኽ፡ስምኽንም፡አመሰግናለኹ፥በዅሉ፡ላይ፡ ቅዱስ፡ስምኽን፡ከፍ፡ከፍ፡አድርገኻልና።
3፤በጠራኹኽ፡ቀን፡በፍጥነት፡አድምጠኝ፤ነፍሴን፡በኀይልኽ፡በብዙ፡አጸናኻት።
4፤አቤቱ፥የምድር፡ነገሥታት፡ዅሉ፡ያመሰግኑኻል፤የአፍኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ሰምተዋልና።
5፤በእግዚአብሔርም፡መንገድ፡ይዘምራሉ፤የእግዚአብሔር፡ክብር፡ታላቅ፡ነውና።
6፤እግዚአብሔር፡ከፍ፡ያለ፡ነውና፥ወደ፡ችግረኛዎችም፡ይመለከታልና፤ትዕቢተኛዎችንም፡ከሩቅ፡ያውቃል።
7፤በመከራ፡መካከል፡እንኳ፡ብኼድ፥አንተ፡ሕያው፡ታደርገኛለኽ፤በጠላቶቼ፡ቍጣ፡ላይ፡እጆቼን፡ትዘረጋለኽ፥ቀኝ ኽም፡ታድነኛለች።
8፤እግዚአብሔር፡ብድራትን፡ይመልስልኛል፤አቤቱ፥ምሕረትኽ፡ለዘለዓለም፡ነው፤አቤቱ፥የእጅኽን፡ሥራ፡ቸል፡አት በል።
_______________መዝሙር፡138፡(139)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥መረመርኸኝ፥ዐወቅኸኝም።
2፤አንተ፡መቀመጤንና፡መነሣቴን፡ዐወቅኽ፤ዐሳቤን፡ዅሉ፡ከሩቅ፡አስተዋልኽ።
3፤ፍለጋዬንና፡ዕረፍቴን፡አንተ፡መረመርኽ፤መንገዶቼን፡ዅሉ፡ቀድመኽ፡ዐወቅኽ፥
4፤የዐመፃ፡ቃል፡በአንደበቴ፡እንደሌለ።
5፤አቤቱ፥አንተ፥እንሆ፥የቀድሞውንና፡የዃላውን፡ዐወቅኽ፤አንተ፡ፈጠርኸኝ፥እጅኽንም፡በላዬ፡አደረግኽ።
6፤ዕውቀትኽ፡ከእኔ፡ይልቅ፡ተደነቀች፤በረታች፥ወደ፡ርሷም፡ለመድረስ፡አልችልም።
7፤ከመንፈስኽ፡ወዴት፡እኼዳለኹ፧ከፊትኽስ፡ወዴት፡እሸሻለኹ፧
8፤ወደ፡ሰማይ፡ብወጣ፥አንተ፡በዚያ፡አለኽ።ወደ፡ሲኦልም፡ብወርድ፥በዚያ፡አለኽ።
9፤እንደ፡ንስር፡የንጋትን፡ክንፍ፡ብወስድ፥እስከባሕር፡መጨረሻም፡ብበር፟፥
10፤በዚያ፡እጅኽ፡ትመራኛለች፥ቀኝኽም፡ትይዘኛለች።
11፤በእውኑ፡ጨለማ፡ትሸፍነኛለች፡ብል፥ሌሊት፡በዙሪያዬ፡ብርሃን፡ትኾናለች፤
12፤ጨለማ፡ባንተ፡ዘንድ፡አይጨልምምና፥ሌሊትም፡እንደ፡ቀን፡ታበራለችና፤እንደ፡ጨለማዋ፡እንዲሁ፡ብርሃኗ፡ነ ው።
13፤አቤቱ፥አንተ፡ኵላሊቴን፡ፈጥረኻልና፥በእናቴም፡ሆድ፡ሰውረኸኛል።
14፤ግሩምና፡ድንቅ፡ኾኜ፡ተፈጥሬያለኹና፡አመሰግንኻለኹ፤ሥራኽ፡ድንቅ፡ነው፥ነፍሴም፡እጅግ፡ታውቀዋለች።
15፤እኔ፡በስውር፡በተሠራኹ፡ጊዜ፥አካሌም፡በምድር፡ታች፡በተሠራ፡ጊዜ፡ዐጥንቶቼ፡ከአንተ፡አልተሰወሩም።
16፤ያልተሠራ፡አካሌን፡ዐይኖችኽ፡አዩኝ፤የተፈጠሩ፡ቀኖቼ፡ዅሉ፡አንድ፡ስንኳ፡ሳይኖር፡በመጽሐፍኽ፡ተጻፉ።
17፤አቤቱ፥ዐሳቦችኽ፡በእኔ፡ዘንድ፡እንደ፡ምን፡እጅግ፡የተከበሩ፡ናቸው! ቍጥራቸውም፡እንደ፡ምን፡በዛ!
18፤ብቈጥራቸው፡ከአሸዋ፡ይልቅ፡ይበዛሉ፤ተነሣኹም፥እኔም፡ገና፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝ።
19፤አቤቱ፥አንተ፡ኀጢአተኛዎችን፡የምትገድል፡ከኾንኽስ፥የደም፡ሰዎች፡ሆይ፥ከእኔ፡ፈቀቅ፡በሉ።
20፤በክፋት፡ይናገሩብኻልና፤ጠላቶችኽም፡በከንቱ፡ያምፁብኻል።
21፤አቤቱ፥የሚጠሉኽን፡እኔ፡የጠላኹ፡አይደለኹምን፧ስለ፡ጠላቶችኽም፡አልተሰቀቅኹምን፧
22፤ፍጹም፡ጥል፡ጠላዃቸው፥ጠላቶችም፡ኾኑኝ።
23፤አቤቱ፥መርምረኝ፥ልቤንም፡ዕወቅ፤ፍተነኝ፡መንገዴንም፡ዕወቅ፤
24፤በደልንም፡በእኔ፡ውስጥ፡ብታገኝ፡እይ፤የዘለዓለምንም፡መንገድ፡ምራኝ።
_______________መዝሙር፡139፡(140)።______________
ለመዘምራን፡አለቃ፡የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ከክፉ፡ሰው፡አድነኝ፥በልባቸውም፡ክፉ፡ካሰቡ፡ከዐመፀኛዎች፡ሰዎች፡ጠብቀኝ፤
2፤ቀኑን፡ዅሉ፡ለሰልፍ፡ይከማቻሉ።
3፤ምላሳቸውን፡እንደ፡እባብ፡ሳሉ፤ከከንፈራቸው፡በታች፡የእፍኝት፡መርዝ፡ነው።
4፤አቤቱ፥ከኀጢአተኛዎች፡እጅ፡ጠብቀኝ፥ርምጃዬንም፡ሊያሰናክሉ፡ከመከሩ፡ከዐመፀኛዎች፡አድነኝ።
5፤ትዕቢተኛዎች፡ወጥመድን፡ሰወሩብኝ፥ለእግሮቼም፡የወጥመድ፡ገመድን፡ዘረጉ፤በመንገድ፡ዕንቅፋትን፡አኖሩ።
6፤እግዚአብሔርንም፦አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፤የልመናዬን፡ቃል፥አቤቱ፥አድምጥ፡አልኹት።
7፤አቤቱ፥ጌታዬ፥የመድኀኒቴ፡ጕልበት፥በሰልፍ፡ቀን፡ራሴን፡ሸፈንኽ።
8፤አቤቱ፥ከምኞቴ፡የተነሣ፡ለኀጢአተኛዎች፡አትስጠኝ፤በላዬ፡ተማከሩ፤እንዳይጓደዱ፡አትተወኝ።
9፤የሚከቡ፟ኝን፡ራስ፡የከንፈራቸው፡ክፋት፡ይክደናቸው።
10፤የእሳት፡ፍም፡በላያቸው፡ይውደቅ፤እንዳይነሡም፡ወደ፡እሳትና፡ወደ፡ማዕበል፡ይጣሉ።
11፤ተናጋሪ፡ሰው፡በምድር፡ውስጥ፡አይጸናም፤ዐመፀኛን፡ሰው፡ክፋት፡ለጥፋት፡ይፈልገዋል።
12፤እግዚአብሔር፡ለድኻ፡ዳኝነትን፡ለችግረኛም፡ፍርድን፡እንዲያደርግ፡ዐወቅኹ።
13፤ጻድቃንም፡በእውነት፡ስምኽን፡ያመሰግናሉ፤ቀኖችም፡በፊትኽ፡ይኖራሉ።
_______________መዝሙር፡140፡(141)።______________
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ወዳንተ፡ጮኽኹ፤ስማኝ፤ወዳንተ፡ስጮኽም፡የልመናዬን፡ቃል፡አድምጥ።
2፤ጸሎቴን፡በፊትኽ፡እንደ፡ዕጣን፡ተቀበልልኝ፥እጅ፡መንሣቴም፡እንደ፡ሠርክ፡መሥዋዕት፡ትኹን።
3፤አቤቱ፥ለአፌ፡ጠባቂ፡አኑር፥የከንፈሮቼንም፡መዝጊያ፡ጠብቅ።
4፤ልቤን፡ወደ፡ክፉ፡ነገር፡አትመልሰው፥ዐመፃን፡ከሚያደርጉ፡ሰዎች፡ጋራ፡ለኀጢአት፡ምክንያት፡እንዳልሰጥ፤ከ ምርጦቻቸውም፡ጋራ፡አልተባበር።
5፤ጻድቅ፡በምሕረት፡ይገሥጸኝ፥ይዝለፈኝም፥የኀጢአተኛ፡ዘይት፡ግን፡ራሴን፡አይቅባ፤ጸሎቴ፡ገና፡በክፋታቸው፡ ላይ፡ነውና።
6፤ኀያላናቸው፡በአለት፡አጠገብ፡ተጣሉ፤ጣፋጭ፡ናትና፥ቃሌን፡ይሰማሉ።
7፤በምድር፡ላይ፡እንደ፡ተሰነጠቀ፡እንደ፡መሬት፡ጓል፥እንዲሁ፡ዐጥንቶቻችን፡በሲኦል፡ተበተኑ።
8፤አቤቱ፡ጌታ፥ዐይኖቼ፡ወዳንተ፡ናቸውና፤ባንተ፡ታመንኹ፥ነፍሴን፡አታውጣት።
9፤ከሰወሩብኝ፡ወጥመድ፥ዐመፅንም፡ከሚያደርጉ፡ሰዎች፡ዕንቅፋት፡ጠብቀኝ።
10፤እኔ፡ብቻዬን፡እስካልፍ፡ድረስ፡ኀጢአተኛዎች፡በወጥመዳቸው፡ይውደቁ።
_______________መዝሙር፡141፡(142)።______________
ጸሎት፤በዋሻ፡በነበረ፡ጊዜ፤የዳዊት፡ትምህርት።
1፤በቃሌ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኽኹ፤በቃሌ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ለመንኹ።
2፤ልመናዬን፡በፊቱ፡አፈሳ፟ለኹ፤መከራዬንም፡በፊቴ፡እናገራለኹ።
3፤ነፍሴ፡በውስጤ፡ባለቀች፡ጊዜ፡መንገዴን፡ዐወቅኹ፤በምኼድባት፡በዚያች፡መንገድ፡ወጥመድን፡ሰወሩብኝ።
4፤ወደ፡ቀኝ፡ተመለከትኹ፡አየኹም፥የሚያውቀኝም፡ዐጣኹ፤መሸሸጊያም፡የለኝም፥ስለ፡ነፍሴም፡የሚመራመር፡የለም ።
5፤አቤቱ፥ወዳንተ፡ጮኽኹ፦አንተ፡ተስፋዬ፡ነኽ፥በሕያዋንም፡ምድር፡አንተ፡ዕድል፡ፈንታዬ፡ነኽ፡አልኹ።
6፤እጅግ፡ተቸግሬያለኹና፡ወደ፡ልመናዬ፡አድምጥ፤በርትተውብኛልና፥ከሚያሳድዱኝ፡አድነኝ።
7፤አቤቱ፥ስምኽን፡አመሰግን፡ዘንድ፤ነፍሴን፡ከወህኒ፡አውጣት፤ዋጋዬን፡እስክትሰጠኝ፡ድረስ፡ጻድቃን፡እኔን፡ ይጠብቃሉ።
_______________መዝሙር፡142፡(143)።______________
ልጁ፡ባሳደደው፡ጊዜ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤አቤቱ፥ጸሎቴን፡ስማ፤በእውነትኽ፡ልመናዬን፡አድምጥ፥በጽድቅኽም፡መልስልኝ።
2፤ሕያው፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ጻድቅ፡አይደለምና፡ከባሪያኽ፡ጋራ፡ወደ፡ፍርድ፡አትግባ።
3፤ጠላትኽ፡ነፍሴን፡አሳዷ፟ታል፥ሕይወቴንም፡በምድር፡ውስጥ፡አጐስቍሏታል፤ቀድሞ፡እንደ፡ሞተ፡ሰው፡በጨለማ፡ አኑሮኛል።
4፤ነፍሴ፡በውስጤ፡አለቀችብኝ፥ልቤም፡በውስጤ፡ደነገጠብኝ።
5፤የቀድሞውን፡ዘመን፡ዐሰብኹ፥ሥራኽንም፡ዅሉ፡አሰላሰልኹ፤የእጅኽንም፡ሥራ፡ተመለከትኹ።
6፤እጆቼን፡ወዳንተ፡ዘረጋኹ፤ነፍሴም፡እንደ፡ምድረ፡በዳ፡አንተን፡ተጠማች።
7፤አቤቱ፥ፈጥነኽ፡ስማኝ፤ነፍሴ፡አልቃለች፤ፊትኽን፡ከእኔ፡አትመልስ፥ወደ፡ጕድጓድም፡እንደሚወርዱ፡አልኹን።
8፤አንተን፡ታምኛለኹና፡በማለዳ፡ምሕረትኽን፡አሰማኝ፤አቤቱ፥ነፍሴን፡ወዳንተ፡አንሥቻለኹና፡የምኼድበትን፡መ ንገድ፡አስታውቀኝ።
9፤አቤቱ፥ወዳንተ፡ተማፅኛለኹና፡ከጠላቶቼ፡አድነኝ።
10፤አንተ፡አምላኬ፡ነኽና፥ፈቃድኽን፡ለማድረግ፡አስተምረኝ፤ቅዱስ፡መንፈስኽም፡በጽድቅ፡ምድር፡ይምራኝ።
11፤አቤቱ፥ስለ፡ስምኽ፡ሕያው፡አድርገኝ፤በጽድቅኽም፡ነፍሴን፡ከመከራዋ፡አውጣት።
12፤በምሕረትኽ፡ጠላቶቼን፡ደምስሳቸው፥እኔ፡ባሪያኽ፡ነኝና፡ነፍሴን፡የሚያስጨንቋትን፡ዅሉ፡አጥፋቸው።
_______________መዝሙር፡143፡(144)።______________
ስለ፡ጎልያድ፤የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡አምላኬ፡ይባረክ፥ለእጆቼ፡ሰልፍን፥ለጣቶቼም፡ዘመቻን፡የሚያስተምር፤
2፤መሓሪዬና፡መሸሸጊያዬ፥መጠጊያዬና፡መድኀኒቴ፤ረዳቴና፡መታመኛዬም፤ሕዝቤንም፡ከእኔ፡በታች፡የሚያስገዛልኝ ።
3፤አቤቱ፥ርሱን፡ታውቀው፡ዘንድ፡ሰው፡ምንድር፡ነው፧ታስብለት፡ዘንድ፡የሰው፡ልጅ፡ምንድር፡ነው፧
4፤ሰው፡ከንቱን፡ነገር፡ይመስላል፤ዘመኑ፡እንደ፡ጥላ፡ያልፋል።
5፤አቤቱ፥ሰማዮችኽን፡ዝቅ፡ዝቅ፡አድርጋቸው፡ውረድም፤ተራራዎችን፡ዳስሳቸው፡ይጢሱም።
6፤መብረቆችኽን፡ብልጭ፡አድርጋቸው፡በትናቸውም፤ፍላጻዎችኽን፡ላካቸው፥አስደንግጣቸውም።
7-8፤እጅኽን፡ከአርያም፡ላክ፡አድነኝም፡ከብዙ፡ውሃዎች፥አፋቸውም፡ምናምንን፡ከሚናገር፥ቀኛቸው፡የሐሰት፡ቀኝ ፡ከኾነ፥ከባዕድ፡ልጆች፡እጅ፡አስጥለኝ።
9፤አቤቱ፥ዐዲስ፡ቅኔ፡እቀኝልኻለኹ፤ዐሥር፡አውታር፡ባለው፡በገና፡እዘምርልኻለኹ።
10፤ለነገሥታት፡መድኀኒትን፡የሚሰጥ፥ባሪያውን፡ዳዊትን፡ከክፉ፡ሰይፍ፡የሚያድነው፡ርሱ፡ነው።
11፤አድነኝ፥አፋቸውም፡ምናምንን፡ከሚናገር፥ቀኛቸውም፡የሐሰት፡ቀኝ፡ከኾነ፥ከባዕድ፡ልጆች፡እጅ፡አስጥለኝ።
12፤ልጆቻቸው፡በጕልማሳነታቸው፡እንደ፡ዐዲስ፡አትክልት፡የኾኑ፥ሴቶች፡ልጆቻቸውም፡እንደ፡ዕልፍኝ፡ያማሩና፡ ያጌጡ፤
13፤ዕቃ፡ቤቶቻቸውም፡የተሞሉ፡በየዐይነቱ፡ዕቃ፡የሚሰጡ፥በጎቻቸውም፡ብዙ፡የሚወልዱ፥በማሰማሪያቸውም፡የሚበ ዙ፥
14፤ላሞቻቸውም፡የሚሰቡ፤ቅጥራቸውም፡መፍረሻና፡መውጫ፡የሌለው፥በአደባባዮቻቸውም፡ዋይታ፡የሌለ፤
15፤እንደዚህ፡የሚኾን፡ሕዝብ፡የተመሰገነ፡ነው፤እግዚአብሔር፡አምላኩ፡የኾነ፡ሕዝብ፡ምስጉን፡ነው።
_______________መዝሙር፡144፡(145)።______________
የዳዊት፡የምስጋና፡መዝሙር።
1፤አምላኬ፡ንጉሤ፡ሆይ፥ከፍ፡ከፍ፡አደርግኻለኹ፥ስምኽንም፡ለዘለዓለም፡ዓለምም፡እባርካለኹ።
2፤በየቀኑ፡ዅሉ፡እባርክኻለኹ፥ስምኽንም፡ለዘለዓለም፡ዓለምም፡አመሰግናለኹ።
3፤እግዚአብሔር፡ታላቅ፡ነው፡እጅግም፡የተመሰገነ፡ነው፤ለታላቅነቱም፡ፍጻሜ፡የለውም።
4፤ትውልደ፡ትውልድ፡ሥራኽን፡ያመሰግናሉ፥ኀይልኽንም፡ያወራሉ።
5፤የቅድስናኽን፡ግርማ፡ክብር፡ይናገራሉ፥ተኣምራትኽንም፡ይነጋገራሉ።
6፤የግርማኽንም፡ኀይል፡ይናገራሉ፥ታላቅነትኽንም፡ይነጋገራሉ፥ብርታትኽንም፡ይነጋገራሉ።
7፤የቸርነትኽን፡ብዛት፡መታሰብ፡ያወጣሉ፥በጽድቅኽም፡ሐሤትን፡ያደርጋሉ።
8፤እግዚአብሔር፡ርኅሩኅና፡መሓሪ፡ነው፥ከቍጣ፡የራቀ፥ምሕረቱም፡ብዙ፡ነው፤
9፤እግዚአብሔር፡ለሚታገሡት፡ቸር፡ነው።ምሕረቱም፡በሥራው፡ዅሉ፡ላይ፡ነው።
10፤አቤቱ፥ሥራኽ፡ዅሉ፡ያመሰግኑኻል፥ቅዱሳንኽም፡ይባርኩኻል።
11፤የመንግሥትኽን፡ክብር፡ይናገራሉ፥ኀይልኽንም፡ይነጋገራሉ፥
12፤ለሰው፡ልጆች፡ኀይልኽን፡የመንግሥትኽንም፡ግርማ፡ክብር፡ያስታውቁ፡ዘንድ፡
13፤መንግሥትኽ፡የዘለዓለም፡መንግሥት፡ናት፥ግዛትኽም፡ለልጅ፡ልጅ፡ነው።
14፤እግዚአብሔር፡በቃሎቹ፡የታመነ፡ነው፥በሥራውም፡ዅሉ፡ጻድቅ፡ነው፤እግዚአብሔር፡የተፍገመገሙትን፡ዅሉ፡ይ ደግፋቸዋል፥የወደቁትንም፡ያነሣቸዋል።
15፤የዅሉ፡ዐይን፡አንተን፡ተስፋ፡ያደርጋል፤አንተም፡ምግባቸውን፡በየጊዜው፡ትሰጣቸዋለኽ።
16፤አንተ፡እጅኽን፡ትከፍታለኽ፥ሕይወት፡ላለውም፡ዅሉ፡መልካምን፡ታጠግባለኽ።
17፤እግዚአብሔር፡በመንገዱ፡ዅሉ፡ጻድቅ፡ነው፡በሥራውም፡ዅሉ፡ቸር፡ነው።
18፤እግዚአብሔር፡ለሚጠሩት፡ዅሉ፥በእውነት፡ለሚጠሩት፡ዅሉ፡ቅርብ፡ነው።
19፤ለሚፈሩት፡ምኞታቸውን፡ያደርጋል፥ልመናቸውንም፡ይሰማል፡ያድናቸዋልም።
20፤እግዚአብሔር፡የሚወዱትን፡ዅሉ፡ይጠብቃል፤ኀጢአተኛዎችንም፡ዅሉ፡ያጠፋል።
21፤አፌ፡የእግዚአብሔርን፡ምስጋና፡ይናገራል፤ሥጋም፡ዅሉ፡ለዘለዓለም፡ዓለም፡የተቀደሰውን፡ስሙን፡ይባርክ።
_______________መዝሙር፡145፡(146)።______________
የሐጌና፡የዘካርያስ፡መዝሙር።
1፤ሃሌ፡ሉያ።ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡አመስግኚ።
2፤በሕይወቴ፡እግዚአብሔርን፡አመሰግናለኹ፤በምኖርበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ለአምላኬ፡እዘምራለኹ።
3፤ማዳን፡በማይችሉ፡በሰው፡ልጆችና፡በአለቃዎች፡አትታመኑ።
4፤ነፍሱ፡ትወጣለች፡ወደ፡መሬቱም፡ይመለሳል፤ያን፡ጊዜ፡ምክሩ፡ዅሉ፡ይጠፋል።
5፤የያዕቆብ፡አምላክ፡ረዳቱ፡የኾነ፡ተስፋውም፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡የኾነ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው፤
6፤ርሱም፡ሰማይንና፡ምድርን፡ባሕርንም፥በእነርሱ፡ያለውንም፡ዅሉ፡የፈጠረ፤እውነትን፡ለዘለዓለም፡የሚጠብቅ፤
7፤ለተበደሉት፡የሚፈርድ፥ለተራቡ፡ምግብን፡የሚሰጥ፡ነው።እግዚአብሔር፡የታሰሩትን፡ይፈታል፤
8፤እግዚአብሔር፡የወደቁትን፡ያነሣል፤እግዚአብሔር፡ዕውሮችን፡ጥበበኛዎች፡ያደርጋቸዋል፤እግዚአብሔር፡ጻድቃ ንን፡ይወዳ፟ል፤
9፤እግዚአብሔር፡ስደተኛዎችን፡ይጠብቃል፤ድኻ፡አደጎችንና፡ባልቴቶችን፡ይቀበላል፤የኀጢአተኛዎችንም፡መንገድ ፡ያጠፋል።
10፤እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ይነግሣል፤ጽዮን፡ሆይ፥አምላክሽ፡ለልጅ፡ልጅ፡ነው።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡146፡(147)።______________
የሐጌና፡የዘካርያስ፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥መዝሙር፡መልካም፡ነውና።ለአምላካችን፡ምስጋና፡ያማረ፡ነው።
2፤እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ይሠራል፥ከእስራኤልም፡የተበተኑትን፡ይሰበስባል።
3፤ልባቸውን፡የቈሰሉትን፡ይፈውሳል፥ሕማማቸውንም፡ይጠግናል።
4፤የከዋክብትንም፡ብዛት፡ይቈጥራል፥ዅሉንም፡በየስማቸው፡ይጠራቸዋል።
5፤ጌታችን፡ታላቅ፡ነው፥ኀይሉም፡ታላቅ፡ነው፥ለጥበቡም፡ቍጥር፡የለውም።
6፤እግዚአብሔር፡የዋሃንን፡ያነሣል፥ኀጢአተኛዎችን፡ግን፡እስከ፡ምድር፡ድረስ፡ያዋርዳል።
7፤ለእግዚአብሔር፡በምስጋና፡ዘምሩ፥ለአምላካችንም፡በመሰንቆ፡ዘምሩ፤
8፤ሰማዩን፡በደመናት፡ይሸፍናል፡ለምድርም፡ዝናብን፡ያዘጋጃል፤ሣርን፡በተራራዎች፡ላይ፡ያበቅላል፤ለምለሙንም ፡ለሰው፡ልጆች፡ጥቅም።
9፤ለሚጠሩት፡ለቍራዎች፡ጫጩቶች፡ለእንስሳዎችም፡ምግባቸውን፡ይሰጣል።
10፤የፈረስን፡ኀይል፡አይወድ፟ም፥በሰውም፡ጭን፡አይደሰትም።
11፤እግዚአብሔር፡በሚፈሩት፥በምሕረቱም፡በሚታመኑት፡ይደሰታል።
_______________መዝሙር፡147።______________
1፡(12)፤ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡አመስግኚ፥
2፡(13)፤ጽዮንም፡ሆይ፥ለአምላክሽ፡እልል፡በዪ፤የደጆችሽን፡መወርወሪያ፡አጽንቷልና፥ልጆችንም፡በውስጥሽ፡ባርኳልና ።
3፡(14)፤በወሰንሽም፡ሰላምን፡አደረገ፥የስንዴንም፡ስብ፡አጠገበሽ።
4፡(15)፤ነገሩን፡ወደ፡ምድር፡ይሰዳ፟ል፥ቃሉም፡እጅግ፡ፈጥኖ፡ይሮጣል።
5፡(16)፤ዐመዳዩን፡እንደ፡ባዘቶ፡ይሰጣል፤ጉሙን፡እንደ፡ዐመድ፡ይበትነዋል፤
6፡(17)፤በረዶውን፡እንደ፡ፍርፋሪ፡ያወርዳል፤በበረዶውስ፡ፊት፡ማን፡ይቆማል፧
7፡(18)፤ቃሉን፡ልኮ፡ያቀልጠዋል፤ነፋሱን፡ያነፍሳል፥ውሃዎችንም፡ያፈሳ፟ል።
8፡(19)፤ቃሉን፡ለያዕቆብ፥ሥርዐቱንና፡ፍርዱን፡ለእስራኤል፡ይናገራል።
9፡(20)፤ለሌላዎች፡አሕዛብ፡ዅሉ፡እንዲህ፡አላደረገም፥ፍርዱንም፡አልገለጠላቸውም።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡148።______________
የሐጌና፡የዘካርያስ፡መዝሙር።
1፤ሃሌ፡ሉያ።እግዚአብሔርን፡ከሰማያት፡አመስግኑት፤በአርያም፡አመስግኑት።
2፤መላእክቱ፡ዅሉ፥አመስግኑት፤ሰራዊቱ፡ዅሉ፥አመስግኑት።
3፤ፀሓይና፡ጨረቃ፥አመስግኑት፤ከዋክብትና፡ብርሃን፡ዅሉ፥አመስግኑት።
4፤ሰማየ፡ሰማያት፥አመስግኑት፡የሰማያት፡በላይም፡ውሃ።
5፤ርሱ፡ብሏልና፥ኾኑም፤ርሱም፡አዟ፟ልና፥ተፈጠሩም፤የእግዚአብሔርን፡ስም፡ያመስግኑት።
6፤ለዘለዓለም፡ዓለም፡አቆማቸው፤ትእዛዝን፡ሰጠ፥አያልፉምም።
7፤እባቦች፡ጥልቆችም፡ዅሉ፥እግዚአብሔርን፡ከምድር፡አመስግኑት፤
8፤እሳትና፡በረዶ፡ዐመዳይና፡ውርጭ፥ቃሉን፡የሚያደርግ፡ዐውሎ፡ነፋስም፤
9፤ተራራዎች፡ኰረብታዎችም፡ዅሉ፥የሚያፈራም፡ዛፍ፡ዝግባም፡ዅሉ፤
10፤አራዊትም፡እንስሳትም፡ዅሉ፥ተንቀሳቃሾችም፡የሚበሩ፟፡ወፎችም፤
11፤የምድር፡ነገሥታት፡አሕዛብም፡ዅሉ፥አለቃዎች፡የምድርም፡ፈራጆች፡ዅሉ፥
12፤ጕልማሳዎችና፡ቈነዣዥቶች፥ሽማግሌዎችና፡ልጆች፤
13፤የእግዚአብሔርን፡ስም፡ያመስግኑ፤ስሙ፡ብቻውን፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ምስጋናውም፡በሰማይና፡በምድር፡ላይ፡ ነው።
14፤የሕዝቡንም፡ቀንድ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል፤የቅዱሳኑንም፡ዅሉ፡ምስጋና፡ወደ፡ርሱ፡ለቀረበ፡ለእስራኤል፡ልጆ ች፡ሕዝብ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡149።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ።ለእግዚአብሔር፡ዐዲሱን፡ቅኔ፡ተቀኙለት፤ምስጋናው፡በቅዱሳኑ፡ጉባኤ፡ነው።
2፤እስራኤል፡በፈጣሪው፡ደስ፡ይበለው፥የጽዮንም፡ልጆች፡በንጉሣቸው፡ሐሤትን፡ያድርጉ።
3፤ስሙን፡በዘፈን፡ያመስግኑ፥በከበሮና፡በመሰንቆም፡ይዘምሩለት።
4፤እግዚአብሔር፡በሕዝቡ፡ተደስቷልና፥የዋሃንንም፡በማዳኑ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋልና።
5፤ቅዱሳን፡በክብር፡ይመካሉ፤በምንጣፋቸውም፡ላይ፡ሐሤትን፡ያደርጋሉ።
6፤የእግዚአብሔር፡ምስጋና፡በጕረሯቸው፡ነው፤ኹለት፡አፍ፡ያለውም፡ሰይፍ፡በእጃቸው፡ነው፥
7፤በአሕዛብ፡ላይ፡በቀልን፡በሰዎችም፡መካከል፡ቅጣትን፡ያደርጉ፡ዘንድ፤
8፤ንጉሦቻቸውን፡በሰንሰለት፥አለቃዎቻቸውንም፡በእግር፡ብረት፡ያስሩ፡ዘንድ፤
9፤የተጻፈውን፡ፍርድ፡ያደርጉባቸው፡ዘንድ።ለቅዱሳን፡ዅሉ፡ይህች፡ክብር፡ናት።ሃሌ፡ሉያ።
_______________መዝሙር፡150።______________
1፤ሃሌ፡ሉያ።እግዚአብሔርን፡በመቅደሱ፡አመስግኑት፤በኀይሉ፡ጠፈር፡አመስግኑት።
2፤በችሎቱ፡አመስግኑት፤በታላቅነቱ፡ብዛት፡አመስግኑት።
3፤በመለከት፡ድምፅ፡አመስግኑት፤በበገናና፡በመሰንቆ፡አመስግኑት።
4፤በከበሮና፡በዘፈን፡አመስግኑት፤በአውታርና፡በእንቢልታ፡አመስግኑት።
5፤ድምፁ፡መልካም፡በኾነ፡ጸናጽል፡አመስግኑት፤እልልታ፡ባለው፡ጸናጽል፡አመስግኑት።
6፤እስትንፋስ፡ያለው፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ያመስግን።ሃሌ፡ሉያ፨

http://www.gzamargna.net